Ghion Maleda
26K subscribers
2.74K photos
521 videos
38 files
795 links
እንኳን ደህና መጡ !

ማስታወቂያ ለማሰራት 👉 @GhionMaleda13

ቴሌግራም ቻናሉን ለመቀላቀል👉@GhionMaleda

ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/GhionMaleda

ደግና ቅን እንሁን ❤🙏
Download Telegram
❤6👎4🥱3
Ghion Maleda
Photo
ከ400 በላይ የወሲብ ቪዲዮዎቿ ከኢንተርኔት እንዲወገዱ ጠየቀች! በእንባ የታጀበ ጥያቄ እና የእናትነት ስጋት

ከላይ በምስሉ የምታያት የቀድሞዋ የወሲብ ፊልም ተዋናይ ላና ሮአድስ (Lana Rhoades) ከቀድሞ ህይወቷ ጋር የተያያዙ ከ400 በላይ ቪዲዮዎች ከኢንተርኔት በቋሚነት እንዲወገዱ በመጠየቅ ትኩረት ስቧለች።

በቀድሞ ህይወቷ የሰራችው ስራ ዛሬም በኢንተርኔት ላይ መቀጠሉ እና የግል ታሪኳ በዚህ መልኩ መታየቱ እንዳሳሰባት ተነግሯል።

አሁን እናት የሆነችው ላና፣ በተለይ ልጇ እያደገ ሲሄድ የቀድሞ ህይወቷን የሚያሳዩ ይዘቶች በኢንተርኔት ላይ መኖራቸው እንደሚያሳስባት ገልጻለች።

የምታቀርበው ጥያቄም ከዚህ ስጋት ጋር የተያያዘ ነው። ልጇ አንድ ቀን የእናቱን የቀድሞ ህይወት በኢንተርኔት ላይ አግኝቶ እንዳይጎዳ እና በቤተሰቡ ላይ የማይፈለግ ተጽእኖ እንዳይፈጠር መፈለጓን አስታውቃለች።

እንደ ላና ጥያቄ፣ በወጣትነት ዘመን የሚደረጉ ውሳኔዎች ከዓመታት በኋላ በሌላ መልኩ ሊመለሱ እንደሚችሉ የሚያሳይ ነው።

ዛሬ በዲጂታል ዓለም ውስጥ አንድ ይዘት ከተለቀቀ በኋላ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ቀላል አይደለም። ይዘቶች በተለያዩ ድረ-ገጾች ሊቀመጡ፣ ሊተላለፉ እና ከመጀመሪያው ምንጭ ቢወገዱም በሌሎች ቦታዎች ሊቀጥሉ ይችላሉ።

ይህም የግል ህይወትን መጠበቅ እና በድረ-ገጾች ላይ የተለቀቀን ይዘት መቆጣጠር ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ያሳያል።

ላና ሮአድስ የምታቀርበው ጥያቄም ከዚህ በላይ የሆነ የግል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ በዲጂታል ዘመን የሰው ልጅ የግል ታሪኩን እንዴት መጠበቅ እንደሚችል የሚያነሳ ጥያቄ ነው።

የላና ታሪክ ለሁሉም የሚያስተላልፈው መልእክት፣ ዛሬ የምንወስነው ውሳኔ ነገ ምን ዓይነት ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል አስቀድሞ ማሰብ አለብን የሚል ነው።

በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምንለቃቸው ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች እና የግል መረጃዎች ከዓመታት በኋላ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ተጽእኖ በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል።

እንዲሁም የሰውን የቀድሞ ህይወት በመመልከት ሳይሆን፣ ዛሬ የሚያደርገውን ለውጥ እና የሚወስደውን ኃላፊነት ማክበር የሚገባ ነው።

Via፦ Abush Gebre
ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
❤27😢11👎4🥱4🕊1🫡1
❤35
Ghion Maleda
Photo
እንኳን ለጻድቁ አቡነ  አረጋዊ  አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤አደረሰን🙏

#የጻድቁ ረድኤት እና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን 🙏

ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት፡፡

አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ ናቸው፡፡ ዘጠኙ ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ሲሆን ተወልደው ያደጉት በአንድ የሮም ግዛት ሥር በተለያየ ቦታ ነው፡፡ አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን በሚገባ ያጠኑት እነዚህ አበው ሰማያዊውን ክብር መርጠው ክርስቲያኖች በሚሳደዱበት በ5ኛው ክፍለ ዘመን በቅድሚያ አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ከዚያም ሌሎቹ ከሮም ወደ ግብጽ በርሃዎች፣ በ470ዎቹ ዓ.ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ በአረጋዊ መሪነት ወደ ኢትዮጵያ በምናኔ መጥተዋል፡፡ 

