Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
6.05K subscribers
2.46K photos
190 videos
6 files
276 links
Official Great Ethiopian Run Telegram Channel.

Call 0116635757 for more details.
Download Telegram
የስፖርቶች ተደራሽነትን ለማስፋት ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአጋርነት ለመስራት ተስማሙ

እ.አ.አ. በ2026 የሚጀምረው አጋርነት የስኬታማውን ውድድር ዓለም አቀፋዊ ስም የበለጠ ከፍ ያደርጋል እንዲሁም ለልጆች የሩጫ እድሎችን በእጅጉ ያሰፋል፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እ.አ.አ. ከ2026 ጀምሮ ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር አብረው ለመስራት የበርካታ ዓመታት የአጋርነት ስምምነት ማድጋቸውን ዛሬ አሳውቋል፡፡ አጋርነቱ ባንኩ በረዥም ርቀት ሩጫ ላይ የነበረውን ግዙፍ እንቅስቃሴ ከአፍሪካ እጅግ ተለዋዋጭ እና በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ የሩጫ ማህበረሰቦች ወደ አንዱ እንዲያሰፋ ያግዘዋል፡፡

ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሶስት ትልልቅ የሩጫ ሁነቶች (events) ላይ በጋራ ይሰራሉ - የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ ፣ የልጆች ሩጫዎች እና ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.። ባንክ ኦፍ አሜሪካ እነዚህን ውድድሮች ተጠቅሞ የኢትዮጵያን ደማቅ የሩጫ ባህል እይታ ለማሳደግ እና በስፖርት፣ ቱሪዝም እና ንግድ አማካይነት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡

ባንክ ኦፍ አሜሪካ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አጋር የመሆኑ ምክንያት ተቋሙ ቀጣዩን ትውልድ ለማነሳሳት እና በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የፅናት ስፖርቶችን ለማስፋፋት ካለው ማህበረሰብ-ተኮር መርሆ የተነሳ ነው፡፡ ይህ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በስፖርት አማካይነት እድገትን የማነሳሳት እና ማህበረሰቦችን የማገዝ የረዥም ጊዜ ቁርጠኝነቱን ሲያጠናክር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫን የሁሉም የህይወት ዘይቤ የማድረግ ዋነኛ ራዕይ ጋርም የተስማማ ሆኗል።

ዝርዝሩን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ
17👏9🔥4🤩2👍1
የቦስተን እና ሺካጎ ማራቶን የውድድር ዳይሬክተሮች በኢትዮጵያ በተደረገላቸው የሞቀ አቀባበል ደስታቸውን ገለፁ።

የሺካጎ ማራቶን የውድድር ዳይሬክተር ኬሪ ፒንኮቭስኪ እና የቦስተን ማራቶን የውድድር ዳይሬክተር ጃክ ፍሌሚንግ ዛሬ ረፋድ በቅድመ-ውድድር ፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጓቸው ንግግሮች፣ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ አዘጋጆችን አድንቀዋል። ሁለቱም ይህ የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ነው።

ጃክ ፍሌሚንግ ሲናገሩ "በአስደናቂ ሀገር በጣም ጥሩ ጊዜ እያሳለፍን እንገኛለን። እዚህ ያለው ሁሉም ሰው ቤታችን ያለን ያክል እንዲሰማን እያደረገን ነው። እሁድ ሩጫውን እስከማይ እጅግ ጓጉቻለሁ" ብለዋል።

በትናንት ምሽቱ ልዩ የዕራት ግብዣ ስነስርዓት ላይ ኬሪ እና ጃክ፣ እንደ ብርሀኔ አደሬ፣ ኃይሌ ገብረስላሴ እና እራሱም የአዘጋጆቹ የክብር እንግዳ ሆኖ አዲስ አበባ የሚገኘው ሞሰስ ታኑይን ጨምሮ በርካታ የቀድሞ የውድድሮቻቸውን አሸናፊዎች የመገናኘት እድል ነበራቸው።

የፊታችን እሁድ የሚካሄደው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 25ኛ ዓመቱን የሚያከብርበት ሲሆን ፤ ውድድሩ የሚወክለውን የማሰባሰብ መንፈስ በማስታወስ "ሀገር በ10 ኪ.ሜ" የሚል መፈክርን ይዘዟል።

