ሐላል ድጅታል ኔትወርክ (Halal Digital Network -HDN) 🇪🇹
7.74K subscribers
933 photos
5 videos
3 files
696 links
ይህ ቻነል ሁለገብ የሆነ ፈላጊና ተፈላጊን አገናኝ ነው። የምትፈልጉትን ሠራተኛ ወይም ያላችሁን የሥራ አይነት ለማመልከት እንዲሁም ድርጅታችሁንና አገልግሎታችሁን ለማስተዋወቅ ይህንን ቦታ ተጠቀሙ። @HalalDigitalNetwork_bot
Download Telegram
እባካችሁ ተባበሯቸው

«ስላም አለይኩም ወላጅ አባታችን ሀጂ ረዲ ሱሩር ለጁምዓ ሰላት ብሎ ከሚኖርበት ፉሪ 04 ቀበሌ አካባቢ እንደወጣ አልተመለሰም እባክህ በማፈላለግ አግዘን። ለብሰውት የነበረው ልብስ በምስሉ ላይ ያለው ነው ከጊዜ ቡኋላ የመጣ የመርሳት ችግር አለበት ።
0911481405
Abduselam Redi
ልጅ »
👍6
📊ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው?

ይህን ቃል በተለያዩ አጋጣሚዎች ሳንሰማው አንቀርም በተለይ አሁን ላይ ይህ ቃል ለብዝዎቻችን እምዛም አዲስ አይደለም ፤ በተለያዩ ሚዲያ ነክ በሆኑ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ቢዝነሶች አገልግሎታቸውን ሲያስተዋውቁ ከዝርዝራቸው መካከል "ዲጂታል ማርኬቲንግ" የሚል እናገኛለን ፣ "ዲጂታል ማርኬቲንግ አሁን ላይ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ ውጤታማ የማርኬቲንግ ዘዴ ነው" ሲባል እንሰማለን ፣ "ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም ዘመናዊዉን የማርኬቲንግ ዘርፍ ሊቀላቀሉ እና ቢዝነስዎን ሊያሳድጉ ይገባል" የሚል መልዕክት ያዘሉ የማነቃቂያ ጽሁፎችም አጋጥመውን ይሆናል ... ለመሆኑ ይህ ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው? ከተለመደው የማርኬቲንግ ዘዴስ በምን ይለያል? እውነት ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም ቢዝነስን ማሳደግ ይቻላል? በየትኛው ደረጃ ላይ ያሉ ቢዝነሶችስ ናቸው ዲጂታል ማርኬቲንግን መጠቀም የሚችሉት?

እስቲ እነዚህን እና መሰል ከዲጂታል ማርኬቲንግ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በሚመልስ መልኩ በዲጂታል ማርኬቲንግ ዙርያ አጭር ዳሰሳ እናድርግ።ዝግጁ ናችሁ? ተከተሉኝ፦

በመጀመሪያ ደረጃ ዲጂታል ማርኬቲንግን በቀላሉ እንድንገነዘብ ስለማርኬቲንግ (Marketing) ጥቅል የሆነ ግንዛቤ እንውሰድ። ማርኬቲንግ (marketing) ማለት "በምርት እና አገልግሎቶች ላይ የገበያውን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል እሴትን (Value) የማጥናት ፣ የመፍጠር እና ለተጠቃሚው የማቅረብ ሂደት ነው። " ከዚህ ገለጻ እንደምንረዳው ማርኬቲንግ "ሂደት" (process) ነው። ይህ ሂደት :- ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ይገዛሉ ተብለው የሚታሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማጥናት እና መለየት ፣ ፍላጎታቸውን መረዳት እና ችግራቸውን ማዳመጥ ፣ ፍላጎታችውን ሊያሟላ ፤ ችግራቸውንም ሊፈታ የሚችል እሴትን አጥንቶ በምርቱ ወይም አገልግሎቱ ላይ ማከል ፣ ከዚያም ማስተዋወቅ ፣ ቀጥሎም ለተጠቃሚዎች አመቺ በሆነ መልኩ ለሽያጭ ማቅረብ እና ከሽያጩም በኋላ ሸማቹ ለምርቱ ወይም አገልግሎቱ ያለው ደንበኝነት ዘላቂ እንዲሆን መስራትን አቅፎ የያዘ ነው።

