𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭🕋
17.6K subscribers
2.26K photos
1.1K videos
15 files
943 links
亗 ꧁﷽꧂ 亗
🤍𝑤𝑒𝑙𝑐𝑜𝑚𝑒 𝑡𝑜 ᴏᴜʀ 𝑐ℎ𝑎𝑛𝑛𝑒𝑙ᥫᩣ
Channel Objective🎊🎊🎊🎊🎊
➻Islamic teachings💛
➻Current information🤗
➻Hadiths and Qurans 🤩


CROSS🔄 @Waver_boy1
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ارح قلبك ... ❤️‍🩹


سورة السجدة 32:4

اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ۖ مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُونَ

አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ከዚያም በዐርሹ ላይ (ስልጣኑ) የተደላደለ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳትም አማላጅም ምንም የላችሁም፤ አትገሰጹምን?
27👍1🥰1🍓1
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭🕋
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭🕋: ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ ❴Part 300❵ #hadith300 "ኢብኑ ዓባስ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል። "ዑመር (ረ.ዐ) በድር ዘመቻ ላይ ከተሳተፉ አንጋፋ ሶሐቦች እኩል ወደ ችሎታቸው ያስገቡኝ ነበር። በነገሩ ደስተኛ ያልነበሩ ሶሐባዎች "ይህ የልጆቻችን እኩያ የሆነ ልጅ ከኛ ጋር እኩል ችሎቱ ላይ መገኘቱ ለምን ይሆን?" አሉ። ዑመርም "ይህ ልጅ ከምታውቁት…
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭🕋:

ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ

❴Part 301❵ #hadith301


"ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት

"የአላህ "እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ" የሚለው የቁርአን አንቀጽ
ከወረደበት ዕለት አንስቶ የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ሶላት በሚስግዱበት ወቅት "ጌታችን ሆይ ጥራት ይገባህ ፥ ምስጋናም ይድረስህ ፥ አላህ ሆይ ምህረትን ለግሰኝ" ማለትን አይተውም ነበር።"

(ቡኻሪና ሙስሊም)



📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/18561

🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
🥰146👍2😢1
ሰዎችን ስትፈራ ትርቃቸዋለህ
🥹አላህን ስትፈራ ግን
ትቀርበዋለህ🌸
83🥰5❤‍🔥3🔥2🕊1
አዳምጡት ትወዱታላችሁ !

መልካም ምሽት
48👍3🔥2
"የትዳር ጥያቄውን ለምን አልተቀበልሽም ?"ብለው ሲጠይቋት

እሷም "በጣም ድሀ ከመሆኑ የተነሳ ገንዘብ ብቻ ነው ያለው" ብላ መለሰችላቸው።

😹😹😹
😁5713👍8😎7👏1
ማልቀስ የድክመት ምልክት አይደለም
ስንወለድ በህይወት እንዳለን ለመናገር ማስረጃችን ነበር!


እናማ እያለቃሳችሁ😭
😢67😁126👍422🤝2
best የምትሉት ቁርአን ቃሪ ማነው
31👍2
🐫የበረሃው እንባ🐫 #ክፍል 12 ይቀጥላል💫


ሞቅ ሞቅ አድርጉት 3:30 ይለቀቃል 🫶
54👍7🥰1
​የበረሃው እንባ

​ክፍል 12

​ፀሐፊ zoya ~

​ኦርሳም የኢዘዲንን ማቃሰት ሲሰማ ደሙ በረዶ ሆነ  የአቡ ሀምዛ ጥይቶች የኢዘዲንን ሁለቱንም እግሮች አጥንታቸውን ሰብረውት ነበር መኪናው ላይ የነበሩት ሰዎች "ቶሎ በል ውጣ " ብለው ቢጮኹም ኦርሳም ግን ጓደኛውን ጥሎ መሄድ አልቻለም መኪናው በግርግሩ መሃል አቧራውን እያነነ ጥሏቸው ነጎደ።