በአርቡ ፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ ከተዋወቁ ሌሎች እንግዶች መካከል አሜሪካዊው የቀድሞ የማራቶን የዓለም ሬኮርድ ባለቤት ካሊድ ካኑቺ እና ኬኒያዊው የቀድሞ የ3000ሜ እና 5000ሜ የዓለም ባለ ሬኮርድ ዳንኤል ኮመን ይጠቀሳሉ። ኮመን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ሶስት የ5000ሜ የዓለም ሬኮርዶች ያሰበረውን (ሁለት የኃይሌ እና አንድ የኮመን) ከኃይሌ ገብረስላሴ ጋር የነበረውን ተፎካካሪነት አስታውሷል።

የሩጫው ቀናት የሚጀምረው ነገ (ቅዳሜ) ማለዳ በእንጦጦ ተራራ በሚካሄደዉ የንጋት የ3ኪ.ሜ. ሩጫ ሲሆን፣ ከዚያም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የ2018 ዩኒሴፍ የልጆች ሩጫ ይደረጋል። ተጠባቂው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድር የሚካሄደው እሁድ ይሆናል።

ተሳታፊዎች ጠዋት 1፡00 መስቀል አደባባይ እንዲደርሱ የውድድሩ ኦፕሬሽንስ ዳይሬክተር ዳግም ተሾመ ሲያሳስብ ፤ የፈጣን ማእበል መነሻ ግዮን ሆቴል እና የዘና ማዕበል መነሻ መስቀል አደባባይ እንደሚሆንም አስታውሷል፡፡

25ኛው ዓመት ልዩ ውድድር ላይ 55ሺህ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ። የዘንድሮ ውድድር አጋሮች ፤ ሶፊ ማልት የስያሜ አጋር ፣ ዩኒሴፍ የመልዕክት አጋር ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ አጋር ፣ ኢትዮ ቴሌኮምና ቴሌ ብር የቴክኖሎጂ አጋር ፣ ዳሽን ባንክ የባንክ አጋር ፣ ፋብ የውበት ሳሙና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫዎች የንዕህና አጋር ፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር ፣ ቶፕ ውሃ ፣ ሃያት ሬጀንሲ ፣ ኢ.ቢ.ሲ. እና አፍራን ሆስፒታል ናቸው።
8
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለ2019 ሩጫችን ነገ ነው ምዝገባችን!

በባንክ ኦፍ አሜሪካ ለሚቀርብላችሁ የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ዝግጁ?

ቀድመው በቴሌብር ይመዝገቡ!

ለፈጣን ማዕበል 900.00 ብር ወይም
ለዘና ማዕበል 700.00 ብር በመክፈል ይመዝገቡ።

#GreatEthiopianrun #PowerToDo #InspireNextGeneration #2026Registration
33👍9
በቴሌብር ምዝገባ ጀምረናል! 🤩

ለፈጣን ማዕበል 900.00 ብር ወይም ለዘና ማዕበል 700.00 ብር በመክፈል ይመዝገቡ!

በባንክ ኦፍ አሜሪካ የሚቀርብላችሁ የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.

ቀድመው ይመዝገቡ!

#GreatEthiopianrun #PowerToDo #InspireNextGeneration #2026Registration
27👍15
ጋዜጣዊ መግለጫ

የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ደብረ ብርሃን እና ሐረርን በመጨመር ዛሬ በይፋ ተጀመረ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ በሚል ስያሜ በስድስት የክልል ከተማዎች ላይ ተከታታይ የሩጫ ውድድር ሊያዘጋጅ ነው።

በ2017ዓ.ም. በ4 መዳረሻ ከተማዎች ላይ የተካሔደው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተከታታይ ውድድር ፤ በዚህም ዓመት ደብረብርሃን እና ሐረርን በመጨመር 6 ከተማዎች ላይ ይካሔዳል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፈውም ዓመት አዘጋጅ በነበሩት ሐዋሳ፣ ጅማ፣ ቦቆጂ እና አርባምንጭ ላይ ለተከታታይ ዓመታት እንዳደረገው ሁሉ ዘንድሮም ስኬታማ ውድድሮችን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ይህ ስፖርት እና ቱሪዝምን በማቀናጀት የሃገራችንን ከተሞች እና የቱሪዝም ስፍራዎችን በስፋት እያስተዋወቀ የሚገኘው መርሃግብር አዳዲስ ከተሞችን በመጨመር ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የሚካሔድ ሲሆን ከጥር እስከ ሐምሌ ፤ ከአንኮበር እስከ ሐረር በር የሚል መርህ ተሰጥቶት ይካሔዳል።

የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ የስድስት ከተሞች ተከታታይ ውድድር ይፋ በተደረገበት የዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስፖርት እና ቱሪዝምን በማስተሳሰር እየሰሯቸው ያሉትን ስራዎች ይበልጥ አጠናክሮ ለመስራት የሚያስችላቸው የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) “ልወቅሽ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያንን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሀገራት ተሳታፊዎችን መሳብ የቻለ ዝግጅት ለመሆን በቅቷል። በዚህ አጋጣሚ ደብረ ብርሃን እና ሐረር የዘንድሮውን ልወቅሽ ኢትዮጵያ መቀላቀላቸዉን ማብሰር እፈልጋለሁ” ብለዋል።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ መሃመድ በበኩላቸው “ስፖርትን ከቱሪዝም ጋር በማጣመር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እየሰራ ያለዉን ስራ እንደ ሚኒስትር መስሪያ ቤት የምናደንቀው እና የምንደግፈው ነው ፤ ከዚህ በኋላ አብረን የምንሰራ ይሆናል ’’ ብለዋል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ በበኩላቸው “ለሃገራችን ‘ልወቅሽ ኢትዮጵያ’ የሚባል አዲስ የቱሪዝም ምርት በማስተዋወቃችን እና ከሩጫ ውድድርነት ባሻገር ኢትዮጵያን በትንሹም ቢሆን ማሳየት በመቻላችን ደስተኞች ነን ፤ ይህ እንዲሳካልን ለሚያግዙን ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ሁሉም አጋሮቻችን ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ተሳታፊዎችም አብረውን እንዲጓዙ እጋብዛለሁ” ብለዋል።

ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎን፣ ጓደኝነትን እና አንድነትን የሚያበረታታው ልወቅሽ ኢትዮጵያ በደብረ ብርሃን ከተማ በጥር 03 ቀን 2018ዓ.ም. የማራቶን ዱላ ቅብብል እና የሀገር አቋራጭ ውድድሮችን በማካተት ጅማሮውን ያደርጋል።
6👍3👏2
💫መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!
ሩጫን የአኗኗር ዘይቤያችን እናድርግ💫

#GreatEthiopianRun #DiscoverEthiopiaClassics #2026Registration #6CitiesSeries #DebreBirhan
11👍7
ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ2018 የ“ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” ተከታታይ ውድድሮችን በአጋርነት

ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ - ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም - ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ2018 የ”ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ”
(Discover Ethiopia Classics) ተከታታይ ውድድሮችን በአጋርነት ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት አድርገዋል። በስምምነቱ መሰረት
ኢትዮ ቴሌኮም በአምስት ዋና ዋና ክልላዊ ውድድሮች ላይ የስያሜ ስፖንሰር (Title Sponsor) በመሆን የሚሳተፍ ሲሆን፤ ይህም ኩባንያው
ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ለቱሪዝም እድገት ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት እና ጽኑ ቁርጠኝነት አንዱ ማሳያ ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የ2018 የሩጫ ተከታታይ ውድድሮችን በአምስት ከተሞች ማለትም በደብረ ብርሃን፣ ሐዋሳ፣ ጅማ፣ በቆጂ እና ሐረር
የሚደረጉት ውድድሮች የስያሜ አጋር ሲሆን፣ የመጀመሪያው ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በደብረ ብርሃን ጥር 3 ቀን 2018 ዓ.ም የሚጀምር
ይሆናል፡፡ ይህም ጤናማ እና አምራች ዜጋን ከመገንባት ባሻገር የኢትዮጵያን ውብ መልክዓ ምድሮች፣ ታሪካዊ ቦታዎችና ባህሎች ለማስተዋወቅ
እና መልካም ማህበራዊ ትስስሮችን ለማጠናከር የላቀ ሚና ይኖረዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የታላቁ ሩጫ የቴክኖሎጂ አጋር በመሆን ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ተሞክሮ እንዲኖራቸው የሚያስችል ልዩ
የሩጫ መተግበሪያ (Running App) በማበልፀግ በስራ ላይ ያዋለ ሲሆን፣ ይህም መተግበሪያ በየትኛውም የሀገራችን አካባቢዎች ለሚከናወኑ ውድድሮች በውድድር ወቅት ያሉ መረጃዎችንና መገኛ ቦታን በቀጥታ ለመከታተል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይሰጣል። ይህ የቴክኖሎጂ ትስስር ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የአኗኗር ዘይቤን ለማስተዋወቅ ከሚያከናውናቸው ስትራቴጂዎች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡

በስምምነቱ ወቅት የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኮሙኒኬሽን ኦፊሰር መሳይ ውብሸት እንደገለፁት ኩባንያው ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር ዘመኑ
የደረሰባቸውን አዳዲስ የቴሌኮም ቴክኖሎጂዎች እና የዲጂታል ሶሉሽኖችን በሀገራችን ተግባራዊ በማድረግ የዲጂታል ኢትዮዽያን ራዕይ እውን
ለማድረግ እያከናወነ ከሚገኘው መጠነ ሰፊ ስራዎች በተጨማሪ ከሌሎች ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በመተባበርና በመቀናጀት ለሀገራችን
ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡

አክለውም “ይህ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ“ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” ተከታታይ ውድድሮች አጋርነት ስምምነትም የዚህ ኢንሸቲቭ አንዱ
አካል ሲሆን፣ ኩባንያው በአካልና በስነ-ልቦና የተገነባ ጤናማ ትውልድ ለመገንባት፣ የሩጫ ውድድሮቹ የሚካሄድባቸው ከተሞችን ይበልጥ
ለማስተዋወቅና የቱሪዝም መዳረሻ ፍሰትን ለመጨመር እየተከናወኑ የሚገኙ ጥረቶችን ለማጠናከር እንዲሁም በሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ
እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በመግለጽ በቀጣይም ለሀገራችን እድገት ቁልፍ ሚና ያላቸውን ተግባራት በመለየትና በቴክኖሎጂ
እንዲታገዙ በማድረግ አጋርነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ በበኩላቸው “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሁልጊዜም ከሩጫ በላይ መሆኑን
በመግለፅ ባህላችንን እና ህዝባችንን የምናውቅበት እና የምናስተዋውቅበት መድረክ ነው” ብለዋል። ዋና ስራ አስኪያጇ አክለውም “ኢትዮ
ቴሌኮምን እንደ ዋና አጋር ማግኘታችን ውድድሮቹን ወደ ላቀ ደረጃ እንድናሸጋግር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው” ብለዋል፡፡

ይህ አጋርነት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪዝምን ለማሳደግ ያለውን የጋራ ራዕይ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ የደብረ ብርሃንን ታሪካዊነት፣
የሐዋሳ ሃይቅን ውብ ገፅታ፣ የጅማን የቡና መገኛነት፣ የአትሌቶች መፍለቂያ የሆነችውን በቆጂን በማጉላት እና የሐረርን የቱሪስት መስህብነት
አጉልቶ በማሳየት ኢትዮጵያን የስፖርት ቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ ያለመ ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ
ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም
15🔥2👍1
🎄ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኝላችኋል። 🎄

#GreatEthiopianRun
👍2213👏3
🚨 ማስታወቂያ! ለአትሌቶች በሙሉ 🏃🏾‍♀️🏃🏾

የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ሐዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን የአትሌቶች ምዝገባ ላይ ነን!

ውድድሩ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ሐዋሳ ላይ ይካሄዳል።

ምዝገባ:- ላምበረት ማራቶን ህንፃ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሯችን በመግኘት አልያም በስልክ በመደወል እንድትመዘገቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ለበለጠ መረጃ
011-663-5757

#GreatEthiopianRun #Ethiopia
8👍3
ጋዜጣዊ መግለጫ

የቡድን ስራ እና የመንገድ ደህንነት መልዕክቶች የጎሉበት 20ኛው አይ.ኤፍ.ኤች./አ.አ.መ.ባ. የዱላ ቅብብል ሩጫ ዛሬ ተካሔደ

20ኛው የአይ.ኤፍ.ኤች./አ.አ.መ.ባ. የዱላ ቅብብል ሩጫ ከቦሌ ቡልቡላ ወደ ኮዬ ፈቼ በሚወስደው መንገድ ላይ ዛሬ ተካሒዷል።

በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አማካኝነት የተዘጋጀው ይህ ልዩ ውድድር፣ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎችን አወዳድሯል። ዝግጅቱ የሁለት አስርት ዓመታትን የአካል ብቃት እና የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት የጠነከረበት እንዲሁም የመንገድ ደህንነት መልዕክቶች የተላለፉበት መድረክ ሆኗል።

