Gion Amhara
70.9K subscribers
21.1K photos
960 videos
149 files
7.99K links
ማንኛውንም ጥቆማ ለመስጠት:-➛ @HaimonAb
Download Telegram

ነገ አርብ ማሐትም 04/01/2011/ ዓ. ም ባህር ዳር
በህዝብ ማዕበል እንደምትጥለቀለቅ ጥርጥር የለኝም ።
ምከንያት ለምትሉ የአማራን መገፋት ከፕሮፌሰር አስራት
በሗላ ለመገመሪያ በመረዳት በርሃውና ቁሩ ሳይገድባቸው
በዱር ገደሉ ከወያኔ ጋር ሲዋደቁ የነበሩት የአዴሃን
ታጋዮች የምስጋና ዝግጅት ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በባህር
ዳር አለማቀፍ እስታድየም ይዘጋጃልና ።
ከዚህ በተጓዳኝ ግንቦት ሰባት ቅዳሜ ባህር ዳር የማመጣ
ሲሆን ይህ የቁማር ድርጅት በአማራ ህዝብ ላይ
የአዴሃንና የአርበኞች ግንባርን ጨምሮ አሁንም በተለያዩ
የአማራ ግዛቶት አርሶ አደሮች ላይ የትጥቅ ማስፈታት
ዘመቻ የቀጠለ ሲሆን ይህንን የግንቦት ሰባት ሴራ
የሚያጋልጡ ባነሮችን በመያዝ በእለተ ቅዳሜ ድርጅቱ
በሚመጣበት ዕለት የተቃውሞ ሰልፍ በዚያው ባህር ዳር
ከተማ ለማካሄድ እንዘጋጅ።
@haimonn @Gionamhara
ሰውዬው አንበሳ ሊያድን ጫካ ይገባል፡፡ እየተሽሎከለከ
ዛፍ ለዛፍ
ሲያነጣጥር፣
የአንበሳውንም ዱካ እያዳመጠ ሲከተል፣ ቆየና አንድ
የአንበሳ ደቦል
በቀስቱ አነጣጥሮ
ጣለ፡፡ ገና ደስታውን ሳያጣጥም የሰውነት ክፍሎቹ እርስ
በርሳቸው
ተጣሉ፡፡ እጁ
አንበሳውን አነጣጥሮ የጣለው እርሱ መሆኑን በማስረዳት
የተለየ
ክብር ሊሰጠው
እንደሚገባ ተናገረ፡፡ ይህንን የሰማው እግሩም
‹መጀመሪያውኑ ማን
ተሸክሞህ መጥተህ
ነው ወጋሁት፣ መታሁት የምትለው› ብሎ ክብሩ የእርሱ
መሆኑን
ገለጠ፡፡ ነገሩን የታዘበው
ዓይንም ‹በምን ዓይተህ ነው ያነጣጠርከው› አለና ክብሩ
የእርሱ
መሆኑን በኩራት ደሰኮረ፡፡
ጆሮም የአንበሳውን ዱካ እኔ በጽሞና ባልከተል የት ታገኙት
ነበር?
ሲል ቀዳሚው ባለ ድል
እርሱ መሆኑን ደነፋ፡፡ አፍና ሆድም ‹ባልተበላ ምግብ
በባዶ ሆድ
እንኳን ማደን መታደን
አይቻልም› ሲሉ ተከራከሩ፡፡
እንዲህ የሰውነት ክፍሎች ሁሉ እየተነሡ ‹ተኳሹ፣ መራዡ፣
አነጣጣሪው፣ እኔ ነኝ› እያሉ
ሲከራከሩ ሰውዬው ወደ ግዳዩ ሳይሄድ ዘገየ፡፡ በዚህ
መካከል
ዓይን ቀና ቢል አንበሳው
ሲሞት ያሰማውን ድምጽ የሰሙ ሌሎች አንበሶች
ዙሪያቸውን
ከበዋቸዋል፡፡ ዓይን
በድንጋጤ ሲፈጥ ያስተዋለው እጅም ለሌሎች አካላት
መከባባቸውን ጠቆመ፡፡ ይህን
የተመለከተው እግር እሮጣለሁ ብሎ ሲያስብ እንኳን
መሮጫ
መሹለኪያ ቀዳዳ አላገኘም፡፡
ቅድም እኔ ነኝ እኔ ነኝ እሉ ሲፎክሩ የነበሩት ሁሉ ለየብቻ
ሮጠው
ማምለጥ
አልተቻላቸውም፡፡ አንበሶቹ ግን የግዳይ ቀለበታቸውን
እያጠበቡ
እያጠበቡ ተጠጉ፡፡
ፍጻሜውም መበላት ሆነ፡፡
ዛሬም በኢትዮጵያ የሚታየው ይሄ ነው፡፡ ባለ ድሉ እኔ ነኝ፣
ታጋዩ እኔ
ነኝ፣ ለውጡን
ያመጣሁት እኔ ነኝ፣ የዚህ ሁሉ ፊታውራሪ እኔ ብቻ ነኝ፣
ሠሪ
ፈጣሪው፣ ያዡ ገናዡ እኔ ነኝ፤
የቅድምና ሩጫ የክብር እሽድድም፡፡ ከአንባሰው ሞት
በኋላ ምን
እናድርግ? ብለው
ከመወያት ይልቅ አንበሳውን የገደለው ማነው? በሚል
ውዝግብ
ውስጥ እንደገቡት
የሰውነት ክፍሎች፣ዛሬም ከተፈጠረው ለውጥ በኋላ ምን
እናድርግ? ችግሩ ተመልሶ
እንዳይመጣ፣ የተሻለ ቀንም እንዲፈጠር ምን እናድርግ?
