Gion Amhara
71.1K subscribers
21.1K photos
960 videos
149 files
7.99K links
ማንኛውንም ጥቆማ ለመስጠት:-➛ @HaimonAb
Download Telegram
🔝#Update ትናንት ታህሳስ 26 ቀን በቋራ ወረዳ በደላ ቀበሌ በቅማንት ስም የተደራጀው ቡድን
ታጣቂዎች ድንገት በመድረስ በማሳቸው ላይ ጥጥ ሲለቅሙ የነበሩ አቶ ሲሳይ ገረመው የተባሉ የአማራ ገበሬን በጩቤ በመውጋት ጦር መሳሪያቸውን አንስተው ሲሸሹ በአከባቢው ከደረሱ ገበሬዎች ጋር በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የበርካቶች ህይወት አልፏል ተባለ
ትናንት ከረፋዱ 4 ስዓት አካባቢ በቋራ በደላ ቀበሌ በተኩስ ልውውጥ የሽነው በለጠ፣ቤዛው እናውጋው፣ሰለሞንና ፍቃዴ የሚባሉ የአማራ ተወላጆች ህይወታቸው ሲያልፍ አቶ አሰፋ አምሳሉና ሲሳይ ገረመው ቆስለው በጎንደርና ባህር ዳር የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ምንጫችን ከስፍራው አረጋግጧል።
በቅማንት ስም ከተደራጀው ቡድንም የስምንት ታጣቂዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን 4 ጀሌዎች እና 7 የታጠቁ በድምሩ 11 የሚሆኑት በአማራ የገበሬ ጦር ቢያዙም ሽንፋ የሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ተረክቦ ወደ ካንብ የወሰዳቸው መሆኑ ተነግሯል።

®አባይ ዘውዱ
@Haimonn @Gionamhara
📌አብኖች‼️

ማይ ጋድ ትንፋሽ እየተቆራረጠ ጨረስሁት። እንዲህ አይነት የጦፈ ቃለመጠይቅ አይቼ አላቅም። ጋዜጠኛ ስሜነህ ባይፈርስ በጋዜጠኝነት ህይወቱ እንዲህ አይነት ክላስ ያለዉ ፖለቲከኛ ገጥሞት የሚያዉቅ አይመስለኝም። ጋዜጠኛዉ እንደ አብረሃ ደስታ ቄጤማ መስለዉት መንፈራገጥ ቢሞክርም(በርግጥ ሃርድ ቶክ ስለሆነ ልክ ነዉ) ለራሱ እስከሚገርመዉ ድረስ ብልጫ ወስደዉበታል። ይኸን ቃለመጠይቅ ጤናማ የሆነ ሰዉ እና የምቀኝነት ካንሰር ወይም ማዴቦ ሲንድረም ተጠቂ ካልሆነ ጠላትም ቢሆን ሊያደንቀዉ የሚገባ ነዉ። እነህን ምርጦች በርካታ ሚሊየኖች ተመልክተዉ ተደመዉባቸዋል። እርግጠኛ ነኝ ዶክተር አብይ ተመስጦ አይቶ በመጨረሻም አጨብጭቦላቸዋል፣ እነ ልጥም አይተዉ ከእነኝህ ጋር መወዳደር እንደማይችሉ ገብቷቸዉ ተስፋ ቆርጠዋል፣ ህወሃት የተኛችበትን መደብ አርጥባ ጭቃ አድርጋዋለች። በአንድ ደቂቃ ማስታወቂያ ያለቀሱ አይኖች ዛሬስ ምን ይሉ ይሆን?
ክርስቲያን "የህወሓት ምልክቶች በጠቅላላ መጠቀም ወንጀል እስከሚሆን እንታገላለን" የሚለዉን ሲናገር በስሜት ለማጨብጨብ ሞክሬ(ስልክ ይዣለሁ እኮ ) live የማይባት ስልኬን ሰብሪያት ነበር።
የሀገራችን ኢትዮጵያ ፖለቲካዎች ሁሉ በአብን ዙሪያ ይሽከረከራሉ።
Christian Tadele, Belete Molla እና የአብን አመራሮች በጠቅላላ የተፈጠራችሁት ለአማራ ነዉ። በቃ ምርጥ ናችሁ‼️

