የሐና ይመር ግጥሞች
228 subscribers
30 photos
1 video
1 file
5 links
ህይወት የማትፈታ ቅኔ ናት ❤😥✍️
ሐና ይመር ✍️✍️
Download Telegram
ሠላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እያልን በወንድማችን ኢዮብ ወልደማርያም (ተክለማርያም) ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት በተማሪዎች ስም በነሐሴ 1/2014 ዕለተ እሑድ ከቀኑ 9:00 የጸሎት እና የዝክር መርሐግብር በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ የተዘጋጀ ስለሆነ እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን።
የምትችሉ ተገኙልን ❤️❤️❤️
አንድ ኦርቶዶክሳዊ አባት "ሰው ሰው ነው ለምን ግብረ ሰዶማዊነት አትፈቅዱልንም?" ተብለው ተጠይቀው "ውሃ ውሃ ነው ለምን ከሽንት ቤት አትጠጣም?" በለው መለሱላቸው።

ድንቅ ንግግር በጣም ስለወደድኩት ላካፍላቹ ብዬ ነው
ደና እደሩ 🤗🤗
Channel photo updated
እንኳን አደረሳቹ ቤተሰብ ❤️
አባቴ እናቴን 🙆‍♀👫

አታለላትና ከቤት አስወጥቶ
አሳደራት ቤቱ ከወንድሟ አጣልቶ
ተጨነቀች ነፍሳ ምድሩ ጠበባት
አይታ ማታቀውን ደስታ እየሰጣት
በመሀል ላይ ታዲያ ወንድሟ ትዝ ሲላት
እንባ በጉንጮቿ ይሽቀዳደማሉ
እንቡጥ ከንፈሮቿን ነክተውት ያልፈሉ
ታዲያ በዚ ጊዜ አባቴ ያዝንና
እንዲ ሲል ያዜማል እሷ እንድትዝናና

ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎችን አስናቅሻቸው

እኔ ግን ሲገባኝ እናቴ አልነቃሽም
ሰሙን እንጂ አንቺ ወርቁን አላየሽም
አስናቁ ex ናት
የያቆቤ እናት

Just like for funn my dad isn't that type of person 🤗🤗🤗
✍️ሐና ይመር
"እስካለው ጠይቁኝ"

ከሞትኩ በኋላ
ዋይታቹ እንዳይበዛ
ደግ የዋህ ነበረች
ሄደች እንደዋዛ
የሚባሉ ቃሎች
እንዳይበዙ በኔ
በህይወት እስካለው
ጠይቁኝ ደግፉኝ ሁኑልኝ ከጎኔ


✍️✍️✍️ ሐና ይመር
ነብስህ በሰላም ትረፋ ባባ 🥺🙏
@hanayimer21
🥺🥺🥺🥺🥺
በቀኙ ያቁምህ
የሐና ይመር ግጥሞች
Photo
Merdat yemtfelgu beweust mesmer tsfulgn yalchuhn begzabher sm tebabrun
አልሞትኩም !


እንደወዳደቄ እንደአነተ አገፉፍ
አልሞቱኩም ይመስገን ቆሚያለው ከአፋፍ




✍️ሐና ይመር
አልተውህም

ለአዲሷ ሴት ለመጣችው
ከኔ በልጣ ለተኘችው

አልተውህም 🤨!

ሰውቻለው ልጅነቴን
አጥቻለው እኔነቴን
ምንም ሳላቅ በህፃንነት
ፔሬድ ሳላይ በጨቅላነት
ወስደህ ያንተ አድርገኸኛል
ከትምህርቴ ለይተኸኛል🥺

ታዲያ ዛሬ ምን ተገኘ😏
እኔን ትተህ ሌላ ሚስመኝ
እኮ ከኔ ምን ጎደለህ
ደሞስ ከኔ ምንስ አጣህ
ልጅነቴን እንዲያ ወስደህ
ነገን ህልሜን ባጭር ቀጭተህ
እኔን ትተህ ሌላ ያሳየህ
በል እስኪ አውጋ ምንጎደለህ

ምንም አይነት መልስ የለህም
እኔም አንተን አልተውህም !🙄

✍️✍️ሐና ይመር
በ17 አመቷ ከኮሌጅ ተባረረች

በ25 አመቷ የምትወዳትን እናቷን በሞት ተነጠቀች

በ26 አመቷ የጀመረችው የመምህርነት ስራ ሊሳካላት አልቻለም

በ27 አመቷ አንድ ሴት ልጅ የወለደችለት ባሏ ጋ ተፋታች

በ28 አመቷ ስራ የሌላት Single mom በመሆኗ ምክንያት ትልቅ የጭንቀት በሽታ ላይ ወደቀች

በ29 አመቷ ከእህቷ ጋ ተጠግታ የመረረ ኑሮን ትኖር ነበረ

በ30 አመቷ ራሷን ለማጥፋት ደጋግማ የምታስብ የነበረ ቢሆንም እጅግ የምትወደውን የፅሁፍ ስራ አጠናክራ ለመቀጠል ራሷን አሳመነች

በ31 አመቷ ፅፋ የጨረሰችውን መፅሃፍ ከ12 ማተሚያ ቤቶች በላይ ውድቅ ቢያደርጉባትም በስተመጨረሻ ለማሳተም ቻለች

በ35 አመቷ 4 መፅሃፍት በማሳተም የአመቱ ምርጥ ፀሃፊ ለመባል በቃች

በ42 አመቷ 11 ሚሊዮን ኮፒ በመጀመሪያው መፅሐፏ በወጣበት ቀን ለመሸጥ የቻለች ብቸኛ ደራሲ ለመሆን በቃች

ይህች ድንቅ ሴት JK Rowling በ30 አመቷ ራሷ ላይ ልትወስን የነበረውን ሃሳብ አስታወሳችሁት??

