የሐና ይመር ግጥሞች
228 subscribers
30 photos
1 video
1 file
5 links
ህይወት የማትፈታ ቅኔ ናት ❤😥✍️
ሐና ይመር ✍️✍️
Download Telegram
የሁላችሁንም inbox መመለስ ስለማልችል ውዶቼ እዚ ጋር ሀሳቤን ልስጥ ፅሁፉን ያጋራዋቹ አንድም እንድትጠነቀቁ ሌላም በኔ መደናበር ፈታ እንድትሉ ነው እንጂ ጫፌን አልነኩኝም እኔም ስልኬም በፍፁም ደህንነት ላይ ነን 😂 ሁላችሁንም አመሰግናለው ለመልካም ምኞታችሁም እነደዛው ❤️❤️❤️😘
ሌላ የንሰሀ እድሜ ለሰጠኸኝ ገናናው እግዚአብሔር ሆይ ክብር ምስጋና ሁሉ ላንተ ይሁን ❤❤🙏
ይናፍቃል 🥺

ሁሉም ይናፍቃል
ያሳለፍነው ፍቅር ድቅን ይልብኛል
ደሞ ስንዋደድ በመኝታችን ላይ
እየተጠጋጋህ ስትሆን ከበላይ
ሁሉም ይናፍቃል
ያሳለፈ ያውቀዋል
ደሞ ከሰሞኑ እጅግ ብሶብኛል
ጥንዶች ባየው ቁጥር እንባዬ ይመጣል
ስታፈቃቅረኝ በምናቤ ያልፈል
ፊልም እስከሚመስለኝ ትዝ ትዝ ይለኛል
መለያየት ክፉ
በመንገድ ብቻዬን እንደብድ ያስወራኛል
መለያየት ክፉ
ካጠገቤ ያሉትን እንዳላይ አርጎኛል
መለያየት ክፉ
በባዶ ሜዳ ላይ ብዙ ያስናፍቀኛል
መለያየት ክፉ
አንተ ሳትኖር እንኳ መዋደድ ያመረኛል
መለያየት ክፉ
ብዙ አስናፍቆኛል😥😥😥

✍️✍️ሐና ይመር
በደለችኝ ይላል 🙄

ታወራለህ አደል
ተበዳይ ይመስል

ትጮሀለህ አደል
በኔ ጥፈት ብቻ ያበቃ ይመስል

እንደው ሌላው ቢቀር
እባክህ እባክህ ባሳለፍነው ፍቅር
ውሸትህን ቀነስ
እውነታውን ነስነስ
ጥሩ ናት ይቅርብኝ
ግን በክፉ አታንሳኝ

እግዜሩስ ምን ይላል ስትሰቅል ስታወረደኝ
ዛሬን አመስግነህ ነገን ስትነሳኝ
ተው በክፉ አታንሳኝ
እኔንም ከአንድዬ እስኪ አታቀያይመኝ

ባንተ የተነሳ ያላጣሁት የለም
እኔ አንተን መርጬ አንተጋ ብመጣም
ወዳጆቼን ክጄ አንተን ባስበልጥም

የተናቀች ሴት
ፈላጊ የሌላት
አድርገህ አሰብከኝ ጊዜ ማያልፍ መስሎህ
እኔ እንደው ቂም አልይዝ ምንም አልልህ
የበላዩ ጌታ ኮማንዶ ሚስት ይስጥህ 🙌

አሜን !

✍️✍️ሐና ይመር
ባረገኝ 🥺🥺

ባረገኝ ባረገኝ
ከጡቶችስ መሀል ምንው ባገደለኝ
ባረገኝ ባረገኝ
መአተብሽን አርጎ ምነው ባስቀመጠኝ
ባረገኝ ባረገኝ
አንዴ ባስቀመጠኝ ሌላ እንዳያምረኝ 😀

ባረገኝ
.
.
.
.
.
ላንዴ ባሳፈረኝ 😭😂

✍️✍️ሐና ይመር
ደርብብኝ

ደርብብኝ እሺ አንተን ካስደሰተህ
ከኔ ጋር እያለህ ሌላ ሰው ካማረህ
ደርብብኝ አባት ፍቅሬ ካላረካህ
ያሰጣጤም ነገር ቅር ቅር ካሰኘህ
ደርብብኝ ውዴ ስጋት እንዳይገባህ
ኑረህም አጠቅመኝ ሁለት ማሊያ ነህ😎

