ግጥም ብቻ
2.88K subscribers
107 photos
9 videos
6 files
71 links
የፍቅር_ግጥሞች
የፍቅር_ታሪኮች
የሙዚቃ_ግጥሞች
የተለያዩ_ግጥሞች
ጠቃሚ_መረጃዎች/አዲስ_ነገር
ቻናላችንን join በማረግ ይቀላቀሉን
@Getem0

ለማንኛውም አስተያየት/ግጥም ለመላክ
@dada_KL
@dada_KL
Download Telegram
~~የአዞ እንባ ~~(ሳሙኤል አዳነ)
ባልበሰለ አይምሮ
ሀገር ልናቆስል ፣
ከራስ ጋር ተጣልተን
ብሄር እንገምዳለን
አዋቂ ይመስል ።
.
እምነት አለኝ የሚል
መፆም ያላቃተው ፣
መነው ይችን ሀገር
ካለችበት ፍዳ
መታደግ አቃተዉ ።
.
ለካስ ውሸት ኖሯል
ያዞ ነው እንባችን ፣
ከይቅርታ ጀርባ
ከሳሽ ነው ልባችን ።
ፀሎት መፃፍ ይዘን
ጦር አለ በጃችን ።
የይምሰል ለቅሷችን
ግፍ እየቋጠረ ፣
ዞሮ እሚያቃጥለን
አሲድ ሆኖ ቀረ ።
.
እባክህ አምላኬ
ፅድቁም ይቅርና
በቅጡ ኮንነን ፣
የአንድናት ልጆች
ተባልተን እንዳናልቅ
አስታራቂ ሆነን ።

@getem0
^^^^^^ሰላም ነህ አትበይኝ^^^^^^

=====================

ሰላምታሽ ካፍሽ ቃል ሰላም እያለ ሲወጣ!
ከከንፈሮችሽ መንቀሳቀስ ልቤን እያስደነገጠ ሲወርድ ሲወጣ! ተይ ተይ ውዴ ሰላም አትበይኝ!
የድሮ ትዝብቴን ያመጣው መሰለኝ!
ከሚገርምሽ ውዴ የፍቅርሽ ነበልባል እየመጣ በህልሜ!
ይሄዳል ከሚዞረው አካል ሰውነቴ ደሜ!

ተይ ሰላም አትበይኝ

ትዝ ይልሻል ውዴ የፍቅራች ጣዕም
ቤት አይበቃም ነበር!
አሁን ግን ወደ ወትሮ በታሪክ ሆኖ
በቀረ ግዜ ነበር!
አውቃለው መመለስ ባይችሉም በነዚያ ቀናቶች!
አሁን ግን አልፈዋል በሄደው ለሊቶች!

እና ምልሽ ውዴ

በፍቅርሽ አጥምቀሽ ከሄድሽ በኅላ!
ዛሬ ግን መተሽ ሰላም ነህ ስትይኝ ዞርኩኝ ወደኅላ!
ያኔ ድሮ ድሮ ፍቅር መስጠት ነው ብለሽ አልነበረ!
ታድያ ምነው የዛሬን ግዜ እንደዛ እንዳልነበረ!

እና ምልሽ

ሰላም ነህ ስትይኝ እንዴት ነኝ ልበልሽ!
እንደዚው ነኝ ብቃ አንቺ ግን እንዴት ነሽ!

💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️

@getem0
የፍቅር ጓደኝነት ለመጀመር መቸኮል የሌለብህ ለምንድን ነው?