​ዙሪያቸው የጥይት እሳት እና የሰዎች ጩኸት ነግሷል ኦርሳም ምንም እንኳ ሰውነቱ በረሃብ ቢዝልም በድንገት ከየት መጣ የማይባል የሃይል መንፈስ ወረረው የቆሰለውንና ደም የሚፈሰውን ኢዘዲንን በትከሻው ስር ደገፈውና በደረቱ እየተሳበ ጓደኛውን እየጎተተ ከእስር ቤቱ ቅጥር ግቢ በስተጀርባ ወዳለው ጥቁር በረሃ ይዞት ተሽሎኮለከ

​"ኦሪ... ተወኝ... እኔ መሞቴ ነው... አንተ ሮጠህ አምልጥ" አለ ኢዘዲን በህመም እየተቃተተ
​"ዝም በል ኢዙ አህመድን አጥተናል አንተን ደግሞ አላጣህም" አለ ኦርሳም ጥርሱን ነክሶ።

​የጥይቱ ድምፅ እየራቃቸው እስኪሄድ ድረስ በደረታቸው እየተሳቡ በአሸዋው ላይ እየተንከባለሉ ለረጅም ሰዓታት ተጓዙ ኦርሳም የጓደኛውን ከባድ ሰውነት እየጎተተ እጆቹ በአሸዋውና በጠጠር ተቆራርጠው ደም እስኪተፉ ድረስ አልቆመም።

ከጦርነቱ ቀጠና ርቀው አንድ ትልቅ የአሸዋ ክምር ጀርባ ሲደርሱ ኦርሳም ዝልጥ ብሎ ወደቀ
​ሌሊቱ ቀዝቃዛ ነው በረሃው ጭልጥ ያለ ጸጥታ ውስጥ ነው ኦርሳም ካለበት ተነስቶ የኢዘዲንን እግሮች ተመለከተ ሁለቱም እግሮቹ ክፉኛ ቆስለዋል የሚለብሰውን አሮጌ ጨርቅ ቀድዶ ደሙን ለመግታት አጥብቆ አሰረው።

​"አመለጠን ኦሪ" አለ ኢዘዲን አይኑን በጭንቅ ከፍቶ
​"አዎ አመለጠን ኢዙ እነዛ ጨካኞች የሉም  እስር ቤቱም የለም  እኔና አንተ ብቻ ነን የቀረነው" አለው ኦርሳም ወደ ሰማዩ ቀና ብሎ ጨረቃዋ አሁንም በደመቅ ሁኔታ ታበራለች።

​ኢዘዲን በህመም ውስጥ ሆኖ ፈገግ አለ "አህመድ... አህመድ ቢኖር ደስ ይለኝ ነበር።"
​በዚያ ሰፊ በረሃ ውስጥ ሁለት ደካማ ወጣቶች አንዱ መራመድ የማይችል ሌላው ደግሞ ጉልበቱ ያለቀበት እጅ ለእጅ ተያይዘው ተኙ በፊታቸው ያለው ጉዞ ረጅም ነው ውሃ የለም ምግብ የለም የኢዘዲን ቁስልም አስጊ ነው ነገር ግን የሁለት ዓመቱ የብረት በር ዛሬ ተሰብሯል።

ንጋቱ ሲቀድ የሊቢያ በረሃ ቅዝቃዜ ተገፎ በሚያቃጥል ትኩሳት መተካት ጀመረ
አንዲት አሮጊት ሴትዮ በበትሯ ነካ ነካ ስታደርገው ኦርሳም በድንጋጤ ከተኛበት ብድግ አለ ሌሊቱ አልፎ ንጋቱ ተተክቷል  የጠዋቷ ፀሐይ በበረሃው አሸዋ ላይ ደም መስላ ወጥታለች ኦርሳም አይኑን ሲገልጥ የተመለከተው ነገር ግን ከፀሐይዋ ይልቅ ያስፈራው ነበር አንዲት በጥቁር ልብስ የተሸፈኑ፣ ፊታቸው በዕድሜና በበረሃ ንፋስ የተሰነጣጠቁ አሮጊት ከፊቱ ቆመዋል።

