Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
6.05K subscribers
2.45K photos
190 videos
6 files
276 links
Official Great Ethiopian Run Telegram Channel.

Call 0116635757 for more details.
Download Telegram
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የ4 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም.

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ በተሰኘው የ2018 ሶፊማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. የበጎ አድራጎት ዘመቻው አማካኝነት ያሰባሰበውን 4 ሚሊዮን ብር በቼሻየር ኢትዮጵያ መናገሻ ቢሮ በተከናወነ ደማቅ ስነ-ስርዓት ለተመረጡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረክቧል።

በዘንድሮው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማት ቼሻየር ኢትዮጵያተስፋ ማህበራዊና ልማት ማህበርየኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን እና እዘነት አካል ጉዳተኞች ህፃናት እና ወላጆች መርጃ ድርጅት በኢትዮጵያ ናቸው።

​በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባስተላለፉት መልዕክት "ዛሬ ማዕከሉን ተገኝቼ በመጎብኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል ፤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴው ባሻገር ህዝብን ከማስተሳሰር ባለፈ፣ ችግረኞችን ለመርዳት የሚያደርገው ጥረት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር ነው።በቀጣይም ሌሎች በርካታ ተቋማትን ማገዛችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።

​አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በበኩሉ "ይህን 'ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ ዘመቻን ስንጀምር ዓላማችን ስፖርታዊ ውድድሩ ለወገኖቻችን መድረሻ እንዲሆን ነበር። ዛሬ ላይ በየአመቱ ተጠናክሮ መቀጠሉ አስደሳች ነገር ነው። ከምንሰበስበው ገንዘብ በላይ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ በሚሰጠው ትኩረት ትልቅ ኩራት ይሰማኛል" ሲል ገልጿል።

​በዕለቱ በግላቸው ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ላሰባሰቡና ለዘመቻው ስኬት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች ልዩ ዕውቅና ተሰጥቷል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ወደፊትም ስፖርትን ከበጎ አድራጎት ጋር በማስተሳሰር ማህበራዊ ግዴታውን መወጣቱን እንደሚቀጥልም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

​ይህ ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ የተሰኘው ዘመቻ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድርን ከማዘጋጀት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው መንገዶች ዋነኛው ሲሆን፤ ከተጀመረም 20 ዓመታትን አስቆጥሯል። ባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ከተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች በማሰባሰብ ለተለያዩ ተቋማት ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። ዘመቻው ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ ተቋማቱ ተከታታይ የድጋፍ ምንጭና የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ ለህጻናት፣ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለተፈናቃዮች የላቀ ፋይዳ ያለው ስራ ሲያከናውን ቆይቷል።
👍123👏2
📌 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን መጋቢት 26 ይካሔዳል - ሰኞ ማለዳ በሲቢኢ ብር ፕላስ ይመዝገቡ 📌

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ

መጋቢት 26  / 2018ዓ.ም.

#EntotoCBERun #GreatEthiopianRun
14
📌 ምዝገባ ተጀምሯል!!! ✍️

🗓 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን መጋቢት 26 ይካሔዳል - በሲቢኢ ብር ፕላስ ይመዝገቡ📱

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ

መጋቢት 26  ቀን 2018ዓ.ም. እንገናኝ!

#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun
11
ውብ ቅዳሜን ከእኛ ጋር ያሳልፉ!🌟

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ💫🏃‍♀️

ነገ - ቅዳሜ - መጋቢት 26 ቀን 2018ዓ.ም. እንገናኝ!

#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun
8👍2
ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✝️

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

#GreatEthiopianRun
21👍3
ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለበዓለ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ! ✝️

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

#GreatEthiopianRun
11👍1🔥1👏1
የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ እሁድ ሚያዝያ 18 ቀን / 2018ዓ.ም. ይካሔዳል

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቱሪዝም ሚኒስትር ጋር በመተባበር እያከናወነው ያለው የ'ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ' የስድስት ከተሞች ውድድር ዘንድሮ በደብረ ብርሃን እና ሐዋሳ የተከናወነ ሲሆን ፤ ቀጣይ አስተናጋጅ ከተማ ጅማ - ሚያዝያ 18 ቀን 2018ዓ.ም. ውድድሩን በድምቀት ታስተናግዳለች።