ዝግጁ ሳትሆን የፍቅር ጓደኝነት እንድትጀምር የሚደረግብህ ጫና በደንብ ያልተማርከውን ትምህርት እንድትፈተን ከመገደድ ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ይህ ምክንያታዊ እንዳልሆነ ግልጽ ነው! ፈተና ላይ የሚቀርቡትን ጥያቄዎች መመለስ እንድትችል ትምህርቱን ለማጥናት ጊዜ ያስፈልግሃል።

የፍቅር ጓደኝነት በመመሥረት ረገድም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው።

የፍቅር ጓደኝነት መመሥረት እንደ ዋዛ የሚታይ ነገር አይደለም። በመሆኑም ከአንዲት ወጣት ጋር የፍቅር ጓደኝነት ስለ መጀመር ከማሰብህ በፊት በጣም አስፈላጊ የሆነን አንድ “ትምህርት” ለማጥናት ይኸውም ወዳጅነት መመሥረት የሚቻልበትን መንገድ ለመማር በቂ ጊዜ ያስፈልግሃል።

እንዲህ ካደረግህ ከጊዜ በኋላ፣ የምትሆንህን ወጣት ስታገኝ ጠንካራ ግንኙነት ለመመሥረት የተሻለ አቋም ይኖርሃል። ጥሩ ጋብቻ የሁለት ጥሩ ጓደኛሞች ጥምረት መሆኑን አትዘንጋ።

የፍቅር ጓደኝነት ሳትጀምር መቆየትህ ነፃነትህን እንደሚገድብብህ ማሰብ የለብህም። እንዲያውም ‘የወጣትነትህን ጊዜ አስደሳች’ በሆነ መንገድ ለማሳለፍ የበለጠ ነፃነት ይሰጥሃል። (መክብብ 11:9) ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ባሕርያትን በማዳበርና ከምንም በላይ ደግሞ መንፈሳዊነትህን በማጠናከር ራስህን ለማዘጋጀት የሚያስችል ጊዜ ይኖርሃል።—ሰቆቃወ ኤርምያስ 3:27

እስከዚያው ድረስ ግን ተቃራኒ ፆታ ካላቸው ወጣቶች ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ትችላለህ። ይህን ለማድረግ ከሁሉ የተሻለው መንገድ ምንድን ነው? ትላልቅ ሰዎች ባሉበት በቡድን ሆኖ (ከወንዶችም ሆነ ከሴቶች ጋር) መጫወት ይቻላል። ታሚ የተባለች ወጣት እንዲህ ብላለች፦ “እንደዚያ ሲሆን ይበልጥ የሚያስደስት ይመስለኛል። ብዙ ጓደኞች ቢኖሩን የተሻለ ነው።” ሞኒካም በዚህ ሐሳብ ትስማማለች። “በቡድን ሆኖ መጫወት በጣም ጥሩ ነው፤ ምክንያቱም የተለያየ ባሕርይ ያላቸውን ሰዎች ማወቅ ትችላላችሁ” በማለት ተናግራለች።

በሌላ በኩል ግን ያለዕድሜህ በአንድ ሰው ላይ ብቻ ትኩረት የምታደርግ ከሆነ ራስህን ለአደጋ ታጋልጣለህ። ስለዚህ አትቸኩል። ከዚህ ይልቅ ይህንን ዕድሜህን፣ ወዳጅነት መመሥረትና ዘላቂ እንዲሆን ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነ ለመማር ተጠቀምበት። እንዲህ ካደረግህ አንድ ቀን የፍቅር ጓደኝነት ለመመሥረት ስትወስን፣ የራስህን ፍላጎትም ሆነ የዕድሜ ልክ የትዳር አጋርህ ከምትሆነው ሴት የምትጠብቃቸውን ባሕርያት በሚገባ ታውቃለህ::

@getem0
#ብለው ከሚነግሩኝ#

ጓዳውን ለመሙላት
እንደማይፍጨረጨር፣
የዕለት ጉርስ ለማግኘት
እንዲያ መሬት ሲጭር፣
ሲወርድ ሲወጣ
ሲለፋ እንዳልነበር፡፡

"አላየሽ ጉድሽን"

