ግጥም ብቻ
2.88K subscribers
107 photos
9 videos
6 files
71 links
የፍቅር_ግጥሞች
የፍቅር_ታሪኮች
የሙዚቃ_ግጥሞች
የተለያዩ_ግጥሞች
ጠቃሚ_መረጃዎች/አዲስ_ነገር
ቻናላችንን join በማረግ ይቀላቀሉን
@Getem0

ለማንኛውም አስተያየት/ግጥም ለመላክ
@dada_KL
@dada_KL
Download Telegram
አንድ እንጀራ ለኛ
◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦
ⓜⓡ◦ ⓣⓡⓤⓜⓟ
ቅንነት በሐበሻ ደግነት በደሙ
ከልጆች አንደበት ከልብ ከሰሙ
በልጅነት ቀመር ባፍላነት ጨዋታ
የተሰመረልን አለን አንድ እይታ
"ወደ ቤት ወዳገር ቤት
አንድ እንጀራ ለኛ ሌላው ለጎረቤት"
በልጅነት አለም ቤትና ሃገር ቤት
አንዳች ምስጢር አለው አንዳች ድብቅ እውነት
እንደዛሬ ሳይሆን
ልምጭ ቆራጭ መዳፍ እንዳሰመረልን
ከክልል ወደዛ ከክልል ወደዚ እንዳከፋፈለን
አይደለም ምክንያቱ ወደቤት ያልንበት
ቤትና ሃገር ቤት በልጆች ልቦና በህብረ ዝማሬ
ዞረው ሚገቡባት የሁሉም መኖርያ ጎጆ ናት ሃገሬ
ደሞም በልባቸው
ካንድ እንጀራ በላይ
አይደለም ልካቸው
መሶብ ሙሉ እንጀራ ቢሞላም በቤቱ ቢትረፈረፍለት
አንድ እንጀራ ወስዶ ያወጣል ከቤቱ እሱ እንዲጠግብለት
እሱ ጠግቦ አድሮ ሳይበላ የሚያድረው ጎረቤት አለበት
በጥሞና ሆነው ከተመረመረ
ለካስ አዋቂ ነው ስራት የደለዘ መስመሩን የጣሰ
መሶብ የሚያራግፍ ስግብግብ ህሊና በላዩ ያነገሰ
ለካስ አዋቂ ነው ከህፃናት ያነሰ
ደሞም ሲያስተውሉት
ግዜ ተንሸራቶ ህፃን ሲጎለምስ ልጅነት ሲረሳ
ያገር ቤት ዝማሬው ካፉ ላይ ተረሳ
በምትኩ ዛሬ መስመሩን አክሮ
ዘውትር የሚለውለው አለው እንጉርጉሮ
"ወደቤት ወደቤት ወደክልል ቤት
አንድ እንጀራ ለኛ ዱላ ለጎረቤት"።

@getem0
#ለኔና_ለነሱ
◦◦◦◦◦◦◦◦◦
ⓜⓡ◦ ⓣⓡⓤⓜⓟ

የቅፅበት ሽራፊ ድቃቂ ደቂቃ
እልፍ ናት በቤቴ አንዲቷ ጨረቃ
ምክኒያቱም በኔ ውስጥ...
ድንጋይ የሚሰብር
ውሀን የሚገትር
አየር የሚቋጥር
ንፋሱን የሚያስር
አለ ብዙ መውደድ አለ ብዙ ፍቅር።
ለነሱና ለኔ
የሰማይ ስፋቱ ያለም እርቀቱ
የመምጣት ትርጉሙ የመሄድ ክብደቱ
የቀን መጨለሙ የለሊት መንጋቱ
ለነሱ እና ለኔ ሌላ ነው ውበቱ
ሌላ ነው ሚስጥሩ ሌላ ነው ግኝቱ።
ለኔና ለነሱ...
አንድ አይነት ደመና ቢያጉረመርምብን
አንድ አይነት ጨለማ ነግቶ ቢመሽብን
አንድ አይነት ሌጊዎን ቢፈትነን እንኳ
እሾህ ቢወጋንም አንድ አይነት አረንቋ
አንድ አይነት ቢሆንም መውጣት መግባታችን
ቢመሳሰል እንኳ መሞት መኖራችን
ለየቅል ነው ፍቺው ለነሱና ለኔ
ሁሉም ለበጎ ነው አለሽና ጎኔ
እንደውም
ከቃላት መካከል ለበጎ የሚለው ቃል
ለነሱና ለኔ ሁለት ቃል ይሰጣል
(ምሳሌ ልንገርሽ ምሳሌው ይቀላል)
ከቀናት ባንድ ቀን ፀሐይ ብትበተን ከሰማይ ላይ ወድቃ
ምድርና መላዋን ጨለማ ቢውጠን ብትከስም ጨረቃ።
ለነሱ...
ያምላክ እርግማን ነው ወይ ያለም ፍፃሜ
ነስሁ የሚል ቃል የጌታ ቅያሜ
ለኔ ግን....
ፀዳሉ አካልሽ የሚያሳሳ ገፅሽ
ፀሐይ እንዳይጎዳው እንዳይደርቅ ውበትሽ
ሰካራም ወልጋዳ ሲጨላልም ወጪ
አንቺን እንዳያይሽ ካለሽበት ወርደሽ ምድር ተቀመጪ
ተብላ ነው ጨረቃ እላለው ለራሴ
ተቀድሷል አንዴ በፍቅርሽ መንፈሴ
(በዚ አያያዜ)
ምን አልባት አይቀርም ሞቼ መበስበሴ
(ግን እንደው አለሜ)
እሱም ለበጎ ነው ካካሌ መፍረሴ::

