Habibi Media Network
676 subscribers
323 photos
33 videos
1 file
87 links
ጥልቅ ትንታኔ፣ በዓለም ዙሪያ ይዳሰሳል! 🌍

ፅሁፎችን ወደ ድምፅ በመቀየር የመረጃ ተደራሽነትን እናረጋግጣለን። ጥልቅ ትንታኔዎች፣ ታሪካዊ ዘጋቢ ፊልሞች እና ወቅታዊ መረጃዎች።

🚩 ዝግጅቶቻችን፦ #መስታወት_አዙሪት | #የሐቅ_ፈለግ

📩 ለማንኛውም አገልግሎት ወይም አስተያየት፦
@Habibi_Media ያናግሩን።
Download Telegram
Habibi Media Network
Photo
ባለ ሁለት ፓስፖርቱ ጋዜጠኛ
==================

@HabibiMediaNetwork  (HMN) የትንታኔ ዴስክ

በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እና በነፃ ሚዲያ ግንባታ ውስጥ ጋዜጠኝነት የማኅበረሰብ ድምፅ፣ የሥልጣን ባለቤቶችን የመሞገቻ እና የእውነት ማሳወቂያ መሣሪያ ነው። ነገር ግን ጋዜጠኝነት የፖለቲካ ፓርቲ አጀንዳዎችን ማስፈጸሚያ፣ የፓርቲ መሪዎችን ከመዋቅራዊ ተጠያቂነት መከለያ እና የሕዝብን የመጠየቅ መብት ማነቆ ሲደረግ ሙያው ክብሩን ያጣል።

የኑሪያ ልጅ ጋዜጠኛ አብድልወሃብ በቅርቡ (June 30/2026) የትምህርት ሚኒስትሩን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን አስመልክቶ፦ "ፕሮፌሰር ብርሃኑን ለመተቸት ቢያንስ ማስተርስ ዲግሪ ያስፈልጋል... ሚኒስትሩ ፖለቲካዊ ውሳኔ ከመስጠት ውጭ በየትምህርት ቤቱ የሚደረገውን ቁጥጥር አይመራም፤ ተጠያቂው መንግሥት ነው" በማለት ያቀረበው ጽሑፍ፣ ከጋዜጠኝነት ሙያ ሥነ-ምግባር፣ ከፖለቲካል ሳይንስ፣ ከሶሲዮሎጂ እና ከሎጂክ ሕጎች አኳያ ከባድ መዋቅራዊ ስብራት አለበት።

ይህ ትንታኔ የጸሐፊውን የተምታቱ መከራከሪያዎች እና የቋመጠበትን "ባለ ሁለት ፓስፖርት" (ጋዜጠኛ እና የፓርቲ አክቲቪስት) በሳይንሳዊ አመክንዮ ከዚህ በታች ተፈትሾ ቀርቧል።

1⃣. የሁለትዮሽ መለኪያ (Double Standard) እና አስገራሚው የአመክንዮ ስብራት

ጸሐፊው ትናንት (July 28/2026) ባወጣው መግለጫ፦ "Ahmedin Jebel-አሕመዲን ጀበል የማይነካ አላህ አይደለም፤ እኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩንም   እተቻለሁ" ሲል ነበረ። በሌላ በኩል ደግሞ፦ "ብርሃኑ ነጋን ለመተቸት ቢያንስ ማስተርስ ዲግሪ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ ያስፈልጋል" ይላል።  ይህ ግልጽ የሎጂክ ስብራትና የሁለትዮሽ መለኪያ ነው፦

     √ የጋራ መብት ወይስ የአካዳሚክ መደብኝነት (Elitism)?
ሀገሪቱን የሚያስተዳድሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ Abiy Ahmed Ali ሆኑ ሚኒስትሮቹ በግብር ከፋዩ ሕዝብ ገንዘብ የሚከፈላቸው የሕዝብ አገልጋዮች (Public Servants) ናቸው። የትምህርት ፖሊሲው የሚጎዳው ወይም የሚጠቅመው ደግሞ ደረጃቸው ምንም ይሁን ምን ሙሉውን ማኅበረሰብ ነው።

     √ የሎጂክ ስህተት (Appeal to Authority፦
በፖለቲካል ሳይንስ እና በማኅበራዊ ሳይንስ አንድን የሕዝብ ባለሥልጣን ለመተቸት የዲግሪ መስፈርት ማስቀመጥ Gatekeeping (የሕዝብን ድምፅ የመቀማት አካሄድ) እና "Appeal to Authority" የሚባል የሎጂክ ስህተት ነው። አንድ ገበሬ ወይም የ2ኛ ክፍል ተማሪ የተበላሸ የትምህርት ሥርዓት ሲገጥመው ለመሞገት "ማስተርስ ዲግሪ" ሊኖረው ይገባል ማለት የዜግነት መብትንና የዲሞክራሲን መሠረታዊ መርህ አለመረዳት ነው።

2⃣. የጋዜጠኝነት ሙያዊ ሥነ-ምግባር እና የ"ጥቅም ግጭት" (Conflict of Interest)

ጋዜጠኝነት እና የፖለቲካ ፓርቲ አክቲቪዝም የተያያዙ ነገር ግን ፍጹም የተለያዩ ወሰኖች አሏቸው። ጸሐፊው በማኅበራዊ ሚዲያ እንደ "ነፃና ገለልተኛ ጋዜጠኛ" ሆኖ እየቀረበ፣ በተግባር ግን የኢትዮጵያ ዜጎች ለወገኔ መስመር (ኢዜማ) የተሰኘው የፖለቲካ ፓርቲ መድረክ ላይ በመቆም የፓርቲውን አመራሮች ሲከላከል ይታያል።

      √ የጥቅም ግጭት አለማስታወቅ (Failure to Declare Conflict of Interest)፦ አንድ ጋዜጠኛ የጥቅም ቁርኝት ያለበትን የፖለቲካ ፓርቲ መሪ (ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን) ሲከላከል፣ አስቀድሞ ለሕዝቡ "እኔ የዚህ ፓርቲ አባል/ደጋፊ ነኝ" ብሎ ግልጽ ማድረግ (Transparency) የሙያ ሥነ-ምግባር ግዴታው ነበር።

     √ ሕዝብን ማጨበረበር፦ የፓርቲ መሪን በጋዜጠኝነት ሽፋን ከአደባባይ ትችት ለመሸፈን መሞከር፣ የጋዜጠኝነትን ሙያዊ ሚዛን ያፈረሰ እና አየር ላይ የተቀመጠ የፓርቲ PR (Public Relations) ሥራ እንጂ ጋዜጠኝነት አይደለም። በአንድ ጊዜ የጋዜጠኛነትን ገለልተኝነት እና የፓርቲ አክቲቪስትነትን "ሁለት ፓስፖርት" ይዞ መጓዝ የሙያ ብልግና ነው።

3⃣. የመዋቅራዊ ተጠያቂነት (Ministerial Accountability) እና የፖለቲካል ሳይንስ ክሽፈት

ይህ ጋዜጠኛ "ብርሃኑ ነጋ የሀገሪቱ መሪ አይደለም፤ በሀገሪቱ ለሚፈጸመው የመብት ጥሰት ተጠያቂው መንግሥት ብቻ ነው፤ ሚኒስትሩ ፖለቲካዊ ውሳኔ ከመስጠት ውጪ እያንዳንዱን ቁጥጥር አይመራም" በሚል ያቀረበው መከራከሪያ የካቢኔ አስተዳደርን ሀሁ አለመረዳት ነው።

