Global Tech_Info
54 subscribers
5 photos
1 file
Daily Tech News | Tips | AI & Gadgets Updates | Hacks & Tutorials
👉https://t.me/GlobalTech_Info
Download Telegram
ጉግል በ9 ቢሊዮን ዶላር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የክላውድ መሠረተ ልማቶችን ሊያስፋፋ ነው፡፡

ኩባንያው ከትምህርት እና ከሰው ኃይል ፕሮግራሞቹ ጎን ለጎን በአሜሪካ አዳዲስ ዳታ ሴንተሮችን በመገንባት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የክላውድ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋት 9 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን አስታውቋል፡፡

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አገልግሎት ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ የክህሎት ልማት እና የዳታ ሴንተር ግንባታ ላይ ኢንቨስትመንቱን እንደሚያስፋፋ ኩባንያው ገልጿል፡፡

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከ100 በላይ በሚሆኑ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጉግል ለኤ.አይ ትምህርት እና ስልጠና 1 ቢሊዮን ዶላር መድቦ እየሰራ ነው፡፡

ኩባንያው በአሜሪካ እስከ 2027 ድረስ የ9 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ በመመደብ ዳታ ሴንተር እንደሚያስፋፋ ይፋ አድርጎል፡፡ ይህም ሰልጣኞችን እያደገ ላለው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ለማዘጋጀት ይረዳል። መዋለ ንዋዩ ዲጂታል ኢኮኖሚን በማሳደግ አሜሪካ በኤ.አይ ፈጠራ የዓለም መሪ ለመሆን የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደሚያሳድግ ተጠቁሟል፡፡

ጉግል ከአሜሪካ በተጨማሪ በሌሎች ሀገሮችም የኤ.አይ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶች እንደሚያስፋፋ ጠቁሟል፡፡
" የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል ይሸፍናል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከት ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች እንዲሁም ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ትናንት ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ደብዳቤ ልኳል፡፡

የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ሥራ አስፈጻማ ቴዎድሮስ ሽዋርገጥ (ዶ/ር) የተፈረመው ደብዳቤው፤ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል እንደሚሸፍንና ተማሪዎች የተማሩትን ይዘቶች የሚፈተኑ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ብሔራዊ ፈተናው ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይዘቶችን መሠረት ያደረገ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትምህርት ቤቶች 9ኛ ክፍልን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት፤ ሌሎቹ ደግሞ በቀድሞው ስርዓተ ትምህርት የተማሩ በመሆኑ ፈተናው ከሁለቱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ የሆኑ ይዘቶች ተጣጥሞ የሚወጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ሪፎርም መሠረት የሁለተኛ ደረጃ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ በማካሔድ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ መገባቱ ይታወቃል፡፡
ንስርኮፕ - ውጤታማ የወንጀል መከላከል ሥራን አስቀድሞ ለመስራት የሚያስችል ሲስተም

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #𝙸𝙽𝚂𝙰 ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ተኛ ጊዜ በ2017 ዓ/ም ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ከተሳተፉና ከተመረቁ ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች መካከል አንዱ ስለሺ አብርሃም ነው፡፡ ስለሺ በሰመር ካምፕ ቆይታው ውጤታማ የወንጀል መከላከል ሥራን አስቀድሞ ለመስራት የሚያስችል ንስርኮፕ (𝙽𝙸𝚂𝙸𝚁𝙲𝙾𝙿) የተሰኘ ሲስተም አበልጽጓል፡፡

ይህ ሲስተም በተለያየ ጊዜና ቦታ የተከሰቱ የወንጀል ድርጊቶችን ከተፈጸሙበት ቦታ፣ ጊዜና የወንጀል ዓይነት ጋር በማስተባበር የወንጀል ትንተና እና ስታትስቲክስ ሰርቶ ለወንጀል ክትትልና ምርመራ አካላት ያቀርባል፡፡ በቀረበው ስታትስቲካዊ መረጃ በመመስረት ውጤታማ የወንጀል መከላከል ሥራን አስቀድሞ ለመስራት አስፈላጊውን የሰው ኃይል በተገቢው ቦታና ሰዓት ለመመደብ ያስችላል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #𝙸𝙽𝚂𝙰 ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ተኛ ጊዜ ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም 629 ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች የተመረቁ ሲሆን፤ ተመራቂዎቹ በግልና በቡድን በመሆን ሰላሳ አንድ (31) ችግር ፈቺ የሆኑ ፕሮጀክቶችን ሰርተዋል፡፡
በተመራቂዎቹ የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
የቴሌግራም አካውንትዎ በመረጃ መንታፊዎች እጅ ከገባ ወይም ሌላ ሰው እየተጠቀመበት እንደሆነ ከጠረጠሩ ምን ያደርጋሉ? 

