ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
"በአላህ ላይ የሚገባውን መመካት ብትመኩ ኖሮ፣ ወፍ ተርባ ወጥታ ጠግባ እንደምትመለሰው ሁሉ አላህ ሲሳይን ይሰጣችሁ ነበር።
✨ሶሂህ ቲርሚዚ (2344)✨

❤53🥰8👍3
የበረሃው እንባ
ክፍል 11
ፀሐፊ zoya ~
.....የባኒ ዋሊድ እስር ቤት ጨለማ ግድግዳዎች የብዙዎችን ሲሳይ በልተው የብዙዎችን ተስፋ አምክነው እነሆ ሁለት ዓመታት ነጎዱ በነዚህ ሁለት ዓመታት ውስጥ በዚያ ጠባብ ክፍል ውስጥ የነበሩት ወጣቶች ቁጥር እየቀነሰ ሄዶ አሁን የቀሩት ሦስት ብቻ ናቸው ኦርሳም ኢዘዲን እና አህመድ
ሁለት ዓመት ሙሉ ብርሃን በናፈቃቸው አይኖቻቸው የሰው ልጅ መሆኑን በረሱ ደላላዎች ግርፋት ስር ኖሩ ሰውነታቸው ከስቶ ከአጥንትና ከቆዳ በስተቀር ምንም አልቀራቸውም ልብሳቸው አልቆ አሁን ሰውነታቸውን የሚሸፍኑት በየተራ በሚወረወርላቸው አሮጌ ጨርቅ ነው።
ኦርሳም አሁን ያን መሬት የሚፍቅበትን እንጨት ከጣለ ቆይቷል መሬቱን ከመቆፈር ይልቅ ግድግዳውን ተደግፎ ዝምታን መርጧል በነዚህ ሁለት ዓመታት ውስጥ የኦርሳም ድምፅ እየቀነሰ ትዝታዎቹም እየፈዘዙ መጥተዋል።
ኢዘዲን ግን አሁንም ያ ጠንካራ መንፈሱ አልተሰበረም "ስማ ኦሪ" አለ ኢዘዲን ድምፁ በረሃብ ቢሰባበርም "እነዚህ ሰዎች እኛን ያልገደሉን ለምንድነው ይመስልሃል ሁለት ዓመት ሙሉ ለምን አቆዩን
ኦርሳም አንገቱን ቀና አድርጎ በፈዘዙ አይኖቹ ተመለከተው "ምናልባት እንድንሞት ስላልተፈረደልን ይሆናል" አለ በደረቀ አንደበት
አህመድ ግን አሁንም በዚያው የቆየ ልማዱ ወደ ጣራው አፍጥጦ ይስቃል አሁን ግን ሳቁ እንደ ድሮው አይደለም የደከመ ይመስላል "እኔ አውቃለሁ" አለ አህመድ ጣልቃ ገብቶ ሳል በቀላቀለ አንደበት "እኛን እዚህ ያቆዩን የሰይጣን ምስክሮች እንድንሆን ነው የሰው ልጅ ምን ያህል ሊጨክን እንደሚችል ለዓለም እንድንናገር። ግን ዓለም የሚሰማ ጆሮ የላትም።"አህመድ በጣም ደክሟል እናም ሞት አፋፍ ያለ ይመስላል
የአህመድ ሳል በክፍሉ ውስጥ ያስተጋባል እያንዳንዱ ሳል ደም ይተፋል ሰውነቱ ሁለት ዓመት ሙሉ የደረሰበትን ግርፋትና ረሃብ መቋቋም አቅቶታል "ኦሪ... ኢዙ..." አለ አህመድ ድምፁ እየራቀ "ዛሬ ጣራው ላይ ያሉት ልጆቼ በጣም ቀርበውኛል እየጠሩኝ ነው እጃቸውን ዘርግተው ና አባዬ እያሉኝ ነው..."