ከማለት
ይልቅ ‹የዚህ ሁሉ
ጫጩት አውራው እኔ ነኝ› የሚል በሽታ ውስጥ ገብተናል፡፡
የአንድ
ሰውነት አካላት
መሆናችን ረስተናል፡፡ የሚና ልዩነት የአስተዋጽዖ ተዋረድ
ፈጥሮብናል፡፡ አሁንም ከትናንት
ሳንወጣ በትናንት አዙሪት ውስጥ እየገባን ነው፡፡
አንድ ሯጭ ምን ያህል ኪሎ ሜትር እንደሮጠ ከማሰብ
ይልቅ ምን
ያህል ከፊቱ
እንደሚቀረው ማሰቡ ነው የሚጠቅመው፡፡ የሮጠው ያለቀ
ጉዳይ
ነው፡፡ የሚሮጠው ግን
ገና የሚቀርና የሚፎካከርበት መድረክ ነው፡፡ ምንም ያህል
እየመራ
ቢሆን ገመዱን በጥሶ
እስካልፈጸመ ድሉ ተጠናቅቋል ማለት አይቻልም፡፡ አንደኛ
ሆኖ
መቅደም አንደኛ ሆኖ
ለመውጣት ብቸኛው ዋስትና አይደለም፡፡ ድሉን እስከ
መጨረሻው
ካላስጠበቀ በቀር፡፡
በአንድ ሀገር ታሪክ ውስጥ አንድ ሰው፣ ቡድን፣ ፓርቲ፣
ማኅበረሰብ
ብቻውን የሚያመጣው
ለውጥ የለም፡፡ ለውጥ የሂደት ውጤት ነውና፡፡ ነገር ግን
የሚታዩና
የማይታዩ ለውጥ
አምጭዎች አሉ፡፡ መቼም የሰው መታወቂያ ላይ የሆድ
ዕቃው ፎቶ
አይወጣም፡፡ የፊቱ
ጉርድ ፎቶ እንጂ፡፡ ያ ማለት ግን ሰውዬው ፊቱ ብቻ ነው
ማለት
አይደለም፡፡ ለውጥና
ትግልም እንደዚያው ነው፡፡ ከፊት የሚታዩት ፊታውራሪዎች
የማይታዩት ውጤቶች
መሆናቸውን ከረሱ አንገትን የዘነጋ ጭንቅላት ይሆናሉ፡፡
ዝናብ
እንዲመጣ የተፈጥሮ
ኃይሎች ሁሉ የተባበረ አስተዋጽዖ እንደሚያደርጉ ሁሉ
ለውጥ
እንዲመጣም ማኅበራዊ
ኃይሎች ሁሉ የሚታይና የማይታይ አስተዋጽዖ አላቸው፡፡
የተሻለውና የሚጠቅመው ነገር ‹እኔ ብቻ ነኝ‹ ና ‹ለእኔ
ብቻ
ነው›
የሚለውን ስሜት አጥፍቶ
‹እኛ ነንና ለእኛ ለሁላችን ነው› የሚለውን እውነታ
መቀበልና
ማስፈን ነው፡፡ ድልን
ማስጠበቅ ድል ከማድረግ በላይ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ለአንድ
የእግር
ኳስ ቡድን ግብ
ከማስቆጠር በላይ የማሸነፊያ ነጥቡን አስጠብቆ
መውጣቱ እጅግ
አድካሚና የበሰለ
ታክቲክ የሚጠይቀው ነው፡፡ ያንን ለማድረግ የሚችለው
ደግሞ
አሥራ አንዱም ተጨዋቾች
‹ግቡ የአጥቂው፣ ድሉ የቡድኑ ነው› ብለው ሲሠሩ ብቻ
ነው፡፡ ግብ
አግቢው ድሉ የኔ ብቻ
ነው ብሎ ካሰበ ኳስ የሚያቀብለው አያገኝም፡፡
እኛ ‹ለውጡ የማን ነው?› እያልን ስንጨቃጨቅ ድል
ያደረግናቸው
ችግሮች መልሰው
እንዳይከቡንና ከፈንጠዝያው ሳንወርድ ወደ ሽንፈቱ
ቀለበት
እንዳይከቱን ‹መከራው የጋራችን
እንደነበረው ሁሉ፣ ድሉም የጋራ፣ የድሉ ፊታውራሪ
ጀግኖችም
የጋራ፣ የሚመጣውም ለውጥ
የጋራ› ብለን ማመን አለብን፡፡
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ
ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ
@haimonn @Gionamhara
አማራ ነኝ እንጅ!!!!!