     √ የሚኒስትሩ መዋቅራዊ ተጠያቂነት፦ በፖለቲካል ሳይንስና በመንግሥት አስተዳደር ሕግ፣ ሚኒስትር ማለት የሥራ መስኩ ከፍተኛ አስፈጻሚ (Chief Executive of the Sector) ነው። የትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣቸው መመሪያዎች፣ የሚፈጽማቸው ስህተቶች እና የመብት ጥሰቶች በሙሉ የመጀመሪያ ተጠያቂው ራሱ ሚኒስትሩ ነው።

      √ ተጠያቂነትን ማሸሽ፦ "ሚኒስትሩ አይጠየቅም፣ መንግሥት ነው የሚጠየቀው" ማለት "የሕክምና ስህተት ለሰራው ሐኪም ተጠያቂው ሐኪሙ ሳይሆን የጤና ሚኒስቴር ነው" ብሎ እንደመከራከር ያለ የሕጻናት ጨዋታ አመክንዮ ነው። ይህ መከራከሪያ ሚኒስትሩን ከሥራው ኃላፊነት ነፃ ለማውጣት የተደረገ የፓርቲ ካድሬዎች የተለመደ የመከላከያ ስልት ነው።

4⃣. የሶሲዮሎጂ ምልከታ፦ የእውቀት የበላይነት (Epistemic Violence) እና የሕዝብ ንቀት

ጸሐፊው፦ "የዓለም አቀፍ ፕሮፌሰር ጭንቅላት በመሀይም* አይለካም... አልቅስ የሶፍት ወጪ ስፖንሰር እናደርጋለን" እያለ የተጠቀመባቸው ቃላት በማኅበራዊ ሳይንስ "Epistemic Violence" (የእውቀት የበላይነትን በመጠቀም ማኅበረሰብን ማሳነስ) ይባላሉ።

     √ የሕዝብ አገልጋይነት ምልከታ፦ ፕሮፌሰርነት የአካዳሚክ ማዕረግ እንጂ የፖለቲካ ከለላ አይደለም። በፖለቲካ ወንበር ላይ የተቀመጠ አካዳሚክ ምሁር፣ የሚዳኘው ባለው የትምህርት ደረጃ ሳይሆን ለሕዝብ በሚሰጠው አገልግሎት እና በፖሊሲዎቹ ውጤታማነት ነው።

     √ የተጠቂነትና የንቀት ቋንቋ፦ ዜጎችን "መሐይም" ፣ "የሶፍት ወጪ ስፖንሰር እናደርጋለን" እያሉ ማፌዝ፣ ጸሐፊው የሙያዊ ትንታኔ አቅም እንደሌለው እና በስሜት ታውሮ የሕዝብን ብሶት እያናናቀ መሆኑን ማሳያ ነው።

ለጋዜጠኛው የቀረቡ  ጥያቄዎች

ይህንን የተንሸዋረረ እይታንና የጸሐፊውን የእውቀት ክፍተት ለማሳየት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ልንጠይቀው እንገደዳለን፦

     1. ስለ ዲሞክራሲያዊ ተጠያቂነት፦
በየትኛው የፖለቲካል ሳይንስ ወይም የዲሞክራሲ መርህ ነው፣ የሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥን ሚኒስትር ለመተቸት "የማስተርስ ዲግሪ" መስፈርት የተደነገገው?

     2. ስለ ጥቅም ግጭት፦
የኢዜማ ፓርቲ መድረክ ላይ ቆመህ የፓርቲህን መሪ እያሞገስክ፣ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ግን እንደ "ገለልተኛ ጋዜጠኛ" ሆነህ ብቅ ማለትህ የጋዜጠኝነት ሙያ ሥነ-ምግባርን መጣስ አይደለምን?

     3. ስለ መዋቅራዊ ተጠያቂነት፦
የትምህርት ሚኒስትሩ በስሩ ባሉ ተቋማት እና ፖሊሲዎች ተጠያቂ ካልሆነ፣ የሥልጣን ወንበሩን፣ ጥቅማጥቅሙን እና ሚኒስትርነቱን ለምን ያዘው፣ መንግስትስ ሃላፊነቱን ለምን ሰጠው ?
Habibi Media Network
Photo
     4. ስለ ሁለትዮሽ መለኪያ፦
ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎች ምሁራንን እና የሃይማኖት አባቶችን ለመተቸት ምንም ዓይነት የትምህርት መስፈርት ሳታስቀምጥ፣ የራስህ የፓርቲ መሪ ዘንድ ሲደረስ ግን "ማስተርስ ዲግሪ" ማስፈለጉ፣ ጋዜጠኝነትህን ለፓርቲ ውግንና አሳልፈህ መስጠትህን አያሳይምን? (እንደማትመልሳቸው ብናውቅም ምላሽህን ግን እፈልጋለን)

#ማጠቃለያ
እውነተኛ ጋዜጠኝነት የሕዝብን መብት ማስከበር እንጂ፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን የትምህርት ማዕረግ ሽፋን በማድረግ ከሕዝብ ትችት መከላከል አይደለም። ጋዜጠኛ አብደል ወሐብ የያዘውን "የጋዜጠኛነት" እና "የኢዜማ አክቲቪስትነት" ሁለት ፓስፖርቶች ለይቶ ማወቅ አለበት። ሕዝቡም እንዲህ ያሉ የቃላት ጨዋታዎችን፣ የሁለትዮሽ መለኪያዎችን እና በጋዜጠኝነት ስም የሚደረጉ የፖለቲካ ማታለያዎችን ነቅቶ ሊገነዘባቸው እና በምሁራዊ አመክንዮ ሊሞግታቸው ይገባል።

ይችንም አንብቧት 👇
https://www.facebook.com/share/p/1DHoRJVjeN/

Habib Beshir
Habibi Media Network
Photo
🕊️ "ይቅር በል ግን አትርሳ" 🤔
ማህበራዊ ሳይንሱ ምን ይላል? በጥልቀት እንመርምረው! 📜


ሰላም የተከበራችሁ የማህበራዊ ሚዲያ ቤተሰቦቻችን! 👋 ዛሬ በህይወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ ስላላት እና ብዙ ጊዜ እንደ መፈክር ስለምንጠቀማት አባባል "ይቅር በል፣ ግን አትርሳ" (Forgive but don't forget) በጥቂቱ በምሁራዊ እይታ እና በጥልቅ ስሜት እንወያይ። 🧠❤️

ይች አባባል ከግል ስሜት ባለፈ ለማህበረሰብ ጥንካሬ እና ለፍትህ ስርአት ያላትን ሚና በማህበራዊ ሳይንስ መነጽር ስንቃኘው እጅግ አስገራሚ እውነታዎችን እናገኛለን።🧠

1⃣. የስነ-ልቦና እይታ፡ለራስ ፈውስ እና ለደህንነት መከለያ (Psychology of Healing & Safety)

ይቅርታ (Forgiveness) 🙏 = የራስ ነጻነት፦  በስነ-ልቦና ጥናት ይቅርታ ማለት የቂም እና የቁጣ ሸክምን (Cognitive load) ከራስ ላይ ማራገፍ ነው። ሸክሙ ሲወርድ ጭንቀት ይቀንሳል፣ የልብ ምት ይስተካከላል። ይቅርታ ሌላውን ሰው ነጻ ከማውጣት ይልቅ፣ የራስን አእምሮ ከቂም እስር ቤት ነጻ የማውጣት ሂደት ነው። 🔓