@Getem0
"ጠብቄሽ ነበረ"
ብር ተበድሬ
ሙታንቲ ቀይሬ
ፀጉሬን አጎፍሬ
ፂሜን አበጥሬ
ገላዬን ታጥቤ ፣ ነውሬን ተላጭቼ
ጫማዬን ወልውዬ ፣ ገበሬን አፅድቼ
አዲስ ካልሲ አጥልቄ ፣ ሽቱ ተቀብቼ
ጠብቄሽ ነበረ
በቅዳሜ ዋጋ
ተከራይቼ አልጋ ።
ስትቀሪ ጊዜ
ሰክሬ ልረሳሸ ፣ በብስጭት ወጣሁ
ራሴን እስክስት ፣እስክሰክር ጠጣሁ ፣
ጠጣሁ
ጠጣሁ
ጠጣሁ
አላስታውሰውም
አልጋ ቤቱ ድረስ ፣ ከማን ጋ እንደመጣሁ፡፡
አልኮል አልኮል ምትል ፣ እቺ ደሞ ማናች
አትጠራጠሪ...
ስትቀሪ ጊዜ ፣ ምትመጣ ሴት አለች፡፡
@getem0
መርዝ ጠጣህ አሉኝ

በመርዝ የማይምቱ ፍጥረታት በሙላ
በውስኪና በጠጅ ባረቄ በጠላ
በካቲካላ መርዝ ሆዳቸው እየሞላ
መርዝ ጠጣህ አሉኝ
ጥዋት በማለዳ ከቤት እኩል ወጠን
እኩል ሌትር መጠን
እነሱ አስር ጣሳ ጠላቸውን ግተው
እነዛም በጠርሙስ አረቄ ተወግተው
እኔ ሁለት ጠርሙስ ፀበሉን ጠጥቼ
መርዝ ጠጣህ አሉኝ
በአፋቸው ገደሉኝ
በአልኰሉ ስካር በዞረ ናላቸው
በኮልታፋ አፋቸው
ትሞታለህ አሉኝ
ከቤት እኩል ወጠን
እኩል ሌትር መጠን
እኔ ከፀበሉ እነሱ ከጠላው በጠዋት ጠጥተን
መርዝ ጠጣህ አሉኝ መፅደቅን አልሜው
መቼስ እብዶች መሀል ጤነኛ ሰው ቢገኝ እብድ ነው ስያሜው



Dani yop

@getem0
@getem0
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ(ልዑል ሀይሌ)
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
መንገድ ጥረጊልኝ
ይህቺን ብቻ አርጊልኝ!
.
ስምሽን እያነሱ
እንዳያስታውሱኝ
በሞተው ትዝታ
እንዳይቀሰቅሱኝ
ያንቺ አለመሆኔን
ዛሬ እንዳሳያቸው
ጨረቃን ፀሐይን
ምድር አውርጂያቸው
ውቅያኖስ ባህሩን
ሰማይ ስቀያቸው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
የረገጥነው አስፋልት
የሄድንበት መንገድ
ያ ያለፈው ፍቅር
ያ ያለፈው መውደድ
ፍፁም ውሸት ብዬ
እንድሸመጥጠው
ተፈጥሮን አዛቢ
መውደዴን እንድተው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ገደሉን ሙዪና
ተራራውን ናጂው
ደመናን አውርደሽ
አፈሩን ውሰጂው
የረገጥሽው መሬት
አምሮ እንድታይበት
በአበባው ፋንታ
ሳማ ትከይበት
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ያ ሁላ ቃል ኪዳን
ተበትኖ እንዲቀር
አይጥ ሀይቅ ትዋኝ
ዓሳ ሰማይ ይብረር
በህይወት ባሉት ምትክ
ሙታኖች ይነሱ
ነገስታት ይውረዱ
ባርያዎች ይንገሱ
.
ይሄን ካረግሽልኝ
መውደዴን ይቅርና
መኖር አቆማለሁ
በመኖር ብረሳሽ
ባለመኖርም ውስጥ
አስታውስሻለሁ

@getem0
@getem0
ደግሞ ማለም ምን ያደርግና?
------------------------
ያልተወለደ ሕልም መቼ ይወደድና
በተረገዘ ሕልም ይሄው ታመምኩና
ከምን መጣው ብሎ አባቱን አማና
ዕህ ብሎ ዋለ አላድርም ይቅርና

ብረሳው እሣት ነው ባስበው በቆመጥ
አባት አረፍ ሲሌ እናትን በረመጥ
ያልተወለደ ሕልም መቼ ይወደድና
የተወለደ ሕልም እንዴት ይረሳና

እንኳን አባት ቀርቶ እናትም ሆንኩና
በኔ ስም ይጠራል አባት ተረሳና!