(Senal De Dios)
((በጨለማው ወራት በድፍረት የዘመርነው መዝሙር) )


ከማረሻው ግርጌ፣ ከቀንበሩ ገመድ፣
ከበሮቼ ጋራ፣
ከጥቁር አፈር ጋር፣
አብሬ እምወጣ፣ አብሬ የምወርድ፣
አንበሳን ታግዬ፣
እንደ ፈረስ ወገብ፣ ቼ ብዬ የማለምድ፣
ሰማዩን አምኜ፣
ስለት የማስገባ፣ ለታቦቴ እምሰግድ፣
አማን አርገኝ ብዬ፣
ከዛውያው ምንጣፍ፤ ለጀማው የማረግድ፣
ምጣድ ያመሰውን፣
ጭስ ያበተለውን፤
የጋመ ባቄላ፣
የተንጣጣ ሰሊጥ፤
እንክክ እንክክ ብዬ፣ እጄ ላይ የማበርድ፣
አማራ ነኝ እንጅ፣
መንገድ ሰፋኝ ብዬ ፣
መንገድ ከገባ ጋር፣ ተነስቼ እማልነጉድ።
አማራ ነኝ እንጅ፣
መሬቱን አምኜ፣
አማን ኢማን ብዬ፣
ባንተው ይሁን ብዬ፣
ባንተው መጀን ብዬ፣አይኔን የማቀና፣
የጎረቤት ማጀት፣
ለምን ሞላ ብዬ፣ በሰው የማልቀና፣
ከወንድሞቼ ጋር፣
ከዘመዶቼ ጋር፣
በሌማት የምጎርስ፣ ንጣይዋን እንጀራ።
አምላክ የሰጠኝን፤
የኛ ብለው ወስደው፤
የተውቱን ደፍተው፤ ጦሜን እያዋሉ፤
ሰባራ ገል ጥደው፤
ይነዘንዙኛል፤
ብንሰጠው ደፋው፤ ጠግቦ ነው እያሉ።
ግን እንዲህም ሆኖ፤
በሽራፊ ምጣድ፤
በሰባራ ገል ላይ፤
እርጥብ ከደረቁ፤
እየቆሰቆስኩኝ፤
የተነኮረውን ወዲያ እያሽቀነጠርኩ፤
ሳሰፋ የምውል፤ ያገሩን እንጀራ፤
በስባሪ ምጣድ፤
ሙሉ ዳቦ ሰሪው፤
እኔ ነኝ እኔ ነኝ ፤
እኔ ነኝ ነፍጠኛው ፤እኔ ነኝ አማራ።
አማራ ነኝ እንጅ፣
አባይ ባጠገቤ፣ አቅፎ የሚስመኝ፣
ጣና በትንፋሹ፣ ባይኑ የሚጠቅሰኝ፣
ጎተራ እንደሁ እንጅ፣
ለወንድሞቼ ራብ፣ ማዴ የማያንሰኝ።
ልጄን በወገቤ በአንቀልባዬ አዝዬ፣
በአገልግል በሰንሰል፣
የሻገተ እንጀራ፣ ጣቢታ አንጠልጥዬ፣
ጎጆዬን ያቀናሁ፣
ቀን ከቀበሮ ጋር፣
ማታ ከጅብ መንጋ፣ ከድብ ጋር ታግዬ።
መታመን የሚሉት፣
መዋደድ የሚሉት፣
የጥቁር አፈር ቃል፣ ልቤ ላይ ተሰርቶ፣
በወንድሞቼ ላይ፣
የተጣደው በደል፣
የሚያብረከርከኝ፣
የሚያብሰከስከኝ፣ ጉልበቴ ስር ገብቶ።
አንበሳ ከጅብ ጋር፣
እኔ እበላ እበላ፣ በሆድ ሲታገሉ፣
አሞራና ውሻ፣
እኔ እግጥ እኔ እግጥ፣
እየበጣጠሱ፣ እየዘለዘሉ፣
በአጥንት ተናጭተው፣ በስጋ ሲጣሉ፣
አንተም ስጥ፣
አንተም ስጥ ፣
ብየ የማስታርቅ ፍቅር የሚርበኝ፣
እኔ ነኝ አማራ፣
እንኳንስ ወንድሜ፣
አራዊት ጫካውን፣
ድካውን ሲነጥቁት፣ የሚያንገበግበኝ።
አኔማ አማራ ነኝ፣
ሰማይ ከዳ ብዬ፣
ምድር ጦፈች ብዬ፣
የከሳው በሬዬን፣ አርጀ እማልበላ፣
ነገ አለልኝ ብዬ፣
የዘር ጃምዮየን፣
ላንዲት ርሃብ ብዬ፣ በእሳት የማልቆላ፣
በቂጣ የማልሽር፣
የአባቶቼን ግዝት፣የአባቶቼን ማላ።
አዎን አማራ ነኝ፣
ስሜ የጠገበ፣
ማርና ነጭ ጤፍ፣ ጮማና ብርንዶ፣
ባልበላም በልተሃል፣
ባልተኩስ ገድልሃል፣
ተብዬ እምጠራ፣
ተብዬ እምፈለግ፣ ፍርደኛ አጋሚዶ፣
አቤት ባይ ባተሌ፣
በሸንጎ በቀዬው፣ ስሜ ፍርድ ለምዶ።
አማራ ነኝ እኔ፣
ደብረ ግሸን ከርቤ፣
ረጅም መቋሚያ፣
እጀን ተደግፌ ታቅፌ እምወጣ፣
እንኳን የገዛ እጄን፣
አሳልመኝ ያለኝን፣
አይዞህ እያልኩኝ፣ ደግፌ እማመጣ።
አማራ ነኝ ጓዴ፣
ከጥማድ እርሻዬ፣
አምላክ የሰጠኝን፣
ጥንቅሽና ውልቢኝ፣
አሻግሬ እያየሁ፣ ማማ ተቀምጬ
አላፊ አግዳሚውን፣
ቅመሱልኝ የምል፣ ከእርሻዬ ቆርጬ።
አማራ ነኝ አዎ፣
በደረቅ ባቄላ፣በእንኩሮ መቀጣ፣
ጣዬ ሲበዛብኝ፣
ገብስ ቆሎዬ ላይ፣
ጉሮሮየን ላረጥብ፣ጠላ የምጠጣ፣
ባልበላሁት ዝልዝል፣
ባልጠጣሁት ማር ጠጅ፣ ሰክሬ እምወጣ።
በኩርማን እንጀራ፣
በድሪቶ ጋቢ፣
በእራፊ መቀነት፣ አንጀቴ ተሳስራ፣
በልቶብናል አሉኝ፣
የወንዙን እንጎቻ፣ ያገሩን እንጀራ።
ምነው ሆዴን ባዩት፣
ምነው ጎተራዬን፣ባዩት ወንድሞቼ፣
ይገባቸው ነበር፣
እነሱን ያቀናሁ፣
እነሱን ያጠገብኩ፣እኔ ተራቁቼ።
ከቶ ምን በድዬ፣ምን አድርጌያቸው ነው፣
ኧረ መጥተው ይዩኝ፣
እህል የጓሸበት፣
ወንድም የተራበ፣ ሆዴ እኮ ባዶ ነው።
ውሃ ጠማኝ ብዬ፣
ሃሩር በላኝ ብዬ፣ ከመንገዴ አልወጣ፣
እኔ አይደለሁም ወይ፣
እፍኝ ውሃ ጠምቶኝ፣
ለእኒያ ወንድሞቼ፣ ባህር የማጠጣ።
