ያ ዑ ኽ ቲ ሱሪ እየለበሱ ፀጉርን እያሳዩ አጅነብይ ወንድን እንደ ሴት ጓደኛ ካዩ ኢማን በልብ ነው የሚባል ነገር የለም ያ ዑኽቲ ሴት ምሰይ አለባበስሺን አሳምሪ 🧕
በልብ የሌለ በተግባር አይታይም❕
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍60❤18💯13
🎉21❤8🔥2👍1
የበረሃ እንባ 💔 [ የሊብያ በርሃ ]
ክፍል 6
ፀሐፊ zoya~
......ኦርሳም በተጫነባት የጭነት መኪና ላይ ሆኖ አንገቱን አዙሮ ወደ ኋላ ተመለከተ የኢዘዲን መኪና ወደ ሌላ አቅጣጫ እየራቀች በካርቱም አቧራ ውስጥ ተዋጠች ያ የለመደው የሚያበረታታውና አይዞህ የሚለው ወንድሙ ከጎኑ የለም አሁን ያለው እሱ አራት የማይውቃቸው የሶማሌ ወጣቶችና መሳሪያ የያዙ ሁለት ጋርዶች ናቸው ግን ኦርሳም ደላሎቹን አተኩሮ ያያቸዋል ጥርጣሬው የሱዳን ሰዎች አይመስሉም ።
መኪናዋ ከተማዋን ጥላ ወደ በረሃማው ዳርቻ ስትነጉድ የድንጋይ ከሰል ማምረቻው ድምፅ ከሩቅ መሰማት ጀመረ ጥቁር ጭስ ሰማዩን ውጦታል ኦርሳም እጆቹን አየት አደረጋቸው ገና ሳይጀምረው መዛል ጀምረዋል በውስጡ ግን "እማ... ሀኪያ... ለእናንተ ስል እቆማለሁ" እያለ ራሱን ያበረታታል ።
በክሊኒኩ ውስጥ የነበረው ፀጥታ በሀኪያ ድንገተኛ ሳል ተሰበረ ወይዘሮ ጀሚላ ደንግጠው ተነሱ ሀኪያ አይኖቿን በጭንቅ ከፍታ እናቷን ተመለከተች "እማ... ዛሬ ስንት ቀኑ ነው?" አለች ድምጿ እየተቆራረጠ
ወይዘሮ ጀሚላ ግንባሯን እየሳሙ " ሶስት ሳምንት ሳምንት አለፈው ልጄ... ግን አይዞሽ ጎረቤቶች ሁሉ ዱአ እያደረጉ ነው" አሏት። ወይዘሮ ጀሚላ የልጃቸውን ሁኔታ እያዩ በውስጣቸው የሚቃጠለውን እሳት ደብቀውታል ኦርሳም በሄደ በሳምንቱ የቤቱ ኪራይ ደርሷል የቀለብ ነገር ደግሞ ሌላ ራስ ምታት ሆኗል።
"ኦሪ... የት ነህ ልጄ? በላህ ወይ? ጠጣህ ወይ?" እያሉ በልባቸው ይጮኻሉ ያቺ ደብዳቤ አሁንም ከደረታቸው አልተለየችም።
ኦርሳም ከመኪናው እንደወረደ የደረሰበት ንዳድና የከሰሉ ሽታ ትንፋሽ አሳጣው አንድ ግዙፍ ሱዳናዊ ደላላ ወደ እሱ መጥቶ በትልቅ አካፋ መሬቱን መታ።
"اسمع! العمل يبدأ الآن!
