𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭
14.7K subscribers
1.95K photos
859 videos
6 files
594 links
亗 ꧁﷽꧂ 亗
🤍𝑤𝑒𝑙𝑐𝑜𝑚𝑒 𝑡𝑜 ᴏᴜʀ 𝑐ℎ𝑎𝑛𝑛𝑒𝑙ᥫᩣ
Channel Objective🎊🎊🎊🎊🎊
➻Islamic teachings💛
➻Current information🤗
➻Hadiths and Qurans 🤩


CROSS🔄 @Waver_boy1
Download Telegram
🤩#ሼሁ_በዳንስ_ቤት👳‍♂ የተሰኘ አጓጊና አስተማሪ ተከታታይ ታሪክ ነገ ምሽት ልንጀምር ነው🤌

ከናንተ የሚጠበቀው ይሄን ፖስት ስር 200❤️‍🔥 Like ማድረግ እና ከላይ ፎቶ ላይ እንደምታዩት ቻናሉን Mute አድርጎ በጉጉት መጠባበቅ ብቻ ነው🫡
❤‍🔥122👍1396🫡2
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭
DAILY  TIP 10 ወጣትነት ጊዜያዊ ደስታ ወይስ ዘላለማዊ የዛሬውን ርዕስ በምርጫ ነው የጀመርነው  በተለይ ይሄ ርዕስ ከኛ ከወጣቶች ጋር  በጣም ቅርበት አለው እኛ ወጣቶች  አብዛሀኛውን ጊዜ እነዚ ነገሮች ይምታቱብናል ዘላለማዊ  ደስታ እየመሰሉን  ጊዚያዊ ደስታን እናስተናግዳለን ።እውነታው ግን እኛ ወጣቶች ዛሬን ምያስደስተንን ፣ አሁን ሚመቸንን ነገር ነው  ለመፈፀም ምንቸኩለው   ላምን ይሆን…
DAILY  TIp 11
ወጣትነት
የእውነት እንኑር
አህባቢ የእውነት እንኑር ከዱንያው ድካም ልባችንን አሳረፈን  ለተፈጠርንበት  አላማ እንኑር
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّاليعبدون
ጋኔንንና ሰውንም፥ሊገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም።

አዎ አላህን በእውነት ፣በደስታ እናምልክ
ከማስመሰል ርቀን ረሃ የሆነ ኑሮን እንኑር
አይበቃንም ልባችን አልደከመም ?? በጣም እኮ ነው የሰለቸን አይደል እንዴ 😔 ወላሂ ከልብ የሆነ መመለስ ፣የእውነት ህይወት መኖር  ይኖርብናል ። እየቀለድን ፣እየወደቅን፣ እየስመሰልን እስከ ዛሬ ቆየን  ከዛሬ ጀምረን ግን እናቁም ለ ጌታችን እየተዘዝን  የእውነት እንኑር ። ለሱ በመታዘዝ  የቀልብ ሰላም እና ደስታን አሰናግኝ ።

አቦ አላህ  ያግራልን
23😭4
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭
ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ ❴Part 55❵ #hadith55 "ኢብን ዐብባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ሽንት ቤት ገቡ፡፡ የ‹‹ውዱእ›› ውሃ አስቀምጩላቸው ነበር፡፡ ‹‹ይህን ያስቀመጠልኝ ማን ነው?›› በማለት ጠየቁ፡፡ ተነገራቸው፡፡ ‹‹አላህ ሆይ ይህን ዲን አሳውቀው፡፡›› በማለት ፀለዩ፡፡ (ቡኻሪ ዘግበውታል) 📋ያለፈው ክፍል👇📋 https://t.me/Hafu_posts/12846…
ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ

❴Part 56❵ #hadith56

"አቡ ቀታዳ (ረ.ዐ) እንዳወሱት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንደኛችሁ ሲጠጣ ዕቃ ውስጥ አይተንፍስ፤ ሲፀዳዳም ብልቱን በቀኝ እጁ መያዝ የለበትም፤ በቀኙም ብልቶቹን አይጠብ፡፡››

(ቡኻሪ ዘግበውታል)




📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/12860

🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
6👍5👏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❤️ የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ ❤️

