Global Tech_Info
54 subscribers
5 photos
1 file
Daily Tech News | Tips | AI & Gadgets Updates | Hacks & Tutorials
👉https://t.me/GlobalTech_Info
Download Telegram
Channel photo updated
🙏
💡 Save phone battery: Turn off Bluetooth & GPS when not needed – extends battery life by 20%.
𝕎𝕒𝕣𝕟𝕚𝕟𝕘!!
የሞባይል ባንኪንግ ላይ ያነጣጠረ አዲስ የአንድሮይድ ቫይረስ መከሰቱ ተነገረ

"ክሊዮፓትራ" የሚል ስያሜ የተሰጠዉ የሞባይል ባንኪንግ ላይ ያነጣጠረ አዲስ የአንድሮይድ ቫይረስ መከሰቱን የሳይበር ደህንነት ስጋቶች ላይ የሚሰራዉ ክሌፊስ #𝙲𝚕𝚎𝚊𝚏𝚢’𝚜 ቡደን አሳወቀ።

የዚህ ቫይረስ መከሰት በሞባይል ባንኪንግ ስጋት እድገት ዉስጥ ከፍተኛ የሚባል ለዉጦች እየተከሰቱ መሆናቸዉን ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

በክሌፊስ ቡድን አማካኝነት በነሃሴ ወር መጨረሻ የተለየዉ ይህ ቫይረስ በአውሮፓ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ባነጣጠሩ መጠነ ሰፊ ዘመቻዎች ዉስጥ ጥቅም ላይ እንደዋለ ተገልጿል።

"ክሊዮፓትራ" የተራቀቀ የባንክ ትሮጃን ቫይረስ የመረጃ መንታፊዎች በርቀት ሆነዉ የተደበቀ ምናባዊ ኔትዎርክ ስርዓትን በመጠቀም ለጥቃት ሰለባ የሆኑ መሳሪያዎችን መቆጣጠር የሚያስችላቸዉ መሆኑ ተነግሯል።

ይህ አጥፊ ሶፍትዌር ከገሃዱ ዓለም የማጭበርበር ሙከራዎች ጋር ቁርኝት የፈጠረ ሲሆን ለጥቃት ኢላማ የተደረጉ አካላት መሳሪያዎቸዉን ቻርጅ ሲያደረጉ እንዲሁም ብዙም ክትትል አይደረግበትም ብለዉ በሚያስቡት ምሽት ላይ ጥቃቶች በጥንቃቄ እንደሚሰነዝሩ ታዉቋል።

የደህንነት ባለሙያዎች ቫይረሱ ለወደፊቱ የዘርፉ ስጋቶች ማሳያ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ያስጠነቀቁ ሲሆን ይህም የፋይናንስ ተቋማትን ላይ ያለዉ የስጋት ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገዉ ጠቁመዋል።

የቫይረሱ መከሰት ለፋይናንሺያል ተቋማት እና ፀረ-ማጭበርበር ቡድኖች፣ ከስታቲክ ትንታኔ በላይ የሆኑ ስራዎችን እንደሚጠበቅባቸዉ ያሳየና በመጠቀሚያ መሳሪያዎች ላይ የሚከሰቱ የባህሪ ለዉጦች ላይ ክትትል ማድረግ እንዲሁም የስጋት ማሳወቂያ መፍትሄዎችን መተግበር ወሳኝ መሆኑን ተገልጿል።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በወርሀ መስከረም

“አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለሀገራችን ኢትዮጵያ እጅጉን ከሚያስፈልጉ እና ኢንቨስት ማድረግ፣ መከታተልና መመራመር ከሚገባን የዘመኑ ቴክኖሎጂዎች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ነው።” ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ያደረጉት ንግግር

በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ተመርቆ ክፍት ሆነ። ይህ ማዕከል ሀገር በቀልና ችግር ፈቺ የኤ.አይ ፈጠራዎችን በማልማት ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ እንድትሆን ያለመ ነበር።

