Gion Amhara
70.9K subscribers
21.1K photos
960 videos
149 files
7.99K links
ማንኛውንም ጥቆማ ለመስጠት:-➛ @HaimonAb
Download Telegram
🔝ቄሮና ነጻነት ይተዋወቃሉ ወይ

ቄሮ የሚለው የኦሮምኛ ቃል በአማርኛ ከመለስነው ወጣት የሚል ትርጉም አለው፤ ከቃሉ ብሎም ከኦሮሞ ወጣት ጋር ችግር እንደሌለበኝ ከመጀመሪያው ማስገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡ ሆኖም አሁን ያለውን የቄሮ መንፈስ ከነጻነት ጋር ይዛመዳል ወይ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ በሥር መሠረቱ እስኪ እንፈትሸው፡፡ ቄሮ የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት ጦማሪ በፈቃዱ ዘኃይሉ ከእስር ቤት እንደወጣ በእንግሊዝኛ የቄሮን መንፈስ አወድሶ ለፈረንጆች ያዘጋጀውን ጽሑፍ በኢሜል ከላከልኝ በኋላ ነው፡፡ የአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የተባለው አዲስ አበባንና ዙሪያዋን አቀናጅተን እናለማለን በሚል የመሀል ከተማው መሬት ችብቸባ በማለቁ የሕወሓት የመሬት ነጋዴዎች ገበያቸውን ሰፋ ለማድረግ የተጠቀሙበት እንደሆነ ብዙ አያጠያይቅም፡፡

የኦሕዴድ የመሬት ከበርቴዎች በብቸኝነት ይዘውት የነበረውን የመሬት ንግድ በአለቆቻቸው ሊነጠቁ እንደሆነ ሲገባቸው የኦሮሞ ወጣቶችን በማደራጀት ተቃውሞ እንዲነሳ ምክንያት ሆነ፡፡ ከምርጫ 2007 በኋላ የቄሮ እንቅስቃሴ ከሩዋንዳው የኢንተርሀምዌ ንቅናቄ ጋር የሚመሳሰል ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ኢንተርሀምዌ የተባለው የወጣት ክንፍ በገዢው ቡድን በኩል ተቋቁሞ ሁቱ ያልሆኑ ዜጎችን በሙሉ ሀብትና ንብረት መቀራመትና የጅምላ ግድያ ላይ ብቻ ያተኮረ እንደነበረው ሁሉ በቄሮ ትእዛዝ በሚል ከ2008 ጀምሮ ኦሮሞ ያልሆነ ዜጋ በጅምላ ተፈናቀለ፡፡ ለምሳሌ በ2007 ዓም በምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ ወረዳ የሚገኙ አማሮችን ቤትና ንብረት ተቃጠለ፤ በ2008 ዓም ደግሞ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ የአማሮች ንብረት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ተዘርፎ ተቃጠለ፡፡ እስከ 2008 የክረምት ወቅት ድረስ የቄሮ ንቅናቄ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎችን ንብረት ከማውደምና ከማፈናቀል ውጭ በቄሮ ትግል የተገኘ አንድም የፖለቲካ ድል አልነበረም፡፡ በቡኖ በደሌ፣ በጂማ ዞን፣ በአርሲና በባሌ፣ በሐረርጌና ምስራቅ ሸዋ ወዘተ የበርካታ ዜጎች ንብረት ወድሟል፡፡