@Johny_Debx 🙏👆ገጣሚ
@getem0
ሃሳብና ቁስል
ብሩኬ(የወይን ፍሬ)
_________
አንድ ስግር ሃሳብ ይወዘዉዘኛል
ከአፈር ከድንጋዩ ጥሎ ያዛምዳል
ከአንቺነትሽ ጥርጊያ ወስዶ ይጥለኛል
መወዝወዝ ከንቱ ነዉ አቋመ ቢስ መሆን
ከጥላ የረገፉ ጥላ አልቦነት ማግነን
ከመጠረግ ሳንኳ ቀልብ አጥቶ መማሰን
ዲዳ ነዉ ሃሳቤ መናገር አይሻ
ቀዉላላ ቅዠቴን ወሮታል ጥቀርሻ
ሌላ ስግር ሃሳብ ከፈረስ ላይ ጣለኝ
ኮርቻ የሌለዉ እኔነቱ ነዳኝ
ቼ ቼ ቼ ………ቼ ፈረሴ
ልኑር ለኔነቴ ልኑር ለመንፈሴ
ብሎ ያሽሟጥጣል መከረኛዉ ነብሴ
ሌላ ስግር ሃሳብ ከታንኳ ላይ ጣለኝ
ጨዋማ ዉሃ ላይ ትዝታ አተከነኝ
የልጅነት ዘመን ኩኩሉ ኩኩሉ
የአፍላነት ፍቅር ብልቃጥ መኮልኮሉ
የለጋነት እድሜ በታንኳ ሲንጋሸሽ
ያላረጀች ጀንበር ጥላኝ ከኔ ስትሸሽ
እሱንም አያለሁ በመንታ ትዝታ እብሰከሰካለሁ
የኗሪዎች አስቀኒ አዉራ ሟች ሆኛለሁ
ሌላ ስግር ሃሳብ ጨረቃ ላይ ጣለኝ
ለብዙ አፍቃሪዎች ትዕይንት አደረገኝ
ከትዝታ በፊት ትዝታ ሳይመጣ
እንዲህ እንደ ዛሬ ፍቅር ሳይቀናጣ
ጨረቃ እያየችን ከንፈር ተሳሳምን
ኮከብ እየቆጠርን ኮከብ ተሰጣጠን
የአንድ ምሽት ፍቅር ዘመን አሻገረን
የቅናቱ ንጋት ዳግም አካካደን
ትዝታ ፈረሱን ልጓሙን ያዝኩና
ያለያየንን ጀንበር ልርገም እንደገና
እኔ ጨረቃ ላይ አንቺ ከመሬቱ
ከሌላ ወንድ ጋር ከንፈር መጓተቱ
ኮከብ ስትቆጥሩ ስትከፋፈሉ
የአንድ ምሽት ግምጫ ፍቅር ነዉ አትበሉ
ያ ስግር ሃሳቤ ብሽቅጥቅጥ አለና
ፈረሱም ከገደል ታንኳዉም ሰመጠና
እኔም ከጨረቃ ተፈነገልኩና
ስግሩን ሃሳቤን ሻርኩት ቆሰልኩና
ከበፊቱ በፊት ሃዘን ከሰዉ ቢበልጥ
መዝለል ነዉ ትዝታን ቁስሉን ባለመላጥ።

መጋቢት 22-2011ዓ.ም
እሁድ 10:30 d/b

@getem0
@getem0
**** እኔ አንተን ስወድህ****
ልክ እንደ ጠዋት እንቅልፍ
ሰመመን የቃጣው
በአእዋፍ ዜማ የታጀበው
የካህናት ወረብ
ፅናፅል የሞላው
ልክ እንደ ሰማይ ጥግ
ፈክቶ እንደሚበራው
እንደ ምስራቅ
ሰማይ ጨረር የጋረደው
እንደ አዲስ ተስፋ
፣፣፣እኔ አንተን ስወድህ፣፣፣

እንደ ቀትር ፀሀይ
ውሎ እንደሚጣፍጥ
የማለዳ ጀምበር
ለመምሸት የሚያምጥ
እንደ ምሳ ሰአት
ደግሞም እንደ መቅሰስ
አንድ ላይ አጣምሮ
ጉራሽ እንደመቅመስ
ልክ እንደዛ ምሳ
ፍቅር እንደሞላው
የአብይ ፆም ውሎ
አስሮ እንዳሰቃየው

።።።እኔ አንተን ስወድህ።።።

አብረን እንደመሳቅ
ደግሞም እንደማልቀስ
የአንድነት ዋዜማን
አብረን እንደመቁረስ
ምሽት ላይ ተጋግዘን
ዘመን እንደመድረስ
በእሳት በውሀ
በባህር መዋኘት
በውህደት አለም
ባንድ መገናኘት
ምድር ስትሞሸር
ፅሀይ ስትዘቀዝቅ
ኮከቦችን ማየት
ጨረቃንም ማድነቅ
እኔ አንተን ስወድህ
ጠዋትና ማታ ሁሌ ማስታውስህ