አለመርሳት (Not Forgetting) 🛑 = ጥንቃቄ፦  አለመርሳት ማለት ቂም በቀል ወይም ቂም መያዝ ማለት አይደለም። ይልቁንም ተሞክሮን ወደ ትምህርት መቀየር እና ራስን ከቀጣይ የስነ-ልቦና እና አካላዊ ጉዳት የመጠበቅ ሂደት ነው። አእምሯችን መጥፎ ነገሮችን የማስታወስ ተፈጥሯዊ ዝንባሌ ያለው (Negativity bias)፣ ለወደፊት ህልውናችን (Survival) ስጋት የሆኑ ነገሮችን ተጠንቅቀን እንድናልፍ እና ጠንካራ ድንበር (Boundary) እንድናበጅ ነው። 🛡️👁️

2⃣. የሶሺዮሎጂ እይታ፡ ማህበራዊ ትስስር እና ተጠያቂነት (Sociology of Cohesion & Accountability)

ይቅርታ 🤝 = ማህበራዊ ሙጫ፦ ሰዎች አብረው ሲኖሩ ግጭት አይቀሬ ነው። ማህበረሰቡ እንደቀድሞው አብሮ እንዲኖር፣ እንዲነግድ፣ እና እንዲጋባ ከተፈለገ ይቅርታ የማህበራዊ ትስስሩን ክሮች መልሶ የመጠገኛ ሙጫ ነው። ❤️🔗

አለመርሳት ⚖️ = ተጠያቂነት፦ ስህተቱን መርሳት ማለት አጥፊው ግለሰብም ሆነ ማህበረሰቡ ከድርጊቱ አልተማረም ማለት ነው። አለመርሳት የማህበረሰቡን የሞራል እና የህግ ድንበሮች የሚያጠናክር ሲሆን፣ ወደፊት ተመሳሳይ ጥፋት እንዳይከሰት እንደ ማህበራዊ ማስጠንቀቂያ ያገለግላል። 🚫

⚖️ 3⃣. የፖለቲካ ሳይንስ እይታ፡ "መቼም አይደገምም!" (Political Science & Transitional Justice)

በተለይ ከጦርነት ወይም ከጭቆና በኋላ ባሉ ማህበረሰቦች ውስጥ ይህ መርህ የ"ሽግግር ፍትህ" መሰረት ነው።

ይቅርታ 👉 ለብሔራዊ እርቅ፦ ሀገራት ወደፊት መጓዝ እና ሰላም መገንባት ከፈለጉ፣ ህዝቦች አብረው መኖር ስላለባቸው (ለምሳሌ በሩዋንዳ እና በደቡብ አፍሪካ እንደታየው) ይቅር መባባል አስፈላጊ ነው። 🇷🇼🇿🇦🕊️

አለመርሳት 🏛️ 👉 ለታሪክ እና ለፍትህ፦ የዚህ ዋነኛ አላማ "መቼም አይደገምም!" (Never Again) የሚለውን ጽኑ ፖለቲካዊ እና ሰብዓዊ አቋም ለትውልድ ለማስተላለፍ ነው።🕯️📚

🌍 የዓለም ታሪክ ትልቅ ትምህርት፦ ይቅር ብለው የረሱት መዘዝ 🤦‍♂️🤦‍♀️

በዓለም ታሪክ ውስጥ ይቅር ብለው ነገር ግን በመርሳታቸው ምክንያት እንደገና ትልቅ ችግር ያጋጠማቸው አጋጣሚዎች አሉ። ለምሳሌ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ፣ አሸናፊዎቹ ሀገራት የጀርመንን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በቸልታ በማለፋቸው (Aggressionን ይቅር ብለው በመርሳታቸው/Appeasement policy)፣ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት እጅግ በከፋ ሁኔታ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል። ታሪክን አለመርሳት ለዚህ ነበር የሚያስፈልገው! ⚔️📉

🔥 አስቡት (Assume)... 👀💭
አንድ በጣም የምታምኑት የቅርብ ጓደኛችሁ ትልቅ ክህደት ፈጸመባችሁ። እጅግ አዘናችሁ፣ ግን በመጨረሻ "ለራሴ ሰላም ስል ይቅር ብዬዋለሁ" አላችሁ። ❤️ ይሁን እንጂ፣ ያደረገውን ነገር ሙሉ በሙሉ ረሳችሁት። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያንኑ ጓደኛችሁ እንደቀድሞው አምናችሁ ትልቅ ምስጢር አጋራችሁት። እሱ ግን በድጋሚ ምስጢራችሁን አሳልፎ ሰጠው፣ ይህ ጊዜ ግን ጉዳቱ የከፋ ሆነ። 😭💔ይህንን ክህደት መርሳታችሁ እንጂ ይቅር ማለታችሁ አልነበረም የጎዳችሁ። ይቅር ብላችሁ ነገር ግን ባታረሱት ኖሮ፣ ሁለተኛ ምስጢር አታጋሩትም ነበር። አለመርሳት ጥበቃችሁ ነበር።

👉 ተራው የእናንተ ነው! 👇ውድ ቤተሰቦቻችን፣ እናንተስ በዚህ ርዕስ ላይ ምን ታስባላችሁ?"ይቅር ብላችሁ" ነገር ግን በመርሳታችሁ ምክንያት በድጋሚ ተመሳሳይ (ወይም የከፋ) ጉዳት የደረሰባችሁ ገጠመኝ አለ? 😢  ለሌሎች ትምህርት ይሆን ዘንድ ታሪካችሁን በአስተያየት መስጫው ላይ አካፍሉን። 💬

@HabibiMediaNetwork
"የሙስሊሙ አጀንዳ እየከሸፈ መሆኑ" ተገለጸ።

በሀገራዊ ምክክሩ ላይ በሚደረጉ ውይይቶች የሙስሊሙ አጀንዳ በአንድ ኡስታዝ አማካኝነት እየከሸፈ መሆኑን ከምክክር ኮሚሽኑ ሾልኮ የወጣ መረጃ አመለከተ።

ኡስታዝ ነዚፍ ከእነ ኡስታዝ ወሒድ ዑመር ጋር በማኅበራዊ ሚዲያ በቀጥታ ስርጭት ባደረጉት ውይይት ይፋ እንዳደረጉት፤ በምክክር መድረኩ ውስጥ የተገኘ ለጊዜው አንድ ስሙ ያልተጠቀሰና በፖለቲካው የገነነ ግለሰብ የሕዝበ ሙስሊሙን መሠረታዊ ጥያቄዎች በማጣጣል የውክልና ሚናውን (በእርግጥ ማን እንደወከለው አልታወቀም)  ወደ ጎን ትቷል።

በመረጃው መሠረት፣ ይህ ግለሰብ የቀረቡትን አምስት የሙስሊሙን መሠረታዊ ጥያቄዎች በመድረኩ ላይ ውድቅ አድርጓል። በተለይም ለረጅም ጊዜ መስዋዕትነት የተከፈለበትንና በትምህርት ቤቶች አካባቢ ሰፊ ትግል የተደረገበትን የኒቃብ ጉዳይ "እዚህ ግባ የማይባል" አድርጎ ማቅረቡ ታውቋል። በዚህም የተነሳ የሌላ እምነት ተከታዮች በጉዳዩ ላይ እንዲያሾፉና ኡስታዙንም "ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ እሱ ነው" በማለት እንዲያወድሱ በር መክፈቱም ተገልጿል።