​"ሞታችኋል ወይስ በሕይወት አላችሁ?" አሉ ሴትዮዋ በጎረነነ ድምፅ አማርኛቸው እየተሰባበረ ።
​ኦርሳም በፍጥነት ወደ ኢዘዲን ተመለከተ ኢዘዲን በደመ ነፍስ ይተነፍሳል እንጂ ራሱን ስቷል እግሮቹ ላይ የታሰረው ጨርቅ በደም ረክሶ ከአሸዋው ጋር ተጣብቋል ኦርሳም የሀገሬን ሰው አገኘው ብሎ በደረቀ አንደበት "እባክሽ... እርጂን... ጓደኛዬ እየሞተ ነው" አለ።

​አሮጊቷ በረጅሙ ተነፈሱ አካባቢያቸውን በጥርጣሬ አማተሩ"የባኒ ዋሊድ እስረኞች ናችሁ አይደል ትናንት ሌሊት ሰማዩ በጥይት ሲነድ ነበር"
​ኦርሳም ምንም አልመለሰም ዝምታው አዎ የሚል መልስ ነበር አሮጊቷ ወደ ኢዘዲን ጠጋ ብለው ቁስሉን አዩት "እግሮቹ ተሰብረዋል  ደሙ ካልቆመ ነፍሱ መቆያ የላትም" አሉና ከያዙት ትንሽ ከረጢት ውስጥ አንዳች ቅጠላቅጠል አወጡ።

​"ስማ አንበሳው..." አሉ ወደ ኦርሳም ዞረው "እኔ እዚህ አካባቢ የምኖር ዘላን ነኝ  ልጆቼን በዚህ በረሃ ቀብሬያለሁእናም ከብዙ ኢትዮጵያውያን ጋር ኖረያለሁ አይነ ውሃቹም ያስታውቃል ኢትዮጵያዊ ናችሁ አይደል መቼስ እናንተን ለሞት አሳልፌ አልሰጥም ግን እዚህ መቆየት አትችሉም  ጠባቂዎቹ ከተረፉ ፍለጋ መውጣታቸው አይቀርም።"

​ኦርሳም የዛለ ሰውነቱን አበረታቶ ኢዘዲንን ደገፈው አሮጊቷ ከጥቂት ርቀት ላይ የደበቋትን አንዲት ግመል አምጥተው ኢዘዲንን በጭንቅ በላዩ ላይ ጫኑት ኦርሳም የግመሏን ገመድ ይዞ አሮጊቷን እየተከተለ በበረሃው አሸዋ ላይ ጉዞ ጀመሩ
​"ስሜ ማሪላ ይባላል" አሉ አሮጊቷ መንገዳቸውን እየመሩ "ወደ ድንኳኔ እንሂድ እዚያ ትንሽ ውሃና ምግብ ታገኛላችሁ  ግን እወቅ... ይህ በረሃ ለደካሞች ቦታ የለውም ጓደኛህ እንዲተርፍ ከፈለግክ ከእንግዲህ አንተ ልቡ ብቻ ሳትሆን እግሮቹም መሆን አለብህ።"

​ኦርሳም ወደ ግመሏ ላይ ወደ ተኛው ኢዘዲን አየ ኢዘዲን በሕልሙ "አህመድ... አህመድ ..." ብሎ ይቃዣል  ኦርሳም የግመሏን ገመድ አጥብቆ ያዘ ከአህመድ ሞትና ከባኒ ዋሊድ ሲኦል የተረፉት ለዚህ ከሆነ እስከ መጨረሻው ለመታገል ወሰነ

ከሰዓታት አድካሚ ጉዞ በኋላ ከሩቅ አንዲት ብቸኛ ድንኳን ታየች ድንኳኗ በአሸዋ ክምሮች መሃል ተሸሽጋ በመኖሯ ከሩቅ ለሚመጣ ሰው በቀላሉ አትታይም ማሪላ ግመሏን አስቆሟትና ኦርሳምን ረድተው ኢዘዲንን አወረዱት።

