ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
14.6K subscribers
622 photos
41 videos
1 file
79 links
ምንም አይነት መፅሀፍ ይዘዙን ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናመጣሎታለን፡
በሚያስገርም "ከ10-50%" በሆነ የዋጋ ቅናሽ ሞክረው ይዩን በአገልግሎታችን ይደሰታሉ

Free delivery
@Guramaylebooks

@Guramayelie 0912319263
Download Telegram
ቴዎድሮስ እንዲህ ሲል ጀማነሽን ይጠይቃል ፦ ህይወት እና ሞትን እንዴት ነው በንፅፅር የምታያቸው? ስለየቱ (ከሞትና ከሕይወት) ማወቅ ነው የበለጠ የሚያረካሽ?

ጀማነሽም ስትመልስ እንዲህ ባማረ አገላለጽ ነበር ፦

ለእኔ በሰው ልጅ የኑሮ ዘመን ውስጥ ሕይወትና ሞት እኩል መሳ ለመሳ አብረው የሚሔዱ ነገሮች ናቸው። የሰው ልጅ ብዙ የሚቸገረውና የማይሆን ጉዳይ ውስጥ የሚገባው ሞቱን እየረሳ ነው የሚመስለኝ። ሞታችንን ብናውቅ ነገ ጥለነው ለምንሔደው አለም መተናነቅና መዋጋት ውስጥ አንገባም ነበር። የጀርመን ተረት ይመስለኛል "ልጄ ሆይ እንደምትኖር ሆነህ ስራ እንደምትሞት ሆነህ ኑር" ይላል። ሞትና ሕይወት እኩል አንድ ቀን ነው የተሰጡን፣ ሁለት ገጽታዎቻችን ሆነው።

ጀማነሽ የሰጠችው መልስ ሁላችንም ሕይወት ላይ የሚሰራ ነውና እንደምንሞት ሆነን እንኑር።

ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ በዚህ መጽሐፉ የሀገራችንን ታላላቅ ሰዎች ጥሩ ጥሩ ጥያቄዎች እያነሳ ያፈላስፋቸዋል የተጠያቂዎቹ መልሶችም ማለፊያ የሆኑ የፍልስፍና ሃሳቦ አሏቸው ያንብቡት ይወዱታል።

ታዲያ መጽሐፉን ሲፈልጉ ከስራ መልስ ያለዎትን የእረፍት ጊዜ በየመጽሐፍ መደብሩ መጽሐፍ በመፈለግ አያባክኑት እርስዎ ቤትዎ ሁነው አረፍ ይበሉ እና ይደውሉልን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ቤትዎ በር ድረስ እናመጣልዎታለን ኸረ እንደውም ከመጽሐፉ ዋጋ ላይም ቅናሽ እናደርግልዎታለን።


ፍልስምና ፩፣ ፪፣ ፫
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
የገፅ ብዛት - 327 የተለጠፈበት ዋጋ - 300 ብር
መሸጫ ዋጋ - 200 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263

Facebook :
facebook.com/guramaylebooks
IG :
Instagram.com/guramayle_books
ሉባር መጽሐፍ የተፃፈበት ማራኪና ልዩ የአፃፃፍ ስልት ለወደፊቱ የኢትዮጵያ ሥነ-ፅሑፍ ራሱን የቻለ ጉልህ አስተዋፅኦ ያደርጋል። ድርሰቱ የተፃፈበት ቅኝት እጅግ ተወዳጅ ከመሆኑ የተነሳ በአንባቢያን ልብ ውስጥ በርካታ ዘመናትን እንዲሻገር ያደርጋል። ደራሲው መምህር በረደድ ገዳሙ በብዙ ደራሲዎች ዘንድ ያልተለመደውን እና ያልተደፈረውን በርካታ ዘውጎችን በአንድ ቅኝት አግባብቶና አጣጥሞ አንድ ወጥ የሆነ ድርሰት በመክተብ አንባቢያን የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ችሏል።