በሰላሌ ብቻ ከ80 በላይ ታርጋቸው አማና ኢትbየሆኑ መኪኖች ወድመዋል፤ ተዘርፈዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የውጭ አገር ኢንቨስተሮች ንብረትም በእጅጉ ወድሟል፤ የናይጀሪያዊውን ዳንጎቴ ሲሚንቶ ጨምሮ፡፡ ለተቃውሞና ለዘረፋ የሚወጡ ወጣቶችም በአገዛዙ በእጅጉ ይጨፈጨፉ ነበር፡፡በዚህም በማስታውሰው የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ በተነሱ ተቃውሞዎች የደብረ ዘይቱን በመጠቅጠቅ አደጋ ሳይጨምሮ ከ200 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል፡፡አገዛዙም በዚህ ሒደት መንገድ ሲዘጉ የተወሰኑ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ እያስፈራራ እቀጥላለሁ የሚል እምነት ነበረው፡፡ በ2008 ክረምት በጎንደር የተጀመረው የአማራው ተጋድሎ የኢትዮጵያን አቢዮት የቀየረ ሆነ፡፡ ሁለት እጅን አጣምሮ መውጣት ብቻ ለውጥ እንደማያመጣ በግልጽ አሳዬ፡፡ ይህ ክስተት ቀደም ሲል የተጀመረው የቄሮን ተቃውሞ ወደ ተጋድሎነት እንዲቀየር ትምህርት ሰጥቶ አልፏል፡፡ የአማራው ሕዝብ ጎንደር ላይ ስለታሠሩ ኦሮሞዎች ጪምረ ድምጽ ማሰማቱ ፀረ አማራ የነበረውን የቄሮ አካሔድ ጥቂት ቢያለዝበውም ሙሉ በሙሉ ግን አጥፍቶታል ማለት አይቻልም፡፡ የቄሮ ትግል ከአገዛዙ ይልቅ በኦሮምያ ክልል የሚኖሩ ንፁሀን ዜጎች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ የአማራው ተጋድሎ በአንድ ወር ሲቀጣጠል ወያኔ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጣ፤ ቄሮ ከ2 ዓመት ያላነሰ ያደረገው ተቃውሞ ግን ለአገዛዙ ስጋት ስላልነበር ምንም አዋጅ ማውጣት አስፈላጊ አልነበረም፡፡ እነ ኃይለ ማርያም ሥልጣን በቃኝ እስከሚሉ ድረስ በ2008ና 9 ዓም በአርማጭሆ ብቻ 597 አማሮች በትግል ላይ ተሰውተዋል፡፡ ከ500 በላይ ንጹሐን ሕፃናትና ሴቶች ሳይቀር በጥይት ተረሽነዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ነበር ኃ/ማርያም ሥልጣን በቃኝ ያለው፡፡ ከዚያስ?በኢሕአዴግ የአሠራር ልማድ ሊቀመንበሩ ከሥልጣን ሲወርድ ቀጣዩ ሊቀመንበር የሚሆነው ምክትሉ ነበር፤ መለስ ሲሞት ኃምደ እንደመጣው፡፡ ሆኖም ሕወሓቶች ሥልጣኑን ለሺፈራው ሽጉጤ ለመሥጠት፣ ኦሕዴዶች ደግሞ ለራሳቸው ስለፈለጉት በመካከል አገር የሚለው ምስል ጠፋ፡፡ በዚህ ሒደት ከእያንዳንዱ ድርጅት 9 በድምሩ 36 አባላት ያለው የፓርቲው ምክር ቤት ሁሉም የራሱን ይመርጣል በሚል ሕወሓቶች ድምፃቸውን ለሺፈራውbሽጉጤ በመስጠት ዐብይም ደመቀም እንዳይመረጡ ነበር ሀሳባቸው፡፡ አቶ ሺፈራው ይመረጣል በሚል አዋሳ ላይ የሲዳማ ባለሀብቶች ድግስ አዘጋጅተው እንደነበር የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡

በመጨረሻው ሰዐት አገር የሚለው ምስል እንዳይጠፋ በሚል እነደመቀ ራሳቸውን ከውድድር አውጥተው ዐቢይ እንዲመረጥ ባያደርጉ ኖሮ እስካሁን ቄሮ በሽፈራው ጅራፍ ይለበለብ ነበር፡፡ አቶ አዲሱ አረጋም ፌስታል ጭንቅላታቸውን ይዘው ከሺፈራው ወይም ከደፂ ኋላ ቱስ ቱስ ከማለት የዘለለ ሚና አይኖራቸውም ነበር፡፡ ለዚያውም የሚፈሩት የደኅንነቱ አለቃ ጌታቸው አሠፋ ካሠነበታቸው ማለቴ ነው፡፡እንግዲህ በቀረበው ሀቅ የቄሮ ትግል ለነጻነት የነበረው ትግል ምንድን ነው? ብለን ስንጠይቅ መልስ የሚኖረን አይመስለኝም፡። እንጂማ ቄሮ ትናንትም ከለውጥ በፊት ይዘርፍ ነበር፤ ዛሬም ከለውጥ በኋላ ከሃያ በላይ ባንኮችን ዘርፏል፡፡ ትናንትም ከአገዛዝ ጋር አልነበረም ትግሉ፤ ዛሬም አካሔዱ ያው ነው፡፡እነ አዲሱ የመንግሥትነት ልምድ የላቸውም፤ ለዚያ ነው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሐፍረትና ኩራታቸውን ሳይለዩ እኩል የሚተፉት፡፡