"ስማ ስራው አሁን ይጀምራል!" እያለ ጮኸበት።
ኦርሳም ምንም አልገባውም ዝም ብሎ ሲያየው ደላላው በትከሻው ላይ ያለውን ሸራ ገፍቶ በትልቅ አካፋ ከሰል እንዲጭን ምልክት ሰጠው።
"ይሄን ሁሉ?" አለ ኦርሳም ወደ ተከመረው ጥቁር ተራራ እያየ ለስድስት ወራት የሚቆየው ስቃይ የመጀመሪያው ሰዓት ተጀመረ
አካፋው በእጁ ላይ ሲያርፍ እንደ እሳት ይለበልበዋል ገና አስር አካፋ ሳይጭን እጆቹ አበጡ ። ፀሐይዋ ጭንቅላቱ ላይ የቆመች ትመስላለች በየአምስት ደቂቃው ውሃ እያለ ቢለምንም ዘበኞቹ ግን በንቀት "በኋላ " በሚል ምልክት ያባርሩታል።
ኢዘዲን የደረሰበት እርሻ በጣም ሰፊ ነው እሱ የተመደበው ትላልቅ የውሃ ቱቦዎችን እየተሸከመ መስኖ ማስተካከል ላይ ነው ስራው ከእርሻ ይልቅ የግንባታ ስራ ይመስላል ኢዘዲን ግን አእምሮው ያለው ኦርሳም ጋር ነው
"ኦሪ... ምስኪኑ ወንድሜ ይሄን ስራ እንዴት ይቋቋመው ይሆን?" እያለ ይጨነቃል አጠገቡ ካለ አንድ ሶማሊያዊ ወጣት ጋር በምልክት ለማውራት ሞከረ።
"ካርቱም... ፎን (ስልክ)?" አለው።
ሶማሊያዊው ግን ራሱን በመነቅነቅ
"ኖ ፎን... ኦንሊ ወርክ (ስልክ የለም... ስራ ብቻ)" አለው። ኢዘዲን ተስፋ መቁረጥ ወረረው ስድስት ወር ሙሉ ያለ ድምፅ ያለ መረጃ መኖር መቃብር ውስጥ እንደመኖር ተሰማው።
ምሽቱ ላይ
በከሰል ማምረቻው ውስጥ ኦርሳም ስራውን ጨርሶ መሬት ላይ ተዘረረ ፊቱ፣ ልብሱ፣ ጥፍሮቹ ሁሉ በጥቁር ከሰል ተለውጠዋል። የሚጠጣው ውሃ እንዲሰጡት ሲለምን አንድ የቆሸሸ ባልዲ ውሃ አመጡለት ውሃው ውስጥ ትናንሽ ነፍሳት ይታያሉ ግን ጥሙ የገደለው ኦርሳም አይኑን ጨፍኖ ጠጣው
ለሊቱን የሚያሳልፉት በአንድ አሮጌ ድንኳን ውስጥ ተጨናንቀው ነው ኦርሳም በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ የሀኪያን ሳቅ አሰበ "ሀኩ... የኔ አበባ፣ ለዚህ ነው እኮ ጥዬሽ የወጣሁት በረሃው ቢበላኝም አንቺ መዳን አለብሽ" እያለ በሹክሹክታ ለራሱ ይናገራል።
በድንገት ከመጋዘኑ ውጭ የተኩስ ድምፅ ተሰማ ሁሉም ደንግጠው ሲነሱ ዘበኞቹ በየቋንቋቸው ይጮኻሉ ኦርሳም ልቡ መምታት ጀመረች"ምን ተፈጠረ?" ብሎ በድንጋጤ ሲያይ ደላሎቹ አንዱን ለማምለጥ የሞከረ ወጣት እየጎተቱ ወደ መሃል አመጡት።
"هذا جزاء من يهرب!"
"ይሄ ለማምለጥ የሚሞክር ሰው ቅጣት ነው!"
