የሐና ይመር ግጥሞች
228 subscribers
30 photos
1 video
1 file
5 links
ህይወት የማትፈታ ቅኔ ናት ❤😥✍️
ሐና ይመር ✍️✍️
Download Telegram
" ረከስኩ ሁዳዴን "

ጠጋ
ጠጋ
ጠጋ
ተጠጋ ወደኔ
ለስላሳ እጆቹን አሳረፈ ከጭኔ.....




✍️🎤ሐና ይመር

join us
@hanayimer21
@hanayimer21
♥️♥️♥️እመቤቴ❤❤

አለም ስትሰለቸኝ ስትጨልምብኝ
የገባሁባቸው በሮች ሲዘጉብኝ
የጌታዬን እናት እንዲ እማፀናለው
እናቴ አትለይኝ አበርችኝ እላለው
ስለሰራኋቸው ስላጠፋኋቸው ስለኔ በደሎች
ታማልደኛለች ከጌታዬ ጋራ ስለእኔ እያነባች
ታዲያ እንዴት ብዬ ተስፋ ልቁረጥ እኔ
ቅድስት ድንግል ማርያም እያለች ከጎኔ
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
❤❤❤❤❤❤❤❤❤♥️
♥️♥️♥️♥️♥️♥️♥️♥️♥️♥️
🙏🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲

✍️✍️ሐና ይመር

@hanayimer21
@hanayimer21
@hanayimer21
መልካም ልደት ይሁን እስከ እለት ፍፃሜ
ዘመነ ፍሰሀ የቁም ነገር እድሜ






ተመስገን አምላኬ መልካም ልደት ለኔ 😁💃
ፍቅር እኔ አውቃለው

ፍቅር እኔ አውቃለው
ማፍቀር ለካ እንዲ ነው
ስለ አንድ ሰው በደል ስለአጠፋው ጥፋት
ስለተላለፈው አስርቱ ትዛዛት
በዚ ሁሉ ስራ በዚ ሁሉ ተግባር
አንድ እሱ መወገር
ስለሰራናቸው ተንኮልና ስህተት
በኛ ቦታ ሁኖ እንድ እሱ መቀጣት
ደሞ ለኛ ብሎ በሰው ፊት መደፋት
ይህ አይበቃ ብሎ ሞትን ወስዶ መሞት
ታዲያ ከዚ በላይ ፍቅር ወዴት አለ...
እሱ ነብሱን ትቶ የኛን አስቀጠለ
እኛን ከፍ አረገ እሱ ዝቅ እያለ
እናም ወዳጆቼ ለኔ ፍቅር ማለት
ያለአንዳች ምክንያት ነው አንድን ሰው መመልከት
ሀብትና ገንዘቡን ምኑንም ሳናየው
ልክ እንደክርስቶስ ልብን መመልከት ነው
❤❤❤❤❤❤❤❤
❤❤❤❤❤❤❤❤
❤❤❤❤❤❤❤❤
❤❤❤❤❤❤❤❤


❤❤❤❤
❤❤❤❤
✍️ሐና ይመር
አይ አንተ

እኔ አንተን ሳቅህ
መሳቅ መጫወቱ ምንም ማይመስጥህ
ከሰው ጋር መግባባት ከቶ የማያሻህ
በተለይ ለእንስቶች መጥፎ እሳቤ ያለህ
ከእናትህ ሌላ ሴት ያለች አይመስልህ
ታዲያ እንዴት ብዬ አንተን አፈቀርኩህ
ልቤ ምን ነክቶት ነው አንተ ላይ ያረፈው
በመንገዱ ሳይህ የምዝለፈለፈው
እጆቼ እግሮቼ ስራቸው ሚቆመው
ኧረ በአዛኚቱ ምን አድርገኸኝ ነው?😭
ድምፅህ ነው እንዳልል አፍህ አላወራ
አይኖችህ አላዩኝ በሱ እንዳላመኻኝ
ሰውነትህ አልል እሱን መች አየሁኝ 😂

አየህ የወንዜ ልጅ አንድ ነገር አለ ....
ልጅን ከወደዱ............
ነውና ነገሩ🙄🙄🙄
እኔ አንተን ስወድህ
እኔ አንተን ሳፈቅርህ

አይንህም 👁👁
ድምፅሀም 👂👂
ይልቅ ሰውነትከም አደሉም መስፈርቴ
መለኪያ የሌለው ፍቅር ነው ህይወቴ ❤❤


✍️✍️ሐና ይመር
@hanayimer21
@hanayimer21
ከባደ ነው🥺🥺🥺🥺

አብረው የኖሩትን በቁም ከመለየት
ደሞም ከሌላ ጋር ሆኖ እንደማየት
ያንተ የሆነን እቃ ለሌላ እንደመስጠት
ነውና ስሜቱ ከባድ ነው በእውነት

ታዲያ እንዴት ብዬ ይህንን ላስረዳው
አንዴ ልቡ ሂዶ እንዴት ልመልሰው
ደሞም ከአብሯደጌ ከሷ ጋር ነው ያለው
ታዲያ እንዴት ብዬ ፍቅሯን ልበጥብጠው

ሆድ ሆዴን ሲብሰኝ😥
እዝን ክፍት ሲለኝ😭😭😭
ደሞ አለቅሳለው አይኔ ደም እስኪለብስ
ያሳለፍነው ጊዜ በአይምሮዬ ሲታወስ
እኔ እንደው አልቻልኩም ከሌላ መላመድ
እናልክ የኔ ሰው......😭😭
የኔ እና የአንተን ጉዳይ እሱ እንደጀመረው
አንድዬ ፈጣሪ እሱ ይጨርሰው 😔😔😔

