🍁❝
“ተስፋው በአንተ ላይ ያለውን ሰው አታሳዝን”
علي بن أبي طالب❝“ተስፋው በአንተ ላይ ያለውን ሰው አታሳዝን”
🫡10👍6🆒1
سورة الكهف .pdf
626.5 KB
ወደ አላህ ከጠራና መልካምን ከሰራ
<<እኔ ከሙስሊሞች ነኝ>>
ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማነው?
አል–ፉሲለት ምዕ[41:33]
﴿ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيماً ﴾
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
عن أبي سَعيدٍ الخُدريِّ عنِ النبيِّ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم أنَّه قال: (( مَن قَرَأَ سورةَ الكَهفِ يومَ الجُمُعةِ أضاءَ له من النورِ ما بَينَ الجُمُعتينِ ))
☞︎︎︎በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሃል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።»

❤11👍5👏5
May Allah's peace and blessings be upon you all
❤17🍓2
ወንጀል ላይ ያሉ ሰዎችን ስትከታተል ሁለት ፈተና ሊገጥምህ ነው....
•ያሉበትን ሁኔታ መመኘት (ሳታስበው)
•እነሱን መናቅ እና በእነሱ #መሳለቅ (ኻቲማ በአሏህ እጅ ብቻ ከመሆኑ ጋር)
ወንጀል ላይ ያሉ ሰዎችን ባለመከታተል እና ስለነሱ ባለማውራት ራስህን ጠብቅ!

👍31❤7🙏3
አንዳንድ ጊዜ አላህ ዋጋህ ከማይከበርበት ክፍል remove ያደርግሃል... so he can place u በምትከበርበት ክፍል ዉስጥ ያስቀምጥሃል።
👍34💯8❤5
ሼሁ በዳንስ ቤት የተሰኘው መፅሃፍ ታሪክ ዛሬ ምሽት 3:30 ይጀመራል 🥳 እስከዚያው #መግቢያውን ተጋበዙልኝ👇🏽🤩
ማስታወሻነቷ፡
ልቡ ወደ ዲኑ እያደላ
ነፍሱና ስሜቱ ወደ ወንጀልና ወደ መጥፎ ስራ
ለምትገፋፋው ወጣት ሁሉ ትሁንልኝ፡፡
«ደራሲው»
«ሼሁ በዳንስ ቤት» የሚለውን መጽሃፍ አንብቤዋለሁ፡፡ ይህ መጽሃፍ በሃገራችን የእስልምና ኃይማኖትን አስመልክቶ ከተጻፉትም ሆነ ከተተረጎሙት በይዘትም ሆነ በዓይነቱ የተለየ ነው፡፡
ይህ መጽሀፍ ወደ መስጊድ ለሚመጣ ሰው ብቻ ዳዕዋ ማድረግ በቂ እንዳልሆነ እንዲያውም ወጣቱ ትውልድ የት
ይውላል ብሎ ጠይቆ በድፍረት
ድረስ በመሄድ ዳዕዋ ማድረግ
በተለያየ መንገድ ሊገኝበት በሚችለው ቦታ ተገቢ መሆኑን ያመለከተ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በተለይ ወጣቱ በዳንስ ቤት፣ በመጠጥ ቤትና በመቃሚያ ቤቶች ጊዜውን በከንቱ እያሳለፈ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ይህን የሙስሊም ህብረተሰብ አካል የሆነውን ወጣት እንዴት ከዚህ ተግባሩ ሊመለስ ይችላል? ማነው እዚህ ቦታ ደርሶ ካለበት አሳዛኝ ሁኔታ ይመልሰዋል? ለሚለው ጥያቄ በሃሚድ ጣሂር የተተረጎመው መጽሃፍ ጥሩ ጥቅም የሚስጥ ይመስለኛል፡፡