ኦርሳም ተንፏቆ ወደ አህመድ ተጠጋ ያ አጥንት ብቻ የሆነውን እጁን ያዘው "አህመድ... አይዞህ ጠንክር ገና ፀሐይን እናያለን" አለው ምንም እንኳ እሱ ራሱ ፀሐይን እንደሚያይ ተስፋ ባይኖረውም።
አህመድ ግን ፈገግ አለ ያ ለሁለት ዓመት ያላቆመው ፈገግታ ዛሬ ብርሃን የተቀላቀለበት ይመስላል "አይ ኦሪ... እኔ ፀሐይን አየኋት ከእናንተ በላይ አየኋት እናንተ ጨለማውን ስታዩ እኔ ብርሃኑን ሳይ ነበር የኖርኩት አሁን ግን መሄጃዬ ነው..." እያለ አይኑን በዝግታ ጨፈነ የአህመድ ትንፋሽ በዚያች ጠባብ ክፍል ውስጥ ለዘላለም ቆመ አዎ አህመድ ልጆቹን እየናፈቀ ሄደ........
ኢዘዲንና ኦርሳም የአህመድን አስክሬን ተደግፈው ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ሁለት ዓመት አብሯቸው የኖረ በምናቡ ዓለም ተስፋ የሆናቸው ሰው ተለያቸው አህመድ አይረሳም አህመድ የውጪውን ዓለም በምናቡ የሚያሳይ ንፁህ ሰው በቃኝ አለ.........
ለሶስት ቀናት የአህመድን ሬሳ ተደግፈው ቆዩ በሶስተኛው ቀን ቂጣ ሲወረወርላቸው ሬሳውን ደላሎች አወጡት የአህመድ አስክሬን በደላሎቹ ፊት ሲወጣ አንዳችም ርህራሄ አልታየባቸውም አንዱ ቁጥር ጎደለ በሚል ንቀት ጎትተው ወሰዱት
ኦርሳምና ኢዘዲን ግን የአህመድ የመጨረሻ ፈገግታ ከአይናቸው ሊጠፋ አልቻለም የአህመድ መሄድ በክፍሉ ውስጥ የነበረውን የመጨረሻውን የምናብ ብርሃንይዞት የሄደ መሰላቸው።
አህመድ ከሄደ በኋላ ክፍሉ ይበልጥ ጠበበ ያቺ ጠባብ ክፍል ቀድሞም ብርሃን አልነበራትም አሁን ግን ተስፋም የራቃት መሰለች አህመድ ሲኖር በሳቁና በምናቡ የክፍሉን ግድግዳዎች ገፍትሮ ሰፊ ዓለም ይፈጥር ነበር አሁን ግን የቀሩት ግድግዳዎች እና የአጥንት ስብስብ የሆኑት ሁለቱ ወጣቶች ብቻ ናቸው።
ኢዘዲን ለረጅም ሰዓታት ዝምታን መረጠ አህመድ ሲሞት አብሮት የሞተ ነገር ያለ ይመስላል ኦርሳም ባቀረቀረበት ዝም አለ። በሁለት ዓመት ውስጥ ደጋፊያቸው ለካስ አህመድ ነበር
"ኢዙ..." አለ ኦርሳም ድምፁ ከጉሮሮው በጥብቅ እየወጣ "አህመድ ፀሐይን አየኋት ብሎ ነው የሄደው እኛስ መች ይሁን ማየት ያለብን እዚህ ሞት እስኪመጣ መጠበቅ አንችልም።"
ኢዘዲን ደከም ባለ ድምፅ መለሰ "ኦሪ... እንዴት ሰውነታችን መቆም እንኳን አቅቶታል እነዚህ ግድግዳዎች ደግሞ ከብረት ይበረታሉ"
ኦርሳም ተስፋ ባይኖርም ተስፋ ለመፍጠር "አህመድ በመጨረሻው ሰዓት የነገረን አንድ ነገር አለ 'እንዳንሞት ስላልተፈረደልን ነው የቆየነው' ብለህ ነበር አዎ መኖር ስላለብን ነው እስካሁን ያለነው ካልሞከርን ግን የአህመድ መስዋዕትነት ትርጉም አይኖረውም።"
በዚያው ምሽት ያልተለመደ ግርግር ከእስር ቤቱ ውጪ ይሰማ ጀመር የመተራመስ ድምፅ የሰዎች ጩኸት እና የከባድ መኪናዎች ኳኳታ የባኒ ዋሊድን ፀጥታ አወከው ደላሎቹና ጠባቂዎቹ ሲደናገጡ ይሰማል በድንገት የክፍላቸው በር በሃይል ተከፈተ አንድ የታጠቀና ፊቱን በጨርቅ የተሸፈነ ሰው ወደ ውስጥ ገባ ኦርሳምና ኢዘዲን ለግርፋት የመጣ መስሏቸው ተኮማተሩ ነገር ግን ሰውየው የያዘውን የእጅ ባትሪ ወደ እነሱ አበራና "መነሳት የምትችሉ ተነሱ ጊዜ የለም" አለ በግርግር ድምፅ።