ዛሬ ተቀይሮ፣
በአቋራጭ ከብሮ፡፡
ከየት እንደመጣ
ማንነቱን ረስቶ፣
ከሃብት ማማ ላይ
ከላይ ከጫፍ ወጥቶ፡፡
የኛን መናጢነት
አቆልቁሎ አማትሮ፣
ባላየ እንዳለፈን በእኛ
ተንበጣሮ፡፡

"አላየሽው ዛሬ"

በዝናውም ልቆ፣
ከዘረፉ ዘርፎ
ከሰረቁ ሰርቆ፡፡
የናጠጠ ሆኗል
ቢጠሩት `ማይሰማ፣
ከበርቴ ተብሎ
በሃገር በከተማ፣
በአንዱ አፍ ሲከፋ
በአንዱ አፍ ሲለማ፣
አንዳንዱ በጉቦ
ሌላው በሙስና
ሲያሙት ሲታማ፡፡



እንዲህ እንዲያ እያሉ
"አላየሽ ጉድሽን"

ብለው ከሚያወጉኝ፣
ጥሩነትህ ቀርቶ
መጥፎ ከሚነግሩኝ፡፡
በቀረብህ ምነው
ምነው በቀረብህ፣
ለኔም ይሻል ነበር
ነጩ ድህነትህ፣
ክፋት ካጠለሸው
ከጠቆረው ሃብትህ፡፡
✍️ ማህሌተ ቅኔ✍️
የካቲት 2010

@getem0
ባቲ ገበያው ዳር ፤
በቀርሳ ብርቱካን ፤
በገርፋ መንደሪን ፤ ተጨምቃ ያደገች ፤
በአውሳ ልጆች ጊሌ ፤
ከጀግና ጋር ውላ ፤ ጀግና ጋር ያደረች ፤
አሳ ባራ ጊቴ ፤
አውቶብስ የሚቴ ፤
በሚል ሃያል ዜማ የተሽሞነሞነች
ባቲ ገበያው ዳር ፤
እንደ ጆፌ ጥላ ፤ ዋርካ የነበረች ፤
ሁሉ የሚዋያት ፤
የባቲ ከራማ አንዲት ሴት ነበረች ።
ሰኞ ገበያው ቀን ፤
ባቲ መቃኛው ላይ ፤
ካለችው ግራር ስር ፤ ጨፌዋን ጎዝጉዛ ፤
ከአፋር ልጆች ወተት ፤
ከአርጎባ ልጅ ቅቤ ፤
ከአሰብ ልጆች ፍቅር ፤ መውደድ የምትገዛ ።
ከገራገር ጥርሷ ፤
ከታማኝ ከንፈሯ ፤
ከረጠበው ቀልቧ ፤
ከቃሏ በስተቀር ፤
የምትከፍለው ገንዘብ ፤ሽልንግ ያልነበራት ፤
ባቴየ መሆኗን ፤
ስንቱ በአሻጋሪ በሩቅ እየለያት ፤
መቼም በአማኑ ቀን ፤
መውደዷን እያየ ፤
አገር ሙሉ ፍቅር ፤ ስንቱ ነየተላት ።
ገንዘብ የማይገዛው ፤
ባውንድ የማይተካው ፤
ሃገር ሙሉ ፍቅር ፤
እንደ ዋርካ ጥላ ፤ ሰብስባ ያደረች ፤
ፈልጉልኝ እስቲ ፤
ባቲ አጣሪ ገንዳ ፤ አንዲት ሴት ነበረች ።
ኧረ ባቲ ባቲ ፤
ባቲ አጣሪ ገንዳ ፣ ቀርሳ ታቹን ቡርቃ ፣
ንግግሯ አዱርስ ነው ፤
እንደ አበጋር እጣን ፤
ቡልቅልቅ እያለ ላገር የሚበቃ ፤
ስንቱን መንገደኛ ፤
ፍዝ አርጋ አስቀረችው ፤
በከዳሚ ጥርሷ ፤ ከም ከም ብላ ስቃ ።
ባቲና ሸጋ ልጅ ፤
ሸጋና በረሃ ፤በምን ተዋወቁ ፤
ሲወደዱ ጊዜ ፤
በፍቅር አስክረው ፤
ሃቅል እየነሱ ፤ ልብስ እያስወለቁ ።
ከበረሃው ግርጌ ፤
ከወበቁ መሃል ፤ የቆሞምኩት በእርጋታ ፤
በንዳዱ መሃል ፤
የምንጎማለለው ልቤ ሳይረታ ፤
ጉልበቴ የጠናው፤
በቀርሳ ልጅ ሳቅ ነው፤ በባቲ ጨዋታ ።
በዚያ ግለት ጠሃይ ፤
በዚያ ወፍራም ነፋስ ፤
በዚያ ደረቅ ወጀብ ፤ በረሃ በዋጠው ፤
ሃየ በል እያልኩኝ የምሸራገጠው ፤
አይደለም በቅስሜ በገዛ ጉልበቴ ፤
ተዘይሬልሽ ነው ፤
ስትይኝ አህሪቡ ስትይኝ በሞቴ ።
ባቲ ገበያው ላይ ፤
ወሎ መጀን ብሎ ፤ አበጋር ተጣራ ፤
ሁሉም አሚን አለ ፤
ወሎ ድብልቁ ፤ የሁሉም እንጀራ ።
ከእንጀራው መሃከል ፤ እንጎቻ ደርሳኝ ፤
እኔም በተራየ ፤
ወሎ መጀን ብየ እሷን ጎረስኩኝ ።
የግጦሽ ሳርና ፤ የወሎ መሬት ፤
አፈሩ ብዙ ነው፤ የተሰራበት ፤
የኛ እንጅ ቅብቅቡ የኔ ማይሉት ፤
ባንተው መጀን ብላኝ ፤
ሁለት ጋሻ መሬት ለሷም ደረሳት ።
ከጥውልግ ጉንጨ ላይ ፤
ደረቅ ከንፈሬ ላይ ፤
በባቲ ብርቱካን ፤
በቀርሳ መንደሪን ፤ ሳልሳም ቀርቼ ጦም አድሬ ቢሆን ፤
የምወድሽዋ ፤
ጠሃይዋም አትበርድም ፤ባቴ ባቲም አይሆን ።