በኦሕዴድ/ኦዴፓ አንድ እየተለመደች የመጣች አካሔድ አለች፤ ይህችውም የጠነከሩ ሲመስላቸው ከእኛ ውጭ ላሳር ሲደነግጡ ደግሞ አብረን ካልሆንን ምን ዋጋ አለን እያሉ አንድ መልክ እንኳ ያጣንባቸው፡፡

®Muluken Tesfaw
♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
ሰበር ዜና‼️

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በአማራ ክልል ተደረገ።

ምንጭ፦ETV
♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
እስካሁን ባለው መረጃ ሶስት አመራሮች በጥይት ተመተዋል። ለህክምና እያመሩ ይገኛሉ።

አመራሮቹ ከደቂቃዎች በፊት ስብሰባ ላይ ነበሩ።

©Ayalew Menber
♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
ምንም ይሁን ምን እንረጋጋ! ዛሬ ላይ መፈንቅለ መንግስት

ዛሬ ባ/ዳር ላይ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮች እንዳሉ ተረጋግጧል፡፡ ጥቃቱም የመላ አማራ እንጅ የማንም አይደለም፡፡ የመፈንቅለ መንግስቱ ዓላማ ምንም ይሁን ምን፤ አማራ አንድነቱን እንዲሰሸረሸር የሚያደርግ አንዳች እንቅስቃሴ፤ ውስጥ እንዳይደረግ አደራ እላለሁ፡፡ ምንም አይነት ጉዳት ቢደርስ እንኳን አደራ፤አንዳች አጸፋ እንዳይሞከር፡፡ በጭራሽ፡፡

መንግስት ደከመ እንጅ አልሞተም፤ መንግስት በህጉ መሰረት የሚለውን ይበል፡፡ በቃ ሌላ ነገር አያስፈልግም፡፡ ግን መቸ ነበር የአማራ ፖለቲካ ታሟል ያልኩት? በቃ ታሞ ከርሟል፤እንግዲህ በጋራ ቁመን እንዲታከም እንሰራለን። ምክንያቱም አሁን ነገሩ ታውቋልና፡፡
አደራ እንረጋጋ፤ ምን ነገር እንዳናደርግ! ነገሩ ማለፉ አይቀርም፡፡ የድፈድፍ ኩራቱ ደግሞ ውሀ እስኪገባው ነው፡፡

©Chuchu Alebachew
♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
ጋዜጠኛ እና የሰብዐዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ እና የአዲስአበባ ባለደራ ምክርቤት አባላት ለደህንነታቸው ሲባል ከባህርዳር ኤርፖርት እንዳይወጡ ተደረገ።

©Eskindr Nega
♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
የአማራ ህዝብ ብልህ ህዝብ ነው። ችግሮችን ማለፍ ይችላል።እንኳን ይህንን ዘመነ መሳፍንትን ተሻግሮ ሀገር ያስረከበ ነው። እናም መፍትሄው አንድነታችን መጠበቅ ብቻ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደራል መንግስት ከሚመራን የቀበሌ ሚኒሻ ቢመራን እንመርጣለን።

©Ayalew Menber
♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
#Update የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አምባቸው መኮንን እና የአዴፓ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ምግባሩ ከበደ ክፉኛ ቆስለዋል ተብሏል::

♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
በጄነራሉ ላይ አደገኛ ሴራ እየተሰራ እንደሆነ ይሰማኛል!!

የEthio 360 media የሚባል የኢሳት ውላጅ ጥቃቱን የአሳምነው ፅጌ ወታደሮች እንደፈፀሙትና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አምባቸው መኮንን እና የአዴፓ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ምግባሩ ከበደ ክፉኛ እንደቆሰሉ ዘግቧል:: በዚህ አጋጣሚ ጀነራሉን ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ እና በተቀነባበረ ሴራ ጄነራሉን ለማሰርና አማራን ዳግም አንገት ለማስደፋት እንደሆነ ይሰማኛል።

የአማራ ህዝብ ከጄኔራል አሳምነው ፅጌ ጎን ሊቆም ይገባል!!

♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
🔝የኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ጥሪ‼️

"የተፈጠረው ነገር ተፈጥሯል። ትልቅነታችን መታየት ያለበት በዚህ ወቅት ነው። ማንኛውም ለአማራ ሕዝብ የሚቆረቆር ሁሉ በዚህ ሰዓት ሕዝባችን የሚጎዳ መረጃ ከማሰራጨት ተቆጥቦ፣ ሕዝባችን እንድናረጋጋ ጥሪ አቀርባለሁ። ችግር ገጥሞናል። የገጠመንን ችግር በጋራ ማለፍ አለብን። የአማራን ሕዝብ ታላቅነት ማስመስከር ያለብን በዚህ ወቅት ነው"

©ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ
♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
ዶ/ር አንባቸውን በጥይት የሚመታ የአማራ ታጋይ ነኝ ባይ…ካለ በእርግጠኝነት እሱ ከአማራ ዘንድ አይደለም። የምንሰማው ሁሉ ያስደነግጣል!! አማራ የእርስ በእርስ ጦርነት የሚያስተናግድበት ትንሽ እንኳ ጉልበት የለውም።

♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
እንረጋጋ፣ እናረጋጋ‼️

አሁን ላይ ባህር ዳር ተኩሱ ቆሟል። መረጋጋት እየተፈጠረ ነው። የአማራ
ልዩ ኃይል ሁኔታውን እያረጋጋ ነው።

በዚህ ሰዓት የሚሰማ አካል ቢኖር የፌድራል መንግስቱ የፀጥታ ኃይሉን
ወደ ባህር ዳር ከማስገባት ቢታቀብ መልካም ነው። ነገሮች እንደ አዲስ
እንዳይባባሱ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

©Belay Manaye
♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
ባህርዳር‼️

አሁን በዚህ ሰዓት በባህርዳር የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል!!

♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ደውል‼️

በአማራ ክልል በተፈጠረው ችግር የፌድራል መንግስት ወደ አማራ ክልል እንዳይገባ የ አማራ ፋኖዎች ፣ የአማራ ወጣቶች በ አንድነት መቆም አለባቸው። ይህ በሁሉም የአማራ ክልሎች ይዛመት።

እነ ንጉሱ ጥላሁን በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሱትን ሴራ እና ደባ የማያቆሙ ከሆነ እርምጃ ይገባል። ድል ለ አማራ ህዝብ!!

®Henoke Yeshetlla
♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ‼️

ዛሬ ሰኔ 15/2011 ዓ/ም ምሽት በባሕር ዳር ከተማ የተከሰተውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ፣ ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል ላይ ይገኛል። እስከዚህ ሰዓት ድረስ የተረጋገጠ መረጃ ማግኝት ባንችልም፣ ከባሕር ዳር የሚወጡ መረጃዎች አሳዛኝ እና መንፈስን የሚያውኩ ሁነው አግኝተናቸዋል።

አብን ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን፣ ሕዝባችን በተለመደው አስተዋይነቱ እና ጨዋነቱ ያጋጠመንን ፈተና እንደሚወጣው ያለንን ሙሉ እምነት እየገለጽን፣ አጋጣሚውን ተጠቅመው የሕዝባችንን አንድነት ከሚፈታተኑ ኃይሎች የጥፋት ተልዕኮ እራሱን እንዲጠብቅ፤ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና አክቲቪስቶችም ሕዝብን የማረጋጋት ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን በአግባቡ እንድትወጡ፤ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

እጣፈንታችንን በራሳችን እጆች እንጽፋለን!

♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት የምንቆምበት ጊዜ ነው‼️

አደጋውን ያቀነባበረውም ያደረሰውም የፌደራል መንግሥት ያቀነባበረውና የመራው ገዳይ ቡድን ነው፡፡ ዓላማው ደግሞ በጣም ግልጽ ነው - ክልሉን ለመበጥበጥና አዳክሞ ለመግዛት ጠንካራ የሚባሉ የሕዝብ ልጆችን ማስወገድ አስፈላጊ መሆኑ በነ አብይ ቡድን ስለታመነበት ነው፡፡ ጉዳዩ መፈንቅለ መንግሥት አይደለም፡፡ ዓላመው በጣም ግልጽ ነው፡፡

አምባቸውንና ጓዶቹን ማስወገድና ክልሉን አዳክሞ ለማንበርከክ ነው፡፡የአብይ አሕመድ እና የአንዳርጋቸው ጽጌ ቀኝ እጅ ንጉሡ ጥላሁን ከአብይ ጋር ሆኖ ያሴረውን ሴራ ካሳካ በኋላ እርምጃው የተቀነባበረውና የተወሰደው በክልሉ ልዩ ኃይል እንደሆነ በማስመሰል መግለጫ “መፈንቅለ መንግሥት ነው” በማለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡ አምባቸውንና ጓዶቹን ለመግደል ያሴሩትም ድርጊቱን የፈፀሙትም አብይና እንደ ንጉሡ ያሉ የእሱ ተላላኪዎችየሚል ናቸው፡፡ ሌላ አካል አይደለም፡፡