በሉባር መጽሐፍ ውስጥ ታሪክ፣ እውቀት፣ ባህል፣ ፍልስፍና፣ ማህበራዊ ሕይወት፣ እምነት፣ ጥበብና ምስጢር በሚጣፍጥ ለዛና ውበት ፍሰታቸውን ጠብቀው፣ ስሜት በሚሰጠው ንፁህ መለኮታዊ ፍቅር ታሽተውና ተለውሰው ዘምረውበታል።

በዚህ ልብ አንጠልጣይ ድርሰት ውስጥ የተሳሉት በታሪክና ገጠመኝ የተካኑት፣ በድንቅ የሕይወት ፍልስፍና የታጀቡት፣ ኢትዮጵያዊ ለዛና ውበትን የተጎናፀፉት ጥንዶች (ማክዳና ሰሎሞን) እጅግ አስተማሪና ጣፋጭ ገፀ ባህሪን ከመላበሳቸው የተነሳ ለትውልድ የምንጊዜም ተምሳሌት ሆነው እንዲኖሩ ያስችላል። በሉባር ውስጥ ያለው የሀገር ፍቅር፣ የሀሳብ ፍሰት፣ የቋንቋ አጠቃቀም፣ የቃላት ሀብት ክምችት፣ ኢትዮጵያዊ ለዛና ውበት ተደማምሮ ድርሰቱን በማንኛውም ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ እንዲኖረው ያስችሉታል።

በጥቅሉ ሉባር ታሪክን ከወቅታዊ ክስተት፣ ፍልስፍናን ከነባራዊ ሁነት፣ ስልጣኔን ከባህልና ወግ ጋር አግባብቶና አጣጥሞ በፍቅር ቅኝት ሞሽሮና ገምዶ የያዘ፤ ትውልድና ሀገርን ለመታደግ ታልሞ የተፃፈ፤ እንደ ስሙ ቅዱስና ከፍ ያለ የሀሳብ ልዕልናን የተጎናፀፈ ድንቅ መጽሐፍ ነው። በአጠቃላይ ሉባር በእጅጉ የተዋጣለትና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቢያነበው ብዙ ያተርፍበታል ብዬ ከልብ ከምጋብዛቸው መጻሕፍት መካከል ግምባር ቀደም ነው።”
#ዶ/ር መስፍን ወጋየሁ
ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ


ሉባር ከበረደድ ገዳሙ እሸቴ
የገፅ ብዛት - 352 የተለጠፈበት ዋጋ - 250 ብር
መሸጫ ዋጋ - 225 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263

Telegram :
t.me/guramaylebooks
Twitter :
twitter.com/guramaylebooks
Facebook :
facebook.com/guramaylebooks
IG :
Instagram.com/guramayle_books
Email :
guramaylebooks@gmail.com
ውድ የጉራማይሌ ቤተሰቦች ለኢትዮጵያ ህጻናት የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል ላለፉት አመታት ያለማቋረጥ ስናደርገው የነበረውን ድጋፍ እስከዛሬ ድረስ የማረጋገጫ ቴክስት ለእያንዳንዳችሁ ስናደርስ እንደነበር የሚታወቅ ነው ከዛሬ ጀምሮ ግን ያን ቴክስት መላክ አልቻልንም 6710 ላይ እንደዛ አይነቱ አገልግሎት ስለተቋረጠ ከዚህ በኋላ ቤተሰቦቻችን ከሚገዙት መጽሐፍ እናደርግ የነበረውን ድጋፍ ሰብሰብ እያደረግን ቀጥታ ወደ ልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል ገቢ የምናደርግ ይሆናል። ጉራማይሌ መጽሐፍት!!!
እንኳን ለጌታችን መደሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
አለማወቅ ዳዊት ወንድማገኝ (ዶ/ር)
የገፅ ብዛት - 352 የተለጠፈበት ዋጋ - 350 ብር
መሸጫ ዋጋ - 310 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263

