Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
6.05K subscribers
2.46K photos
190 videos
6 files
276 links
Official Great Ethiopian Run Telegram Channel.

Call 0116635757 for more details.
Download Telegram
የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ እሁድ ሚያዝያ 18 ቀን / 2018ዓ.ም. ይካሔዳል

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቱሪዝም ሚኒስትር ጋር በመተባበር እያከናወነው ያለው የ'ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ' የስድስት ከተሞች ውድድር ዘንድሮ በደብረ ብርሃን እና ሐዋሳ የተከናወነ ሲሆን ፤ ቀጣይ አስተናጋጅ ከተማ ጅማ - ሚያዝያ 18 ቀን 2018ዓ.ም. ውድድሩን በድምቀት ታስተናግዳለች።

በ6 ከተሞች የሚካሔደው የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተከታታይ ውድድር ሶስተኛዋ መዳረሻ የሆነችው ጅማ ለ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ ዝግጅቷን በማጠናቀቅ ላይ ትገኛለች።

ይህ ውድድር ወላጆች ልጆቻቸውን በተገቢው ጊዜ ክትባት እንዲያስከትቡ የሚያበረታታውን ‘ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ’ የውድድር መልዕክት ይዞ ቀርቧል፡፡

የ15ኪ.ሜ.፤ የ5ኪ.ሜ እና የየህፃናት ሩጫዎችን ያካተተው ይህ ውድድር ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ10 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ዜጎችን እንደሚያሳትፍ ይጠበቃል። በ15ኪ.ሜ. ውድድሩ ላይ ከአዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች ወደ ጅማ የሚጓዙ ከ90 በላይ ተሳታፊዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፤ በ5ኪ.ሜ. ውድድሩ ላይ ከጅማ እና አካባቢው አትሌቶች እንዲሁም ከ4000 በላይ የጤና ሯጮች ይሳተፋሉ።

ሩጫው ከሚካሔድበት ቀን ሚያዝያ 18 አስቀድሞ ባለው ቅዳሜ የሚድሮክ ሆራይዘን ፕላንቴሽን የቡና እርሻ ጉብኝት እና የ5ኪ.ሜ. የእግር ጉዞ እና ሌሎች የጉብኝት እና የመዝናኛ ዝግጅቶች ተካተውበታል።

የዘንድሮውን ውድድር ስኬታማ ለማድረግ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት እየሰሩ የሚገኙት ውድድሩን እና ጅማ ከተማን ለማድመቅ የተዘጋጁት ኢትዮ ቴሌኮም፣ ቴሌብር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ሮተሪ ኢትዮጵያ፣ ፔፕሲ፣ ዳሽን ባንክ፣ ሚድሮክ ሆራይዘን፣ ቶፕ ውሃ፣ ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት እንዲሁም አፍራን ሆስፒታል ናቸው፡፡
15👍7
የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ ቡናን ከሩጫ ጋር አስተሳስሮ ተከናወነ

የ"ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ" (Discover Ethiopia Classics) ውድድር አካል የሆነው የ2018 የኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ ዛሬ ጠዋት በጅማ ከተማ ተካሄደ።

በውድድሩ ላይ ከ4,000 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች ተሳትፈዋል። ውድድሩን የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀድር እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች በክብር እንግድነት ተገኝተው አስጀምረውታል።

የዘንድሮው ውድድር "ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ" (End Polio Now) የሚል መልዕክትን በማስተላለፍ ለጤና ግንዛቤ ትልቅ ትኩረት የሰጠ ነበር።

ከአባ ጅፋር ቤተመንግስት ተነስተው በከተማው መሃል ፈረንጅ አራዳ ፍፃሜያቸውን ባደረጉት የ15 ኪሎ ሜትር የጤና ሯጮች ውድድር በወንዶች ጃፈር ጀማል እና በሴቶች የግሌ እሸቱ አንደኛ በመውጣት አሸንፈዋል።