​ኢዘዲን አሁንም በከፊል ራሱን ስቷል ማሪላ ወዲያውኑ ጥቂት ፍየል ወተትና ውሃ አቀረቡላቸው ኦርሳም ለሁለት ዓመታት እንዲህ ያለ ጣዕም አያውቅም ነበር ሆኖም ቅድሚያ የሰጠው ለኢዘዲን ነበር በጥቂት ውሃ የደረቀ ከንፈሩን አራሰለት።

​ማሪላ በድንኳኑ ጥግ የነበረውን እሳት አንድደው ያመጡትን ቅጠላቅጠል ከእንስሳ ስብ ጋር ቀላቅለው ለኢዘዲን ቁስል መድኃኒት አዘጋጁ "ቁስሉ ውስጥ ያለው ጥይት መውጣት አለበት ካልሆነ ግን መርዙ ወደ ሰውነቱ ይሰራጫል" አሉ ማሪላ በቁርጠኝነት።

ኦርሳም የጓደኛውን እጅ አጥብቆ ያዘ ኢዘዲን በህመም ሲጮኽ ኦርሳም አብሮት ይቃትታል ያ የሁለት ዓመት እስር ቤት ግርፋት ያላስለቀሰው ኦርሳም የኢዘዲን ስቃይ ግን ልቡን ሰነጠቀው
​ምሽት ላይ ማሪላና ኦርሳም ከድንኳኑ ውጪ ተቀመጡ በረሃው ላይ የነፈሰው ነፋስ የአሸዋ ሽታ ይዞ ይከንፋል።


​"ማሪላ..." አለ ኦርሳም ድምፁ እየተሰባበረ "ለምንድነው የረዳሽን እኛ እኮ ባእድ ነን።"
​ማሪላ ወደ ራቀው ሰማይ አሻቅበው አዩ "ልጄ... በዚህ በረሃ ላይ ስንት እናቶች ልጆቻቸውን በናፍቆት እንደሚጠብቁ አውቃለሁ  እኔም እናት ነኝ የሰው ልጅ በየደረሰበት ቀለምና ቋንቋ ቢለዋወጥም  ስቃዩ ግን አንድ ነው አንተ ጓደኛህን ጥለህ አለመሄድህ የሰውነትህ ትልቁ ምስክር ነው።"

"ልጆቼ እዚህ ብትቆዩ አገግማችሁ ብትሄዱ ደስ ይለኝ ነበር ግን ዛሬውኑ ባህር ተሻግራችሁ ማለፍ አለባችሁ እና እዛ ስትደርሱ ኤርትራውያን ነን ትላላችሁ አለዚያ ስቃይ ውስጥ ትገባላችሁ ምክንያቱም ኢትዮጵያ የሰላም ኖቤል አላት "
ኢዘድንን እግሩን እያሰሩለት

" እሺ እናቴ ግን በባህር እንዴት መጓዝ እንችላለን "አለ ኦርሳም
"አላህ ያለውን ነው ሚሆነው በመጀመሪያ ከዛ አታስቡ አብረን የሆነ ቦታ ወስዳቹሃለው እዛ ዘዴ አናጣም

​ማሪላ የኢዘዲንን እግር በንጹህ ጨርቅ አጥብቀው ካሰሩ በኋላ በድንኳኑ ውስጥ የነበረችውን አሮጌ ሳጥን ከፈቱ  በውስጡ ጥቂት የሊቢያ ቂጣ እና ትንሽ የታሸገ ውሃ አወጡ "ይህንን ያዙ መንገዱ ረጅም ነው" አሉ በሃዘን እያዩዋቸው።
52👍2
​ኦርሳም የኢዘዲንን እጅ በትከሻው ላይ አደረገው ኢዘዲን ምንም እንኳ ህመሙ ባይለቀውም ማሪላ ያደረጉለት የቅጠላቅጠል ህክምና ደሙን ገትቶለታል "እማማ ማሪላ... ስለ ሁሉም ነገር አመሰግናለሁ" አለ ኢዘዲን ድምፁ እየተንቀጠቀጠ።
​​.......
.......
............
ከ 100🥰 ቡሃላ .......
#ክፍል_12_ይቀጥላል☆....
114👍9
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መታየት ያለበት ጉዳይ!