✍️✍️ ሐና ይመር
ድብቁ ስሜቴ

ኤጭ ምን አይነት ስቃይ ነው
ድብቁ ስሜቴ ደሞ ሊመጣ ነው

እፍን እያረገ ሆዴን ሊስብሰው ነው
የቱ መሰላቹ 😞😞

አይኔ እያነባ እምባ የማይወረደው
አምርሬ እያለቀስኩ ድምፄ ማይሰማው
ከሰው መሀል ሁኜ ሰው ሚስናፍቀው
መራመድ እየቻልኩ አሳስሮ ሚስቆመው
ሀዘኔን ለማውጋት አፌን የሚዘጋው
ያለፈውን ነገር የሚብሰለስለው
ያጣውትን ነገር ሁሌ ሚስታውሰው
ለኔ ለኔ ለኔ
ለኔ ብቻ እኮ ነው
ይሄ የሚገባው
በሌላው አይንማ እብድ ነው ሚስብለው
ድብቁ ስሜቴ ባጭሩ ይሄ ነው 🥺

✍️✍️ሐና ይመር

ሁላችንም ለሰው የማናወራቸው ድብቅ ስሜት አሉን ይሄን ግጥም እንድፅፍ ያረገችኝ በinbox ድብቅ ስሜት አለኝ ያለችኝ በፀሎት ነች በፂዬ አንቺ ብቻ አደለሽም ሁላችንም ድብቅ ስሜት አለን!

ቸር አምሹልኝ 🤗🤗
እነዚህን የመሰሉ አበባ ማግኘት ሲፈልጉ
@ablakat12 lay yangrugn yalubet dres ametalew😍☺️☺️
አዎ ለኔ ይኼ አይገባም!

ጥሩ ሰው አይደለሁ ግን እግዚአብሔር ሁሌም ጥሩ ያደርግልኛል።የሆነ ነገር አልተሳካም ብዬ ሳዝን ከዛ የተሻለ ነገር ይሰጠኝና ያለፈው እንኳንም አልተሳካ እላለሁ።አመስጋኝ አይደለሁም ግን አታመሰግነኝም ብሎ እኔን መንከባከቡን የማያቆም አባት አለኝ🥹 አንዳንዴ ቁጭ ብዬ ሳስብ ምን ያህል ቢወደኝ ነው?ቆይ ምን አድርጌለት ነው?ማነው እንደ እግዚአብሔር እኔን ልጁን ሊወድ የሚችለው?እንዴት ባመሰግነው ነው ላደረገልኝ ነገር የምከፍለው?እላለሁ።አውቃለሁ ደካማ ነኝ ግን ደግሞ "ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ"🥰🥰
በምድር ላይ ሳለሁ ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ስወድቅ የሚያነሳ ስደክም የሚያበረታ ስከፋ የሚያጽናና ብቻዬን የማይተወኝ አምላክ አለኝ እናም ሁሌ ይደንቀኛል😍
መድኅኔዓለም ሆይ በእውነት የአንተ ልጅ መሆይ ምንኛ መታደል ነው❤️❤️ሁሌም ክበርልኝ ከፍ ከፍ በልልኝ🙏🙏🙏
ልጅነቴ
ንፅህናዬ
ማደጌ በቀረብኝ
ልጅነቴን ሳስብ እንባዬ ይመጣል ተወልጄ ባደኩባት አከባቢ ማህበራዊ ሂወት የደራ ነው እና እኔ እራሴን ሀና መሆኔን ሳቅ ጭቃ እያቦካው ነው እኛ ቤት በስተቀኝ በኩል የነ መሀመድ ጊቢ አለ በግራ በኩል ደሞ የነሰጠኝ በነመሀመድ ጀርባና በነ ሰጠኝ ቤት አልፎ 2ለተኛው ጊቢ የጓደኞቼ ቤት ነው በነመሀመድ ቤት ጀርባ ያለው ጓደኛዬ አሁን ላይ በዛ ስሙ እንዲጠራ ባይፈልግም እኛ ድሮ "አቡጣሬ" እንለው ነበር የነሰጠኝ ቤትን አልፎ ያለው ጓድኛዬ ደሞ አቤል ይባላል ከሁለቱ ጋር የልጅነት ትዝታዬ ነው ግን የአቤልን ልንገራቹ አባሮሽ ሚባለው ጨዋታ ትዝ አላቹ ኣ እሱን ስንጫወት እንዲባርረን አቤል ደረጀ ነው ሚባለውና እኛ "አቤል ደረጀ ሳይበላ አረጀ" እንል ነበር ስንለው ያሯሯርጠን ነበር አሁን ላይ ሳስበው ጊዜ በጣም ይገርመኛል አቡጣሬ ደሞ የእቃቃ ባሌ ነበር በጣም ከረዥም ጊዜ በኋላ ጓደኛ እንደያዘ ሲነግረኝ አንድ ግጥም ፅፌ ነበር 😂
እንዲህ ይላል

