ይቺን የገጠር ቤተክርስቲያን በዚህ በማህበራዊ ሚዲያ በተጀመረ ንቅናቄ እዚህ ደረጃ አድርሰናታል
በከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ሀገረ ስብከት በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የምትገኘው የጎፎሬ ደብረ መንክራት በአታ ለማርያም ቤተክርስቲያን በእናንተ በውድ ኦርቶዶክሳውያን የሁል ጊዜ ድጋፍና ትብብር የመሠረቱ ሥራና የመቅደሱ አራቱ ኮሎን ተሞልቷል።
እንደምታውቁት ይቺ ቤተክርስቲያን በዚህ በማህበራዊ ሚዲያ በተጀመረ በተጀመረ ንቅናቄ እዚህ ደረጃ አድርሰናታል። ለዚህ ያበቃን ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ለዚህ ለተቀደሰ ዓላማ ሥራው የሚያስፈልገውን በሁሉ አይነት የረዳችሁን ....
እግዚአብሔር ሁል ጊዜ በበረከት በጤና በፍቅር በአንድነት ይጎበኛችሁ እመብርሃን ከዓለም ክፉ ነገሮች ሁሉ ጥላ ከለላ ትሁነችሁ።
ለዚህም ድጋፋችሁ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንዲሁም በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም እያመሰገንን ለቀጣዩ የኮሎን ሙሌትና ለሌሎችም ሥራዎች ...
የተለመደውን ከ10ብር ጀምሮ ድጋፍ በማድረግ የልዑል እግዚአብሔርን ቤት እንዲሁም የበአታ ለማርያም መታሰቢያ ሠርተን በረከተ ሥጋ ወነፍስ እንድናገኝና ለገጠሩ ምዕመናን አለኝታ እንድንሆን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የልገሳ ሂሳብ ቁጥሮች (የህንፃ አሰሪ ኮሚቴ)፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000624326281
አቢሲኒያ ባንክ፦ 240587815
አዋሽ ባንክ፦ 013201006748101
📞 ለበለጠ መረጃና የሞራል ድጋፍ፦ 0933055802 ወይም 0911414852 ደውለው "አለንላችሁ" በማለት ከጎናቸው መሆንዎን ይግለጹ።
በቴሌግራም ገጽ ለማግኘት👉 @degnet0321
#ትኩረት ለገጠር ቤተክርስቲያን

❤21🙏8👍3👏1
ካለህበት የሱስ ወይም የጭንቀት አረንቋ ለመውጣት የምትከተለውን እምነት መቀየር አያስፈልግህም።
በህይወታችን ውስጥ ትልቁ ውጊያ ከራሳችን ጋር የምናደርገው ውጊያ ነው። ብዙ ጊዜ መንገድ ሲጠፋን፣ ህይወት ሲመሰቃቀልብን ወይም በሱስ ማዕበል ውስጥ ስንወድቅ ጥፋቱን ወደ ሌላ ነገር ማላከክ እንወዳለን።
ነገር ግን እውነተኛው ለውጥ የሚመጣው ከውጪ ሳይሆን ከውስጣችን መሆኑን ይሄ ወጣት በተግባር አስመስክሯል።ወንድማችን በቀደመው ህይወቱ እንደ አብዛኞቹ ወጣቶች በሱስ ዓለም ውስጥ ተዘፍቆ....