በአትሌቶች መካከል በተደረገው የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶችብሩክ ዘለቀ ፣ ኦሊፈን ዲባባ እና ማዲ ሪዳ ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ሲያሸንፉ ፤ በሴቶች ዝናሽ ግዛው ቀዳሚ ስትሆን ማርሸት መላኩ እና ሊና አብዱ ተከታትለው ገብተዋል።

ዕድሜያቸው ከ16 እና ከ11 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የተዘጋጀው ውድድር በልዩ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን፣ የወደፊት ተተኪ እና ተስፈኛ አትሌቶች ታይተውበታል። በሁሉም የዕድሜ ክልል ላሉት ታዳጊዎችም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአጋር ድርጅቶቹ ጋር በመሆን ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አበርክቷል።

ጅማ የዘንድሮው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ የሩጫ ተከታታይ ውድድር ሶስተኛ መድረሻ ስትሆን፣ ቀጣዩ ውድድር በሯጮች መፍለቂያዋ በቦቆጂ ከተማ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም (May 24, 2026) ይካሔዳል።
👍43
📌 ምዝገባ በነፃ!
በሲቢኢ ብር ፕላስ ላይ ተጀምሯል ✍️

🗓 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን ግንቦት 1 ቀን ይካሔዳል

በቀላሉ በሲቢኢ ብር ፕላስ ይመዝገቡ📱

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ

ቅዳሜ - ግንቦት 1 ቀን 2018ዓ.ም. እንገናኝ!

#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun #Entoto
2
17ኛው የአውሮፓ ቀን የህፃናት ሩጫ በመጪው እሁድ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ይካሄዳል።

ይህ የሩጫ ውድድር 2,500 ህፃናት ከወላጆቻቸው ጋር የሚያሳልፉበት ልዩ ቀን ነው።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የዘንድሮው ዝግጅት ላይ ዕድሜያቸው እስከ 14 ዓመት የሆኑ ህፃናት በአራት የዕድሜ ዘርፎች ማለትም፦ ከ14 ዓመት በታች፣ ከ11 ዓመት በታች፣ ከ8 ዓመት በታች እና ከ5 ዓመት በታች ተከፋፍለው ይወዳደራሉ።

የአውሮፓ ቀን የህፃናት ሩጫ ማህበራዊ ተሳትፎን፣ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን እና ማህበረሰባዊ ትስስርን የሚያበረታታ ዋና ዓመታዊ ኩነት ሆኗል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን አጋርነት ለማጠናከር፣ ለባህል ልውውጥ እና ለእውቀት ሽግግር እንደ አስፈላጊ መድረክ ያገለግላል። ዝግጅቱ ቤተሰቦችን፣ ትምህርት ቤቶችን እና ድርጅቶችን በአንድነት እና በደስታ መንፈስ ያገናኛል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኤምስበርገር ከዝግጅቱ አስቀድሞ ባስተላለፉት መልዕክት የዕለቱን አስፈላጊነት ሲገልጹ፡- “በአውሮፓ ቀን የምናከብረው የጋራ እሴቶቻችንን ብቻ ሳይሆን የወጣቶችን ጉልበት እና አቅም ጭምር ነው። በአዲስ አበባ የሚካሄደው የአውሮፓ ቀን የህፃናት ሩጫ ማህበረሰቦችን፣ ትምህርት ቤቶችን እና አጋሮችን በማቀናጀት አሳታፊነትን፣ ጤናን እና ወዳጅነትን ያበረታታል። እነዚህ ህፃናት የወደፊቱ የአውሮፓ ህብረት እና የኢትዮጵያ ትብብር በተስፋ፣ በአንድነት እና ለሚቀጥለው ትውልድ በሚፈጠሩ ዕድሎች ላይ የተገነባ መሆኑን ያስታውሱናል” ብለዋል።