የእቃቃ ባሌ...🤦‍♀

የእቃቃ ባሌ እንዳልነበርክ ያኔ
ዛሬ ላይ አየውህ ሆነህ የሰው ቅኔ

ቅኔው አይፈታም በጣም ከብዷል አሉ
እስኪ በል ንገረኝ ምንድነው ይሄ ሁሉ

ታስታውሰዋለህ ያን ደጉን ዘመን
ተሞሽረን ነበር እኔ እና አንተ ሆነን👫

እኔ የማገባው...
የእቃቃ ባሌን ነው..

እያልኩኝ ሳወራ ይስቁብኝ ነበር ጓደኞቼ ሁላ
ለካስ ሰምተው ነበር ማግባትህን ሌላ

ነገሩ ወዲ ነው ሠው ነው የነገረኝ
እንዳገባክ እንኳን አንተ ብትደብቀኝ😢

ማወቅ ነበረብኝ እኔም ሚስት እኮ ነኝ😜
ከአሁኗ የቀደሙኩ የልጅነትህ ነኝ

አግብቻለው አግቢ ብትለኝ ምን ነበር
እንደዚ በተስፋ አልጠብቅም ነበር😭😭

  ይሄን ግጥም ፅፌ ስጨርስ ልኬለት ነበር ዮንቨርሲቲ ነበር የዛኔ ስልክለት ደው ሎ ለምን አንጋባም ያለኝን አረሳውም😂😂😂
ብቻ ማደጌ ያስጠላኛል ከማደጌ መናደድ የተነሳ የፃፍኳት አንድ ግጥምም አለች ላውጋላቹ ቆይ

እድገት በሰውነት.....

ሰው እንደተረዳው..
እኔም እንደማየው..

ያደኩ ይመስለኛል
ከሠውነቴ አካል
ሁሉ ተለውጡአል

እንደው በትንሹ ዳሌዬ አከባቢ ጡቴም አጎጥጉጧል 😂
እንደዛ ጉች ጉች ብለው የነበሩ ዛሬ ላይ አብጠዋል

አሞኝ ይሆን እንዴ እንደዚ ያበጠው
ብዬ አስብና ትዝ ሲለኝ ደሞ ለካስ አድጌ ነው🤔

ታዲያ ምን ያደርጋል ማደግ በሰውነት
ቢቻል እንዲ ነበር መሆንም ያለበት

በአካል እንዳደኩት
ለውጥ እንዳመጣሁት

በአስተሳሰቤም ላይ ማምጣት ነበረብኝ
በበሰለ አይምሮ ማሰብ ነበረብኝ

ታድያ ምን ያደርጋል ምንስ ይፈይዳል
በሰውነት ብቻ እድገት ምን ይጠቅማል

ብቻ ያኔ እንዳደኩ ያወኩት ጡቴ ሲጎጠጉጥ ሰው ሲየኝ አፍር ነበር ዳሌየም ሲጨምር ሚጣ ስታድጊ ልምጣ ሲሉኝ በቃ ማደጌን ጠላሁት 😭😭😭

ማደጌን የጠለሁት የውሸት ኑሮዬ በዝቶብኝ ነው ልክ ደሞ ከማደግ አልፌ እዛች የፈረደባት ሀይስኩል ስገባ ሌላ አሁን ላይ ትዝታን ሚጭር ታሪክ

1 ቀን ቢመለስ.....