በዘመናዊ የራስታ ገፅታ (Rastafarian lifestyle) ተፅዕኖ ስር ወድቆና ከነበረበት የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እምነትና ስርዓት ርቆ የኖረ ወጣት ነበር። በብዙዎች ዘንድ "ተስፋ የለውም" ተብሎ ሊታሰብ የሚችል የህይወት ምዕራፍ ላይ ነበረ።
ነገር ግን አንድ ቀን ቆም ብሎ እራሱን መከረ፤ ዘከረም። "ችግሩ ያለው እምነቴ ጋር ሳይሆን እኔነቴ ጋር ነው" ብሎ አመነ። መጥፎ ልምዶቹን፣ አሉታዊ የህይወት ፈተናዎቹን በበጎነት ለመቀየር ወሰነ።
ወደ እናት ቤተክርስቲያኑ ተመልሶ፣ በወንጌል ቃል እራሱን አበልፅጎ እና አድሶ ለትልቅ ክብር እራሱን አበቃ።
ዛሬ ይሄ ወንድማችን ሱስን አሸንፎ፣ ያንን የድሮ ማንነቱን ጥሎ ታላቁ ምስጢር በሆነው በስርዓተ ጋብቻ፣ በቅዱስ ቁርባን ህይወት ውስጥ ገብቶ ትዳር መስርቷል።
በእምነቱ ፀንቶ፣ ክርስትናን በተግባር ኖሮ ለብዙ ወጣቶች ትልቅ ትምህርት እና ተስፋ የሚሆን አርአያነትን አሳይቷል።
ህይወትህን ለመቀየር፣ ካለህበት የሱስ ወይም የጭንቀት አረንቋ ለመውጣት የምትከተለውን እምነት መቀየር አያስፈልግህም። እምነትህ ውስጥ ያለውን እውነት መኖር እና እራስህን መቀየር ብቻ ነው የሚጠበቅብህ!
ግዮን ማለዳ
Joined & Share 👉T.me/GhionMaleda

❤32🤝6💊4👀2🤔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሴዶ ማርሻል እና ጆኒ መንገድ ላይ ተደባደቡ
በጉጉት ለሚጠበቀውና ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀበት ታላቅ ፍልሚያ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው፣ ውልና ፊርማቸውን አጠናቀው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፍለሚያቸውን ለማየት...
የሚጠብቃቸው ሴዶ ማርሻል እና ጆኒ ባልተጠበቀ ሁኔታ መንገድ ላይ ተገናኝተው በቡጢና በትግል መጋጠማቸው ከላይ ከቪዲዮ ተመልከተናል ።
የግጭቱ አጀማመር አስገራሚና አሳዛኝ ነበር። የፌደራል ፓሊስ አጠገባቸው ባለበት ሁኔታ ሴዶ ማርሻል ማህበረሰባዊ አሻራውን ለማሳረፍ ችግኝ ይዞ በቆመበት ሰዓት፣ ጆኒ በቅፅበት ከበስተጀርባው በመምጣት እግሩን ይዞ ለመጣልና ለመቆለፍ (Lock) ጥረት አድርጓል።
ሆኖም ግን በአካባቢው በነበሩ የፖሊስ አባላትና በህዝብ ርብርብ ሳይከፋፈል ሊገላገሉ ችለዋል።
ይህ ክስተት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ከመሆኑ ባለፈ፣ በኢትዮጵያ ስፖርት እና በስፖርተኞች ስነ-ምግባር ዙሪያ ትልቅ ጥያቄ ያስነሳና ስጋትም ፈጥሯል።
በህጋዊ መንገድ መድረክ ተዘጋጅቶላቸው፣ ህዝብ በክብር የሚጠብቃቸው ስፖርተኞች በመንገድ ላይ የጎዳና ላይ ጠብ ውስጥ መግባታቸው ለሙያው ያላቸውን ክብር ያሳንሳል።
ስፖርት ህፃናትና ወጣቶች በአርአያነት የሚከተሉት ዘርፍ ነው። እንዲህ አይነት ድርጊቶች ግን ለወጣቱ ትውልድ የተሳሳተ መልዕክት ያስተላልፋሉ።
ማህበረሰባዊ በጎ ተግባር (ችግኝ የመትከል ስራ) እየተከናወነ ባለበት እና ሰላማዊ ድባብ ባለበት ቦታ ላይ እንዲህ አይነት ጥቃት መፈጸም ፍፁም ተገቢ አይደለም።
ማህበረሰባዊ በጎ ተግባር እየተከናወነ ባለበትና የፌደራል ፓሊስን በመናቅ በሚመስል መልኩ መሰል ችግሮችን መፈጠር ከህግ አኳያስ አያስጠይቃቸውም ? ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ ?