ንጉሡም በመልካም ተቀብሎ በአክሱም ቤተ ቀጢን ማረፊያ ቦታ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም የግዕዝ ቋንቋ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ በአቡነ ሰላማ፣ በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለውንና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ የነበረውን ክርስትና እንደገና አቀጣጠሉት፤ ለዓመታትም ወንጌልን ሰበኩ በርካታ መጻሕፍትንም ተረጎሙ፡፡ በኋላም የየራሳቸው የምናኔ ቦታ በመምረጥ ወንጌልን እየሰበኩና ስለሀገራችን እየጸለዩ ኖረዋል፡፡

አባታችን አቡነ አረጋዊ በደብረ ዳሞ ታላቅ ገድል ፈጽመዋል፡፡ ማኅሌታዊው ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ፡፡ ጻድቁ ተጋድሏቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው ጥቅምት 14 ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል፡፡ ጌታም የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ጥር 14ም ጻድቁ የተወለዱበት ቀን ነው፡፡

መናንያንና ገዳማውያን የዓለምን ክብር ንቀው ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ የወንጌል ብርሃን እንዲበራ፣ ትልቅ ሥራ ሰርተዋል፡፡ ጸሎታቸው አሁንም ተአምር ያደርጋል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
❤30🙏11🥰3🤣2
Ghion Maleda
Photo
ሁለቱም የህፃኑ አባት ነኝ ያሉ ግለሰቦች በDNA አባት አለመሆናቸው ተረጋገጠ

በእግረኛው ሚዲያ በእግረኛው ሚዲያ የቀረበው የቪዲዮ ፕሮግራም አወዛጋቢ የሆነው ይቺው እናት ከብዙ ወንዶች ጋር ግንኙነት በማድረጓ የልጁ አባት እያወዛገበ ይገኛል።

አሁንም ቢሆንየልጅ አባትነት ጉዳይ ይዞ የቀረበ ሲሆን፣ የሁለት ግለሰቦች (ደሳለኝ አሰፋ እና አብዱልቃድር አደን) እና የህጻኑ ፊሮምሳ ዲኤንኤ ምርመራ ውጤት ይፋ ሆኗል።

ከላይ በቪዲዮጰእንደምታዩት በሁለቱ ተወዳዳሪ አባቶች፣ የልጁ እናት ሸኔ ጂን ፒተርስ እና ህጻኑ ፊሮምሳ በአካል በመገኘት በፌዴራል ፖሊስ ፎረንሲክ ምርመራ ቢሮ የተረጋገጠውን ውጤት በጉጉት ሲጠብቁ የቆዩበትን ሁኔታ ያሳያል።

በመጨረሻም በፌዴራል ፖሊስ ፎረንሲክ ምርመራ ምክትል ዋና መምሪያ የተሰጠው ኦፊሴላዊ የዲኤንኤ ምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው....

ከአቶ ደሳለኝ አሰፋ እና ከአቶ አብዱልቃድር አደን የተወሰደው ጄኔቲክ ከህጻን ፊሮምሳ ደሳለኝ ጋር ሲመሳከር የእነዚህ ሁለቱም ግለሰቦች የወላጅ አባት የመሆን እድላቸው ዜሮ በመቶ (0%) ሆኖ ተመዝግቧል።

ውጤቱ ሲታወቅ ሁለቱም ግለሰቦች የተሰማቸውን ሐዘንና መደንገጥ የገለጹ ሲሆን፣ እናቷ በበኩሏ የልጁን የማሳደግ ሀላፊነት በህግ አግባብ ለደሳለኝ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኗን ተናግራለች።

በእግረኛው ሚዲያ በተሰራው ዝግጅት መሰረት በሰፊው ሲጠበቅ የቆየው የህጻን ፊሮምሳ የዲኤንኤ ምርመራ ውጤት ይፋ ሆኗል።

በፌዴራል ፖሊስ ፎረንሲክ ምርመራ ቢሮ የተረጋገጠውና በወንድማገኝ ጸጋዬ (ምክትል ኮማንደር) የተፈረመው ኦፊሴላዊ ሰነድ እንደሚያረጋግጠው...