ዛሬ Harry Potter የተሰኘው ስራዋ የአለም ብራንድ ሆኖ ከ15 ቢሊየን ዶላር በላይ ያስገባ ስራ ነው ያኔ ተስፋ ቆርጣ ቢሆንስ?

ወደከፍታው መውጫ መንገድ ቀልሎ አያውቅም ፤ የሚዘጋብሽ በር ይበዛል ፤ መንገድሽን በእሾህ የሚያጥረው ብዙ ነው ነገር ግን ተስፋ አለመቁረጥ ፤ በራስሽ ማመን ፤ መሰጠት ፤ ጠንክሮ መስራት እና ራስን ማከም ወደፊት በትጋት መራመድ❤

ITS NEVER TOO LATE


Happy women's day ❤️❤️
እምነት ይኑረን እንጂ እግዚአብሔር ሁሌ ከኛ ጋር ነው ማርያምን ዚሬ ምን እናዳጋጠመኝ ልንገራቹ ...

ከጋራ ወደ ሀይሌ ጋርመንት ለመሄድ ባጃጅ ውስጥ ገባው ስገባ አንድ ወንድ ነበር ከዛ እኔ ገባው አንድ ሰው መጣ ልጁ አሁንም ጋርመንት እያለ ይጠራል ሁለት ሰዎች መጡ ከፍት ገቡ መንገድ ጀመርን ዝናብ ስለነበር ጥላዬን አጠፌ እንዳላበሰብሳቸው ብዬ ጫማዬ ላይ ላስቀምጥ ዝቅ አልኩ ከዛ በምን ፍጥነት ቦርሳዬን እንደከፈተው አላቅም ስልኬ ግማሽ ላይ ሁኗል ከዛ የሆነ ነገር ቀፈፈኝ ቀና ስል ቦርሳዬ ተከፍቷል አንተ ሌባ ብዬ መጨህ ጀመርኩ
ባለጌ
ሌባ
ቆሻሻ ያልሰደብኩትን ጠይቁኝ 🙄
ከዛ ዝጊ አለኝ ከፊት ያሉት መሳቅ ጀመሩ ከዛ ገባኝ አንድ ላይ እንደሆኑ ወራጅ አለ አልኩ 🧐
ጋርመንት አላልሽም አለኝ ሹፌሩ አውረደኝ በቃ ከዛ መሳቅ ጀመሩ ወደ ዳር ወጣ ብዬ እርዱኝ አልኩ
🙄😂 ወፍ ማንም ከዛ መጮህ ጀመርኩ አውርዳት አለ ከጎኔ ያለው ጋርመንት ሳንደርስ ኮንደሚኒየም ጋር ገፍተር አርጎ አወረደኝ ጅልነቴ 10 አውጥቼ እንካ ማለት ሹፌሩን ሻይ ጠጭበት ብለው አዙረው ላጥ ከሄዱ በኋላ

ሌቦች
ባለጌዎች 😂😂😂😂
ሆ ምን ያላልኩት አለ እስከ ጋርመንት በእግሬ እየሮጥኩ 🤸🏽‍♀️🤸🏽‍♀️🏃‍♀️🏃‍♀️🏃‍♀️🏃‍♀️🏃‍♀️🤣🤣🤣🤣
ለ 30 ደቂቃ ሚሆን ቆም ብዬ ተረጋግቼ ወደቤቴ ታክሲ ይዜ ገባው
ምን ልላቹ ነው እግዚአብሔር ጥላ ከለላ ሆኖልኝ እንጂ
እንደዛ አፌን ስከፍት ቢመተኝስ በዚ ስንት ነገር በበዛበት ወደ ሌላ ቦታ ቢወስዱኝስ ብቻ በእግዚአብሔር ብቻ ሁሌም እምነት ካለን ከሞትም እናመልጣለን ❤🙏
24/7/2015
የሁላችሁንም inbox መመለስ ስለማልችል ውዶቼ እዚ ጋር ሀሳቤን ልስጥ ፅሁፉን ያጋራዋቹ አንድም እንድትጠነቀቁ ሌላም በኔ መደናበር ፈታ እንድትሉ ነው እንጂ ጫፌን አልነኩኝም እኔም ስልኬም በፍፁም ደህንነት ላይ ነን 😂 ሁላችሁንም አመሰግናለው ለመልካም ምኞታችሁም እነደዛው ❤️❤️❤️😘
ሌላ የንሰሀ እድሜ ለሰጠኸኝ ገናናው እግዚአብሔር ሆይ ክብር ምስጋና ሁሉ ላንተ ይሁን ❤❤🙏