ግዮን ማለዳ
T.me/GhionMaleda

❤25😁15🤪5👻3🤬2
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ያገኙትን የ50 ሺህ ዶላር ሽልማት ወደ ኢትዮጵያ ላኩ
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/ኢየሱስ በየካቲት 2023 ከሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ ያገኙትን የ50 ሺህ ዶላር....
የሽልማት ገንዘብ በትግራይ ክልል በጦርነቱ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶች ድጋፍ ለሚያደርጉ ሁለት ድርጅቶች በሙሉ መለገሳቸው ታውቋል።
ይህ የተበረከተው የገንዘብ ድጋፍ "ማምስ ፎር ማምስ" ለተሰኘው ድርጅትና "የትግራይ ሴቶች ማኅበር" በእኩል መጠን መከፈሉን ሁለቱ ተቋማት ማክሰኞ ዕለት በመቀሌ ከተማ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
ድርጅቶቹ እንደገለጹት የተደረገላቸው ይህ ልገሳ በጦርነቱ ወቅት የፆታዊ ጥቃት ሰለባ ለሆኑና በተለያዩ ምክንያቶች ከባድ ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶች የመልሶ ማቋቋሚያና የዕለት ተዕለት የኑሮ...
መደገፊያ እገዛዎችን ለማቅረብ የሚውል ሲሆን ይህም ተጎጂዎቹ የደረሰባቸውን ቀውስ ተቋቁመው ሕይወታቸውን በአዲስ መልክ መልሰው እንዲገነቡ አቅም ይፈጥርላቸዋል ተብሏል። Via፦ ያፌት ገ/ህይወት

❤28👏8🔥3💊2🙏1🕊1
በአዲሷ ካዛንቺስ መንደር ‼️
የሚመኙት ያማረ ነገዎ እውን ይሆን ዘንድ‼️
👉በካሬ ከ 89,815 ብር ጀምሮ
ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ 80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ 95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ 140 ,160 ካ.ሜ
✍ ቅድመ ክፍያ 15%
❇️ በ አጭር ጊዜ የሚረከቡት 💁
📍በግቢው ውስጥ
➾ ት/ቤት እና የጤና ማዕከል
➾ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ ሜዳወች
➾መዋኛ ገንዳ
➾የሳይክል እና የእግር ሽርሽር ስፍራዎች
➾ሰፊ የመኪና መቆሚያ ከ24/7 ጥበቃ ጋር
➾የመኪና ቻርጀር ስፍራዎች እና የንግድ ሞል
📍በግቢው ዙሪያ
➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
➾የእምነት ተቋማ እና
አለም አቀፍ ሆቴሎች
📍የቤቶቹ እይታ
➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ
❇️ ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።
ፈጥነው በመወሰን የትርፋማነቱ ተጠቃሚ ይሁኑ📞 ይደውሉ 0911-63-67-90
Channel: t.me/addis_home_finder
Telegram : @kassu23
በ WhatsApp ማግኘት ከፈለጉ
https://wa.me/251777636790

👍4❤3🤔1🤝1
"ከዚህ የፓርላማ ተሳትፎዬ ማጠናቀቂያ ማግስት ራሴን ከማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ አግልያለሁ።" -ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ-
ታዋቂው ፖለቲከኛ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ የፓርላማ ቆይታቸውን መጠናቀቁ ተከትሎ ከቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ።