በኢትዮጵያ የቴሌግራም አካውንት መጠለፍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት እየተለመደ የመጣ የሳይበር ጥቃት ነው። ብዙዎች የሚያጋጥማቸው መጠለፍ በቴክኒክ ብቃት ሳይሆን በሰዎች የጥንቃቄ ጉድለት የሚፈጠር ነው።

የቴሌግራም አካውንትዎ በመረጃ መንታፊዎች (Hackers) እጅ ከገባ ወይም ሌላ ሰው እየተጠቀመበት እንደሆነ ከጠረጠሩ፣ በፍጥነት የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይኖርብዎታል፡-
1. ሌሎች መሣሪያዎችን ማቋረጥ (Terminate Sessions)
ይህ በጣም አስፈላጊው እርምጃ ነው። መንታፊው የከፈተውን ግንኙነት ለመዝጋት፦
•  ወደ Settings ይግቡ።
•  Devices (ወይም በአንዳንድ ስልኮች Privacy and Security > Active Sessions) የሚለውን ይጫኑ።
•  ከእርስዎ ስልክ ውጭ ያሉትን ሁሉንም መሣሪያዎች "Terminate all other sessions" በማለት ያስወግዱ።

2. ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) ማብራት
መንታፊው ተመልሶ እንዳይገባ ፓስዎርድ ማዘጋጀት አለብዎት፦
•  Settings > Privacy and Security > Two-Step Verification ውስጥ ይግቡ።
•  ጠንካራ ፓስዎርድ እና የማገገሚያ ኢ-ሜይል (Recovery Email) ያስገቡ።
•  ማሳሰቢያ፦ መንታፊው ቀድሞ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫን ካበራው፣ አካውንቱን "Reset" ለማድረግ 7 ቀን ሊጠብቁ ይችላሉ::
ዳታ ፕሮቨናንስ (Data provenance) ተዓማኒነት ላለው የኤ.አይ ቴክኖሎጂ

ዳታ ፕሮቨናንስ (Data provenance) ማለት የዳታዎችን ወይም የዳታ ቋቶችን ታሪክ፣ ከየት እንደመጡ፣ እንዴት እንደተሰበሰቡ፣ የማን እንደሆኑ፣ እንዴት እንደተሰሩ እና በመጨረሻም እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋሉ የመከታተል ሂደት ነው፡፡ ለውሳኔ አሰጣጥ እና ለኤ.አይ ቴክኖሎጂ አስፈላጊ የሆነው ዳታ መተማመንን፣ ተጠያቂነትን እና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የዳታ ፕሮቨናንስ አስፈላጊ መሆኑን የአይ.ቢ.ኤም ድረ-ገጽ መረጃ ያሳያል፡፡

የዳታ ፕሮቨናንስ መኖር የተለያዩ የኤ.አይ ሥርዓቶችን ለማበልፀግ ጥቅም ላይ የዋሉ ዳታዎች በሕጋዊ መንገድ የተሰበሰበ ስለመሆናቸው፣ ፍቃድ እንደተሰጠባቸው፣ ወይም በተሰበሰበው ዳታ ውስጥ የተደበቀ አድልዎ ወይም ማጭበርበር መኖሩን ማረጋገጥ እንዲቻል ያደርጋል፡፡

ለአብነት ሕመሞችን ለመመርመር ኤ.አይን የሚጠቀም የጤና አጠባበቅ ሥርዓት ውስጥ የዳታ ፕሮቨናንስ ሐኪሞች የታካሚውን ዳታ ከመነሻው እንዲከታተሉ፣ በሥነ-ምግባር መሰብሰቡን እንዲያረጋግጡ እና ቴክኖሎጂው ዳታውን የተጠቀመበትን መንገድ እንዲረዱ ያስችላል።

ይህም የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ይበልጥ ግልጽ፣ ተግባራዊ ለማድረግ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከሰው ልጅ እሴቶች እንዲሁም ፍላጎቶች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ አቅም የሚሆን ነው፡፡
የመረጃ መንታፊዎች የዋትሳፕ አካዉንትዎን ለመጥለፍ ምን አይነት ስልቶችን ይጠቀማሉ?

