ለሚድያ ባለሞያዎች - የመጨረሻ ጥሪ!
ሀዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. ለሚካሔደው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድር ላይ በቦታው ተገኝተው መዘገብ ለሚፈልጉ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሚድያዎች የይለፍ መታወቂያ ለማዘጋጀት ፤ ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም እንድትመዘገቡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የመጨረሻ ጥሪውን ያቀርባል!
የሚድያ ምዝገባ የምናከናውነው እሰከ 08 ህዳር 2018ዓ.ም. ነው!
👉 https://ethiopianrun.org/accreditation

❤9👍1
ካሊድ ካኑቺ እና ፔሬስ ጄፕቺርቺር የ25ኛው ዓመት ውድድር የእንግዶች ዝርዝር ላይ ተጨምረዋል
የቀድሞው የማራቶን የዓለም ሬኮርድ ባለቤት እና የሺካጎ ማራቶን የአራት ጊዜ አሸናፊው አሜሪካዊ ካሊድ ካኑቺ እንዲሁም የወቅቱ የማራቶን የዓለም ሻምፒዮን ኬኒያዊቷ ፔሬስ ጄፕቺርቺር ፤ እሁድ ህዳር 14 በአዲስ አበባ በሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 25ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ውድድር ላይ በእንግድነት እንደሚገኙ አረጋግጠዋል፡፡
ካኑቺም እንደ ኃይሌ ገብረስላሴ ሁለቴ የዓለም ሬኮርድን ሰብሯል - በመጀመሪያ እ.ኤ.አ. በ1999 በሺካጎ በ2፡05፡42 ሰዓት እና ከሶስት ዓመታት በኋላ በለንደን የራሱን ሰዓት በአራት ሴኮንዶች ወደ 2፡05፡38 በማሻሻል፡፡ ካኑቺ በለንደኑ ውድድር ፖል ቴርጋትን እና ኃይሌ ገብረስላሴን ቀድሞ ሲያሸንፍ ሁለቱ በቅደም-ተከተል 2ኛ እና 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡
ካኑቺ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ስለሚያደርገው ጉዞ ሲናገር ‹‹በተወዳዳሪነቴ ወቅት ከብዙ ኢትዮጵያዊያን ጋር የመለማመድ እና የመወዳደር እድል ነበረኝ፡፡ ጠንካራ ሰራተኝነታቸው እና ለሩጫ ያላቸው ፍቅር ለስኬታቸው ዋነኛ ምክንያት ነበሩ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ መገኘት እና በዚያ ያሉ ጓደኞቼን ማግኘት አጓጉቶኛል›› ብሏል፡፡
ለ2025 የሴቶች ከስታዲየም ውጪ የዓመቱ ምርጥ አትሌትነት የታጨችው ኬኒያዊቷ የማራቶን ኮከብ ፔሬስ ጄፕቺርቺርም ከ8 ዓመት ሴት ልጇ ናታሊያ ጋር ወደ አዲስ አበባ ትመጣለች፡፡ በቶኪዮ የኦሊምፒክ ማራቶንን ካሸነፈች አንድ ዓመት በኋላ በ2015 በታላቁ ሩጫ ላይ ተገኝታ የነበረችው ጄፕቺርቺር፣ በእዚያው በቶኪዮ ኢትዮጵያዊቷ ተፎካካሪዋ ትዕግስት አሰፋን በጥቂት ሰኮንዶች ቀድማ በማራቶን የዓለም ሻምፒዮንነትን ከተቀዳጀች ሁለት ወራት ብቻ ተቆጥረዋል።
‹‹ያ ውድድር ከእጄ እንዲያመልጥ በጭራሽ አልፈለኩም፡፡ ድሉን እጅግ ፈልጌው ነበር›› ስትል ጄፕቺርቺር ከሁለት ወራት በፊት በቶኪዮ ስላገኘችው ድል ታስታውሳለች፡፡ ከመንፈቅ በፊት ትዕግስት ድል ባደረገችበት እና የጄፕቺርቺርን የ2024 ክብር በወሰደችበት የለንደን ማራቶን፣ ኬኒያዊቷ ውድድሩን አቋርጣ ነበር፡፡
በሶስት የዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮናዎች ሶስት የግል የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያሸነፈችው ጄፕቺርቺር አሁን የአራት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮን ስትሆን ፤ በቦስተን፣ ኒው ዮርክ እና ለንደን በማሸነፍ የሶስት-ጊዜ የዓለም ሜጀር ማራቶን ባለድል ነች፡፡