ኦርሳም ኢዘዲንን ደገፍ አድርጎ ለማቆም ሞከረ እግሮቻቸው ቢንቀጠቀጡም የነፃነት ሽታ ግን አዲስ ጉልበት ሰጣቸው ከክፍሉ ሲወጡ በየኮሪደሩ የወደቁ አስክሬኖችንና የተሰባበሩ በሮችን ተሻገሩ።
ከሁለት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጪውን አየር ተነፈሱ ምንም እንኳ ሌሊት ቢሆንም የጨረቃዋ ብርሃን ለእነሱ ከቀትር ፀሐይ በላይ በራች በረሃው ላይ የቆሙት የጭነት መኪናዎች የተረፉትን እስረኞች እየጫኑ ነው።
ኦርሳም ወደ ሰማዩ ቀና ብሎ አየ "አህመድ..." አለ በለሆሳስ "አሁን ፀሐይን ባታያትም ጨረቃዋን ግን በአንተ አይን እያየኋት ነው።"
ነገር ግን ነፃነታቸው ገና ሙሉ አልነበረም ወደ መኪናው ሊወጡ ሲሉ ከሩቅ አንድ ድምፅ ተሰማ የደላላው የአቡ ሀምዛ ድምፅ ነበር "አይሳካላችሁም ማንም ከዚህ በህይወት አይወጣም " እያለ ወደ እነሱ መተኮስ ጀመረ
ኢዘዲን ኦርሳምን ወደ መኪናው ገፋውና እሱ ራሱ መሬት ላይ ተከለለ ጥይቶቹ በመኪናው ብረት ላይ ሲያርፉ "ቺክ ቺክ" የሚል ድምፅ ያሰማሉ ነገር ግን የ ኢዘድን የማቀሰት ድምፅ መሰማት ጀመረ ኦሪ ወደ ኢዘድን ሲያይ.........
.......
.......
............
ከ 100🥰 ቡሃላ .......
☆#ክፍል_12_ይቀጥላል☆....

❤116👍6🥰4
አስካሁን ላልተኛችሁ ዱአ ላርግላቺሁ ያ አላህ
አሪፍ ሀያት ስጠን
እያየህ ኢማንን ጨምርልን
ሀያትና ኢማናችን ከተስማሙ ኢክራም እና ኢልሀምን ጨምርልን 🤲
----------------------------------አሚን
አሪፍ ሀያት ስጠን
እያየህ ኢማንን ጨምርልን
ሀያትና ኢማናችን ከተስማሙ ኢክራም እና ኢልሀምን ጨምርልን 🤲
----------------------------------አሚን
❤19😁17🤯4🫡4👍1
ሱብሂ ሰላት ማለት ልክ እንደ
ጦር ሜዳ ነው ጀግኖች እንጂ
አይካተቱበትም💯
ቤቱ ከተኛ ጫማ ንጉስ እና
መስጂድ ከሚሰግድ ደሀ ሰው
የደሀው ሰውዬ ጫማ በላጭ ነች❤️
ጦር ሜዳ ነው ጀግኖች እንጂ
አይካተቱበትም💯
ቤቱ ከተኛ ጫማ ንጉስ እና
መስጂድ ከሚሰግድ ደሀ ሰው
የደሀው ሰውዬ ጫማ በላጭ ነች❤️
🍓18💯9👏6❤2👍2😢1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ارح قلبك ... ❤️🩹
سورة السجدة 32:4
اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ۖ مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُونَ
አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ከዚያም በዐርሹ ላይ (ስልጣኑ) የተደላደለ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳትም አማላጅም ምንም የላችሁም፤ አትገሰጹምን?