©Amanuel Abinet
@Haimonn @Gionamhara
🔝#update
በግድ ወደ ቡሌ ሆራ ተመለሱ የተባሉት የአማራ ተማሪዎች ተቃውሟቸው እያሰሙ ነው።
"በዘር መፈናቀል መጠቃት ይቁም"
"ከዚህ የመጣ ነው ሞትን አምልጠን እንጅ ፣ረፍት ተሰጦን አይደለም"

©ልሣነ_ዐማራ
@Haimonn @Gionamhara
📌መረጃ ‼️

የሱር ኮንስትራክሽን መኪኖች ከጮንጮቅ በጭልጋ-ኮኪት አድርጎ በአብድራፊ ከዛም ሁመራ-
መቀሌ ለመግባት መንገድ ጀምሯል። በአሁን ሰአት ሸኸዲ ከተማ እየገባ ነው ተብሏል።
ጥብቅ ክትትል ይደረግበት‼️

©ልሣነ_ዐማራ
@Haimonn @Gionamhara
📌ትላንት በዋልታ ቲቪ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አመራሮች ክርስቲያን ታደለ እና ረ/ፕ በለጠ ሞላ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ሲጠቃልል፦
ክርስቲያን ታደለ

''የአማራነት መመሪያችን''
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ
ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ ነው።
📌መመሪያችን እንደሚለው የምንሰራቸውን እንቅስቃሴዎች የምናሰላው የአማራ ህዝብ በወርዱ እና በስፋቱ ልክ ተጠቃሚ እንዲሆን
ነው። ሌሎች ልዩ የመልማት ፀጋ እንዳላቸው እኛም ለሀገር ባበረከትነው ልክ እኩል ተጠቃሚ እንሁን ነው የምንለው።
📌የአማራ ህዝብ ተፈጥሮአዊ ባህርይው
በግለሰብ ማንነት የሚያምን ነው።
📌ፌደራሊዝሙም የትንሾች ፈላጭ ቆራጭ አስፈፃሚ ነው። 70% የሚሆነው የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ማሻሻል ቢፈልጉ አይችሉም ምክንያቱም ማሻሻል የሚችሉት ውህዳን ናቸው።
📌ማንነት ጥቅል ነው። በደም ብቻ አይደለም።

በለጠ ሞላ

📌የአማራ ህዝብ አሁን ላለበት ሁኔታ አንዱ
ተጠያቂው አዴፓ(ብአዴን) ነው።
📌የብሄር እና የህልውና ትግል አለ።እኛ
የምናደርገው ትግል እንደ ህወሃት እና ኦነግ በሚያደርገው መልክ ማየት የለባችሁም። እነሱ ታሪካዊ መሠረት የሌለው ትርክት ይዘው ለመምጣት አማራን በጠላትነት ፈርጀው መጡ።
አማራ እንደ ህዝብ ጠላት የሆነበት ታሪክ የለም።
እኛም እንደ ህዝብ ጠላት ብለን የፈረጅነው ህዝብ የለም። ስህተትም ነው። አማራ በጠላትነት የተፈረጀው ሆን ተብሎ የህወሓትን ጥቅም ለማስከበር እና ህዝቡን ለመጉዳት ነው የተንቀሳቀሰው።
📌እትዮጵያ እንድትቀጥል የሚፈልግ ሀይል እኛን መደገፍ አለበት።