የካኑቺ እና ጄፕቺርቺር ስሞች ከዚህ ቀደም ይፋ በተደረጉት ሶስቱ ኬንያውያን አትሌቶች ፖል ቴርጋት ፣ ዳንኤል ኮመን እና ሞሰስ ታኑይ’ን በያዘው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ላይ የሚታደሙ እንግዶች አስደናቂ ስብስብ ላይ ተጨምረዋል።

❤18👍11
ፋንታዬ በላይነህ የመጀመሪያ ድሏን አቤ ጋሻሁን ደግሞ አራተኛ የድል ሪከርዱን በ10 ኪ.ሜ. ለማሳካት በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መድረክ ይወዳደራሉ
የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ. የአትሌቶች ውድድር ቅድመ እይታ
የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ካሸነፈች ገና ሁለት ሳምንታትን ብቻ ያስቆጠረችው የ25 ዓመቷ ፋንታዬ በላይነህ እሁድ በሚካሄደው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪሎ ሜትር የሴት አትሌቶች ውድድር ላይ ተጠባቂ አትሌት ናት። ልክ እንደ ቦስተኑ ውድድር ፤ በ2016 ዓ.ም. የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድርን በ32 ደቂቃ ከ28 ሰከንድ አሸናፊ ሆና ከገባችው መልክናት ውዱ ጋር ትፋለማለች።
ፈንታዬ እጅግ ስኬታማ ከሆነው የውድድር ዘመኗ በኋላ እየመጣች ነው። በቶኪዮ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5000 ሜትር ውድድር ተሳትፋ ዘጠነኛ ሆና አጠናቃለች። ከዚህ ቀደም በለንደን ዳይመንድ ሊግ መዲና ኢሳን ተከትላ ሁለተኛ ሆና ስታጠናቅቅ የግል ምርጥ ሰዓቷን ወደ 14 ደቂቃ ከ30.90 ሰከንድ ዝቅ አድርጋለች። በመንገድ ላይ የ10 ኪሎ ሜትር ምርጥ ሰዓቷ እ.ኤ.አ. በ2025ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ከቫሌንሲያ 10 ኪሜ ያስመዘገበችው 30፡00 ነው።
ሌላዋ ጠንካራ አትሌት እ.ኤ.አ. የ2023 የቲ.ሲ.ኤስ. አምስተርዳም ማራቶን አሸናፊ የሆነችው መሠረት በለጠ ስትሆን ፤ የሩጫ ሰዓቷም 2፡18፡21 ነበር። ረዘም ያሉ ርቀቶችን በመሮጥ ትልቅ ልምድ ያላት ሲሆን በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ደግሞ በዴጉ ማራቶን በ2፡24፡08 አሸንፋለች። የመሠረት ለ10 ኪ.ሜ. ምርጥ ሰዓት 32፡39 በዚህ ዓመት ግንቦት ወር ላይ በቦልደር ቦልደር 10 ኪ.ሜ. ውድድር ላይ ያስመዘገበችው ነው።
ለመጨረሻ ጊዜ በ2015ዓ.ም. የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድርን ያሸነፈው አቤ ጋሻሁን ፤ በ2009 እና በ2012ዓ.ም. ከነበሩት ድሎች ጋር ተዳምሮ ሶስት ጊዜ ማሸነፍ የቻለ ብቸኛው ወንድ አትሌት ነው። አቤ በዚህ ውድድር ላይ ባለፉ ዓመታት ታላቁ ሩጫ ላይ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ካጠናቀቁ ሁለት አትሌቶች ጋር ይፎካከራል። በ2017ዓ.ም. አዲሱ ነጋሽ ከአሸናፊው ቢኒያም መሃሪ (28፡26) አንድ ሰከንድ ብቻ ዘግይቶ ሁለተኛ ሆኖ ስላጠናቀቀ ዘንድሮ ለአሸናፊነት ይፎካከራል።
ሌላው በ2016ዓ.ም. ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኃይለማርያም አማረ ሲሆን የ10 ኪ.ሜ. ምርጥ ሰዓቱ 27፡32 ሲሆን በ2015ዓ.ም. ከአቤ ጋሻሁን በመቀጠል ሁለተኛ ሆኖ ነበር። ከሌሎች ሊታዩ ከሚገባቸው አትሌቶች መካከል በግንቦት ወር የታላቁ ቦቆጂ ሩጫ የ12 ኪ.ሜ. ያሸነፈውና የበቆጂ ፈርጥ የሆነው ወጣት አትሌት ሰዩም ድሪባ ነው። ይህም በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዘጋጁት የክልል ውድድሮች ለወጣት አትሌቶች እንዴት መነሻ እንደሆኑ ያሳያል።
