Ghion Maleda
21.6K subscribers
2.52K photos
334 videos
37 files
648 links
እንኳን ደህና መጡ !

ማስታወቂያ ለማሰራት 👉 @GhionMaleda13

ቴሌግራም ቻናሉን ለመቀላቀል👉@GhionMaleda

ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/GhionMaleda

ደግና ቅን እንሁን 🙏
Download Telegram
" ከ2010 ዓ/ም እስከ 2015 ዓ/ም የዲግሪ ተመራቂዎች በሙሉ የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ በድጋሚ ፈተና ሊፈተኑ ነው " በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተና ህዝብ አደናጋሪ ነው።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች (በፌስቡክ እና ቲክቶክ) ላይ የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ያዘጋጀውንና ለህዝብ አስተያየት ይፋ ያዳረገውን አዲስ ረቂቅ መመሪያ በማዛበት....

" ከ2010 እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ የተመረቁ ተማሪዎች በሙሉ የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ ሲባል በድጋሚ ፈተና ሊሰጣቸው ነው " በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ፍጹም የተሳሳተ እና ህዝብን የሚያደናግር ነው።

ህዝብ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፋ የተደረገው መመሪያ በትክክል እነማንን ነው የሚመለከተው ?

ይህ መመሪያ/አሰራር የሚመለከተው በቀድሞው ዲፕሎማ (10+3፣ 12+2 ወይም ቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 ስልጠና) ተመርቀው፣ ነገር ግን የደረጃ አራት የብቃት ማዕቀፍ (COC) ሳይኖራቸው የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ዲግሪ (MA) ወይም ሦስተኛ ዲግሪ (PhD) የያዙትን ብቻ ነው።

እነዚህ ዜጎች የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ አሁን በያዙት የትምህርት ደረጃ/የያዙት ዲግሪን መሰረት ተደርጎ የሚሰጠውን ፈተና መውሰድና ማለፍ ይኖርባቸዋል።

በአጭሩ የሚመለከተው ወይም ተፈጻሚነቱ :-
- ለዲግሪ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) ፈተና ሳይወስዱ ዲግሪ የተማሩ እና የተመረቁ።
- የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) የወሰዱት ለዲግሪ ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የሆኑ ተማሪዎች ላይ ነው።

በመደበኛው መንገድ የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው (ለምሳሌ የ12ኛ ክፍል ማለፊያ አምጥተው) የገቡ፣ ወይም ከዲፕሎማ ተነስተው የCOC ፈተና አልፈው ዲግሪ የጫኑ እና የተመረቁ ዜጎችን ይህ መመሪያ አይመለከታቸውም። የትምህርት ማስረጃቸውም ያለ ምንም ተጨማሪ ፈተና እንደ ቀድሞው ይረጋገጥላቸዋል።

መመሪያው በአሁኑ ወቅት በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለና እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለህዝብ አስተያየት ክፍት የተደረገ መሆኑ ታውቋል።

         T.me/GhionMaleda
           ግዮን ማለዳ
24👏5👍3😁3🤝2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አባብን ይዞ የተገኘው ጠንቋይ በቁጥጥር ስር ዋለ

በቆጋታ ወረዳ ኤዞ ከተማ በተደረገ ክትትል፣ “እባብ” በባንዲራና በእንጨት ላይ ጠምጥሞ በህዝብ መሃል ሲንቀሳቀስ የነበረ አንድ ጠንቋይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል።

ድርጊቱን የታዘቡ የአካባቢው ነዋሪዎችና ህዝብ በሁኔታው በመገረም በከፍተኛ ሁኔታ ድምፃቸውን እያሰሙ አካባቢውን ሲያናውጡት እንደነበር ግዮን ማለዳ ከቦታው የተላከለት ቪዲዮ ላይ ተመልክቷል።

ግለሰቡ ድርጊቱን ሲፈጽም በነበረበት ወቅት የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ያዋሉት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ በህግ እየተመረመረ መሆኑ ተገልጿል።

ወንጀልን የመከላከል ትግላችን ሁልጊዜም ከሕግ ሥርዓት ባልወጣ መልኩ መሆን አለበት። ማኅበረሰቡ መሰል ድርጊቶችን በንቃት ይዞ ለፖሊስ ማስረከቡ የሚበራታታ ቢሆንም ቅጣቱንና ውሳኔውን ግን ሙሉ በሙሉ ለሕግና ለፍርድ ቤት መተው ለነገው ማኅበራዊ ሰላማችን አስተማማኝ ዋስትና ነው።