«ሼሁ በዳንስ ቤት» በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሃፍ ለዳዕዋ ለሰዎች በተለይ ለወጣቱ ለሁሉም ሙስሊም ህብረተሰብ ክፍል በጥቅሉ ጥሩ ጠቀሜታ ያለው ይመስለኛል፡፡
አላህ ሱ.ወ ከክፉ ስራና ከመጥፎ ድርጊት እንዲጠብቀን እንማፀናለን፡፡ ውድ የዚህ መጽሃፍ አንባቢያን፡-
ይህ መጽሃፍ ሽህ ዓሊ ጠንጣዊ «የህይወት ታሪኬ» በሚል መጽሐፋቸው ውስጥ ከጻፉት ተወስዶ የተተረጎመ ሲሆን መጽሀፉ ብዙ የተለያዩ ርዕሶችን ያካተተ ቢሆንም ከነዚህ መካከል «ሼሁ በዳንስ ቤት» የሚለውን ርዕስ መርጬ ለአንባቢያን ለማቅረብ ሞክሬያለሁ፡፡
ሼህ ዓሊ ጠንጣዊ በመግቢያቸው ላይ እንደሚጠቅሱት ይህን መጣጥፍ የጻፉት በ1946 እ.ኤ.አ ነው፡፡ በወቅቱ የሚታተሙ ጋዜጦችና መጽሄቶች የሳቸውን ጽሁፍ በሰፊው ያሰራጩት ሲሆን በአንባቢያን ዘንድም ተወዳጅነትን ያተረፉ ነበሩ፡፡
ሼህ ዓሊ ጠንጣዊ ብዙ የዲን መጽሀፍትን የጻፉ ሲሆኑ እንደ አብነት
የሚጠቀስላቸው እና ከአረብኛ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው ኢማን በሚል ርዕስ የፃፉት መጽሐፋቸው ነው፡፡
ሼህ ዓሊ ጠንጣዊ ሶሪያዊ ሲሆኑ በሶሪያ ዩኒቨርሲቲ የህግና የሸሪዓ መምህር ብሎም የከፍተኛ ፍርድ ቤት የዳኞች ኃላፊ በመሆን እንዳገለገሉ ስለእሳቸው የተጻፉ መጽሃፎች ያስረዳሉ፡
በእኒህ ታላቅ ሰው ከተፈጸመው መጽሃፍ «ሼሁ በዳንስ ቤት» የሚለውን ርዕስ መርጬ በመተርጎም ለኢትዮጵያ ሙስሊም አንባቢ ሳቀርብ በተለይ ለወጣት አንባቢያን ብዙ ፋይዳዎች ሊያስገኝ ይችላል ከሚል ሃሳብ በመንደርደር ነው፡፡ በእርግጥ ከዚህ መጽሃፍ ውስጥ የተጠቀሱት ቀላል የማይባሉ ነገሮች ኢትዮጵያ የተለያዩ የሃይማኖት ተከታይ አገር እንደ መሆኗ መጠን ከባህልና ወጉ ጋር ላይጣጣሙ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን መጽሀፉ የያዘው መልዕክት ለዲን አፍቃሪ ወጣቶች ብዙ እውቀት ሊያስጨብጣቸው ይችላል፡፡ በተጨማሪም ራሳቸውን ዘወር ብለው እንዲያዩና ውሏቸውንና ስራቸውን እንዲመለከቱ ታደርጋቸዋለች ብዬ እገምታለሁ፡፡
ለሁላችንም አላህ ቀጥተኛውን መንገድ እንዲወፍቀን እመኛለሁ::
🎉13❤12👍4🙏1
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
.......ሼሁ በዳንስ ቤት👳♂......
🗣ተርጓሚ፦ሐሚድ ጧሂር እድሪስ
✎ ፀሐፊ፦𝕞𝕦𝕜𝕖𝕣𝕖𝕞
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
🌟በ 𝕙𝕒𝕗𝕦 𝕚𝕤𝕝𝕒𝕞𝕚𝕔 𝕡𝕠𝕤𝕥 የተዘጋጀ🌟
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
╔════•| ✿ |•════╗
#ክፍል_ 1⃣
╚════•| ✿ |•════╝
በትናንትናዋ ዕለት መስጊድ ውስጥ ሶላቴን ጨርሼ ሳሰላምት፡፡ እገሌን ሳላስበው ውል ሲል አየሁት አይኔን አላመንኩትም ጥቂት ቆይቼ ወደሱ በመሄድ እሱነው አይደለም ብዬ አትኩሬ አየሁት በርግጥም በደሙና በስጋው እሱ እራሱ ነበር። አላህን በጣም የፈራ ሆኖ በተረጋጋ መንፈስ ስርዓቱን የጠበቀ ሶላት ይሰግዳል።
