HaqCheck
429 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
#Alert

ከሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሚድያ መጥፋትን ተከትሎ ከ291 ሺህ በላይ ተከታይ ካላቸው የቴሌግራም ቻናሎች እስከ 10ሺህ በላይ ተከታይ እስካላቸው የፌስቡክ ገጾች ድረስ “ጠ/ሚ አብይ አህመድ ኮማ ውስጥ መሆናቸው ተረጋግጧል” የሚሉና ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በcerebro vascular accident (stroke) ተጠቅተው ኮማ ውስጥ ገብተዋል” በሚል መግለጫ የተደገፈ አንድ ምስል በማህበራዊ ሚድያው ላይ ሲዘዋወር ቆይቷል።

ሀቅቼክ ይህንን ምስል የዛሬ አመት ጥር 16 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ ታጁዲን አህማዲ በተባለ እና ከ 3900 በላይ ጓደኞች ባሉት የፌስቡክ የግል አካውንት ላይ ተጋርቶ አግኝቶት የነበረ ሲሆን በወቅቱም የጠቅላይ ጽ/ቤት በጠ/ሚ አብይ አህመድ ደህንነትን በተመለከተ የሚሰራጩ መረጃዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን በይፋዊ ገጹ ላይ አስታውቆ ነበር።

ምስሉ Gofund me በተባለ እርዳታ ማሰባሰቢያ ድረ-ገፅ ላይ ቢዱሀን ታፓ የተባለ ሰው በደረሰበት የልብ ምት መቋረጥ (cardiac arrest) ምክንያት ሲረዳበት በነበረው ጆን ሆፕኪንስ ሆስፒታል መሞቱን ተከትሎ የታማሚውን ሚስት ፕሪሲላ ራይንን ለመርዳት በማሰብ ምስሉን በመጠቀም በድረ ገጹ ላይ ገንዘብ ለማሰባሰብ የተጋራ ምስል እንደሆነ ታውቋል።
ሀቅቼክ በዚህ ምስል ዙሪያ ከዚህ ቀደም ያስነበበውን ፅሁፍ ሙሉውን ያንብቡ።

https://bityl.co/DRWW
👍1
#Alert

DTU Students Page (የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ገፅ) በሚል ስም የተከፈተ እና ከ18ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ ሐምሌ 18 ፤ 2014 ዓ.ም “አትሌት ኮ/ል ደራርቱ ቱሉ ላደረገችው አስተዋፅኦ ከአለም ኦሎምፒክ ኮሚቴ እጅግ ዘመናዊ BMW መኪና ተሸለመች” በሚል የፅሁፍ መግለጫ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከአንድ ፈረንጅ ሴት ጎን ቆማ የምትታይበት ምስል አጋርቶ ነበር። ስለ አትሌቷ የዘመናዊ BMW መኪና መሸለም የተገኘ መረጃ ባይኖርም ምስሉ የተቀናበረ እና ሀሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል። አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከአንድ ፈረንጅ ሴት ጎን ቆማ የምትታይበት የመጀመሪያውና ትክክለኛው ምስል ሐምሌ 2 ፤ 2014 ዓ.ም ላይ “Ira BMW Stratham” በተሰኘ የትዊተር አካውንት ላይ ተገኝቷል። ስለዚህም ምስሉ የተቀነባበረ ነው።

የተጣሩ መረጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ከሀቅቼክ ገፆች ያግኙ፡
ቴሌግራም፡ t.me/HaqCheck
ፌስቡክ፡ www.facebook.com/HaqCheck
ትዊተር፡ www.twitter.com/HaqCheck
ድረ ገፅ፡ www.haqcheck.org
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሳምንታዊ የሀቅቼክ ፕሮግራም በ አርትስ ቴሊቪዥን እና በአዲስ ዘይቤ የ ዩቲዩብ ቻናል ላይ ይከታተሉን።
🔥1
መረጃን ሳያጣሩ አያጋሩ!
#የሀሰተኛመረጃጥቆማ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አውታሮች ላይ የሚዘዋወረውን ይህን ምስል ያጋሩ ፖስቶች አሜሪካዊው ቢልየነር ቢልጌትስ በተደረገለት አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ጋዜጠኛዋ ስለ ስኬቱ ሚስጥር በጠየቀችው ጊዜ አንድ ባዶ ቼክ አውጥቶ የፈለገችውን ያህል የገንዘብ መጠን እንድትፅፍ ቢነግራትም ጋዜጠኛዋ በተደጋጋሚ ቼኩን እንደመለሰች ያስነብባሉ። በመጨረሻም አሜሪካዊው ቢልየነር ቢልጌትስ የስኬቱ ሁሉ ሚስጥር እንደሷ ያገኛቸውን እድሎች አለማሳለፉ እንደሆነ እንደነገራትና ሊሰጣት የነበረውን ቼክ ተቀብሏት እንደቀደደው ፅፈዋል።

ይህ መረጃ በሀገራችን ኢትዮጵያ በቻ ሳይሆን በአለም ላይ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ ሲዘዋወር የቆየ ነው።

ነገር ግን ምስሉ የተወሰደው የተለያዩ ታዋቂ እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በማቅረብ ቃለ-ምልልሶችን በሚያደርገው እና This Morning በተሰኘው የቴሌቪዥን ሾው ላይ የነበረ ሲሆን ቪድዮው ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም በቴሌቪዥኑ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ተጋርቷል።

