Golden Age
1.87K subscribers
276 photos
9 videos
151 files
524 links
Explore our channel for inspiring and motivating content, including speeches, videos, photos, and written pieces. Discover book reviews, future plans of rFIR, and join us on a journey of growth.
Youtube channel https://www.youtube.com/@GoldenAgerfir
Download Telegram
ወዳጆቼ ... አላህ ወደቀልባችን ተመልክቶ ከሱ ዉዴታ ዉጭ ሌላ ትልቅ ዓላማ እንደሌለን ካወቀ በቂ ነው።

አላህ ሆይ ትልቁ ሀሳባችን አንተ ነህ ማለትም ወደርሱ መቃረብ (ተወሱል) ነው።

https://t.me/GoldenAge2013
እንደ ጨለመ አልቀረምና ነጋ :: በህይዎት ጉዞ ውስጥ ምሽት ውስጥ ያላችሁ ሰዎችም ህጉ ነውና ንጋት እንደሚመጣ ከልባችሁ እመኑ :: ከጨለመ ብርሃን ይመጣ ዘንድ ለጧት ፀሐይ ትዕግስት ለማታ ብርሃን ደግሞ የማብራት ያስፈልጋል :: ለዚህ ጊዜና ቦታ ገደብ ሲኖረው በየትኛውም ጊዜና ቦታ ብርሃንን ለማግኘት ከፈለጋችሁ ደግሞ የአላህን ብርሃን መከጀል ግድ ነው :: ለእርሱ ደግሞ አንድ ነገር ያስፈልጋል :: ሰዎች በጨለማው ተሸንፈው ጥልቅ እንቅልፍ ላይ በሆኑበት ሰዓት ንቃት ውስጥ ሆኖ ከላይ የሚወርደውን የእርሱን ብርሃን መቀበል ማለት ነው :: ሌሊት ለእርሱ ሲሉ ከሚነቁት ያድርገን :: ጨለማችን ይገፈፍ :: ህይዎታችን በብርሃን ይሞላ :: አሚንንን !!

መልካም ውሎ !!

https://t.me/GoldenAge2013
ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ?
🌹🌹🌹 💎💎 🌹🌹🌹

💚 በእናቱ ሆድ ውስጥ እያለ ወላጅ አባቱን በሞት ተነጠቀ።

💛 የስድስት ዓመት ህፃን እያለ ወላጅ እናቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ?

❤️ የስምንት ዓመት ህፃን እያለ በፍቅር ተንከባክበው ያሳደጉት አያቱን አይቀሬ የሆነው ሞት ወሰዳቸው።

💚 እንደ አይን ብሌናቸው የሚሳሱለት አጎቱ እና በማራኪ ስብዕናው ተረታ የትዳር አጋሩ ለመሆን የበቃቸው ውድ ባለቤቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ከአይኑ ተሰወሩ። ለህይወቱ ወሳኝ የነበሩትን ምሰሶዎች ሞት ነጠቀው። ያ ፈታኝ ጊዜ «የሀዘን ዓመት» የሚል ስያሜ ተሰጠው።

ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ??

💛 በምድር ላይ ከሁለት ዓመታት ዕድሜ በላይ ያልቆዩ ሁለት ህጻናት ወንድ ልጆቹን በማለዳ ሞት ቀጠፋቸው። በህፃናቱ ፈገግታ ደምቆ የነበረው ቤት የሀዘን ጥላ አጠላበት።

❤️ ከእርሱ ህልፈት በኋላ በስድስተኛው ወር በሞት ከተከተለችው ተናፋቂ ልጁ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ልጆቹ በህይወት እያለ ወደ መጪው ዓለም ተጓዙ።

ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ?