ከተሳታፊ የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች መካከል የዩጋንዳዎቹ ሌዊ ቸላንጋት እና ቪክቶር ቸሮቲች ጠንካራ ተፎካካሪዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል። በሁለቱም ፆታዎች የአትሌቶች ውድድሮች ላይ ከኬንያ እና ታንዛኒያ የመጡ አትሌቶችም ይገኛሉ።
እሁድ ህዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. በሚደረገው ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ላይ የአትሌቶች ውድድሮች ከጤና ሯጮች ውድድሮች ጥቂት ደቂቃዎችን ቀደም ብሎ በ1:55 ሰዓት እና በ1:57 ሰዓት ላይ ይጀመራሉ። የጤና ሯጮች ውድድሮች ፈጣን ማዕበል በ2፡00 ሰዓት እና ዘና ማዕበል በ2፡10 ሰዓት ላይ ይጀመራሉ።
25ኛው ዓመት ልዩ ውድድር ላይ 55ሺህ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ። የዘንድሮ ውድድር አጋሮች ፤ ሶፊ ማልት የስያሜ አጋር ፣ ዩኒሴፍ የመልዕክት አጋር ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ አጋር ፣ ኢትዮ ቴሌኮምና ቴሌ ብር የቴክኖሎጂ አጋር ፣ ዳሽን ባንክ የባንክ አጋር ፣ ፋብ የውበት ሳሙና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫዎች የንዕህና አጋር ፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር ፣ ቶፕ ውሃ ፣ ሃያት ሬጀንሲ ፣ ኢ.ቢ.ሲ. እና አፍራን ሆስፒታል ናቸው።

❤26👍14
የስፖርቶች ተደራሽነትን ለማስፋት ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአጋርነት ለመስራት ተስማሙ።
እ.አ.አ. በ2026 የሚጀምረው አጋርነት የስኬታማውን ውድድር ዓለም አቀፋዊ ስም የበለጠ ከፍ ያደርጋል እንዲሁም ለልጆች የሩጫ እድሎችን በእጅጉ ያሰፋል፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እ.አ.አ. ከ2026 ጀምሮ ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር አብረው ለመስራት የበርካታ ዓመታት የአጋርነት ስምምነት ማድጋቸውን ዛሬ አሳውቋል፡፡ አጋርነቱ ባንኩ በረዥም ርቀት ሩጫ ላይ የነበረውን ግዙፍ እንቅስቃሴ ከአፍሪካ እጅግ ተለዋዋጭ እና በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ የሩጫ ማህበረሰቦች ወደ አንዱ እንዲያሰፋ ያግዘዋል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሶስት ትልልቅ የሩጫ ሁነቶች (events) ላይ በጋራ ይሰራሉ - የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ ፣ የልጆች ሩጫዎች እና ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.። ባንክ ኦፍ አሜሪካ እነዚህን ውድድሮች ተጠቅሞ የኢትዮጵያን ደማቅ የሩጫ ባህል እይታ ለማሳደግ እና በስፖርት፣ ቱሪዝም እና ንግድ አማካይነት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አጋር የመሆኑ ምክንያት ተቋሙ ቀጣዩን ትውልድ ለማነሳሳት እና በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የፅናት ስፖርቶችን ለማስፋፋት ካለው ማህበረሰብ-ተኮር መርሆ የተነሳ ነው፡፡ ይህ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በስፖርት አማካይነት እድገትን የማነሳሳት እና ማህበረሰቦችን የማገዝ የረዥም ጊዜ ቁርጠኝነቱን ሲያጠናክር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫን የሁሉም የህይወት ዘይቤ የማድረግ ዋነኛ ራዕይ ጋርም የተስማማ ሆኗል።
ዝርዝሩን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ

❤17👏9🔥4🤩2👍1
የቦስተን እና ሺካጎ ማራቶን የውድድር ዳይሬክተሮች በኢትዮጵያ በተደረገላቸው የሞቀ አቀባበል ደስታቸውን ገለፁ።
የሺካጎ ማራቶን የውድድር ዳይሬክተር ኬሪ ፒንኮቭስኪ እና የቦስተን ማራቶን የውድድር ዳይሬክተር ጃክ ፍሌሚንግ ዛሬ ረፋድ በቅድመ-ውድድር ፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጓቸው ንግግሮች፣ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ አዘጋጆችን አድንቀዋል። ሁለቱም ይህ የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ነው።
ጃክ ፍሌሚንግ ሲናገሩ "በአስደናቂ ሀገር በጣም ጥሩ ጊዜ እያሳለፍን እንገኛለን። እዚህ ያለው ሁሉም ሰው ቤታችን ያለን ያክል እንዲሰማን እያደረገን ነው። እሁድ ሩጫውን እስከማይ እጅግ ጓጉቻለሁ" ብለዋል።
በትናንት ምሽቱ ልዩ የዕራት ግብዣ ስነስርዓት ላይ ኬሪ እና ጃክ፣ እንደ ብርሀኔ አደሬ፣ ኃይሌ ገብረስላሴ እና እራሱም የአዘጋጆቹ የክብር እንግዳ ሆኖ አዲስ አበባ የሚገኘው ሞሰስ ታኑይን ጨምሮ በርካታ የቀድሞ የውድድሮቻቸውን አሸናፊዎች የመገናኘት እድል ነበራቸው።
የፊታችን እሁድ የሚካሄደው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 25ኛ ዓመቱን የሚያከብርበት ሲሆን ፤ ውድድሩ የሚወክለውን የማሰባሰብ መንፈስ በማስታወስ "ሀገር በ10 ኪ.ሜ" የሚል መፈክርን ይዘዟል።
በአርቡ ፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ ከተዋወቁ ሌሎች እንግዶች መካከል አሜሪካዊው የቀድሞ የማራቶን የዓለም ሬኮርድ ባለቤት ካሊድ ካኑቺ እና ኬኒያዊው የቀድሞ የ3000ሜ እና 5000ሜ የዓለም ባለ ሬኮርድ ዳንኤል ኮመን ይጠቀሳሉ። ኮመን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ሶስት የ5000ሜ የዓለም ሬኮርዶች ያሰበረውን (ሁለት የኃይሌ እና አንድ የኮመን) ከኃይሌ ገብረስላሴ ጋር የነበረውን ተፎካካሪነት አስታውሷል።
የሩጫው ቀናት የሚጀምረው ነገ (ቅዳሜ) ማለዳ በእንጦጦ ተራራ በሚካሄደዉ የንጋት የ3ኪ.ሜ. ሩጫ ሲሆን፣ ከዚያም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የ2018 ዩኒሴፍ የልጆች ሩጫ ይደረጋል። ተጠባቂው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድር የሚካሄደው እሁድ ይሆናል።
ተሳታፊዎች ጠዋት 1፡00 መስቀል አደባባይ እንዲደርሱ የውድድሩ ኦፕሬሽንስ ዳይሬክተር ዳግም ተሾመ ሲያሳስብ ፤ የፈጣን ማእበል መነሻ ግዮን ሆቴል እና የዘና ማዕበል መነሻ መስቀል አደባባይ እንደሚሆንም አስታውሷል፡፡
25ኛው ዓመት ልዩ ውድድር ላይ 55ሺህ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ። የዘንድሮ ውድድር አጋሮች ፤ ሶፊ ማልት የስያሜ አጋር ፣ ዩኒሴፍ የመልዕክት አጋር ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ አጋር ፣ ኢትዮ ቴሌኮምና ቴሌ ብር የቴክኖሎጂ አጋር ፣ ዳሽን ባንክ የባንክ አጋር ፣ ፋብ የውበት ሳሙና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫዎች የንዕህና አጋር ፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር ፣ ቶፕ ውሃ ፣ ሃያት ሬጀንሲ ፣ ኢ.ቢ.ሲ. እና አፍራን ሆስፒታል ናቸው።
የሺካጎ ማራቶን የውድድር ዳይሬክተር ኬሪ ፒንኮቭስኪ እና የቦስተን ማራቶን የውድድር ዳይሬክተር ጃክ ፍሌሚንግ ዛሬ ረፋድ በቅድመ-ውድድር ፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጓቸው ንግግሮች፣ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ አዘጋጆችን አድንቀዋል። ሁለቱም ይህ የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ነው።