ክርስቲያን ታደለ

አብን ብሎ ሀገራዊ ፓርቲ እንዴት ይሆናል?
📌ደማዊ የማይቀየር እና እስከሞት ይሄዳል።
አውሮፓውያን እስከ 1870 ዓ.ም ድረስ እንደ ሀገር ያቆማቸው ደማዊ ማንነት ነው።
📌አማራነት ደምም ነው ስነ ልቦናዊ ስሪትም ነው።
📌ህወሃት የዘር ማጥፋት የፈፀመ ድርጅት ነው የህወሃትን አርማ እና ምልክት መጠቀም ወንጀል
የሚሆንበትን ስርዓት ነው የምንፈጥረው። ልክ የናዚን ዛሬ በአለም ላይ የተጠቀመ ሁሉ እንደሚወነጀለው። ህወሃት አሸባሪ ብቻ ሳይሆን
2.5 ሚሊዮን የአማራን ህዝብ የት ገባ ብሎ የጠየቅ ድርጅት ነው።
📌120 ህዝባዊ መድረክ ስናካሂድ የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ለይተናል።
1. የግዛት እና የህዝብ የኢ-ተነጣጣይነት
(የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ርስቱን እና ወገኖችን ወደ ተለያዩ ክልሎች ተካሎበታል) ይህነን
መፍታትተ።
2.የአማራ ያልተወከለበት ህገ መንግስት
እንዲቀየር።
3.በፀጋችን ልክ መልማት አለብን።
4.በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ አማራዎች
የራሳቸውን ቋንቋ የመጠቀም መብታቸው
እንዲከበር እና አስተዳደራዊ ውክልና
እንዲኖራቸው ማድረግ። ለምሳሌ፦ 15 ሚልዮን አማራ በኦሮሚያ ይኖራል ግን ምንም አይነት ውክልና የላቸውም በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል፣በሃረሪ...
5.የአማራ ህዝብ ሀገር ገንቢ ከመሆኑ አንፃር የፖለቲካ ውክልና እንዲሰጠው። በዓለም ካሉ ሀገራት 133ቱ የህዝባቸው ቁጥር 2.5 ሚሊዮን ነው። ስለዚህ ወያኔዎች የአማራን አንድ ሃገር
የሚሆን ህዝብ አጥፍተዋል።የአማራ ህዝብ በህዝቡ ቁጥር ማግኘት የሚገባውን በ10 ዓመታት ውስጥ 70 ቢሊዮን ብር ሳያገኝ ቀርቷል።
6.አማራ ጠል ትርክት ለዘመናት አማራ መጤ እየተባለ ሲፈናቀል ሲገደል ኖሯል። ስለዚህ ህዝባችን በግለሰብ እና በድርጅት ደረጃ ይቅርታ እንዲጠየቅ እና ተመጣጣኝ ካሳ እንዲያገኝ እንፈልጋለን።
እነዚህ ጥያቄዎች ጠቅለል ሲደረጉ በሁለት ከፍለን እናያቸዋለን፦
1ኛ.የፍትህ
2ኛ.የእኩልነት ጥያቄዎች ናቸው።