💚 የአባቱ ጥሪት የነበሩት አጎቱ ተገደሉ። መገደል ብቻም ሳይሆን የሰው ልጅ ያደርገዋል ተብሎ የማይታሰብ ጭራቃዊ ተግባር በአካላቸው ላይ ተፈፀመ። አንዲት እንስት አስክሬኑን በሰንጢ አስቀድዳ ጉበቱን በላችው። የዚህ ሰው ሀዘን ከሚገመተው በላይ በረታ።

💛 ጧኢፍ ነዋሪዎቿን በነቂስ አውጥታ የስድብ እና የድንጋይ ናዳ እንዲወርድበት ፈቀደች። ምድር ከሰውነቱ የሚፈሰውን ደም መጠጠች። ታሪክ ክስተቱን በደማቅ ገጹ አስፍሮ ለትውልድ አስተላለፈ።

ጧኢፍ መስክሪ ለዚያ አርበኛ
ለሰላሙ አባት ለዓለም ሁነኛ
ነዋሪዎችሽ የሰሩት ግፍ
በሙሐመድ ላይ ባንቺው ደጃፍ
መላ አካሉን አሰቃዩት
ሰላም ባመጣ በደም ሸኙት
ያሆደ ባሻ ይቅር አላቸው
ሊጠፉ ደርሰው ደረሰላቸው


ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ??

❤️ በአንድ ታላቅ ዘመቻ የፈት ጥርሱ ተሸረፈ። ብርሃናማ ፊቱ በደም ተለወሰ።

💚 ግንባሩን ከመሬት አዋዶ ከፈጣሪው ጋር በለሆሳስ ሲያወራ የመካ ቂሎች በትከሻዎቹ መሃል የግመል አንጀት እና ደም ሲያፈሱበት ግንባሩን ከመሬት ለአፍታ አላነሳም ነበር።


ስለዚህ ሰው ምን ትላላችሁ ?

💛 በመተት እና ድግምት ሲያሰቃኙት፣ በመርዝ የተለወሰ ምግብ ሲሱጠት፣ ከሚናፍቅው የትውልድ ቀዬ ሲባረር «ይቅር ባይነት» የዘውትር ስንቁ ነበር ።

❤️ ይህን ሁሉ ስቃይ በተሸከመ አካልና መንፈሱ ታግዞ እግሮቹ አስከሚያብጡ ድረስ ሌሊቱን ሙሉ በመቆም አመስጋኝ ባሪያ ለመሆን ከአምላኩ ጋር ያወጋል።


እናት ለልጇ በትምህርቱ ዓለም ብቻ የከፈለችውን መስዋዕትነት ብንፈትሽ አንድ ነገር ይከስትልናል። ለአብራኳ ክፋይ ከልጅነት እስከ ወጣትነት የዕድሜ ዘመኑ የዋለችው ውለታ መለኪያ የለውም። ከማዋዕለ-ህፃናት እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ይዘልቅ ዘንድ በትንሹ 23 ዓመታትን የፈጀ ጥረት ታደርጋለች። የእናት እያንዳንዱ የህይወት ምዕራፍ በአደገኛ ምጥ የተሞላ ነው። አንተን ከወለደችበት ምጥ ባሻገር ሌላ ስፍር ቁጥር የለሽ የህይወት ምጥ አለ።

ይህን ከግንዛቤ ካስገባችሁ

ውስን በሆኑ 23 ዓመታት ውስጥ ብቻ የሰውን ልጅ ከፍጡራን ባርነት አላቆ አላህን ወደማምለክ ነፃነት ያሻጋገረ ፣ ከጠባብ ዓለማዊ ህይወት አውጥቶ ወደ ሰፊው የመንፈስ ዓለም ያመጠቀ ፣ ከምድራዊ እምነቶችና ስርዓቶች ጭቆና አላቆ ለኢስላም ፍትህ ያበቃ ፈርጡ የሰው ልጅ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم) ውለታ ምን ያህል የከበደ መሆኑን ትገነዘባለህ።

ልቦቻችን ውሃ እንዳጣ የዓረቢያ ምድረ በዳ ስንጥቅ በዝቶባቸዋልና ፈለግህን በመከተል በፍቅርህ ይረሰርሱ ዘንድ አላህ ያግዘን !!!