ጃክ ፍሌሚንግ ሲናገሩ "በአስደናቂ ሀገር በጣም ጥሩ ጊዜ እያሳለፍን እንገኛለን። እዚህ ያለው ሁሉም ሰው ቤታችን ያለን ያክል እንዲሰማን እያደረገን ነው። እሁድ ሩጫውን እስከማይ እጅግ ጓጉቻለሁ" ብለዋል።
በትናንት ምሽቱ ልዩ የዕራት ግብዣ ስነስርዓት ላይ ኬሪ እና ጃክ፣ እንደ ብርሀኔ አደሬ፣ ኃይሌ ገብረስላሴ እና እራሱም የአዘጋጆቹ የክብር እንግዳ ሆኖ አዲስ አበባ የሚገኘው ሞሰስ ታኑይን ጨምሮ በርካታ የቀድሞ የውድድሮቻቸውን አሸናፊዎች የመገናኘት እድል ነበራቸው።
የፊታችን እሁድ የሚካሄደው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 25ኛ ዓመቱን የሚያከብርበት ሲሆን ፤ ውድድሩ የሚወክለውን የማሰባሰብ መንፈስ በማስታወስ "ሀገር በ10 ኪ.ሜ" የሚል መፈክርን ይዘዟል።
በአርቡ ፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ ከተዋወቁ ሌሎች እንግዶች መካከል አሜሪካዊው የቀድሞ የማራቶን የዓለም ሬኮርድ ባለቤት ካሊድ ካኑቺ እና ኬኒያዊው የቀድሞ የ3000ሜ እና 5000ሜ የዓለም ባለ ሬኮርድ ዳንኤል ኮመን ይጠቀሳሉ። ኮመን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ሶስት የ5000ሜ የዓለም ሬኮርዶች ያሰበረውን (ሁለት የኃይሌ እና አንድ የኮመን) ከኃይሌ ገብረስላሴ ጋር የነበረውን ተፎካካሪነት አስታውሷል።
የሩጫው ቀናት የሚጀምረው ነገ (ቅዳሜ) ማለዳ በእንጦጦ ተራራ በሚካሄደዉ የንጋት የ3ኪ.ሜ. ሩጫ ሲሆን፣ ከዚያም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የ2018 ዩኒሴፍ የልጆች ሩጫ ይደረጋል። ተጠባቂው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድር የሚካሄደው እሁድ ይሆናል።
ተሳታፊዎች ጠዋት 1፡00 መስቀል አደባባይ እንዲደርሱ የውድድሩ ኦፕሬሽንስ ዳይሬክተር ዳግም ተሾመ ሲያሳስብ ፤ የፈጣን ማእበል መነሻ ግዮን ሆቴል እና የዘና ማዕበል መነሻ መስቀል አደባባይ እንደሚሆንም አስታውሷል፡፡
25ኛው ዓመት ልዩ ውድድር ላይ 55ሺህ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ። የዘንድሮ ውድድር አጋሮች ፤ ሶፊ ማልት የስያሜ አጋር ፣ ዩኒሴፍ የመልዕክት አጋር ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ አጋር ፣ ኢትዮ ቴሌኮምና ቴሌ ብር የቴክኖሎጂ አጋር ፣ ዳሽን ባንክ የባንክ አጋር ፣ ፋብ የውበት ሳሙና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫዎች የንዕህና አጋር ፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር ፣ ቶፕ ውሃ ፣ ሃያት ሬጀንሲ ፣ ኢ.ቢ.ሲ. እና አፍራን ሆስፒታል ናቸው።
❤8
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለ2019 ሩጫችን ነገ ነው ምዝገባችን!✨
በባንክ ኦፍ አሜሪካ ለሚቀርብላችሁ የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ዝግጁ?✨
ቀድመው በቴሌብር ይመዝገቡ!
ለፈጣን ማዕበል 900.00 ብር ወይም
ለዘና ማዕበል 700.00 ብር በመክፈል ይመዝገቡ።
#GreatEthiopianrun #PowerToDo #InspireNextGeneration #2026Registration

❤33👍9
✅ በቴሌብር ምዝገባ ጀምረናል! 🤩
ለፈጣን ማዕበል 900.00 ብር ወይም ለዘና ማዕበል 700.00 ብር በመክፈል ይመዝገቡ! ✨
በባንክ ኦፍ አሜሪካ የሚቀርብላችሁ የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.