((( ጃ ኖ ))💚💛


@getem0
@getem0
እውነተኛ ፍቅር ምን አይነት ነው?

ሳይኮሎጂስቶች የፍቅር ሦስት መአዘን የሚሉት ንድፈ-ሀሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የእውነተኛ ፍቅር መገለጫዎች…

1.    ጥልቅ ስሜት (passion)

ፍቅረኛዬን ሳያት/ሳስባት የምወድላት፣ የማደንቅላት እና የምደነግጥላት ነገር ሊኖር ይገባል፡፡ ያ ነገር ለኔ ልዩ ስሜት የሚሰጠኝ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ወይ ዞማ ፀጉሯን…ወይ ብርሃን ፈገግታዋን…ወይ የጠቆሩ ብሌኖቿን…ወይ ውብ ተክለሰውነቷን…ወይም ሌላ፡፡ ይህ ጥልቅ ስሜት ከባህሪ/ስብዕና ይልቅ ወደ አካላዊ ገፅታ የሚያደላ ይመስላል፡፡

2.   ቅርበት/ቁርኝት (intimacy)

ፍቅረኛዬ የቅርብ ጓደኛዬም መሆን አለባት፡፡ በመሀከላችን ምስጢር የሚባል ነገር ከቶ ሊኖር  አይገባም፡፡ የቅርበቱ መጠን ልክ እንደ ቅርብ የወንድ/የሴት ጓደኛ አይነት እንዲሆን ይፈለጋል፡፡ ለቅርብ ጓደዬ የምደብቀው፣ ለመንገር የማፍረው ባጠቃላይ ስለራሴ የማልነገረው ነገር የለም፡፡ ለፍቅር ጓድዬም እንዲሁ መሆን አለበት፡፡ ይሄ በሌላ ቋንቋ መጠናናት የምንለው ነገር ነው፡፡