ሰአት አጠቃቀም በነብያችን ሱና መሰረት
19
አላህ ለማንም ውብ የሆነን ፊት
ሊሰጥ ይችላል‥ ነገር ግን ውብ
የሆነችን ልብ ከሰጠህ ሁሌም ሊያይህ
እንደሚፈልግ እወቅ።🌸

   
68🥰7👍5💯3
الصلاة خير من النوم
 

ሶላተል ፈጅር👉🏻

🌸አትርሱ እ... 😊👇

🌸اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ عِلْمًا نَافِعًا، وَرِزْقًا طَيِّبًا، وَعَمَلًا مُتَقَبَّلًا❤️‍🩹

🤍ሌላው ደሞ

ሱጁድ የሽክምህ ማራገፍያ ነው የተጫናችሁ ሃሳብ ሁሉ ከላያችሁ ላይ እስኪራገፍ ድረስ ሱጁድ አስረዝሙ🧎‍♂️
ሱጁድ ማለት በግንባርህ መሬት ላይ ተደፍተህ ለመሬት ታንሾካሹካለህ ድምፅህ ግን ሰማይ ቤት ይሰማል እኔንም በዱአቹ አትርሱኝ 🤲🤍😊

ғяԀı.....✍️

مع السلام🤗
47🥰3🍓1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ ❤️

🌙 ሰባኹል ኸይር / ሰባኹል ኑር

📖🎧 #ቁርኣን  || PART ❸❸❶

⭐️ 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭 || SHARE 😊
👍85
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭🕋
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭🕋: ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ ❴Part 301❵ #hadith301 "ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት "የአላህ "እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ" የሚለው የቁርአን አንቀጽ ከወረደበት ዕለት አንስቶ የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ሶላት በሚስግዱበት ወቅት "ጌታችን ሆይ ጥራት ይገባህ ፥ ምስጋናም ይድረስህ ፥ አላህ ሆይ ምህረትን ለግሰኝ" ማለትን አይተውም ነበር።" (ቡኻሪና…
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭🕋:

ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ

❴Part 302❵ #hadith302


"አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፦

"የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ለህልፈት እስኪበቁ ድረስ አላህ በርሳቸው ላይ የሚያወርደውን ራዕይ (ወህይ) አከታተለ፡፡ "ወህይ" በብዛት በወረደበት ወቅት ነው መልዕክተኛው (ሶ.ዐ.ወ) የሞቱት፡፡"

(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውጣል)



📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/18580

🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
🥰124😢2
ሚስቴን ያገቷት ሰዎች እያስፈራሩኝ ነው☹️
.
100ሺ ብር ካላመጣክ ሚስትክን
.
.

እንለቃታለን ብለው🫣
😁89😱74😎3💔2🤯1
〽️ University ምደባ

ተማሪዎች የምደባ ውጤታቸውን በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት https://student.ethernet.edu.et/view-placement ማየት ይችላሉ ብሏል።

ቅሬታ ያላቸው ምደባው ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በኦንላይን  ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints ብቻ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።
👍81
🐫የበረሃው እንባ🐫 #ክፍል 13 ይቀጥላል💫