በ2014 ዓ.ም ወደ ኢንስቲትዩትነት ያደገው ተቋሙ “አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለሁሉም!” በሚል መሪ ቃል በጤና፣ ግብርና፣ አገልግሎት፣ ፋይናንስ እና ሌሎች በርካታ ዘርፎች ውስጥ ቴክኖሎጂውን በማልማት ላይ ይገኛል። ለአብነትም ኢንስቲትዩቱ ያበለጸገው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሞባይል መተግበሪያ በዓለማቀፍ ደረጃ ምርጥ የፖሊስ መተግበሪያ መሆን ችሏል። ይህም ኢትዮጵያ በኤ.አይ ዘርፍ ያላትን ዓለማቀፍ ተወዳዳሪነት አሳይቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ከሀገር ውስጥ እንዲሁም ዓለማቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ዙሪያ የምርምር እና ልማት ስራዎችን በመስራት ለአፍሪካ ተምሳሌታዊ ተቋም ለመሆን እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያ ከኤ.አይ ቴክኖሎጂ የምታገኛቸውን ጥቅሞች በአግባቡ ለመጠቀምና ተያያዥ ስጋቶችን ለማስቀረትም የሚያስችል ብሔራዊ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ በማጸደቅ ዘርፉን እየመራ ይገኛል።

ኢንስቲትዩቱ ሃገራችን ለቴክኖሎጂው እድገት የሰጠችውን ልዩ ትኩረት ዕውን ለማድረግ ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት ወሳኝ መሆኑን ተገንዝቦ የኤ.አይ የታዳጊዎች የክረምት ስልጠና፣ የኤ.አይ ክበባት እና በኤ.አይ የሦስተኛ ዲግሪ የትምህርት መርሓ ግብሮችን በማዘጋጀት እየሰራ ይገኛል።

ወርሀ መስከረም በኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ልማት እና ትግበራ መሰረት የተጣለበት ወር ሆኖ ይወሳል።
❤1
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ወርቁ ጋቸና እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ ተፈራርመዋል።

የስምምነት ሰነዱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ትብብርን በማጠናከር የምርምር፣ የትምህርት እና ልማት ሥራዎችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በማገዝ ለማሳደግ ያለመ ነው።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ወርቁ ጋቸና በኢንዱስትሪ እና በትምህርት ዘርፎች መካከል ያለውን ትስስር ለማጎልበት ኢንስቲትዩቱ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አክለውም በስምምነቱ መሰረት ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸውን የምርምር ሥራዎች በኤ.አይ በማገዝ ለሀገራችን ችግር ፈቺ የሆኑ የልማት ውጤቶችን ለማበርከት መስራት አለብን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ እየሰራ ያለው ስራ ለአፍሪካ ተምሳሌታዊ ነው ሲሉ አድንቀዋል። ከዚህ በተጨማሪም ስምምነቱ ዩኒቨርሲቲው እየሰራ ያለውን የዲጂታላይዜሽን ስራ ይበልጥ እንደሚያጎለብት እና ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ስምምነቱ ኢንስቲትዩቱ በሚያዘጋጃቸው የኤ.አይ የታዳጊዎች የክረምት ስልጠና እና የሶስተኛ ዲግሪ መርኃ ግብሮች ላይ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ በማሳተፍ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል እንዲኖር እድል ይፈጥራል ሲሉ ተናግረዋል።

ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የቴክሎጂውን ዘርፍ የሚመራ የሰው ሃይል እጥረት ተግዳሮት እንደሆነ ተገለጸ

ጥቅምት 6/2018 ዓ/ም፤ ባሕር ዳር፡- 6ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የሁለተኛ ሳምንት መርሀ ግብር በጣና ዳር ፈርጧ ባሕር ዳር ተካሂዷል፡፡ በዚህም የመርሃ ግብሩ አካል የሆነው የፓናል ውይይት “ዲጂታላይዜሽን፣ ስማርት ከተማ እና የሳይበር ደህንነት” በሚል ርእስ ተካሂዷል፡፡

በፓል ውይይቱ ላይ የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እዳላማው፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዩዳሄ አርአያስላሴ፣ የአማራ ክልል የሲቪል ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ባንቻምላክ ገብረማርያም፣ እና የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው በፓናሊስትነት ተሳትፈዋል፡፡ ውይይቱን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ በአወያይነት መርተውታል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በፓናሉ ውይይቱ ላይ እንደገለጹት፤ ዲጂታላይዜሽ እና ስማርት ከተማ ተግባራዊ ማድረግ  የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ትልቅ የመወዳደሪያ አቅም መሆኑን አንስተዋል፡፡  የዲጂታላይዜሽን እና የስማርት ከተማ ጽንሰ ሀሳብ  የአገልግት አሰጣጥን የሚያዘምን፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ የሚያቀላጥፍ  እና ተደራሽ የሚያደርግ እንዲሁም  ምርታማነትን  በማረጋገጥ በሀገራት ኢኮኖሚ ላይ የራሱን በጎ አሻራ  የሚያኖር ነው ብለዋል፡፡  እነዚህን የቴክኖሎጂ ትሩፋቶች  ዘላቂ እና አስተማማኝ  ለማድረግ ከቴክኖሎጂ ጋር አብሮ የሚዘመን የህግ ማእቀፍ ወሳኝ መሆኑን አንስተው፤
ጉግል በ9 ቢሊዮን ዶላር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የክላውድ መሠረተ ልማቶችን ሊያስፋፋ ነው፡፡