እያለ ደላላው በጅራፍ ልጁን ይገርፈው ጀመር።
ኦርሳም አይኑን ጨፈነ። እዚህ ቦታ ህግ የለም፣ እዚህ ቦታ ርህራሄ የለም ያለው ስራ፣ ስቃይና ሞት ብቻ ነው ያ ያሰበው ስድስት ወር እንደ ስድስት ሺህ ዘመን ረዘመበት።
ያ የታፈነ ድቅድቅ ጨለማ በጅራፍ ድምፅና በሚያሳቅቅ ጩኸት ተሞላ ኦርሳም አይኑን ጨፍኖ የልጁን ስቃይ ቢሰማውም በውስጡ የሚሰማው ህመም ግን ከጅራፉ በላይ ነበር
"ሰው... እንዴት ለሰው እንዲህ ይጨክናል?" የሚለው ጥያቄ ጭንቅላቱን ሊያፈነዳው ደረሰ ስድስት ወር እንዲህ ባለ ጀሃነም ውስጥ መቆየት ማለት መሞት መሆኑ ገባው።
ጎህ ሲቀድ ዘበኞቹ በዱላ ድንኳኑን እየመቱ ቀሰቀሷቸው። ኦርሳም ትላንት ከሰል ሲያካፋ በወጡት ፊኛዎች ላይ የከሰሉ አቧራ ገብቶ እጆቹ እንዲያብጡ አድርጓቸዋል ጣቶቹን ማጠፍ አቅቶታል።
የወይዘሮ ጀሚላ ቤት አሁን ጭር ብሏል ጎረቤቶች መጥተው "አይዞሽ" ማለቱን ሰልችተውታል ዛሬ ግን የቤት አከራያቸው አቶ በሽር ደጃፍ ላይ ቆመዋል
"ወይዘሮ ጀሚላ... አውቃለሁ ችግር ላይ ነሽ ግን እኔም የምተዳደረው በዚህ ነው። የሁለት ወር ኪራይ ካልተከፈለ ቤቱን መልቀቅ አለባችሁ" አሏቸው ፊታቸውን አዙረው።
ወይዘሮ ጀሚላ ልባቸው በሃዘን ተሰበረ " በሽር ... ልጄ ለስራ ሄዶ እኮ ነው... እስኪመለስ ድረስ" ብለው ቢማጸኑም አከራዩ ግን "ልጅሽ የት እንደሄደ ሰምተናል በረሃ የገባ ሰው ደግሞ የሚመለስ ይመስልሻል ?" ብለው በቁስላቸው ላይ እንጨት ሰደዱባቸው። ወይዘሮ ጀሚላ ደጃፉ ላይ ቁጭ ብለው ምርር ብለው አለቀሱ ሀኪያ ግን በክሊኒኩ ውስጥ ሆና ይሄን ሁሉ አታውቅም የምትጠብቀው ወንድሟን ብቻ ነው።
ኦርሳም ዛሬም እንደ ትላንቱ አካፋውን አንስቷል ፀሐይዋ ልክ 12 ሰዓት ሲሆን ንዳዷን መርጨት ጀመረች በአጠገቡ ያለው ሶማሌያዊ ወጣት በድካም መንቀጥቀጥ ጀምሯል ኦርሳም እጁን እየመመመውም ቢሆን ወደ ልጁ ጠጋ ብሎ አይዞህ በሚል ምልክት ያገዘው ጀመር
በመሃል ግን አንድ ያላሰበው ነገር ተከሰተ ትላንት ማምለጥ የሞከረውን ልጅ የገረፈው ያ ግዙፍ ሱዳናዊ ወደ ኦርሳም ቀረበ ኦርሳም ለጥቃት የተዘጋጀ ይመስል ደረቱን ነፋ ሱዳናዊው ግን ዛሬ ቁጣ አልታየበትም።
"انت اثيوبي؟"
(አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ? አለው
ኦርሳም አማርኛ እንጂ አረብኛ እንደማይችል ቢታወቅም "ኢትዮጵያ" ብሎ መለሰ።"
ሱዳናዊው ዝቅ ባለ ድምፅ "እኔም እናቴ የናንተ ዘር ናት ግን እዚህ ቦታ ላይ ማንም አያውቅም ሳይህ ታታሪ ነህ ከሁሉም ትለያለህ " አለውእየተንተባተበ በአማርኛ ኦርሳም በድንጋጤ አየው ። ሱዳናዊው ከኪሱ አንድ ትንሽ ቁራጭ ዳቦ አውጥቶ በከሰል ወደ ተለወጠው የኦርሳም እጅ አቀበለውና "በፍጥነት ብላው" ብሎት ዞር አለ።
ኦርሳም ያቺን ዳቦ ለሁለት ከፍሎ ግማሹን ለሶማሌያዊው ጓደኛው ሰጠው። ያቺ ዳቦ ለኦርሳም የዛሬው ብርታት ሆነችው።
.......