ሞቅ ሞቅ አድርጉት 3:30 ይለቀቃል 🫶
39👍10
​የበረሃው እንባ


​ክፍል 13


​ፀሐፊ zoya ~


.....​ማሪላ ያዘጋጁት አሮጌ መኪና ከድንኳኑ ጀርባ ተሸሽጎ ነበር ሌሊቱ እየገፋ ሲሄድ ኦርሳም እና ማሪላ ኢዘዲንን በጭንቅ ወደ መኪናው የኋላ ወንበር አስገቡት የኢዘዲን ትኩሳት እየጨመረ ነው በየመሃሉ የሚተነፍሰው ትንፋሽ ይፋጃል
​"አይዞህ ኢዙ... ትንሽ ነው የቀረን" ይላል ኦርሳም የጓደኛውን እጅ እንደያዘ ግን ውስጡን ፍርሃት ወሮታል  "ከእንግዲህ ባህሩን እንዴት እንሻገራለን እግሩ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ጀልባ ላይ እንዴት ይቆማል" የሚለው ጥያቄ በአእምሮው ይመላለሳል።

​ማሪላ መኪናውን እያሽከረከሩ ወደ ባህር ዳርቻው ሲቃረቡ የጨው ሽታ እና የባህሩ ድምፅ መሰማት ጀመረ። ​"ስማኝ ልጄ " አሉ ማሪላ አይናቸውን ከመንገዱ ላይ ሳይነቅሉ "እዚህ አካባቢ ያሉ የጀልባ ደላሎች ልብ የላቸውም ገንዘብ ብቻ ነው የሚያውቁት  እኔ የምወስዳችሁ ግን አንዲት ነፍስ ወዳለችው ሰው ዘንድ ነው እሱ ሰሪፍ ይባላል... እንደ እናንተው ስደተኛ ነበር ዛሬ ግን እዚህ ባህር ዳርቻ ላይ ለሚያልፉት ረዳት ሆኗል።"

​መኪናው አንዲት ዝቅተኛ ቤት አጠገብ ቆመች ከቤቷ ውስጥ አንድ ጠንካራ ሰው ወጣ  ማሪላ ሁኔታውን አስረዱት  ሰሪፍ  ወደ ኢዘዲን ቀረብ ብሎ አየውና ራሱን በመታከክ "ይህ ልጅ በዚህ ሁኔታ ባህር መግባት የለበትም  ጀልባዋ ላይ መቶ ሰባ ሰው ይጫናል መተፋፈኑ እና ግፊቱ ቁስሉን ያመረቅዘዋል" አለ።

​ኦርሳም ተንበርክኮ የሰሪፍ እጅ ያዘ  "እባክህ... ባኒ ዋሊድ ተመልሰን እንድንሞት አትተወን እኔ እሸከመዋለሁ እኔ እጠብቀዋለሁ ብቻ አሳፍረን።"
​ሰሪፍ በሃዘን ኦርሳምን አየው "እሺ... ግን አንድ ነገር እወቁ  ባህሩ ላይ ማንም ለማንም አይደርስም ሞገድ ሲነሳ ሁሉም ራሱን ነው የሚያድነው።"


​ንጋት ላይ ማሪላ ሊሰናበቷቸው መጡ ኦርሳም እኚህን ባለውለታ እናት ሲለይ እንባው አልቆም አለ "እናቴ... ላደረግሽልን ሁሉ ምላሹን ፈጣሪ ይክፈልሽ" አላት ​ማሪላም በደረቁ እጆቻቸው ግንባሩን ሳሙት
"ልጄ... በሄድክበት ሁሉ ኤርትራዊ ማለቱን አትርሳ ዛሬ ቢከፋም ነገ ሀገርህ መመኪያ ትሆንሃለች ኤርትራዊ ነኝ በሉ ያልኩህ ለጊዜው ነፍሳችሁን ለማዳን ነው ግን ማንነታችሁን በውስጣችሁ ቅበሩት ሂዱ... አላህ ከእናንተ ጋር ይሁን"