የልጁ አባትነት ጥያቄ አንስተው የነበሩት አቶ ደሳለኝ አሰፋ እና አቶ አብዱልቃድር አደን የህጻኑ ባዮሎጂካል ወላጅ አባቶች የመሆን እድላቸው ዜሮ በመቶ መሆኑ በይፋ ታውቋል።

ውጤቱ በቀረበበት ሰዓት ሁለቱም ግለሰቦች ከፍተኛ የስነልቦና ጫናና ሐዘን የገጠማቸው ሲሆን፣ አቶ ደሳለኝ አሰፋ ህጻኑ የራሱ ባይሆንም እንኳ እንደ አባት ሆኖ በህግ አግባብ ተረክቦ ለማሳደግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

የልጁ እናት ሸኔ ጂን ፒተርስም አባቶች አለመሆናቸው በመረጋገጡ ምክንያት ህጻኑን በህግ አግባብ ለደሳለኝ አሰፋ አሳልፎ ለመስጠት መስማማቷን ተናግራለች።

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
❤15😁9🥱5💔4👎2🤔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በፍቺ፣ በጸጸትና በይቅርታ ዙሪያ ያተኮረው ይህ አዲሱ የኮሜዲያን ያሲኖ ሥራ የብዙዎችን ልብ እየነካ ነው

"ብዙዎች ከአእምሮ በላይ ሆንክብን!" የሚለው አስተያየት በኮሜዲያን ያሲኖ ከላይ በምታኑት አዲስ የቪዲዮ ሥራ ዙሪያ የተሰማውን አድናቆት ያንጸባርቃል። በፍቺ ፣ በጸጸትና በይቅርታ ዙሪያ ያተኮረው ይህ ሥራ በርካቶችን እንዲያስቡና ስለ ሕይወት ግንኙነቶች እንዲወያዩ እያደረገ ነው።

የኮሜዲያን ያሲኖ አዲሱ ሥራ በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ስህተቶችን፣ የጸጸትን ስሜትና ይቅርታ የሚኖረውን ዋጋ ይዳስሳል። ከቀልድ ባሻገር ሰዎች ስለ ራሳቸው ውሳኔዎችና ስለ ሌሎች ሰዎች ስሜት እንዲያስቡ የሚጋብዝ መልዕክት ይዟል።

በተለይም ከስህተት መማር፣ ከልብ ይቅርታ መጠየቅና ለሰላም መትጋት የሚሉትን እሴቶች ያነሳል።

ባለትዳሮች ቢለያዩም እንኳን ለልጆቻቸው የወደፊት ሕይወትና ስነ-ልቦናዊ ደህንነት ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው የሚያስገነዝብ መልዕክትም አለው። አለመግባባት ቢኖርም መከባበርና መተሳሰብ እንደሚያስፈልግ ያስታውሳል።

ከከባድ ስሜታዊ ጉዳት በኋላም ሰው ራሱን አረጋግቶ ከቀድሞ ስህተቶቹ በመማር ወደፊት መጓዝ እንደሚችል የሚያሳየው ይህ ሥራ፣ ከተመልካቾች ዘንድ አድናቆት እያገኘ ነው። በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በፈጠራ ሥራዎቹ መልዕክት ለማስተላለፍ ለሚያደርገው ጥረትም አድናቆት ቀርቦለታል።

እናንተስ ምን ትላላችሁ?ይቅርታ የተሰበረን ግንኙነት እንደገና ሊገነባ ይችላል? ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪኪ

Via፦ ጉርሻ
ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
❤22👍20👏7💔6😭3🕊1
😭9❤5🤬3
Ghion Maleda
Photo
በ3 ዓመቷ ተስርቃ አይኗ እንዲጠፋ ተድርጋ እናቷ ሙታብኝ ነው በማለት በመላ ኢትዮጵያ የተለመነባት “ጉኒ” እስከ መምህር የደረሰችበት የህይወት ትግል

ይህቺ እህታችን ከጋዜጠኛ ቁምነገር አህመድ ያደረገችው ቆይታ እጅግ ልብ ሰባሪና አስተማሪ ብለን ግዮን ማለዳዎች ስለሰብን እንደሚከተለው ልናከፍላችሁ ወደድን።

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን መርጦ ለማርያም ከተማ አካባቢ ነፍሴ ሳር ምድር ወረዳ (መጥገና) በተባለች ውብ ስፍራ፣ ሕይወት ለቤተሰቦቿ ሰላማዊና ፍቅር የሞላባት ነበረች።