አማራነት‼️
@Haimonn @Gionamhara
አንድ አርባዊ ውጪ የማቃቸው ወዳጂ
አድርጊያቸው
ልጄን ሊያስተምሩ መፅሐፍ ሰጥቻቸው
ጠርዘው ላኩሉኝ ደግ ሰው ስላቸው https://telegram.me/one1lovee
🔝"በገና ጨዋታ
አይቆጡም ጌታ"
....
ኢየሱስ ክርስቶስ የጠፋውን አዳም ፍለጋ አምላክ ፍፁም ሰው ሆኖ በከብቶች ግርግም(በረት፣ጋጣ) በሀገረ እስራኤል ተወለደ፡፡
...
የጌታ በፍፁም ትህትና መወለድ ለሰው ልጆች ድህነት እና ለሰዋዊ ክብር የተበረከተ ልዮ ስጦታ ነው፡፡
..
ለዚህም ዘመን በኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ይሰፈራል፡፡ሮማያኑ(ካቶሊካውያኑ) የኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደ 2019 ኛ ዓመት ይደፍናል፡፡በኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ 2011 ኛ ይሰፍራል፡፡ቆጠራውም አቡሻኻር ይባላል፡፡መነሻው የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ነው፡፡
...
ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደባት የእስያዋ ሀገር እስራኤል እየሩሳሌም የተሰኘች የሃይማኖት ከተማ አለቻት፡፡ ኢትዮጵያውያን ወደ ቅድስቷ ከተማ ለስድስት ወራት ተጉዘው የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ያከብሩባት ነበር፡፡
...
ንጉስ ላሊበላ የእየሩሳሌምን ጉዞ አስቀርቶ በሀገሩ ለማድረግ ዳግማዊት እየሩሳለምን በሮሃ አደባባይ በቡግና አውራጃ ላስታ ላይ ተከለ፡፡
....
ላሊበላ ዓለም ካሏት 1051 የተመዘገቡ ቅርሶች መካከል ፍፁም የተለየ እና አስገራሚ በመሆን ከዓለም ስምንቱ ደማቅ ቅርሶች መካከል አንዱ ነው፡፡ንጉስ ላሊበላ የተወለደው ታህሳስ 29 ቀን በ 1101 ነውና በአሰሩት ፍልፍል አብያተክርስቲያን ልደቱ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ጋር መሳ ለመሳ ይከበራል፡፡ ላሊበላ ዳግማዊ እየሩሳሌም በመሆኗ እና የላሊበላ ልደት በዓል ታህሳስ 29 በመሆኑ የገና በዓልን በልዮ ድምቀት ታከብራለች፡፡
...
ቀደሞት አባቶች ራስን ለመቻል ባላቸው ጉጉት ኢየሩሳለምን በሮሃ አኖሩ፡፡የዘመን ቀመርን በራሳቸው አሰሉ፡፡ፊደል እና ቋንቋን ፈጠሩ፡፡ ዶክተር ስርግው ገላ እንደሚሉት አማርኛ ቋንቋ የበለፀገው በነንጉስ ላሊበላ ዘመን ነው፡፡አባቶቻችን እንዲህ ናቸው፡፡
...
ፈላስፋው ሰለሞን ደሬሳ በኛ ሃገር ሀይማኖት ከእምነትነቱ ልቆ ማንነት ሆኗል ይላል፡፡እውነት ነው፡፡ላሊበላ የመላው ኢትዮጵያዊን አሻራ እንጂ የክርስቲያኖች ብቻ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ በክርስትናም ሆነ በእስልምና ሃይማኖቶችን ቀድማ ተቀብላ ከባህል እና ወጓ ጋር አዛንቃ በሀይማኖቷ ታሪክ፣ባህል እና ማንነት የፈጠረች ልዮ ሃገር ናት፡፡
....
ክብር በራሳቸው ቀለም ሀገር ለገነቡ አባቶቻችን!
...
ለእምነቱ ተከታዮች መልካም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ይሁንላችሁ!!
@Haimonn @Gionamhara
📌የዘንድሮ ገና ልዩ የሚያደርገዉ
‼️
ኤርትራን ከትግራይ የሚያገናኘዉ የዛላንበሳ ድንበር ተከርችሞ ተዘግቶ ኤርትራን ከአማራ የሚያገናኘዉ የሁመራ ድንበር መከፈቱ እና

ጋዜጠኛ አበበ ገላዉ የሰማይ ስባሪ የሚያክል ማስጠንቀቂያ ለልጥ ካድሬዎች መስጠቱ ነዉ
የእነኝህ የህወሓት እና ልጥ አጃቢዎች ለቅሶ ደግሞ ለእኛ ጣፋጭ ሙዚቃ ነዉ።
ይመቻችሁ