ቀድመው ይመዝገቡ!

❤27👍15
ጋዜጣዊ መግለጫ
የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ደብረ ብርሃን እና ሐረርን በመጨመር ዛሬ በይፋ ተጀመረ
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ በሚል ስያሜ በስድስት የክልል ከተማዎች ላይ ተከታታይ የሩጫ ውድድር ሊያዘጋጅ ነው።
በ2017ዓ.ም. በ4 መዳረሻ ከተማዎች ላይ የተካሔደው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተከታታይ ውድድር ፤ በዚህም ዓመት ደብረብርሃን እና ሐረርን በመጨመር 6 ከተማዎች ላይ ይካሔዳል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፈውም ዓመት አዘጋጅ በነበሩት ሐዋሳ፣ ጅማ፣ ቦቆጂ እና አርባምንጭ ላይ ለተከታታይ ዓመታት እንዳደረገው ሁሉ ዘንድሮም ስኬታማ ውድድሮችን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ይህ ስፖርት እና ቱሪዝምን በማቀናጀት የሃገራችንን ከተሞች እና የቱሪዝም ስፍራዎችን በስፋት እያስተዋወቀ የሚገኘው መርሃግብር አዳዲስ ከተሞችን በመጨመር ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የሚካሔድ ሲሆን ከጥር እስከ ሐምሌ ፤ ከአንኮበር እስከ ሐረር በር የሚል መርህ ተሰጥቶት ይካሔዳል።
የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ የስድስት ከተሞች ተከታታይ ውድድር ይፋ በተደረገበት የዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስፖርት እና ቱሪዝምን በማስተሳሰር እየሰሯቸው ያሉትን ስራዎች ይበልጥ አጠናክሮ ለመስራት የሚያስችላቸው የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) “ልወቅሽ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያንን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሀገራት ተሳታፊዎችን መሳብ የቻለ ዝግጅት ለመሆን በቅቷል። በዚህ አጋጣሚ ደብረ ብርሃን እና ሐረር የዘንድሮውን ልወቅሽ ኢትዮጵያ መቀላቀላቸዉን ማብሰር እፈልጋለሁ” ብለዋል።
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ መሃመድ በበኩላቸው “ስፖርትን ከቱሪዝም ጋር በማጣመር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እየሰራ ያለዉን ስራ እንደ ሚኒስትር መስሪያ ቤት የምናደንቀው እና የምንደግፈው ነው ፤ ከዚህ በኋላ አብረን የምንሰራ ይሆናል ’’ ብለዋል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ በበኩላቸው “ለሃገራችን ‘ልወቅሽ ኢትዮጵያ’ የሚባል አዲስ የቱሪዝም ምርት በማስተዋወቃችን እና ከሩጫ ውድድርነት ባሻገር ኢትዮጵያን በትንሹም ቢሆን ማሳየት በመቻላችን ደስተኞች ነን ፤ ይህ እንዲሳካልን ለሚያግዙን ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ሁሉም አጋሮቻችን ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ተሳታፊዎችም አብረውን እንዲጓዙ እጋብዛለሁ” ብለዋል።
ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎን፣ ጓደኝነትን እና አንድነትን የሚያበረታታው ልወቅሽ ኢትዮጵያ በደብረ ብርሃን ከተማ በጥር 03 ቀን 2018ዓ.ም. የማራቶን ዱላ ቅብብል እና የሀገር አቋራጭ ውድድሮችን በማካተት ጅማሮውን ያደርጋል።

❤6👍3👏2
💫መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!