ህብረተሰቡ ከእንዲህ አይነት አደገኛ እና አሳሳች የጠንቋዮች ድርጊት ራሱን እንዲጠብቅ እንዲሁም መሰል ድርጊቶችን ሲመለከት በአፋጣኝ ለጸጥታ አካላት ሪፖርት በማድረግ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ መልዕክት ተላልፏል።ከዚያ ወጭ የደቦ ፍርዶችን መፍረድ በፍጹም ትክክል አይደለም ።

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
13👍4🥱4🤣2🤝2🤬1👻1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንዲሁ አይነት ኢፍትሀዊ የመንጋ ፍርድ ሊቆም ይገባል !
🤣13👍6💔64👏3🥱3💊1
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጥቂ የሆነው አዲስ ግደይ በስርአተ ተክሊል ዛሬ ተሞሸረ!

አዲስ ግደይ ከጅማ ባሻገር ከምትገኘው አጋሮ ከተማ ትውልዱ ነው። በቀድሞው አጠራሩ በብሔራዊ ሊጉ ስልጤ ወራቤ ያሳየውን ድንቅ ብቃት ተከትሎ በሲዳማ ቡና እንዲፈለግ ሆነ።

በክለቡም በነበረው አምስት አመታትን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበረሰብ ጋር ተዋወቀ ፣ በክለቡ ደጋፊዎችም ዘንድ ተዜመለት ፣ በሚያስቆጥራቸው አስደናቂ ጎሎች ፣ በሚያሳያቸውም የደስታ አገላለፅም በበርካቶች ለመታወቅ በቃ።

በሲዳማ ቡና ሲጫወት ከሀዋሳ ጓደኛው ካደረጋት የአሁኗ ባለቤቱ ማርታ ወርቁ ጋር ዘለግ ካለው ጎደኝነት በኋላም ከቅዱስ ጊዮርጊስ አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀጥሎ ዛሬ በሰኔ ፆም የፍቺ ቀን በስርአተ ተክሊል ጋብቻቸውን ፈፀሙ።

አዲስ ግደይ ከአመት በፊት ሳይታሰብ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ለፍቅረኛው የታገቢኛለሽ ጥያቄ ቀለበት ማበርከቱን ግዮን ማለዳ ከአመታት በፊት በፍቅር ህይወታቸው ጊዜ አጋርቶ ነበር።

አስገራሚ የቅጣት ምት ጎሎች ፣ ፈገግ ከሚያስብሉ የደስታ አገላለጶች ፣ ከእነዛ አስከፊ ጉዳቶች በኋላ በደስታ ሲቃ ለዚህች ቀን ስለደረስክ እንኳን ደስ አለህ አዲስ ግደይ እንዲሁ የቤተክርስቲያን ስርዓት ጨብቆ ለዚህ ክብር መብቃት ትልቅ ፅናትና መታደል ይጠይቃል ። እንኳን ደስ አለህ ወኝድማችን 🙏

Via፦ ጋዜጠኛ ቴወድሮስ ታከለ
ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
41🙏10👏3🔥2🤝1
አንደኛዋ ልጄ የአባቷን ህመም መቋቋም አቅቷት ትምህርቷን አቋረጠች አባቷ አቅብጦ ስላሳደጋት ከበዳት !

አግኝቶ ማጣት ከባድ ነው ። ebs ቲቪ ከውበት በላይ የተሰኘ የተቀደሰ ፕሮግራም አለው።ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ ስራዎችን የሚሰሩ ሰዎችንሙሉ ቀንወጪያቸውን ሸፍኖ ልብሶች በመግዛት ምሳና እራት በመጋበዝ ተጨማሪ የሚቋቋሙበት ገንዘብ በመስጠት ያግዛቸዋል።

ዛሬ ያገዙት ተረኛው ሰው ዳንኤል ፀጋዬ ይባላል።በደረሰበት አደጋ ንብረቱን በሙሉ ሸጦ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ስራ በመስራት የሚተዳደር ሰው ነው።የዳንኤል ታሪክ አሳዛኝ ቢሆንም የእህቱ ትዕግስት ታሪክ ግን በጣም ያሳዝናል።

ትዕግስት ከሮቤል ጋር በነበራት ቆይታ በእንባ
እየታጠበች የተናገረችው ታሪክ ያሳዝናል። ወንድሜ ዳንኤል የሚያከራየው 6 ሞተር ነበረው።