ግን ይህን ሰው ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በተሳሳተ መንገድ ያጉል ስልጣኔ እና የስሜትን ፈረስ የሽምጥ እየጋለበ በጥመትና በክህደት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቆ መውጣት ከማይችልበት ወንጀል ውስጥ በመግባት አሉ የተባሉ ደናሾችን፣ አሸብሻቢዎችን እና ተወዛዋዦችን እያሳደደ በነበረበት ወቅት ነው᎓᎓ ይህ ስራው ልክ የፍቅር መፅሐፍ ስናነብ የምናገኘውን የፍቅር ታሪክ እሱ እራሱ በውኑ የሚሰራው መስሎ ነበር የሚሰማው፡፡ ዲኑን እና አቅሉን መርሳቱን ያየች አንዷ አሸብሻቢ ደግሞ ሞኝነቱን እና የዋህነቱን በማየት የኪሱን ደም የልቡን ውሃ በመምጠጥ ፍቅሩን ሳታስጨርሰው ገፍትራ በመጣል አባራው የሰዎች ሁሉ መሳለቂያ ሆኖ በነበረበት ወቅት ነበር የማውቀው፡፡
ይህ ሰው እባክህ እያለ የሚጠራው አእምሮ _ ነበረው፡፡ ግን የአእምሮውን ጥሪ አልተቀበለውም፡፡ መካሪ ወንድሞችና ጓደኞች ነበሩት፡፡ ግን ለምክራቸው ጆሮ ዳባ ልበስ በማለቱ፡-"ምከረው ምከረው ካልሰማ መከራ ይምከረው" በማለት ለሸይጣን፣ ብሎም ለበሽታ፣ለድህነት እና ለጀሃነም አጋልጠው ተውት
ግን ያንቀን መስጊድ ውስጥ አላህን ሱ.ወ በፍርሃት እና በስርዓት ሲገዛ ሳየው በጣም ተገረምኩ፡፡ ሶላቱን ሰግዶ እስኪጨርስ ድረስ በትዕግስት ጠበኩት፡፡ ልክ ሶላቱን ሰግዶ ሲያበቃ ጠጋ ብዬ ሰላም ማለቴን አለማለቴን በቅጡ ሳላውቀው ቀጥታ ከዚህ ቦታ እንዴት ሊመጣ እንደቻለ ጠየኩት፡፡
እሱም እንዲህ አለኝ አይ አንተ የድሮ ጓደኛዬ!!» ከዚህ ቦታ አመጣጤ ብዙ አስገራሚና አስደናቂ ታሪክ አለው” አለኝ፡፡
እስኪ ታሪኩ ምን እንደሁ አጫውተኝ” አልኩት በመገረም፣
•
“ይህን
ታሪኬንማ እዚህ አላህ ቤት
ውስጥ ልነግርህ
ይከብደኛል መስማት ከፈለክ ወደ ቤቴ እንሂድ እና ታሪኩን ላጫውትህ” አለኝ
እኔም ታሪኩ ምን እንደሆነ ለመስማት በመጓጓት ወደ ቤቱ ተከትየው ሔድኩ፡፡
እሱም እንዲህ ሲል ታሪኩን ያጫውተኝ ጀመር
አሁን እኔ ወደ አላህ ሱ.ወ ቶብቼ መመለሴ ካላህ የተሰጠኝ ስጦታ ነው፡፡ ሰበብ ያደረገልኝ ደግሞ መስጊድ ውስጥ ያየሃቸውን ሼህ ነው አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸውና፡፡ በኝህ ሼህ ምክንያት አላህ ሱ.ወ. የጥመትና የተሳሳተ መንገድ ከተከተልን በኋላ እኔም ሆንኩ እኔን መሰል ብዙ ሰዎችን ቅኑን መንገድ ሰጥቶናል መርቶናል ለዚህም አልሃምዱሊላህ።
በርግጥ ድሮ እንደምታውቀኝ በዲናቸው ጠንካራና ብርቱ የሆኑ በርካታ የዳዕዋ ሰዎችን አውቅ ነበር፡፡ ስለብዙ ጠንካራና ዓቢድ ዑ ለማዎች ከንጉስ ፊት ቀርበው ሀቅን ከመናገር ወደኋላ ከማይሉ ለሀቅ ሲሉ ማንንም የማይፈሩ የአሊሞችን ታሪክም ብዙ ሰምቻለሁ ግን ወላሂ! ወላሂ! እልሃለሁ እንደኝህ አይነት ሼህ ጠንካራና
ጀግና ተዋውቄም አይቼም ሰምቼም አላውቅም” አለኝ᎓᎓
“ምን አደረጉ ሼሁ?! እንዲህ ልትላቸው የቻልክ?” አልኩት፡፡
ያደረጉትን አልሰማህም እንዴ?!” አለኝ፡፡
በእውነት አልሰማሁም! እባክህ ንገረኝ አኮ ምን አደረጉ?”