🌙 ሰባኹል ኸይር / ሰባኹል ኑር



📖🎧 #ቁርኣን  || PART ❶❻

⭐️ 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭 || SHARE 😊
17
🍁علي بن أبي طالب

“ተስፋው በአንተ ላይ ያለውን ሰው አታሳዝን”
🫡10👍6🆒1
سورة الكهف .pdf
626.5 KB
ወደ አላህ ከጠራና መልካምን ከሰራ
   <<እኔ ከሙስሊሞች ነኝ>>
ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማነው?
አል–ፉሲለት ምዕ[41:33]




‏﴿ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيماً ۝ ﴾

አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡


عن أبي سَعيدٍ الخُدريِّ عنِ النبيِّ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم أنَّه قال: (( مَن قَرَأَ سورةَ الكَهفِ يومَ الجُمُعةِ أضاءَ له من النورِ ما بَينَ الجُمُعتينِ  ))


☞︎︎︎በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሃል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።»
11👍5👏5
ዱንያ ተመቸንም አልተመቸንም
በሞት ይጠናቀቃል ‼️
💯26👍10💔3
May Allah's peace and blessings be upon you all
17🍓2
ወንጀል ላይ ያሉ ሰዎችን ስትከታተል ሁለት ፈተና ሊገጥምህ ነው....

•ያሉበትን ሁኔታ መመኘት (ሳታስበው)

•እነሱን መናቅ እና በእነሱ
#መሳለቅ (ኻቲማ በአሏህ እጅ ብቻ ከመሆኑ ጋር)

ወንጀል ላይ ያሉ ሰዎችን ባለመከታተል እና ስለነሱ ባለማውራት ራስህን ጠብቅ!
👍317🙏3
አንዳንድ ጊዜ አላህ ዋጋህ ከማይከበርበት ክፍል remove ያደርግሃል... so he can place u በምትከበርበት ክፍል ዉስጥ ያስቀምጥሃል።
👍34💯85
አላህ በሳቃችሁ ውስጥ ያለውን ሀዘናችሁን
የሚረዳ የሚያስረሳ ሰው ይስጣችሁ❤️‍🩹
43👍4🥰1
ጁሙዓህ እንዴት ነበር አህባብ??
🥰106👌4
ሼሁ በዳንስ ቤት የተሰኘው መፅሃፍ ታሪክ ዛሬ ምሽት 3:30 ይጀመራል 🥳 እስከዚያው #መግቢያውን ተጋበዙልኝ👇🏽🤩

ማስታወሻነቷ፡
ልቡ ወደ ዲኑ እያደላ
ነፍሱና ስሜቱ ወደ ወንጀልና ወደ መጥፎ ስራ
ለምትገፋፋው ወጣት ሁሉ ትሁንልኝ፡፡
«ደራሲው»

«ሼሁ በዳንስ ቤት» የሚለውን መጽሃፍ አንብቤዋለሁ፡፡ ይህ መጽሃፍ በሃገራችን የእስልምና ኃይማኖትን አስመልክቶ ከተጻፉትም ሆነ ከተተረጎሙት በይዘትም ሆነ በዓይነቱ የተለየ ነው፡፡
ይህ መጽሀፍ ወደ መስጊድ ለሚመጣ ሰው ብቻ ዳዕዋ ማድረግ በቂ እንዳልሆነ እንዲያውም ወጣቱ ትውልድ የት
ይውላል ብሎ ጠይቆ በድፍረት
ድረስ በመሄድ ዳዕዋ ማድረግ
በተለያየ መንገድ ሊገኝበት በሚችለው ቦታ ተገቢ መሆኑን ያመለከተ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በተለይ ወጣቱ በዳንስ ቤት፣ በመጠጥ ቤትና በመቃሚያ ቤቶች ጊዜውን በከንቱ እያሳለፈ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ይህን የሙስሊም ህብረተሰብ አካል የሆነውን ወጣት እንዴት ከዚህ ተግባሩ ሊመለስ ይችላል? ማነው እዚህ ቦታ ደርሶ ካለበት አሳዛኝ ሁኔታ ይመልሰዋል? ለሚለው ጥያቄ በሃሚድ ጣሂር የተተረጎመው መጽሃፍ ጥሩ ጥቅም የሚስጥ ይመስለኛል፡፡
«ሼሁ በዳንስ ቤት» በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሃፍ ለዳዕዋ ለሰዎች በተለይ ለወጣቱ ለሁሉም ሙስሊም ህብረተሰብ ክፍል በጥቅሉ ጥሩ ጠቀሜታ ያለው ይመስለኛል፡፡