በአደጋ ምክንያት ዛሬ ሳንቡሳ በመሸጥ ልጅ ማስተዳደር ይከብዳል። ባለቤቴ ራሱ ስትሮክ ታሞ ቤት ከተኛ ስድስት ዓመቱ ነው።

ተሳቢ መኪና ፣ ሚኒባስ እና ብዙ ንብረት ነበረን። ንብረቶቻችንን ለህክምና ሸጠን ጨረስነው።ያለንን ንብረት በሱ ህክምና አጣን።

ሶስት ልጆች አሉኝ። ልጆቼ ብዙ ነገር ለምደዋል። ሻይ ሸጬ ለነሱ እንጀራ ይዞ መግባት ከብዶኛል።አንደኛዋ ልጄ የአባቷን ህመም መቋቋም አቅቷት ትምትርቷን አቋረጠች።

አባቷ አቅብጦ ስላሳደጋት ከበዳት። ሁሉም ነገር በእንድ ጊዜ ጎደላት።የመሐከለኛው ልጄ ትንሽ ይረዳ'ኛል። የበፊት ህይወታችንን ትተን አዲስ ህይወት ጀምረናል።

አንዳንድ ጊዜ መኪና ስር ግቢ ግቢ ይለኛል።ዘመዶቼም ሆኑ ጓደኞቼ አሁን ያለሁበትን ቤት አያውቁትም። ድሮ ሲያልፉ ሲያገድሙ ግን የእኛ ቤት ቤታቸው ነበር።

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
😭2918💔15🤔6🙏2🥱2
ግብረሰዶማውያንን የጫነችው የቅንጦት መርከብ በቱርክና ግብፅ ወደቦች እንዳትገባ ተከለከለች።

ከሰሞኑን " አትላንቲስ ኢቨንትስ " በተባለ የአሜሪካ የጉዞ ድርጅት የተከራየችና 2,000 ገደማ ግብረሰዶማውያንን የጫነች " ስካርሌት ሌዲ " የተሰኘች የሜዲትራኒያን ባህር የቅንጦት መርከብ ወደ ቱርክ እና ግብፅ ወደቦች እንዳትገባ ተከልክላለች።

መርከቧ በቱርክ ኩሻዳሲ እና ኢስታንቡል ወደቦች እንዳታርፍ የተከለከለች ሲሆን፣ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ውሳኔው የጉዞው ዓላማ ከሀገሪቱ ሞራላዊና ሥነ-ምግባራዊ እሴቶች እንዲሁም ማኅበራዊ ደንቦችና እሴቶች ጋር ስለማይጣጣም መሆኑን ገልጸዋል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪች ካምቤል በኩባንያው 36 ዓመታት ታሪክ ውስጥ እንዲህ ያለው ንገረ ሲገጥማቸው የመጀመሪያ እንደሆነ ገልጸዋል።

መርከቧ ከቱርክ እገዳ በኋላ የጉዞ አቅጣጫዋን ወደ እስክንድርያ ግብፅ ብታዞርም፣ የግብፅ ባለሥልጣናትም መርከቧ ወደ ሀገሪቱ የባህር ክልል እንዳትገባ አግደዋታል።

ግብፅ ለእገዳው የሰጠችው ይፋዊ ማብራሪያ ባይኖርም፣ ድርጅቱ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጉዞ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉን አስታውሶ በውሳኔው መደነቁን ገልጿል።

በእነዚህ እገዳዎች ምክንያት ተሳፋሪዎች በግብፅ ሊያደርጓቸው የነበሩት የፒራሚድ እና የታሪክ ስፍራዎች ጉብኝቶች የተሰረዙ ሲሆን፣ መርከቧ መስመሯን ቀይራ ወደ ክሬት ግሪክ እና ኮቶር ሞንቴኔግሮ ለማምራት ተገድዳለች።መረጃው ከ ' ዘ-ጋርዲያን ' የተወሰደ ነው ።

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
👍4113👏9🙏3🔥1
በካዛንቺስ መሃል ከተማ — ያለምንም የዋጋ ጭማሪ እና ወለድ የቤት ባለቤት ይሁኑ!

በአዲስ አበባ እምብርት ካዛንቺስ ሳይት፣ በሁሉም አቅጣጫ በሚያማምሩ ፓርኮች እና መዝናኛዎች የተከበበ፣ ምንም አይነት የመሰረተ ልማት (የውሃ፣ የመብራት፣ የመንገድ) ስጋት የሌለበት ድንቅ የመኖሪያ መንደር!

