ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
15.1K subscribers
617 photos
41 videos
1 file
81 links
ምንም አይነት መፅሀፍ ይዘዙን ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናመጣሎታለን፡
በሚያስገርም "ከ10-50%" በሆነ የዋጋ ቅናሽ ሞክረው ይዩን በአገልግሎታችን ይደሰታሉ

Free delivery
@Guramaylebooks

@Guramayelie 0912319263
Download Telegram
የካህሳይ አብርሃም መጽሐፍ በአሲምባ የግል ታሪኩ ላይ ያተኮረ ነው። የታሪክ ኩርባዎቹም፦ ወላጆቹ፣ ከሱ ጋር ነፍስ የተቀባበለው ይመር ንጉሤ የተባለው ገበሬ ፤ እና አሲምባ የወለደለት ድላይ የተባለች ጓድ ፍቅረኛው፤ ናቸው። መጽሐፉ የአሲምባ ጓዶቹ ታሪክ ላይ ያተኮረ ነው። ባለታሪኩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊት (የኢሕአፓ የታጠቀ ክንፍ) ውስጥ እስከነበረበት ወቅት ድረስ፣ ያሳለፈውን ሁኔታ በመንተራሱ፤ አንድም በዚያው አካባቢ የተወለደ በመሆኑ፣ አንድም እዚያው የታገለ በመሆኑ፣ ስለትግራይ ልዩ ልዩ ስፍራዎችም በቅርበት ያስረዳናል። በኢሕአሠ ዐይን በመመልከት፤ በዚያ ክልል ይንቀሳቀሱ የነበሩትን ሌሎች ድርጅቶች ሁኔታም ያገናዝብልናል። ከቦታው፣ ከፖለቲካው እንቅስቃሴ እና ከህዝቡ አኳያ ያ ጊዜ ምን አይነት ስዕል ይታይበት እንደነበር ያስረዳናል። (ገጣሚ፣ ፀሐፊ፣ ተርጓሚ፣ ጋዜጠኛ... ነብይ መኮነን ስለመጽሐፉ ከሰጡት አስተያየት የተወሰደ)

የአሲምባ ፍቅር. በካሕሳይ አብርሃ ብስራት
የገፅ ብዛት - 439 የተለጠፈበት ዋጋ - 300 ብር
መሸጫ ዋጋ - 260 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
ከዚህ በፊት ያሳተማቸው ሶስቱ መጽሐፍት ፀረ-666፣ ሣድስ፣ እና አልፈራም በሰፊው ተወዳጅነትን ያስገኙለት ጋዜጠኛ መምህር ዐቢይ ይልማ የመጀመሪያውን መጽሐፉን ቀጣይ ክፍል ፀረ-666 ቁጥር 2 ለገበያ አቅርቦልናል። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ።

ፀረ-666 ቁ2. መ/ር ዐቢይ ይልማ
የገፅ ብዛት - 222 የተለጠፈበት ዋጋ - 280 ብር
መሸጫ ዋጋ - 200 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
ሕይወት ከባድ ነች - በጭንቀቶች፣ በውጥረት፣ በአስፈሪ ክስተቶች የተሞላች። እና ይህንን ሁሉ ጠራርጎ ለማስወገድ ምን ማድረግ ይኖርብናል? እንዴትስ እነዚህን ሁሉ ችግሮች እንደ ተራ ነገር ንቀን ልናልፋቸው እንችላለን?
ፍልስፍና ቀላል ሆኖ ሊተገበር የሚችል መፍትሄ ያቀርብልናል -
#ሜሜንቶ_ሞሪ
ሜሜንቶ ሞሪ የላቲን ሃረግ ሲሆን ትርጓሜውም “እንደምትሞት አስታውስ” ማለት ነው። አይቀሬ ስለሆነው ሞት ስታስብ ለዚህ ሁሉ ጉዳይ መጨነቄ አግባብ ነው ወይ? የሚል ጥያቄን ታነሳለህ።
የሮም ንጉስ እና ፈላስፋ የነበረው ማርክስ አውሬሊየስ ይህን ሃሳብ አጥብቆ ይወደዋል። ሞት ተፈጥሯዊ እና አይቀሬ ነው ንብረትን ለማፍራት መሮጥ፣ አለማዊ ሃብትን ማሳደድ… ይህ ሁሉ ልፋታችን ይዘነው ለማንሄደው ኮተት ነው ይለናል። አንድ ቀን አፈር እንሆናለን፤ ስለምንስ ምድራዊ ጊዜያችንን በጭንቀት ውስጥ እናሳልፋለን?
ሶቅራጠስም፣ ዘርዓ ያዕቆብም የዘመናቸው ወፈፌዎች ነበሩ። እንኳን ሊጠየቁ ሊታሰቡ እንኳ የከበዱ ጥያቄዎችን አንስተው መርምረዋል። ሶቅራጠስን ያስገደለው፤ ዘርዓ ያዕቆብንም ከአገር ያሰደደ ፍልስፍና ምንድን ነው?


ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጥስ
ትርጉም በፍሉይ ዓለም
የገፅ ብዛት - 352 የተለጠፈበት ዋጋ - 350 ብር
መሸጫ ዋጋ - 220 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
የዕውቀት ብልጭታ. ከከበደ ሚካኤል
የገፅ ብዛት - 184 የተለጠፈበት ዋጋ - 250 ብር
መሸጫ ዋጋ - 200 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263

Telegram :
t.me/guramaylebooks
Twitter :
twitter.com/guramaylebooks
Facebook :
facebook.com/guramaylebooks
IG :
Instagram.com/guramayle_books
Email :
guramaylebooks@gmail.com
መጽሐፉ የተተረጎመው በ1970ዎቹ ውስጥ ሲሆን፣ ተርጓሚው ማዕከላዊ ምርመራ ድርጅት እሥር ቤት ውስጥ ታሥሮ ሳለ የተረጎመው ነው። በዚያን ዘመን ወደዚያ እሥር ቤት ምንም ወረቀት የማይገባ ስለሆነ፣ ያለው አማራጭ በሲጋራ ወረቀቶች ላይ መተርጎም ብቻ ነበር! ልዩ የሚያደርገው ይሄ ነው። በአፃፃፉ ረገድ፣ ቃል በቃልም በአዛምዱ ትርጉምም በአንድምታ - ትርጓሜም የተቀነበበ በመሆኑ፣ አንባቢ በቀላሉ እንደሚረዳውና እንደሚረካበት እምነታችን ፅኑ ነው።
የተርጓሚ ነብይ መኮንን የእሥር ቤት ወዳጁ ስለመጽሐፉ የሰጠው አስተያየት።
Gone with the wind (ነገም ሌላ ቀን ነው) ከብዙ አመታት በፊት በነብይ መኮንን ተተርጉሞ ለንባብ የበቃ ምርጥ ረጂም ልብወለድ ነው።


ነገም ሌላ ቀን ነው ትርጉም ነብይ መኮንን
የገፅ ብዛት - 507 የተለጠፈበት ዋጋ - 350 ብር
መሸጫ ዋጋ - 300 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ከኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነጥሎ ማየት ይከብዳል፡፡ ቤተክስርቲያኒቱ ለኢትዮጵያ ህልውና ዋጋ ብትከፍልም ለውለታዋ ጥርስ እንዲነከስባት ሆናለች፡፡
ለመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክስርቲያን በምን ምክንያት ጥርስ ተነከሰባት? ውለታዋና በደሏስ ምንድነው?
እስልምና፣ ወንጌላውያን እና ካቶሊክ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጋር የነበራቸው ሙግት በአስደናቂ ሁኔታ በመጽሐፉ ውስጥ ተዳስሷል፡፡ በሙግቱ ማን ረትቶ ይሆን?
ላሊበላ ሶስት ቀናት ሞቶ የተገለጠለት አስገራሚ ሚስጥርም ተካትቶበታል፡፡ ብዙም ያልተነገረለት ላሊበላ ሞቶ የተገለጠለት ምስጢር ምን ይሆን?
ታቦተ ፂዮንን በአይናቸው ያዩት አጼ ኢያሱን ጨምሮ የጥቂት ሰዎች ምስክርነት በሚገርም ሁኔታ በመጽሐፉ ላይ ሰፍሯል፡፡ ታቦተ ፂዮንን በአይናቸው ያዩ ሰዎች ምን ተናረው ይሆን?
ኦርቶጵያ መጽሐፍ የሚነግረን ብዙ አስገራሚ ታሪኮች አሉ፡፡