ቀኑ ይናፍቀኛል
እማይመለስ ነገር አንዴ ሆኖብኛል
1ቀን መመለስ ቢቻል ኑሮ ያኔ
ያን ቀን መልስልኝ እለው ነበር እኔ
እኔና አንተ ሆነን የፎረፍንበትን
ከአስተማሪያችን ጋር የተሯሯጥንበትን
በ15 ዴቃዋ ሻይ የጠጣንበትን
ከጓድኞቻችን የጠፈንበትን
ደሞም እጄን ይዘህ
አንገቴ ስር ገብተህ
የወደፊት ሚስቴ አንቺ ነሽ እያልከኝ
ከጓድኞቼ ፊት ሳሩን ያሰርክልኝ
በቬሎ መጋባት አደለም ብርቃችን
እኛ ተጋብተናል በዩኒፎርማችን
በፊርማ  የተጋባን እስኪመስለን ድረስ
ተማሪ አስተማሪ እስኪረገን ርዕስ
እንዋደድ ነበር
እንዲያ ነበር ፍቅር
ተማሪ ቢሆንም ምንም ባይኖረው ብር
ከታክሲው ቀንሶ ይጋብዙኝ  ነበር
አትዘልቁም አትልፉ
አትደርሱም ከአፋፉ
ያሉኝን ሰምቼ ትቼህ የሄድኩበትን
ዛሬም ረግመዋለው አንተን የተውኩበትን

ሌላ ትኩሳት እዚጋ ደሞ 🥺🥺🥺 አባቴ ይሄን ፁሁፍ ያነበበው ቀን በቢጫ ፔስታል ልብሴን አርጎ ደና ሰንብች ነው ሚለኝ ወደታሪኬ ስመለስ ማደጌን እጠለዋለው ልክ እንደልጅነቴ አባሮሽ መጫወት ልክ የእቃቃ ሚስት መሆን ልክ ደሞ እንደ ሀይስኩል አፍቃሪዬ በዪኒፎርም ሲያገባኝ ብቻ የውሸት ሚመስል እውነቶች ልጅነቴ ይናፍቀኛል አንዳንዴ ወደልጅነቴ ብመለስ ለማን ሚስት እሆናለው 😂😂😂😂😂 ለአቡጣሬ ወይስ ለሀይስኩሉ አፍቃሪዬ እሱን ተመልሼ አይቼ ብነግራቹ ውስጤ ነበር ግን አድጊያለው ምናለ ባላድግ 🥺🥺

በነገራቹ ላይ ልጅነቴ ይሄ ብቻ አደለም በወፍ በረረ ነው የነገርኳቹ ብዙ ብዙ አለ እግዚዮ የኔ ጉድማ አያልቅም ለዛሬ ይብቃኝ እንጂ🙏🙏

Based on true story

✍️ሐና ይመር
እንቆቅልህ ?


እንቆቅልህ
ምን አቅልሽ
ሀገሬን አይተሀል
የትኛዋ ሀገርሽ
አንተ ሳትመጣ ድሮ የነበረቸው
የድሮ ሰፈሬ ያልፈራረሰችው
ታሪክ እንደታሪክ አኑራ የቆየችው
እኔጃ ያቺ ያለማቸው ......
አዎ አውቀሀታል ያችን ነው የምልህ
እንደው በመላኩ አይተሀት ታቃለህ ?
ድሀ እንደልቡ ሰርቶ ሚኖርባት
አንዳሁኑ ጊዜ ሰው የማይናቅብት
ሁሉም እንደአቅሚቲ ወቶ ሚገባባት
አይተሀታል ያቺ የሚስግኗን ሀገር?
እኔ አላየዋትም ካለሆነ ሀገር ልስጥሽ?
ሀገር ልስጥሽ አልከኝ😳
አስኪ ስጠኝ ብልህ የቱን ነው ምሰጠኝ
ወንድም በወንድሙ የተነሳባትን
በደም አሜኬላ የተናወጠችውን
እህት በወንድሟ የተደፈረችባትን
ወይስ ህፃን እንደንስሳ የታራደባትን
የቱን ነው ?ሀገር ልስጥሽ ያልከው?
እኔጋ ያለቸውን የለመለመችው ኢትዮጵያዬን ልስጥሽ?
እኔ ያንተን ኢትዮጵያ መች እፈልጋለው
ወንድም ወንድሙን ሲያርድ እንዴት ቆሜ አያለው
ያባቶቼ ታሪክ ሲጠፋ እያየው
አንዴት እሺ ብዬ እቀበልሀለው
ድሀዋ ተርባ መች እኔ ጠግባለው

ሀገር ስጠኝ 🥺😭😭
ያንተን ሳይሆን
የኔን የኔን የድሮዋን
ያቺን ሚስኪን እንስፍስፏን
ሀገሬ ጌጤን ኢትዮጵያዬን
ስጠኝ በቃ አቢሲኒያዬን😭

✍️✍️ሐና ይመር