ከመንግስት ጋር በጋራ (70/30) እየገነባን ያለነውን ይህንን እጅግ ዘመናዊ አፓርታማ ከ2 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እናስረክባለን።
ልዩ ጥቅሞች፦
Fixed Rate፦ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ወይም የወለድ ክፍያ የለውም!
ምቹ አከፋፈል፦ በሂደት የሚከፈል ማራኪ የክፍያ ስልት።
ታማኝነት፦ በኩባንያው ቀጥተኛ የሽያጭ ባለሙያ የሚስተናገዱበት አስተማማኝ እድል።
📐 ያሉን የአማራጮች እና የክፍያ ዝርዝር (15% ቅድመ ክፍያ ብቻ)

🛏 ባለ 1 መኝታ (55 ካሬ)
አጠቃላይ ዋጋ፦ 5,830,385 ብር
15% ቅድመ ክፍያ፦ 874,557 ብር

🛏 ባለ 2 መኝታ (80 ካሬ)
አጠቃላይ ዋጋ፦ 8,480,560 ብር
15% ቅድመ ክፍያ፦ 1,272,084 ብር

🛏 ባለ 3 መኝታ (95 ካሬ)
አጠቃላይ ዋጋ፦ 10,070,665 ብር
15% ቅድመ ክፍያ፦ 1,510,600 ብር

🛏 ባለ 4 መኝታ (160 ካሬ)
አጠቃላይ ዋጋ፦ 16,961,120 ብር
15% ቅድመ ክፍያ፦ 2,544,168 ብር

📞 አሁኑኑ ይደውሉ — ሳይቱን ይጎብኙ!
እድሉ ሳያመልጥዎት ቀጠሮ ለመያዝ እና ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በታማኝነት እና በሃላፊነት እጠብቆታለሁ።
📱 ስልክ፦ 09-11-63-67-90
👤 የድርጅቱ የሽያጭ አማካሪ ፦ ካሳሁን አንዷለም
💬 Telegram: @kassu23
🟢 WhatsApp:
https://wa.me/251777636790
4👍3🤔1🤝1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቦሌ አትላስ አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብና ንፋስ በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት ደረሰ

በትናንትናው ዕለት ከላይ በቪዲዮ እንደምትመለከቱት በአስደንጋጭ ሁኔታበዋና ከተማዋ ቦሌ አትላስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጣለው ኃይለኛ ዝናብ እና በነፈሰው ብርቱ ንፋስ ምክንያት...

ከአንድ የግንባታ ቦታ ላይ የብረት ቁሳቁሶች ተፈንቅለው በመውደቃቸው በአቅራቢያው በነበረ ዘመናዊ መኪና ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል።

ምንም እንኳን በንብረት ላይ አደጋው ጉዳት ቢያስከትልም፣ በአምላክ ምስጋና ይግባና በአደጋው ወቅት በሰው ሕይወትም ሆነ አካል ላይ የደረሰ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደሌለ ተረጋግጧል።

Video Credit:- bereket de
ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
34🥱9🤝4💔2👎1🤬1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰው አይጠመዳችሁ በፈጣሪ ስም መጨረሻውን ሳትመለከቱ አንዳታቋርጡት😀😀

ይህቺ ከቪዲዮ ላይ የምትመለከቷት እህታችን እንደዚህ የለፋችበት ዘፈኗን ከዩትዩብ በኮፒራይት አስወርደውባት የሷን ዩቲዩብ አዘግተውባታል ። አሁን ላይ የራሷን ዘፈን የራሳቸው ገጽ ላይ ለጥፈውት እየሸቀሉበት ነው

ብዙዎች መብቷ ነው ለምን አተዋትም ሲሉ ጥቂቶች ደግሞ ይገባታል እያሉ ይገኛሉ ። ቀሪዎቹ ደግሞ ገና ልጅ ናት ይሄንን ያህል እውቀት ላይኖራት ይችላል እያሉ ነው ። እናንተስ ምን ትላላችሁ? ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ ?