ልጆቻቸውን ማስመዝገብ የሚፈልጉ ወላጆች እና አሳዳጊዎች አሁንም በቦሌ ዓለም ሲኒማ እና ላምበረት በሚገኘው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።
11👍9🔥1
17ኛው የአውሮፓ ቀን የህፃናት ሩጫ ተካሄደ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 17ኛው የአውሮፓ ቀን የህፃናት ሩጫ ዛሬ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል። በዕለቱ ከ2,000 በላይ ህፃናት ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን የሩጫውን ውድድር እና ልዩ ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን በደስታ አሳልፈዋል።

ይህ የህፃናት ሩጫ ዕድሜያቸው እስከ 14 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎችን ያሳተፈ ሲሆን፣ ተሳታፊዎቹ በአራት የዕድሜ ዘርፎች ማለትም ከ14፣ ከ11፣ ከ8 እና ከ5 ዓመት በታች ተከፋፍለው የሜዳ ላይ ፉክክር አድርገዋል። ዝግጅቱ ለህፃናቱ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ከማስተማሩም በላይ አዳዲስ ጓደኞችን የሚያፈሩበት እና ከወላጆቻቸው ጋር የማይረሳ ጊዜ የሚያሳልፉበት መድረክ ሆኖ ተጠናቅቋል።

የዘንድሮው ዝግጅት ከዓለም አቀፍ የእናቶች ቀን ጋር መገጣጠሙ ለዕለቱ ልዩ ድምቀት ሰጥቶታል። ተሳታፊ ህፃናት ለእናቶቻቸው ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር እና አክብሮት በልዩ ልዩ ስነ-ስርዓቶች የገለጹበት ሲሆን፣ በደስታ እና በቤተሰባዊ ፍቅር የታጀበው ይሄው አከባበር የህፃናቱን ስፖርታዊ ውድድር ይበልጥ ትርጉም ያለውና ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክር እንዲሆን አድርጎታል።

የአውሮፓ ቀን የህፃናት ሩጫ በየዓመቱ የሚካሄድ ትልቅ ኩነት ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን ጠንካራ ወዳጅነት በስፖርት እና በባህል ልውውጥ ማክበር ነው። በዛሬው ዕለትም ህፃናቱ በስፖርት አካዳሚው ሜዳ ላይ ያሳዩት ተሳትፎ እና ስፖርታዊ ጨዋነት የዝግጅቱን ስኬታማነት አረጋግጧል።

በሩጫው ማጠቃለያ ላይ በሁሉም የዕድሜ ዘርፎች ለተሳተፉ ህፃናት ሜዳሊያ የተሰጠ ሲሆን፣ አሸናፊ ለሆኑት ደግሞ ልዩ ሽልማቶች ተበርክተዋል።
👍86
📌 ምዝገባ ነገ ማለዳ 12:00 ሰዓት ላይ ይጀምራል! 

በቀላሉ በሲቢኢ ብር ፕላስ በነፃ ይመዝገቡ ✍️ 

🗓 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን ግንቦት 29 ቀን ይካሔዳል

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ

ቅዳሜ - ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም. እንገናኝ!

#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun #EntotoPark
👍62
📌 የዚህ ወር የእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ምዝገባ ላይ ነን! 🔖

በቀላሉ በሲቢኢ ብር ፕላስ በነፃ አሁኑኑ ይመዝገቡ 📲

🗓 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን ግንቦት 29 ቀን ይካሔዳል

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ

ቅዳሜ - ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም. እንገናኝ!

#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun #Entoto
7👍3
ግንቦት 29 - በእንጦጦ ፓርክ በመገኘት ቅዳሜ ጠዋትን ከኃይሌ ጋር ያሳልፉ 🤩!

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ላይ ለመሳተፍ እስካሁን ካልተመዘገቡ አሁኑኑ በሲቢኢ ብር ፕላስ በነፃ ይመዝገቡ!

#EntotoCBERun #GreatEthiopianRun #VisitAddisAbaba
7🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ኃይሌ የቅዳሜ ቀጠሯችሁን በእንጦጦ ፓርክ እንድታደርጉ ይጋብዛችኋል! 🤩

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ

#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun
👍63🔥2