ኩባንያው ከትምህርት እና ከሰው ኃይል ፕሮግራሞቹ ጎን ለጎን በአሜሪካ አዳዲስ ዳታ ሴንተሮችን በመገንባት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የክላውድ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋት 9 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን አስታውቋል፡፡

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አገልግሎት ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ የክህሎት ልማት እና የዳታ ሴንተር ግንባታ ላይ ኢንቨስትመንቱን እንደሚያስፋፋ ኩባንያው ገልጿል፡፡

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከ100 በላይ በሚሆኑ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጉግል ለኤ.አይ ትምህርት እና ስልጠና 1 ቢሊዮን ዶላር መድቦ እየሰራ ነው፡፡

ኩባንያው በአሜሪካ እስከ 2027 ድረስ የ9 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ በመመደብ ዳታ ሴንተር እንደሚያስፋፋ ይፋ አድርጎል፡፡ ይህም ሰልጣኞችን እያደገ ላለው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ለማዘጋጀት ይረዳል። መዋለ ንዋዩ ዲጂታል ኢኮኖሚን በማሳደግ አሜሪካ በኤ.አይ ፈጠራ የዓለም መሪ ለመሆን የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደሚያሳድግ ተጠቁሟል፡፡

ጉግል ከአሜሪካ በተጨማሪ በሌሎች ሀገሮችም የኤ.አይ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶች እንደሚያስፋፋ ጠቁሟል፡፡
" የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል ይሸፍናል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከት ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች እንዲሁም ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ትናንት ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ደብዳቤ ልኳል፡፡

የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ሥራ አስፈጻማ ቴዎድሮስ ሽዋርገጥ (ዶ/ር) የተፈረመው ደብዳቤው፤ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል እንደሚሸፍንና ተማሪዎች የተማሩትን ይዘቶች የሚፈተኑ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ብሔራዊ ፈተናው ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይዘቶችን መሠረት ያደረገ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትምህርት ቤቶች 9ኛ ክፍልን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት፤ ሌሎቹ ደግሞ በቀድሞው ስርዓተ ትምህርት የተማሩ በመሆኑ ፈተናው ከሁለቱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ የሆኑ ይዘቶች ተጣጥሞ የሚወጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ሪፎርም መሠረት የሁለተኛ ደረጃ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ በማካሔድ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ መገባቱ ይታወቃል፡፡
ንስርኮፕ - ውጤታማ የወንጀል መከላከል ሥራን አስቀድሞ ለመስራት የሚያስችል ሲስተም

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #𝙸𝙽𝚂𝙰 ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ተኛ ጊዜ በ2017 ዓ/ም ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ከተሳተፉና ከተመረቁ ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች መካከል አንዱ ስለሺ አብርሃም ነው፡፡ ስለሺ በሰመር ካምፕ ቆይታው ውጤታማ የወንጀል መከላከል ሥራን አስቀድሞ ለመስራት የሚያስችል ንስርኮፕ (𝙽𝙸𝚂𝙸𝚁𝙲𝙾𝙿) የተሰኘ ሲስተም አበልጽጓል፡፡

ይህ ሲስተም በተለያየ ጊዜና ቦታ የተከሰቱ የወንጀል ድርጊቶችን ከተፈጸሙበት ቦታ፣ ጊዜና የወንጀል ዓይነት ጋር በማስተባበር የወንጀል ትንተና እና ስታትስቲክስ ሰርቶ ለወንጀል ክትትልና ምርመራ አካላት ያቀርባል፡፡ በቀረበው ስታትስቲካዊ መረጃ በመመስረት ውጤታማ የወንጀል መከላከል ሥራን አስቀድሞ ለመስራት አስፈላጊውን የሰው ኃይል በተገቢው ቦታና ሰዓት ለመመደብ ያስችላል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #𝙸𝙽𝚂𝙰 ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ተኛ ጊዜ ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም 629 ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች የተመረቁ ሲሆን፤ ተመራቂዎቹ በግልና በቡድን በመሆን ሰላሳ አንድ (31) ችግር ፈቺ የሆኑ ፕሮጀክቶችን ሰርተዋል፡፡
በተመራቂዎቹ የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
የቴሌግራም አካውንትዎ በመረጃ መንታፊዎች እጅ ከገባ ወይም ሌላ ሰው እየተጠቀመበት እንደሆነ ከጠረጠሩ ምን ያደርጋሉ? 

