Ghion Maleda
21.6K subscribers
2.52K photos
336 videos
37 files
651 links
እንኳን ደህና መጡ !

ማስታወቂያ ለማሰራት 👉 @GhionMaleda13

ቴሌግራም ቻናሉን ለመቀላቀል👉@GhionMaleda

ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/GhionMaleda

ደግና ቅን እንሁን 🙏
Download Telegram
እነሆ ሁለትም ሶስትም ሆነው በጊዜያዊ ጎጆ መጠለያ በስምህ ተሰብሰበዋልና አንተ በመካከላቸው ተገኝ 🙏

በጊዜያዊ ጎጆ መጠለያ ውስጥ የሚገኘውን ታሪካዊና መንፈሳዊ ቦታ ወደ ሙሉ ቤተ-መቅደስ ለመቀየር ስራ ተጀመሯል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በወላይታ ሀገረ ስብከት፣ በካዎ ኮይሻ ወረዳ የምትገኘው የኮይሻ ዋሙራ ሳጋዶራ በዓታ ለማርያም ቤተክርስቲያን በአሁኑ ወቅት በጠባብና ጊዜያዊ መጠለያ (መቀኞ) ውስጥ ትገኛለች።

ይህንን በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ የሚገኘውን ታሪካዊና መንፈሳዊ ቦታ ወደ ሙሉ ቤተ-መቅደስ ለመቀየር እንዲሁም ለቀጣይ የማስፋፊያ ሥራዎች ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋታል።

ድጋፎቹ የሚውሉት ለቅዳሴና ለተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚውሉ ቁሳቁሶች። ለግንባታ ዕቃዎች ማለትም ቆርቆሮ፣ ምስማር፣ ሲሚንቶ እና ሌሎች የግንባታ ግብዓቶች። እንዲሁም ለምዕመናን አገልግሎት እንዲመች ይዞታውን ለማስፋት።

ለእነዚህ ተግባራት ማስፈጸሚያ ከ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ወጪ እንደሚጠይቅ ተገምቷል። በመሆኑም ደጋግ ኢትዮጵያውያን አቅማችሁ በፈቀደ መጠን በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የዚህ በረከት ተካፋይ እንድትሆኑ ቤተክርሲትያኗ ጥሪ አቅርባለች።


የልገሳ ማድረጊያ የባንክ አካውንት፦ ስም: ሳጋዶራ በዓታ ማርያም

1000707796026-CBE

ለበለጠ መረጃና የሞራል ድጋፍ 0916141439 ወይም 0915536425 ☎️ በመደወል አይዞአችሁ በሏቸው 🙏

በቴሌግራም ለማግኘት 👉 @sagadora12

“ሁለት ወይም ሦስት ሆናችሁ በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና። (ማቴ 18፥20)

#ትኩረት ለደቡብ ኢትዮጵያ ገጠር አብያተክርስቲያናት !
21🙏9👍5🤔1
የተገጠመለትን ጉሉኮስ ነቅሎ ከሆስፒታል ያመለጠው ታራሚ በቁጥጥር ስር ዋለ

በጂንካ ማረሚያ ተቋም በስርቆት ወንጀል ተከሶ የነበረውና በጤና ችግር ምክንያት ወደ ጂንካ ዞናል ሆስፒታል ለህክምና የገባው ታራሚ ከሆስፒታል ካመለጠ በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጂንካ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አስታወቀ ።

የተቋሙ አዛዥ ምክትል ኮማንደር አስቻለው ነሬሬ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ታራሚው በስርቆት ወንጀል ተከሶ መደበኛ ቀጠሮውን እየተከታተለ የነበረ ሲሆን በጤና ችግር ምክንያት ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጂንካ ዞናል ሆስፒታል ተልኮ ነበር ።

ታራሚው ሆስፒታል በነበረበት ወቅት በህክምና ላይ የተገጠመለትን ጉሉኮስ ነቅሎ ሌሊት 2 ሰዓት አካባቢ ማምለጡ ተገልጿል ።

መረጃ የደረሳቸዉ የማረሚያ ተቋሙ አመራሮች ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ባደረጉት ክትትል ከሌሊቱ 10 ሰዓት ተይዞ  ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ።