❤27👍1🥰1🍓1
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋: ✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 300❵ #hadith300 "ኢብኑ ዓባስ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል። "ዑመር (ረ.ዐ) በድር ዘመቻ ላይ ከተሳተፉ አንጋፋ ሶሐቦች እኩል ወደ ችሎታቸው ያስገቡኝ ነበር። በነገሩ ደስተኛ ያልነበሩ ሶሐባዎች "ይህ የልጆቻችን እኩያ የሆነ ልጅ ከኛ ጋር እኩል ችሎቱ ላይ መገኘቱ ለምን ይሆን?" አሉ። ዑመርም "ይህ ልጅ ከምታውቁት…
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋:
✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨
❴Part 301❵ #hadith301
"ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት
"የአላህ "እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ" የሚለው የቁርአን አንቀጽ
ከወረደበት ዕለት አንስቶ የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ሶላት በሚስግዱበት ወቅት "ጌታችን ሆይ ጥራት ይገባህ ፥ ምስጋናም ይድረስህ ፥ አላህ ሆይ ምህረትን ለግሰኝ" ማለትን አይተውም ነበር።"
(ቡኻሪና ሙስሊም)
📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/18561
🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫

🥰14❤6👍2😢1
"የትዳር ጥያቄውን ለምን አልተቀበልሽም ?"ብለው ሲጠይቋት
እሷም "በጣም ድሀ ከመሆኑ የተነሳ ገንዘብ ብቻ ነው ያለው" ብላ መለሰችላቸው።
😹😹😹

😁56❤13👍8😎7👏1
ማልቀስ የድክመት ምልክት አይደለም
ስንወለድ በህይወት እንዳለን ለመናገር ማስረጃችን ነበር!
እናማ እያለቃሳችሁ😭
ስንወለድ በህይወት እንዳለን ለመናገር ማስረጃችን ነበር!
😢67😁12❤6👍4☃2✍2🤝2
❤54👍7🥰1
የበረሃው እንባ
ክፍል 12
ፀሐፊ zoya ~
ኦርሳም የኢዘዲንን ማቃሰት ሲሰማ ደሙ በረዶ ሆነ የአቡ ሀምዛ ጥይቶች የኢዘዲንን ሁለቱንም እግሮች አጥንታቸውን ሰብረውት ነበር መኪናው ላይ የነበሩት ሰዎች "ቶሎ በል ውጣ " ብለው ቢጮኹም ኦርሳም ግን ጓደኛውን ጥሎ መሄድ አልቻለም መኪናው በግርግሩ መሃል አቧራውን እያነነ ጥሏቸው ነጎደ።