በፕሮግራሙ ላይም ስለ ቢልየነሩ የግል ጉዳዮች እና ስለሚያወጣቸው ወጪዎች የተጠየቀበት አጭር ፕሮግራም ሲሆን እነዚህ የማህበራዊ ሚድያ ፖስቶች እንደሚናገሩት በምስሉ ላይ ጋዜጠኛዋ የምትመልስለት ባዶ ቼክ ሳይሆን This Morning የሚል ፅሁፍ ያለበት ኩባያ በስጦታ መልክ ስታበረክትለት ነው።

ምስሉን ለማጣራት ሀቅቼክ ሙሉ ቪድዮውን የተመለከተ ሲሆን በቪድዮው ውስጥ ቢልጌት ለጋዜጠኛዋ የሰጣት ምንም አይነት ቼክ እንደሌለ አረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ ቢልየነሩ ለጋዜጠኛዋ ቼክ እንዳቀረበላት የሚያሳይ ምንም መረጃ ማግኘት አልተቻለም።
👍1
#የሀሰተኛመረጃጥቆማ

ከሰሞኑን በተለያዩ የፌስቡክ ገፆች ላይ የሚዘዋወር የአንድ ሰው ምስልን በማጋራት ሰውየው የህወሓት ቃል አቀባይ የሆነው አቶ ጌታቸው ረዳ እንደሆነ ግምቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። ከዚህ በተጨማሪ በምስሉ ላይ የሚታየው ግለሰብ አንድ እግር የሌለው በመሆኑ ምስሉ በፎቶሾፕ የተቀነባበረ ነው ያሉም አልጠፉም።

ከዚህ ባለፈም ምስሉ ላይ የሚታዩትን የመከላከያ ሰራዊት ልብስ የለበሱ ግለሰቦች እና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አርማ ያለበትን ወረቀት የተመለከቱ በበኩላቸው ምስሉ የጌታቸው ረዳ ሊሆን የሚችልበት ምንም ምክያንት የለም ሲሉ ተደምጠዋል።

ሀቅቼክም ይህን ከሰሞኑን አወዛጋቢ የነበረውን ምስል ለማጣራት ባደረገው ጥረት ምስሉ ከዚህ በፊት ነሀሴ 5 ቀን 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ ከሌሎች 6 ምስሎች ጋር ተጋርቶ አግኝቶታል። የፕሬስ ድርጅቱ ዜና የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት 75 ሚልዮን ብር የሚገመት የአይነት እና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የሚያስነብብ ሲሆን በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዣንጥራር አባይ እና የመከላከያ ሰራዊት ሚ/ር ዲኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉዊጅ በቦታው ተገኝተው እንደነበር ሪፖርቱ ያስነብባል።

ስለዚህም ሀቅቼክ ባደረገው መረጃውን የማጣራት ስራ ምስሉ የዛሬ አመት የተጋራ እንደሆነ እና ምስሉ በፎቶሾፕ የተቀነባበረ ሳይሆን በምስሉ ላይ የሚታዩት ግለሰብ የህወሓት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ እንዳልሆኑ አረጋግጧል።
ኤደን አብይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ ናት?

በታህሳስ 3 ቀን 2009 ዓ.ም ላይ EthioTube በሚል ስም የተከፈተ አንድ የዩቲዩብ ቻናል ስጦታ ሾው የተሰኘ አንድ ፕሮግራም የጀመረ ሲሆን በተለይም ፕሮግራሙ በአሜሪካ እና አካባቢው የሚኖሩ ስኬታማ እና አርዓያ ይሆናሉ የሚላቸውን ኢትዮጵያውያኖችን እየጋበዘ ልምድ እንዲያካፍሉ ያደርጋል።

በፕሮግራሙ ላይም የመጀመሪያ ተጋባዥ የነበረችው ትውልድ ኢትዮጵያዊቷ ኤደን አብይ ስትሆን በወቅቱም ይህች ግለሰብ በትምህርቷ ውጤታማ ከመሆኗም ባሻገር በአሜሪካው ኋይት ሃውስ የኢንተርንሺፕ ፕሮግራም ላይ እንደተሳተፈች ተገልጿል። በEthioTube ላይ የተላለፈው ይህ ቪድዮም እስካሁን ድረስ ከ118 ሺህ ጊዜ በላይ እይታ ማግኘት ችሏል።

ከዚህ ቪድዮ መለቀቅ በኋላም የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ መረጃዎች ኤደን አብይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ በማለት መረጃውን ሲያዘዋውሩ የቆዩ ሲሆን በተለይም የኤደን አብይ ከቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ጋር መልኳን በማመሳሰል የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ይህች ሴት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ እንደሆነች ያመኑ አልጠፉም።

ነገር ግን ሀቅቼክ በስፋት እየተዘዋወሩ ያሉት ቪድዮዎች ሀሰተኛ እንደሆኑ እና በቪድዎቹ ላይ የምትታየው ግለሰብም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ እንዳልሆነች ማረጋገጥ ችሏል።

ሙሉ ፅሁፉን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://bit.ly/3wngAQi

የተጣሩ መረጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ከሀቅቼክ ገፆች ያግኙ፡
ቴሌግራም፡ t.me/HaqCheck
ፌስቡክ፡ www.facebook.com/HaqCheck
ትዊተር፡ www.twitter.com/HaqCheck
ድረ ገፅ፡ www.haqcheck.org
👍1
በሀገራችን የማህበራዊ ሚዲያ ምህዳሮች ውስጥ በሀሰት የተፈበረኩ መረጃዎች ሊሰራጩ የሚችሉ ይመስሎታል?