ዓላማቸው የክልሉ ልዩ ኃይል መፈንቅለ መንግሥት አደረገ ትርክት በማድራት በአንድ በኩል እነ አምባቸውን ማስወገድ፣ እዚያው በዚያው ደግሞ ልዩ ኃይሉ መምታት ነው፡፡ ሐቁ ይህ ነው፡፡ የአማራ ልጆች ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት የምንቆምበት ጊዜ ነው፡፡ በአውራጃ እና በልዩ ልዩ መንገድ ተከፋፍለን እርስ በርሳችን እንድንፋጅላቸው የሚፈልጉ ኀይሎች ኀብረታችንን ለመበተን እየሠሩ ነው፡፡ ፈጽሞ እድል ልንሰጣቸው አይገባም፡፡የገጠመንን ፈተና በታላቅ ብስለት ማለፍ ይገባናል፡፡

አማሮች የጽናትና የአይበገሬነት ምሳሌዎች ነን፡፡ በጽናትና በአማራዊ ኅብረት እንቁም፡፡ አንድነታችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንጠብቅ!!

©Ras Asteraw Kebede.
♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
#Update የአማራ ፖሊስ ኮሚሽነር #አበረ_አዳሙ ባህር ዳር የተፈጠረው ሁኔታ ተረጋግቷል ብለዋል!

©Belay Manaye
♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
<<መፋንቅለ መንግስት የተባለው ፍፁም ስህተት ነው። መፈንቅለ መንግስት በየሰፈሩ አይደረግም። ፌደራል መንግስቱ ወደ ክልሉ ለመግባት ሆን ብሎ ፈልጎ የፈጠረው ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር። ይሄን መላው አማራ ተባብሮ መመከት አለበት!>>

ጀኔራል አሳምነው ፅጌ በስልክ ለAdiss fortune ከተናገሩት

♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
#Update የኢፌዴሪ መከላከያ ስራዊት ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮነንም በጥይት ተመትተው ሆስፒታል መግባታቸው እየተነገረ ነው።

♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️
በአማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ዘመቻ በአስቸኳይ ይቁም!!!

በሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ በነጻነት እንዳበራች ዛሬ ላይ እንድትደርስ የአማራው ሕዝብ መስፈሪያ የለሽ ዋጋ መክፈሉ ታሪክ ምስክር ነው:: ሃገራችን ተስፋፊና ወራሪ ሃይሎችን መክታ ሉዐላዊነቷ አስጠብቃ እንድትኖር የመላው ዜጎቿ ተጋድሎ ውጤት ቢሆንም አማራው ግንባር ቀደም በመሆኑ ለውጪና ለውስጥ ጠላቶች ኢላማ እንዲሆን አድርጎታል:: በዚህም ባለፉት 50 አመታት ግልጽ ጥቃት ተከፍቶበት ብዙ መከራን ሊያስተናግድ ተገዶ ቆይቷል::

በተለይ ባለፉት 28 አመታት አማራው በግልጽ ማንነቱን መሰረት ያደረገ የጥቃት ዘመቻ ተከፍቶበት ዋጋ ሲከፍል ቢቆይም ከኢትዮጵያዊ ማንነቱ ወርዶ በብሄር ላለመደራጀት በትግዕስት ለመቆየት ሞክሯል:: የመከራው መርግ መክበድ የግፍ መበራከትና የስቃዩ ብዛት ሳይወድ በግድ በብሄር ማንነቱ ተሰባስቦ እንዲመክት ተገዷል::

ሕወሃት ኦነግና ግብረአበሮቻቸው አማራውን ገለን ቀብረነዋል :: አከርካሪው ተሰብሮ እንዳይነሳ አርገን ጥለንዋል:: ቢሉም በማንነቱ መሰባሰብ በጀመረ ማግስት ያሳየው መነሳሳት ጠላቶቹን ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ ጥሏቸዋል:: የአማራው መነቃቃትና መደራጀት ለአማራው ብቻ ሳይሆን ጥላቻና የግንጠላ አጀንዳ ያላቸውን የጽንፈኛ ሃይሎችን ሕልም አምክኖ ለመላው ኢትዮጵያዉያን ብሄሮች ሕልውና ጭምር ተስፉ በመሆኑ አደረጃጀቱ እንዲመክን አንድነቱ እንዲበተን በግልጽና በስውር ሰፊ ዘመቻ ተከፍቶበት ቆይቷል::