©Amanuel Abnet
@Haimonn @Gionamhara
🔝ተኩ መተኪ የትህነግ የሁመራ ወኪል ነበር። በርካታ የወልቃይት አማሮችን ሲያሳፍን ሲያስገድል የነበረ ሰው ነው። በቅርቡ የትግራይ ክልል ፀጥታ ኃላፊ ሆኖ ተሹሟል። በቅርቡ ጎንደር ላይ በተደረገው ሰልፍ ሶስት ሰላዮቹ ተይዘውበታል።
ዛሬ አቶ ገዱ ሁመራ እንዳይገባ ወጣቶችን አደራጅቷል ተብሏል። ሁመራ ትህነግ አማራውን አፈናቅሎ ከትግራይ በርካታ ሰዎችን በማስፈር የቀየረው ከተማ ነው። ያም ሆኖ ከግማሽ በላይ አማራ ይኖርበታል።
አቶ ገዱ ወደ ትግራይ ሳይሆን ወደ ሁመራ አታልፍም ተብሏል። እሱ ግን ወጣቶች ምርት እንዳያልፍ አደረጉ ብሎ መግለጫ ሰጥቶባቸዋል። ጥሩ ነው ይየው❗️

©Getachew Shiferaw
@Haimonn @Gionamhara
🔝በዓሉ ይብቃንና ወደ ሞታችን እንመለስ‼️

መንግስት አልባው እና የጦር ቀጠና የሆነው የምዕራብ ጎንደር ዞን ዛሬም አንድ ጀግና አጥቷል፡፡
ታጋይ ብርሌው ብቃለ
የአማራ ክልል መንግስት እንኳን ደስ ያለህ ልጆችህ በየ ቦታው እየረገፉ ይገኛሉ፡፡ በተደጋጋሚ እየታፈን እየታገትን እየሞትን አሁንም የመንግስትን ድጋፍ እየጠየቅን እዚህ ደርሰናል፡፡የዘር ፍጅት ቀጥተኛ ተጠቂው አማራ ብቻ ነው፡፡ ይህ የመጨረሻው ደወል መሆኑን እወቁት፡፡
በተደጋጋሚ ቀጠናውን መቆጣጠር አላቃተንም ነገርግን .........ብሎ የሚደልለን የአማራ ክልል እዚህ ጋ ጨዋታውን ያቁም!
#ሽንፋም ይገደባል #አማራም በልጆቹ ታሪኩን ያድሳል
ለመላው ቤተሰቦቹ ና የትግልአጋሮቹ መፅናናትን እመኛለሁ፡፡

©Abat Yemataw
@Haimonn @Gionamhara
📌የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሁመራ ከሚኖሩ የትግርኛ ተናጋሪዎች በተወሰኑ ወጣቶች ተቃውሞ ደረሰባቸው።

ዛሬ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና ከዶ/ር ደ/ጺዎን ገ/ሚካኤል የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈ ወርቂ ጋር በመሆን የአማራን ክልል ከኤርትራ ጋር የሚያገናኘውን መስመር በይፋ ለመክፈት ወደ ሁመራ አቅንተዋል።" በተወሰኑ የትግርኛ ተናጋሪ ወጣቶች በሰላማዊ መንገድ የተስተጋባው የተቃውሞ ድምጽ የሚበረታታ ነው።ላለፉት እረጅም አመታት ድምጻቸውን እንዳያሰሙ ተደርገው በህወሃት ተረግጠው ይኖሩ የነበሩት ቤተሰቦቻችን በጋራ ባደረግነው ትግል ዛሬ ለሰላማዊ ሰልፍ በቅተዋል።
#ነገር ግን በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተሰሙትና የተያዙት አጀንዳዎች ግን ፍጹም ስህተት ናቸው።

አቶ ገዱ የአማራ ህዝብ መሪ ሁነው እያገለገሉ በመሆኑ ከጥያቄው ውጭ የተግባር እንቅስቃሴ የሚደረግ ከሆነ መልሱ ለጥቂት ወጣቶች ብቻ ሳይሆን ሌላ ጊዜ ህወሃት በሌላ ቦታ ላይ ድምጹን እንዳያሰማ አድርገን መልስ እንደምንሰጥ ማሳወቅ እንፈልጋለን። አቶ ገዱን ማውረድ የኛ የአማራ ህዝብ ተግባር ነው።በጥፋታቸው ልክ እንደምንጠይቃቸውም የሚታወቅ ሁኖ ህወሃት ላሳዬው ንቀት ተቆጥሮ የሚመለስለት ይሆናል።
ትግላችን ይቀጥላል።