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

https://t.me/GoldenAge2013
ወርቅ የምታወጡና አትርፋችሁ የምትሸጡ ይመስል የሰዉን ገመና እና ነዉር አትከታተሉ።

የፈተና ወጥመድ አጥምዳችሁም ሰው ሲወድቅ አይታችሁ ለመሳቅም አትቸኩሉ።

ሰዎች ሁሉ ይፈተናሉ ።
የሚወድቁ አሉ።
የሚያልፉም አሉ።

ለወደቁት እዘኑላቸው እንጂ አትሳለቁ።
ስላለፋችሁ አመስግኑ እንጂ አትመፃደቁ።

ቀልባችሁ ሁኔታዎችን በሚገለባብጥ ጌታ እጅ እንዳለች አትዘንጉ።
ዛሬ ጠንካራ ብትሆኑ እንኳ ነገ ደካማ ልትሆኑ ትችላላችሁ።

https://t.me/GoldenAge2013
🔞አሳዛኝ ታሪክ ነው።

ሴትየዋ ልትወልድ ኦፕራሲዮን ክፍል አስገቧት ና ቆንጅዬ ወንድ ልጅም ተገላገለች።
ልክ ልጇን እንደተገላገለች እሷ ግን አረፈች።ባልየው በጣም አዘነ በራሱ ህፃኑን ተንከበክቦ ማሳደግ ስለማይችልም ህፃኑን
ለአክስቱ አስረከቦ ለ7 ወራት መራራ የሀዘን ግዚያትን ካሳለፈ በኋላ ሌላ ምስት አገባ።

ከአዲሷ ሚስቱም አሏህ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ልጅለሶ ሰጠው። ከ3 አመታት በፊት ለአክስቱ ሰጥቶ የነበረውንም የመጀመሪያ
ልጁን ከራሱ ጋ ሊያኖረው አመጣው።
ያን ግዜ የአዲሷ ምስቱ ሁኔታ ተቀየረ።

ይሄን 4 አመት ማይሞላው ጨቅላ ህፃን ትበድለው ጀመር። ያለ ርህራሄ በተደጋጋሚ ያለጥፋቱ ትቀጣዋለች። ጭንቀቷ ሁሉ ለራሷ ልጆች እንጂ ደንታም የላትም።ምግብም ከልጆችዋ ለይታው ለብቻው ነበር ምትሰጠው። የሆነ ቀን እች ሴት ቤተሰቦችዋን እራሷ ቤት እራት ግብዣ ትጣራቸዋለች።

የተለያዩ የምግብ አይነቶች ተዘጋጅተውም
ነበር እናም ይሄ እድሜው 4 ማይሞላው ጨቅላ (የሙት ልጅ) ከነዚህ ምግቦች ሊቀምስ እጁን ሲዘረጋ በጣም ትጮህበትና እያመናጨቀችው ከቤት ይዛው ትወጣለች።

ወደ በረንዳ አውጥታው እንግዳ እስኪወጣ ድረስ ከበረንዳ ንቅንቅ እንዳይል ታስጠነቅቀውና ቁራሽ ዳቦ በጁ አስይዛ እዛው
በረንዳ አስቀመጠችው። ሌሊቱ በጣም ይበርድ ነበር አይደለም ለህፃን ለአዋቂ ከባድ
ነበር።ብርዱም በጣም በረታበት ቤት ገብቶ እንዳይተኛ የ አባቱ ሚስት አስጠንቅቃዋለች።
ህፃኑም በገዛ ቤቱ ባዳ ሆኖ የሰጠችውን ቁራሽ ዳቦ እየበላ እዛው ተጣጥፎ እንቅልፍ ወሰደው።

ሰዐቱም ረፈደ እንግዳውም ወጣ ሴትዮዋም በረንዳ ያለውን ልጅ ረስታው ልጆችዋን ይዛ መኝታ ክፍሏ ገባች። ሰዓቱ ረፍዷል ባል ከስራ አርፍዶ ገባ። እራት ላቅርብልህ ስትለው ውጭ እንደበላ ነግሯት ልጁ የት እንዳለ ሲጠይቃት
"መኝታ ክፍሉ ተኝቷል" አለችው በዛ ብርድ በረንዳ እንደጣለችው ረስታ.. ሰውየውም ተኛ።