ማኅበራዊ እና መዋቅራዊ ትንታኔ

ይህ ክስተት ከአንድ ግለሰብ የአደባባይ ንግግር (Public Discourse) ባለፈ፣ በማኅበረሰብ ውክልና (Social Representation) መነጽር ሲታይ ከባድ መዋቅራዊ ስብራትን ያሳያል።

አንድ ግለሰብ የማኅበረሰብ መሪ (Public Figure) ሚናን ይዞ አደባባይ ሲወጣ፣ ግላዊ አተያዩን በማኅበረሰብ የጋራ እሴት ላይ መጫኑ ተቋማዊ ህልውናን (Institutional Integrity) ይፈታተናል። ይህ ዓይነቱ የውስጥ ክፍተትን በአደባባይ ማሳየት ማኅበረሰቡን ለተቃራኒ ትርክቶች የሚያጋልጥና የመብት ጥያቄዎችን መዋቅራዊ መሠረት የሚያናጋ ነው።

ሊወሰዱ የሚገባቸው የመፍትሔ እርምጃዎች

ይህ ድርጊት ወደፊት የከፋ ማኅበራዊ ቀውስ ከመፍጠሩ በፊት፣ የሚከተሉት አፋጣኝ መዋቅራዊ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል፦

1.  የውክልና ድንበርን ማሳመር (Demarcation of Representation)፦ የሚመለከታቸው አካላት፣ ኡስታዞች እና የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ይህ ግለሰብ ማኅበረሰቡን እንደማይወክል እና አቋሙም ከኢስላማዊ መሠረቶች ጋር የሚቃረን መሆኑን በይፋ ማሳወቅ እና ከሙስሊሙ አጀንዳ ላይ "እጅህን አንሳ፤ ሙስሊሙ አልወከለህም!" የሚል ግልጽ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መሥራት።

2. ለመንግሥትና ለኮሚሽኑ ግልጽ መልእክት ማስተላለፍ፦ መንግሥትም ሆነ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ከእንደዚህ ዓይነት ግለሰቦች ጋር የሚያደርጉት ውይይት የሙስሊሙን ተቋማዊ ድምጽ እንደማይወክል በተደራጀ መልኩ ማሳሰብና ማስጠንቀቅ።

መዋቅራዊ የሚዲያ ሥራዎችን ማስፋፋት፦ አጫጭር ስሜታዊ ምላሾችን ከመስጠት ይልቅ፣ ጉዳዩን ከሥሩ የሚመረምሩ ጥልቅ ትንታኔ ያላቸውን መዋቅራዊ ዘገባዎች (Structural Reporting) እና የድምጽ ፕሮግራሞችን (Audio Features) በማስፋፋት ትክክለኛውን መረጃ ለሕዝብ ማድረስ ያስፈልጋል።

በቀጣይ ደግሞ ይህ ኡስታዝ አመተ ምህረትን እና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ በምክክር ኮሚሽኑ ውይይት ላይ ያነሳቸውን ነጥቦች ይዘን እንመለሳለ።

የቪዲዎው መረጃ እዚህ 👇 ይገኛል
https://www.facebook.com/share/v/1Btd52H64W/

@HabibiMediaNetwork
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"አመተ_ምህረት እየሱስ የተወለደበት ስለሆነ ምንም ችግር የለውም"

ፋይሉ ረዘም ስላለ ሙሉውን እዚህ መጫን አልቻልኩም። ስለዚህ የፈለገ እዚህ ገብቶ መመልከት ይችላል 👇

https://www.facebook.com/share/v/19JmkmQpCD/

@HabibiMediaNetwork
"ሒጃብ ከተፈቀደ በቂ ነው" - የኒቃብ ጉዳይ በሀገራዊ ምክክሩ፡ የተዳፈነ አጀንዳ ወይስ የስትራቴጂካዊ ትግል ጥሪ?

(HMN - ልዩ የዜና ትንታኔ እና የፖሊሲ ማሳሰቢያ)

በማኅበራዊ ሚዲያ በቀጥታ ስርጭት በተካሄደውና እነ ኡስታዝ ሙዓዝ ነዚፍን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ አካላት በተሳተፉበት የውይይት መድረክ ላይ፣ የንጽጽር ምሁሩ ኡስታዝ ወሒድ ዑመር ያቀረበው መረጃ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ በተለይም የኒቃብ ጉዳይን አስመልክቶ አዲስ አገራዊ መነጋገሪያ መሆኑ አልቀረም።

ኡስታዝ ወሒድ "ያለውን ሂደት ደርሼበታለሁ" ባለው መረጃ መሠረት፣ በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ውይይቶች ላይ የኒቃብ ጉዳይ ተገቢውን ትኩረት እንዳላገኘና እንዲያውም "ጭራሽ አታስቡት" ወደሚል ድምዳሜ እየተገፋ መሆኑ ተገልጿል። ለዚህም እንደ ምክንያት የቀረበው "ኒቃብ ግዴታ (ፈርﺽ) ነው ወይስ ሱና?" የሚለው የፊቅህ (የእስልምና ሕግጋት) ልዩነት ሲሆን፣ "አብዛኛው ሰው ሒጃብ ከተፈቀደ በቂ ነው" የሚል እምነት አለው በሚል የተሳሳተ ውክልና አጀንዳው ውድቅ እየተደረገ መሆኑን ኡስታዙ በጥልቅ ስሜት ውስጥ ሆኖ ሃሳቡን አጋርቷል።

የጸጥታና ፍተሻን ጉዳይ በተመለከተም በሴት የጸጥታ አስከባሪዎች መፈተሽ እንደሚቻል መፍትሔ ቢቀርብም፣ ጉዳዩ ሆን ተብሎ ወደ ጎን እየተገፋ መሆኑ ተነግሯል።

•••
#የማኅበራዊ_ሳይንስ_እና_የፖሊሲ_ምልከታ
ይህ መረጃ አሳዛኝ እና ልብ ሰባሪ ቢሆንም፣ የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ገና ያልተቋጨ በመሆኑ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ወደ ስትራቴጂካዊ የፖሊሲ ሙግት መሸጋገርን ይጠይቃል። ሐቢቢ ሚዲያ ኔትወርክ (HMN) ይህንን ጉዳይ ከተለያዩ አንግሎች አንጻር ሲተነትነው የሚከተሉትን መዋቅራዊ ስብራቶችን እና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፦

1⃣. መንግሥት የሥነ-መለኮት (Theology) ዳኛ አይደለም።

በአንድ ሀገራዊ የፖሊሲ መድረክ ላይ ትልቁ ስህተት "ኒቃብ ሱና ነው ወይስ ፈርﺽ?" የሚለውን የሃይማኖት ውስጣዊ ክርክር መነሻ ማድረግ ነው። በዘመናዊ የፖለቲካ ሳይንስ መንግሥት ወይም የሲቪክ ኮሚሽን የሃይማኖት ሕግጋትን የመተርጎም ሥልጣን የለውም። አንድ ዜጋ (ሙስሊም ሴት) ኒቃብ መልበስ የሃይማኖቷ አካል መሆኑን አምና ከተገበረችው፣ የመንግሥት ኃላፊነት ይህንን ሕገ-መንግሥታዊ የእምነትና ራስን የመግለጽ መብት (Freedom of Expression and Religion) ማክበር እንጂ፣ የሃይማኖት አዋቂዎችን ጠቅሶ "ግዴታ ስላልሆነ ተዉት" ማለት የብዙኃን ማንነቶች ተከታይ ከሆነ ህዝብ መሪ ወይም መንግስት የሚጠበቅ አይደለም።