(አንድን ሰው በደንብ ለማወቅ ያ ሰው በተለያየ ጊዜ እና ሁኔታ የሚያሳየውን ባህሪ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ምን ያስደስተዋል/ያስደንቀዋል፣ ምን ያሳዝነዋል፣ ምን ያናድደዋል፣ ምን ያስፈራዋል፣ ለተለያዩ ነገሮች ያለው ምልከታ ምን ይመስላል እና የመሳሰሉትን ነገር ለማወቅ ከሰውየው ጋር ዘለግ ያለ ጊዜ መዝለቅ ያስፈልጋል፡፡)

3.   ቁርጠኝነት/ዘላቂ ስሜት (commitment)

ከፍቅረኛዬ ጋር ለረጅም ጊዜ (የሕይወት ዘመኔን) አብሬአት ልቆይ እፈልጋለሁ ወይ? ለዚህ ጥያቄ እውነቱ ሁልጊዜም እውስጣችን አለ፡፡ ለውስጣችን ጆሮ ከሰጠነው መልሱ ሩቅ አይደለም፡፡

ጥልቅ ስሜትና ቅርበት ሳይኖርበት አብሮ የመኖር ቁርጠኝነት ብቻ ያለውን ፍቅር ባዶ ፍቅር ብለው የስነ-ልቦና ሰዎች ይጠሩታል፡፡
👐👐👐👐👐👐👐👐👐
JOIN us
👐👐👐👐👐👐👐👐👐
💑💏ፍቅር ያሸንፋል💏💑
@getem0
🤔🤔🤔 #የገባኝ 🤔🤔🤔

በኖሩኳቸው ትንሽ ዕድሜዎች
ባየዋቸው ጥቂት ሁነቶች
ሁሌም የሚገባኝ
ሁሌም የሚታየኝ
መድረሻዬ ነው ፍቅርሽ
ማብቂያዬ ነው ሴትነትሽ
አየሽ በትላንቴ ሸራ በብሩሼ ቀለም
መልክሽን እንጂ አንቺን መሣል አልችልም
ሠነፍ አትበዩኝ ሠንፌ እኮ አይደለም
የዕውቀቴ መጠን በአንቺ አይለካም
ይለካ እንኳን ቢባል መለኪያ የለውም
ብቻ ምን አለፋሽ ድፍረትን ደፍሬ
ፍቅሬን በትዝታሽ ሚዛን ሠፍሬ
ይሄን አስመሰልኩት ምኞቴን ቀምሬ
ነገን በዛሬ ላይ አዲስ ቀን ጀምሬ
የአዙሪቴ ጥጉ አንቺ ሆነሻል ፍቅሬ