ወዲያው የቀድሞ ሚስቱ በህልሙ መጣችበት እና.... "ልጅህን ድረስለት" አለችው።
ሰውየውም ከእንቅልፉ ደንግጦ ተነሳና ልጁ የት ነው ብሎ ሚስቱን ሲጠይቃት..
"አልጋው ላይ ተኝቷል አልኩህ እኮ" አለችው።
ሰውየውም ድጋሚ ተኛ። ሟች ሚስቱ ድጋሚ በህልሙ መጣች። "ልጅህን ድረስለት" አለችው። ሰውየው ከመጀመሪያው በጣም ደንግጦ ከእንቅልፉ ነቃ።

"ልጄ የት ነው ያለው?" ብሎ ድጋሚ ጠየቃት
ሴትየዋም "ምንድነው ዝም ብለህክፍሉ ምትጨናነቀው ልጁ ተኝቷል አንተም በቃ ዝም ብለህ ተኛ" ትለዋለች። ሰውየውም ለሶስተኛ ግዜ ተመልሶ ተኛ።እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረገው በህልሙ የቀድሞ ሚስቱ ከመጀመሪያው ለየት ባለ ሁኔታ ፊቷን ቀይራ መጣችና...

"በቃ ተወው ልጁ እኔ ጋ መጥቷል" ስትለው
በድጋሚ ሰውየው ከእንቅልፉ ነቃ። ልጁ የሚያድርበትም ክፍል በፍጥነት ሲሄድ ልጁ የለም። በድንጋጤ ልጁን ይፈልገው ጀመር... ሁሉም ክፍል ፈልጎ አጣው ድንገት የበረንዳውን በር ሲከፍት...

ልጁ በረንዳ ላይ ነው ከብርዱ ብዛት ሰውነቱ ደርቋል። ጭንቅላቱን በሁለት እግሮቹ መሀል እስገብቶ....ሴትየዋ ከሰጠችው ቁራሽ ዳቦ ግማሿን በልቶ ግማሹ አጠገቡ ወድቋል።

አባቱ ሲያንቀሳቅሰው ምንም የለም ቀና ሲያረገው ልጁ ግን እችን አለም ተሰናብቷል።
ያለ እናት እቅፍ ያደገው ልጅ የእናቱ እቅፍ ናፍቆት ከናፈቃት እናቱም ተገናኝቷል...
😭😭😭😭😭😭😭😭
# ኢና_ሊላሂ_ወኢና_ኢለይሂ_ራጂዑን ይሄን ፅሁፉን ለወዳጅዎ ያጋሩ

በራሳቹ ልጅ ለይ እንዲደርስ ማትፈልጉትን በሰው ልጅ ለይ እንዲደርስ አትፍቀዱ።

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

https://t.me/GoldenAge2013
እንደማያችሁ ሆኜ የማወራችሁ ወዳጆቼ ሆይ ለኔም ለናንተም ሶባሐል ኸይር !

ጁሙዓ መሆኑን አስታውሳችኋል አይደል

* ጁሙዓ ቀን ሱብሒን በጀማዓ መስገድ ምንዳው ትልቅ ነው
* በሶደቃ ያለ ሶደቃም ያደራችሁ በማለዳ ሻወራችሁን ዉሰዱ፣

* የማለዳ ዚክር አስታውሱ፣
* ሶለዋት አብዙ፣
* ቁርአንን በዋናነት ሱረቱል ከህፍን አንብቡ፣

* ቀደም ብላችሁ መስጂድ ለመገኘት ሞክሩ፣
* አንዲት ድብቅ ሰዓት አለችና በተለይ ከዐስር በኋላ ፀሐይ እሰክትጠልቅ ድረስ ዱዓ አብዙ።
* በቀኑ ዉስጥ ሶደቃ፣ ዚያራም ሆነ ሌሎች ኸይር ሥራዎች ይወደዳሉ።


https://t.me/GoldenAge2013