"በዳንስ ቤት ውስጥ ዳዕዋ አደረጉ፡፡”
“ምን?! ይህንንስ አላምንም” አልኩት
”እንዴት? እስካሁን አልሰማህም እንዴ? ከዚህች አዱኛ እርቀሃል ማለት ነዋ!᎓᎓ ወሬው እኮ በየጋዜጦች ተዘግቧል በየመንገዱም ተነግሯል ሰው ሁሉም ለብዙ ጊዜ አውርቶታል” አለኝ፡፡
ታዲያ ሼሁ በዳንስ ቤት ውስጥ ምን አይነት ዳዕዋ አደረጉ?”አልኩት፡፡
በመጀመሪያ ሼሁ ሁልጊዜ መስጊዱን ሲመለከቱት መስጊዱ ውስጥ የሚያዩዋቸው የተለመዱ ፊቶችን (ሽማግሌዎችና ጎልማሶች) ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት ግን መስጊዱ በወጣት ተማሪዎች እና በወጣት ሰጋጆች ይሞላ ስለ ነበር ሼሁ ይህ ነገር እያሳሰባቸውና እየከነከናቸው መጣ፡፡
ከእለታት እንድ ቀን ለሽማግሌዎቹና ለጎልማሶች እንዲህ ሲሉ ጠየቁ
የሰፈሩና የከተማው ወጣቶች የት ሔዱ? ሽማግሌዎች ግን ሊነግሯቸው ፍቃደኛ ባለመሆን ዝም አሏቸው ሼሁ ጥያቄያቸውን በመድገም ከዚህ መስጊድ ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት እኮ ከናንተ በበለጠ የሚመለከተው ወጣቶችን ነው᎓᎓ ታዲያ እነዚህ ወጣቶች የት ደረሱ? የት ሄዱ?” ሲሉ ጠየቁ
ሽማግሌዎችም እንግዲህ ሼሁ ይህን ያህል ካመረሩ መናገር አለብን ብለው በማሰብ እንዲህ ሲሉ ነገሯቸው፡፡
የከተማው ወጣትማ የሚያመሸው ሲኒማ ቤት፣ ዳንስ
ቤትና ቁማር ቤት ነው᎓᎓” አሏቸው፡፡
ዳንስ ቤት?! ሲኒማ ቤት?! ደግሞ ይሄ ምንድንነው?” ሲሉ ሼሁ በአግራሞት ጠየቁ
ለምን ብትለኝ ሸሁ ስለነዚህ ነገሮች አይተውም ሰምተውም አያውቁም᎓᎓
ሼሁ መልሰው ዳንስቤትና ሲኒማ ቤት ምን እንደሆነ ሽማግሌዎችን እንዲያብራሩላቸው ጠየቁ!
ከዚህ በፊት ሼሁ በዱንያ ውስጥ የሚያውቁት ነገር ቢኖር ቤታቸውን ከዚያም መስጊድ፣ ሀዲስና እንዲሁም፣ ነብዩ አንዲህ አሉ፣ አላህ እንዲህ አለ ብቻ ነበር።”
እኮ ታዲያ ሽማግሌዎች ለሼሁ ምን ብለው መለሱ? ስል በስሜት ጠየኩት፡፡

ይቀጥላል .....❤️🔥
Like 1⃣0⃣0⃣+♥️ካልሆነ ቀጣዩ ክፍል አይለቀቅም🚫
★ @Hafu_posts🪄 || ★ 𝖍𝖆𝖋𝖚 𝖕𝖔𝖘𝖙🌙 ★
❤173👍21
ምሽቱ በተለይ ለብቸኞች ስንት ሀሳብ ይዞ ይመጣል መሰላችሁ.. ያላገቡት የወደፊት ዕጣፈንታቸዉን አርቀው በማየት ያብሰለስላሉ፣ የተፋቱት ፍራሻቸው ላይ ጋደም ብለው በትዝታ ባህር ዉስጥ ይዋኛሉ፣ ባል/ሚስት የሞተባቸው አልሽር አልደርቅ ያላቸዉን ቁስል ለማድረቅ ይታገላሉ ...