ኦርቶጵያ ትርጉም ራሴላስ ጋሻነህ
የገፅ ብዛት - 352 የተለጠፈበት ዋጋ - 350 ብር
መሸጫ ዋጋ - 220 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
ስለሃገሩ ተናግሮ አይጠግብም ሃገር በቀል እውቀቶች ላይ ብዙ ለፍቷል ኢትዮጵያዊነት በደምስሩ ውስጥ ገብቷል። ይጠቅማል ያላቸውን እውቀቶች፣ኢትዮጵያዊ ፍልስፍናዎች ሳይደክም ለትውልዱ ዘርቷል አሁንም እየዘራ ይገኛል።በሃይማኖቱ ድርድር አያውቅም ሃሰተኞችና አላዋቂዎችን ይሞግታል ።ዘረኞች እጅግ አብዝተው ይጠሉታል ። ኢትዮጵያዊነት ላይ ያጠነጠኑ በዙ አጫጭር ስልጠናዎችን ሰጥቷል።ላመነበት ጉዳይ ወደ ኋላ አያውቅም።
መምህር ፋንታሁን ዋቄ ።
አሁን ላይ ያየውን የምእራቡን እሳቤ ከተለያዩ እይታ አንጻር አይቶ በመጽሐፍ መልክ ይዞልን ብቅ ብሏል ።
"ሥዝም ሰብዊነት /secular humanism / የልማታዊ ወንጀሎች ምንጭ" ።
ይህ መጽሐፍ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቢያነበው ያተርፍበታል። ተጽሐፈ ዲበኩሉ።


ሥዝም ሰብአዊነት ፋንታሁን ዋቄ
የገፅ ብዛት - 471 የተለጠፈበት ዋጋ - 390 ብር
መሸጫ ዋጋ - 350 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ
የሞት ፍርድ የተፈረደባት አንዲት እንስት ይቅርታ ጠይቂና የሞት ፍርዱ ይነሳልሽ ብትባል እንቢ አሻፈረኝ ትላለች፡፡
ምሕረትን እንዳትቀበል ያደረጋት፣ ሕይወቷን ያስመረረውና የሞት ጽዋውን ያሰኛት ምክንያት ምን ይሆን?
ከእስር ቤት የምትወጪበት አንድ ተስፋ ተገኝቷል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ የይቅርታ መልዕክት ፅፈሽ ይቅርታ እንዲደረግልሽና ሁለተኛ ወንጀል ላለመስራት ቃል የምትገቢ ከሆነ ከእስር ቤት እንደምትወጪ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡”
“ይቅርታ እኔ ነፃ መሆን አልፈልግም፡፡ ለሰራሁት ወንጀል ደግሞ ይቅርታ መጠየቅ አልፈልግም፡፡ በዚያ ላይ እናንተ ወንጀል ብላችሁ የምትጠሩት ወንጀል አይደለም” አልኩት፡፡ “ከዚህ ወጥቼ አንተ እንደምትለው እንደገና መኖር ብጀምር መግደሌን አላቆምም፡፡ ስለዚህ የይቅርታ ደብዳቤ ለፕሬዚዳንቱ መላክ አያስፈልግም፡፡ እኔ በመኖርም፣ በመሞት… በሁለቱም አሸናፊ ነኝ፡፡”


ማራ ትርጉም መላኩ ዓለም
የገፅ ብዛት - 206 የተለጠፈበት ዋጋ - 250 ብር
መሸጫ ዋጋ - 170 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
"ጎሹ አረጀና ልቡ ቢዘናጋ
ጉራምባ ወረደ አንበሳን ሊወጋ
ጎሹ እስከነልጁ ጉራምባ ላይ ወርዶ
ያንበሳውን ፊት ቢያይ ወደቀ ተዋርዶ።"

