Hakim
56.2K subscribers
27.7K photos
279 videos
690 files
5.22K links
Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.
Download Telegram
የጧፍ ማብራት እና ቤተሰብ ማፅናኛ ፕሮግራም | በጥበበ ጊዮን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

በህክምና ተማሪዎች ፣ እጩ ሀኪሞች ፣ ሬዚደንቶች ፣ ስፔሻሊስቶች ፣ ሰብ-ስፔሻሊስቶች እና የዶ/ር አንዱአለም ወዳጅ ዘመድ በተገኘበት ።

ባህርዳር
ጥበበ ጊዮን ሆስፒታል
27/5/17 ዓ.ም

📷 Debol team

@HakimEthio
Why Choose ECT?

we provide Electroconvulsive Therapy (ECT) service at Sitota Center for Mental Health Care. ECT is a safe, fast, and effective treatment for severe depression and other mental health conditions. It is recommended for:

  Rapid relief for severe depression and suicidal risk.
Helps when eating, drinking, or basic functions are affected.
Works when medications fail, especially if ECT helped before.
A vital option when medications pose risks.
For those who experience severe side effects.
When other treatments don’t work.

Modified ECT | Safe for patients | Fast-acting

📞 CALL 0995011035 NOW for a consultation!

Email:  sitota.psych.info@gmail.com

Location:  https://maps.app.goo.gl/oFVRaZFvWNugLYfv8

🔗 https://sitotapsy.com
Fb: fb.me/sisotapsy
Tg: t.me/sitotapsy

@HakimEthio
የፈ/ህ/አጠ/እስፔሻላይዝድ ሆስፒታ ሠራተኞች በዶ/ር አንዷለም ዳኘ መታሰቢያ በመታደም ለጥበበ ጊዮን እስታፎች እና ለዶ/ር አንዷለም ቤተሠቦች አጋርነታውን ገልጸዋል::

ዶ/ር አንዷለም የቀዶ ጥገና ትምህርቱን አብዛኛውን አመት ያጠናቀቀው በፈለገ ህይወት አጠቃላይ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያሳለፈ ሢሆን ስራው በሁሉም እስታፍ ሲታወስ ይኖራል

By: Dr. Desalegn Getahun from felege hiwot

@HakimEthio
አስታውሳለሁ ዶ/ር አንዱአለምን ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ያገኘሁት የመጀመሪያ ዐመት የህክምና ተማሪ ሆኜ ነበር። በጊዜው በጅማ ዩኒቨረሲቲ ለህክምና ትምህርት ከተመደቡ ተማሪዎች አንዱ ነበር።

የቅድመ ህክምና (premed) ትምህርቶችን በምንወስድበት ወቅት በተለይ organic chemistry lab አብረን ለመጀመሪያ ጊዜ በግሩፕ እንድንማማር ስንመደብ የእሱን ባህሪ በቅርበት የመረዳት ዕድል ገጠመኝ። ለሰው ያለው አክብሮት፣ ለስራ ያለው ትጋትና ተነሳሽነት፣ እንዲሁም ሩህሩህና የዋህ ባህሪውን ገና የመጀመሪያ ቀን አየሁ። ይህ ባህሪው አንድም ቀን ሳይቀየር ተመርቀን እስክንወጣ ዘልቋል።

አንዱአለም በባህሪና በሩህሩህነቱ ብቻ አለነበረም የሚመሰገነው፤ በነበረው ብሩህ አዕምሮ ጭምር እንጂ። በጊዜው ስንመረቅ ዶ/ር አንዱአለም የከፍተኛ ውጤት ሜዳሊያና ዋንጫ ሲሸለም ምነው ለፀባይም ዋንጫና ሜዳሊያ ተዘጋጅቶ ቢሸለም ያሉት ብዙዎች ነበሩ።

ዶ/ር አንዱአለምን በሚያሳዝን ሁኔታ በጨካኞች ተነጥቀናል። በእርሱ ሞት ጭካኔ ደግነትን፤ ጥላቻ ፍቅርን፣ ጨለማ ብርሀንን በልጠው ተገኙ። እጅግ ልብ ይሰብራል። በዚህ አጭር ዕድሜው የሚሊዮኖችን ልብ የዳሰሰ ባለምጡቅ አዕምሮ ባለቤትና ሩህሩህ ወንድማችን ሞት ፍትህ ትሻለች። በልባችን የገነባንለት ሀውልት በአደባባይ እንደሚቆምለት ተስፋ አለኝ። ለቤተሰቡና ወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ያድለን።

"ሞት እንኳን ጨክኖ ወስዶ ከሚያስቀረው
ምን አለ ደጋጉን ዳግመኛ ቢፈጥረው።"

ዶ/ር አሻግሬ ገ/ሚካኤል

@HakimEthio
Join us for the second webinar of the EMA's 61st Annual Medical Conference pre-conference CME!


🗓 Date: February 13, 2025

🕑 Time: 2:00-3:30 PM (8:00 local time)

Webinar Title: Pediatrics anesthesia in resource-limited settings: Challenges and Opportunities

🤝 Organized in collaboration with the Ethiopian Anesthesiologist Society

📜 1.5 CEU Certificate

🔗 Register here: 👉 pre-conference-cmes
#EMA #CME #AMC #IHE #HealthExhibition #MedicalConference
የካንሰር ቀን በየአመቱ ጥር 27 በአለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል። የቀኑ አላማም በህመሙ ዙሪያ ያሉትን የተሳሳቱ ግንዛቤዎች መለወጥ እንዲሁም ከህመሙ ጋር እየታገሉ ላሉ ሰዎች የተስፋ ብርሃን ማብራት ነው።

ሆፕ ኦንኮሎጂ በሃገራችን የመጀመሪያው የካንሰር የህክምና ማዕከል ሲሆን የዘንድሮውን የአለም የካንሰር ቀን ከጤና ሚኒስቴር፣ ከብሪጀ ዘ ጋፕ ኢትዮጵያ፣ ከኢትዮጵያ ሄማቶሎጂ እና ኦንኮሎጂ ማህበር እንዲሁም ማናኪ ሄልዝ ኬር ጋር በመተባበር ቀኑን በማዕከሉ ውስጥ በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።

በእለቱም ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች፣ ከካንሰር ያገገሙ ብርቱ እና ለሌሎች ታካሚዎች ጥንካሬ መሆን የቻሉ ግለሰቦች እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት አካላት ተገኝተው ማዕከሉን ጎብኝተው እና ስለወደፊት የካንሰር ህክምና ላይ ውይይትም አድርገው አሳልፈዋል።


World Cancer Day is celebrated globally every year on February 4.
The purpose of the day is to change misconceptions about the disease and to shine a light of hope for those fighting cancer.

Hope Oncology, the first specialized cancer center in Ethiopia, commemorated this year’s World Cancer Day at their center in collaboration with Ministry of Health, Bridge the Gap Ethiopia,  Ethiopian Hematology and Oncology Society, and Manaki Health Care.

The event was attended by various stakeholders, including cancer survivors who serve as a source of strength for other patients, government officials, and invited guests. While they were there, they toured the facility and engaged in discussions about the future of cancer treatment in Ethiopia.

@HakimEthio