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
😁148💔4👍2🥱2🖕1🤝1
የምርጫ ቀን ስለሆነ መንግስትም የለም በማለት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ወጣት
 
አቶ አክሊሉ አለማየሁ የተባለው ግለሰብ በኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ ሲዶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ደብተር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕድሜዋ 15 ዓመት የሚሆናትን ታዳጊ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፍዱ 4 ሰዓት ገደማ  የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈፅሟል።
 
ተከሳሹ 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሚካሄድበት ዕለት ተበዳይን መንገድ ላይ ጠብቋት ዛሬ የምርጫ ቀን ስለሆነ መንግስትም የለም በማለት አንድ ጊዜ ወገቧ ላይ እና አንድ ጊዜ ትከሻዋ ላይ በመምታት እራሷን ከሳተች በኋላ ያለፍላጎቷ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅሞባታል።
 
የወረዳው ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት  ብርቱ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አደራጅቶ መዝገቡን ለወረዳው ዐቃቤ ህግ ልኳል።
 
የወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ መዝገቡን ተመልክቶ ክስ መመስረቱን የአሪ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ  በየነ ጉዶ ተናግረዋል።

ክሱ የቀረበለት የደቡብ ኣሪ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት በ12 ዓመት  ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወስኗል፡፡ Via፦ዳጉ ጆርናል

የ12 አመት ጽኑ እስራት ውሳኔ አስተማሪ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ ?

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
10👎9🤪8🥱4🤬3👍2
ዶናልድ ትራምፕን የምትመስለው ስፔናዊቷ ገበሬ የመገናኛ ብዙኃን መነጋገሪያ ሆናለች!

በሰሜን ምዕራብ ስፔን ገጠራማ ስፍራ (ጋሊሲያ) የምትኖረው ዶሎሬስ ሌይስ አንቴሎ የተባለችው አዛውንት፣ ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባላት አስገራሚ መመሳሰል የተነሳ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በድጋሚ ከፍተኛ ትኩረት እየሳበች ትገኛለች።

እ.ኤ.አ. በ2018 ስለ ገጠር ህይወት የሚዘግብ አንድ ጋዜጠኛ የዕድሜ ባለጸጋዋን ዶሎሬስን በፈረንቃ (አካፋ) ተደግፋ በፎቶ ካሜራው አስቀርቷት ነበር።

በፎቶው ላይ ያላት የፀጉር ቀለም፣ የፊት አወቃቀር እና አስተያየት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ፍጹም አንድ አይነት በመሆኑ በወቅቱ ዓለምን አስገርሞ የነበረ ሲሆን...

ይህ ምስል አሁን በ2026 በድጋሚ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በስፋት እየተጋራ ይገኛል። የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የሁለቱን ምስሎች ጎን ለጎን በማነፃፀር "መንትዮች ናቸው" እስከማለት ደርሰዋል።

ዶሎሬስ ይህንን አጋጣሚ በጣም በሚያስቅ ሁኔታ የተቀበለችው ሲሆን፣ በወቅቱ ለሀገር ውስጥ ጋዜጣ በሰጠችው አስተያየት፦

"ምስሌ በጣም ሩቅ ቦታ የተጓዘ ይመስላል፤ እኔ እንደማስበው ግን ይህ የሆነው በፀጉሬ ቀለም ምክንያት ነው" ስትል በፈገግታ ተናግራለች።

ይህ ድንገተኛ ዝና በገጠሯ ስፔን የምትመራውን ቀለል ያለ የግብርና ህይወት አላስተጓጎላትም፤ ይልቁንም አሁንም ድረስ በደስታ ስራዋን እየቀጠለች ትገኛለች ነው የተባለው። Via፦ መናኸሪያ ሬዲዮ

እናንተ እንዴት አያችሁት ዶናልድ ትራምፕን ትመስላለች ወይስ አትመስልም ? ሀሳባችሁን አካፍሉን እስኪ ?

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
😁136👏3👍2👎1🤔1🤝1
ሲዳማ ቡና 200 መቶ ካሬ መሬት በሀዋሳ ከነካርታውና በተጨማሪ 1 ሚሊዮን ብር ለእያንዳንዱ ተጫዋቾች ሸለመ

የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምዮን የሆነው ሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ ለክለቡ ተጫዋቾች ለእያንዳንዳቸው የ200 ካሬ መሬት እና የ1 ሚሊዮን ብር የሲዳማ ክልል ሸልሟል ። የክለቡ ወሳኝ አስጨፋሪ ለሆነዉም ለኢያ ቡኒዬ የ200 ካሬ ሽልማት ማበርከቱን ግዮን ማለዳ ተመልክቷል ።

ከዚህ በተጨማሪ የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው ሲዳማ ቡና በሀዋሳ ሐይሌ ሪዞርት የዕራት እና የሽልማት ስነስርዓት ተደርጓል ።

የሲዳማ ቡና ከ20 አመት በታች ክለብን ቻምፒዮን ያደረገው ወጣቱ አሰልጣኝ አመሀ ዘውዴ የ2 መቶ ካሬ መሬት ሀዋሳ ላይ እንዲሁም የክለቡ አጠቃላይ 6 ሚሊዮን ተሸልመዋል!