Telegram :
t.me/guramaylebooks
Twitter :
twitter.com/guramaylebooks
Facebook :
facebook.com/guramaylebooks
IG :
Instagram.com/guramayle_books
Email :
guramaylebooks@gmail.com
ክርስቶስ ወ ገብረክርስቶስ

እዩት ይሔን ጠቢብ
ሸራው እስኪደማ፡ በቀይ እየወጋ
በደም እየሣለው፡
እንጨት አመሳቅሎ፡ ዳግም ክርስቶስን
ጨርቁ ላይ ሰቀለው፡፡
ቀራንዮ ሆነ የወጠረው ሸራ፡
ጎለጎታ ሆነ የወጠረው ሸራ፡
አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ፡፡
ደም ከደም አረገው አበዛበት ጣር
ብሩሹን አሹሎት እንደ ጎኑ ጦር፡፡
እየወጋ ሣለው፡ በጣም ጨከነበት፡
ገብረክርስቶስም ክርስቶስ ላይ ከፋ፡
የቆዳው ዓይነቱ በደም ተከልሎ ዘሩ እስከሚጠፋ
እየወጋ ሣለው፡ እየሣለ ወጋው፡
ዘሩ እስከማይለይ መልኩ ዝም ብሎ
ደሙ እስከሚናገር፡
የትም ያለ ፍቅር እንዳይኖረው አገር፡
እንዳንለው ፈረንጅ እንዳንለው ጥቁር፡
እንዳንለው ቀይ፡
በመስቀል ላይ ሞቶ ያየውን ስቃይ
በቆዳ በቀለም እንዳናሳንሰው
በደሙ ተሰቅሎ ሰው ያዳነውን ሰው፡፡
ከቀናት ባንዱ ዕለት፡
ሰዎች ሲሟገቱ በቀለሙ ጉዳይ፡ ሲከራከሩበት
በተመፃዳቂ የምሑር አንደበት፡
ባንዱ አፍ ሲጠቁር፡
ባንዱ አፍ ሲነጣ፡
መታገስ አቃተው ሠዓሊው ተቆጣ!
ሥሜቱ ገንፍሎ በብሩሽ ጫፍ ወጣ፡፡
ሐሣቡን የሚገልፅ ቀለም እስከሚያጣ፡
ሸራ ላይ ሰቀለው እንጨት አመሳቅሎ፡
አልወጣልህ አለው ፍቅርን ሥሎ ሥሎ፡፡
ሥሎ---ሥሎ----ሥሎ፡
ፍቅርን ሥሎ ሥሎ፡
በሣለው እየወጋ፡ በደማው እየቀባ፡
'ክርስቶስ ደሙ እንጂ ዘሩ አልተሰቀለም
እንጨቱ ላይ ያለው ዕውነት ይሔ አይደለም፡፡'
እያለ እስኪናገር የሥዕሉ አንደበት
ገብረክርስቶስም ለክርስቶስ 'ሚሆን ቀለም እስኪያልቅበት፡
በነጩ ሸራ ላይ እስካሁን የሚወርድ ደም አፈሰሰበት፡፡
ቀለም፡ ቀይ ቀለም
የደም ቀለም፡ የጥላ ቀለም
የሁሉም ነው'ንጂ የማንም አይደለም፡
ፍቅር ዘር አይደለም።