.......
............
ከ 100🥰 ቡሃላ .......
☆#ክፍል_6_ይቀጥላል☆....

❤113👍8😢6
﴿٨٨﴾ يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ
በዚያ ቀን ገንዘብም ልጆችም አይጠቅሙም
﴿٨٩﴾ إِلَّا مَنۡ أَتَى ٱللَّهَ بِقَلۡبٖ سَلِيمٖ
ከአላህ ዘንድ ንጹሕ ልብ ይዞ የመጣ ሰው ግን እንጂ
﴿٩٠﴾ وَأُزۡلِفَتِ ٱلۡجَنَّةُ لِلۡمُتَّقِينَ
ጀነትም አላህን ለሚፈሩት ቀረበች
﴿٩١﴾ وَبُرِّزَتِ ٱلۡجَحِيمُ لِلۡغَاوِينَ
ገሀነምም ለተሳሳቱት በግልጽ ተገለጠች
﴿٩٢﴾ وَقِيلَ لَهُمۡ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡ تَعۡبُدُونَ
እነሱም የምትገዙት የነበራችሁት የት አሉ? ተብለው ይጠየቃሉ
﴿٩٣﴾ مِن دُونِ ٱللَّهِ هَلۡ يَنصُرُونَكُمۡ أَوۡ يَنتَصِرُونَ
ከአላህ ሌላ የምትገዙት እነሱ ሊረዷችሁ ይችላሉን? ወይስ ራሳቸውን ሊረዱ ይችላሉን?

🥰8❤6💯4
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋
✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 295❵ #hadith295 ". አብደላህ ኢብኑ በሸር አል- አስላሚ (ረ.ዐ) እንዳሰተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) "ከሰዎች ሁሉ በላጩ ዕድሜው የረዘመና ሰራውም መልካም የሆነለት ነው፡፡" ብለዋል፡፡ (ቲርሚዚይ ዘግቦታል ሐሰን ነውም ብሎታል) 📋ያለፈው ክፍል👇📋 https://t.me/Hafu_posts/18438 🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨
❴Part 296❵ #hadith296
"ዓነሰ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አሰተላልፈዋል፦
"አጎቴ ዓነስ ኢብኑ ነድር (ረ.ዐ) በበድር ፋልሚያ አልሳተፍም ነበር፡፡ "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሙሽሪኮች ከተፋለሙበት የመጀመሪያ ወጊያ ላይ አልተሳትፍኩም፡፡ አላህ ከሙሽሪኮች ጋር ለመፋለም ካበቃኝ የምሠራውን