ማርኬቲንግ ማለት በጥቅሉ ይህ ከሆነ፤ ዲጂታል ማርኬቲንግ፡ ዘመናዊ የሆነ አንድ የማርኬቲንግ አካል ሲሆን ፤ ይህም ዘመኑ ያፈራቸውን አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን( በዋናነት ኢንተርኔትን በመጠቀም) ደንበኞችን የማፈላለግ ፣ ምርት እና አገልግሎቶችን የማስተዋወቅ እና ከደንበኞች ጋር ጥሩ ግንኙነትን በመፍጠር ደንበኝነታቸውን ዘላቂ የማድረግ ሂደት ነው።ይህ እንግዲህ በአጭሩ ስንገልጸው እንጂ ዲጂታል ማርኬቲንግ ሰፊ እና የተለያዩ ዘርፎች ያሉት እራሱን የቻለ አንድ መስክ ነው።

ማርኬቲንግ ለየትኛውም ቢዝነስ መሳካት ትልቅን ሚና ከሚጫወቱ መሳሪያዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል።ዲጂታል ማርኪቲንግ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ፤ ደንበኞችን ማፈላለግ እና ምርት እና አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ የመሰሉ የማርኬቲንግ ስራዎች እንደ ጋዜጣ እና መጽሔት ባሉ የህትመት ውጤቶች ፣ እንደ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ባሉ የሚዲያ አውታሮች እንዲሁም በየመንገዱ በተተከሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ይሰራ ነበር።ዲጂታል ማርኬቲንግ ከመጣም በኋላ ቢሆን እነዚህ የማስተዋወቂያ መንገዶች ዛሬም ድረስ ይሰራባቸዋል።

ኢንተርኔት እና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ብቅ ብቅ ማለታቸውን ተከትሎ ጥቅም ላይ እየዋለ የመጣው ዲጂታል ማርኬቲንግ በተለመዱት የማርኬቲግ ዘዴዎች ለመስራት አስቸጋሪ የነበሩ የማርኬቲንግ ስራዎችን በቀላሉ እና እጅግ ውጤታማ በሆነ መልኩ በመፈጸም በማርኬቲንግ ዘርፉ ላይ ከአሰራር ጀምሮ ትልቅን ለውጥ ፈጥሯል

ምንም እንኳን በኢንተርኔትን አማካኝነት የሚሰሩ የማርኬቲንግ ስራዎች ከዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ ትልቁን ድራሻ ቢይዙም ፤ ያለ ኢንተርኔት የሚሰሩ በዲጂታል ማርኬቲንግ ስር የሚካተቱ የማርኬቲንግ ስራዎች አሉ።ለምሳሌ :- በሞባይል መተግበሪያዎች (mobile apps) እና በአጭር የጽሁፍ መልዕክቶች (SMS) አማካኝነት የሚሰሩ የማርኬቲንግ ስራዎች በዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።ምክንያቱም ዲጂታል ማርኬቲንግ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው "አዳዳኢስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የሚሰራ የማርኬቲንግ ስራ ነው"

ዲጂታል ማርኬቲንግ "E-CRM" ላይ የተመሰረተ የንግድ አካሄድ ላይ የሚያተኩር ሲሆን "E-CRM (Electronic Customer Relationship Management)" ቃል በቃል ሲተረጎም "ኤሌክትሮኒክ የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር" እንደማለት ሲሆን ፤ ይህም አንድ ቢዝነስ ወይም ድርጅት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የደንበኞቹን መረጃ የሚያሰባስብበት እንዲሁም ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት እና መስተጋብር የሚያስተዳድርበት ስርዓት ነው።