2⃣. የጸጥታ ስጋት የሰብዓዊ መብት መግፈፊያ ሊሆን አይችልም

የሃይማኖት ንፅፅር ምሁሩ ኡስታዝ ወሒድ ዑመር በሰአቱ *መፍትሄው ይሆናል" ብሎ እንዳስቀመጡት፣ ማናቸውንም የጸጥታ ሥጋቶች (ማንነትን ከማረጋገጥ አኳያ) በሴት የጸጥታ አካላት ፍተሻ ማካሄድ የሚቻልበት "ምክንያታዊ መስተንግዶ" (Reasonable Accommodation) በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰራበት አሠራር ነው። የጸጥታ ፍተሻን ምክንያት በማድረግ በአለባበሳቸው ምክንያት ብቻ ዜጎችን ከትምህርት እና ከሥራ ገበታ ማግለል መዋቅራዊ መድልዎ (Structural Discrimination) ነው።

3⃣. "ሒጃብ ይበቃል" የሚለው አደገኛ የድርድር ፖለቲካ

የአብዛኛው ሰው ጥያቄ ሂጃብ ስለሆነ ኒቃብን መተው እንችላለን" የሚለው አስተሳሰብ፣ አናሳዎችን የመጨፍለቅ አደገኛ አካሄድ ነው። መብት በቁጥር ብዛት ወይም በጥቂቶች ፈቃድ የሚቸር ሳይሆን፣ ለሁሉም እኩል የሚረጋገጥ ዴሞክራሲያዊ እሴት ነው።

•••

📌 ለባለድርሻ አካላት የቀረበ ጥብቅ የፖሊሲ ማሳሰቢያ

HMN በዚህ ሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ላይ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት እንዳይሰራ ለሚመለከታቸው አካላት የሚከተለውን ጥብቅ ማሳሰቢያ ያቀርባል፦

🔹 ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) እና የኡለማ ምክር ቤት፦

የኒቃብ ጉዳይ የግለሰቦች የትርክት መጫወቻ ከመሆን ወጥቶ፣ ተቋማዊ ባለቤትነት ሊወስድበት ይገባል። "ኒቃብ የእስልምናው አካልና የሙስሊም ሴቶች ሕገ-መንግሥታዊ መብት ነው" የሚል ግልጽ የፖሊሲ ሰነድ ለምክክር ኮሚሽኑ በአስቸኳይ ማቅረብ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው። @Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

🔹 በምክክር ኮሚሽኑ ውስጥ ለሚሳተፉ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተወካዮች፦

በመድረኩ ላይ የምትወክሉት የራሳችሁን የፊቅህ ግንዛቤ ሳይሆን፣ የኒቃብ መብት ተነፍጎ ለዓመታት ከትምህርት ቤት የተባረረችውን፣ እንባዋ የፈሰሰውን እና ከሥራ ገበታ የተገለለችውን ሙስሊም ሴት ነው። ስለዚህ ጥያቄውን ከ"ሱና እና ግዴታ" ክርክር አውጥታችሁ "የዜግነት እኩልነትና የሰብዓዊ መብት" ጥያቄ አድርጋችሁ በጽናት ልትሞግቱ ይገባል።

🔹 ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን፦

እውነተኛ አገራዊ መግባባት የሚፈጠረው ሁሉም ዜጋ (አለባበሱንና እምነቱን ጨምሮ) በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ተቀባይነት ሲኖረው ነው።  የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኒቃብን ማግለል የአንድን ማኅበረሰብ አካል ከሀገራዊው ሥዕል መገንጠል መሆኑን ተገንዝቦ፣ አሳታፊ (Inclusive) የሆነ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ እናሳስባለን።
@Ethiopian National Dialogue Commission -

🔹 ለሚዲያ ባለሙያዎች እና አክቲቪስቶች፦
ከዛሬ ጀምሮ የኒቃብን ጉዳይ ከስሜታዊ ልቅሶ አውጥተን፣ በሰብዓዊ መብት፣ በሕገ-መንግሥት እና በአካዳሚያዊ መከራከሪያዎች በማጀብ ትክክለኛውን ጫና (Advocacy) መፍጠር አለብን።

🔹 ለማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች

መሰል ጉዳዮችን እየተቀባበልን (ሼር እየተደራረግን) በማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ መፍጠር መቻል ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው።

ይህ ጉዳይ የሙስሊም ሴቶች ብቻ ሳይሆን፣ የሀገሪቱ የፍትህ፣ የእኩልነት እና የዴሞክራሲ ሥርዓት መለኪያ ሚዛንም ነው።

እነ ኡስታዝ ወሒድ ኒቃብን በማስመልከት የተናገሩበት የቪዲዮ መረጃ እዚህ ጋር አለ 👇
https://www.facebook.com/share/v/1MVajarSVC/

በሽር#ኒቃብ_መብቴ_ነው #ሀገራዊምክክር #የሃይማኖትነፃነት #ኢትዮጵያ #NiqabIsMyRight #FreedomOfReligion #EthiopianMuslims #HumanRights #NationalDialogueEthiopia #HMN #HabibBeshir #UstazWahidOmer #UstazMuazNezif

ሼር ይደረግ 🔄

✍️ ሐቢብ በሽር

@HabibiMediaNetwork
🔴 የኒቃብ መብት በሀገራዊ ምክክሩ፡ የተጠለፈው አጀንዳ እና ሊወሰድ የሚገባው መዋቅራዊ የትግል መስመር!

🔴በሐቢቢ ሚዲያ ኔትወርክ (HMN) የትንታኔ ዴስክ


በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መድረኮች ላይ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ መሠረታዊ ጥያቄዎች (በተለይም የኒቃብ ጉዳይ) የውክልናን ትርጉም ባልተረዱ ግለሰቦች እየተኮላሸ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች አደባባይ መውጣታቸው ይታወቃል። ይህ ክስተት ስሜትን የሚነካ ቢሆንም፣ እኛ እንደ ማኅበረሰብ ከስሜታዊ ልቅሶ እና እርስ በርስ ከመወነጃጀል ወጥተን፣ ትግላችንን ወደ ምሁራዊ፣ ሕገ-መንግሥታዊ እና አመክንዮአዊ የፖሊሲ ሙግት ከፍ ማድረግ አለብን። ጉዳዩን በተለያዩ መዋቅራዊ ትንታኔ መነጽር ስንፈትሸው፣ አጀንዳው ለምንና እንዴት መስተካከል እንዳለበት የሚከተሉትን ዐበይት እውነታዎች እናገኛለን፦

1⃣. መንግሥት የሥነ-መለኮት ዳኛ አይደለም!

