ጋዜጣዊ መግለጫ
የእንግሊዝ ሃገር አንጋፋ አትሌቶች ስብስብ የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ አካል የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ።
ሐሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም.፦
ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑ አንጋፋ አትሌቶችን ያሰባሰበ ቡድን በዛሬው ዕለት ከእንግሊዝ ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ እንግሊዛዊያኑ ተሳታፊዎች የፊታችን የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም. በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በሚካሄደው 14ተኛው ሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን ላይ ይወዳደራሉ፡፡
ከተሳታፊዎቹ ውስጥ ከ55 አመት በላይና ከ5000 ሜትር በላይ ውድድር የዓለም ሻምፒዮን እንዲሁም ከ65 ዓመት በላይ የማራቶን ሪከርድ ባለቤት የሆነው ቤን ሬይኖልድስን ይገኝበታል የሪከርዱ ሰዓትም 2 ሰዓት ከ47 ደቂቃ ነው። በተጨማሪም ቡድኑ በ5 ኪ.ሜ. ርቀት ውድድር በጣም ፈጣኑን የእንግሊዝ ከ60 ዓመት በላይ አንጋፋ አትሌት ሯጮች መሐከል ሁለቱን ያካትታል።
የእንግሊዛውያኑ ቡድን የመጀመሪያዎቹን ዘጠኝ ቀናት ቆይታውን በአዲስ አበባ በልምምድና በጉብኝት ያሳልፋል፡፡ አባላቱም በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ አንዳንዶቹ በመንገድ፣ በትራክ እና በሀገር አቋራጭ ውድድር ላይ በተለያየ የዕድሜ ክልል ባሉ የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ።
በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሞብላይዜሽን አስተባባሪ ሃላፊ የሆኑት አብዱራዛቅ አሌዊ ስለ ቡድኑ ሲናገሩ "እነዚህ ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ አንጋፋ አትሌቶች ምን ያህል ፈጣን ሰዓት እንዳላቸው ማየት አስደናቂ ነው። ኢትዮጵያ ያሉ ሯጮችም ይህን ማየት እንደሚያበረታታቸውና የራሳቸውን የሩጫ ግቦች ማስቀመጥን እንዲቀጥሉ እንደሚያነሳሳቸው ተስፋ አደርጋለሁ። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያም በሀዋሳ በሚገኘው የግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ከእንግሊዝ ከመጡት አንጋፋ አትሌቶች ጋር ለመወዳደር ኢትዮጵያዊ አንጋፋ አትሌቶችን ያቀፈ ቡድን አዘጋጅቷል" ብለዋል፡፡
የእንግሊዝ ቡድንን አስተባባሪ የሆነው ስቲቭ ዋትሞው እንደተናገረው "ይህ ጉዞ ለውጤት የበቃው የእኔን ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣት ከሪቻርድ ጋር ባደረግነው ውይይት ነው። ስለ ዕቅዶቼ ለጓደኞቼ መንገር እንደጀመርኩ ሌሎችም መቀላቀል ፈለጉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ስልጠና እና ውድድር ለመካፈል እንዲሁም የዚህን አስደናቂ ሀገር ባህልና ታሪክ ለማየት በጣም ጓጉተናል።" ብለዋል፡፡
የ2018 የኢትዮ ቴሌኮም የሀዋሳ ሃይቅ ዓለም አቀፍ ግማሽ ማራቶን በቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ቴሌብር ፣ ዳሽን ባንክ፣ ፔፕሲ፣ ፋብ የውበት ሳሙና፣ ቶፕ ውሃ፣ ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት እንዲሁም በአፍራን ሆስፒታል ድጋፍ የተዘጋጀ ነው።
የ2018ቱ ኢትዮ ቴሌኮም የሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን በሀዋሳ ሃይቅ ዳርቻ ላይ በሚገኝ መንገድ ላይ የካቲት 1 ቀን 2018ዓ.ም. በድምቀት ይካሔዳል።

❤5
🤩 የልወቅሽ ኢትዮዽያ ክላሲክስ 2ኛ መዳረሻችን በነበረችው ሀዋሳ ውብ የእረፍት ቀናት እና ሩጫ ውድድር ነበረን ✨
2018 ኢትዮ ቴሌኮም ሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን✨
ቀጣይ መዳረሻችን - ጅማ - ሚያዝያ 18 ቀን 2018ዓ.ም.
✨ይጎብኙ፣ ይሩጡ፣ ሀገርዎን ይወቁ ✨
#GreatEthiopianRun #DiscoverEthiopiaClassics #2026Registration #6CitiesSeries #LHHM