ለሠዓሊና ገጣሚ ገ/ክርስቶስ ደስታ የተፃፈ ከቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ)
ለመላው ሙስሊም ወገኖቻችን ሁሉ፣
እንኳን ለዒድ አልፊጥር በዓል አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!!!
አነጋጋሪዉ እና ቆራጡ የአለማችን ድንቅ መሪ የታላቋ ራሺያ ፕሬዝዳንትን ግለ ታሪክ መሰረት ያደረገዉ firest person ሚለዉ ድንቅ መፅሀፍ በገበያ ላይ ዋለ።
ፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ፑፒን ከልጅነት እስከ መሪነት የሂወት ጉዟቸዉ ምን እንደሚመስል መጽሀፉ ላይ በግልጽ ተቀምሯል።
#ቭላዲሚር ፑቲን የተወለዱት በሌኒንግራድ አሁን ላይ ሴንት ፒተርስ በርግ ሲህን በሌንግራንድ ስቴት ዩንቨርሲቲ የህግ ትምህርት ተከታትለዋል።
# ለ16 አመታት በኬጂቢ የዉጭ መረጃ መኮንንነት ሰርተዋል።
# ሌተናል ኮሎኔልነት ማዕረግ የደረሱ ሲሆን በ1996 የፕሬዝዳንት ቦሪስ የልሰን አስተዳደርን ለመቀላቀል ወደ ሞስኮ ተዘዋዉረዋል ።
# 1999 ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነዉ ከመመረጣቸዉ በፊት የፌደራል ደህንነት አገልግሎት (FASB) ዳሬክተርና የፀጥታዉ ምክር ቤት ፅሀፊ ሆነዉ ለአጭር ጊዜ አገልግለዋል።
ሊከድኑት የሚሳሱለት ተወዳጁ ሉባር መጽሐፍ ለሁለተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ።

ድርሰቱ ከጎንደር ፋሲለደስ እስከ ዘጌ ጊዮርጊስ፤ ከዘጌ ጊዮርጊስ እስከ ዳጋ እስጢፋኖስ፤ ከዳጋ እስጢፋኖስ እስከ ጣና ቂርቆስ፤ ከጣና ቂርቆስ እስከ ዲማ ጊዮርጊስ የተዘረጋ መሳጭ ታሪክ

ታሪክን- ከወቅታዊ ክስተት፣ ፍልስፍናን- ከነባራዊ ሁነት፣ እውቀትን - ከጥበብ፣ ስልጣኔን - ከባህልና ወግ ጋር አግባብቶና አጣጥሞ በፍቅር ቅኝት ሞሽሮና ገምዶ የያዘ መጽሐፍ፤

እንደ ስሙ ቅዱስና ከፍ ያለ የሀሳብ ልዕልናን የተጎናፀፈ መጽሐፍ ነው። ቢያነቡት በርካታ ህይወት ቀያሪ ተሞክሮዎችን ከተሟላ እርካታ ጋር ያገኙበታል።
ዐፄ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት
ከተክለ ጻድቅ መኲሪያ
የገፅ ብዛት - 708 የተለጠፈበት ዋጋ - 557 ብር
መሸጫ ዋጋ - 495 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
ዳግማዊ ምኒልክ ካህናትንና ሴቶች ሳይቀሩ ባንድነት አስተባብረው ኢትዮጵያውያንን ባንድ እግር አቁመው በአገር ወራሪ ፊት አሰልፈዋል ቀኑን ሙሉ በማዋጋት ይኸን ዓለም የተዶነቀበትን ድል ባኙበት ማታ ወደ ሰፈራቸው ሲመለሱ : አዲ ፈቂ ጐታ ላይ ወጥተው በእንዳ ሰንበት ቤተክርስቲያን ገብተው ይኸን ድል ለሰጣቸው እግዚአብሔር ምስጋና አቅርበዋል። አዲ ፈቂ በእንዳ ኪዳነ ምሕረት በመነኮሲይቶ ተራራ መካከል የሚገኝ ነው። የአዲ ፈቂም ተራራ ከባሕር ከፍታው 2062 ሜትር ነው። ከሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት ወደዚህ መሔድን የመረጡት ምናልባት ጦርነቱ የተደረገው የካቲት 23 ቀን እሑድ ስለሆነ የአዲፈቂ ቤተ ክርስቲያን እንዳ ሰንበት (የሰንበት ቤተ ክርስቲያን) ስለሆነ ዕለተ ሰንበት ‘የለቱ ለት ቀናኝ’ በሚሉ እምነት ይሆናል።