ደጃዝማች ካሳ ኃይሉ ‹‹ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› ተብለው ከመንገሳቸው በፊት ከግዛት ባላባቶች ጋር ካደረጓቸው ታላላቅ ጦርነቶች መካከል አንዱ የነበረው ኅዳር 19 ቀን 1845 ዓ.ም ጉር አምባ ላይ የተካሄደውን የጉራምባ ጦርነት ላይ ደጃዝማች ጎሹ ዘውዱን ከሸነፉ በኋላ የተገጠመላቸው ግጥም ነው።
ደጃዝማች ጎሹ ዘውዴ የራስ ኃይሉ ዮሴዴቅ የልጅ ልጅ (የወይዘሮ ድንቅነሽ ኃይሉ ልጅ) እንዲሁም የዳሞቱ ባላባት የደጃዝማች ዘውዴ ልጅ ናቸው፡፡ ልጃቸው ደጃዝማች ብሩ ጎሹ ከአባቱ ጋር ሆኖ ጉር አምባ ላይ ከደጃዝማች ካሣ ጋር እየተዋጋ ሳለ፣ አባቱ ደጃዝማች ጎሹ መመታታቸውን ሲያይ ሸሽቶ ዳሞት ገብቶ ነበር፡፡ በኋላም ተይዞ ድንጋይ ተሸክሞ ደጃዝማች ካሣን ምህረት ጠይቋል፡፡ ከመጽሐፉ የተወሰደ።


ዐፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት
ከተክለ ጻድቅ መኲሪያ
የገፅ ብዛት - 514 የተለጠፈበት ዋጋ - 456 ብር
መሸጫ ዋጋ - 410 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የኢድ-አል አድሃ በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን ።
ሚካኤል አስጨናቂ የጻፋቸውን ወጎችና አጫጭር ታሪኮች ለኅትመት ከመብቃታቸው አስቀድሞ አነባቸው ዘንድ ያቀረበውን ግብዣ በአክብሮት ተቀብዬ ተመልክቻቸው ነበር።
ምስክር ለመቆም በቂ ይመስሉኛል።
እጅግ መልካም የሆነ የማስታወስና የመተረክ ብቃት ያለው ማዕከላዊ ጸሐፊ (ደራሲ) ሆኖ አግኝቼዋለሁ መጽሐፉን የሚያነቡም ቢያተርፉ እንጂ እንደማይከስሩ ስምዐ - ጽድቄን አስቀምጫለሁ።
በእርግጠኝነት ተወዳጅ መጽሐፍ ለመሆን የሚቻለው ሥራ ነው። "ሸግዬ ሸጊቱ" !።!
ገጣሚ፣ ደራሲ እና ባለቅኔ ኤፍሬም ሥዩም ስለመጽሐፉ የሰጠው አስተያየት።


ሸግዬ ሸጊቱ ሚካኤል አስጨናቂ
የገፅ ብዛት - 292 የተለጠፈበት ዋጋ - 350 ብር
መሸጫ ዋጋ - 260 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
የኢትዮጵያ ታሪክ ከዓፄ ይኹኖ አምላክ እስከ ዓፄ ሱስንዮስ ከ1270 - 1632 ዓ.ም

ይህ መጽሐፍ የመካከለኛውን ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ በጥሩ አተያይ የሚያትት አዲስ መጽሐፍ ሲኾን የሰለሞናዊውን ሥርወ መንግሥት ከአነሳሱ እስከ ውድቀቱ እና በወይ ባህር ክልል የነበረውን የሙስሊሙንና የአውሮፓውያንን ፉክክር የሚዳስስ በእስታኤላዊው ፕሮፌሰር ሞርድኃይ አቢር የተፃፈ ሲሆን በበሳል የአተረጓጎም ብቃት በማውሮ አዛሪዮስ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል።

መጽሐፉ አስቸጋሪውንና ውስብስቡን የመካከለኛውን ዘመን የሚተነትንንና የዘመኑን የታሪክ ክፍተት የሚሞላ እንዲሁም የእስልምና ኃይሎች መነሳትን የኦሮሞን መስፋፋት ፣ የሰለሞናዊው መንግስት የውድቀት ምክንያቶች፣ በቀይ ባህር ዳርቻ የነበሩት የትግራይ ሹማምንቶች የአውሮፓውያንን ሽርክና በተጓዥነት ስም የሚመጡ አውሮፓውያን ስውር ፍላጎት ጭምር ተተንትኖበታል።