በ6 ከተሞች የሚካሔደው የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተከታታይ ውድድር ሶስተኛዋ መዳረሻ የሆነችው ጅማ ለ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ ዝግጅቷን በማጠናቀቅ ላይ ትገኛለች።

ይህ ውድድር ወላጆች ልጆቻቸውን በተገቢው ጊዜ ክትባት እንዲያስከትቡ የሚያበረታታውን ‘ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ’ የውድድር መልዕክት ይዞ ቀርቧል፡፡

የ15ኪ.ሜ.፤ የ5ኪ.ሜ እና የየህፃናት ሩጫዎችን ያካተተው ይህ ውድድር ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ10 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ዜጎችን እንደሚያሳትፍ ይጠበቃል። በ15ኪ.ሜ. ውድድሩ ላይ ከአዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች ወደ ጅማ የሚጓዙ ከ90 በላይ ተሳታፊዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፤ በ5ኪ.ሜ. ውድድሩ ላይ ከጅማ እና አካባቢው አትሌቶች እንዲሁም ከ4000 በላይ የጤና ሯጮች ይሳተፋሉ።

ሩጫው ከሚካሔድበት ቀን ሚያዝያ 18 አስቀድሞ ባለው ቅዳሜ የሚድሮክ ሆራይዘን ፕላንቴሽን የቡና እርሻ ጉብኝት እና የ5ኪ.ሜ. የእግር ጉዞ እና ሌሎች የጉብኝት እና የመዝናኛ ዝግጅቶች ተካተውበታል።

የዘንድሮውን ውድድር ስኬታማ ለማድረግ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት እየሰሩ የሚገኙት ውድድሩን እና ጅማ ከተማን ለማድመቅ የተዘጋጁት ኢትዮ ቴሌኮም፣ ቴሌብር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ሮተሪ ኢትዮጵያ፣ ፔፕሲ፣ ዳሽን ባንክ፣ ሚድሮክ ሆራይዘን፣ ቶፕ ውሃ፣ ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት እንዲሁም አፍራን ሆስፒታል ናቸው፡፡
15👍7
የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ ቡናን ከሩጫ ጋር አስተሳስሮ ተከናወነ

የ"ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ" (Discover Ethiopia Classics) ውድድር አካል የሆነው የ2018 የኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ ዛሬ ጠዋት በጅማ ከተማ ተካሄደ።

በውድድሩ ላይ ከ4,000 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች ተሳትፈዋል። ውድድሩን የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀድር እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች በክብር እንግድነት ተገኝተው አስጀምረውታል።

የዘንድሮው ውድድር "ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ" (End Polio Now) የሚል መልዕክትን በማስተላለፍ ለጤና ግንዛቤ ትልቅ ትኩረት የሰጠ ነበር።

ከአባ ጅፋር ቤተመንግስት ተነስተው በከተማው መሃል ፈረንጅ አራዳ ፍፃሜያቸውን ባደረጉት የ15 ኪሎ ሜትር የጤና ሯጮች ውድድር በወንዶች ጃፈር ጀማል እና በሴቶች የግሌ እሸቱ አንደኛ በመውጣት አሸንፈዋል።

በአትሌቶች መካከል በተደረገው የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶችብሩክ ዘለቀ ፣ ኦሊፈን ዲባባ እና ማዲ ሪዳ ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ሲያሸንፉ ፤ በሴቶች ዝናሽ ግዛው ቀዳሚ ስትሆን ማርሸት መላኩ እና ሊና አብዱ ተከታትለው ገብተዋል።

ዕድሜያቸው ከ16 እና ከ11 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የተዘጋጀው ውድድር በልዩ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን፣ የወደፊት ተተኪ እና ተስፈኛ አትሌቶች ታይተውበታል። በሁሉም የዕድሜ ክልል ላሉት ታዳጊዎችም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአጋር ድርጅቶቹ ጋር በመሆን ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አበርክቷል።

ጅማ የዘንድሮው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ የሩጫ ተከታታይ ውድድር ሶስተኛ መድረሻ ስትሆን፣ ቀጣዩ ውድድር በሯጮች መፍለቂያዋ በቦቆጂ ከተማ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም (May 24, 2026) ይካሔዳል።
👍43