ከዚያ ወርደው ሠራዊቱ “እየገደለ ሰጠው ላሞራ!” እያለ በሆታ እያጀባቸው በደስታና በእልልታ ወደ ሰፈራቸው ደረሱ። ወደ ድንኳናቸው ገብተው በዙፋናቸው እንደ ተቀመጡ ፥ ጦርነቱን እንደ ወንድ በትጋት የተካፈሉት የሚወድዋቸው ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ በኢትዮጵያ ልማድ ለዠግና ፥ ለገዳይ እንደሚደረገው ሁሉ ንጉሠ ነገሥቱ ወደ ተቀመጡበት ዙፋን ቀርበው እጅ ነሥተው የድል አድራጊነት ምልክት የሆነውን የወርቅ ሎቲ በዦሮአቸው አንጠለጠሉላቸው።

በማግሥቱም ፥ በዓድዋና በአክሱም ዙሪያ ያሉ ካህናት ለድሉ በዓል ተሰብስበው ነበርና ምራቱ በቅድሚያ ለአክሱም ካህናት ስለተሰጠ ካህናቱ ከድጓ ውስጥ “ሞዖ ለሞት ሰዓሮ ለጣኦት ወገብረ ትንሣኤ በሰንበት” (የድጓው ትርጉም “ሞትን አሸነፈ ጣኦትንም ሻረ ፥ በሰንበትም ትንሣኤ አደረገ” ተብሎ ለጌታችን በጳውሎስ የተነረውን ለምኒልክ ለማውረስ ነው። ጢሞቴዎስ ምዕ.1 ቁ.10 ፥ ዕብ.2 ቁ.14) የሚለውን ጥቅስ ገሠው አዜሙ። ምስማክም “እንተ ቀጥቀጥኮ አርእስቲሁ ለከይሲ ወትሁቦሙ ሲሳዮሙ ለሕዝበ ኢትዮጵያ” የሚለው ከዳዊት መዝሙር ተዘመረ።

በአዲስ አበባ ገና የጦርነቱ ወሬ ሳይሰማ ውጊያውና ድሉ በተፈጸመበት ቀን የጊዮርጊስ ለት የቤተ ክርስቲያኑ አለቃ መምህር ጽጌ የሚባሉት ሊቅ የተቀኙት መወድስ ቅኔ እንዶ ትንቢት ሆኖ ተደንቆ ላቸዋል። ቅኔው ታሪካዊ ስለሆነ እንደሚከተለው አስፍረነዋል።

በሕፅነ ምኒልክ ይረፍቅ ሰማዕተ ልዕልና
ወበሕፅነ ሰማዕት ይትሐወስ አሰረ ምኒልክ ላዕክ
እስመ እም ሮምያ ፈትተ አድባረ ድንጋጼ ወሀውከ
ምኒልክ ንጉሠ አድኅኖ ዘኢዮር መልአክ
ወእግረ ምኒልክ ኢይትሐወክ
እስመ በቅድሜሁ የሐውር ጸያሔ ፍኖት ወልደ አምላክ
ቡርክትሂ ገነተ ጽጌ እስመ ውእቱ ቡሩክ
ዓለመ ምኒልክ ቀዳማዊ ዘይመጽእ ምኒልክ
ወሎቱ ሶርያ ትሰግድ ወታስተበርክ
በጽባህ እስመ ቀርበ ሙስና ሮምያ መሥዋዕተ ሠርክ

በሙሉ ሁሉን መተርጐም ምንም ያህል ስለማይጠቅም ከሙሉው አንዳንዱን ፍሬ ነገር ግዕዝ ለማያውቁ እናብራራለን። አምስተኛውና ስድስተኛው ሐረግ ፥ “ወእግረ ምኒልክ ኢይትሐወክ። እስመ በቅድሜሁ የሐውር ጸያሔፍ—ኖት ወልዶ አምላክ” “መንገድ ጠራጊው ወልደ አምላክ በፊቱ ስለሚሔድ ፥ የምኒልክ እርምጃ አይደናቀፍም” ማለት ነው ወልዶ አምላክ የራስ መኰንን የክርስትና ስም ስለሆነ መኰንን ግንባር ቀደም ጦር አዝማች እየሆኑ በአላጌና በመቀሌ እየተዋጉ ለንጉሠ ነገሥቱ የጦርነት ጉዟቸውን ያቀኑትን ለመጥቀስ ነው።