ታራሚው በተከሰሰበትን ወንጀል በመፀፀት ህጉ የሚሰጠውን ውሳኔ ተቀብሎ መታረም ሲገባው ለህክምና በተላከበት ወቅት ማምለጡ በጉዳዩ ላይ በህግ አግባብ ምርመራ ተደርጎ ውሳኔ ይሰጣል ሲሉ ኮማንደር አሰቻለው ነሬሬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በመባ ወርቅነህ

Joined & Share 👉T.me/GhionMaleda
Joined & Share 👉T.me/GhionMaleda
😁106🔥2🤪1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ ወቅታዊው የክረምት ዝናብ መግባቱን ተከትሎ ከላይ በቪዲዮ እንደምታዩት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሚገርሙ የፈጠራ የሥራ ዕድሎችና ማኅበራዊ ታሪኮች መከሰታቸውን ቀጥለዋል።

በቅርቡ በሰፊው መነጋገሪያ በሆነው ቪዲዮ ላይ በግልጽ እንደሚታየው፣ አንድ ንቁና ብልህ ወጣት በጎርፍ የተጥለቀለቁ የከተማዋን መንገዶች መሻገር የከበዳቸውን እግረኞች በጀርባው አዝሎ ማሻገር ጀምሯል።

ይህ ወጣት እግረኞች ውድ ጫማቸውና ልብሳቸው በጭቃና በጎርፍ ውሃ ሳይበላሽ ወደ ፈለጉበት ቦታ እንዲሻገሩ በማድረግ በምላሹ ተመጣጣኝ የገንዘብ ክፍያ የሚቀበል ሲሆን፣ ይህ የቢዝነስ አስተሳሰቡ በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ትልቅ አድናቆትንና መደነቅን ፈጥሯል።

የክረምቱ ወቅት በመጣ ቁጥር የከተማዋ የመሰረተ ልማት ክፍተት የራሱን ፈተና ይዞ ቢመጣም፣ ወጣቶች ችግሩን ወደ መልካም የገቢ ምንጭነት የሚቀይሩባቸው እንዲህ ያሉ አስገራሚና ስራ ፈጣሪ ታሪኮች መደመጣቸውን ይቀጥላሉ።

ግዮን ማለዳ

Joined & Share 👉T.me/GhionMaleda
Joined & Share 👉T.me/GhionMaleda
😁2012🤪3🖕2💊2🥱1
Ghion Maleda
Photo
#Update
የኢንተርኔትና የማኅበራዊ ሚዲያ ዓለም የሰዎችን ሕይወት መለወጡን በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ አዲሱ የዕድል ብርሃን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በምትገኝ አንዲት ታዳጊ ላይ በድምቀት አብርቷል።

ነገርየው የጀመረው ታዋቂው ፎቶግራፍ አንሺ ምስክር ከበደ ወደ ገጠር መንደር ባደረገው ጉብኝት ወቅት ኤልሳቤጥ ደስታ የተባለችውን ታዳጊ እጅግ ማራኪ፣ ተፈጥሯዊና አስደናቂ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ማጋራቱን ተከትሎ ነው።

የኤልሳቤጥ ልዩ ተፈጥሯዊ ውበት፣ ሳቢ ፈገግታና አቋም የብዙዎችን ቀልብ በአንድ ጊዜ የሳበ ሲሆን፣ ይህ በፈገግታ የታጀበ የቫይራል ክስተትም በፍጥነት ወደ ትልቅ የሕይወትና የዓለም አቀፍ የሙያ ዕድል ተቀይሯል።

በአሁኑ ወቅት የኤልሳቤጥ አስደናቂ ገጽታ የዓለም አቀፍ ሞዴሊንግ ኤጀንሲዎችንና ታዋቂ ዓለም አቀፍ ብራንዶችን ትኩረት በእጅጉ የሳበ በመሆኑ በርካታ የሥራ ጥያቄዎችና ጥቆማዎች እየጎረፉላት ይገኛል።