አላህ ሱ.ወ ከክፉ ስራና ከመጥፎ ድርጊት እንዲጠብቀን እንማፀናለን፡፡ ውድ የዚህ መጽሃፍ አንባቢያን፡-
ይህ መጽሃፍ ሽህ ዓሊ ጠንጣዊ «የህይወት ታሪኬ» በሚል መጽሐፋቸው ውስጥ ከጻፉት ተወስዶ የተተረጎመ ሲሆን መጽሀፉ ብዙ የተለያዩ ርዕሶችን ያካተተ ቢሆንም ከነዚህ መካከል «ሼሁ በዳንስ ቤት» የሚለውን ርዕስ መርጬ ለአንባቢያን ለማቅረብ ሞክሬያለሁ፡፡
ሼህ ዓሊ ጠንጣዊ በመግቢያቸው ላይ እንደሚጠቅሱት ይህን መጣጥፍ የጻፉት በ1946 እ.ኤ.አ ነው፡፡ በወቅቱ የሚታተሙ ጋዜጦችና መጽሄቶች የሳቸውን ጽሁፍ በሰፊው ያሰራጩት ሲሆን በአንባቢያን ዘንድም ተወዳጅነትን ያተረፉ ነበሩ፡፡
ሼህ ዓሊ ጠንጣዊ ብዙ የዲን መጽሀፍትን የጻፉ ሲሆኑ እንደ አብነት
የሚጠቀስላቸው እና ከአረብኛ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው ኢማን በሚል ርዕስ የፃፉት መጽሐፋቸው ነው፡፡
ሼህ ዓሊ ጠንጣዊ ሶሪያዊ ሲሆኑ በሶሪያ ዩኒቨርሲቲ የህግና የሸሪዓ መምህር ብሎም የከፍተኛ ፍርድ ቤት የዳኞች ኃላፊ በመሆን እንዳገለገሉ ስለእሳቸው የተጻፉ መጽሃፎች ያስረዳሉ፡
በእኒህ ታላቅ ሰው ከተፈጸመው መጽሃፍ «ሼሁ በዳንስ ቤት» የሚለውን ርዕስ መርጬ በመተርጎም ለኢትዮጵያ ሙስሊም አንባቢ ሳቀርብ በተለይ ለወጣት አንባቢያን ብዙ ፋይዳዎች ሊያስገኝ ይችላል ከሚል ሃሳብ በመንደርደር ነው፡፡ በእርግጥ ከዚህ መጽሃፍ ውስጥ የተጠቀሱት ቀላል የማይባሉ ነገሮች ኢትዮጵያ የተለያዩ የሃይማኖት ተከታይ አገር እንደ መሆኗ መጠን ከባህልና ወጉ ጋር ላይጣጣሙ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን መጽሀፉ የያዘው መልዕክት ለዲን አፍቃሪ ወጣቶች ብዙ እውቀት ሊያስጨብጣቸው ይችላል፡፡ በተጨማሪም ራሳቸውን ዘወር ብለው እንዲያዩና ውሏቸውንና ስራቸውን እንዲመለከቱ ታደርጋቸዋለች ብዬ እገምታለሁ፡፡

ለሁላችንም አላህ ቀጥተኛውን መንገድ እንዲወፍቀን እመኛለሁ::
🎉1312👍4🙏1
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
        .......ሼሁ በዳንስ ቤት👳‍♂......