ይህንንም ተቋቁሞ እራሱን ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል የሚያደርገውን ዝግጅት ለመቀልበስ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተቀናበረ ሴራና የፖለቲካ አሻጥር መፈንቅለ መንግስት በሚል ሰበብ በአንድ ቡድን የበላይነት በሚመራ የፌዴራል ጣልቃ ገብ ወታደራዊ ወረራ ስር እንዲውል ተደርጏል:: ይህንን በዓለም ታሪክ ተሠምቶ የማያውቅና ፍጹም ግልጽነት የጎደለው ድርጊት በጽኑ እናወግዛለን:: ለሃገር የማይበጅና ሁሉንም ወገን ዋጋ የሚያስከፍልና መሪውን የሚያስጠይቅ እርምጃ ባስቸኳይ እንዲቆም የሕዝቡን መብትና ነጻነት እንዲያከብሩ በጥብቅ እናሳስባለን::

ጠቅላይ ሚንስትሩ ድርጅታቸውና የፌዴራል ካቢኔያቸው ሃገር ሊያፈርስ ሕዝብን ለአመጽ ከሚጋብዝ ድርጊት ተቆጥበው ዘለቄታዊ አብሮነታችን እንዲቀጥልና ሰላማችን እንዲከበር ግልጽና አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ እንጠይቃለን:: የአማራው ሕዝብ የጀመረውን መብቱን የማስጠበቅና ሕልውናውን የመከላከል
ትግል ሳይከፋፈል አንድነቱን አጥብቆና አጠንክሮ እንዲቀጥል ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን::

እንዲሁም :-
1, መፈንቅለ መንግስት በሚል ተራ የቅጥፈት ፖለቲካ ሃገሪቷ ብሄራዊ አደጋ ላይ የወደቀች አስመስሎ በዶር አብይና በመንግስታቸው የቀረበው ዘገባና ፍረጃ አስቸኳይ የሆነ ማብራሪይ እንዲሰጥበት::

2, ከአማራ ክልል ፍቃድና እውቅና ውጪ በጠቅላይ ሚንስትሩ አዝማችንት በፌዴራል ወታደሮች የተደረገው ጣልቃ ገብነት ሕጋዊ አግባብነት የሌለው በመሆኑ ውሳኔውን የሰጠው አካል እንዲጠየቅ የፈጸሙትም ድርጊት በነጻና ገለልተኛ አካል እንዲጣራ

3, በአንድ ቡድንና ብሄር የበላይነት የሚመራው ወታደራዊ ካውንስል የሚወስዳቸው እርምጃዎች ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ባስቸኳይ ከአማራ ክልል ለቆ እንዲወጣ ጸጥታ የማስከበሩን ሃላፊነት ለክልሉ ፀጥታ ሃይል እንዲያስረክብ

4, ከሕግ አግባብና ግልጽ ባልሆነ ምክንያት የታሰሩ የክልሉ አመራሮችና የአማራ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲፈታ ጥፉት አደረሱ የተባሉም ካሉ በግልጽ እንዲዳኙ እንዲደረግ

5, ምንም ባልተጣራ ምክንያት በፌዴራል መንግስት በአማራ ሕዝብና መሪዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ : በሃገሪቱ የኢታማጆር ሹምና በጡረተኛው ጀነራል ላይ ምንነቱ ያልታወቀው ግድያ ገለልተኛና እለም ዓቀፍ አጣሪ ኮሚሽን ተቋቁሞ ሂደቱ እንዲጣራ

6, ከሕግ አግባብ ውጪ የአማራውን ሕዝብ ትጥቅ የማስፈታት እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆም: ሰላም ለማስፈን በሚል ሰበብ በሕዝቡ ላይ የሚደረገው ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን::

7, ኢሳት የተባለው ሚድያ ሕዝባዊ ወገንተኛነቱን ትቶ ለገዥዎች ልሳን በመሆን ያልተጣራ ዘገባና ውንጀላን በስፋት በማናፈስ እውነትን ለማድበስበስ ከሚያደርገው እርካሽ ተግባር እንዲቆጠብ ሕዝባችንም የሚዲያ ተቋሙን ቅጥረኛ ተግባር ተረድቶ እንዳይታለል በጥብቅ እናሳስባለን!

ድል ለሕዝባችን!
ጀግናችን ነህ!! 😭😭😭

♨️ @Haimonn @Gionamhara ♨️