𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭
14.8K subscribers
1.96K photos
864 videos
6 files
602 links
亗 ꧁﷽꧂ 亗
🤍𝑤𝑒𝑙𝑐𝑜𝑚𝑒 𝑡𝑜 ᴏᴜʀ 𝑐ℎ𝑎𝑛𝑛𝑒𝑙ᥫᩣ
Channel Objective🎊🎊🎊🎊🎊
➻Islamic teachings💛
➻Current information🤗
➻Hadiths and Qurans 🤩


CROSS🔄 @Waver_boy1
Download Telegram
ማስቲካ እና መዘዙ

እስኪ ዛሬ ትንሽ ስለጤና እናውራ


ማስቲካ የጨጓራ በሽተኛ እንደሚያደርግ ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ?

ምን መሰላችሁ ጨጓራ ስራውን የሚጀምረው ከአእምሯችን መልክት ሲላክለት ነው። ለምሳሌ፦ ወፍጮ ሚፈጭ ነገር እሱ ጋር ከመድረሱ በፊት  የሚያስፈጭ ሰው መምጣቱን ሲያይ የወፍጮ ተቆጣጣሪው ያስነሳዋል።

ጨጓራም ልክ እንደዛው ነው።
አእምሮ የወፍጮ ተቆጣጣሪ ብንል
ጨጓራ ደግሞ ወፍጮ ነው

እናላችሁ እንዴት ነው ታድያ የጨጓራ በሽተኛ የሚያደርገው? ካላችሁ

አጅሬ አእምሮ አፍ ውስጥ ጥርስ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል።ልክ ማኘክ ሲጀምር ለጨጓራ ወፍጮውን አንሳው ይለዋል። ጨጓራም ስራውን ይጀምራል።  ከዛም እንደምታውቁት ማስቲካ አይዋጥምና ይቆይበታል። ትዕዛዙን በመተግበር ጨጓራ በባዶ እርስ በራሱ እፋፋቃል እና ጨጓራም ይላጣል ወይም ይቆስላል። ሰውየውም የጨጓራ በሽተኛ ይሆናል። ከዛም ምግብ ስንበላ ለመፍጨት ይቸገራል።



በነገራችን ላይ ማስቲካ ምግብ ጨጓራ ላይ ሲከብደን እንዲፈጭ የሚያደርገው ለዚህ ነው እና ጥቅምም ጉዳትም አለው።

ከዶክተር የምልበት ቀን ይምጣ
😁278👏8👍6🍓1
አልሆነልኝም ብለህ አትዘን ምንም ነገር የሚሆነዉ ፈጣሪ ሲፈቅድ ብቻ ነዉ።😇

መልካም ቀን🌤
34👍7
ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፡፡ «ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ (በርኅራኄ) እንዳሳደጉኝ እዘንልላቸውም» በል፡፡
الإسراء 17:24💖
🥰276🤗6
የሴቶች የጋብቻ መስፈርት ይሄ ቢሆን ኖሮ_19-08-23_07-18-09-925
AudioLab
ለፈገግታ የሴቶች የጋብቻ መስፈርት ይሄን ቢሆን ኖሮ👇
ድምፁን ፈገግ በሉበት

1.ቁርአን ያልሀፈዘ ከሀዲስ ደግሞ ቡኻሪ ወይም ሙስሊም ያልሀፈዘ እኔ አላገባውም። ብለው በጭራሽ ውሳኔ በአንድነት አድማ ቢያደርጉ ኖሮ፦


ሙዚቃ የሚያዳምጥበት ጆሮው ቁርአን እንጂ ሌላን አይሰማም ነበር።


2.በየ ጥጋጥጉና በየ አጥሩ ሴትን ለመጀንጀን በሶሻል ሚድያ የከተመው ወጣት ሁሉ እገሊትን እንዳታመልጠው በየ አጥሩና በየ ጥጋ ጥጉ ሁሉ ቁርአንና የቁርአን ድምፅ ብቻ ይሞላ ነበር።

3.ይገርማችኋል ዋይፋይ ባለበት አካባቢ እራሱ የቃሪእ ድምፅ ብቻ ነበር የሚያወርደው።

ምክንያቱም ጊዜው ካባከነው ምን እንደሚገጥመው አስባችሁታል?


4.መርከዞችና መድረሳዎችማ ተከፍተው ትንሽ ቀን ሳይሆን ሰአት ላረፈደ ክፍት ቦታ አያገኝም ነበር።


ሴት ስትስተካከል ኡማው በሙሉ ይስተካከል።


👓እስቲ ሴቶች በዚህ ላይ ከዛሬ ጀምሮ አድማ አድርጉና እንዴት ሷሊህ ዓሊም እንደምንሆን ተመልከቱን።በአንድ አመት ውስጥ ብቻ ብዙ ሷሊህና ዓሊም ወንድ እንሆናለን።

ወስኑና እኛም እናሳያችሁ።

እኛ ወንዶች ስንባል እኮ............