በኢትዮጵያ የቴሌግራም አካውንት መጠለፍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት እየተለመደ የመጣ የሳይበር ጥቃት ነው። ብዙዎች የሚያጋጥማቸው መጠለፍ በቴክኒክ ብቃት ሳይሆን በሰዎች የጥንቃቄ ጉድለት የሚፈጠር ነው።

የቴሌግራም አካውንትዎ በመረጃ መንታፊዎች (Hackers) እጅ ከገባ ወይም ሌላ ሰው እየተጠቀመበት እንደሆነ ከጠረጠሩ፣ በፍጥነት የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይኖርብዎታል፡-
1. ሌሎች መሣሪያዎችን ማቋረጥ (Terminate Sessions)
ይህ በጣም አስፈላጊው እርምጃ ነው። መንታፊው የከፈተውን ግንኙነት ለመዝጋት፦
•  ወደ Settings ይግቡ።
•  Devices (ወይም በአንዳንድ ስልኮች Privacy and Security > Active Sessions) የሚለውን ይጫኑ።
•  ከእርስዎ ስልክ ውጭ ያሉትን ሁሉንም መሣሪያዎች "Terminate all other sessions" በማለት ያስወግዱ።

2. ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) ማብራት
መንታፊው ተመልሶ እንዳይገባ ፓስዎርድ ማዘጋጀት አለብዎት፦
•  Settings > Privacy and Security > Two-Step Verification ውስጥ ይግቡ።
•  ጠንካራ ፓስዎርድ እና የማገገሚያ ኢ-ሜይል (Recovery Email) ያስገቡ።
•  ማሳሰቢያ፦ መንታፊው ቀድሞ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫን ካበራው፣ አካውንቱን "Reset" ለማድረግ 7 ቀን ሊጠብቁ ይችላሉ::
ዳታ ፕሮቨናንስ (Data provenance) ተዓማኒነት ላለው የኤ.አይ ቴክኖሎጂ

ዳታ ፕሮቨናንስ (Data provenance) ማለት የዳታዎችን ወይም የዳታ ቋቶችን ታሪክ፣ ከየት እንደመጡ፣ እንዴት እንደተሰበሰቡ፣ የማን እንደሆኑ፣ እንዴት እንደተሰሩ እና በመጨረሻም እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋሉ የመከታተል ሂደት ነው፡፡ ለውሳኔ አሰጣጥ እና ለኤ.አይ ቴክኖሎጂ አስፈላጊ የሆነው ዳታ መተማመንን፣ ተጠያቂነትን እና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የዳታ ፕሮቨናንስ አስፈላጊ መሆኑን የአይ.ቢ.ኤም ድረ-ገጽ መረጃ ያሳያል፡፡

የዳታ ፕሮቨናንስ መኖር የተለያዩ የኤ.አይ ሥርዓቶችን ለማበልፀግ ጥቅም ላይ የዋሉ ዳታዎች በሕጋዊ መንገድ የተሰበሰበ ስለመሆናቸው፣ ፍቃድ እንደተሰጠባቸው፣ ወይም በተሰበሰበው ዳታ ውስጥ የተደበቀ አድልዎ ወይም ማጭበርበር መኖሩን ማረጋገጥ እንዲቻል ያደርጋል፡፡

ለአብነት ሕመሞችን ለመመርመር ኤ.አይን የሚጠቀም የጤና አጠባበቅ ሥርዓት ውስጥ የዳታ ፕሮቨናንስ ሐኪሞች የታካሚውን ዳታ ከመነሻው እንዲከታተሉ፣ በሥነ-ምግባር መሰብሰቡን እንዲያረጋግጡ እና ቴክኖሎጂው ዳታውን የተጠቀመበትን መንገድ እንዲረዱ ያስችላል።

ይህም የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ይበልጥ ግልጽ፣ ተግባራዊ ለማድረግ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከሰው ልጅ እሴቶች እንዲሁም ፍላጎቶች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ አቅም የሚሆን ነው፡፡
የመረጃ መንታፊዎች የዋትሳፕ አካዉንትዎን ለመጥለፍ ምን አይነት ስልቶችን ይጠቀማሉ?