በምክክር መድረኩ ላይ የኒቃብን ጉዳይ ውድቅ ለማድረግ የተሞከረበት ዋነኛው ሰበብ "ኒቃብ በእስልምና ግዴታ (ፈርﺽ) አይደለም፤ ሱና ነው" የሚል የሃይማኖት ውስጣዊ የፊቅህ ክርክር ነው። ይህ በፖለቲካል ሳይንስ እጅግ አደገኛ የሆነ የአውድ ስብራት (Contextual Fallacy) ነው።

√ ሕገ-መንግሥታዊ አመክንዮ፦ ዘመናዊ መንግሥትም ሆነ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የሃይማኖት ሕግጋትን የመተርጎም (Theological Interpretation) ሥልጣን የላቸውም። "የትኛው ልብስ ፈርﺽ ነው፣ የትኛው ሱና ነው" የሚለው የመጅሊስ እና የኡለማዎች ድርሻ ነው።

√ የፖሊሲው ትክክለኛ መልክ፦ አንዲት ሙስሊም ሴት ኒቃብ መልበስ የሃይማኖቷ እና የማንነቷ መገለጫ መሆኑን አምና ከተገበረችው፣ የመንግሥትና የተቋማት ብቸኛ ኃላፊነት ይህንን ሕገ-መንግሥታዊ የእምነትና ራስን የመግለጽ መብት (Freedom of Expression and Religion) ማክበር ብቻ ነው። ስለዚህ የውክልና ቦታ ላይ የተቀመጡ አካላት ጉዳዩን የፊቅህ ክርክር ከማድረግ አውጥተው፣ "የዜግነት እኩልነትና የሰብዓዊ መብት ጥያቄ" መሆኑን በአመክንዮ ማስረዳት አለባቸው።

2⃣. "የጸጥታ ስጋት" የመዋቅራዊ መድልዎ ሽፋን ሊሆን አይችልም

ኒቃብን ከተቋማት (ትምህርት ቤቶች እና መሥሪያ ቤቶች) ለማግለል የሚቀርበው ሁለተኛው ሰበብ "የማንነት ማረጋገጥና የጸጥታ" ጉዳይ ነው።

√ ምክንያታዊ መስተንግዶ (Reasonable Accommodation)፦ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች መሠረት፣ የጸጥታ ፍተሻ እና የእምነት ነጻነት ሳይጋጩ አብረው ሊሄዱ የሚችሉ ጉዳዩች ናቸው። ማንነትን ማረጋገጥ ሲያስፈልግ በሴት የጸጥታ አካላት አማካይነት በተዘጋጀ ክፍት ቦታ (Private Screening) መፈተሽ እጅግ ቀላልና ዘመናዊ አሠራር ነው።

√ ይህንን አማራጭ ወደ ጎን ትቶ፣ የጸጥታ ፍተሻን ሰበብ በማድረግ ዜጎችን በአለባበሳቸው ምክንያት ብቻ ከትምህርት እና ከሥራ ገበታ ማግለል፣ በአካዳሚያዊ ቋንቋ መዋቅራዊ መድልዎ (Structural Discrimination) ይባላል። እውነተኛ አገራዊ መግባባት የሁሉንም ዜጋ ማንነት ባካተተ (Inclusive) ሥርዓት እንጂ፣ አንዱን በማግለል አይመጣም።

3⃣. አብዛኛው ሰው "ሂጃብ በቂ ነው" የሚለው የተሳሳተ የውክልና ፖለቲካ"

ብዙኃኑ ሙስሊም ሂጃብ ከተፈቀደለት በቂ ነው፣ ስለዚህ ኒቃብን እንደ አጀንዳ መተው እንችላለን" የሚለው የኡስታዝ ተብዬዎች የድርድር አቀራረብ መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ጽንሰ-ሐሳብን የካደ ነው።

√ የመብት የማይከፋፈልነት (Indivisibility of Rights)፦ የሰብዓዊ መብት በቁጥር ብዛት (Majority rule) ወይም "ይህ ይበቃችኋል" በሚል የጥቂቶች ችሮታ የሚሰጥ አይደለም። የሺህ ሴቶች ሂጃብ የመልበስ መብት መከበሩ፣ የአንዲት ኒቃብ ለባሽ እህታችንን መብት ለመግፈፍ ምክንያት ሊሆን አይችልም መብት ለሁሉም እኩል ሲረጋገጥ ብቻ ነው ፍትህ የሚባለው።

ለሕዝበ ሙስሊሙ፣ ለምሁራን እና ለዲጂታል አክቲቪስቶች የቀረበ ጥሪ!

የማኅበራዊ ሚዲያ ጩኸት አጀንዳ ሊያቀጣጥል ይችላል፤ ነገር ግን መዋቅራዊ ለውጥ የሚያመጣው የተደራጀ ምሁራዊ ተጽዕኖ (Digital Intellectual Advocacy) ብቻ ነው። ስለዚህ፦

1. ስሜትን ወደ አመክንዮ እንቀይር፦
ከዛሬ ጀምሮ የኒቃብን ጉዳይ ስናነሳ የግለሰቦችን ስም ከማጥፋትና ከመነታረክ እንውጣ። ትኩረታችንን ሕገ-መንግሥታዊ አንቀጾችን፣ ሰብዓዊ መብቶችን እና ማኅበራዊ እኩልነትን ዋቢ ባደረጉ አሳማኝ ጽሑፎችና ቪዲዮዎች ላይ ብቻ እናድርግ።

2. ተቋማዊ ባለቤትነትን እንጠይቅ፦
ጉዳዩ ከግለሰቦች እጅ ወጥቶ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) እና የዑለማ ምክር ቤት ተቋማዊ አቋም (Policy Brief) ወስደው ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በይፋ እንዲያስገቡ ጫና እንፍጠር።

3. የተሳሳቱ ውክልናዎችን በአደባባይ እንሻር፦
ማኅበረሰቡን የማይወክሉ፣ ተቋማዊ አጀንዳን በግል ስሜት የሚቀለብሱ ግለሰቦች፣ በየትኛውም መድረክ የሙስሊሙ ድምጽ እንዳልሆኑ በግልጽ እናሳውቅ።

ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት። የሁላችንም የምትሆነው ደግሞ ማንነታችን፣ እምነታችን እና መብታችን ያለ ምንም መሸራረፍ በሕግ እና በመዋቅር ሲከበርልን ብቻ ነው! መብት በምክንያት እና በጽናት እንጂ በስሜት አይመለስም!

HMN - እውነትን በመረጃ እና በአመክንዮ እንተነትናለን!

@HabibiMediaNetwork
🇪🇹 የብሔር ወይስ የእምነት ማንነት?

🇪🇹 ማህበራዊ ተቋማት (Social Institutions) የሰዎችን የእለት ተዕለት ህይወት እንዴት እንደሚቀርፁ እና አንዳንዴም እንዴት እንደሚያገልሉ ማየት ሁሌም አሳሳቢ ነው። ዛሬ የታሪክ ምሁሩ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ያነሳው ሀሳብ፣ ከአንድ ተራ የግለሰብ መብት ጥያቄ አልፎ የሀገራችንን መዋቅራዊ መሰረት (Structural foundation) የሚፈትሽ ጥልቅ ጉዳይ ነው።

Sociological Imagination እንደሚነግረን፣ በየአካባቢው በግለሰቦች እና በእምነት ተቋማት ላይ የሚደርሱ ጫናዎች የትልቁ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅር (Public Issue) ነፀብራቆች ናቸው። ኡስታዝ አሕመዲን በጥልቀት እንዳብራራው፣ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት መግቢያ ሀገራዊ ባለቤትነትን በ"ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች" ላይ ብቻ መገደቡ፣ የእምነት ማህበረሰቦችን በሀገር ግንባታው ውስጥ ሁለተኛ ደረጃ (Secondary status) እንዲይዙ አድርጓቸዋል።

ይህ መዋቅራዊ ማዕቀፍ ምን አመጣ?