በጭብጨባ ብዛት፣
በምርቃት ግሳት፣
ሞቅ ሞቅ አይለኝ፣ወደላይ አልወጣ፣
በእርግማን ውርጅብኝ፣
በስድብ ነበልባል፣
ተሰደብኩኝ ብዬ፣ ወደ ታች አልመጣ።
ከላይ ነኝ አላልኩህ፣
ከታች ነኝ አላልኩሽ፣ አለሁ በእኩሌታ፣
ማነው የሚሰፍረኝ፣
ማነው የሚያጉድለኝ፣
ከባንዲራው ቀለም፣ ከባቶቼ ቦታ።
አዎን አማራ ነኝ፣
ጦቢያ የምትባል፣
የነፃነት ሰንደቅ፣
ያኔ ስትበጃጅ፣ ያኔ ስትሰራ፣
አንድ ላይ ሲማገር፣ የቤቷ ወጋግራ፣
እኔ አይደለሁም ወይ፣
ውሃ ልኳን ያቆምኩ፣ ወንድሞቼ ጋራ፣
እንዴት እጎድላለሁ፣
ካስቀመጡኝ መንበር፣ ካስቀመጡኝ ስፍራ።
አዎን አማራ ነኝ፣
የፈረሰ ማገር፣
የፈዘዘ ወራጅ፣
የዛለ ምሰሶ፣
እንደገና እንስራ፣
እንትከል እያልኩኝ፣
የደለቅኩት ድቤ፣
ከተሰማ ባገር፣
ከሞቀ በዃላ፣
በጅጌ በደቦ፣ በቀየው ታውጆ፣
አዳ ምን ዋጋ አለው፣
ሁሉም ሳር ይመዛል፣
ያድርበት ይመስል፣
በገፈፈ ክዳን፣ በዘመመ ጎጆ።
እረ እኔ አማራ ነኝ፣
የቦዘኔ ቃሪያ፣
የጤፍ ዱቄት ቂጣ፣
የሳማ ነጭ ወጥ፣"
የማሽላ ቆሎ፣
እንጀራ ነው ብዬ፣
እየገረገረኝ ቆርሸ፣ እምበላ፣
ጮማ ነው እያሉኝ፣
ቅቤ ነው እያሉኝ፣
ማጀቴን ያላዩ፣ ሰምቶ አዳሪ ሁላ።
ይህንን ስሰማ፤
በምን ይችል ጥርሴ፤ሳቄ ይመጣኛል፤
ሰው በሽተኛ ነው፤
ላም እየገደለ፤ ቅቤ እንዴት ይመኛል።
አዎን አማራ ነኝ፣
አሳድረኝ ብሎ፣
ቁራሽ ስጠኝ ብሎ፣ከመጣ ከኔ ቤት
አልጋዬን የምለቅ፣
ቁልፍልፍ ብዬ፣
መደብ እምተኛ፣ በታበሰ ማጀት፣
ጦሜን የምተኛ፣
በባዶ ማድጋ፣ በተቋጠረ አንጀት።
ታዲያ እኔ ነኝ ባዳ??
እኔ ነኝ ባይተዋር???
በወንድሞቼ ደጅ፣
ሚዛን ያጎደለኝ፣ ለአይናቸው ቀልዬ፣
በአባቶቼ ማጀት፣
ሰርክ የምገፈተር፣
ና ውረድ ና ግባ፣ ና ውጣ ተብዬ።
የአባቶቹን ሃገር፣
የአርበኞቸን ርስት፣
ያንተ ቤት አይደለም፣
እያሉ ዘበቱ፣
በሽሙጥ አይናቸው፣ አባረሩኝ በቃ፣
ባዶ እጄን ሰደዱኝ፣
ያለ ስንጥር አፈር፣ ያላንዲት ጦሪቃ፣
ገፈተሩኝ ጓዴ፣
ሰው አላየም ብለው፣
በጠቆረው ሰማይ፣ ሌት በጠፍ ጨረቃ።
ዳቦ እንጋግር ብለው፤
ወንድሞቼ ሁሉ፤
እፍኝ ዱቄት ይዘው፤
ባንድ ገበቴ ላይ፤
አቡክተን ሸላልመን ጋግረን ባንዲት እቃ፤
የኔ የኔ ባዩ፤
ስስት ሊገለው ነው፤ በልተን ሳናበቃ።
የኛ በሚል ፊደል፤
የኛ በሚል ደም ላይ፤
የኛ በሚል ገድል፤
ሰማይና ምድሯ፤ በተሰራች ሃገር፤
ያባትህን አጥንት፤
ወዲህ ነው እያሉ፤
ወዲያ ነው እያሉ፤ በቁጭት መማገር፤
እየዘመዘሙ እየጎነጎኑ፤ በሞተ ትዝታ፤
በጦቢያ ሰማይ ላይ፤
የኔ ማለት እብደት፤
በጠበል በዱኣ፤ የማይሽር በሽታ።
አማራነት ደም ነው፤
አማራነት መንፈስ፤
በእምነት የታጠረ፤ ባፅም የተዘራ፤
አፈሩን ቢጭሩት፤
እንደጉዳይ ቅጠል፤

ከጥቁር አፈር ስር፤ ከባንዲራው ጋራ።
ይስሙ ንገሯቸው፣
ከነ ሻሾ በረት፣
ከነ ላሎ ማጀት፣
ሺ ጊዜ ቢታለብ፣ ማለቢያው ቢሞላ፣
ለስሙ ነው እንጅ፣
ፈርዶብኝ ነው እንጅ፣
በአዋዜ አይደለም ወይ፣
በእሬት አይደለም ወይ፣
ከወንድሞቼ ጋር፣ ፈትፍቼ እምበላ።
አዎን፣
ከባዶ ሌማት ላይ፣
ከዱባ መረቅ ላይ፣
ዘመን የሚሻገር፣
እንቅብ የሚሞላ፣
ጣቢታ እየጋገርኩ፣ ተአምር የምሰራ፣
በኢትዮጲያዊነት ቀስተደመና ላይ፤
በተሳለው ቀለም፤
ለሁሉም የሚሆን፤
ዘመን አሻጋሪ፤
ቀለም እያበዛሁ፤ህብር የምሰራ፤
ልጄን ያቃመስኩት፤
ሃገር የጋገረው፤የዋጀራ እንጀራ፤
ማተቤ የፀናው፤
ቃሌ የታተመው፤ ከባንዲራው ጋራ፤
እኔ ነኝ ሸማኔው፤
እኔ ነኝ ባንዲራው፣
እኔ ነኝ ሰንደቁ ፣
እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ አማራ።
@Gionamhara
#update በአብደራፊ ከተማ ዛሬ ሁለት ወጣቶች በጥይት
መቁሰላቸው ተነገረ
በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በቀን የግብርና ስራ
የተሰማሩ በአብደራፊ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶች በአዲስ