©Masresha Setie
@Haimonn @Gionamhara
🔝በኢትዮጵያ በኩል ከአማራ ግዛት እንዲሁም በኤርትራ በኩል ከጋሽ ባርካ ጋር የሚያገናኘዉ መንገድ አቶ ገዱ፤ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ እና ኢሳያስ አፈወርቂ እንዲሁም እንዳንድ የሌሎች ክልሎች ባለስልጣናትም በተገኙበት ተከፍቷል፡፡ለምሳሌ ከትግራይ ክልል ዶ/ር ደብረጺዎን በእንግድነት ተገኝቷል፡፡
ከአዲስ አባባ-ባህርዳር-ጎንደር-ሁመራ-ባሬንቱ-አስመራ ያለዉ መንገድ ትልቅ የንግድ ቀጠና ነዉ፡፡ ዛሬ በገና በአል ላይ ሰብሰብ ብላችሁ እያወራችሁ ያላችሁ ሰወች ይሄን የንግድ መስመር እንዴት መጠቀም እንዳለባችሁ መወያየት አለባችሁ፡፡ የአማራ ህዝብ እንደ ዝንጀሮ ጋራ እየቆፈረ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ሊያቆም ይገባል፡፡ ለንግድ ያለንን አመለካከት ሙሉ በሙሉ መቀየር አለብን፡፡ እርሻ እንዲሁም መንግስታዊ አስተዳደር ዉስጥ የመሳተፍ ልምድ ቢኖረንም ንግድ አካባቢ በእጅጉ የራቅን ነን፡፡ኢኮኖሚዉን ያልተቆጣጠረ የህብረተሰብ አካል ሁሌም ቢሆን በባርነት ነዉ የሚኖረዉ፡፡
ከበኣል ጋር ተያይዞ የሆነ ስህተት ፈጽሚያለዉ፡፡ ይሄ መድረክ ሳገኝ ሞቅ የሚለኝ ነገር አልተወኝም፡፡ እና የአካባቢዉ ሰዉ ተሰብስቦ ጠላዉን እየጠጣ ባለበት ሰአት ይሄ አዲሱ በቴሌቢጅን ምናየዉ ጉንጩ ሞላ ሞላ ያለዉ ሰዉየ ሲያወራ ለጉድ አደል አለ አንደኛዉ ከቢጫነት ወደ ጥቁርነት የተቀየረች የንብ ምልክት ያለበት ኮፍያ ያረገ፡፡ አይ ያችን ዉሃ ያሰራት ቀን እንዲየያዉ ያሰራት ብለህ አለች ራቅ ብላ አጇን ጉንጯ ላይ ጣል አድርጋ የኔን ወሬ ቆማ የምትከሸክሸዉ እከስቴ፡፡ እሚገርምህ ያ ሌባ ሊቀመንበር---- ከ----(ስሙን አልፌዋለዉ) እስከ አዲሱ መንደር የሚያደርሰዉን መንገድ ሊሰራ ብሎ 400 ሺህ ብር አዋተን እሄዉ ስኒከር እና ጁባ እያቀያየረበት ነዉ፡፡ እይ እሱን እማ ካላነሳልን ማፈራችን ነዉ አለ ሌላኛዉ አንድ እግር ታጣፊ ክላሽ በግራ እጁ ይዞ ጠላዉን ፉት እያለ፡፡ አዲሱ መሪ ዶ/ር አብይ ስለማገኘዉ እነግረዋለዉ አልኩ እንዲያዉ ሳላስበዉ ነዉ አንዲት ዋንጫ እኮ ናት እንደዚህ የምታስለፈልፈኝ፡፡ ዛሬ ከኤርትራ ጋር ያለዉን መንገድ ሊከፍት እንደሚሄድ አዉቃለዉ አልኳቸዉ፡፡ መቸም ዜና እንደሚሆን ሰላወኩ ሬዲዮኑ ሲከፈት ጸጥ እንዲሉ ነገርኳቸዉ፡፡ ሲከፈት እራሱ የመጀመሪያዉ ወሬ እሱ ነዉ፡፡ አሁን መቶ ፐርሰንት እርግጠኛ ናቸዉ ጠቅላይ ሚኒስቴሩን በቅርበት እንደማዉቀዉ ወይም ጓደኛዉ እንደሆንኩ፡፡ ቀጥሎ ያሉኝ የሽንሽናዉ ዉሃ እኮ ደረቀ ያ የድሮዉ አግረ ደረቅ መንግሰት በስሚንቶ ሰራንላችሁ ብለዉ አድርቀዉት ሄዱ አሉኝ፡፡አይ ሴቱ ተቸገር ዉሃ ፍለጋ አለ አንደኛዉ ሸማግሌ ዘመዳችን፡፡ ምንም ችግር የለም ይሰራል ብያቸዋለዉ፡፡ የኔ ከዚህ በኋላ ወደዚህ ቀበሌ መመለስ ከዚህ ዉሃ ጋር የተሳሰረ ሁኗል፡፡ ካልተሰራ ልሄድ አልችልም፡፡ ዶ/ር አብይ ትረስት ፈንድ ካለዉ ላይ ትቂት ብር መድቦ ካላሰራዉ ጉድ ሁኛለዉ፡፡ አዉቀዋለዉ ይሰራል ብየ መቸም የሚቀጥለዉ አመት ላይ ያዉ ከሆነ ምን እንደሚሆን ታዉቃላችሁ፡፡