ለሰዎች ያሳያል፡፡" አሉ። የኡሑድ ዕለት ሙስሊሞቹ ወደኋላ አፈገፈጉ። "አላህ ሆይ! እነኝህ ባልደረቦቼ ወደኋላ በማፈግፈግ የፈፀሙት ድርጊት ላንተ እተዋለሁ። እነዚያኞች
(ሙሽሪኮችን ማለታቸው ነው) ነቢዩን
(ሰ.ዐ.ወ) በመውጋት ከፈጸሙት ድርጊት እጄን ንፁህ አደርጋለሁ" አሉ። ከዚያም ወደ ፍልሚያው መስክ ሲያመሩ ሰዕድ ኢብኑ ሙዓዝን አገኟቸው። "ሰዕድ ኢብኑ ሙዓዝ ሆይ! ጀነትንለመጎናፀፍ እመኛለሁ። በከዕባ ጌታ ይሁንብኝ! ከኡሁድ (ተራራ) ወዲህ ማራኪ ሽታዋ እያወደኝ ነው" አሉ። "እርሱ (አነስ) የፈፀመውን (የጀግንነት ተግባር) መፈፀም አልቻልኩም ነበር" አሉ ሰዕድ። ከሰማንያ ሦስት እስከ ሰማንያ ዘጠኝ የሚደርሱ በጎራዴ የተመቱ በጦር ወይም በቀስት ፍላም የተወጉ ቦታዎች (ሰውነታቸው ላይ) ተመልክተናል። በአጋሪዎች ተገድለውና አካላቸው ተቆራርጠው ነበር ያገኘናቸው። ከእህታቸው ውጭ ያወቃቸው አልነበረም። በጣቶቻቸው አሻራዎች ነበር የለየቻቸው። ዓነስም አክለው እንዲህ ብለዋል። "ተከታዩ የቁርኣን አንቀፅ የወረደው ለእርሳቸውና መሰሎቻቸው እንደሆነ እገምታለሁ፦
"ከአማኞቹ በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አልሉ፡፡ ከነርሱም ስለቱን የፈጸመ (ለሃይማኖቱ የተገደለ) አልለ፤ ከነርሱም ገና የሚጠባበቅ አልለ፡፡ (የገቡበትን ቃል) መለወጥንም አልለወጡም፡፡"
(አል- አህዛብ 23)
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/18451
🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫

🥰12❤8👍3🔥2
ስልክህን እናትህም፣ አባትህም፣ እህትህም፣ ወንድምህም፣ ሚስትህም፣ ልጅህም፣ ጓደኛህም… ቢያየው ችግር ከሌለው… ጥሩ ላይ ነህ።🙃
©
©
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍79🤯6❤2
ما كُتِبَ لك سيأتيك ولو كنتَ تحت جبل، وما لم يُكْتَ لك لن تناله ولو كان بين يديك.»
ለአንተ የተጻፈልህ ከተራራ ስር ቢሆን እንኳ
ያገኝሃል፤ ያልተጻፈልህን በእጆችህ
መዳፍ ውስጥ ቢሆን እንኳ አታገኘውም🙌
ለአንተ የተጻፈልህ ከተራራ ስር ቢሆን እንኳ
ያገኝሃል፤ ያልተጻፈልህን በእጆችህ
መዳፍ ውስጥ ቢሆን እንኳ አታገኘውም🙌
👌33❤6❤🔥2👏2👍1
ነገ ስኬት ብቻ አይደለም
ሞትም አለ!!
ነገር ግን አላህዬ ለእናቴ ስትል
ስኬቴን አስቀድምልኝ🥺🤲
ሞትም አለ!!