ዶክተር ደሳለኝ ባለፉት 10 ዓመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባሕር ዳር ከተማ መራጮችንና የሕዝብን ድምፅ በመወከል በንቃት ሲሳተፉ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።
በዚህም በማኅበረሰብ አገልግሎት፣ በጣና ሐይቅ የእንቦጭ አረም መከላከል አክቲቪዝም፣ በፓርቲ ምስረታ እና በፓርላማ አባልነት የነበራቸውን የትግል ምዕራፍ በስኬት ማጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።
የፓርላማ አባሉ ባስተላለፉት መልእክት፣ እጅግ አስቸጋሪ በነበሩት ዓመታት ፍርሃትን አርቆ ጽናትን ለሰጣቸው ለልዑል እግዚአብሔር እና ለቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና አቅርበዋል።
በተለይም የባሕር ዳር ከተማ መራጮቻቸው ላሳዩአቸው ድጋፍና ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በፊት ለ45 ቀናት በታሰሩበት ወቅት በጸሎትና በሐሳብ አብረዋቸው ለነበሩ ወገኖቻቸው በሙሉ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
ለጋዜጠኞች፣ ለምክር ቤት አባላትና ለቅርብ የትግል አጋሮቻቸው ምስጋናቸውን ያካፈሉ ሲሆን፣ በትናንትናው ዕለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ «አብረን እንስራ» በማለት ላቀረቡላቸው ጥሪና በበጎ ጎኑ ለገለጹላቸው አስተያየት አክብሮታቸውን ገልጸዋል።
የፓርላማ አባሉ የወደፊት የሕይወት አቅጣጫቸውን በተመለከተ ፤ በሙያቸው (በአካዳሚክስ) ሀገራቸውን ማገልገላቸውን እንደሚቀጥሉ በአዳዲስ...
የሥራ ውጥኖች (Startups) ላይ በስፋት እንደሚሰማሩ፣ ለቤተሰቦቻቸው በቂ ጊዜና ትኩረት መስጠት እንደሚፈልጉ በይፋ አስታውቀዋል።
ዶ/ር ደሳለኝ፣"ከዚህ የፓርላማ ተሳትፎዬ ማጠናቀቂያ ማግስት ራሴን ከማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ አግልያለሁ።ለጊዜው በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ በአባልነትም ሆነ በደጋፊነት የማልሳተፍ መሆኑን በይፋ አሳውቃለሁ" ብለዋል።
ፖለቲካዊ ተሳትፎአቸው ቢያበቃም፣ የአማራን ሕዝብ አንድነት በሚያጠናክሩ፣ የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ያለውን አብሮነት በሚያሳድጉ፣ እንዲሁም...
የኢትዮጵያውያንን ኑሮ በሚያሻሽሉ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሙያቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም፣ ለእውነተኛ ብሔራዊ ውይይትና እርቅ ያላቸው መሻት አሁንም ጽኑ መሆኑን በመግለጽ፣ አዲሱ የ2019 ዓ.ም የሰላምና የፍቅር ዘመን እንዲሆን ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

Telegram
Ghion Maleda
እንኳን ደህና መጡ !
ማስታወቂያ ለማሰራት 👉 @GhionMaleda13
ቴሌግራም ቻናሉን ለመቀላቀል👉@GhionMaleda
ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/GhionMaleda
ደግና ቅን እንሁን ❤🙏
ማስታወቂያ ለማሰራት 👉 @GhionMaleda13