ምሽት4:25 አ አ

Jerry dimple

@getem0
@getem0
ኡደት
""""""

ፈጣሪ ሸመነ
አንድ ሁለት እያለ ምድርን አሳመረ
ህይወትን አደለ ሁሉንም ፈጠረ
ነፍስን ከስጋ ጋር በፍቅር አቆራኘ
ለስጋ በምድር ምግብን አናኘ።
(ሰውም ይሄን ሲያገኝ)
ለእውነት መኖር ትቶ ለሆዱ አደረ
ጥጋብን ወደደ ስለ ሰው ችላ አለ
የከሲታዎች ሞት
በአንድ ቦርጭ ውስጥ ሆነ
(እንዲ ነዋ ቅሉ)
የሰው ልጅ ከእንስሳ በሀሳብ ቢልቅም
ሆዳም ሰው ሆድ እንጂ ፍቅርን አያቅም
ደፍ ደፏን ያስባል በሀሳብ አይመጥቅም
እሩቅ.... አያስብም!

*
ፈጣሪ ቀረፀ
ተፈጥሮ ላይ ጀጋኝ ሞትን አሰረፀ
በሞቱት መተኪያ ህይወትን አነፀ
በሞት ነፍስን አዛኝ ባደረጋት አፍታ
ሀዘንን አሳ'ጥቶ ሰጣት ለደስታ።
(ሰውም ይሄን ሲያገኝ)
ደስታው ቅጥ አጣና
ለስሜቱ ኖሮ ይሰፈር ጀመረ በፈጣሪ ቁና
ልኩን መያዝ ትቶ እግዜር አስከፋና
ይከተል ጀመረ የሲኦልን ዳና!

(እንዲ ነዋ ቅሉ)
የተደሰተ ሰው ልቡ ጮቤ ይረግጣል
የረጋችን ሰማይ
እግሩን አንፈራጦ አሻቅቦ ይመታል
በደስታው ሲሰክር ፈጣሪን ይረሳል
ፈጣሪን ሲረሳ
ከኔ በላይ ጌታ እያለ ይፎክራል።

*
ፈጣሪ ጠረበ
የሰውን ባህሪ ሁሉን አነበበ
ለሰው ነፍስ ማደሻ ተክልን ተከለ
በዚም አላበቃም አእዋፍን ፈጠረ
(ፈጣሪ ጠረበ)
የሰውን ባህሪ ሁሉን አነበበ
ትንሽ እንዲፈራ አውሬን አሰፈረ
ትንሽ እንዲጀግን ብልጠትን አደለ።
(ሰውም ይቺን ሲያገኝ)
በኖረው ብልጠት ላይ ጭካኔን ዘራበት
ፍቅርን ሰላም ትቶ ፀብ አበቀለበት
ብልጠቱ በዛና ግፍ ደራረበበት
ሚዛን ተዛባና ፍርድን አጓደላት

(እንዲህ ነዋ ቅሉ)
በግ በጅልነቱ ተገፍቶ እየኖረ
የፍየል ብልጥነት
ከግራ አዋላት ምንም አልጠቀመ
ምላሷም አልበጃት ጩኸት ብቻ ሆነ!

***
ፈጣሪ ጠረበ....አነፀ....ገነባ
የተፈጥሮን ኡደት ከነጋ ከጠባ
አንድ ሁለት ብሎ ፈካ እንደአበባ

(ግን ይቺን ሲያገኙ)
አንዳንድ ያልታደሉ
የፈጣሪ ፍጥረት ተፈጣሪ ሆኑ
በእግዜር ታለፉና በሰው ተፈጠሩ

(እንዲያ ነዋ ቅሉ)

በፈጣሪ ማሳ ሰው ክፉ ማብቀሉ
ረግጦ የገዛን ቆሞ መሸለሙ
ጭካኔ ያለው ሰው በሰው መታበሉ
አረም እና እህል አንድ ላይ መብቀሉ

(እንዲያ ነዋ ቅሉ...እንዲያ ነዋ ቅሉ)

አብርሃም

@getem0
@getem0
የተሠበረ የራቁት ፍቅር

#Johny_Debx
"""""""""፠"""""""""፠"""""""""
ስኖር የወለድኩት ሣልኖር ያልደረስኩት
ሳብ አድርጌ ጎተት መች ወጣው አየሁት
ሳምግ ስመግ ቢለኝ?
.......ኧረ ወደላይ ነው~
.......የራቁት ሩቅ ነው!

መውደድ የት መሀላው በጸሎት ለዋለ፣
በገዜ ዕርምታ ቆይ ልሂድ ና ልምጣ ዕየማለ
ደስታ ተራራ ነው ግን ደረስክ ከስሩ፣
ና ውጣ ይለኛል 'ስደርስ' ለሹሩሩ !