❤18👍2
በየወሩ የሚካሄደው የእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ከየካቲት ወር ጀምሮ ተመልሷል።
የካቲት 05 ቀን 2018 ዓ.ም.
በጉጉት የሚጠበቀውና በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዘጋጀው ወርሃዊው 'እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ' የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር ዳግም ተጀመረ። የፊታችን የካቲት 7 ቀን 2018ዓ.ም. በሚካሄደው በዚህ ውድድር፣ ከተለመደው የስፖርት እንቅስቃሴ እና ውድድር ባለፈ የፍቅረኛሞች ቀንን (Valentine's Day) ታሳቢ ያደረጉ ልዩ ዝግጅቶች ተካተዋል።
ሩጫ ወዳጆች ሁሉ በውድድሩ ላይ እንዲሳተፉ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ባሉበት ቦታ ሆነው በሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ አማካኝነት በነፃ እና በቀላሉ መመዝገብ እንዲችሉ አድርጓል።
በተጨማሪም ወደ እንጦጦ ፓርክ የሚደረገውን ጉዞ ምቹ እና ቀላል ለማድረግ የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ለተሳታፊዎች በመሄጃ መንገዳቸው ላይ ያሉትን የአዲስ አበባን አዳዲስ መዳረሻዎች እየጎበኙ ወደ ፓርኩ አድርሶ የሚመልስ የትራንስፖርት አገልግሎት በነፃ አዘጋጅቷል።
የወሩ የሩጫ መርሃ-ግብር «የእኔ አጋር ይሮጣል» (My Valentine is Running) በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፣ጥንዶች በጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበትን መንገድ ታሳቢ አድርጎ ተዘጋጅተል። ይህንንም ለማበረታታት ጥንዶች የሚፎካከሩበትና አሸናፊዎች የሚሸለሙበት ልዩ ፉክክር አንዱ የውድድሩ ድምቀት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ ጥንዶች በኩሪፍቱ ሪዞርት ልዩ ሽልማቶች ይበረከቱላቸዋል።
ስለ ውድድሩ መግለጫ
የእንጦጦ ፖርክ ሲቢኢ ሩጫ በየወሩ የተለያየ ጭብጥ በመያዝ የሚዘጋጅ የ5ኪ.ሜ. የፓርክ ሩጫ ነው። ውድድሩ ማህበረሰቡ በስፖርት እንዲነቃቃ፣ ተፈጥሮን እንዲያደንቅ እና ሩጫን ቋሚ ልምምዱ እንዲያደርግ ዓላማ ያደረገ ወርሀዊ ውድድር ነው።

❤7👍1
ለታላቁ ሩጫ አባላት በሙሉ!
ከእናንተ ቤተሰቦቻችን ጋር ሁሌም የምናሳልፋቸው ጊዜያት አስደሳች መሆናቸው ይታወቃል።
በመጪው ቅዳሜ ማለዳ በሚደረገው የእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን ላይ ደግሞ እየተዝናናን ከታላቁ ሩጫ አባላት ጋር ዕውቅና የምንሰጣጥበት ልዩና አዝናኝ ዝግጅት ይኖረናል።
ስለሆነም በፎቶው ላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ውስጥ የምትመርጧቸውን ዕጩ ተሸላሚዎች ለ @Zak_Abdu በመላክ እንድታሳውቁን በትህትና እንጠይቃለን።
በየዘርፉ ከሚጠቆሙ ተሳታፊዎች መሐከል በተደጋጋሚ የተመረጡትን የመጨረሻ ዕጩዎች እናሳውቃለን።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ!

❤9👍1
🚨 ማስታወቂያ 🚨
💫የእንጦጦ ፓርክ ሲ.ቢ.ኢ. ሩጫችን ወደ የሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ ተዘዋውሯል 💫
🤩ቀጣይ ሳምንት የካቲት 14 እንገናኝ🤩
✨እንጦጦ ፓርክ ሲ.ቢ.ኢ. ሩጫ✨
የካቲት 14 እንገናኝ!
#EntotoCBERun #GreatEthiopianRun

👍6❤2🤩2