Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
6.05K subscribers
2.46K photos
190 videos
6 files
276 links
Official Great Ethiopian Run Telegram Channel.

Call 0116635757 for more details.
Download Telegram
🚨 ማስታወቂያ! ለክለቦች፣ ለአትሌት ማናጀሮች እና በግል ለሚወዳደሩ አትሌቶች በሙሉ 🏃🏾‍♀️🏃🏾

የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. የአትሌቶች ምዝገባ ተጅምሯል!

ምዝገባ:- ላምበረት ማራቶን ህንፃ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአችን በመግኘት አልያም በስልክ በመደወል እንድትመዘገቡ / አትሌቶቻችሁን እንድታስመዘግቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ለበለጠ መረጃ
011-663-5757
011-663-3646

#GreatEthiopianRun #Ethiopia #ANATIONIN10KM #10k
12👍2
በነጻ 💫ምዝገባ!!!!

የእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ምዝገባ ተጀምሯል!

ለአዲስ አመት አዲስ ስጦታ!

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ💫💫

#GreatEthiopianrun #Ethiopia #entoto #cbe
👍1813
ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ በእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን እንገናኝ!

📌ጥቅምት 1 / 2018!

አሁኑኑ በሲቢኢ ብር ፕላስ ተመዝግበው ይቀላቀሉን!

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ

#GreatEthiopianRun #EntotoCBERun
7🤩1
🎉 50 ቀናት ብቻ - ቀሩን! 📢

ሀገር በ10ኪ.ሜ.

በአንድነት ድምቅ ፍክት ልንል - 50 ቀናት ብቻ ይቀሩናል

💫 2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ህዳር 14

#GreatEthiopianrun #25thEdition #10k #ANationIn10km
18👏8
የ2018 ዩኒሴፍ የልጆች ሩጫ ምዝገባ እና ‘ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ’ ዘመቻ ተጀመረ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ2018 ዩኒሴፍ የልጆች ሩጫ ምዝገባን እንዲሁም የ'ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ' ዘመቻ ማስጀመሩን ዛሬ በህያት ሬጀንሲ በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ አድርጓል።

በተለያዩ የዕድሜ ደረጃዎች ለልጆች የሚዘጋጀው ይህ ልዩ የውድድር ቀን ከ11 ፣ ከ8 እና ከ5ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች ሁሉ ክፍት ነው።

ከነገ ጀምሮ በቦሌ አለም ሲኒማ እና በታላቁ ሩጫ ቢሮ ላምበረት ምዝገባ የሚካሔድ ሲሆን ፤ የመመዝገቢያ ዋጋ 400 ብር ብቻ ነው ሲሆን ‘የልደት ምዝገባ ለሁሉም ህጻናት’ በሚል መሪ ቃል ይካሔዳል።

በተጨማሪም በመግለጫው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. አካል የሆነው የ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ የበጎ አድራጎት ዘመቻ መጀመሩ ይፋ ተደርጓል።

ዘንድሮም በዘመቻው አራት (4) ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ የታቀደ ሲሆን ፤ ቼሻየር ኢትዮጵያ ፣ ተስፋ ማህበራዊ እና ልማት ማህበር እና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ድጋፍ እንዲደረግላቸው በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የተመረጡ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ናቸው።

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያሉ የታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች ደጋፍ ማሰባሰብ የሚችሉባቸው የድረ-ገፅ እና የመሰብሰቢያ ቅጽ  አማራጮች ይፋ ተደርገዋል። በተጨማሪም የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ምዝገባ ላላከናወኑ በተጨማሪ ክፍያ የሚደረግ ጥቂት ምዝገባ ለዚሁ አላማ ይውላል።

በዝግጅቱ ላይ ባለፉት የውድድር ዓመታት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ40ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ እንዲችል ያገዙ እና ድጋፍ ያሰባሰቡ ድርጅቶች  እና ግለሰቦች ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
19🔥3👍2👏1
🚨ማስታወሻ በግል ለምትወዳደሩ ወንድ አትሌቶች በሙሉ! 🏃‍♂️🏃‍♂️🏃‍♂️

የአትሌቶች ማጣሪያ የፊታችን ቅዳሜ በእንጦጦ ፓርክ ስለሚካሄድ ምዝገባችሁን ያላጠናቀቃችሁ ከአሁኑ እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን።

ማለዳ 12:00ሰዓት ላይ ወደ እንጦጦ የሚወስዳችሁ መኪና 4ኪሎ ምኒሊክ ትምህርት ቤት ጋር ስላዘጋጀን ከ12:00 በፊት እንድትገኙ!

🗓 ቅዳሜ - ጥቅምት 1 ቀን 2018

2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.