አለም የሚገኘውን በባነር የተሰራ የመለስ ዜናዊን ፎቶ
ቀዳደው መጣላቸውን ተከትሎ በተተኮሰ ጥይት ሁለት
ወጣቶች ቆስለው ወደ ጎንደር ሆስፒታል ሪፈር መባላቸው
ታውቋል።
ዛሬ መስከረም 3 ቀን 2011 ዓ•ም ከማለዳው 3 ስዓት
ጀምሮ በከንቲባ ጽ/ቤት አዳራሽ የተሰበሰቡ ከ1 ሽህ
በላይ የሚሆኑ ወጣቶች እስከ 8 ስዓት በከንቲባ
የአስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ አመራሮች የተወያዩ ሲሆን
በውይይታቸውም "ገጀራ፣ቦንብና ጥይት እያደሉ እርስ
በርስ እንድንጨፋጨፍ እያደረጉ ያሉ የህወሐትን ተልዕኮ
እየተወጡ ያሉት አቶ ስዩም ወዳቦ() እና ነጋሲ የሳሚ
ወንድም ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
በተለይ በሀምሌ 2010 ዓ•ም አያሌ የቀን ሰራተኞች
ከካንባቸው እርስ በርስ እንዲገዳደሉ አድርገዋል ከተባሉት
መካከል አቶ ሳሚና ነጋሲ ከአካባቢው መሰወራቸው
ይታወቃል።
በሁኔታው የተበሳጩት ወጣቶች ስብሰባውን አፍርሰው ወደ
አብደራፊ ቀበሌ 02 አዲስ አለም በመሄድ "መለስ ለእኛ
ክፉ እንጅ ጥሩ ሰሪ አይደለም"በማለት የመለስ ፎቶ
የተሰቀለበትን ብረት በመንቀል ባነሩን ቀዳደው መጣላቸው
ተሰምቷል።
ከሰሞኑ የአብደራፊ 01 ቀበሌ ነዋሪዎች መስቀል
አደባባይ አካባቢ የእነ ዶ/ር አብይ አህመድ፣የእነ ደመቀ
መኮንን ፣ለማ መገርሳና ገዱ አንዳርጋቸው ፎቶን በባነር
አሰርተው መስቀላቸው የፈጠረው ስሜት እንዳለውም
ተገልጧል።
ብዙ ጥይት ወደ ላይ ሲተኮስ እንደነበርና በመጨረሻም
ከትግሬዎች በተተኮሰ ጥይት ሁለት ወጣቶች ቆስለው ወደ
ጎንደር ሆስፒታል ሪፈር መላካቸውን ምንጮች ከስፍራው
ገልፀዋል።
አንደኛው እጁን ሌላኛው ደግሞ ደረቱን መመታቱ
ተነግሯል።መከላከያና የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ ገብተው
ሁኔታውን እያረጋጉት መሆናቸው ታውቋል።
አባይ ዘውዱ
@haimonn @gionamhara
# ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ
ግንቦት ዜሮ መስከረም አምስት በባህርዳር ከተማ
ሰልፍ እንደጠራና የድርጂቱ መሪ ብርሀኑ ነጋ
እንደሚገኝ ታውቋል። ሆኖም እዳይመጡ ከመከልከል
ይልቅ በህገ-መንግስቱ መሰረት ተቃውሞአችንን
እንድናሰማ ከአማራ ሙህሮች ጥሪ ቀርቧል። እነዚህ
የስድሳወቹ የፖለቲካ ቁማርተኞች በአማራ ሰመዓታት
ደም እንዲቀልዱ አንፈቅድላቸውም። መላው
የባህርዳር አማሮች በነቂስ ወጥተን አሳፍረን
መመለስ ይኖርብናል።
አማራ-ታሪኩን-ያድሳል ድል ለአማራ
@Haimonn @Gionamhara
የብአዴን ምክክር ስለ አብን
ብአዴን ከዞን አማራሮች ጋር!ስለ # አብን መክሯል።
"27 አመት እንደ ኤሌ ስናዘግም #አብን በ3ወር ውስጥ
የክልሉን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን ህዝብ
ቀሚያስገርም ፍጥነት ጥሎን ተራምዷል።አብን የብአዴንን
ደካማነት ለኢትዮጵያ ህዝብ ያሳየ ድርጅት ነው።እኛ እንደ
አብን ለመፍጠን ብንሞክር አንችልም።አብን ውስጥ ያለው
ሀይል!በትልቅ ሞራል የተገነባ ወጣት ያለበት ትኩስ ሀይል
ነው። ብአዴን ውስጥ!አብን ውስጥ እንዳሉ አይነት
ልጆችን ለማግኘት 27አመት ይፈጅበታል።"
"ከብአዴን አመራሮች ውስጥ!ወደ አብን ለመቀላቀል
ያደፈጡ ቡድኖችም አሉ።ድርጅታችን ብአዴን እንደ አብን
መሆን ባይችል እንኳ!አብን የሚከተለውን መርህ ሙሉ
ለሙሉ ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ተቀብሎ እንቅስቃሴ
ካልጀመረ!ብአዴን ታሪክ ሆኖ ይቀራል።
ስለዚህ ብአዴን ውስጥ ያለን አመራሮች!በአመለካከት እና
በእውቀት ራሳችንን በመገንባት ህዝብ ፊት መቅረብ
የሚችል አመራር ማሰባሰብ መቻል አለብን።
አብን ውስጥ ያሉ አባሎች!ብአዴን ውስጥ ካሉ አመራሮች
የተሻለ እውቀትና ህዝባዊ ተቀባይነት አላቸው።