ይህን ተከትሎም ታዋቂው በጎ አድራጊ ማስተር አብነት ይህችን የከምባታ እንቁ የሆነች ታዳጊ ሕይወቷን ሙሉ በሙሉ ለመለወጥና ወደ ላቀ የስኬት ማማ ለማድረስ ወደ አዲስ አበባ ይዟት እየመጣ ይገኛል።

ይህ ተፈጥሯዊ ተሰጥኦ ከዲጂታል ዕድል ጋር የተገናኘበት ልብ የሚነካ ታሪክ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን (ዲያስፖራውን) ጭምር በእጅጉ ያነጋገረ ሲሆን፣ ኤልሳቤጥን በቅርቡ በዓለም አቀፍ የፋሽን መድረኮች ላይ የኢትዮጵያን ውበት ስታስተዋውቅ ለማየት ትልቅ ጉጉት ተፈጥሯል።

የግዮን ማለዳ የዝግጅት ክፍል የዚህችን አዲስ የኢትዮጵያ ዕንቁ የሕይወት ለውጥና የጉዞ ስኬት በቅርበት መከታተሉን ይቀጥላል።

T.me/GhionMaleda
ግዮን ማለዳ
40👏12👍6🤔1🖕1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በካዛንቺስ መሃል ከተማ — ያለምንም የዋጋ ጭማሪ እና ወለድ የቤት ባለቤት ይሁኑ!

በአዲስ አበባ እምብርት ካዛንቺስ ሳይት፣ በሁሉም አቅጣጫ በሚያማምሩ ፓርኮች እና መዝናኛዎች የተከበበ፣ ምንም አይነት የመሰረተ ልማት (የውሃ፣ የመብራት፣ የመንገድ) ስጋት የሌለበት ድንቅ የመኖሪያ መንደር!

ከመንግስት ጋር በጋራ (70/30) እየገነባን ያለነውን ይህንን እጅግ ዘመናዊ አፓርታማ ከ2 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እናስረክባለን።
ልዩ ጥቅሞች፦
Fixed Rate፦ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ወይም የወለድ ክፍያ የለውም!
ምቹ አከፋፈል፦ በሂደት የሚከፈል ማራኪ የክፍያ ስልት።
ታማኝነት፦ በኩባንያው ቀጥተኛ የሽያጭ ባለሙያ የሚስተናገዱበት አስተማማኝ እድል።
📐 ያሉን የአማራጮች እና የክፍያ ዝርዝር (15% ቅድመ ክፍያ ብቻ)

🛏 ባለ 1 መኝታ (55 ካሬ)
አጠቃላይ ዋጋ፦ 5,830,385 ብር
15% ቅድመ ክፍያ፦ 874,557 ብር

🛏 ባለ 2 መኝታ (80 ካሬ)
አጠቃላይ ዋጋ፦ 8,480,560 ብር
15% ቅድመ ክፍያ፦ 1,272,084 ብር

🛏 ባለ 3 መኝታ (95 ካሬ)
አጠቃላይ ዋጋ፦ 10,070,665 ብር
15% ቅድመ ክፍያ፦ 1,510,600 ብር

🛏 ባለ 4 መኝታ (160 ካሬ)
አጠቃላይ ዋጋ፦ 16,961,120 ብር
15% ቅድመ ክፍያ፦ 2,544,168 ብር

📞 አሁኑኑ ይደውሉ — ሳይቱን ይጎብኙ!
እድሉ ሳያመልጥዎት ቀጠሮ ለመያዝ እና ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በታማኝነት እና በሃላፊነት እጠብቆታለሁ።
📱 ስልክ፦ 09-11-63-67-90
👤 የድርጅቱ የሽያጭ አማካሪ ፦ ካሳሁን አንዷለም
💬 Telegram: @kassu23
🟢 WhatsApp:
https://wa.me/251777636790
7👍5👏1🤔1
ነፍሰ ጡሯን ጨምሮ በሿሿ ወንጀል የተሰማሩ
ዘጠኝ ሿሿ አድራጊዎች ተያዙ!

ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 1:40 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሪቼ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው። የግል ተበዳይ ከአጎና ወደ እስታዲየም ለመሄድ በማሰብ ኮድ 3-83620 ኦሮ ነጭ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በማስቆም ትገባለች።

ተጠርጣሪዎችም የግለሰቧን ወደ ተሽከርካሪው መግባት ተከትለው በማዋከብ እና ትኩረቷን በማሳጣት ይዛው ከነበረው ቦርሳ ውስጥ 32 ሺ ብር ግምት ያለው ሳምሰንግ ስልክ ሰርቀው ጥለዋት ይሄዳሉ።

ይህን የተመለከቱ የትራፊክ ፖሊሶች ተሽከርካሪውን በማስቆም እና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ ሰርተዋል። ተጠርጣሪዎቹ ከተያዙ በኋላ በተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገ ፍተሻ 7 ስልኮች መገኘታቸውን የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ነፍሰ ጡር መኖሯ የተገለጸ ሲሆን የቀን ውሎ አበል በመክፈል እና ተሽከርካሪ በመከራየት ወንጀሉን የሚፈፅሙ ግለሰቦች....

እንዳሉ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ትራንስፖርት ሲጠቀም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

Via፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ
ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
12🙏9😁3🤬3🥱3🤮2
ከዓለም ዋንጫ ጭዋታዎችን እንዳይዳኝ በአሜሪካ የታገደው ሶማሊያዊው ዳኛ ዑመር በጅግጅጋ ከተማ በታላቅ እና ደማቅ አቀባበል ተደረገለት ።

ሶማሊያዊው ዳኛ ኦማር አርታን በሶማሊ ክልል በሁለት ዞኖች መካከል የሚደርግ የእግር ኳስ ጨዋታን ለመዳኘት ኢትዮጵያ መግባቱን ግዮን ማለዳ ተመልክቷል ።

በአቀባበሉ ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት፣ ከንቲባው፣ የወጣቶች ሚኒስትር፣ የባምቤዳ ኃይል፣ የባህልና የሙዚቃ ቡድኖች እንዲሁም የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ዳኛ ዑመር አሜሪካ ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር ግንኙነት አለው በሚል የዓለም ዋንጫ ጭዋታዎችን ለመዳኘነት ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ክልከላ ማስቀመጧ ይታወሳል ። በዚህም ምክንያት በዓለም ዋንጫ የሚገኘው ገቢ 100ሺ $ የሀገሩ ባለሀብቶች አሰባስበው አብርክተውለታል።

ኦማር አብዱልከድር አርታን ሰኔ 22 ቀን የኩዌት ፕሪሚየር ሊግ የፍጻሜ ጨዋታን የዳኘ ሲሆን ነሐሴ 6 በኦስትሪያ ሳልዝበርግ በፒኤስጂ እና አስቶን ቪላ መካከል የሚካሄደውን የዩኤፋ ሱፐር ካፕ ጨዋታ እንዲዳኝም ግብዣ ቀርቦለታል።

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
@GhionMaleda
18😁4🤪2
👎12🤣82🥱2👍1
በግ ሰርቆ ሲያርድ የተያዘው ወጣት!

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው በጭልጋ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ሰራቆ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ነው። አንድ ግለሰብ በግ ሰርቆ ብቻ ሳይሆን ደፍሮ እዚያው ሲያርድ በኅብረተሰቡ ንቁ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ተይዟል። ወጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ባደረጉት ፈጣን ጥቆማ ሌባው በጉን አርዶ ሳይጨርስ በቁጥጥር ሥር ውሏል።

የተቆጡት ነዋሪዎች ግለሰቡ የሠራውን ወንጀል ለሁሉም ማስተማሪያ እንዲሆን የታረደውን በግ አሸክመው በአካባቢው ሲያዞሩት ቆይተዋል። ማኅበረሰቡ አካላዊ ጉዳት ሳያደርስበት፣ በመጨረሻም ተጠርጣሪውን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስዶ አስረክቧል።

“ሌባና አውጪ መቼም ቢሆን መቀጣት አለበት!” በሚለው ሐሳብ ላይ ማንም አይስማማም። የኅብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ እና ለሕግ አስከባሪዎች የሚያደርገው ጥቆማ ወንጀልን በዘላቂነት ለመከላከል እጅግ አስፈላጊ ነው።