#GreatEthiopianrun #10k #25thEdition #ANationIn10km #Ethiopia #EntotoPark
12👍2🤩1
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ህዳር 14 ቀን በሚደረገው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ላይ ለሚያሸንፉ አትሌቶች በድምሩ ከ1.8ሚሊዮን ብር በላይ ሊሸልም ነው።

ከ2017 ዓ.ም. ጀምሮ የአለም አትሌቲክስ (Label Road Race) ደረጃ የተሰጠው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ሃያ አምስተኛ ዓመት ውድድሩን በማስመልከት በአንደኛነት ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች የሚያበረክተውን የገንዘብ ሽልማት ወደ አራት መቶ ሺህ (400,000) ብር ከፍ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ሽልማቱ በውድድሩ ላይ ባለፈው አመት ለአሸናፊዎች በሽልማትነት ተበርክቶ ከነበረው 250ሺህ ብር በስልሳ በመቶ (60%) አድጓል። በተመሳሳይ ሁለተኛ ለሚሆኑ የ200ሺህ አንዲሁም ሶስተኛ ሆነው ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች የ100ሺህ ብር ሽልማት አንደሚበረከት ይፋ ተደርጓል።

የውድድሩን ጥራት አና የአትሌቶችን ፉክክር ከፍ ማድረግ አንዲቻልም በክለብ አና የስፖርት ማኔጅመንት ውስጥ ከሚገኙ አትሌቶች በተጨማሪ በግል ለሚወዳደሩ አትሌቶች ዕድል ለመፍጠር ቅዳሜ ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም. በእንጦጦ ፓርክ የማጣሪያ ውድድር ይካሔዳል። ይህም ማጣሪያ በግል ለሚወዳደሩ አትሌቶች በውድድሩ ላይ የመሳተፍ ዕድልን ይፈጥርላቸዋል።

ቅዳሜ ከአትሌቶች የማጣሪያ ውድድር በተጨማሪም 9ኛው ዙር የወርሃዊው እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ላይ ባለፉት ውድድሮች ላይ ሰባት እና ከዛ በላይ ለሆነ ጊዜ የሮጡ ተሳታፊዎች ልዩ ሽልማት ይበረከትላቸዋል።
27
💫ሰባተኛ ዙር ልምምዳችንን ከአህመድ የጤና ቡድን አባላት ጋር

እሁድ ወሎሰፈር እንገናኝ

የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.

#GreatEthiopianrun #25thEdition #10k #ANationIn10km
👍156🔥1
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻው አዲስ ታሪክ ለመፃፍ አልሟል

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ2018 ሶፊ ማልት አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድሩ ጋር አያይዞ በየዓመቱ በሚያካሂደው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከ4 ሚሊዮን ብር የበለጠ ለመሰብሰብ አልሟል።

ይህም በውድድሩ አማካይነት በተሰበሰበ ገንዘብ መጠን ቀዳሚውን ቦታ የሚይዝ ይሆናል፡፡ ዘመቻው ባለፈው ዓመት ከ3 ሚሊዮን ብር የበለጠ አሰባስቧል፡፡ ከ25 ቀናት በኋላ ፤ ህዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. የሚካሄደው የዚህ ዓመቱ ውድድር 25ኛ ዓመቱን የሚያከብርበት በመሆኑ በተለየ ስሜት እየተዘጋጀም ይገኛል፡፡
 
‹ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ› በሚል የሚጠራው ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ የተጀመረው በ1998 ዓ.ም. ፤ በ5ኛው የውድድር ዓመት ነበር፡፡ ባለፉት 20ዓመታት በዘመቻው ከ43 ሚሊዮን ብር የበለጠ ተሰባስቦ ከ60 ለበለጡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ተከፋፍሏል፡፡
 
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዚህ ዘመቻ አስተባባሪ አብድራዛቅ አለዊ፣ ከታለመው የገንዘብ መጠን 75በመቶውን መደበኛው የምዝገባ ጊዜ ከተዘጋ በኋላ በተከናወነው የመጨረሻው የምዝገባ ጊዜ ከፍ ባለ ዋጋ ከተከናወነው ምዝገባ ለማሰባሰብ እንዳቀዱ ገልጿል። ለዘመቻው ድጋፋቸውን ሲሰጡ የቆዩ በርካታ ድርጅቶች ለጋስነትንም ጠቅሶ አመስግኗል።
 
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአምስት ዓመታት በፊት ጀምሮ GivenGain በተሰኘው ድረ-ገፅ አማካይነት ከሀገር ውጪ የሚገኙ ተሳታፊዎችም ለዘመቻው ድጋፍ እንዲያደርጉ ማመቻቸቱ ይታወቃል።
 
በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ተመርጠው በዚህ ዓመት ተጠቃሚ የሚሆኑት ሶስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ቼሻየር ኢትዮጵያ ፣ ተስፋ ማህበራዊ እና ልማት ማህበር እንዲሁም የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ናቸው፡፡
36👍11
ቴርጋት ፣ ታኑይ እና ኮመን  - የኃይሌ ገ/ስላሴ ታላላቅ ተፎካካሪዎች - በ25ኛ ዓመት የታላቁ ሩጫ ውድድር ላይ ይገኛሉ