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ብአዴን ከአብን አመራሮች
ጋር ፊት ለፊት ቀርቦ መከራከር የሚችል አቅም ያለው
የብአዴን አመራር አለው ለማለት አያስደፍርም።አብን
ውስጥ አባሎቹ ሳይቀሩ የብአዴንን አመራሮቹ መዘረር
የሚችሉ ወጣቶች አሉበት።ስለዚህ ራሳችንን ተወዳዳሪ
ለመሆን ብቻ ሳይሆን ለአሸናፊነት የሚያበቃን ፖለቲካዊ
አቋምና እውቀት መገንባት ግዴታችን ነው።ይህን
ካላደረግን ክልሉን መሉ ለሙሉ ለመረከብ የቆመ ትልቅ
ሀይል ከፊታችን አለ።
ይህ ሲባል ግን! # አብንን የጎሪጥ እንድታዩት
አይደለም።ከዚህ ውስጥ የብአዴን አመራር ሆናችሁ:አብን
ውስጥ የሚሰራ ጓደኛችሁ/ወንድማችሁ ሊኖር
ይችላል።ስለዚህ ከወንድሞቻችሁ ጋር የምትጋሩት ሀሳብ
እንጅ!የሚያጣላችሁና የጎሪጥ እንድትተያዩ የሚያደርጋችሁ
ምክንያት መኖር የለበትም።"
"አብንም:ብአዴንም ለክልሉ ህዝብ መብትና ጥቅም ነው
የምንሰራው:የምንሄድበት መንገድ ሊለያይ
ይችላል:መድረሻችን ግን አንድ ነው።አብንን መምከር
የሚችል አቅም ያለው አመራር ብአዴን ውስጥ
ካለ:ድርጅቱ እንዲመክረውና አቅጣጫ እንዲያሳየው
ያበረታታል።ብአዴንም ከአብን ምክርና የተሻለ ሀሳብ
እንዲሁም:ለህዝብ ጥቅም መከበር የተሻለ መንገድ ነው
ብሎ የሚያስበው ሁሉ ይቀበላል።"
# ሰማያዊ_ይግዛው
@haimonn @Gionamhara
Miky Amhara
በሳዳም ሁሴን ወይም በሱኒ ማይኖሪቲ ይመራ የነበረዉ
የኢራቅ አስተዳደር በአሜሪካ እርዳታ ከተወገደ በኋላ
ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ የኢራቅ ዲያስፖራ ወደ ሀገር
በመመለስ የፖለቲካ ተሳትፎ ማድረግ ጀመረ፡፡ የተለያዩ
ተቃዋሚ መሪዎች፤ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ወደ ኢራቅ
በመመለስ ቀስ በቀስ ስልጣን ያዙ፡፡ አሜሪካኖች እኒህን
ዲያስፖራዎች መጀመሪያ በሃገሪቱ በፖለቲካዊ እና
ኢኮኖሚያዊ ዙሮያወች ላይ አማካሪ ሆነዉ እንዲቆዩ
ብታድርግም ቀስ በቀስ ግን ከዉጭ አገር የመጡት ሰወች
ባብዛኛዉ ሺአወች እና ኩርዶች የፖለቲካ ስልጣኑን
ተቆናጠጡት፡፡ ስልጣን መያዝ ብቻ ሳይሆን እነዚህ
ስልጣን የያዙ ዲያስፖራዎች በአሜሪካ እና አዉሮፓ
ያሉትን ዘመዶች በሙሉ እየጠሩ ስልጣን ሰጧቸዉ፡፡ አንድ
አንድ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በቤተሰብ ብቻ የተያዙ
ነበሩ፡፡ ከትቂት ጊዜ በኋላ በተካሄደዉ ምርጫም ኢራቅ
የመጀመሪያዉ አንግሊዛዊ-ኢራቃዊ (ዲያስፖራ) Jaafari
የተባለ ሰዉ ጠቅላይ ሚኒስቴር አድርጋ መረጠች፡፡
ባጠቃላይ 30 አመት በላይ በጭቆና ሲማቅቅ የነበዉ
ህዝብ እና ወጣት ተረስቶ ይህ የዲያስፖራ ቡድን ተቧድኖ
ፖለቲካዉንም ኢኮኖሚዉንም ተቆጣጠረዉ፡፡ የሚሾሙት
ሰወች በብቃት ሳይሆን ባጠቃላይ በጓደኝነት እና በዘምድ
አዝማድ ሆነ፡፡ወዲያዉም በዲያስፖራዉ ቡድን እና
በሀገሬዉ ኢራቃዊ መካከል ከፍተኛ መቃቃር ተፈጠረ፡፡
ወጣቱ በብዛት ስራ አጥ ሆነ፡፡ ሌብነት እና ስርቆት
ተበራከተ፡፡ አሜሪካኖች ኢራቅን ለመልሶ መገንባት ብለዉ
የመደቡት ወደ 100 ቢሊየን ዶላር በላይ ተዘረፈ፡፡
በመንግስት ስር የነበሩ ድርጅቶች ፕራይቬታይዝ በማድረግ
ዲያስፓራዉ እና የአሜሪካ ካምፓኒዎች ተቀራመቷቸዉ፡፡
እኒህ ድርጅቶች ወዲያዉ በመቶሽህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን
ከስራ ገበታ አሰናበቱ፡፡ ብዙም ሳይቆይ የኢራቅ ወጣት
ይሄን የዲያስፖራ መንግስት አይንህን ላፈር አሉት፡፡
እንደገና አመጽ ተነሳ፡፡ከዛን ጊዜ ጀምሮ ኢራቅ ከአራት
በላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቀያይራለች፡፡ ዲሞከራሲ
እናስፍናለን ብለዉ የመጡት ዲያስፖራወች ህዘቡን
አማራዉ እና ዘርፈዉ ጭራሽ ወጣቱ አይ ኤስ አይ ኤስ
እና ሌሎች ቡድኖችን በመቀላቀል ኢራቅን የባሰ
አወደማት፡፡