ነገር ግን ከዚህ ክስተት ጀርባ ልናሰምርበት የሚገባ አንድ ትልቅ ስጋት አለ። በአሁኑ ወቅት ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችን በአደባባይ እያዞሩ ማዋረድና መሰል የሕዝብ ቅጣቶች እየተበራከቱ መጥተዋል። ይህ አካሄድ በወቅቱ ወንጀልን የሚቀንስ ቢመስልም፣ ውሎ አድሮ ግን ማኅበረሰቡ ራሱ ፈራጅና አስፈጻሚ የሚሆንበትን የደቦ ፍርድ እንዳያበረታታ ከፍተኛ ስጋት እየፈጠረ ይገኛል።

ወንጀልን የመከላከል ትግላችን ሁልጊዜም ከሕግ ሥርዓት ባልወጣ መልኩ መሆን አለበት። ማኅበረሰቡ ሌባውን በንቃት ይዞ ለፖሊስ ማስረከቡ የሚበራታታ ቢሆንም ቅጣቱንና ውሳኔውን ግን ሙሉ በሙሉ ለሕግና ለፍርድ ቤት መተው ለነገው ማኅበራዊ ሰላማችን አስተማማኝ ዋስትና ነው።

በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አስተያየት ይኖራችኋል? ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ ?

T.me/GhionMaleda
ግዮን ማለዳ
15🤣6🤬2🥱2💔2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከላይ እንደምታዩት አንድ ወጣት በምሽት በከተማ አስፓልት ዳርቻ ላይ ለቆመ ጅብ የታሸገ ላስቲክ ወተት ሲያጠጣው የሚያሳይ ሲሆን፣ ድርጊቱ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያና መደነቅን ፈጥሯል።

በአንድ የከተማ መንገድ ላይ የኢትዮጵያ ታርጋ ከለጠፈ መኪና አጠገብ የቆመው ፈርጠም ያለ ጅብ፣ ወጣቱ የያዘለትን የላስቲክ ወተት በሰላማዊ ሁኔታ ሲጠጣ ይስተዋላል።

ወጣቱም እንስሳውን “ጠጣ... አትናከስ” እያለ በረጋ መንፈስ ሲያናግረውና ወተቱን ሲያጋራው ይሰማል። ጅቡም ወተቱን በተረጋጋ ሁኔታ ከጠጣ በኋላ የተደፋውን ጭምር ከመሬት ላይ ሲልስ ይታያል።

ይህ ዓይነቱ ከዱር እንስሳት ጋር የሚደረግ የቅርብ ንክኪ በሐረር ከተማ “የጅብ መጋቢዎች” ዘንድ የተለመደ ባህል ቢሆንም፣ እንዲህ ባለው መደበኛ የከተማ አስፓልትና የመኖሪያ መንደር ውስጥ ጅብን በቅርበት ወተት መመገብ ግን ለብዙኃኑ እንግዳና አስገራሚ ክስተት ሆኖባቸዋል።

በርካታ የቪዲዮው ተመልካቾች በወጣቱ ድፍረትና ለእንስሳው ባሳየው ሩኅሩኅነት ሲደነቁ፣ ሌሎች ደግሞ አደገኛ ሊሆን ከሚችል የዱር እንስሳ ጋር እንዲህ ያለ የቅርብ ግንኙነት ማድረግ የሚያስከትለውን የደኅንነት ስጋት በሃሳብነት አንስተዋል።

እናንተ ጨክናችሁ ከጅብ ጋር እንዲህ ታደርጋላችሁ ? ቀጣይ ምን የሚደረገው ይመስላችኋል ? ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ ?

@GhionMaleda
@GhionMaleda
20😁9🥱3🤝3🤬1
3
" ከ2010 ዓ/ም እስከ 2015 ዓ/ም የዲግሪ ተመራቂዎች በሙሉ የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ በድጋሚ ፈተና ሊፈተኑ ነው " በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተና ህዝብ አደናጋሪ ነው።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች (በፌስቡክ እና ቲክቶክ) ላይ የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ያዘጋጀውንና ለህዝብ አስተያየት ይፋ ያዳረገውን አዲስ ረቂቅ መመሪያ በማዛበት....