በሀገራችን በአሁኑ ወቅት የሚፈጸሙ የዋትሳፕ ጥቃቶች ከረቀቀ የቴክኖሎጂ ስርቆት ይልቅ፣ የሰዎችን ስነ-ልቦናዊ ክፍተት እና ማህበራዊ ትስስርን መነሻ ያደረጉ ናቸው።

ጠላፊዎች የእኛን ጠንካራ ማህበራዊ መስተጋብር፣ ለሃይማኖታዊ ተቋማት ያለንን ጥልቅ አክብሮት እና ለጋራ ጉዳዮች (ግሩፖች) የምንሰጠውን ከፍተኛ እምነት እንደ ጥቃት መሳሪያ በመጠቀም አካውንታችንን ይዘርፋሉ።

🛑የጥለፋው ሂደት ደረጃ በደረጃ

👉1.ስልክ ቁጥርን ማደን: ጠላፊው መጀመሪያ የእርስዎን ስልክ ቁጥር ከተለያዩ የዋትሳፕ ግሩፖች የተቋም፣ የእቁብ፣ የሃይማኖት፣ የሰፈር ወይም የገበያ ግሩፖች ላይ ያገኛል።

👉2.በእርስዎ ቁጥር አካዉንት የመክፈት እንቅስቃሴ: ጠላፊው በራሱ ስልክ ላይ የዋትሳፕ አፕሊኬሽኑን ከፍቶ የእርስዎን ስልክ ቁጥር ያስገባል። በዚህ ጊዜ ዋትሳፕ ትክክለኛው ባለቤት መሆንዎን ለማረጋገጥ ወደ እርስዎ ስልክ በኤስኤምኤስ (SMS) ባለ 6 አሃዝ ኮድ ይልካል።

👉3. የማታለያ መልእክት: ይህ የጥቃቱ አደገኛ ክፍል ነው። ኮዱ ወደ ስልክዎ እንደደረሰ፣ ጠላፊው በሚከተሉት መንገዶች በማታለል ኮዱን እንዲነግሩት ያደርጋል፦

#የግሩፕ_አድሚን_በመምሰል፦ "ከግሩፑ እንዳትወጣ አሁን የደረሰህን የደህንነት ኮድ ላክልኝ" በማለት ያስፈራራል።

#የቅርብ_ሰው_በመምሰል፦ ቀድሞ የተጠለፈ የጓደኛዎን አካውንት በመጠቀም "በስህተት ወደ አንተ ስልክ ኮድ ልኬያለሁ፣ እባክህ መልስልኝ" ይላል።

#የሽልማት_ድርጅት_በመምሰል፦ "የቴሌ ወይም የባንክ ሽልማት ደርሶዎታል፣ ለማረጋገጥ ኮዱን ይንገሩን" በማለት የሰዉን የማግኘት ጉጉትን እንደ ማታለያ ይጠቀማል።
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ነጥቦች ተግባራዊ ያድርጉ

በሀገራችን ኢትዮጵያ ከ12 ሚሊየን በላይ እንዲሁም በዓለማችን 3.7 ቢሊየን ገደማ ንቁ ወርሃዊ ተጠቃሚዎች (Active users) ያሉት ፊስቡክ የማሕበራዊ ትስስር ገጽ፤ በርካታ መንግስታዊ እና የግል ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ከተገልጋዮች  ጋር ቅርብ የሆነ ግንኙነት ለመፍጠር ይህንኑ ፕላትፎርም ይጠቀማሉ፡፡  

ይህን ያህል በርካታ ቁጥር ተቃሚዎች ያሉት የፌስቡክ  ገጽ በየእለቱ ከሦስት መቶ ሺ እስከ ስድስት መቶ ሺ ያህል የፕላትፎርሙ ተጠቃሚዎችን   አካውንቶችን ሰብሮ የመግባት (log in) የጥቃት  ሙከራዎች ያስተናገዳሉ፡፡ በርግጥ እነዚህ የጥቃት ሙከራዎቹ  ከሙከራ ሳይዘሉ በፕላትፎረሙ ጠንካራ  የደህንነት ስርአት ይከሽፋሉ፡፡

እነዚህን የጥቃት ሙከራዎች ለመከላከል ተቋማትም ይሁን ግለሰቦች የሚከተሉትን የጥንቃቄ መንገዶች ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸል፡፡