ግን እኮ መድፈሩንስ ልድፈር
ስህተቱም ይሁን በኔ ይጀመር
እኔ የምፈራው እኔ የምሰጋው
በአንቺ እየታሰብኩ
በአንቺ እየታወኩ
የኔ የምለው እኔነቴ ጠፍቶ
አንቺ እንዳልባል ወንድነቴ ቀርቶ
ስር የሌለው ቅፅል መሰረት መስርቶ
አንቺ ላጲስ ሆነሽ እስራስ ሆኜ እኔ
እየሳልኩሽ ኖሬ በአላቂ ዘመኔ
እየሳልኩሽ ልሙት ለፍቅር ስህል ቅኔ
~~~~~~~~~~~~~~~~~
#ተክለ_ዮሀንስ(ከሰባተኛ)

@getem0
@getem0
ለቫላንታይን ቀን አክባሪ ሴቶች የተገጠመ ግጥም።
======"============================ ባል
አታይም ( ባላታይም)!!! VS Valantine!!!!!


ካምና ከዘንድሮ፣ ታገባለች ሲሉ፣
እናቷ በምኞት፣ጠላ እየዘለሉ፣
አባቷም በምኞት፣ፍሪዳ እየጣሉ፣
አንድኛውን ጎበዝ፣ ባንዱ እያናጠሩ፣
ይኸው ስንት ዘመን፣
እሷም አላገባች፣ እነሱም አልዳሩ።
በስንት ሺህ ፓሪ ፣ሺህ ጎበዝ ሲስማት፣
አንዱ ያዝኩኝ ብሎ፣ሌላው ሲቀበላት፣
ከንፈር ሳሚው በዝቶ፣ ፈልቶ በሽቅድድም፣
እንደነካት ቀረ፣
አምና የሳመችው፣ዘንድሮን ላይደግም።
ሁሌም ባመት ባመት፣አዲስ ነው ድግሷ፣
ባለተራ ወዳጅ፣ ቀይ ጃኖ አልብሳ፣
እሷ ምን አለባት፣
ለተራበው ቀልቧ፣ጌት ዳውን ነው ምሷ፣
ይኸው በአመት በአመት፣
ቫላንታይን እንጅ፣ባል አታይም እሷ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ቃል መፍቻ፤፤፤ """""ምስ""""ማለት የሱስ ማስታገሻ ፣
የአመል ማብረጃ ማለት ነው።



@getem0
@getem0
ጎረቤቴ

ማጀትሽ ማጀቴ
ውዷ ጎረቤቴ
ልጅሽ ተላኪዬ
ክንብንብ ልባስሽ
ማቀፊያ አንቀልባዬ
የኔ እማዋይሽ
ውዷ እህቴ ሆይ
የምስጢሬ ጓዳ
እንዴት ቆየሽ ከረምሽ?
እህታለም እናት
ናፍቆትሽ በረታ
ተካዥ አደረግሽኝ
ያ የደስ ደስ ገጽሽ
የዋለለ ለታ
የእመቤቴን ብቅል
ፈጨሁ አበርክቼ
አቤት ወዬ ብዬ
ድምጽሽ ቃጭሎብኝ
ዘዉትር በጆሮቼ
የኔ እማዋይሽ
መሬቷ እህቴ
ጎደለብኝ ዛሬ
ክፋኛ ናፈቅሽኝ
አንችንም እንደኔ
እንባ ፈንቅሎሻል?
ኸረ የኔስ ይብሳል
ስንቱን ዘልቀዋለሁ
በዚች በጽህፈቴ
ይልቁን የኔ እህት
ስልኳን ስትይዥ
በዚህ ደውይልኝ
ዓይንሽ ቢርቅብኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ
የኔ እማዋይሽ
ውዷ ጎረቤቴ
የስስት እህቴ
ባልንጀራ እናቴ
ክፉኛ ናፈቅሽኝ።
ህልው ፀጋዬ
@getem0
ቃል ልግባልሽ

አፈቅርሻለሁ ልል ቀናትን አልመርጥም
ወደድኩሽ ለማለት ሰበብ አልፈልግም
በእያንዳዷ ሰከንድ በሁሉም ደቂቃ