አባቷ "አያ ነብሮ" (እውነተኛ ስሙ ጫኔ/አያሌው ይባላል)፣ እናቷ "ሰሞኔ" እንዲሁም እህቷ "እጅጋየሁ" ከሚባሉ የቤተሰብ አባላት ጋር በጋራ ትኖር ነበር። በቤተሰቦቿ ዘንድ በፍቅር "ጉኒ" (የምታምር ትንሽ ጤፍ) እየተባለች ትጠራ ነበር።

ገና የ3 ዓመት ህፃን ሳለች ከእኩዮቿ ጋር በወንዝ ዳር ሾላ እየበላችና እየተጫወተች የነበረችው ይህቺ ንጹህ ሕፃን፣ የሰው ልጅ እስከዚህ ድረስ ጨካኝ ሊሆን ይችላል ብላ ያሰበችበት ቀን ግን የሕይወቷን አቅጣጫ ለወጠው።

በወንዝ ዳር እየተጫወተች ሳለች አካል ጉዳተኛ የሆነና እጁ የተቆረጠ "ክንዴ" የተባለ ግለሰብ በታላቅ ተንኮል "እታተየ አምጣት ብለውኝ ነው" ብሎ አታልሎ ወሰዳት። ህፃኗን ይዞ ወደ ጨለምተኛ ጫካ ከተሻገረ በኋላ፣ በሰብአዊነት ሊታሰብ የማይችል አሰቃቂ ወንጀል ፈጸመባት።

አይኗ ላይ የቅንጭብ (የቁልቋል) ወተት በመንጠባጠብ ሁለቱንም ዓይኖቿ በኬሚካል አቃጠላቸው፤ በሂደትም እይታዋ ሙሉ በሙሉ ጠፋ። ክንዴ የተባለው ግለሰብ ጉኒን ብቻውን አልያዘም፤ ህፃናትን ከየቦታው እየሰረቀ እንደ ሸቀጥ ለጓደኞቹ (እንደ ዘውዱና ዳምጤ ላሉት) ያከፋፍል ነበር።

እይታዋ የጠፋውን ህፃን ጉኒን ወደ አዲስ አበባ እና ልዩ ልዩ የሀገሪቱ ክፍሎች (አደማ፣ ሀረር፣ ጋምቤላ፣ ባሌ፣ ላሊበላና አክሱም ድረስ) በመውሰድ "እናቷ ሞታብኝ ነው" እያለ እንዲለምኑ ያስገድዳቸው እንደነበር መናገሯን ግዮን ማለዳ ከንግግሯ ተመልክቷል ።

ህፃናቱ በቀን እስከ 5,000 እና 6,000 ብር አምጥተው እንዲያስረክቡ ይገደዳሉ። የታዘዙትን ያህል ብር ካላመጡ በጭካኔ ይደበደባሉ፤ ጭንቅላታቸው ላይ እስከ ዛሬም የሚታይ ከባድ ጠባሳ አላቸው። ሳማ ተጎዝጉዞባቸው በእሱ ላይ እየተንበረከኩና እያለቀሱ እንዲለምኑ ይደረግ ነበር።

ከዚህም በላይ ከ4 ዓመቷ ጀምሮ በክንዴና በባልደራቦቹ የከፋ የፆታዊ ጥቃት (ድፍረት) ይፈጸምባት ነበር። ለፖሊስ ወይም ለሰዎች እንድትናገር "ብትናገሩ አርዳችኋለሁ" በሚል በቢላዋ እየዛተ ያስፈራራቸው ነበር።

በስቃይና በመንከራተት ዓመታት ውስጥ አልፋ በሻሸመኔ መስጊድ ደጃፍ ስትለምን፣ በሻሸመኔ የአይነ ስውራን ትምህርት ቤት ታስተምር የነበረች አንዲት ደግ ፈረንጅ ሴት ህፃናቱ በከባድ በደል ውስጥ እንዳሉ ተረዳች። ፈረንጂዋ ሴት መኪና ውስጥ በመክተት ታዳገቻቸው፤ አጥባ፣ መግባ፣ ደብቃና ከክንዴ እጅ አውጥታ ትምህርት ቤት አስገባቻቸው። ስሟንም "አለምፀሐይ" ብላ አወጣችላት።