ዙሪያቸው የጥይት እሳት እና የሰዎች ጩኸት ነግሷል ኦርሳም ምንም እንኳ ሰውነቱ በረሃብ ቢዝልም በድንገት ከየት መጣ የማይባል የሃይል መንፈስ ወረረው የቆሰለውንና ደም የሚፈሰውን ኢዘዲንን በትከሻው ስር ደገፈውና በደረቱ እየተሳበ ጓደኛውን እየጎተተ ከእስር ቤቱ ቅጥር ግቢ በስተጀርባ ወዳለው ጥቁር በረሃ ይዞት ተሽሎኮለከ
"ኦሪ... ተወኝ... እኔ መሞቴ ነው... አንተ ሮጠህ አምልጥ" አለ ኢዘዲን በህመም እየተቃተተ
"ዝም በል ኢዙ አህመድን አጥተናል አንተን ደግሞ አላጣህም" አለ ኦርሳም ጥርሱን ነክሶ።
የጥይቱ ድምፅ እየራቃቸው እስኪሄድ ድረስ በደረታቸው እየተሳቡ በአሸዋው ላይ እየተንከባለሉ ለረጅም ሰዓታት ተጓዙ ኦርሳም የጓደኛውን ከባድ ሰውነት እየጎተተ እጆቹ በአሸዋውና በጠጠር ተቆራርጠው ደም እስኪተፉ ድረስ አልቆመም።
ከጦርነቱ ቀጠና ርቀው አንድ ትልቅ የአሸዋ ክምር ጀርባ ሲደርሱ ኦርሳም ዝልጥ ብሎ ወደቀ
ሌሊቱ ቀዝቃዛ ነው በረሃው ጭልጥ ያለ ጸጥታ ውስጥ ነው ኦርሳም ካለበት ተነስቶ የኢዘዲንን እግሮች ተመለከተ ሁለቱም እግሮቹ ክፉኛ ቆስለዋል የሚለብሰውን አሮጌ ጨርቅ ቀድዶ ደሙን ለመግታት አጥብቆ አሰረው።
"አመለጠን ኦሪ" አለ ኢዘዲን አይኑን በጭንቅ ከፍቶ
"አዎ አመለጠን ኢዙ እነዛ ጨካኞች የሉም እስር ቤቱም የለም እኔና አንተ ብቻ ነን የቀረነው" አለው ኦርሳም ወደ ሰማዩ ቀና ብሎ ጨረቃዋ አሁንም በደመቅ ሁኔታ ታበራለች።
ኢዘዲን በህመም ውስጥ ሆኖ ፈገግ አለ "አህመድ... አህመድ ቢኖር ደስ ይለኝ ነበር።"
በዚያ ሰፊ በረሃ ውስጥ ሁለት ደካማ ወጣቶች አንዱ መራመድ የማይችል ሌላው ደግሞ ጉልበቱ ያለቀበት እጅ ለእጅ ተያይዘው ተኙ በፊታቸው ያለው ጉዞ ረጅም ነው ውሃ የለም ምግብ የለም የኢዘዲን ቁስልም አስጊ ነው ነገር ግን የሁለት ዓመቱ የብረት በር ዛሬ ተሰብሯል።
ንጋቱ ሲቀድ የሊቢያ በረሃ ቅዝቃዜ ተገፎ በሚያቃጥል ትኩሳት መተካት ጀመረ
አንዲት አሮጊት ሴትዮ በበትሯ ነካ ነካ ስታደርገው ኦርሳም በድንጋጤ ከተኛበት ብድግ አለ ሌሊቱ አልፎ ንጋቱ ተተክቷል የጠዋቷ ፀሐይ በበረሃው አሸዋ ላይ ደም መስላ ወጥታለች ኦርሳም አይኑን ሲገልጥ የተመለከተው ነገር ግን ከፀሐይዋ ይልቅ ያስፈራው ነበር አንዲት በጥቁር ልብስ የተሸፈኑ፣ ፊታቸው በዕድሜና በበረሃ ንፋስ የተሰነጣጠቁ አሮጊት ከፊቱ ቆመዋል።
"ሞታችኋል ወይስ በሕይወት አላችሁ?" አሉ ሴትዮዋ በጎረነነ ድምፅ አማርኛቸው እየተሰባበረ ።
ኦርሳም በፍጥነት ወደ ኢዘዲን ተመለከተ ኢዘዲን በደመ ነፍስ ይተነፍሳል እንጂ ራሱን ስቷል እግሮቹ ላይ የታሰረው ጨርቅ በደም ረክሶ ከአሸዋው ጋር ተጣብቋል ኦርሳም የሀገሬን ሰው አገኘው ብሎ በደረቀ አንደበት "እባክሽ... እርጂን... ጓደኛዬ እየሞተ ነው" አለ።