ሁሉን የምታይ የምታውቅ ጌታዬ ሆይ! ለከበዳቸው ባሮችህ ሁሉ ምሽቱን አግራላቸው🤲🏽

🥰37🙏10❤7
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™
DAILY TIp 11 ወጣትነት ✨የእውነት እንኑር✨ አህባቢ የእውነት እንኑር ከዱንያው ድካም ልባችንን አሳረፈን ለተፈጠርንበት አላማ እንኑር وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّاليعبدون ጋኔንንና ሰውንም፥ሊገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም። አዎ አላህን በእውነት ፣በደስታ እናምልክ ከማስመሰል ርቀን ረሃ የሆነ ኑሮን እንኑር አይበቃንም ልባችን አልደከመም ?? በጣም…
DAILY TIP12
ወጣትነት
✨ጌታችን✨
እስኪ ደግሞ ዛሬ ስለ ጌታችን አላህ መሀሪነት እና እዝነት ትንሽ ነገር እንበል
አላህ እኛ ባሮቹን በእዝነቱ ባይ ዳብሰን ኑሮ ህይወት ከባድ ነበረች ይሀው ዛሬም በ እዝነቱ አለን እንደ ወንጀሎቻችን ቢሆንማ
በመሬት ላይ መንቀሳቀስ አንችልም ነበር
ጌታችን አላህ ግን በወንጀል ፣በጥፋት ላይ ብንሆን እንኳ ወደሱ እንድንመለስ ይፈልጋል
አይገርምም እያጠፋ ብትሆን እንኳ ወደሱ እንድንቃረብ የሚሻ ጌታ። ለባርያው ያለውን ውዴታ ረሱ በዚ ልናይ እንችላለን ታድያ እኛ ወጣቶች ምን እንጠብቀለን የአለመቱ መሪ እንዲ የሚጠብቀን ከሆነ እኛስ ለምን ራቅነው?? 🧐 ሰበብ አናብዛ ወንጀሌ ነው እየልን ይልቅ ቀኑ ሳይሄድ መጨረሻችን ሳይደርስ እንመለስ።
አቦ አላህ ያግራልን
ለባረያው አዛኝ ነው ያስገርማል ፍቅሩ
ሁሉንም አዋቅ ከላይ እስከ ሰሩ።

❤25😢2👍1
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™
✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 56❵ #hadith56 "አቡ ቀታዳ (ረ.ዐ) እንዳወሱት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንደኛችሁ ሲጠጣ ዕቃ ውስጥ አይተንፍስ፤ ሲፀዳዳም ብልቱን በቀኝ እጁ መያዝ የለበትም፤ በቀኙም ብልቶቹን አይጠብ፡፡›› (ቡኻሪ ዘግበውታል) 📋ያለፈው ክፍል👇📋 https://t.me/Hafu_posts/12860 🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨
❴Part 57❵ #hadith57
"ኢብን ዐብባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ አንድ ጊዜ ‹‹ውዱእ›› አድርገዋል፡፡
(ቡኻሪ ዘግበውታል)
📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/12889
🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫

🥰8❤7🍓1
✍️የምድር ላይ ህይወትህ መፅሀፍህ ነው ፤ ነገ የትንሳኤ ቀን አላህ ፊት ታነበዋለህ፤
ስለዚህ ለህይወትህ መጥፎ ደራሲ ከመሆን ተጠንቀቅ።
ስለዚህ ለህይወትህ መጥፎ ደራሲ ከመሆን ተጠንቀቅ።
👍24❤8
❤️🩹ነፍስ እንኳን በአካል ትለያልለችና
ምንም ነገር እስከመጨረሻው ከእኔ
ጋር ይቆያል ብለህ አታስብ።
ምንም ነገር እስከመጨረሻው ከእኔ
ጋር ይቆያል ብለህ አታስብ።
🥰31❤9👍8
🤩#ሼሁ_በዳንስ_ቤት👳♂ ምሽት 3:00 ይቀጥላል✅
አህባቡ ዝግጁ ነው እስኪ 👍❤️ አሳዩኝ ❔
አህባቡ ዝግጁ ነው እስኪ 👍❤️ አሳዩኝ ❔
ከናንተ የሚጠበቀው ይሄን ፖስት ስር ❤️🔥 Like ማድረግ እና ከላይ ፎቶ ላይ እንደምታዩት ቻናሉን Mute አድርጎ በጉጉት መጠባበቅ ብቻ ነው🫡
❤40👍5
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
.......ሼሁ በዳንስ ቤት👳♂......