የኛ ሀገርም አዝማሚያዉ ወደ እዚህ የሚሄድ ይመስላል፡፡
ልክ እንደ ኢራቅ ሽአዋች የኦሮሞ ኢሊቶች እኛ ተጎድተናል
ጊዜዉ የኛ ነዉ መግዛት ያለብን እኛ ነን ይላሉ፡፡ አጠቃላይ
ከ 30 አመት በላይ ዉጭ ሀገር የኖረ ዲያስፖራም መሬት
ላይ ያለዉን ህዝብ እኔ ነኝ ማዉቅልህ፤ አንተ አትደራጅ፤
ይህ ፖሊሲ ያዋጣል አይነት አካሄድ እየሄዱ ነዉ፡፡
እንዲያዉም ከድህረ ህዋሀት በኋላ ሀገሪቱን ለ 40
አመታት አይተዋት የማያዉቁ ሰወች ሁሉ የኢኮኖሚ እና
የፖለቲካ አማካሪ እየሆኑ ያሉበት ሁኔታ ነዉ ያለዉ፡፡ ቀስ
በቀስ ደግሞ ሚኒስቴር ይሆናሉ፡፡ ይህ አደገኛ እና 30
አመት ሲሰቃይ የነበረዉን ወጣት ወደ ጎን ያገለለ አካሄድ
መጨረሻዉ ላያምር ይችላል፡፡
ባጠቃላይ አሁን ከዉጭ ሀገር እየገቡ ያሉ ሰወች
የሀገሪቱን የፖለቲካ ፍላጎት የተረዱ የወጣቱን ፍላጎት
የተረዱ ሳይሆን ከፍተኛ የሆነ የስልጣን ጥም ያለባቸዉ፤
መታወቅን ብቻ የሚፈልጉ፤ እንጅ ወጣቱን አሳትፎ አገር
ለመገንባት የሚሆኑ አይመስለኝም፡፡ ልክ የኢራቅ
ዲያስፖራወች ለሀገሪቱ ሌላ ጣጣ ይዘዉ እንደመጡበት
የእኛ በዲያስፖራዉ ለብዙ አመታት የቆዩ ሽማግሌወችም
ጣጣ ይዘዉ እየመጡ ነዉ፡፡ ህዝቡን የበሰለ ፖለቲካ
እንዲያካሂድ ከማድረግ ይልቅ በስሜት የተሞላ እና
የባንዴራ ፖለቲካ ብቻ እየሆነ ነዉ፡፡ በአጉል ስሜታዊ
ፕሮፖጋንዳ ህዝቡም የበሰለ እና የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና
ፖለቲካዊ ችግሮች ላይ እንዳያተኩር አድርጎታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይም እኒህን ሽማግሌወች
appeal ከመዳርግ ይልቅ ወደ ወጣቱ መዞር እና ወጣቱን
ተሳታፊ እንዲሆን ቢያደርግ የተሻለ ሀገራዊ መግባባት ላይ
መድረስ ይቻላል፡፡ የመንግስታዊ አስተዳደሩን ለተማሩ እና
ጥሩ የመሪነት ሚና ላላቸዉ ወጣቶች ከፍት በማድረግ
የተሻለ ለዉጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ ከዛም በላይ ወጣቱ
በአይዲዮሎች የተለከፈ ስላልሆነ መሬት ላይ ባለዉ ችግር
ላይ አተኩሮ ስለሚሰራ የተሻለ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
ሽማግሌወቹ አንደኛ በአይዲዮሎጅ ጭንቅላታቸዉ የተዘጋ
እና ለመደራደር ዝግጁ ያልሆኑ ናቸዉ፡፡ ሁለተኛ መሬት
ላይ ያለዉን የወጣቱን ችግር የሚረዱ ሳይሆኑ ምናባዊ
በሆነ ትርክት እራሳቸዉን ቆፍድደዉ የያዙ ናቸዉ፡፡
ሌላዉ ማክሮ ኢኮኖሚዉ አቴንሽን እንደተሰጠዉ ሁሉ
ማይክሮ ኢኮኖሚዉ ላይ በስፋት መስራት ያስፈልጋል፡፡
በጤና፤ በትምህርት፤ በሌሎች ማህበራዊ ዘርፎች እና
በስራ አጥነትን በመቀነስ፤ አንተረፕረነርሽፕ እና ኢኖቬሽን
በማበረታት በኩል ኢኮኖሚዉን ማንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡
በክልሎች መካከል ያለዉ የድንበር ሁኔታ፤ የማንነት
ጥያቀቄወች እና የፍትሃዊ ሃብት ክፍፍል በቶሎ መስመር
መያዝ አለበት፡፡
በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ በኦነግ በኩል
ያለዉን ጫና ሳይፈራ በራሱ ቪዥን ሀገሪቱን መምራት
መቻል አለበት፡፡ አሁን ላይ የምናየዉ እኛ ነዉ ለዉጡን
ያመጣነዉ እና እኛ እንደፈለግን እንሆናለን የሚለዉን
መቀበል የለበትም፡፡ አንዳንድ ሰወች ራሳቸዉን የሀገር መሪ
አድርጎ መቁጠር የጀመሩ ይመስላል፡፡ ይህ የጠቅላይ
ሚኒስቴሩን legitimacy undermine ያደርጋል፡፡
ህዋሀትም አሁን ድረስ በሀገሪቱ ስተራክቸር ዉስጥ
ያለዉን human resource and money በመጠቀም
ትንንሽ ግጭቶችን ሲያሰፋ እና ሲያበረታታ ይታያል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ nation reconstruction ላይ
እንዲያተኩር ሳይሆን እኒህን ግጭቶች ላይ እንዲያተኩር