ፍቅር የደገሠው'
ለችግር የዳረው;
ሀሳብ ዕሷን ማየት፡
ረጅም አለንጋ የተረረ መሬት፡፡
ግና?
ግርፊያው መች ተጠላ ተኩሱ ወደታች
ጠመንጃ ወዳጅ.............. ተፈቃሪ ነች !
ታዲያ ~
ወዲያ~

ከዚህ በላይ ፍቅር
ከዚህ በላይ ችግር
ኧረ ዕንዴት ይረሳል ፣ ኧረ የት ይገኛል!
ራቅ ራቅ ስል ጅራፍ ይጠራኛል'
የራቁት ዕሩቅ ነው አጥብቀኝ ይለኛል!

@Johny_Debx 👈
@getem0
5ሳንቲም
10 ሳንቲም
25 ሳንቲም
50 ሳንቲም፣
ላረግነው ውለታ አልተመሰገንም፣
((((ብታምኑም ባታምኑም የግጥሙ ርዕስ ነው))))
#ሳሙኤል_አለሙ
....

እኔነኝ ያለ 100g ዳቦ፣
በ5 ሳንቲ ይገዛል ለቁርስ ተመድቦ፣

ከጓደኛ ጋራ
የወግ ወጉን ይዞ እንዳይሆን በደረቅ፣
በ5ሳንቲ አምስት ደስታ ከረሜላ
ነበረ የሚያደምቅ፣

ሁለት 5 ሳንቲ ወድቆ ያገኘ ሰው
ወደ ሆቴል ዘልቆ አይኑንም አፍጥጦ፣
በየአይነቱን ያዛል ከኪሱ መዥልጦ፣
➋➎
መንገድ ላይ ስትሄድ ወድቆ ያየኸው ሰካራም፣
በስሙኒ ሳንቲ የጠጣው ብርሌ አፋ አያስጠጋም፣
➓➓➓➓➓
50 ሳንቲ ከኪሱ ያኖረው፣
ከጎኑ ማይጠፋ ብዙ ጀሌ አለው፣
አንድ ሁለት ብሎ ልዘርዝረው ካለ፣
ለሌላው ይተርፋል ለራሱ እየቻለ።

@Sazi5
@getem0
አባት´ማ

እነሱ ካንተ እኩል ወንድ መባላቸው
እነሱ ካንተ እኩል ስም መሰጠታቸው
ለኔ ከዚያም በላይ ለእኔ ከአባት በላይ
አሁንም ላውራልህ ወጥቼ አደባባይ
ባይበላም ባይጠጣም ባይገባ ከቤት
ከደጃፍ ቁጭ ሲል ደስ ይላል አባት
አሁን ነው የገባኝ እንዲያ የሚሉት ተረት
እረ ለመሆኑ .. ለእነሱ ወንድ ብሎ ስም ያወጣላቸው
ከአንተ ከአባቴ እኩል ያረጋቸው

እናም የኔ ቆንጆ እናማ የእኔ ክብር
ሞተሀል ተብሎ ስገኝ በአንተ ቀብር
አላመንኩም ነበር
ግን ....ግን....
አሳመነኝ ጊዜ አሳመነኝ አመት
ካንተ ተለይቼ ብቻዬን ኖርኩበት
ካንተ መለየቱ አንድንም ትልቅ ቅዠት
አንድም ትልቅ እውነት
አባት ማለት ስሙ ለአንተ ቢያንስብም
የወንድነት ልኩ አባት ስለሆነ
አባዬ ስላልኩህ አንተም አልከፋህም

ላላገኝህ ሄደህ ዘመናት አለፉ
ቀናትና ሰከንድ በፍጥነት ከነ ፉ
ከህልሜ ባንኜ ህልም ባደረኩት
ቅዠቴንም ትቼ እውነት ባስመሰልኩት
ያንተን አለመኖር መኖር ከተባለ
እንደው በለወጥኩት

እኔ ግን ያመኛል
ወንዶች የተባሉት ካንተ እኩል ሲጠሩ
በለምለም ሜዳ ላይ ገለባ እየዘሩ
እናማ
ወልዶ ማሳደጉ ወንድ ሆኖ መፈጠር
የአባን አባትነት አያክልም ነበር

እናም የኔ አባት እናም የኔ ቀለም
በስጋ ባትኖር ብትርቅ ከዚህ አለም
ከትዝታችን ላይ የረ ሳሁት የለም

አባት ማለት ለእኔ ስኖር በዘመኔ
፻(100)አለቃው ይትቤ
የአንገት ማህተቤ
የ የ ቀን ክታቤ
ለዛሬው ማንነት መ ሰረት የሰጠኝ
ለእኔ እሱ ነው አባት በዚህ ምድር ስገኝ።

(ነፃነት ይትባረክ)