ከኬንያ አንጋፋ የረጅም ርቀት ሩጫ አትሌቶች መካከል ሦስቱ - ፖል ቴርጋት፣ ዳንኤል ኮመን እና ሞሰስ ታኑይ – እሁድ ህዳር 14 ቀን 2018 በሚካሄደው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪሎ ሜትር ላይ ለመገኘት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ተገለፀ።

ሦስቱም አትሌቶች በዓለም አቀፍ የሩጫ ሕይወታቸው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን በ1994ዓ.ም. ከመሠረተውና የኢትዮጵያ የረዥም ርቀት ሩጫ ምልክት ከሆነው ከኃይሌ ገብረሥላሴ ጋር ከፍተኛ ተፎካካሪነት ነበራቸው።

ቴርጋት ቀደም ሲል እ.ኤ.አ. በመስከረም ወር 2003 በበርሊን የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ከሰበረ በኋላ በውድድሩ ላይ በእንግድነት ተገኝቶ ነበር። በ1990ዎቹ ከኢትዮጵያዊው ጓደኛው ኃይሌ ጋር ከፍተኛ ፉክክር የነበረው ሲሆን ፤ በ1996 እና በ2000 ኦሎምፒክ ኃይሌን በመከተል የብር ሜዳሊያውዎችን አግኝቷል። ሁለቱም ወደ ማራቶን ሲያድጉም ፉክክሩ የቀጠለ ሲሆን፣ ኃይሌ በሴፕቴምበር 2007 በመጀመሪያው የማራቶን ክብረ ወሰን የዓለም ሪከርዱን ከቴርጋት በ29 ሰከንድ ልዩነት ወስዷል።

ዳንኤል ኮመንም ከ1996 እስከ 1998 ባሉት ሦስት ዓመታት በትራክ ላይ ከኃይሌ ገብረሥላሴ ጋር ከባድ ፉክክር ነበረው።

እ.ኤ.አ. 1996 በተካሔደው የአትላንታ ኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ ያልተካተተው ኮመን በሴፕቴምበር 1 ቀን 1996 በጣሊያኗ ሪየቲ የ3000 ሜትርን 7፡20.67 በመሮጥ  የዓለም ክብረ ወሰንን ይዞ ነበር ፤ ይህም ጃኮብ ኢንገብሪግስተን በኦገስት 2024 እስኪሰብረው ድረስ ለ28 ዓመታት ያህል ዘልቋል። በ1997 ኮመን የ5000ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን 12፡39.74 በመሮጥ ከኃይሌ ወስዶ የነበረ ቢሆንም ኃይሌ በ12፡39.36 በመሮጥ በአንድ ዓመት ውስጥ መልሶ ወስዶታል።

ሞሰስ ታኑይ በዚህ ወር መጨረሻ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜው ነው። ታኑይ የሁለት የዓለም ሻምፒዮና አሸናፊ (በ1991 በትራክ እና በ1995 በጎዳና ላይ) ሲሆን ፤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአጋርነት የሚሰራው የኤልዶሬት ማራቶን የውድድር ዳይሬክተር ነው። ታኑይ በ1993 የዓለም ሻምፒዮና የ10,000ሜትር ውድድር ላይ ከኃይሌ ገብረሥላሴ ጋር አይረሴ ፉክክር ቢያደርግም በመጨረሻው ዙር ጫማው በመውለቁ ኃይሌ አሸንፎት እንደነበር ይታወሳል።

ሶስቱም የኬንያ ታላላቅ አትሌቶች ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ በእንግድነት ታድመውበት በነበረው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መድረክ ላይ በድጋሚ ከኃይሌ እና ከሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ጋር መገኘት የ25ኛውን ዓመት ክብረ በዓል በሚያደምቁት 55,000 ተሳታፊዎች ላይ ተጨማሪ ደስታን ይፈጥራል።

የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪሎ ሜትር መነሻዎቹን መስቀል አደባባይ እና ግዮን ሆቴል በማድረግ ፤ እሁድ ህዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. ይካሔዳል።
27🔥2👏1
2 ሳምንት ብቻ ቀርቶናል - እየተዘጋጃችሁ ነው?

የ9ኛ ሳምንት ልምምዳችንን ፤ ከህያት ሬጀንሲ እና ከብላቴና ጤና ቡድን ጋር ሆነን እንቀጥላለን

እሁድ ማለዳ ወሎሰፈር አደባባይ  እንገናኝ!
2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.!

#GreatEthiopianRun #10k #25thEdition #ANationIn10km #RaceInNumbers #10WeeksChallenge
20👍3
ለሚድያ ባለሞያዎች - የመጨረሻ ጥሪ!

ሀዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. ለሚካሔደው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድር ላይ በቦታው ተገኝተው መዘገብ ለሚፈልጉ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሚድያዎች የይለፍ መታወቂያ ለማዘጋጀት ፤ ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም እንድትመዘገቡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የመጨረሻ ጥሪውን ያቀርባል!

የሚድያ ምዝገባ የምናከናውነው እሰከ 08 ህዳር 2018ዓ.ም. ነው!

👉 https://ethiopianrun.org/accreditation
9👍1