ሩጫን የአኗኗር ዘይቤያችን እናድርግ💫
#GreatEthiopianRun #DiscoverEthiopiaClassics #2026Registration #6CitiesSeries #DebreBirhan

❤11👍7
ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ2018 የ“ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” ተከታታይ ውድድሮችን በአጋርነት
ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ - ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም - ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ2018 የ”ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ”
(Discover Ethiopia Classics) ተከታታይ ውድድሮችን በአጋርነት ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት አድርገዋል። በስምምነቱ መሰረት
ኢትዮ ቴሌኮም በአምስት ዋና ዋና ክልላዊ ውድድሮች ላይ የስያሜ ስፖንሰር (Title Sponsor) በመሆን የሚሳተፍ ሲሆን፤ ይህም ኩባንያው
ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ለቱሪዝም እድገት ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት እና ጽኑ ቁርጠኝነት አንዱ ማሳያ ነው፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም የ2018 የሩጫ ተከታታይ ውድድሮችን በአምስት ከተሞች ማለትም በደብረ ብርሃን፣ ሐዋሳ፣ ጅማ፣ በቆጂ እና ሐረር
የሚደረጉት ውድድሮች የስያሜ አጋር ሲሆን፣ የመጀመሪያው ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በደብረ ብርሃን ጥር 3 ቀን 2018 ዓ.ም የሚጀምር
ይሆናል፡፡ ይህም ጤናማ እና አምራች ዜጋን ከመገንባት ባሻገር የኢትዮጵያን ውብ መልክዓ ምድሮች፣ ታሪካዊ ቦታዎችና ባህሎች ለማስተዋወቅ
እና መልካም ማህበራዊ ትስስሮችን ለማጠናከር የላቀ ሚና ይኖረዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም የታላቁ ሩጫ የቴክኖሎጂ አጋር በመሆን ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ተሞክሮ እንዲኖራቸው የሚያስችል ልዩ
የሩጫ መተግበሪያ (Running App) በማበልፀግ በስራ ላይ ያዋለ ሲሆን፣ ይህም መተግበሪያ በየትኛውም የሀገራችን አካባቢዎች ለሚከናወኑ ውድድሮች በውድድር ወቅት ያሉ መረጃዎችንና መገኛ ቦታን በቀጥታ ለመከታተል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይሰጣል። ይህ የቴክኖሎጂ ትስስር ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የአኗኗር ዘይቤን ለማስተዋወቅ ከሚያከናውናቸው ስትራቴጂዎች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡
በስምምነቱ ወቅት የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኮሙኒኬሽን ኦፊሰር መሳይ ውብሸት እንደገለፁት ኩባንያው ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር ዘመኑ
የደረሰባቸውን አዳዲስ የቴሌኮም ቴክኖሎጂዎች እና የዲጂታል ሶሉሽኖችን በሀገራችን ተግባራዊ በማድረግ የዲጂታል ኢትዮዽያን ራዕይ እውን
ለማድረግ እያከናወነ ከሚገኘው መጠነ ሰፊ ስራዎች በተጨማሪ ከሌሎች ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በመተባበርና በመቀናጀት ለሀገራችን
ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡
አክለውም “ይህ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ“ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” ተከታታይ ውድድሮች አጋርነት ስምምነትም የዚህ ኢንሸቲቭ አንዱ
አካል ሲሆን፣ ኩባንያው በአካልና በስነ-ልቦና የተገነባ ጤናማ ትውልድ ለመገንባት፣ የሩጫ ውድድሮቹ የሚካሄድባቸው ከተሞችን ይበልጥ
ለማስተዋወቅና የቱሪዝም መዳረሻ ፍሰትን ለመጨመር እየተከናወኑ የሚገኙ ጥረቶችን ለማጠናከር እንዲሁም በሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ
እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በመግለጽ በቀጣይም ለሀገራችን እድገት ቁልፍ ሚና ያላቸውን ተግባራት በመለየትና በቴክኖሎጂ
እንዲታገዙ በማድረግ አጋርነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ በበኩላቸው “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሁልጊዜም ከሩጫ በላይ መሆኑን
በመግለፅ ባህላችንን እና ህዝባችንን የምናውቅበት እና የምናስተዋውቅበት መድረክ ነው” ብለዋል። ዋና ስራ አስኪያጇ አክለውም “ኢትዮ
ቴሌኮምን እንደ ዋና አጋር ማግኘታችን ውድድሮቹን ወደ ላቀ ደረጃ እንድናሸጋግር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው” ብለዋል፡፡
ይህ አጋርነት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪዝምን ለማሳደግ ያለውን የጋራ ራዕይ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ የደብረ ብርሃንን ታሪካዊነት፣
የሐዋሳ ሃይቅን ውብ ገፅታ፣ የጅማን የቡና መገኛነት፣ የአትሌቶች መፍለቂያ የሆነችውን በቆጂን በማጉላት እና የሐረርን የቱሪስት መስህብነት
አጉልቶ በማሳየት ኢትዮጵያን የስፖርት ቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ ያለመ ነው።
ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ
ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም

❤15🔥2👍1