አሮጊቷ በረጅሙ ተነፈሱ አካባቢያቸውን በጥርጣሬ አማተሩ"የባኒ ዋሊድ እስረኞች ናችሁ አይደል ትናንት ሌሊት ሰማዩ በጥይት ሲነድ ነበር"
ኦርሳም ምንም አልመለሰም ዝምታው አዎ የሚል መልስ ነበር አሮጊቷ ወደ ኢዘዲን ጠጋ ብለው ቁስሉን አዩት "እግሮቹ ተሰብረዋል ደሙ ካልቆመ ነፍሱ መቆያ የላትም" አሉና ከያዙት ትንሽ ከረጢት ውስጥ አንዳች ቅጠላቅጠል አወጡ።
"ስማ አንበሳው..." አሉ ወደ ኦርሳም ዞረው "እኔ እዚህ አካባቢ የምኖር ዘላን ነኝ ልጆቼን በዚህ በረሃ ቀብሬያለሁእናም ከብዙ ኢትዮጵያውያን ጋር ኖረያለሁ አይነ ውሃቹም ያስታውቃል ኢትዮጵያዊ ናችሁ አይደል መቼስ እናንተን ለሞት አሳልፌ አልሰጥም ግን እዚህ መቆየት አትችሉም ጠባቂዎቹ ከተረፉ ፍለጋ መውጣታቸው አይቀርም።"
ኦርሳም የዛለ ሰውነቱን አበረታቶ ኢዘዲንን ደገፈው አሮጊቷ ከጥቂት ርቀት ላይ የደበቋትን አንዲት ግመል አምጥተው ኢዘዲንን በጭንቅ በላዩ ላይ ጫኑት ኦርሳም የግመሏን ገመድ ይዞ አሮጊቷን እየተከተለ በበረሃው አሸዋ ላይ ጉዞ ጀመሩ
"ስሜ ማሪላ ይባላል" አሉ አሮጊቷ መንገዳቸውን እየመሩ "ወደ ድንኳኔ እንሂድ እዚያ ትንሽ ውሃና ምግብ ታገኛላችሁ ግን እወቅ... ይህ በረሃ ለደካሞች ቦታ የለውም ጓደኛህ እንዲተርፍ ከፈለግክ ከእንግዲህ አንተ ልቡ ብቻ ሳትሆን እግሮቹም መሆን አለብህ።"
ኦርሳም ወደ ግመሏ ላይ ወደ ተኛው ኢዘዲን አየ ኢዘዲን በሕልሙ "አህመድ... አህመድ ..." ብሎ ይቃዣል ኦርሳም የግመሏን ገመድ አጥብቆ ያዘ ከአህመድ ሞትና ከባኒ ዋሊድ ሲኦል የተረፉት ለዚህ ከሆነ እስከ መጨረሻው ለመታገል ወሰነ
ከሰዓታት አድካሚ ጉዞ በኋላ ከሩቅ አንዲት ብቸኛ ድንኳን ታየች ድንኳኗ በአሸዋ ክምሮች መሃል ተሸሽጋ በመኖሯ ከሩቅ ለሚመጣ ሰው በቀላሉ አትታይም ማሪላ ግመሏን አስቆሟትና ኦርሳምን ረድተው ኢዘዲንን አወረዱት።
ኢዘዲን አሁንም በከፊል ራሱን ስቷል ማሪላ ወዲያውኑ ጥቂት ፍየል ወተትና ውሃ አቀረቡላቸው ኦርሳም ለሁለት ዓመታት እንዲህ ያለ ጣዕም አያውቅም ነበር ሆኖም ቅድሚያ የሰጠው ለኢዘዲን ነበር በጥቂት ውሃ የደረቀ ከንፈሩን አራሰለት።
ማሪላ በድንኳኑ ጥግ የነበረውን እሳት አንድደው ያመጡትን ቅጠላቅጠል ከእንስሳ ስብ ጋር ቀላቅለው ለኢዘዲን ቁስል መድኃኒት አዘጋጁ "ቁስሉ ውስጥ ያለው ጥይት መውጣት አለበት ካልሆነ ግን መርዙ ወደ ሰውነቱ ይሰራጫል" አሉ ማሪላ በቁርጠኝነት።
ኦርሳም የጓደኛውን እጅ አጥብቆ ያዘ ኢዘዲን በህመም ሲጮኽ ኦርሳም አብሮት ይቃትታል ያ የሁለት ዓመት እስር ቤት ግርፋት ያላስለቀሰው ኦርሳም የኢዘዲን ስቃይ ግን ልቡን ሰነጠቀው