ከሁሉ የቅኔ ሐረጐች የመጨረሻው መስመር ፥ “በጽባህ እስመ ቀርበ ሙስና ርምያ መሥዋዕተ ሠርክ” “የሮማ ጥፋት እንደ ዕለት መሥዋዕት በጧት ቀርቧል” ያሉት ለባለቅኔው እንደ ደንበኛ ትንቢት ተቆጥሮላቸዋል። በእርግጥም ግንባር ቀደም ሆኖ በጧት ግሥጋሤ ደርሶ የተማረከው የዤኔራል አልቤርቶኒ ጦር የተመታውና የኢጣልያ ጦር ቅስሙ የተሰበረው ከጧቱ ላይ ስለሆነ “በጽባሕ እስመ ቀርበ ሙስና ሮምያ . . .” ብለው የጦርነቱ ዕለት የጦርነቱን ወሬ ሳይሰሙ የተቀኙትና በተግባር የተፈጸመው በትክክል ተገናኝቷል። አዲስ አበባም እንደገቡ ዐፄ ምኒልክ ይኸንኑ ሰምተው ሸልመዋቸዋል ይባላል።

🟢 🟡 🔴

ከ ተክለጻዲቅ መኩርያ
"ዐፄ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት" መጽሐፍ ላይ የተወሰደ
ስሙ መጽሐፍትን በትረካ የሚያቀርብላችሁ የሞባይል መተግበሪያ ነው። ሲፈልጉ በቋሚ ደንበኝነት ተመዝግበው ሲፈልጉ ደግሞ በአንድ ጊዜ ክፍያ አባል መሆን ይችላሉ። የብዙ ደራስያንን ስራዎች በድምጽ በመቅዳት እያቀረቡ ነው ለምሳሌ በብዙ አንባብያን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት የአዳም ረታ መጽሐፍትም ይገኙበታል።
ከዚህ በተጨማሪም የታላላቆቹ ደራስያን አለማየሁ ገላጋይ፣ እንዳለጌታ ከበደ፣ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ አንዷለም አራጌ፣ ዮርዳኖስ አልማዝ እና ሌሎችም ስራዎች ተካተውባቸዋል። መተግበሪያቸውን አውርደው ነጻ የሚለቀቁ መጽሐፍቶቻቸውን አዳምጠው ቼክ ያድርጉ እና ከወደዱት ቀጣዩ የእርስዎ ምርጫ ነው።
ጉግል ማከማቻ ፡ https://bit.ly/SemuGooglePlay
አፕል ማከማቻ፡https://apple.co/3gzblVH
ድረ-ገፅ፡ https://www.semuaudiobooks.com/
ከዚህ መጽሐፍ ገጾች የምታገኛቸው ነገሮች በከፊል፡-
በዓለማችን ታዋቂ የሆኑ ባለፈጠራ ክህሎትና ስኬታማ ሰዎች ራዕያቸውን እውን ሊያደርጉ የቻሉበትን ድብቅ ልማድ፤
ፍርኃትን ወደ ብርታት፤ ችግርን ወደ ኃይል፤ የቀድሞ ችግርን ወደ ድል መቀየር የሚያስችል ተቀዳሚ ብልኃት፤
ራሳችሁን ብርቱ በማድረግ ቸልተኝነትን አሸንፋችሁ በሥራችሁ ላይ የምታንፀባርቁበትን ብልኃት መገንዘብ፤
ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ልማዶች በመረዳት የልዕለ-ሰብ ብቃት የተላበሰ እና በሥነ-ምግባር የታነፀ ስብዕናን መላበስ፤
ነገገሮችን በቀላል መንገድ፤ በውበትና በሰላም የምትከውኑበትና ልዩ ጥበብ ማወቅ . . .
ሮቢን ሻርማ- የዓለማችን የአመራር ጥበብና የግል አቅም ማጐልበት አማካሪዎች ቁንጮ ነው፡፡ የእርሱ ደንበኞች ከሆኑት መካከል- ዓለም አቀፍ ዝነኞች፣ ቢሊየነሮች፣ የኤን. ቢ. ኤ ቅርጫት ኳስ ከዋክብት . . . . እንዲሁም ከኩባንያዎች ደግሞ ስታርባክስ፣ ፌዴክስ፣ ጀነራል ኤሌክትሪክ፣ ማይክሮሶፍት፣ ናይክ እና ቲ. ዲ. ባንክ ይጠቀሳሉ፡፡ ከ15 ሚሊዮን እትም የበለጠ የተሸጠለትና ሥራዎቹ በ 92 ቋንቋዎች ተተርጉመው የተነበቡለት ሻርማ በዓለም አቀፍ የተነባቢነት ደረጃ በሕይወት ካሉ ደራሲያን አንደኛ ነው፡፡