    🗣ተርጓሚ፦ሐሚድ ጧሂር እድሪስ

          ✎ ፀሐፊ፦𝕞𝕦𝕜𝕖𝕣𝕖𝕞
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

  ┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
     🌟በ 𝕙𝕒𝕗𝕦 𝕚𝕤𝕝𝕒𝕞𝕚𝕔 𝕡𝕠𝕤𝕥 የተዘጋጀ🌟
  ┖━─━─━─━─━─━─━─━┚

      ╔════•| ✿ |•════╗
                  
#ክፍል_ 1⃣
      ╚════•| ✿ |•════╝



በትናንትናዋ ዕለት መስጊድ ውስጥ ሶላቴን ጨርሼ ሳሰላምት፡፡ እገሌን ሳላስበው ውል ሲል አየሁት አይኔን አላመንኩትም ጥቂት ቆይቼ ወደሱ በመሄድ እሱነው አይደለም ብዬ አትኩሬ አየሁት በርግጥም በደሙና በስጋው እሱ እራሱ ነበር። አላህን በጣም የፈራ ሆኖ በተረጋጋ መንፈስ ስርዓቱን የጠበቀ ሶላት ይሰግዳል።
ግን ይህን ሰው ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በተሳሳተ መንገድ ያጉል ስልጣኔ እና የስሜትን ፈረስ የሽምጥ እየጋለበ በጥመትና በክህደት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቆ መውጣት ከማይችልበት ወንጀል ውስጥ በመግባት አሉ የተባሉ ደናሾችን፣ አሸብሻቢዎችን እና ተወዛዋዦችን እያሳደደ በነበረበት ወቅት ነው᎓᎓ ይህ ስራው ልክ የፍቅር መፅሐፍ ስናነብ የምናገኘውን የፍቅር ታሪክ እሱ እራሱ በውኑ የሚሰራው መስሎ ነበር የሚሰማው፡፡ ዲኑን እና አቅሉን መርሳቱን ያየች አንዷ አሸብሻቢ ደግሞ ሞኝነቱን እና የዋህነቱን በማየት የኪሱን ደም የልቡን ውሃ በመምጠጥ ፍቅሩን ሳታስጨርሰው ገፍትራ በመጣል አባራው የሰዎች ሁሉ መሳለቂያ ሆኖ በነበረበት ወቅት ነበር የማውቀው፡፡
ይህ ሰው እባክህ እያለ የሚጠራው አእምሮ _ ነበረው፡፡ ግን የአእምሮውን ጥሪ አልተቀበለውም፡፡ መካሪ ወንድሞችና ጓደኞች ነበሩት፡፡ ግን ለምክራቸው ጆሮ ዳባ ልበስ በማለቱ፡-"ምከረው ምከረው ካልሰማ መከራ ይምከረው" በማለት ለሸይጣን፣ ብሎም ለበሽታ፣ለድህነት እና ለጀሃነም አጋልጠው ተውት
ግን ያንቀን መስጊድ ውስጥ አላህን ሱ.ወ በፍርሃት እና በስርዓት ሲገዛ ሳየው በጣም ተገረምኩ፡፡ ሶላቱን ሰግዶ እስኪጨርስ ድረስ በትዕግስት ጠበኩት፡፡ ልክ ሶላቱን ሰግዶ ሲያበቃ ጠጋ ብዬ ሰላም ማለቴን አለማለቴን በቅጡ ሳላውቀው ቀጥታ ከዚህ ቦታ እንዴት ሊመጣ እንደቻለ ጠየኩት፡፡
እሱም እንዲህ አለኝ አይ አንተ የድሮ ጓደኛዬ!!» ከዚህ ቦታ አመጣጤ ብዙ አስገራሚና አስደናቂ ታሪክ አለው” አለኝ፡፡
እስኪ ታሪኩ ምን እንደሁ አጫውተኝ” አልኩት በመገረም፣

“ይህን
ታሪኬንማ እዚህ አላህ ቤት
ውስጥ ልነግርህ
ይከብደኛል መስማት ከፈለክ ወደ ቤቴ እንሂድ እና ታሪኩን ላጫውትህ” አለኝ
እኔም ታሪኩ ምን እንደሆነ ለመስማት በመጓጓት ወደ ቤቱ ተከትየው ሔድኩ፡፡
እሱም እንዲህ ሲል ታሪኩን ያጫውተኝ ጀመር
አሁን እኔ ወደ አላህ ሱ.ወ ቶብቼ መመለሴ ካላህ የተሰጠኝ ስጦታ ነው፡፡ ሰበብ ያደረገልኝ ደግሞ መስጊድ ውስጥ ያየሃቸውን ሼህ ነው አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸውና፡፡ በኝህ ሼህ ምክንያት አላህ ሱ.ወ. የጥመትና የተሳሳተ መንገድ ከተከተልን በኋላ እኔም ሆንኩ እኔን መሰል ብዙ ሰዎችን ቅኑን መንገድ ሰጥቶናል መርቶናል ለዚህም አልሃምዱሊላህ።