ነገር ግን አላህዬ ለእናቴ ስትል
ስኬቴን አስቀድምልኝ🥺🤲
❤86😢7💔5🥰3
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁32😎6❤4
ለገዛ እስትንፋሴ እድሳት ለስክነቴ ሙላት
የዱንያ ጀነቴ
በልቤ አንተን ማውሳት።
የኔ አላህ🥀
የዱንያ ጀነቴ
በልቤ አንተን ማውሳት።
የኔ አላህ🥀
🍓53❤12👏3
የበርሃው እንባ💔 {የሊብያ ሕይወት }
ክፍል 7
ፀሐፊ zoya~
ምሽት ላይ ኦርሳም ድንኳኑ ውስጥ ተኝቶ ሳለ ያ "እናቴ ኢትዮጵያዊት ናት" ያለው ርህሩህ ዘበኛ በድጋሚ መጣ ስሙ መሀመድ ይባላል መሀመድ አጠገቡ ተቀምጦ ድምፁን ዝቅ አድርጎ እንዲህ አለው
"ነገ ከዚህ ትለቃላችሁ... ወደ ሌላ ቦታ ትወሰዳላችሁ።"
ኦርሳም ደንግጦ ተነሳ "ወደ ሊቢያ?" ብሎ ጠየቀ።
መሀመድ ግን ራሱን በመነቅነቅ "አይደለም... እዚህ ካርቱም ውስጥ ሌላ ትልቅ የግንባታ ሳይት አለ።l እዛ ስራው ከዚህ ይከብዳል። እኔ ግን ላግዝህ እሞክራለሁ ግን ብዙም ተስፋ አታድርግ እዚሁ ልቆይ እችላለሁ " አለው።
ኦርሳም በፍርሃት ተዋጠ "አንድ ጓደኛ አለኝ እሱን እዛ አገኘው ይሁን ? እሱን ሳላገኘው የትም አልሄድም" አለ በ መሀመድ ባይ የልጁ ጭንቀት ገብቶታል። "ተወው... በረሃ ላይ ጓዴ አይባልም " ብሎት ሄደ።
ወይዘሮ ጀሚላ ክሊኒኩ ውስጥ ካለው የሀኪያ አልጋ አጠገብ ተቀምጠዋል። የሀኪያ ጤንነት ትንሽ መሻሻል ቢያሳይም የአእምሮዋ እረፍት ግን አልተመለሰም።
"እማ... ዛሬ ኦሪን በህልሜ አየሁት" አለች ሀኪያ አይኖቿን ጨፍና "በጣም ጥቁር በሆነ ቦታ ውስጥ ሆኖ ውሃ ጠማኝ እያለ ነበር እማ... የሆነ ነገር ሆኗል አይደል?"
ወይዘሮ ጀሚላ የሀኪያን ፊት እየደባበሱ "የለም ልጄ... በረሃው ሞቃት ስለሆነ ይሆናል አላህ ይጠብቀው" አሏት ነገር ግን በውስጣቸው ያለው ስጋት እያደገ መጣ የቤት ኪራዩ መከፈል ያለበት ቀን ዛሬ ነው አቶ በሽር ደግሞ የዛሬን ቀን ቀጠሮ ሰጥተው ነበር ቤታቸው ቢዘገይም ሀኪያን ይዘው የት እንደሚሄዱ አያውቁም
በማግስቱ ጠዋት ኦርሳም እና ጓደኞቹ ወደ መኪናው እንዲጫኑ ተደረገ ኦርሳም መሀመድን በዓይኑ ፈለገው ነገር ግን መሀመድ በዛ የለም። መኪናዋ ተንቀሳቅሳ ጥቂት እንደሄደች ግን አንድ ሌላ የጭነት መኪና ፊት ለፊታቸው ቆመች
ከመኪናው ላይ ወጣቶች እንዲወርዱ ተደረገ። ኦርሳም በመስኮት በኩል ትኩር ብሎ ሲያይ የልቡ ትርታ ቆመ "ኢዘዲን" ብሎ ጮኸ
ኢዘዲንም በዛኛው መኪና ላይ ሆኖ ኦርሳምን አየው "ኦሪ"