ቴሌግራም ቻናሉን ለመቀላቀል👉@GhionMaleda
ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/GhionMaleda
ደግና ቅን እንሁን ❤🙏
❤25👍7🙏3👏2👎1
የራሳቸውን ሽንት በመጠጣት ህይወታቸውን ያቆዩት ጥንዶች
የራሳቸውን ሽንት በመጠጣት ህይወታቸውን ያቆዩት ጣሊያናውያን ጥንዶች በዶሎማይት ተራሮች ለስድስት ቀናት ከጠፉ በኋላ በህይወት ተገኝተዋል ።
እንደ "ኢል ሬስቶ ዴል ካርሊኖ" መጽሔት ዘገባ ከሆነ ዳቪዴ እና ቺያራ የተባሉት እነዚህ ጥንዶች፣ በጉዟቸው ላይ መንገዳቸውን ስተው ጥቅጥቅ ባለው የጥድ ደን ውስጥ ቆይተዋል።
ቅዝቃዜውን ለመቋቋም ከዛፍ ቅጠሎችና እንጨቶች ጊዜያዊ መጠለያ የሰሩ ሲሆን፣ ምግብና ውሃ በመራቃቸው ጉልበታቸውን ለመቆጠብ ካሉበት ሳይንቀሳቀሱ የነፍስ አድን ቡድን እስኪመጣ ጠብቀዋል።
በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥም የዱር ፍራፍሬዎችን በመመገብ እና በመጨረሻም ትንሽ ምንጭ እስኪያገኙ ድረስ የራሳቸውን ሽንት በመጠጣት ህይወታቸውን ለማቆየት ተገደዋል።
የጥንዶቹ መጥፋት ከቀናት በኋላ ለባለስልጣናት ሪፖርት የተደረገ ሲሆን፣ ፖሊስ እና የተራራ ነፍስ አድን ቡድኖች ባደረጉት ከፍተኛ ፍለጋ ዛሬ ጠዋት ሊያገኟቸው ችለዋል።
ጥንዶቹ በወቅቱ በጣም ደክመው የነበረ ቢሆንም በጥሩ የአእምሮ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።ባለሙያዎች ግን የሰውነትን ድርቀት የሚያባብስ በመሆኑ ሽንት መጠጣትን ፈጽሞ እንደማይመክሩ አስታውቀዋል። Via፦ ፌደል post
እርስዎ መሰል ችግሮች ወይም ለህመምዎ መዳኋኒት የራሳችሁ ሽንት ቢሆን ይወስዱታል ? ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አካፍሉን እስኪ ?

❤17🤣6🙏4🥱2🤪1
መንገድ ላይ ተጥላ ያገኘቻትን ህፃን ጡት እያጠባች ከራሷ ልጆች ጋር እኩል እያሳደገች የምትገኝ እናት !
ይህች ከላይ በምስሉ የምትመለከቷት እህታችን የትራፊክ ፖሊስ ሙሉጎጃም ትባላለች። እንደምትመለከቷት ያቀፈቻትን ህጻን በአንድ ወቅት በባህርዳር ከተማ ከገጠር መንገድ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ይቺን ህፃን ተጥላ ስታገኛት በዚያ ወቅት ጡቷቿን በማጥባት ለጊዜው ህይወቷን ታድጋ ነበር ።
ይሄ ጉዳይ በተፈፀመ ሰምን ግዮን ማለዳ ተከታታይ ዘገባ ሰርተን ነበር። በመቀጠልም "እኔ አሳድጋታለሁ" ብላ በሕጋዊ መንገድ ህፃኗን ተረክባ እናቷ ሆነች።
ጡት እያጠባች፣ ከራሷ ልጆች ጋር እኩል በፍቅር እና በእንክብካቤ እያሳደገቻት የምትገኝ እውነተኛ ጀግና ናት ። ይህች ጀግና የትራፊክ ፖሊስ ልባዊ ምስጋና፣ ክብር እና ትልቅ ድጋፍ ይገባታል ። አብዛኛውን ጊዜ ባህርዳር ዲፖ አካባቢ ትገኛለች።
የበጎ ተግባሯን ለብዙዎች በማጋራት እና #ሼር በማድረግ ለሌሎችም አርአያ እንድትሆን ማድረግ ይገባናል ። እንዲሁ አይነት ደጋጎችንና ርህራሄ ያላቸውን ሰዎች ፈጣሪ ያብዛልን 🙏

❤60🙏14💔4🔥3👏2🥱1😭1💊1
በትዳር ከተጣመሩ በኋላ ከጫጉላ ቤታቸው ቀጥታ ወደ 12 ክፍል ፈተና ማዕከል በማቅናት የተፈተኑት ጥንዶች
በ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና ከሚወስዱ የኮንሶ ዞን ተማሪዎች መካከል፣ በትጋት፣ በጽናትና በቁርጠኝነት ለሌሎች ተማሪዎች አርአያ የሆኑ ተፈታኞች ይገኛሉ።
እነዚህ ተማሪዎች የትምህርት ዕድሜ ወይም የቤተሰብ ኃላፊነት ለትምህርታቸው እንቅፋት እንዳይሆን በማድረግ ሌሎችን የሚያነሳሱ ምሳሌዎች ሆነዋል።