የኢትዮጵያ ታሪክ ከዓፄ ይኹኖ አምላክ እስከ ዓፄ ሱስንዮስ ከ1270 - 1632 ዓ.ም ተርጓሚ ማውሮ አዛሪዮስ
የገፅ ብዛት - 314 የተለጠፈበት ዋጋ - 380 ብር
መሸጫ ዋጋ - 250 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
የኢህአዴግ የማጥቃት ጦርነት በምዕራብ አምቦን አልፎ በሰሜን ዓባይን ተሻግሮ በምሥራቅ ደብረብርሃንን ተቆጣጥሮ በሁሉም አቅጣጫ ወደ ዋና ከተማይቱ እየቀረበ በሄደ ጊዜ ከፕሬዚዳንት መንግሥቱ ህዝብ የሚጠብቀው ነገር ነበር። ቢያንስ ቤተ መንግሥት ዙሪያ በታማኝነት የሚጠብቃቸውን ልዩ ብርጌድ ይዘው እስከመጨረሻው ይፋለማሉ አለበለዚያም የሶማሊያው መሪ ዚያድ ባሬ እንዳደረገው ታማኙን ጦራቸውን ይዘው ወደ አንድ አቅጣጫ ይወጣሉ ተከታይም ካገኙ ተጠናክረው ውጊያውን ይቀጥላሉ የሚል ነው። በብሔራዊ ሸንጎ አራተኛ ጉባኤ ወቅት የስብሰባው ተካፋይ የነበሩ አንድ ጳጳስ "ክቡር ፕሬዚዳንት ሁሌም ስለዚህች አገር ተንገብግበው ሲናገሩ እሰማለሁ፤ ዛሬም ብዙ ነገር ተናግረዋል፤ ህዝቡም ከጎንዎ እንደሚሆን አምናለሁ። ኢትዮጵያ የመበታተን አደጋ አንዣቦባታል። እስከመጨረሻው ሞተን ልናድናት ይገባል። ያለፉት የኢትዮጵያ መሪዎች ብዙዎቹ ጥሩ ታሪክ አላቸው። አፄ ቴዎድሮስ እጃቸውን ለጠላት ላለመስጠት ሽጉጣቸውን ጠጥተው አልፈዋል። ከእርስዎም የምንጠብቀው ይኼንኑ ነው። ብዙ ሃሜት ይሰማል አገር ጥለው ሊሄዱ ነው እያለ ሰው ያወራል። እኔ ግን እልዎታለሁ ! እዚህቹ የተቀመጡበት ወንበር ላይ ደርቀው መቅረት አለብዎት እንጂ ህዝቡን ትተው እንዳይሸሹ " ብለው ስጋታቸውን ገልጸው ነበር።

ትውልድ ያናወጠ ጦርነት ክፍል ፩ ሻለቃ ንጋቱ ቦጋለ
የገፅ ብዛት - 354 የተለጠፈበት ዋጋ - 355 ብር
መሸጫ ዋጋ - 260 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
ትውልድ ያናወጠ ጦርነት ክፍል ፪ ሻለቃ ንጋቱ ቦጋለ
የገፅ ብዛት - 334 የተለጠፈበት ዋጋ - 355 ብር
መሸጫ ዋጋ - 260 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
#የፍልስፍና_ሀሁ
እና
#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ

#እውነት_ምንድን_ነው? የሚለው ጥያቄ የምንጊዜም እንቆቅልሽ ጥያቄ ሆኖ ኖሯል፡፡ ከግሪክ እስከ ሮም፣ ከህንድ እስከ ጃፓን፣ ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ ድረስ በተለያዩ ዘመናት የኖሩ አያሌ ፈላስፎች ይህን ጥያቄ ለመመለስ እድሜያቸውን ሰውተዋል፡፡