ሁለቱም መኪናዎች ጎን ለጎን ቆሙ ደላሎቹ ወጣቶቹን እያቀያየሩ መመደብ ጀመሩ ኢዘዲን ወደ ኦርሳም መኪና ተወረወረ ሁለቱም እርስ በእርስ ተቃቀፉ የባርነት ቀንበሩ ቢከብድም አብሮ መሆን ግን ለሁለቱም ትልቅ ብርታት ነበር።
"ብሮ... እንዴት ነህ? ተጎድተሃል እኮ" አለ ኢዘዲን የኦርሳምን ጥቁር የከሰል እጆች እያየ
" ኢዙ... አሁን አንተ መጣህ አሁን አልፈራም" አለ ኦርሳም በእንባ ታጅቦ።
መኪናዋ አሁን ሁለቱንም ይዛ ወደ አዲሱና ይበልጥ አስፈሪ ወደሆነው የግንባታ ቦታ አመራች ስድስት ወሩ ገና አላበቃም ፈተናው ግን እጥፍ ሆኖ ቀጠለ።
መኪናዋ አቧራዋን እያቦነነች "ኦምዱርማን" ተብሎ በሚጠራው የካርቱም ዳርቻ ወደሚገኝ አንድ ግዙፍ የግንባታ ሳይት አስገባቻቸው ኦርሳም እና ኢዘዲን ተቃቅፈው ከመኪናው ሲወርዱ የደረሰባቸው ሽታ የቆሻሻ መጣያ እንጂ የሰው መኖሪያ አይመስልም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያንና ሶማሌያውያን በፀሐይ ተቃጥለው አጥንታቸው ወጥቶ አይኖቻቸው በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሲሰሩ አዩ
"ኢዙ... ይሄ ላይፍ አይደለም ይሄ ጀሃነም ነው" አለ ኦርሳም በደረቀ አንደበቱ
ኢዘዲን የኦርሳምን ትከሻ አጥብቆ ያዘው "ኦሪ... አሁን ማልቀስ መፍትሄ አይደለም። እዚህ መተርፍ ካልቻልን አስከሬናችን እንኳን አገር አይገባም። አይንህን ክፈት ጆሮህን ስጥ " አለው ሊያበረታታው እየሞከረ
አንድ ጥቁር መነጽር ያደረገ ደላላ ወደ እነሱ ቀረበ በእጁ የያዘውን የላስቲክ ጅራፍ መሬት ላይ እያጮኸ በአረብኛ ጮኸ
"يا كلاب! العمل 14 ساعة في اليوم. ما في نوم، ما في شكوى!"
"እናንተ ውሾች በቀን 14 ሰዓት ነው የምትሰሩት። እንቅልፍ የለም ቅሬታ የለም"
አንዱ በደረቁ ተረጎመላቸው "ለስድስት ወር እዚህ ግቢ ውስጥ ነው የምታድሩት አንድ እርምጃ ወደ ውጭ የወጣ ሰው ጥይት ነው የሚጠብቀው የምትሰሩት ገንዘብ በቀጥታ ለእኛ ነው የሚገባው ካለቀሳችሁ ትገረፋላችሁ ከታመማችሁ ትጣላላችሁ።"
ኦርሳም ትልቅ ሲሚንቶ ተሸክሞ ወደ አራተኛ ፎቅ እንዲወጣ ተገደደ ጫማው ተቀዶ ጣቶቹ መሬት ይነካሉ በየደረጃው ሲወጣ ጉልበቱ ይንቀጠቀጣል ጥሙ ጉሮሮውን ዘግቶታል መተንፈስ ሲያቅተው ደረጃው ላይ ለጥቂት ሰከንድ አረፍ ለማለት ሲሞክር ከጀርባው የጅራፍ ድምፅ ተሰማ።
"قوم! يا حبشي!"