🗣ተርጓሚ፦ሐሚድ ጧሂር እድሪስ
✎ ፀሐፊ፦𝕞𝕦𝕜𝕖𝕣𝕖𝕞
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
🌟በ 𝕙𝕒𝕗𝕦 𝕚𝕤𝕝𝕒𝕞𝕚𝕔 𝕡𝕠𝕤𝕥 የተዘጋጀ🌟
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
╔════•| ✿ |•════╗
#ክፍል_ 2⃣
╚════•| ✿ |•════╝
ከዚያማ ሽማግሌዎቸ ለሼሁ ዳንስ ቤትና ሲኒማ ቤት ማለትማ ትልቅ አዳራሽ ሲሆን ከቤቱ ደረት ላይ ከፍ ያለ ትልቅ መደብ መሰል የእንጨትና የብረት ድርድር ያለበት ሲሆን ትልቅ መጋረጃም አለው ይህ ሰፊ አዳራሽ ደግሞ በወንበር የተሞላ ነው፡፡ ወንበሩ በሰዎች ከተሞላ በኋላ የትልቁ መደብ መጋረጃ ይከፈትና ከሀፍረተ ስጋቸውና ከጡታቸው ላይ ብጣሽ ጨርቅ የለጠፉ እራቁታቸውን የሆኑ ሴቶች ዳሌያቸውን እያወዛወዙ እጃቸውን እያውለበለቡ እግራቸውን እያነሱ በመዝለል የሚጫወተበት ቦታ ነው” አሏቸው
ሼሁ በቃችሁ! በቃችሁ!” አሉና “ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጅዑን” ካሉ በኋላ ሴቶች ከወንዶች ፊት እርቃናቸውን ይጫወታሉ ነው የምትሉኝ?! ይህ በዚህች አለማችን በተለይ በዚህች በከተማችን ይደረጋል ብዬ አንድም ቀን ጠርጥሬም አስቤም አላውቅም!! በሉ ተነሱ አሁን ወደዚህ ዳንስ ቤት እንሂድ?” አሉ ሼሁ ወደ ዳንስ ቤት እንሂድ ነው የሚሉት እንዴ ሼሆቹ? አሉ ሽማግሌዎች᎓᎓
አስቀያሚ ወንጀል ሲፈጸም እና ከስርዓት የወጣ ጋጠወጥነት ሲስፋፋ በጉልበቱ መቀየርና ስርዓት ማስያዝ ካልቻልን በነብዩላህ ዳውድ እና በነብዩላህ ዒሳ ዘመን የወረደው እርግማን ሳይወርድብን በፊት እኛ በምላሳችን ዳዕዋ በማድረግ እነዚህን ሰዎች መለወጥ አለብን፡፡” አሉ ሼሁ ተናደው።
እስኪ ሼሁ ትንሽ ተረጋጉ! አሁን እኛ ወደዚህ ዳንስ ቤት ሂደን ዳዕዋ ብናደርግ ይስቁብናል ይሳለቁብናል ብሎም እንጅ የምንለውን አይሰሙንም ሼሁ! አሉ ሽማግሌዎች
ሼሁ በመቆጣት እኛ ከነብያቶች አንበልጥም፡፡ ነፍሳችን ከነሱ ነፍስ የተሻለች አይደለችም፡፡ ለአላህ ሲሉ ነብዮች ተስቆባቸዋል፣ ተደብድበዋል፣ ተሰቃይተዋል አንድም ቀን ግን ተሸንፈው፣ ሰልችተው፣ ተስፋ ቆርጠው አያውቁም፡፡ እኛ ያለብን ማድረስ ነው፡፡ ሂዳያን የሚሰጠው ግን አንዱ አላህ እሱ ብቻ ነው፡፡ እና አሁን ተነሱ እንሂድ፡፡” አሉ ሼሁ
ሼሆቹ አሁን እኛ ወደ ዳንስ ቤት ከምንሄድ ይልቅ በስፖርት በጤናና በጥበብ ስም በየትምህርት ቤቱ ሴቶች ቁምጣ ሱሪ ለብሰው ጡታቸውን አሹለው ከወንዶች ፊ ት ኳስ ሌላም ሌላም ነገር እንዲጫወቱ በማለት መምህራኖች አዲስ ፈሊጥ አምጥተው ሴት ልጆቻችንን ለሰይጣን እያጋለጧቸው እና ምግባረ ብልሹነት እያስተመሯቸው ስለሆነ በመጀመሪያ ትምህርት ቤቶች ሂደን ብናስተምር ጥሩ ይመስለናል።” አሉ ሽማግሌዎቹ