©ሚኪ አማራ
@Haimonn @Gionamhara
📌ያልተገባው የ1990 ዎቹ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦርነት ድሮውንም ቢሆን የተካሄደው በኢኮኖሚ አሻጥር ምክንያት ነው፡፡ትህነግ የአስመራ ነጋዴዎች መቀሌን እንዳያልፉ በማድረግ ከመሃል አገር ጥሬ እቃ እየዘረፈ በውድ ለኤርትራ ነጋዴዎች መሸጥን ለመደ፡፡ ትህነግ ከጅማ ቡና እያመጣ መቀሌ ወይም አዲግራት ላይ በውድ ዋጋ ይሸጣል፡፡ ከሰሞኑሞ ከጎጃም እና ከሸዋ ጤፍ በእርካሽ ዋጋ ወደ መቀሌ ያስገቡና በውድ ዋጋ ለኤርትራ ይሸጣሉ፡፡ ይህ በመሆኑም የዳቦ ዋጋ በትግራይ ተወደደ፡፡ቅሬታም አስነስቷል፡፡ የዛላንበሳ መስመር ለመሃለኛው የኢትዮጵያ ክፍል በንግድ ሳያስተሳስር ቀረ፡፡ የአስመራ ነጋዴዎች ከመቀሌ እንዳያልፉ አድርገው የኮንትሮባንድ ንግዱን ተቆጣጠሩት፡፡
...
ትህነግ ከተከዜ ማዶ ለኢኮኖሚዋ ስትል በጊዜዋ ጉልበት የያዘችው መሬት እንደሆነ ታውቃለች፡፡በሁመራ እና በወልቃይት ግዛቶች ሆነ ህዝቦች እምነት የላትም፡፡ የሁመራን ግዛት እንደ ምሽግ እና እንደ ኮንትሮባንድ የንግድ ማዕከል መጠቀም በአማራጭነት ይዛለች፡፡ ስለዚህ በሁመራ በኩል መደበኛ የንግድ መስመር እንዲከፈት ትህነግ አልፈለገችም ነበር፡፡ የሁመራም ህዝብ እንዲጠቀም አትፈልግም፡፡፡ የትህነግ ደጋፊዎች ይሄ መስመር በመከፈቱ ዶክተር ደብረፅዮንን ሳይቀር እያወገዙ ነው፡፡ ትህነግ ከተከዜ ማዶ እና የራያን ግዛት አለማመኗን ሁሌ እያሳየች ነው፡፡
...
በሁመራ ጎንደር ባህርዳር አዲስ አበባ ያለው መስመር እስከ ሞያሌ እና ድሬድዋ የንግድ መስመር ለመዘርጋት የኢትዮጵያም ለኤርትራም ጠቃሚ ነው፡፡የትህነግን የኢኮኖሚ አሻጥርም ይቀንሳል፡፡ ደቡብ እና ኦሮሚያ ቡናቸውን በዚህ መስመር ያለ ትህነግ እጅ ለማሳለፍ ይቻላቸዋል፡፡
...
ነገር ግን ትህነግ ከትግራይ ክልል ውጭ ያለውን የኢትዮጵያ ክፍል ሰላማዊ እንዳይሆን በማድረግ ንግዷን ከሽሬ እንዳያልፍ ለማድረግ ሳትጥር አትቀርም፡፡ በጎንደር በኩል በቅማንት ኮሚቴ ስም ፣በኦሮሚያ በኦነግ ማለያ በመጫወት መንገዶችን መዝጋት ፣ተጓዦችን በመዝረፍ የንግድ ግንኙነቱን ልታቋርጥ ትችላለች፡፡