@getem0
@getem0
ተፈላሰፍ አለኝ

📝📝📝

ተመሰጥ ተደመም ተመልከት ተፈጥሮ
እይታህን አጥራ አስተውል በአንክሮ
ተገንጠል ተለየው ናቀው ይህን ዓለም
ቆሞ አንቀላፍቷል በቁሙ በማለም
ጠይቅ ተመራመር ግለጠው መጽሐፉን
አራግፈው መርምረው እየው ብራናውን
የአባቶችን እውቀት ባሕረ ሃሳቡን
ግባና ፈትሸው ቅኔ ማህሌቱን
ጥበብን ፈልጋት እውቀትን አስሳት
ግባ ከመድራሳው እውነትን ፈልጋት


ተነስ ተመራመር ተፈላሰፍ አለኝ
ጥልቅ ብለህ ስመጥ ግባበት አሰኘኝ
የኋላውን እውቀት የዛሬን መነሻ
የነገን አብነት መንገድ መቀየሻ
አንሳው አሞግሰው አይረሳ ከቶ
የፀና ዛፍ የለም ስሩ ተበላሽቶ
አለኝ አስታወሰኝ የህሊናው ደውል
ሊያባንነ ኝ ቢሻ ካንቀላፉ መሃል
ይህንንም ነግረውኝ ጠፉ ተሰወሩ
አነቃነው ብለው ርቀው በረሩ
መች ተረዱኝና....
አውቆ የተኛን ሰው...መሆኑን ነገሩ

🗒🗒🗒

ኪነ ዳን

@getem0
@getem0
#ሽር---ሸረሪቷ

አንጀቷን ---
የተቋጨውን ከእትብቷ
ወተቷን ---
የተሾመውን ከግቷ
ወለላዋን ---
የተሰራውን በደሟ
ቅርሷን ---
ያኖረችውን በስሟ
አወጣችው ! - እያማጠች
እንደ ፈትል - እያደራች
እንደ ጅማት - እየላገች
እሷ ---
ቤተሰሪዋ ...
ብቸኛዋ ...
ኗሪዋ ...
ድምፅ የላትም ---
አትሰማም
ኮቴዋ እንኳን ---
አይጣራም
ዝም - ሽው
ሽክርክርክር ...
አቅታዋን ገትታ
መዞር
በዝምታ በጸትታ ---
መሽከርከር
ያለ ተራዳ ---
ድንኳን ማቆም
ያለ ካስማ ---
ቱሻ ማገም
ትንፋሽ የለ ---
ወይ ኮሽታ
ጣሪያ ማድራት ---
በዝምታ በጸትታ
ወራጀ የለ ---
ባለ ማገር
በጸጥታ ---
ትንፋሽ መስበር ...
ጣሪያ ሠርታ ---
መሽከርከር
ግድግዳ ሠርታ ---
ሳትወጥር
ሽር - ሸረሪቷ ---
ኃያል ጥበቧን ሰጥታ
አጀብ ዘመኗን ፈጅታ ---
ሽር --- ሸረሪቷ
ላንዲት መዓልት ቆይታ
አዲስ ቤቷን ሰርታ
ሽር --- ሸረሪቷ ---
ሁሉን ነገር ረስታ ...

ሚያዚያ ---- 1977
የማለዳ ስንቅ
(አበራ ለማ)

@getem0
@getem0
# የመሸባት……..
ትላንት ዛሬን ወልዶ
ዛሬም ነገን ናፍቆ
እየተያያዙ ሲጉአዙ ሲጉአዙ
ሲሄዱ ሲነጉዱ
ቆሜ አሳልፌአቸው
…………………………….
ቁጭ ብዬ ሳያቸው
ይተባበራሉ ይከባበራሉ
ሰኞ ከማክሰኞ
አሮብም ካሙስ ጋር
አብረው ይሄዳሉ
ይፍጣጠራሉ ይወላለዳሉ
እነሱም እንደ ሰው
ያድጋሉ ይሞታሉ
###################
ይህንን የምልህ ምለፈልፍብህ
ልሰብክህ አይደለም ጊዜን ላስተምርህ
እኔው ተገርሜ ተደንቄ እኮ ነው
አንተን ላማክርህ ያኔን ላስታውስህ
*
*
*
አስታወስከው አይደል ያኔ ያልኩትን ጊዜ
ያበዛው ስህተቴን ያስቃኘኝ ትካዜን
የፍቅሬን መግለጫ ፊደል ምመርጥልህ
ኢሜል ምልክልህ
በ ቀን አስር ጊዜ በ ስልክ ማወራህ
ላግኝህ እያልኩኝ የምጨቀጭቅህ
አስታወስከው አይደል…….
የረፍትህን ጊዜ
ያቺን ቅድስት ሀሙስ ብዬ የሰየምኳትን
በናፍቆት በጉጉት ሁሌ ምቆጥራትን
ነገ እኮ ሀሙስ ነው እያልኩኝ ለሁሉም የማወራላትን
###############################
ታድያ…………………………………………………..
###############################
ለማንስ ላካፍለው ይህንን ስህተቴን
ለማንስ ላውርሰው ይህን ነጩን ጸጉሬን
የተጨማደደው ያረጀውን ፊቴን
ሸካራውን እጄን
ፍለጋ ያደከመው የጠቆረው እግሬን