ሼሁ ግን የለም የለም አላህ ቢሻ የምንጀምረው በዳንስ ቤቱ ነው” አሉ ሼሁ፡፡ ሽማግሌዎች ሼሁ በአቋማቸው መፅናታቸውንና ማምረራቸውን ሲያዩ እንዲህ አለ -
“እንዲህ ከሆነማ ከሲኒማ ቤቱ ሄደን ቦታ እስክናዘጋጅለዎት ድረስ እድል ይስጡን? አሉ።
በኋላስ ምን ሆነ? እውነት ሸሁ ወደ ዳንስ ቤት ሔዱ? አልኩት የሆነውን ለማወቅ ጓጉቼ መጀመሪያ ሽማግሌዎቹ ወደ ዳንስ ቤቱ በመሔድ የዳንስ ቤቱን ባለቤት ከትርኢቱ መካከል ያለችውን የእረፍት ጊዜዋን ሩብ ሰአት እንዲያከራያቸው እና ሸሆቹ በዚህች ሰኣት ውስጥ ዳዕዋ እንዲያደርጉባት ጠየቁት፡፡
የዳንስ ቤቱ ባለቤት ሰዎቸ ጤነኛ እንዳልሆኑ በመጠራጠር አፍጥጦ ተመለከታቸው! እብድም መሰሉት፡፡ በጣም ፈራቸው፡፡ ተከናንበው ወደለበሱት ጋቢም አጮልቆ ተመለከተ ምን አልባት ከመካከላቸው አንዱ ከጉያው አውጥቶ በብረት ዘነዘና ሳያስበው ራሱን እንዳይበጠርቁው ፈራ፡፡ እንዲሁም ከጋቢያቸው በታች ወደለበሱት ልብስ ማየት ጀመረ፡፡ ምን አልባት እነዚህ ሰዎች ከአማኑኤል ሆስፒታል አምልጠው እሱን መቋደሻ ሊያደርጉት የመጡ እብዶች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሞከረ፡፡ ከዚያም እንዲህ ሲል አሰበ፡- አንዱ እጁን ሰዶ ሳይንቀው በፊት ወደኋላ በመሸሽ ወንበሩን ገፋ አድርጎ ከመቀመጫው በመውጣት ለረዳቶቹ የዑዑታ እና የርዳታ ድምፅ አሰምቶ _ እርዳታ ጠይቆ ከነዚህ ሼሃቸውን ይዘው ሲኒማ ቤት ለመምጣት ካሰቡ እብዶች የሚያወጣው ሰው በመፈለግ አይነት ተቅበዘበዘ፡
ነገር ግን ሽማግሌቹ የዳንስ ቤቱ ባለቤት እንደፈራቸው ስለገባቸው አንደኛው የሸሚዙን ኮሌታ አጣምሮ እንቅ አድርጎ በመያዝ ጎትቶ ከፊታቸው ካቆመው በኋላ በሩብ ሰአት ውስጥ ሼሁን ለማስተናገድ ሌሊቱን ሁሉ ቁጭ ብሎ አድሮ ከሚያገኘው ገቢ የበለጠ ብር አስታቀፉት
የዳንስ ቤቱ ባለቤት ይህን ሲያይ
አላመነም፡፡ በጣም ተደሰተ፣ ተፍነከነከ፡፡ _ ዳንስ ቤቱ ቤታቸው እንደሆነ በመንገር እስከበሩ ድረስ በመሔድ ከሸኛቸው በኋላ በተባለው ቀን ተዘጋጅቶ እንደሚጠብቃቸው ነገራቸው፡፡
የዳንስ ቤቱ ባለቤት ይህን የማይታለፍ እድል በማግኘቱ በጣም ተደሰተ፡፡ ሸሁንም በዚህ ሁኔታ ሊያዋርዳቸውና ሊጠቀምባቸው መንገድ በማግኘቱ ሁለት ወፍ ባንድ ዲንጋ! ሲል አሰበና ጊዜ ሳይወስድ ቀጥታ ወደ ማተሚያ ቤት በመሄድ የሳምንቱ አስገራሚው ክስተት» በማለት ትልቅ ማስታወቂያ በማሰራት ሼሁ በዳንስ ቤት) በሚል ርእስ ያሸበረቀ ፖስተር ከዳንስ ቤቱ ፖስተር መለጠፊያ ላይ ለጠፈ