አዲስ ተስፋዬ እና ዳዊት ጉራሾ በትዳር ትስስር ከተጣመሩ በኋላ፣ ከጫጉላ ቤታቸው ቀጥታ ወደ ፈተና ማዕከል በማቅናት ትምህርታቸውን ለማሳካት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ከኮንሶ ዞን ኮልሜ ወረዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጡት በረከት ታሪኩ እና እንግዳነች ዳባ እናትና ልጅ ሲሆኑ፣ በአንድ ጊዜ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ መዘጋጀታቸው ለብዙዎች አስደናቂና አነቃቂ ተሞክሮ ሆኗል የግዮን ማለዳ ቤተሰቦች ።
ኮንሶ ዞንም እነዚህን በትጋትና በጽናት የተሞሉ ተማሪዎች በመኩራት፣ በመጪው ፈተና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መልካም ምኞቱን ገልጿል። ግዮን ማለዳ መረጃውን ያገኘው ከኮንሶ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው።
ጥንዶች ወደ ከፍተኛ ተቋም (የዩንቨርስቲ) መግቢያ ውጤት ያመጡ ይሆን ? ውሳኔያቸውን እንዴት አያችሁት ? ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ?

❤16🤣5👏2🥱1👻1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update
በሮቤ ከተማ አስተዳደር አዶሼ ክፍለ ከተማ ሮቤ የተሽከርካሪ መናሕርያ ውስጥ አንድን የጤና ባለሞያ ከላይ በቪዲዮ እንደምታዩት በደቦ የደበደቡ ወጣቶች በእስራት ተቀጡ።
እንደ ሮቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሐላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ጌታቸው ታምሩ ገለፃ፦
1ኛ ሱልጣን ሑሴን ፣ 2ኛ ኢብራሔም ሑሴን እና 3ኛ ቦንሣ አወሉ የተባሉ ተከሳሾች የአንደኛ ተከሣሽ የእጅ ስልክ ጠፋ በሚል ሠበብ በአንድ የጤና ባለሞያ ላይ በደቦ ከፍተኛ ድብደባ በማድረስ የአካል ጉዳት አድርሰዋል።
ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓም ከጥዋቱ አንድ ሠዓት ተኩል ላይ አሮጌው መናሕርያ ውስጥ የጊኒር ከተማ ጤና ፅህፈት ቤት የጤና ባለሞያ የሆኑትን ዋቆ ከድር የተባሉትን የአንደኛ ተከሣሽ ሞባይል በመጥፋቱ ወስደኃል በሚል ያልተረጋገጠ ማስረጃ በቡድን ተደራጅተው የድብደባ ወንጀል ፈፅመውባቸዋል።
ባልተጣራና ባልተረጋገጠ ጉዳይ በመቀናጀት የፈፀሙት የድብደባ ወንጀል በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ቁጣ ማስከተሉ ይታወሳል፡፡
አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በውንብድና ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን የተመለከተው የሮቤ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት....
ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት እያንዳንዳቸዉን በሁለት ዓመት ከሶስት ወራት እስራት ተወስኖባቸዋል ። ግዮን ማለዳ መረጃውን ያገኘው ከሮቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምርያ ኮሙኒኬሽን ነው ።

❤19👏2👎1🔥1😁1
ለራሱ ምርቃት የተገዛው በሬ ወግቶት ህይወቱ ያለፈው ተመራቂ !