ለሲዳማ ቡና እዚህ መድረስ መሠረቱ የሆኑት የቀድሞው ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ሳሳሞ እውቅ እና የ2 መቶ ሺህ ብር ሽልማት ተሰጥቷቸዋል!

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ እግር ኳስ ለአንድ የአሰልጣኝ ፊርማ ለማግኝት እስከ 28 ሚሊዮን ብር ደርሷል ። ክለቦች ይሄ ነው የሚባል ገቢ ስለሌላቸው ከመንግሥት በጀት ተቀንሶ ነው ውድድሮችን ሆነ የቡድኑን አባላቶች ወጭ የሚሸፍኑት ።

በቀጣይ አመታት የኢትዮጵያ ክለቦች የህዝብን በጀት ከመጋራት ወጥተው እራሳቸውን እንዲሚችሉ ተስፋ እናደርጋለን !

የሲዳማ ቡና ተጫዋቾችና የቡድን አባላት እንዲሁም የክለቡ ደጋፊዎች በግዮን ማለዳ ስም እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንፈልጋለን 👏👏 እንኳን ደስ አላቸው ሲዳማዎች 🥰

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
31🥱8😁5🤝4
መልካም ልደት ብላቴናው👑🎂

ሸገር አዲሳባ ዕልልታ ተሰምቷል
የሴቱን ባናቅም ወንድ አንድ ሰው ተወልዷል
ከራዬ ማህፀን ተወለደ ቴዲ
ካሣ ብሎ ማልቀሰ አበቃ ከእንግዲ
እምዬ ጦቢያ ምንኛ ቀንቶሻል
መቅደላ ያጣሽውን በአዲስ አግኝተሻል
ፍቅር አስተማሪ ጀግና መቶልሻል …!!

ቴዲ አፍሮ ዛሬ 50 አመት ልደቱን ያከብራል ።
የምንወድህ በምክንያት ነው!!ፍቅር ያሸንፋል!!!

መልካም ልደት በሉት እስኪ ?

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
90👍17🙏7👏5🔥3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአዲስ አበባ ግራር ኮንዶሚኒየም አካባቢ ከባድ የትራፊክ አደጋ ደረሰ

በዛሬው እለት ከስልጤ ሰፈር ወደ ግራር ኮንዶሚኒየም በሚወርደው መንገድ ላይ አስደንጋጭ የትራፊክ አደጋ ተከስቷል።

አንድ የጭነት መኪና (ሲኖ ትራክ) ቁልቁለቱን በሚወርድበት ወቅት ፍሬን እምቢ በማለቱ (በመበላሸቱ) ምክንያት ቁጥጥር ውጪ ሆኗል። በአደጋው ምክንያት በግምት እስከ 6 የሚደርሱ መኪናዎች ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በአደጋው አንድ ሰው ቪትስ (Vitz) መኪና ውስጥ የነበረ በአስቸኳይ ወደ አለርት ሆስፒታል ተወስዶ የሕክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል።

እንዲሁም በአዲስ አበባ ግራር ኮንዶሚኒየም አካባቢ በሲኖ መኪና ሙሉ በሙሉ በወደመው የቪትዝ (Vitz) መኪና ውስጥ የነበረችው ህጻን ሴት ልጅ ያለምንም ጉዳት በሰላም ተርፋለች!