...
ትህነግ 30 ሺ ሰራዊት የነበረውን ኦነግ በማባባል በ 1983 ማርካዋለች፡፡በ 1984 ከሀገር አባራዋለች፡፡ከዚያም አሸባሪ ብላ ወደ በረሃ ሸኝታዋለች፡፡ ይሁን እንጂ የኦነግ አጋር በመምሰል የእነ ዶክተር አብይን አስተዳድር ለመረበሽ ኦነግን ምርኩዝ እያደረገች ነው፡፡ ኦነግም በ 1983 ሰላሌን፣አዳማን(ናዝሬትን) ፣ቢሾፍቱን(ደብረዘይት) የነፍጠኛ ይዞታዎች ናቸው ውሰዱልኝ እንዳላለ ዛሬ ወሎ የኔ ነው ይል ይዟል፡፡ በ 1984 ምድረገኝ ( ከሚሴ) ኦነግ በሽግግር መንግስቱ ጊዜ 20% ኦሮሞኛ ተናጋሪዎች ስላሉ ብሄረሰብ አስተዳድርነት ተሰጠው፡፡ ቆይቶ ግን ወሎን ጠቅሎ ራያ የኔ ነው፡፡ከትህነግ ጋር ወሰነኛ ነኝ ማለቱ አልቀረም፡፡ይህን ምኞቱን ትህነግ አማራ እና ኦሮሞን ለማጣላት ትጠቀምበታለች፡፡
...
የዶክተር አብይ አስተዳድር በኦሮሞ እና በሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠላ ፀረ ፌዴራል መንግስት ነው ፡፡ደርግ ነው እያለች ነው፡፡
ባለፈው ቅዳሜ ትህነግ የወታደር ሂሊኮፍተር ለማስጠለፍ በሁመራ በኩል ሙከራ አስደረገች፡፡እሁድ ደግሞ ለሀገር ክብር ሳይጨነቁ በውጭ ሀገር መሪ ፊት ዶክተር አብይ እና አቶ ገዱን "ሌባ" ብለው እንዲሰደቡ አደረጉ፡፡በእርግጥ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ የትህነግ ቁማር ስለሚገባቸው የበለጠ ይንቃቸው ካልሆነ ሌላ የተለየ ትርጉም አይሰጡትም፡፡ በተዘረፈ መሬት ቁሞ ሌላውን ሌባ ብሎ መስደብ የተለየ የብልግና ጥበብ ይጠይቃል፡፡ ይሄ ጥበብ በብቸኝነት ትህነግ ቤት አለ፡፡
...
የሁመራ መስመር መከፈት ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ በረከት እንጂ መርገም አይሆንም፡፡ ለኮንትሮባንዶች ብቻ መርገም ሊሆን ይችላል፡፡

©የሺሀሳብ አበራ
@Haimonn @Gionamhara