🔍 1⃣. መዋቅራዊ ተጋላጭነት (Structural Vulnerability)፦ በአንቀጽ 39 የተረጋገጠው የብሔር ብሔረሰቦች መብት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማይገደብ ሲሆን፣ የእምነት መብት ግን ሊታገድ የሚችል ሆኖ ተቀምጧል። ይህ ህጋዊ ክፍተት የእምነት ተቋማትን በቀላሉ ለጥቃት ክፍትና  ተጋላጭና  ያደርጋቸዋል።

🔍 2⃣. የታሪክ እና የባለቤትነት መነጠል፦ ዜጎች ሀገሪቱን ያቆሟት በእምነት እና በሞራል እሴቶቻቸው ጭምር መሆኑን በመዘንጋት፣ ማንነትን በቋንቋ እና በጂኦግራፊ ብቻ በማጠር የእምነት ተቋማትን እንደ "መጤ" የመቁጠር አዝማሚያዎችን ፈጥሯል።

🔍 3⃣. ፍትሃዊ ያልሆነ ውክልና፦ በፖለቲካው መድረክ እውቅና የሚሰጠው ለብሔር ስብጥር ብቻ መሆኑ፣ የእምነት ማህበረሰቦች እንደ አንድ ትልቅ ማህበራዊ ሃይል ድምፃቸውን እንዳያሰሙ አድርጓል።

💡 የመፍትሄው አቅጣጫ ምንድነው?

ኡስታዝ አሕመዲን እንዳስቀመጠው ጥያቄው የመንግስት ሃይማኖት ይኑረን ሳይሆን፣ ሕገ-መንግስቱ ሲሻሻል የሀገሪቱ ባለቤቶች ብሔሮች ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ የእምነት ማህበረሰቦችም ጭምር መሆናቸው በመግቢያው ላይ በግልጽ ይካተት የሚል ነው። ይህ ሲሆን፦
√ እውነተኛ እና ሁሉን አሳታፊ የሆነ ሀገራዊ ውል (Social Contract) ይፈጠራል።

√ የትኛውም የእምነት ማህበረሰብ በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍል በነፃነት የመኖር ህገ-መንግስታዊ ዋስትና ያገኛል።

√ መስጊዶች፣ አብያተ ክርስቲያናት እና ታሪካዊ ቅርሶች ከመዋቅራዊ ጥቃት ይድናሉ።

የሀገራችን የፖለቲካ ትርክት ከብሔር አጥር ወጥቶ፣ የሁላችንንም እሴት ወደሚያከብር ሰፋ ያለ መዋቅር መሸጋገር አለበት።

ይህንን ሀሳብ እናንተስ እንዴት ታዩታላችሁ? የብሔር ፖለቲካው የእምነት ነፃነትን እና አብሮነትን እየጋረደው ነው ብላችሁ ታምናላችሁ? ሀሳባችሁን ከስር አጋሩኝ።

👇 ሙሉውን ጽሑፍ እዚህ ያገኙታል።
https://www.facebook.com/share/p/1EKJMLK1fN/

#HabibiMediaNetwork #HMN #Ethiopia #Sociology #MediaAnalysis #SocialStructure

@HabibiMediaNetwork
"ጥርሴን በዚርኮኒያ ካሰራሁ በኋላ መቃም እችላለሁ ?"
××××××××××××××××         ×××××××××××××××××
ቪዲዮው (https://www.facebook.com/share/r/19B4x37R4B/) ላይ የምትመለከቱት የህክምና ባለሙያ የምትናገረውን ስንሰማ ማመን ይከብዳል። አንድ ሰው ለአንድ ጥርሱ ከ15,000 እስከ 30,000 ብር አውጥቶ፣ እጅግ ጠንካራ የሆነውን "ዚርኮኒያ" (Zirconia) የጥርስ ጃኬት አሰርቶ... ያንን የድንጋይ ያህል ጠንካራ የሆነ ጥርስ በጫት ብቻ ፈጭቶና ጨርሶ ወደ ሀኪም ቤት ይመለሳል!

ይህንን ስንሰማ ራሳችንን የምንጠይቀው አንድ ጥያቄ አለ፦ ሰው ራሱን ምን ያህል ቢጠላ፣ ሱስስ ምን ያህል አእምሮን ቢቆጣጠር ነው በዚህ ልክ ራስን ለጥፋት አሳልፎ የሚሰጠው?

ይህ ክስተት የባለ ታሪኩ የአንድ ግለሰብ ችግር ብቻ አይደለም። በአዲስ አበባ፣ በአርባ ምንጭ፣ በዲላ፣ በከሚሴ፣ በኮምቦልቻ፣ በደሴ እና በሌሎችም ከተሞቻችን ወጣቱን ትውልድ ሽባ እያደረገው ላለው ትልቅ የማህበራዊ ቀውስ (Social Crisis) አንድ ማሳያ ነው።

ጉዳዩን ከግለሰብ ድክመት ባለፈ በጥልቀት ስንመለከተው፣ ወጣቱ ለምን ወደዚህ ማምለጫ ገባ? የሚለው ጎልቶ ይወጣል። "ስራ አጥነት፣ የተስፋ መቁረጥ ስሜት እና የጫት ሱስ በማህበረሰቡ ውስጥ እንደ "መደበኛ" (Normal) ተደርጎ መቆጠሩ፣ ትውልዱን እያስተዋለ ወደ ገደል እየመራው ነው።
ገንዘቡን አውጥቶ ጤናውን የሚገዛውም፣ ያንኑ ጤና መልሶ በገዛ እጁ የሚያጠፋውም ራሱ ወጣቱ ሆኗል። ይህ የትውልድ ብክነት ዝም ተብሎ የሚታለፍ አይደለም። መነጋገር፣ መወያየት እና መፍትሄ ማምጣት ግድ ይለናል!

* ለመሆኑ እናንተስ በዙሪያችሁ የምታዩት እውነታ እና ገጠመኝ ምንድን ነው?
*በእናንተ አካባቢ  አንድ ሰው ለአንድ ቀን ለጫት ምን ያህል ያውጣል ?

@HabibiMediaNetwork
ሸይኽ አል-ሱደይስ የመውሊድ በዓልን ማክበር ከሱና አስተምህሮ ጋር የሚጋጭ መሆኑን አስጠነቀቁ

HMN || ነሐሴ 14/2018

የመስጂደል ሐራም ኢማም እና የሁለቱ ቅዱሳን መስጊዶች የበላይ ኃላፊ ሸይኽ አብዱራህማን አል-ሱዳይስ የመውሊድ በዓልን ማክበር ከነቢዩ (ሱ.ዐ.ወ) እና ከአሱሐቦቻቸው ተግባር ጋር የሚጋጭ ተግባር መሆኑን በመግለፅ፣ ህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ ማስተላለፋቸውን Islamic Information የተሰኘው የ ፌስቡክ ገጽ ዘግቧል።

ሸይኽ አል-ሱዳይስ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ከመስጂደል ሐራም በሰጡት ጥብቅ ማህበረ-ሃይማኖታዊ መልዕክት፤ በሃይማኖቱ ስም የሚከናወኑ አዳዲስ ባህላዊ ልማዶች ከእስልምና መመሪያ እና ከሱና ስርዓት ውጭ በመሆናቸው የእስልምናን መሰረታዊ አስተምህሮ በጥብቅ መከተል እንደሚገባ አስረድተዋል።

በ ሐቢብ በሽር

@HabibiMediaNetwork
Habibi Media Network
Photo
ሙስሊሙ ማህበረሰብ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ተልዕኮ በተግባር በመኖር ሕያው አደራውን እንዲወጣ መልዕክት ተላለፈ