" ከ2010 እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ የተመረቁ ተማሪዎች በሙሉ የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ ሲባል በድጋሚ ፈተና ሊሰጣቸው ነው " በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ፍጹም የተሳሳተ እና ህዝብን የሚያደናግር ነው።

ህዝብ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፋ የተደረገው መመሪያ በትክክል እነማንን ነው የሚመለከተው ?

ይህ መመሪያ/አሰራር የሚመለከተው በቀድሞው ዲፕሎማ (10+3፣ 12+2 ወይም ቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 ስልጠና) ተመርቀው፣ ነገር ግን የደረጃ አራት የብቃት ማዕቀፍ (COC) ሳይኖራቸው የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ዲግሪ (MA) ወይም ሦስተኛ ዲግሪ (PhD) የያዙትን ብቻ ነው።

እነዚህ ዜጎች የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ አሁን በያዙት የትምህርት ደረጃ/የያዙት ዲግሪን መሰረት ተደርጎ የሚሰጠውን ፈተና መውሰድና ማለፍ ይኖርባቸዋል።

በአጭሩ የሚመለከተው ወይም ተፈጻሚነቱ :-
- ለዲግሪ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) ፈተና ሳይወስዱ ዲግሪ የተማሩ እና የተመረቁ።
- የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) የወሰዱት ለዲግሪ ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የሆኑ ተማሪዎች ላይ ነው።

በመደበኛው መንገድ የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው (ለምሳሌ የ12ኛ ክፍል ማለፊያ አምጥተው) የገቡ፣ ወይም ከዲፕሎማ ተነስተው የCOC ፈተና አልፈው ዲግሪ የጫኑ እና የተመረቁ ዜጎችን ይህ መመሪያ አይመለከታቸውም። የትምህርት ማስረጃቸውም ያለ ምንም ተጨማሪ ፈተና እንደ ቀድሞው ይረጋገጥላቸዋል።

መመሪያው በአሁኑ ወቅት በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለና እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለህዝብ አስተያየት ክፍት የተደረገ መሆኑ ታውቋል።

         T.me/GhionMaleda
           ግዮን ማለዳ
24👏5👍3😁3🤝2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አባብን ይዞ የተገኘው ጠንቋይ በቁጥጥር ስር ዋለ

በቆጋታ ወረዳ ኤዞ ከተማ በተደረገ ክትትል፣ “እባብ” በባንዲራና በእንጨት ላይ ጠምጥሞ በህዝብ መሃል ሲንቀሳቀስ የነበረ አንድ ጠንቋይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል።

ድርጊቱን የታዘቡ የአካባቢው ነዋሪዎችና ህዝብ በሁኔታው በመገረም በከፍተኛ ሁኔታ ድምፃቸውን እያሰሙ አካባቢውን ሲያናውጡት እንደነበር ግዮን ማለዳ ከቦታው የተላከለት ቪዲዮ ላይ ተመልክቷል።

ግለሰቡ ድርጊቱን ሲፈጽም በነበረበት ወቅት የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ያዋሉት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ በህግ እየተመረመረ መሆኑ ተገልጿል።

ወንጀልን የመከላከል ትግላችን ሁልጊዜም ከሕግ ሥርዓት ባልወጣ መልኩ መሆን አለበት። ማኅበረሰቡ መሰል ድርጊቶችን በንቃት ይዞ ለፖሊስ ማስረከቡ የሚበራታታ ቢሆንም ቅጣቱንና ውሳኔውን ግን ሙሉ በሙሉ ለሕግና ለፍርድ ቤት መተው ለነገው ማኅበራዊ ሰላማችን አስተማማኝ ዋስትና ነው።

ህብረተሰቡ ከእንዲህ አይነት አደገኛ እና አሳሳች የጠንቋዮች ድርጊት ራሱን እንዲጠብቅ እንዲሁም መሰል ድርጊቶችን ሲመለከት በአፋጣኝ ለጸጥታ አካላት ሪፖርት በማድረግ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ መልዕክት ተላልፏል።ከዚያ ወጭ የደቦ ፍርዶችን መፍረድ በፍጹም ትክክል አይደለም ።

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda
13👍4🥱4🤣2🤝2🤬1👻1