​ጀልባዋ ትንሽ የጎማ ጀልባ  Zodiac ነች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እርስ በርስ እየተጋፉ ሊገቡባት ይሞክራሉ  ኦርሳም ኢዘዲንን በጀርባው አዝሎ በጭንቅ ወደ ጀልባዋ መጨረሻ አካባቢ ተቀመጠ ​"ኦሪ..." አለ ኢዘዲን በደከመ ድምፅ
"ወዬ ኢዙ?"
"ባህሩ በጣም ሰፊ ነው... የምናልፍ ይመስልሃል ።"
"እናልፋለን ተስፋ አትቁረጥ ... አሁን ተኛና እረፍት አድርግ።" ​ጀልባዋ ሞተሯ ተነስቶ ወደ ጥልቁ የሜዲትራኒያን ባህር ጉዞ ጀመረች የሊቢያ የባህር ዳርቻ እየራቀ ሲሄድ  ኦርሳም ወደ ኋላ ዞሮ አሻግሮ ተመለከተ ያ የሁለት ዓመት ስቃይ የጓደኛው የአህመድ ደም የፈሰሰበት ምድር የባኒ ዋሊድ ግድግዳዎች... ሁሉም በጨለማ ውስጥ እየጠፉ ነው።

ጀልባዋ ወደ ጥልቁ ባህር እየገባች በሄደች ቁጥር ማዕበሉ ይበልጥ እየጠነከረ መጣ  ያቺ የጎማ ጀልባ በሰው ብዛት ተጭና ስለነበር በእያንዳንዱ ማዕበል ስትላጋ የውስጡ ስደተኛ ሁሉ "አላህ" እያለ ይጮኻል  ኦርሳም ግን አንድም ቃል አልተነፈሰም የኢዘዲንን ደካማ አካል ደረቱ ላይ አጣብቆ ይዞታል የባህሩ ጨው ቁስሉን እየለበለበው ኢዘዲን በህመም ይቃትታል።

​"ኦሪ... ውሃ... ውሃ እባክህ" አለ ኢዘዲን በደረቀ አንደበት በጀልባዋ ላይ ካለው ግፊያ የተነሳ ኦርሳም ውሃውን ካስቀመጠበት ቦርሳ ውስጥ ለማውጣት አልቻለም ሰው በሰው ላይ ተደራርቧል እንዲያውም አንዳንዶቹ "አትንቀሳቀስ ጀልባዋን ትገለብጣታለህ" እያሉ ይጮኹበታል።

​ሌሊቱ እየጠነከረ ሲሄድ ባህሩ ይበልጥ ተቆጣ ያቺ ጠባብ የጎማ ጀልባ በማዕበሉ ላይ እንደ ቅጠል ትወዛወዛለች  የኢዘዲን ትንፋሽ እያጠረ መጣ የቆሰሉ እግሮቹ በባህሩ ኖራና ጨው ተለብልበው መንቀሳቀስ አቁመዋል ኦርሳም ጓደኛውን በሁለት እጆቹ አቅፎ "አይዞህ ኢዙ... አትተኛ... እናትህ እየጠበቀችህ ነው" እያለ በጆሮው ያንሾካሹካል።

​ድንገት ግን የጀልባዋ ሞተር ድምፅ ተለወጠ "ክሽ... ክሽ..." አለና ቆመ ዙሪያው ጭልጥ ያለ ጸጥታ ነገሰ የሞተሩ ድምፅ ሲጠፋ የሚሰማው የባህሩ ሞገድ ድምፅ ብቻ ሆነ በጀልባዋ ላይ የነበሩት 170 ሰዎች ጸጥ አሉ።

​"ምን ሆነ?" የሚል የድንጋጤ ሹክሹክታ ተሰማ
"ነዳጅ አልቋል" አለ ጀልባዋን ሲያሽከረክር የነበረው ወጣት ድምፁ እየተንቀጠቀጠ
​በሰዎች ፊት ላይ ሞት ሲያንዣብብ ታየ መሃል ባህር ላይ  በጨለማ ያለ ሞተር... ጀልባዋ ቀስ በቀስ ውሃ ማስገባት ጀመረች ሰዎች መጮኽና ማልቀስ ጀመሩ አንዳንዶቹ በያዟቸው ትናንሽ ኩባያዎች ውሃውን ወደ ውጭ ለመድፋት ይታገላሉ።