በማድረግ micro manager ሆኖ እንዲቀጥል ነዉ
ፍላጎታቸዉ፡፡ ስለዚህም ወሳኝ የሚባሉ የመንግስት
ተቋማት (ወታደሩ፤ ደህንነቱ፤ ቴሌ) የ deTPLFication
ስራ ያስፈልገዋል፡፡The Oromo elites wanted to
make the PM as a shadow prime minister,
and the Tigray elites wanted to make him a
micromanager. ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ከዚህ አጣብቂኝ
ወቶ በራሱ ራእይ መምራት ካልጀመረ አዝማሚያዉ ጥሩ
አይሆንም።
@haimonn @gionamhara
አሁን ላይ ብዙ የተኙ አማራ ወገኖች አሉን።ኢትየጲያ ኢትዮጲያ ያለው ሁሉ ለአማራ የቆመ ይመስለዋል።ኢትዮጲያ ለአማራ የተሰጠች የአደራ እቃ አይደለችም ለአማራ የማትሆን ኢትዮጲያ ገደል ልትገባ ትችላለች።አሁን ላይ አለ የሚሉት አንድነት ቅብ እንጅ እውነትነት እንደሌለው ልነግራችሁ እወዳለሁ ።አሁንም ድረስ የአማራ መገደል እና መፈናቀል እንደቀጠለ ነው።ትናንት ቤንሻንጉል ላይ የሆነውን ማየት፣አዲስ አበባ ላይ የሚኒሊክን ሀዉልት እናፈርሳለን የሚሉትን ማየት አማራ ይበቃው ነበር ነገር ግን አሁንም ተኝተናል።ከሰሞኑ አንድ አንድ ሰዎች ጋር ሳወራ ነበር የአማራ ብሄርተኝነት ገና በሁለት እግሩ እንዳልቆመ ተረድቻለሁ።አሁንም መካከላችን ሁነው የአማራ ብሄርተኝነት አማራን ለመገንጠል የተነሳ ሀይል አስመስለው የሚነዙ የከሰሩ አንድነት ሰባኪዎች አማራውን በኢትዮጲያ ስም የስልጣን መጠቀሚያ ሊያደርጉት አሰፍስፈው ይገኛሉ።እንንቃ አሁንም የአማራ potential ስጋቶች እስካልተወገዱ ድረስ አሁንም ብሄርተኝነታችን ብቸኛው መዳኛ መንገዳችን ነው።
©ሳሙኤል አበበ
@samibdr @gionamhara
#የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አመራሮች እና አባላት በባሕር ዳር ከተማ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው፡፡

አሁን ላይ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም የባሕር ዳር ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት አቀባበል እየተደረገላቸው ነው፡፡
@Haimonn @Gionamhara
#በአማራ ክልል አፈ ጉባኤ ወሮ.ወርቅሰሙ ማሞ የሚመራው ልዑክ ዛሬ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝቷል፡፡

በቆይታቸውም ሁለቱ ሀገራት የጀመሩትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የአማራ ክልል የተወሰነ ርቀት እንደተጓዘ ገልጾ፤ምክር ቤቱ ያለውን ልምድ እንደሚያካፍልም ተናግሯል፡፡
ምክር ቤቱ ሁለቱ ሀገራት የጀመሩትን ግንኙነት አድንቋል፡፡

የተጀመረውን ግንኙነት ለማጠናከርም ሁለቱም አካላት በጋራ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል፡፡
የአማራ ክልል ምክር ቤት ልዑካን ቡድን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ስጦታም አበርክቷል፡፡

በምክር ቤት አፈ ጉባዔ የሚመራ የሃይማኖት አባቶችን ያካተተ ልዑክ ወደ ኤርትራ የሚያቀናው የሁለቱን አገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና ትስስርን ለማጠናከር ነው፡፡
©Amma
@Haimonn @Gionamhara
በጠላታችን ዓጋሜዎች አቀነባባሪነት በመተከል የተገደሉ
ወገኖቻችን ደም ፈሶ አይቀርም አማራ ተደራጅና መመከት ጀምር!!
@samibdr @gionamhara
አማራ እባክህ በርህ ላይ መጠው እስኪገድሉህ አትጠብቅ።መደራጀት ያለህ ብቸኛ አማራጭ ነው።አንድነት የምትሉን ሁሉ እሄን እያየሁ ከናንተ የውሸት አንድነት ሞት ይሻለኛል።
@samibdr @gionamhara