ላንተ!
ለልጆችህ !
ወይንስ ለራሴው!
በ ቤዛዊት ከበደ

@getem0
@getem0
# የመሸባት……..
ትላንት ዛሬን ወልዶ
ዛሬም ነገን ናፍቆ
እየተያያዙ ሲጉአዙ ሲጉአዙ
ሲሄዱ ሲነጉዱ
ቆሜ አሳልፌአቸው
…………………………….
ቁጭ ብዬ ሳያቸው
ይተባበራሉ ይከባበራሉ
ሰኞ ከማክሰኞ
አሮብም ካሙስ ጋር
አብረው ይሄዳሉ
ይፍጣጠራሉ ይወላለዳሉ
እነሱም እንደ ሰው
ያድጋሉ ይሞታሉ
###################
ይህንን የምልህ ምለፈልፍብህ
ልሰብክህ አይደለም ጊዜን ላስተምርህ
እኔው ተገርሜ ተደንቄ እኮ ነው
አንተን ላማክርህ ያኔን ላስታውስህ
*
*
*
አስታወስከው አይደል ያኔ ያልኩትን ጊዜ
ያበዛው ስህተቴን ያስቃኘኝ ትካዜን
የፍቅሬን መግለጫ ፊደል ምመርጥልህ
ኢሜል ምልክልህ
በ ቀን አስር ጊዜ በ ስልክ ማወራህ
ላግኝህ እያልኩኝ የምጨቀጭቅህ
አስታወስከው አይደል…….
የረፍትህን ጊዜ
ያቺን ቅድስት ሀሙስ ብዬ የሰየምኳትን
በናፍቆት በጉጉት ሁሌ ምቆጥራትን
ነገ እኮ ሀሙስ ነው እያልኩኝ ለሁሉም የማወራላትን
###############################
ታድያ…………………………………………………..
###############################
ለማንስ ላካፍለው ይህንን ስህተቴን
ለማንስ ላውርሰው ይህን ነጩን ጸጉሬን
የተጨማደደው ያረጀውን ፊቴን
ሸካራውን እጄን
ፍለጋ ያደከመው የጠቆረው እግሬን

ላንተ!
ለልጆችህ !
ወይንስ ለራሴው!
በ ቤዛዊት ከበደ
@getem0
..... ይሆናል

እንቅልፈ በአይኔ ሳይዞር
በቅዠት አለም ውስጥ ካንቺ ጋ ስጣመር

ከእውነት በራቀ
በይሆናል ተስፋ እጅግ በረቀቀ
የትዳር አለም ውስጥ ባንቺ ስደሳሰት
በሚያምረው ቬሎሽ ላይ ህልሜን ሳጣጥማት

እጅሽም ከእጀ ተጣምረው ሲታዮ
ቀለበት ሳስርልሽ ሰወች እኛን ሲያዮ

ግንባርሽን ስስመው ፈገግ ስትይ
የግራዋ አጥንቴ ሁነሽ ስትሞይ

በምንም ማይናድ ትዳርን መስርተን
እጅግ ደስ የሚሉ ልጆችንም ወልደን

ፈጣሪን አክብረን ብለነው ተመስገን
ኑሮዋችን ሲደራ በእጅጉ ተባርከን ይህ ነው የኔ ምዕናብ
ይህ ነው የኔ ሀሳብ
ለመኖር ያስቻለኝ ደስታን አድሎኝ
ህልሜ ነው ደስታየ ፈጣሪ የሰጠኝ