ሰዎች ይህን አስደሳች ዜና ለማየት ተሰበሰቡ፡፡ በርግጥ የፖስተሩ ርዕስ ቢያስገርማቸውም ሼሁ በዳንስ ቤት ይመጣሉ ብሎ ያሰበ ግን ማንም የለም፡፡ ያሰቡት ነገር ቢኖር አዲስ እና ከውጭ አገር የመጣች ታላቅ ደናሽ ሳያስቡት ዳንስ ቤቱ ሊያሳያቸው ያሰበ ወይም አንድ ያልተለመደ አዲስ ዳንስ ሊያቀርብላቸው ያሰበ ነበር የመሰላቸው፡፡
ጊዜውን ጠብቆም የፖስተር ማስታወቂው እውን የሚሆንበት ቀን በመድረሱ፡- የከተማው ህዝብ ሴት ወንድ ሳይል ግልብጥ ብሎ ወደ ዳንስ ቤቱ መጣ፡፡ በትኬት መስኮቶች ግፊያ ተጀመረ፡፡ የትኬት ዋጋ ጨመረ አንዳንድ ሰዎች በዛ ያለ ትኬት በመግዛት ከዳንስ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሆነው መጋፋት ለማይፈልጉ ሰዎች በጥፍ ዋጋ መቸብቸብ ጀመሩ፡፡ የዛን እለትም ትኬት ለመግዛት ከሚጋፉት ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነበርኩ” አለኝ፡፡
በኋላስ ምን ተከሰተ? አልኩት»
በኋላማ ሰው ቦታ ቦታውን ይዞ ተቀመጠ፡፡ ቦታም ያጣ ቆመ፡፡ የመድረኩ መጋረጃ ገና መሸብሸብ ሲጀምር ሰው ጭብጨባውን አቀለጠው፡፡ ፉጨትና ጩኸት ተደባለቀ።
በኋላስ?” አልኩት በወሬው በመመሰጥ፡፡
ወገብ ሁሌ የሚያውቋትና ከሚስት ከልጆቻቸው አብልጠው የሚወዷት ለሷ ሲሉ ገንዘባቸውንና ጊዜያቸው ን የሚያባክኑላት፣ ዲናቸውን የሚረሱላት አሸብሻቢ ከብልቷና ጡቷ ላይ ብጣሽ ጨርቅ መሳይ ለጥፋ እግሮቿን ወደ ላይ ከፍ በማድረግ እየተሸከረከረች ከመድረኩ ብቅ አለች፡፡ እንደገና ጭብጨባው ቀለጠ፡፡ _ ያሸብሻቢዋ ከሙዚቃው ጋር እኩል በመውረግረግ ዳንሷን ቀጠለች። አሸብሻቢዋ ዳንሱን ስትጨርስ ስሟን እየጠሩ በመጮህና በማፏጨት ይደገም! ይደገም! በማለት አንቧረቁ፡፡ ዳንሱ ተደገመ፡፡ ይህ በንዲህ እንዳለ የረፍት ሰአት ∙ በመድረሱ ለሩብ ሰአት ያህል የመድረኩ መጋረጃ ተዘጋ”

❤54🔥3🥰2
በኋላስ ምን ሆነ?” አልኩት᎓᎓
ከሩብ ሰአት የእረፍት ጊዜ በኋላ እረፍቱ ማብቃቱን የሚያበስረው ደወል አቃጨለ፡፡ ሁሉም ቦታ ቦታውን ያዘ፡፡ ግን የመድረኩ መጋረጃ አልተከፈተም፡፡ የሚቀጥለውን ትዕይንት ለማየት ሰው በጉጉት በመጠባበቅ በግራቸው መሬት እየደበደቡ በእጃቸው እያጨበጨቡ የዳንሰኛዋን ስም ይጠሩ ጀመር
የመድረኩ መጋረጃ መከፈት ሲጀምር ሰው ፀጥ ረጭ ማለት ጀመረ ከዚያ ከሚወዱት ተውረግራጊ ገላ ሌላ ያማረ ነገር ይመጣል ብለው ሲጠባበቁ የነበሩት ሰዎች ያዩት ግን ሌላ ነገር
ነበር”፣
እኮ ምን አዩ?” አልኩት ያዩትን ለመስማት በመቸኮል......

❤72👍8