HMN || ነሐሴ 15/2018

የታሪክ ምሁር፣ ጸሐፊው እና ተመራማሪው ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል፤ የነቢዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ተልዕኮ መረዳት እርሳቸውን በቃል ከመውደድ ባለፈ፣ የሕይወት አቅጣጫን በሳቸው ፈለግ መቅረፅን እንደሚጠይቅ አሳሰቡ።

ምሁሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት ማህበረ-ሃይማኖታዊ  መልዕክት እንዳብራሩት፤ እውነተኛ ተከታይ መሆን የተላኩበትን ዓላማ በሕይወት ላይ እውን በማድረግ፣ የተልዕኳቸው አስቀጣይ እና የተግባር ሰው መሆንን በፅኑ የሚጠይቅ የዘወትር ኃላፊነት ነው።

ከዚሁ መሰረታዊ ሀሳብ ጋር አያይዘውም፣ የአላህ መልዕክተኛን (ሰ.ዐ.ወ) ነቢይነት ማወቅ ብቻውን በቂ አለመሆኑን የጠቆሙት ኡስታዝ አሕመዲን፤ ማወቅ በአዕምሮ ውስጥ የሚቀመጥ መረጃ ብቻ በመሆኑ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወዳጅነት ከዚያ የላቀ የተግባር መገለጫን የሚሻ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በዚህም መሰረት፣ እያንዳንዱ ሙስሊም የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ተልዕኮ በትክክል ተረድቶት እንደሆነ ወይንም እርሳቸውን በማወደስ ንግግር ውስጥ ብቻ ተድበስብሶ የቀረ ጉዳይ መሆኑን ራሱን በጥልቀት ሊጠይቅ እና ሊፈትሽ እንደሚገባ አብራርተዋል።

በተጨማሪም የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተልዕኮ በሲራ (ታሪክ) ድርሳናት ውስጥ ተዘግቶ የሚቀር እና የሆነ ጊዜ ትዝ ሲለን ብቻ የምናነሳው መፈክር ሳይሆን፣ እያንዳንዳችን በየዕለቱ በተግባር ልንተረጉመው የተጣለብን ሕያው አደራ መሆኑን በመልዕክታቸው አስምረውበታል።

በማጠቃለያ መልዕክታቸውም፣ አላህ ይህንን መለኮታዊ አደራ ከመወጣት አንፃር እውነተኛ ተከታይ እና የነቢዩን ስብዕና የተላበሰ ትውልድ እንዲያደርገን፣ በእለተ ትንሳኤም ምልጃቸውን (ሸፋዓቸውን) ለግሶ በጀነት የእርሳቸው ጎረቤት እንዲያደርገን ሲሉ ዱዓ አድርገዋል።

@HabibiMediaNetwork
ከባድ ሐዘን፣ ከባድ ህመም

إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

Indeed, to Allah we belong and to Allah we shall return

እኛም የአሏህ ነን ወደርሱም ተመላሾች ነን

ውድ ወንድሜ ሙሐመድ በሽር ወደ አኼራ ተሻግሯል። ይህን መርዶ መስማት እጅግ ከባድ እና ልብ የሚሰብር ሐዘን ሆኖብኛል።
አላህ (ሱ.ወ) ማረፊያውን በጀነተል ፊርዶስ ያድርግለት፤ የቀብር ህይወቱንም ብሩህ ያድርግለት። ለኔም ሆነ ለቤተሰቦቻችን እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ አላህ መጽናናትን ይስጠን።

ውድ ወንድሞቸ እባካችሁ በዱዓችሁ አስቡት።

እኔ ሐቢብ በሽር ስሆን ውድ ወንድሜ ደግሞ ሙሐመድ በሽር (አንጋፋው እና የቤቱ መጀመሪያ😭)

ወንድምን ያህል ነገር ሙቶ ያውም ታላቅ ወንድም... ለመጻፍም ይሁን ምንም ለማለት ይከብዳል... ግን ዱዓችሁን በመከጀል ብቻና ብቻ ነው እናም... ።

ውዱ ነብያችን (ሰ.ዓ.ወ) ወደ አኼራ ከተሻገሩበት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሰኞ ረቢል-ዓወል 11 1501 ውዱ ወንድሜ ማሜም ...
 
  ሐቢብ በሽር

@HabibiMediaNetwork
Habibi Media Network
የልብ ማህደር #8 🖼️💡 እውነተኛው ጀግና፡ ስሜትን የመግዛት ጥበብ! "እውነተኛ ጀግና (ጠንካራ) ማለት ትግል ገጥሞ ሰዎችን በጉልበት የሚያሸንፍ ሳይሆን፣ በቁጣ ጊዜ ራሱን መቆጣጠር የሚችል ሰው ነው!" (የነብዩ ሙሐመድ ﷺ አስተማሪ ንግግር) ይህ ጥልቅ ሀዲስ፣ በማህበራዊ ሳይንስና በስነ-ልቦና (Psychology) እጅግ ወሳኝ የሆነውን "ስሜትን የመቆጣጠር ብቃት" (Emotional Intelligence)…
የልብ ማህደር #9

የውቡ ትዕግስት ሚስጥር

• ከቀደምት ደጋግ ሰዎች አንዱ እንዲህ አለ፦ "ይህች ዓለም እጅግ ቀላልና የተመቻቸች ብትሆን ኖሮ፣ 'ትዕግስት' (ሶብር) ከጀነት በሮች አንዱ አይሆንም ነበር!"

• ሌላኛው ደግሞ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ፦ "ውብ የሆነው ትዕግስት (ሶብሩን ጀሚል) ምንድን ነው?"
እርሱም መለሰ፦ "በመከራና በፈተና ውስጥ ሆነህ፣ ልብህ 'አልሐምዱሊላህ ሲል ነው።"

የህይወት መንገድ ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ አይደለም። በምንጓዝበት ጎዳና ላይ እንቅፋቶች፣ የልብ ህመሞች፣ ማጣቶችና ውጣ ውረዶች ያጋጥሙናል፣ የወደድነውን በማጣት፣ ያፈቀርነውን በመነሳት ልባችን ስብር ሊል ይችላል ። ምክንያቱም ይህች ዱንያ የፈተና ሀገር ናትና።

ነገር ግን እነዚህ ፈተናዎች ትዕግስትን ተላብሰን የጀነትን በር እንድናንኳኳ የተሰጡን የወርቅ ቁልፎች መሆናቸውን ስንቶቻችን እናስተውል ይሆን?

ብዙ ጊዜ መከራ ሲገጥመን፣ ሃዘን ሲደራረብብን እናማርራለን፤ አካላችን ብቻ ሳይሆን ልባችንም ይደክማል። እውነተኛውና "ውቡ ትዕግስት" ግን መከራውን አለመሰማት፣ ወይም ስሜት አልባ መሆን አይደለም። ይልቁንም ህመሙና ፈተናው ውስጥ ሆነንም፣ ልባችን በፈጣሪ ውሳኔ ረክቶ በውስጥ ሰላም "አልሐምዱሊላህ" ማለት መቻሉ ላይ ነው።

#አልሐምዱሊላህ

@HabibiMediaNetwork
በዘርፉ እውቀቱ ያላችሁ ለስራ ትፈለጋላችሁ
👇
https://www.facebook.com/share/p/17MByuuDJj/