©ኦኒ
@getem0
#እዮብ_መኮንን_ደብዝዘሽ

መልክን የሻረዉ አንቺ ጋር ምን ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ አየሁ ልቤ ስትገቢ ካንቺ በላይ ቆንጆ
ሞልቶ ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ካንች በላይ እዉቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው መልክን የሻረዉ አንቺ ጋር
ምን ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ፣ አየሁ ልቤ ስትገቢ ካንቺ በላይ ቆንጆ
ሞልቶ ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ካንች በላይ እዉቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው ለኔው ጥቅም በኔው ሰው ተመክሬ
አላውቅም አብልጬ፣ ከልብ አምርሬ
አሁን ለምን ገባኝ፣ ባንቺ ሲመከር
ያሉግንን ብለሺኝ፣ የምፍጨረጨር ከኔ ነው፣ ወይ
ካንቺ ነው
ልቤን ለጅሽ፣ የሰጠነዉ ማኩረፍ የኔ ነበር አልሸፋፈንኩም
ካንቺ ጀምሬ ግን አልተቀየምኩም
ምንድነው ብርቅ ሆኖ የሚያስወድደኝ
ሁሉሺን እንዳደንቅ የሚያስገድደኝ የት ብለው፣ የትቢሄዱ
መስፈርት የለም፣ ከወደዱ መልክን የሻረዉ አንቺ ጋር ምን ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ፣ አየሁ ልቤ ስትገቢ ካንቺ በላይ ቆንጆ
ሞልቶ
ያዉቃል ልቤም ቀርቦምአይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው ካንቺ በላይ አውቀታቸው ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው ተቀይሩዋል አይኔ፣ ወዷል
መልክሺን
ስመዝኑሽ ያደንቁዋል፣ ሲቀርቡሽ አንቺን
ቆንጆም ዉብም ለኔ ያንቺ አይነት ብቻ ባይም ልቤ አያምንም፣ እንዳለሽ አቻ
የት ብለው፣
የት ቢሄዱ
መስፈርት የለም፣ ከወደዱ ተቀይሯል አይኔ፣ ወዷል
መልክሺን
ሲመዝኑሽ ያደንቋል፣ ሲቀርቡሽ አንቺን
ቆንጆም ዉብም ለኔ ያንቺ አይነት ብቻ ባይም ልቤ አያምንም፣ እንዳለሽ አቻ
ግን
በምንበለጥሻቸው
ቆንጆወቹን @getem0
/አበባው መላኩ/
...........እስከማዕዜኖ
አቤል በፀጋ እርቆ በየዋህነት ከመጠቀበት፣
ቃየል በንፍገት ከብሮ መቀመቅ ከወረደበት፣
የጓለመህያው ታሪክ ሲጀመር የጠቆረበት፣
እንውረድ ብሎ ወንድሞን እስትንፋሱን የነጠቀበት፣
ሃዘና ስምይ ወብ ካያ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ፣
የሞት ታሪክ ሲነገር ባዝማናት መሃል ሊነገር፣
የመጀመሪያው መላዕክ ታሪኩን ሲፅፈው እንደዚህ ነበር፣
ክሌቱ አሃው መንገረ ቀላዩ ውረዱ፣
እኒህ ሁለት ወንድሞች ወደ አዘቅት የሄዱ፣
አንደኛው ሟች ሊሆን ገዳይ ሊሆን አንዱ፣
አሃዱ ተመይተ ወይ ተመይተ አሃዱ፣
አንደኛው ሲመለስ ሁለተኛው እዚያው የቀረ፣
ውረድ እንውረድ ያለው ወንድሙ ገድሎት ነበር፣
.
.
.
.
.
.
.
ከዚህ የቀን ጎዶሎ ነው ከዚህ ክህደት በውኃላ፣
ከተራራው አናት እና ከግርጌ በቆመው መሃል መተማመኑ የላላ፣
....
.
.
የአዳም የልጅ ልጅ ሁሉ ምን ቢጀግን ምን ቢያቅራራ፣
ምን ደግ ንግርት ቢያስነግር ምን በማዕረግ ቢጠራ፣
ይገሉኝ ይሆን እያለ ነው ውረድ ሲሉት የሚፈራ፣
እናም መውረድ ሞቱ ነው አንዴ ደርቡን ከወጣ፣
ውረድ ሲባል በመውረዱ ነው ወንድሙ ሂወቱን ያጣ፣
.
.
.
......................
በእርግጥ ለምን ይወርዳል መውረድስ ማንን ጠቀመ፣
የወረደውን መግደሉ ለዘላለሙ ካልቆመ፡፡
.
.
አበባው መላኩ
@getem0
#አዬ_ሙሴ_ግሪክ

አንድ ግሪክ ነበር አሉ ከጠላት በፊት
አራት ኪሎ ሰፈር መጠጥ ምግብ ቤት
ከፍቶ የሚነግድ በጣም የታወቀ
መኳንንቱ ሳይቀር እየተሰረቀ
ጓዳው ተለይቶ ጉዱ እንዳይወጣ
እቤቱ የሚውል ሲበላ ሲጠጣ !

ከእለታት አንድ ቀን በሁዳዴ ቀን
ደንበኛው የሆነ አንድ መኮንን
ከለመዱት ጓዳ ተሰርቀው ገቡና
ሲበሉ ሲጠጡ ሲያወሩ ዋሉና
ሊወጡ ሲነሱ እንዲህ አሉት ሙሴን

"ሙሴ ልብ አድርግ በፃም ቀን መግደፌን
ኀላ እንዳትናገር ለማንም ቢሆን !
ትልቅ ሰው ነኝና ክርስቲያን አማራ
አገር ጉድ ይለኛል ስሜን ብትጠራ !"

ግሪኩም መለሰ " ጌታዬ ምን ቆርጦኝ
እርሶ ብቻ አይደሉም አደራ ያሉኝ !

ደጃዝማች ታፈሰ ባላምበራስ ግርማ
ቀኛዝማች አደራ እነራስ ይማማ
መኳንንቱ ሁሉ በጦም የሚበላ
አደራ ብሎኛል ከበላ በኃላ ፤
ስለዚህ ግዴለም አያስቡ ፍጹም
በኔ ይሁንብዎ ማንም አይሰማውም !"

አለና ሲጨርስ ሰውየው ደንግጠው
እንዲህ አሉ ይባላል ሲወጡ ተናደው

"አዬ ሙሴ ግሪክ ወራዳ ገገት
ምስጢር መያዙ ነው አሁን ባንተ ቤት !"

1951 አ.ም
አዲስ አበባ
የመስከረም ጮራ
#አሰፋ_ገ/ማርያም ተሰማ

@getem0
@getem0
@getem0