ምሽት ላይ ማሪላና ኦርሳም ከድንኳኑ ውጪ ተቀመጡ በረሃው ላይ የነፈሰው ነፋስ የአሸዋ ሽታ ይዞ ይከንፋል።
"ማሪላ..." አለ ኦርሳም ድምፁ እየተሰባበረ "ለምንድነው የረዳሽን እኛ እኮ ባእድ ነን።"
ማሪላ ወደ ራቀው ሰማይ አሻቅበው አዩ "ልጄ... በዚህ በረሃ ላይ ስንት እናቶች ልጆቻቸውን በናፍቆት እንደሚጠብቁ አውቃለሁ እኔም እናት ነኝ የሰው ልጅ በየደረሰበት ቀለምና ቋንቋ ቢለዋወጥም ስቃዩ ግን አንድ ነው አንተ ጓደኛህን ጥለህ አለመሄድህ የሰውነትህ ትልቁ ምስክር ነው።"
"ልጆቼ እዚህ ብትቆዩ አገግማችሁ ብትሄዱ ደስ ይለኝ ነበር ግን ዛሬውኑ ባህር ተሻግራችሁ ማለፍ አለባችሁ እና እዛ ስትደርሱ ኤርትራውያን ነን ትላላችሁ አለዚያ ስቃይ ውስጥ ትገባላችሁ ምክንያቱም ኢትዮጵያ የሰላም ኖቤል አላት "
ኢዘድንን እግሩን እያሰሩለት
" እሺ እናቴ ግን በባህር እንዴት መጓዝ እንችላለን "አለ ኦርሳም
"አላህ ያለውን ነው ሚሆነው በመጀመሪያ ከዛ አታስቡ አብረን የሆነ ቦታ ወስዳቹሃለው እዛ ዘዴ አናጣም
ማሪላ የኢዘዲንን እግር በንጹህ ጨርቅ አጥብቀው ካሰሩ በኋላ በድንኳኑ ውስጥ የነበረችውን አሮጌ ሳጥን ከፈቱ በውስጡ ጥቂት የሊቢያ ቂጣ እና ትንሽ የታሸገ ውሃ አወጡ "ይህንን ያዙ መንገዱ ረጅም ነው" አሉ በሃዘን እያዩዋቸው።

❤51👍2
ኦርሳም የኢዘዲንን እጅ በትከሻው ላይ አደረገው ኢዘዲን ምንም እንኳ ህመሙ ባይለቀውም ማሪላ ያደረጉለት የቅጠላቅጠል ህክምና ደሙን ገትቶለታል "እማማ ማሪላ... ስለ ሁሉም ነገር አመሰግናለሁ" አለ ኢዘዲን ድምፁ እየተንቀጠቀጠ።
.......
.......
............
ከ 100🥰 ቡሃላ .......
☆#ክፍል_12_ይቀጥላል☆....
.......
.......
............
ከ 100🥰 ቡሃላ .......
☆#ክፍል_12_ይቀጥላል☆....
❤113👍9
✨الصلاة خير من النوم ✨
ሶላተል ፈጅር👉🏻⏰
🌸አትርሱ እ... 😊👇
🌸اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ عِلْمًا نَافِعًا، وَرِزْقًا طَيِّبًا، وَعَمَلًا مُتَقَبَّلًا❤️🩹
🤍ሌላው ደሞ
ሱጁድ የሽክምህ ማራገፍያ ነው የተጫናችሁ ሃሳብ ሁሉ ከላያችሁ ላይ እስኪራገፍ ድረስ ሱጁድ አስረዝሙ🧎♂️
ሱጁድ ማለት በግንባርህ መሬት ላይ ተደፍተህ ለመሬት ታንሾካሹካለህ ድምፅህ ግን ሰማይ ቤት ይሰማል እኔንም በዱአቹ አትርሱኝ 🤲🤍😊
ғяԀı.....✍️
مع السلام✨🤗

❤47🥰3🍓1