✍️✍️ሐና ይመር
@hanayimer21
@hanayimer21
ሴት መሆን ቀላል አደለም
😥
😥
😔
✍️✍️🎤🎤🎤🎤ሐና ይመር
@hanayimer21
@hanayimer21
እንጃልኝ


🙆‍♀🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀
✍️🎤ሐና ይመር
@hanayimer21
@hanayimer21
ሳመኝ


ከንፈሬ እርቦታል
ድርቅ ብሎብኛል
እሱስ የውጭ ነው
ጥርሶቼ በልዘው
አይኖቼ እንባ ሞልተው
ምላሴ ተሳስሮ ማውራት ተስኖታል
ጆሮዬ እንኳ በአቅሙ መስማቱን አቁሟል
እጄን አጠይቀኝ ለመፃፍ ካልሆነ መች ይንቀሳቀሳል
ኧረ ስንቱን ላውራ መላ አካላቴን ተቆጣጥረኋዋል

ምን አለበት አሁን

ምን አለበት አሁን

አንድ ግዜ ስመኸኝ
ደረቁ ከንፈሬ ቢለሰልስልኝ
የበለዘው ጥርሴ እንደው ቢነጣልኝ
የሚያነባው አይኔ እንደው ቢቆምልኝ
ማያወራው አፌ በተናገረልኝ

ምን አለበት አሁን

እንዴ እንኳ ስመኸኝ
ከዚህ ሁሉ ህመም እንደው ብትፈውሰኝ

ምን አለበት አሁን?😔😔😔😔


✍️✍️ሐና ይመር

@hanayimer21
@hanayimer21
ተዋበች

ከፀጉራ እሰከ ጥፍራ ተውባ መታለች
በአጠገብህ ስታልፍ ትወሰወሳለች
ታዲያ ምን ያደርጋል ልጅቷ የኔ ነች
ብዬ ሳልጨርሰው ከሌላ ተዋበች


አይ ተዋበች ግፍሽ ግን 😂😂😂

✍️✍️ሐና ይመር
ረሳውት🥰

የበደልከኝ በደል ብዙ ሁኖ ሳለ
ተውኩት እረሳውት ፈጣሪ ስላለ
እንዲህ ሲል ተናግሯል
ይቅር እንድላቹ ይቅር በሉ ብሏል


dear ላስቀየምከኝ ልጅ ይቅር ብዬሀለው🥰


✍️ሐና ይመር
እምቢ 🥺

እምቢ አልሄድም ከሌላ
ተው ግን የኔ አለም ፈልግ ሌላ መላ
በኋላ ይሆናል ገላዬ የሌላ🥺
እንዳትለምነኝ ከሄድኩ በኋላ
🥺🥺🥺🥺🥺🥺

ሚስቶቻችሁን ለሌላ አሳልፈቹ ለምሰጡ 🥺🥺🥺🥺

✍️ሐና ይመር
ሁለት ጥቅም

ፀሀይ እንዲሞቀን ደመቀች አበራች
ጨረቃም በግሏ ብርሀን እንዲሆነን ያላትን ለገሰች
አየህ የኔ አለም የሁለቱን አንድነት
እየተላለፉ ሲያደምቁ የሰው ህይወት
ከነሱ ተምረህ ጥምረት አስበልጠህ
ከከቤ ጋ እንድሆን ፍቀድልኝ ባክህ 😁

😂😂😂💪💪
አቤት እውቀት እኔኮ አላስብ 😁😁
✍️ሐና ይመር
ናፈከኝ

እንደ እህል እራብከኝ
እንደ ውሀ ጠማኸኝ
እንደታረዘ ሰው ልለብስህ አሰብኩኝ

ቢቸግር ነው እንጂ
ቢቸግር ነው እንጂ
🤦‍♀
🤷‍♀
ሰው ለሰው ምግቡ ከቶ እንዴት ይሆናል
ሰው ለሰው መጠጡ ከቶ እንዴት ይሆናል

ግን

ግና

ግን

ሰው ለሰው ልብሱ ግን መሆንን ይችላል
እቅፍ ስታረገኝ ሙቀት ይሰማኝል
ከዚ ወዲያ ታዲያ አልባሽ የት ይገኛል
ና
ፍ
ቀ
ኸ
ኛ
ል

✍️ ሐና ይመር
አገጣለው😁



እና እንደነገርኩህ ሁል ጊዜ አገጣላው
ሀዘኔን በጥርሴ አሸንፈዋለው
ምንም እንኳ ህይወት መራራ ብትሆንም
እንባ ሚስፈስስሰኝ ምክንያቴ ቢበዛም
ሀዘኔን በውስጤ ዋጥ አረገውና
ሳቅ ሳቅ እላለው ዳግም እንደገና

💪💪❤️❤️

✍️✍️ሐና ይመር
@hanayimer21
አሁን ደሞ ሙዚቃ እናዳምጣለን 💃


ይመጣል ይሄዳል ፍቅር እና ሰው
ወስዶ ማይመልስ ያው ሞት ብቻ ነው
ሆዴ ረጋ ረጋ በል
ረጋ ረጋ
አትውረድ ቆላ
አትውጣ ደጋ
አረ ወዴት ወዴት
ወዴት ትሄድ ነው
አንድ መኖር ነው
አንድ መሞት ነው

አስቱ❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ነፍስህን ይማረው 🥺

ማመን ቢከብደኝም ሞትህን ልቀበል
ማርያምን ከፍቶኛል ቆይ እሺ ምን ልበል

😭😭😭🥺🥺🥺

josh🥺🥺
ማረው🥺🥺🥺


ገና በለጋ እድሜው ወስደኸዋልና
እኛስ እንዴት እንሁን በምን እንፅናና

ሁሌም እ/ር በስራው ትክክል ነው የወደደውን አደረገ ነብስህ በሰላም ትረፍ josh 🥺