የጀግና ማኒፌስቶ
ሮቢን ሻርማ
የገፅ ብዛት - 370 የተለጠፈበት ዋጋ - 350 ብር
መሸጫ ዋጋ - 260 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ባህላችን አሁንም አለ አልተዘነጋም የኛ ድርሻ ማስቀጠል ብቻ ነው!!! 💚💛❤️
የካህሳይ አብርሃም መጽሐፍ በአሲምባ የግል ታሪኩ ላይ ያተኮረ ነው። የታሪክ ኩርባዎቹም፦ ወላጆቹ፣ ከሱ ጋር ነፍስ የተቀባበለው ይመር ንጉሤ የተባለው ገበሬ ፤ እና አሲምባ የወለደለት ድላይ የተባለች ጓድ ፍቅረኛው፤ ናቸው። መጽሐፉ የአሲምባ ጓዶቹ ታሪክ ላይ ያተኮረ ነው። ባለታሪኩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊት (የኢሕአፓ የታጠቀ ክንፍ) ውስጥ እስከነበረበት ወቅት ድረስ፣ ያሳለፈውን ሁኔታ በመንተራሱ፤ አንድም በዚያው አካባቢ የተወለደ በመሆኑ፣ አንድም እዚያው የታገለ በመሆኑ፣ ስለትግራይ ልዩ ልዩ ስፍራዎችም በቅርበት ያስረዳናል። በኢሕአሠ ዐይን በመመልከት፤ በዚያ ክልል ይንቀሳቀሱ የነበሩትን ሌሎች ድርጅቶች ሁኔታም ያገናዝብልናል። ከቦታው፣ ከፖለቲካው እንቅስቃሴ እና ከህዝቡ አኳያ ያ ጊዜ ምን አይነት ስዕል ይታይበት እንደነበር ያስረዳናል። (ገጣሚ፣ ፀሐፊ፣ ተርጓሚ፣ ጋዜጠኛ... ነብይ መኮነን ስለመጽሐፉ ከሰጡት አስተያየት የተወሰደ)

የአሲምባ ፍቅር. በካሕሳይ አብርሃ ብስራት
የገፅ ብዛት - 439 የተለጠፈበት ዋጋ - 300 ብር
መሸጫ ዋጋ - 260 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
ከዚህ በፊት ያሳተማቸው ሶስቱ መጽሐፍት ፀረ-666፣ ሣድስ፣ እና አልፈራም በሰፊው ተወዳጅነትን ያስገኙለት ጋዜጠኛ መምህር ዐቢይ ይልማ የመጀመሪያውን መጽሐፉን ቀጣይ ክፍል ፀረ-666 ቁጥር 2 ለገበያ አቅርቦልናል። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ።

ፀረ-666 ቁ2. መ/ር ዐቢይ ይልማ
የገፅ ብዛት - 222 የተለጠፈበት ዋጋ - 280 ብር
መሸጫ ዋጋ - 200 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263