ስለዲጂታል ማርኬቲንግ አልጨረስንምኧረ እንደውም አልጀመርንም!
ነገር ግን ጽሑፉ ከዚህ በላይ እንዳይረዝም ለዛሬ እዚህ ላይ ለማቆም እገደዳለው።ቀጥለው በሚኖሩን ጽሁፎች ስለዲጂታል ማርኬቲንግ ፣ ስለ ዓይነቶቹ ፣ ስለ ስልቶቹ ፣ በፊት ከተለመደው የማርኬቲንግ አሰራር ጋር ያላቸውን ልዩነት ይበልጥ በዝርዝር እንዳስሳለን። ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም ቢዝነስዎን የተሳካ ለማድረግ የሚያስቡ ከሆነ ወይም ስለዲጂታል ማርኬቲንግ በማወቅ ስለ አዳዲስ ነገሮች ያልዎትን ጠቅላላ ዕውቀት ማሳደግ የሚፈልጉ ከሆነ የዚህን ጽሁፍ ቀጣይ ክፍሎች እንዲከታተሉ እጋብዝዎታለው።
===============
By:Salim Selim /Graphic designer/
#digital_marketing
@salworks
👍10
«አሰላሙአለይኩም ያጀመዓ በፎቶ ላይ የምታዩት ከድር ደድገባ ይባላል መስማትም ሆነ መናገር አይችልም ሀሙስ ማለትም በቀን 23/03/2015 ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም በእለቱ የለበሰው ልብስ ሲልቨር ከለር ሹራብ የሙስሊም ኮፍያ ጂንስ ሱሪ እንዲሁም ነጠላ ጫማ አድርጎ የነበረ ሲሆን እሱን ያየ ወይም ያለበትን የሚያቅ እንድትጠቁሙን በአላህ ስም እንጠይቃለን
ስልክ ቁጥር 0922484417
0915947647»
👍4
Applicants must send any useful documents related to their previous work exposures and academic backgrounds.
Telegram:- @addiscapital_contact
👍1👎1
ይቺንን መኪና ያያቹ አዳማ ላይ ተሰርቆዋል አፋልጉኝ
 
አፍልጉኝ

share ↔️share↔️share ⤵️

ይህች ታርጋዋ B16919 አ.አ ኮድ 3 የሆነችው Toyota Corolla   መኪና ህዳር 9 /2015። አርብ 5 ሠዓት ላይ በአዳማ ናዝሬት ከተማ በሌባ ተሰርቆ  የጠፍ ሲሆን እስካሁን ሊገኝ አልቻለም እና ያያቹ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውላቹ  እንድታሳውቁን እንጠይቃለን ።

0930642193
👍61
ዛሬ የባድ ወልዶች በሒክማህ ዩኒቨርስቲ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ለእንግዶች ያቀረቡት ባህላዊ ምግብ!

ስሙ ማን ይባላል?
👍4🥰1
የተዘረፈውን የወንድማችንን መኪና በማስመለስ እንተባበረው!

ይህ ወንድማችን ጥሮ ግሮ ቤተሰቦቹን የሚያስተዳድርበትን መኪና አባኮራን ሰፈር አራት መንታ አካባቢ ና ስራ አለ ብለው ወደ ፎቅ እንዲወጣ ካደረጉት በኋላ ምድር ላይ መኪናውን አስነስተው ወስደውበታል ከዚህ በታች የተገለፀውን መኪና የተመለከተ እንድትተባበሩን በአላህ ስም እንጠይቃለን።
Hilux
ሲንግል ጋቢና
5 ጋንች
ነጭ ቀለም
ቀይ ስትራይብ
1983 ሞዴል
በሩ ላይ አረብኛ ማህተም ያለው
ታርጋ አ/አ ኮድ 3-99341

በ 0911148335 ይደውሉልን
ስለ ትብብሮ ከወዲሁ እናመሰግናለን!
👍8
አስቸኳይ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ
~
ተፈላጊዋ :-

ስም:- ነስሪያ ሐሰን
ሰፈሯ:- አጃምባ፣
ት/ቤቷ:- ስልጤ ሰፈር፣
የለበሰችው:- እጅ የሌለው ጂልባብ፣ ኒቃብና ነጭ ጫማ፣
እድሜዋ:- 13 ዓመት፣
ቀጭን ረዘም ያለች። ዛሬ ት/ቤት ብላ ወጥታ አልተመለሰችም።
ያያችሁ ወይም መረጃ ያገኛችሁ በነዚህ ስልክ ቁጥሮች በማሳወቅ ተባበሩን:-

0913490510
0947484034
0920311402
እባካችሁ መልእክቱን በፌስቡክም በማሰራጨት ተባበሩን።
👍4
«ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር የሒሳብ ሠራተኛ ይፈለጋል!

ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ በአካውንቲንግ እና ተያያዥ ሞያዎች በዲግሪ የተመረቀ

ተፈላጊ የስራ ልምድ፦ 1 አመት እና ከዛ በላይ

ፆታ፦ ወንድ

ደሞዝ፦ በስምምነት

የስራ አድራሻ፦ አዲስ አበባ

የማመልከቻ ግዜ፦ እስከ ጥር  10/2015 ዓ.ል

ለማመልከት፦ የሚወዳደሩበትን የሥራ መደብ በመጥቀስ ሲቪ፣ የት/ት ማስተጃና የስራ ልምድ በተከታዩ ኢሜል ወይም የቴሌግራም አድራሻ ይላኩ፦
nesiha.org@gmail.com
+251972757575


©: ነሲሓ ጆብስ
👍5🥰1
Job Title: Afar transcriber

Job Type: Contractual

Work Location: Anywhere/remote

Job Description: We are looking for native Afar Transcribers.

The Work is very simple just listen to Afar audio and type it in the Afar

Note The Work Will Be on an Online Platform and you need a Laptop/PC with stable internet connection

You Have To work daily i.e. 30 Mins of minimum

Female applicants are highly encouraged

Contact...@Bint_abdusomed
አፋልጉን
ከታች ፎቶዉን የምትመለከቱት ወጣት መሀመድ አረብ ሼህ ሁሴን ይባላል።መሀመድ ተወልዶ ያደገዉ በአማራ ክልል አሮሞ ብሔረሰብ ዞን አርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጃራ ቀጨማ ቀበሌ ነዉ።ከአራት አመታት በፊት ወደ ሰዉዲ አረቢያ ተሰዶ ነበር።በሳዉዲ አረቢያ ቆይታዉ ሁለት አመት ድረስ ከቤተሰቡ ጋር ይገናኝ ነበር።ይሁን እንጂ ይሄ ወጣት ከሁለት አመታት ወዲህ ደዉሎ የማያዉቅና የት እንዳለ ድመፁ ስለ ጠፋን:ወጣት መሀመድን ያየ ወይም ያየች ካለ በሰዉዲ አረቢያ ቁጥር። ........+966581422854

በእትዮጵያ ቁጥር................+251905949876
..................+251933661179
በኢሞ እና በቴሌግራም እንድታሳዉቁን በማክበር እንጠይቃለን
ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ።
ላይክና ሼር በማድረግ ይተባበሩን።
IYYAAFANNOO
Dargaggeesa suuraa isaa armaan gadii irratti argitan kun maqaan isaa Mohaammad Arab Sheh Huseen jedhama.Mohaammad Arab Sheh Huseen dhalatee kan guddate Naannoo Amaaraa Godina Saba Oromoo Aanaa Arxummaa Fursii Ganda Jaarraa Qacamaatti. Waggoota Arfan darban dura gara biyya Saudi Arabiyaa godaanee ture.Hanga waggaa lamaatti maatiifi Hiriyoota Waliin bilbilaan walqunnamaa ture.Haata'u malee waggoota lamaan darbaniif Mohaammad Karaa sagalee bilbilaatiin Maatiifi Hiriyoota isaatiin walqunnamee hin beeku.Sagaleen Mohaammad dhabameera.Kanaaf Namni Dargoo Mohaammad Argitan Karaa Lakkoofsa bilbilaa Itoophiyaa fi
Karaa lakkoofsa bilbilaa saudi Arabiyaa,akkasumas Telegram fi Omodhaan Akka nuu beeksiftan kabajaan isiin Gaafanna.Namni Mohammad arge yookiin agarte Gatii Dadhabbii Keessanii rabbiin Isiniif haa Kaffalu. Like fi share gochuun nu waliin ta'aa.
lakk +966581422854
lakk +251905949876
.......+251933661179
«የተለመደ ትብብራችሁን እንሻለን!

በምስሉ ላይ የምትታየው መኪና ዛሬ በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በር ላይ አቁሞ ለጉዳይ ወደ ቢሮ እንደገባ ሰርቀው ወስደዋታል::
Model 5L
ታርጋ 76924
የተለመደ ትብብር ታደርጉልን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን!!
መረጃችሁን 0930697415 ደውላችሁ አሳውቁን:: ወሮታ ከፋይ ነን::»
👍1