​ኦርሳም ቀና ብሎ ጨረቃዋን አያት ያቺ በበረሃው ምሽት ያያት ጨረቃ ዛሬም አለች "አህመድ ሆይ... አንተ በበረሃው አሸዋ ውስጥ ቀረህ  እኛ ደግሞ በባህሩ ውስጥ ልንቀር ነው" ሲል ለራሱ አጉተመተመ።

የጀልባዋ ውሃ መሙላትና የሰዎቹ ጩኸት ባህሩን አወከው ሞተሩ በቆመ በግማሽ ሰዓት ውስጥ የጎማዋ ጀልባ ግማሽ አካል በውሃ ተሞላ "ልንሰጥም ነው እርዱን" የሚሉ ጩኸቶች ከየአቅጣጫው ይሰማሉ  ኦርሳም ኢዘዲንን በትከሻው አዝሎ ጀልባዋን አጥብቆ ይዟታል

​"ኦሪ... ይቅር በለኝ... እኔ ነኝ ሸክም የሆንኩት " አለ ኢዘዲን ውሃው ወገቡ ላይ ሲደርስ "ዝም በል አብረን ነው የምናልፈው " አለ ኦርሳም ምንም እንኳ ተስፋው እየተሟጠጠ ቢሆንም።

​ድንገት ከላይ የሚመጣ ታላቅ ንፋስና ከፍተኛ ድምፅ ሰማዩን አናወጠው የባህሩ ሞገድ በኃይል ሲረጭ  ከደመናው መሃል ግዙፍ መብራቶች ወደ ጀልባዋ አበሩ የሄሊኮፕተር ድምፅ ነበር

​"ሄሊኮፕተር ሄሊኮፕተር " ጩኸቱ ተቀየረ የነፍስ አድን ሰራተኞች ከላይ ሆነው ገመዶችንና ትናንሽ ጀልባዎችን ማውረድ ጀመሩ ነገር ግን ጀልባዋ መጨረሻዋ ላይ ደርሳ ነበር ልክ የመጀመሪያው ገመድ እንደወረደ የጎማዋ ጀልባ በሰው ብዛት ተጭና ስለነበር በሁለት ተሰነጠቀች።

​ኦርሳምና ኢዘዲን ወደ ጨለማው ባህር ውስጥ ተዘፈቁ ​ኦርሳም የጨው ውሃው አይኑንና አፍንጫውን እየለበለበው ወደ ላይ ለመውጣት ታገለ በአንድ እጁ ኢዘዲንን አንቆ ይዞታል የሄሊኮፕተሩ መብራት ባህሩን ሲያጥለቀልቀው ኦርሳም በዙሪያው ብዙ ሰዎች ሰጥመው ሲቀሩ አየ 😭
የባህሩ ድምፅ በለቅሶና በዋይታ ተሞላ
​በዚያ መሃል ከሄሊኮፕተሩ የወረደ አንድ የነፍስ አድን ሰራተኛ ወደ ኦርሳም ተጠጋ ኦርሳም በደመነፍስ የኢዘዲንን እጅ ለረዳቱ ሰጠ "እሱን... እሱን ቀድመህ አውጣው" ብሎ ጮኸ።

​ኢዘዲን በገመድ ወደ ላይ ሲሳብ ኦርሳም ማየት የቻለው የመጨረሻው ነገር ቢኖር በባህሩ ላይ የሚንሳፈፉትን የአህመድ መሰል ጓደኞቹን አስከሬን ነበር የባኒ ዋሊድ እስረኞች ግማሹ በበረሃ ግማሹ ደግሞ በባህር ተበሉ...።

​ኦርሳምም በገመድ ተስቦ ሄሊኮፕተሩ ውስጥ ሲገባ ራሱን ከመሳቱ በፊት ያየው ነገር ቢኖር በደም የረከሰውን የኢዘዲን እግርና ሰማያዊውን ባህር ነበር።
​​.......
.......
............
ከ 100🥰 ቡሃላ .......
#ክፍል_14_ይቀጥላል☆....
🥰10247😢13👍6