በቅርቡ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ዘርፍ በታላቅ ስኬት ተመርቆ፣ ለነገው ህይወቱ ትልቅ ተስፋ ሰንቆ የነበረው ፍሰሐ አስማማው እጅግ ልብ በሚሰብር አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ይህ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ከሳምንት በፊት ነበር የምርቃት ካባውን የደረበው። ወላጆችና ዘመድ አዝማድም የምርቃቱን ደስታ አብረውት ለማሳለፍ ከጎንደር ጋይንት (ጎብጎብ) ከተማ ወደ ተወለደበት አካባቢ ይዘውት አምርተው ነበር።
ነገር ግን በትላንትናው ዕለት ለምርቃቱ ድግስ ተብሎ የተገዛው በሬ በድንገት ወግቶት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
የዚህ ወጣት ስኬትና ህልም በአጭር የተቀጨበት አሳዛኝ የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ በጋይንት ጎብጎብ ቀራኒዮ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የክፍል ጓደኞቹና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት ተፈፅሟል።
አንዳንድ ሀዘኖች ለመግለጽ ቃላት ሁሉ ይጠፋል እናቱ አባቱን ምን ተብሎ ማፅናናት ይችላል ? ብቻ ሕይወት እንድህ ነች እሩቅ ስናስብ በአጭር እንዲሁ መቅረት💔 😭
ለወላጆቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለጓደኞቹ በሙሉ ፈጣሪ ፍጹም መፅናናትን ይስጥልን። የወንድማችንን ፍስሐ ነፍስ በአፀደ ገነት ያሳርፍልን። #RIP
Via፦ ጉርሻ

💔37😭33❤9👍3🤬1🥱1
ለእናቱ የገባውን ቃል ለመጠበቅ አስክሬን ቤት አስቀምጦ ለተፈተነው ታዳጊ ካሊድ ቃሲም የመኖሪያ ቤት ሊገነባለት ነው::
ከሦስት ሳምንታት በፊት እናቱ ባረፉበት ዕለት የገባውን ቃል ለማክበር ሲል አስክሬን ቤት ውስጥ ትቶ የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተናውን በመፈተን መላውን የሀገሪቱን ሕዝብ በከፍተኛ ሐዘን ያስለቀሰውና ያስደመመው ታዳጊ ካሊድ ቃሲም፣ አዲስ የመኖሪያ ቤት ሊገነባለት መሆኑ ተሰማ።
በሸገር ከተማ አስተዳደር ኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ ከሁለት ታናናሽ ወንድሞቹ ጋር የሚኖረው ይህ የ14 ዓመት ታዳጊ፣ በወቅቱ እናቱ በጽኑ ታመው በነበሩበት ወቅት “እኔ አንድ ነገር ብሆን እንኳ ለዓመታት የለፋህበትን ፈተና እንዳታቋርጥ” በማለት ያስገቡትን ጥብቅ ቃል ለመጠበቅ የጠዋት ፈተናውን ተፈትኖ፣ ከሰዓት ደግሞ እናቱን አልቅሶና ቀብሮ በመመለስ የከሰዓት ፈተናውን ማጠናቀቁና “ቃልሽን አላጠፍኩም እማ!” ማለቱ ይታወሳል።
ዛሬ በተሰማው አዲስና ተስፋ ሰጪ መረጃ መሠረት፣ ለታዳጊውና ለታናናሽ ወንድሞቹ ቋሚ የቤት መፍትሔ ለመስጠት የሸገር ከተማ የኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለቤት ግንባታ የሚሆን መሬት በይፋ አዘጋጅቶ አስረክቧል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የመኖሪያ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ገንብቶ ለታዳጊዎቹ ለማስረከብ ቃል ገብቷል።
ወላጅ አባቱ ከእነርሱ ርቆ በጅጅጋ ከተማ ሌላ ትዳር መሥርቶ በመኖሩ ምክንያት እናታቸውን አጥተው ብቻቸውን ለቀሩት ለእነዚህ ወንድማማቾች የተደረገው ይህ የመሬትና የቤት ግንባታ ድጋፍ፣ የታዳጊውን ታማኝነትና ብርታት ያከበረ እንዲሁም ማኅበራዊ አጋርነትን በተግባር ያሳየ መሆኑ ተገልጿል። -Via FastMereja

❤36👍8👏4🙏3💔1🤝1