የአዲስ አበባ የቀለበት መንገድ ምረቃን ተከትሎ የተጀመረው ይህ የዱላ ቅብብል ሩጫ፤ በአሁኑ ወቅት በብዙ ተቋማት ዘንድ የሚጠበቅ የሰራተኞች የጋራ ቀን ሆኗል።

የዘንድሮው ውድድር “የ6ታችን ቃልኪዳን” (Our Pact) በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን፣ ይህም በቡድን አባላት መካከል ያለውን ትስስር እና በመተባበር ማሸነፍን የሚያጎላ ነው።

አራት የቡድን አባላቶች እያንዳንዳቸው አራት ኪሎ ሜትሮችን በሮጡበት የአትሌቶች ምድብ ከፍተኛ ፉክክር ታይቷል። በዚህም መሰረት በሁለቱም ፆታ ከኢ.ኮ.ስ.ኮ. የተሰባሰቡ አትሌቶች በአንደኛ እና ሶስተኝነት ሲያጠናቅቁ የኢትዮ ኤሌክትሪክ አትሌቶች ሁለተኛ ሆኘዋል።

ከአትሌቶች ውጭ እያንዳንዱ ቡድን ስድስት አባላትን የያዘ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ተወዳዳሪ 1 ኪሎ ሜትር በመሮጥ በድምሩ 6 ኪሎ ሜትር ርቀትን ሸፍነዋል። ውድድሩ በዘጠኝ የተለያዩ ዘርፎች አሸናፊዎችን የሸለመ ሲሆን፤ ይህም የመንግስት ተቋማትን፣ የንግድ ድርጅቶችን፣ ጂም እና የጤና ቡድኖችን፣ ኤምባሲዎችን፣ ባንክና ኢንሹራንስን፣ ሆቴሎችን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን (NGOs) እንዲሁም የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አባላትና ጓደኞችን ያካተተ ነበር።

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የኤምባሲ ዘርፍ የቻይና ኤምባሲ ቡድን ልዩ ቅንጅት በማሳየት ውድድሩን ሲያሸንፍ፣ በሆቴሎች ዘርፍ አሸናፊዎቹ ኃይሌ ግራንድ ሆቴሎች ደግሞ ከምድባቸው ባሻገር የአጠቃላይ የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ድልን ተቀዳጅተዋል።

ይህ የ20 ዓመታት የውድድር ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን የቻይና ኮሙኒኬሽን ፈርስት ሃይዌይ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (CCFHEG/CCCC) የሚያበረክተው ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል። የሲ.ሲ.ሲ.ሲ (CCCC) የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ ዌይ ቺያንግዩ በመድረክ ላይ ሲናገሩ “ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን እና የስፖርታዊ ጨዋነትን ለማሳደግ ብቻ ሳይሆን፣ የማህበራዊ ኃላፊነታችንን ለመወጣት በተለይም የመንገድ ደህንነት ግንዛቤን ለማስጨበጥ ይህንን ዝግጅት በቋሚነት ለማዘጋጀት ቁርጠኞች ነን” ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን (AACRA) የጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ተክለፃዲቅ በበኩላቸው የመንገድ ደህንነት የጋራ ትብብርን የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸው፤ "ይህ ውድድር ስፖርትን ከማሳደጉም ባለፈ የአብሮነትና የትብብር ተምሳሌት ሆኖ ለሁለት አስርት ዓመታት ዘልቋል" ብለዋል። ወ/ሮ ትዕግስት አክለውም "የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የብዙ አካላትን ርብርብና የተጠቃሚዎችን ተሳትፎ ይፈልጋል፤ ስለዚህ የመንገድ መሰረተ ልማት ሀብቶችን በባለቤትነት ስሜት በመጠበቅ የራሳችንን እና የሌሎችን ህይወት እንድናድን አሳስባለሁ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
7👍4
ምዝገባ ተጀምሯል!
ሲቢኢ ብር ፕላስ ላይ ገብተው በነፃ ይመዝገቡ!

በድጋሚ የተመለሰው እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ - የመጀመሪያ ወር ውድድር

ቅዳሜ የካቲት 7 በእንጦጦ እንገናኝ

#EntotoPark #CBE #GreatEthiopianRun
11