"ተነስ አንተ ሀበሻ"
ጅራፉ የኦርሳምን ጀርባ ሰንጥቆት አለፈኦርሳም በህመም ጮኸ ደሙ ከጥቁር ከሰል ጋር ተቀላቅሎ በሸሚዙ ላይ ፈሰሰ ኢዘዲን ከሩቅ ሆኖ ይሄን ሲያይ ሊሮጥ ሲል ሌላ ዘበኛ በመሳሪያ ሰደፍ ደረቱን መታው
"ኦሪ!እንዳትወድቅ ተነሳ" ብሎ ጮኸ ኢዘዲን ደረቱን እየሸ።
ወይዘሮ ጀሚላ ዛሬ ቤታቸውን ለቀዋል አቶ በሽር የሁለት ወር ኪራይ በማጣታቸው እቃቸውን አውጥተው ደጃፍ ላይ ጥለውታል ሀኪያ ገና ከክሊኒክ አልወጣችም ወይዘሮ ጀሚላ ግን የት እንደሚወስዷት አያውቁም በአንድ አሮጌ ፌስታል የኦርሳምን ልብሶችና ደብዳቤውን ይዘው የአንድ መስጊድ ጥግ ተጠግተዋል
"አላህ ሆይ... ልጄን ከዚህ መከራ አውጣ እኔን ብትገለኝም እሱን ለሀኪያ አትርፍልኝ" እያሉ የልጃቸውን ደብዳቤ በእንባቸው አራሱት ደብዳቤው ላይ ያለው "በቅርቡ እመጣለሁ" የሚለው ቃል አሁን እንደ ጩቤ ልባቸውን ወጋቸው
ምሽቱን የሚሰጣቸው ምግብ አንድ ቂጣ እና ትንሽ የቆሸሸ ውሃ ብቻ ነው ኦርሳም ጀርባው እየለበለበው መሬት ላይ ተኝቷል ኢዘዲን የሸሚዙን ጨርቅ ቀዶ በውሃ አርሶ የኦርሳምን ቁስል ያብስለታል
"ኦሪ... ሶሪ ብሮ ለኔ ብለህ ነው እዚህ ኬዝ ውስጥ የገባኸው" አለ ኢዘዲን እያዘነ
"አይ ኢዙ... እኔ የመጣሁት ለሀኪያ ነው እሷ ከዳነች እኔ ብሞትም አይቆጨኝም አለ ኦርሳም በደከመ ድምፅ "ግን ኢዙ... ስድስት ወር እዚህ መቆየት አንችልም በየቀኑ ሰው እየሞተ ነው። ዛሬ አንዱን ሶማሌያዊ ወስደው ቀበሩት እኛም ተራችን ሳይደርስ የሆነ ነገር ማድረግ አለብን።"
ኢዘዲን ወደ ዙሪያው ተመለከተ።ግድግዳው ከፍ ያለ ነው ጋርዶቹ የታጠቁ ናቸው
በድንገት ያ መሀመድ የተባለው ዘበኛ በጥላ ውስጥ ሆኖ ወደ እነሱ ጠጋ አለ በእጁ አንድ ትንሽ ስልክ ይዟል "ሁለት ደቂቃ ብቻ... ለቤተሰብ ደውሉ" አላቸው በዝቅተኛ ድምፅ
የኦርሳም ልብ በሃይል መምታት ጀመረ ስልኩን ተቀብሎ የእናቱን ቁጥር ነካ።

❤111😢21💔2❤🔥1
ሰላም .... የጌታዋን ትእዛዝ ተከትላ
ራሷን በሒጃብ በሸፈነች እንስት ላይ!!🧕
ራሷን በሒጃብ በሸፈነች እንስት ላይ!!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🥰98❤19🍓9
🌿 ተወኩል ማለት ይሄ አይደል? 🤲
😔 መፍትሄው ምን እንደሆነ አታውቅም... ቀጣይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አትችልም...
ምንም ዓይነት መውጫ መንገድ እየታየህ አይደለም...
🤍 ግን...
"ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፤ ይመራኛል።"
ይህንን እምነት በየትኛውም አጣብቂኝ ውስጥ ብትሆን እንኳን አትልቀቀው።
✨ "አይቻልም" የሚባል ነገር በአላህ ዘንድ የለም። 🤲
🌊 እርሱ ከነቢዩ ሙሳ (ዐለይሂስ-ሰላም) ጋር እንደነበረው፣ ከእኛም ጋር ነው።
🌹 ኢንሻአላህ... ይመራናል፣ ያበረታናል፣ መንገድም ይከፍትልናል። ❤️

❤43💯8👍4🍓2❤🔥1