በርግጥ ድሮ እንደምታውቀኝ በዲናቸው ጠንካራና ብርቱ የሆኑ በርካታ የዳዕዋ ሰዎችን አውቅ ነበር፡፡ ስለብዙ ጠንካራና ዓቢድ ዑ ለማዎች ከንጉስ ፊት ቀርበው ሀቅን ከመናገር ወደኋላ ከማይሉ ለሀቅ ሲሉ ማንንም የማይፈሩ የአሊሞችን ታሪክም ብዙ ሰምቻለሁ ግን ወላሂ! ወላሂ! እልሃለሁ እንደኝህ አይነት ሼህ ጠንካራና
ጀግና ተዋውቄም አይቼም ሰምቼም አላውቅም” አለኝ᎓᎓
“ምን አደረጉ ሼሁ?! እንዲህ ልትላቸው የቻልክ?” አልኩት፡፡
ያደረጉትን አልሰማህም እንዴ?!” አለኝ፡፡
በእውነት አልሰማሁም! እባክህ ንገረኝ አኮ ምን አደረጉ?”
"በዳንስ ቤት ውስጥ ዳዕዋ አደረጉ፡፡”
“ምን?! ይህንንስ አላምንም” አልኩት
”እንዴት? እስካሁን አልሰማህም እንዴ? ከዚህች አዱኛ እርቀሃል ማለት ነዋ!᎓᎓ ወሬው እኮ በየጋዜጦች ተዘግቧል በየመንገዱም ተነግሯል ሰው ሁሉም ለብዙ ጊዜ አውርቶታል” አለኝ፡፡
ታዲያ ሼሁ በዳንስ ቤት ውስጥ ምን አይነት ዳዕዋ አደረጉ?”አልኩት፡፡
በመጀመሪያ ሼሁ ሁልጊዜ መስጊዱን ሲመለከቱት መስጊዱ ውስጥ የሚያዩዋቸው የተለመዱ ፊቶችን (ሽማግሌዎችና ጎልማሶች) ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት ግን መስጊዱ በወጣት ተማሪዎች እና በወጣት ሰጋጆች ይሞላ ስለ ነበር ሼሁ ይህ ነገር እያሳሰባቸውና እየከነከናቸው መጣ፡፡

ከእለታት እንድ ቀን ለሽማግሌዎቹና ለጎልማሶች እንዲህ ሲሉ ጠየቁ
የሰፈሩና የከተማው ወጣቶች የት ሔዱ? ሽማግሌዎች ግን ሊነግሯቸው ፍቃደኛ ባለመሆን ዝም አሏቸው ሼሁ ጥያቄያቸውን በመድገም ከዚህ መስጊድ ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት እኮ ከናንተ በበለጠ የሚመለከተው ወጣቶችን ነው᎓᎓ ታዲያ እነዚህ ወጣቶች የት ደረሱ? የት ሄዱ?” ሲሉ ጠየቁ
ሽማግሌዎችም እንግዲህ ሼሁ ይህን ያህል ካመረሩ መናገር አለብን ብለው በማሰብ እንዲህ ሲሉ ነገሯቸው፡፡
የከተማው ወጣትማ የሚያመሸው ሲኒማ ቤት፣ ዳንስ
ቤትና ቁማር ቤት ነው᎓᎓” አሏቸው፡፡
ዳንስ ቤት?! ሲኒማ ቤት?! ደግሞ ይሄ ምንድንነው?” ሲሉ ሼሁ በአግራሞት ጠየቁ
ለምን ብትለኝ ሸሁ ስለነዚህ ነገሮች አይተውም ሰምተውም አያውቁም᎓᎓
ሼሁ መልሰው ዳንስቤትና ሲኒማ ቤት ምን እንደሆነ ሽማግሌዎችን እንዲያብራሩላቸው ጠየቁ!
ከዚህ በፊት ሼሁ በዱንያ ውስጥ የሚያውቁት ነገር ቢኖር ቤታቸውን ከዚያም መስጊድ፣ ሀዲስና እንዲሁም፣ ነብዩ አንዲህ አሉ፣ አላህ እንዲህ አለ ብቻ ነበር።”
እኮ ታዲያ ሽማግሌዎች ለሼሁ ምን ብለው መለሱ? ስል በስሜት ጠየኩት፡፡