በሀገራችን በአሁኑ ወቅት የሚፈጸሙ የዋትሳፕ ጥቃቶች ከረቀቀ የቴክኖሎጂ ስርቆት ይልቅ፣ የሰዎችን ስነ-ልቦናዊ ክፍተት እና ማህበራዊ ትስስርን መነሻ ያደረጉ ናቸው።

ጠላፊዎች የእኛን ጠንካራ ማህበራዊ መስተጋብር፣ ለሃይማኖታዊ ተቋማት ያለንን ጥልቅ አክብሮት እና ለጋራ ጉዳዮች (ግሩፖች) የምንሰጠውን ከፍተኛ እምነት እንደ ጥቃት መሳሪያ በመጠቀም አካውንታችንን ይዘርፋሉ።

🛑የጥለፋው ሂደት ደረጃ በደረጃ

👉1.ስልክ ቁጥርን ማደን: ጠላፊው መጀመሪያ የእርስዎን ስልክ ቁጥር ከተለያዩ የዋትሳፕ ግሩፖች የተቋም፣ የእቁብ፣ የሃይማኖት፣ የሰፈር ወይም የገበያ ግሩፖች ላይ ያገኛል።

👉2.በእርስዎ ቁጥር አካዉንት የመክፈት እንቅስቃሴ: ጠላፊው በራሱ ስልክ ላይ የዋትሳፕ አፕሊኬሽኑን ከፍቶ የእርስዎን ስልክ ቁጥር ያስገባል። በዚህ ጊዜ ዋትሳፕ ትክክለኛው ባለቤት መሆንዎን ለማረጋገጥ ወደ እርስዎ ስልክ በኤስኤምኤስ (SMS) ባለ 6 አሃዝ ኮድ ይልካል።

👉3. የማታለያ መልእክት: ይህ የጥቃቱ አደገኛ ክፍል ነው። ኮዱ ወደ ስልክዎ እንደደረሰ፣ ጠላፊው በሚከተሉት መንገዶች በማታለል ኮዱን እንዲነግሩት ያደርጋል፦

#የግሩፕ_አድሚን_በመምሰል፦ "ከግሩፑ እንዳትወጣ አሁን የደረሰህን የደህንነት ኮድ ላክልኝ" በማለት ያስፈራራል።

#የቅርብ_ሰው_በመምሰል፦ ቀድሞ የተጠለፈ የጓደኛዎን አካውንት በመጠቀም "በስህተት ወደ አንተ ስልክ ኮድ ልኬያለሁ፣ እባክህ መልስልኝ" ይላል።

#የሽልማት_ድርጅት_በመምሰል፦ "የቴሌ ወይም የባንክ ሽልማት ደርሶዎታል፣ ለማረጋገጥ ኮዱን ይንገሩን" በማለት የሰዉን የማግኘት ጉጉትን እንደ ማታለያ ይጠቀማል።
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ነጥቦች ተግባራዊ ያድርጉ

በሀገራችን ኢትዮጵያ ከ12 ሚሊየን በላይ እንዲሁም በዓለማችን 3.7 ቢሊየን ገደማ ንቁ ወርሃዊ ተጠቃሚዎች (Active users) ያሉት ፊስቡክ የማሕበራዊ ትስስር ገጽ፤ በርካታ መንግስታዊ እና የግል ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ከተገልጋዮች  ጋር ቅርብ የሆነ ግንኙነት ለመፍጠር ይህንኑ ፕላትፎርም ይጠቀማሉ፡፡  

ይህን ያህል በርካታ ቁጥር ተቃሚዎች ያሉት የፌስቡክ  ገጽ በየእለቱ ከሦስት መቶ ሺ እስከ ስድስት መቶ ሺ ያህል የፕላትፎርሙ ተጠቃሚዎችን   አካውንቶችን ሰብሮ የመግባት (log in) የጥቃት  ሙከራዎች ያስተናገዳሉ፡፡ በርግጥ እነዚህ የጥቃት ሙከራዎቹ  ከሙከራ ሳይዘሉ በፕላትፎረሙ ጠንካራ  የደህንነት ስርአት ይከሽፋሉ፡፡

እነዚህን የጥቃት ሙከራዎች ለመከላከል ተቋማትም ይሁን ግለሰቦች የሚከተሉትን የጥንቃቄ መንገዶች ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸል፡፡