ብለዋል ሴቶች ምን ትላላችሁ?


©ⓄⓅⓎ
27💯5🔥2👍1
የሸሸሁት ካንተ ቢሆንም
መሸሸጊያዬ ግን አንተው ነህ

ያ አላህ ❤️‍🩹
🔥25😢12💔1210
በቅዱስ ቁርአን ረጅሙ ምእራፍ ማን ነው ስንት አንቀጾች አሉት?
10
💡 መልስ


ሱረቱል በቀራ
286 አንቀፆች አሉት
👍83
የ ቡኻሪእ ትክክለኛ ስማቸው ማን በመባል ይታወቃል?
4
መልስ

ሙሀመድ ኢብኑ ዒስማኢል
6👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❤️ የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ ❤️

🌙 ሰባኹል ኸይር / ሰባኹል ኑር



📖🎧 #ቁርኣን  || PART ❶❼❽

⭐️ 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭 || SHARE 😊
🥰31👍1
Forwarded from Channel Help
🤲በዛሬው እለት ፈተና🎓 እና ከባድ የዱንያ ሐጃ ላለባችሁ የምታደርጉት ዱዓ በተጨማሪ ለቀናችሁ ፍካት የሚሆን አጭርና ማራኪ ቁርዓን ተጋበዙልኝ🎙

🚨ወላሂ ሐቂቃ ማስታወቂያ ነው ተቀላቀሉ🕌
2
በእስልምና ሚስጥር ሆነው መያዝ ያለባቸው 1⃣0⃣ ነገሮች
=======================
1⃣ የራስህ ወንጀሎች፡ አላህ 👆 በምህረቱ የሸፈነልህንና የደበቀልህን ወንጀል አደባባይ አታውጣው።

2⃣ የሌሎች ሰዎች ነውርና ወንጀል፡ የሰውን ነውር የሸፈነ፣ አላህ የቂያማ ቀን ነውሩን ይሸፍንለታል። የሌሎችን ሚስጥር ጠባቂ ሁን።

3⃣ የቤተሰብ ውስጥ ጉዳዮች፡ በቤተሰብ መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችና ውስጣዊ ጉዳዮች ከቤት ደጃፍ ሊወጡ አይገባም።

4⃣ የትዳር ውስጥ ሚስጥሮች፡ በባልና ሚስት መካከል ያሉ ማንኛቸውም የትዳር ጉዳዮች እጅግ የተከበሩ እና ለሶስተኛ ወገን ሊነገሩ የማይገባቸው ናቸው።

5⃣ በድብቅ የምትሰራቸው ዒባዳዎች፡ ሪያእ (ይዩልኝ/ይስሙልኝ) አጅርህን እንዳያበላሸው፣ በአንተና በጌታህ መካከል ያሉ አምልኮዎችን ሚስጥር አድርግ።

6⃣ የምታገኘው ገቢ፡ የገቢህን መጠንና የገንዘብህን ልክ ሚስጥር ማድረግ ከክፉ ዓይንና ከምቀኝነት (ሐሰድ) ይጠብቅሃል።

7⃣ ቀጣይ የህይወት እርምጃህ፡ ነብዩ ⏩️ «ጉዳዮቻችሁን በሚስጥር በመያዝ አሳኩ» እንዳሉት፣ የተለየ እቅድህን ከማሳካትህ በፊት አታውራ።

8⃣ ሰዎች ያመኑህ ሚስጥር (አማና)፡ ሰዎች አምነውህ የነገሩህ ማንኛውም ሚስጥር "አደራ" ነው፤ አማናህን ጠብቅ፣ የሰውን ቃል አታባክን።

9⃣ ህልሞችህ እና ስኬቶችህ፡ ትልልቅ ምኞቶችህን እና ያገኘሃቸውን ድሎች ለሁሉም አታውራ (ሰው ሁሉ በስኬትህ ይደሰታል ማለት አይደለምና)።

1⃣0⃣ የህይወት ፈተናዎችህ እና መከራዎችህ፡ ብሶትህንና ጭንቀትህን ለሰው አብዝተህ ከማማረር ይልቅ መፍትሄ ሰጪ ለሆነው ለአዛኙ ጌታህ ለአላህ ብቻ አቅርብ።

Copy
💯132👍2🫡1