አለምፀሐይ የብሬል (Braille) ትምህርቷን በሻሸመኔ ከተማራች በኋላ በማዘር ቴሬዛ ድርጅት በኩል አልፋ ትምህርቷን ቀጠለች።

በ1999 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት የትምህርት ፈተናዎችንና የሕይወት መሰናክሎችን በፕሮፌሰሮች ድጋፍ ዐለፈች።

በ2004 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ጽሑፍ (በአማርኛ) የመጀመሪያ ዲግሪዋን አጠናቃ በድል ተመረቀች።

ዛሬ ላይ መምህር አለምፀሐይ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በማስተማር ተማሪዎቿና የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተሮች የሚወዷትና የሚያከብሯት አንምር አርአያ መምህር ሆናለች።

ምንም እንኳን በውጪ ስኬታማና የብዙዎች መምህር ቢሆንም፣ በውስጧ ግን የሚንገበገብ ጥልቅ ቁስል አለ።

በልጅነቷ በደረሰባት ግፍ ምክንያት ወንዶችን የመፍራት፣ የብቸኝነት እና የጤና መታወክ (የሆድና የደም ዝውውር ችግሮች) ይፈታተኗታል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ "እናትና አባቴ እነማን ናቸው? ወገኖቼ የት አሉ?" የሚለው የማንነት ጥያቄ እንቅልፍ ይነሳታል። ወላጆቿን እና ቤተሰቦቿን ለማግኘት የእርስዎ እርዳታ ያስፈልጋል!

ይህችን ህፃን ተሰርቃ ሕይወቷ በግፍ የጨለመባት፣ ዛሬ ግን በጽናት ቆማ ቤተሰቦቿን የምትሻውን መምህር አለምፀሐይን ለመርዳት የሚከተሉትን መረጃዎች ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ፦

የተወለደችበት ቦታ፦ ምስራቅ ጎጃም፣ መርጦ ለማርያም፣ ነፍሴ ሳር ምድር፣ መጥገና (መርገጫ ወንዝ አጠገብ)

የአባቷ ስም/መጠሪያ፦ ጫኔ/አያሌው ("አያ ነብሮ")የእናቷ ስም፦ ሰሞኔ የእህቷ ስም፦እጅጋየሁ
የአያቷ ስም፦ውብዓለም የልጅነት ስሟ፦ጉኒ
📞 የመገናኛ ስልክ ቁጥሮች

📱 0910105055 ወይም 0910105060

ይሄንን መረጃ ለብዙሃን ሰዎች እንዲደርስ የእናንተ አንድ #ሼር የዚህችን እህታችን የብዙ ዓመታት እምባውንና እና የጠፏትን ቤተሰቦቿን ሊያገናኛት ይችላል ሼር በማድረግ እንድተባበሩን በፈጣሪ ስም እንማፀናለን ።

የሴቶች ጥቃት ይቁም ! ሴት እህት እናት ናት!

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
💔20😭18❤11👍7🤬5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፅሚ ይዞ የተወለደው ህፃን ልጅ

ከላይኛው ከንፈሩ በላይ የጢም ቅርጽ የሚመስል ጥቁር ፀጉር ያሳያል የተባለ የአንድ አዲስ የተወለደ ሕፃን ፎቶግራፍ በኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ ሰፊ ትኩረት ስቧል።

ከላይ በቪዲዮ ላይ እንደምታዩት ይህ ያልተለመደ የፊት ገጽታ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ቢሆንም፣ የምስሉ ትክክለኛነት ግን እስካሁን በግልጽ አልተረጋገጠም።

ፎቶግራፉ እውነተኛ መሆኑን ወይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተቀናበረ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ተላማጅ መረጃ የለም።

በሕክምናው ዓለም አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ላኑጎ (Lanugo) በመባል የሚታወቅ ለስላሳ የሰውነት ፀጉር ይዘው የመወለድ ተፈጥሯዊ አጋጣሚ ቢኖርም፣ ይህም ቢሆን የዚህን የተወሰነ ምስል እውነተኛነት ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ አያስችልም።

ምን ያስባሉ፤ እንደዚህ ያሉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና በተፈጥሮ መካከል ያሉ አጠራጣሪ ምስሎችን እንዴት ይመለከቷቸዋል?

Via ፦The UAE Times
ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
❤16🤣11👎4👍2🥱2🫡2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሊሰማው የሚገባ ቪድዮ ነው
❤15👏7👍1🤔1