የመኪናውን ስባሪና ፍርስራሽ ስንመለከት ማመን ቢከብድም፣ ህጻኗ ከፍርስራሹ ውስጥ በሰላም ስትወጣ በቦታው የነበረው የሰዎች ጩኸትና የደስታ ልቅሶ በእውነት እጅግ የሚገርምና ልብ የሚነካ ነበር! የሰውን ልጅ ተስፋ መቁረጥ ወደ ታላቅ ደስታ የቀየረ ድንቅ ቅጽበት ነበር።

ሰው ተስፋ በሚቆርጥበትና ሁሉም ነገር አከተመለት በሚባልበት ቅጽበት፣ እርሱ በሚያስደንቅ ጥበቡ ተአምርን ያሳያል።

በእውነት ፈጣሪ ካለማን ይነካል?
የማይታመን ነው ለተጎዱት ወገኖቻችን ፈጣን ማገገምን እንመኛለን! ፈጣሪ ሀገራችንንና ህዝባችንን ከአደጋ ይጠብቅ።

Via አደም ከስፍራው
ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
33🙏19💔5🥱3😭3
10🙏9👍2
እነዚህ ጥቂት ምዕመናን ለሀገራቸውና ለነፍሳቸው የሚጸልዩበትን ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበትን በእናተ እገዛ እዚህ አድርሰናታል🙏

እነዚህ ጥቂት ምዕመናን ለሀገራቸውና ለነፍሳቸው የሚጸልዩበትን፣ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚያገኙትን፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበትን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ  ለመሥራት ለበርካታ ዓመታት ያሰቡ ቢሆንም በእነርሱ አቅም የሚሆን አይደለምና ተስፋ ቆርጠው እንደሚገኙ ከወራት በፊት ዘግበን ነበር።

ይቺ ቤተክርስቲያን በዚህ በማህበራዊ ሚዲያ በተጀመረ በተጀመረ ንቅናቄ እዚህ ደረጃ አድርሰናታል።

በእናንተው በውድ ኦርቶዶክሳውያን ድጋፍ፣ በጎፎሬ ደብረ መንክራት በአታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የመቅደስ ቅድስትና የቅኔ ማኅሌት የኮሎን ሥራዎች በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀዋል። ለዚህ ላበረከታችሁት ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን።

በጎን ደግሞ የሌሎች የእምነት ድርጀቶች በዚህ ደሳሳ ጎጆ የሚትጸልዩ አቅም የሌላችሁ ነችሁና ወደ እኛ ኑ በማለት ታላቅ የሆነ የስነልቦና ጫና እያደረሱባቸው ይገኛሉ እነርሱ ግን ይህንንና ሌሎችንም ጫናዎችን ችላው በሃይማኖታቸው ጸንተው ዛሬም አሉ ።

ስለዚህ ውድ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ለበጎ ነገር የሚትተጉ የተዘጉና የተዘነጉ የገጣሪቷን ቤተክርስቲያን ለማገዝና በረከት ለማግኘት ሁሌ የምትጥሩ በሀገር ውስጥና በውጪ የሚትኖሩ በዚህ ሥራ እንድትሰተፋ በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም እንጠይቃለን ።

ነገር ግን በአቅርቦት እጥረት ምክንያት 24 የበራንዳ ኮሎኖችን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ አልተቻለም። ለዚህ የሚያስፈልጉት፦

🔹 ባለ14 ፌሮ ብረት – 72 ቤርጋ
🔹 ባለ8 ፌሮ ብረት – 48 ቤርጋ
🔹 ሲሚንቶ – 36 ኩንታል
🔹 የባለሙያዎች የሥራ ክፍያ

በአጠቃላይ 490,800 ብር ያስፈልጋል።   ውድ የእመቤታችን ልጆች፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ ሁላችሁም በዚህ ታላቅ የበረከት ሥራ የበኩላችሁን አሻራ እንድታኖሩ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

እመቤታችን ድንግል ማርያም በምልጃዋ ዘወትር ትጠብቃችሁ፣ ከክፉ ሁሉ ትሰውራችሁ፣ መልካም ምኞታችሁንም ትፈጽምላችሁ። ከ10 ብር ጀመረን  ሃያ አራቱን የበራንዳ ኮሎን እንሙላ 🙏

የልገሳ ሂሳብ ቁጥሮች (የህንፃ አሰሪ ኮሚቴ)

🏦 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000624326281
🏦 አቢሲኒያ ባንክ፦ 240587815
🏦 አዋሽ ባንክ፦ 013201006748101

📞 ለበለጠ መረጃና የሞራል ድጋፍ፦ 0933055802 ወይም 0911414852 ደውለው "አለንላችሁ" በማለት ከጎናቸው መሆንዎን ይግለጹ።     

በቴሌግራም ለማግኘት፦ @degnet0321

#ትኩረት ለገጠር ቤተክርስቲያን

@GhionMaleda
13🙏9👍3👏2
😭8🤬31👎1