ከሰዎች ተለይተው በየዋሻውና በየምኩራቡ እውቀትን ክፉኛ ቢሹም፣ እስካሁን ሁሉንም የሚያስማማ መልስ ሊገኝ አልቻለም፡፡ ይሁንና የሁሉም መልስ ደግሞ ስህተት ነው ለማለት አይቻልም፡፡ ሁሉም የየራሱ እውነት አለውና፡፡ ፍለጋው አሁንም ቀጥሏል፡፡ ሁለቱም መጽሐፍት #የፍልስፍና_ሀሁ እና #ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ ደግሞ አብረውን እውነትን ይፈልጋሉ፡፡

ፍጥረትና ህይወት ከየት ተገኘ?
የምንኖረው ለምንድን ነው?
የህይወት የመጨረሻው አላማ ምንድን ነው?
ለምን ወደዚህ ምድር መጣን?
ወዴትስ እንሄዳለን?

እነዚህና ሌሎች አያሌ ጥያቄዎች የእውነትን እውነተኛ መልስ ይጠብቃሉ፡፡ ዴስካሬት በፕላቶ መልስ ቢስቅም፣ ሩሶ በስፒኖዛ ፍልስፍና ቢበሳጭም፣ ፓይታጎራውያን በኢፒስኩሮሶች ቢያፌዙም፣ ሁሉም ግን በአንድ ነገር ብቻ ፈጽሞ ይስማማሉ፡፡

#የመጨረሻው_የጥበብ_ፍለጋ ፍልስፍና መሆኑን፡፡

#የፍልስፍና_ሀሁ እና #ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ መጽሐፍት ስለ ፍልስፍና አስደናቂና አዝናኝ ጉዞ ይተርካሉ፡፡

ከአቴንስ እስከ ኤፌሶን፣ ከለንደን እስከ ፓሪስ፣ ከንጉስ እስከ ባሪያ በተለያየ ዘመን የኖሩ አለምን የቀየሩ ፈላስፎችን በር ያንኳኳሉ፡፡ መሰረታዊ ፍልስፍናን ማወቅ አለብኝ ለሚልና የኢትዮጵያንና የአለምን ፍልስፍናን ለተጠማ አንባቢ እነዚህ መጽሐፍት ትልቅ ገጸ በረከቶች ናቸው፡፡

ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጥስ 220 ብር
የፍልስፍና ሀሁ 220 ብር
ይህ መጽሐፍ የታላቁ ንጉሰ ነገስት የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ እና የኢትዮጵያን ታሪክ የያዘ ትልቅ ቅርስ ነው። መጽሐፉ በውስጡ የያዛቸው እጅግ በርካታ የኢትዮጵያ ታሪክ ውጣ ውረዶች አሉት። በዚያ አባጣ ጎርባጣ በበዛበት ጉዞ ውስጥ ጃንሆይ ከልጅነት ዘመናቸው ጀምሮ እስከ ስደታቸው ያለው ታሪክ በውብ የአፃፃፍ ቴክኒክ ተደራጅቶ እነሆ ለዳግም ንባብ በቅቷል።
በዚህ መፅሐፍ ውስጥ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ፀንታ እንድትቆም ልጆችዋ እና ንጉሰ ነገስትዋ የተጓዙበትን ረጅም መንገድ እና የከፈሉትን መስዋዕትነት የሚዘክር የአንድ ታላቅ ንጉስን ብዕር እናነባለን። ድንቅ መጽሐፍ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው እና በቤቱ የመጽሐፍት መደርደሪያ ላይ ሊኖሩት የሚገባ ነው። ጋዜጠኛ እና አርታኢ ጥበቡ በለጠ ስለመጽሐፉ የሰጠው አስተያየት።


ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
የገፅ ብዛት - 284 የተለጠፈበት ዋጋ - 460 ብር
መሸጫ ዋጋ - 390 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
Audio
"ኢትዮጵያዊነት"
ከአንዷለም ቡኬቶ የማህበራዊ ገጽ የተወሰደ።
በዚህ አስከፊ ጊዜ የሀገራችንን ስም በጥሩ ላስነሱ አትሌቶቻችን ክብር ይገባቸዋል። 💚💛❤️
እንኳን በሰላም ለሀገራችሁ አበቃችሁ። 🙏🙏🙏