ይቀጥላል .....❤️‍🔥

Like 1⃣0⃣0⃣+♥️ካልሆነ ቀጣዩ ክፍል አይለቀቅም🚫

@Hafu_posts🪄 || ★ 𝖍𝖆𝖋𝖚 𝖕𝖔𝖘𝖙🌙
174👍21
ምሽቱ በተለይ ለብቸኞች ስንት ሀሳብ ይዞ ይመጣል መሰላችሁ.. ያላገቡት የወደፊት ዕጣፈንታቸዉን አርቀው በማየት ያብሰለስላሉ፣ የተፋቱት ፍራሻቸው ላይ ጋደም ብለው በትዝታ ባህር ዉስጥ ይዋኛሉ፣ ባል/ሚስት የሞተባቸው አልሽር አልደርቅ ያላቸዉን ቁስል ለማድረቅ ይታገላሉ ...

ሁሉን የምታይ የምታውቅ ጌታዬ ሆይ! ለከበዳቸው ባሮችህ ሁሉ ምሽቱን አግራላቸው🤲🏽
🥰37🙏107
𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭
DAILY  TIp 11 ወጣትነት የእውነት እንኑር አህባቢ የእውነት እንኑር ከዱንያው ድካም ልባችንን አሳረፈን  ለተፈጠርንበት  አላማ እንኑር وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّاليعبدون ጋኔንንና ሰውንም፥ሊገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም። አዎ አላህን በእውነት ፣በደስታ እናምልክ ከማስመሰል ርቀን ረሃ የሆነ ኑሮን እንኑር አይበቃንም ልባችን አልደከመም ?? በጣም…
DAILY  TIP12
ወጣትነት
ጌታችን
እስኪ ደግሞ ዛሬ ስለ ጌታችን አላህ   መሀሪነት እና እዝነት ትንሽ ነገር እንበል 
አላህ  እኛ ባሮቹን  በእዝነቱ ባይ ዳብሰን ኑሮ  ህይወት ከባድ ነበረች  ይሀው  ዛሬም በ እዝነቱ አለን  እንደ ወንጀሎቻችን  ቢሆንማ 
በመሬት ላይ መንቀሳቀስ  አንችልም ነበር
ጌታችን አላህ ግን  በወንጀል ፣በጥፋት ላይ ብንሆን እንኳ ወደሱ እንድንመለስ  ይፈልጋል
አይገርምም  እያጠፋ ብትሆን እንኳ  ወደሱ እንድንቃረብ የሚሻ ጌታ። ለባርያው ያለውን ውዴታ ረሱ በዚ ልናይ እንችላለን  ታድያ እኛ ወጣቶች ምን እንጠብቀለን   የአለመቱ መሪ እንዲ የሚጠብቀን ከሆነ  እኛስ  ለምን ራቅነው?? 🧐 ሰበብ አናብዛ  ወንጀሌ ነው እየልን  ይልቅ  ቀኑ ሳይሄድ  መጨረሻችን  ሳይደርስ  እንመለስ።

አቦ አላህ ያግራልን

ለባረያው አዛኝ ነው ያስገርማል  ፍቅሩ
ሁሉንም  አዋቅ  ከላይ  እስከ ሰሩ
25😢2👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❤️ የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ ❤️

🌙 ሰባኹል ኸይር / ሰባኹል ኑር



📖🎧 #ቁርኣን  || PART ❶❼

⭐️ 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭 || SHARE 😊
18
✍️የምድር ላይ ህይወትህ መፅሀፍህ ነው ፤ ነገ የትንሳኤ ቀን አላህ ፊት ታነበዋለህ፤
ስለዚህ ለህይወትህ መጥፎ ደራሲ ከመሆን ተጠንቀቅ።
👍248