ፀሀይም ባትወጣ ባትደምቅም ጨረቃ
ሰማዩ እንኳን ቢናድ ኮከቦች ቢረግፉ
ጥላቻ አግዝፈው ፍቅርን ቢፀየፉ
ቀናት ቢሰየሙ ስም ቢወጣላቸው
የፍቅር ባይባል መጠርያ ስማቸው
አንቺ ከለሽልኝ ለኔ የፍቅር ናቸው
በእያንዳንዷ ሰከንድ ፍቅሬን ብነግርልሽ
ጨርሶ አይቻልም እኔ አንቺን ልገልፅሽ

የፍቅር ቀን ብሎ አለም በሰየመው
በቃልኪዳን ብዛት በተንበሸበሸው
ባማሩ ጥንዶች ፊት በቀይ በደመቁ
ፍቅርን በልባቸው ብዙ በሰነቁ
ከፊታቸው ቆሜ ውዴ ቃል ልግባልሽ
ከምገልፀው በላይ እኔ እንደማፈቅርሽ

@getem0
@getem0
አታፍቅር አይባል ሆኖብን ተፈጥሮ
አይገኝም እና መውደድ በቀጠሮ
አንድ ቀን ሰይሞ የፍቅርን ውሎ
ቀኑን ቢሰይመው ቫላንታይን ብሎ
ፍቅር የለም እያለ
የሚያስበው ጭራሽ
አንዷን ሲላት
ሰማሁ እንኳን አደረሰሽ
ቅድሚያ ልክ ነበር
ደግሞ አፈረሰው
ቫላንታይን ሞልቷል
ፍቅር ነው የጠፋው


በቀን ሶስት ጊዜ
ሲጣሉ የኖሩ ሁለት ጥንዶች ስታይ
ዛሬ ላይ ተቃቅፈው
ፍቅርን ቢሰሩ አላፊ አግዳሚው ላይ

ዛሬን ላይ ባየኸው ፈፅሞ አትደመም
ነገ ስታያቸው
እሱ በግራ ነው እሷ በቀኝ አለም

ስለዚህም ቀኑን በኔ እይታ ወሰንኩ
ስሙንም ቀይሬ
ማላታይኑ ደይ እንዲሆን አፀደቅኩ

ፅሁፉ እኔን አይወክልም‼️

መልካም ቀን ለጥንዶች!!👫💑


@getem0
*ቫላንታይንስ ደይ *(ሳሙኤል አዳነ)

ፍቅር ነው...
ስትስቂ አሳስቄሽ፣
ስትሄጅ ናፍቄሽ፣
ስትመጭ መርቄሽ፣
ስትከፊ ደግም የአይኖችሽ እንባ
በልቤ እየገባ፡እኔም አነባለሁ፤
በአንች መታመም ታማሚ እሆናለሁ፡፡

ታሪክ ነው ፣
ድምፅሽን ሣልሰማ ልቤ እየጨነቀው፤
የሞባይል ካርዴ ባንች ነው የሚያልቀው።
አንችን ስወድሽ ቀን ፡እኔን ስለተውኩኝ፤
ጊዜህን ብትይኝ፡ሁሉን ነገር ትቼ ካንችጋራ ሆንኩኝ

ታሪክ ነው፣
አንች ሪሞት ሆነሽ፡እኔ ደሞ ቻናል፤
play pause ስትይኝ ፡የስንቱ መዝናኛ ሚዲያ ሆነናል።
ደሞ ከሰሞኑ...
ሚዲያ የሚሉት መረጃ ማይርቀው፣
የፍቅረኛሞች ቀን ብሎ እያከበረ ልቤን አስጨነቀዉ።

እህህ...
valantines day በእኔው እይታ፤
የሞኞች ዕብደት ነው፤የሞኞች ጨዋታ፤
አድማጭ የሌለበት የስብሰባ ቦታ ።
ለምን ብትይ...
ዛሬ የፍቅር ቀን ነገ የጥላቻ፣
ፍቅርና ውሸት ቀን ቆጠራ ብቻ።
እውነቱን ልንገርሽ፣
ፍቅር በባህሪው ቀን ቆጠራ አያውቅም።
አበባ እያሳየ የሰው ልብ አይሠርቅም።
ዛሬ እያስደሰተ ነገ አያስለቅስም።

እሡን ተይውና
ይሄውልሽ ፍቅሬ
አንች ብጠይኝም እኔ ወድሻለሁ፣
መልሰሽ ከመጣሽ፤
በልቤ ዙፍን ላይ
አስቀምጥሻለሁ።
ቦታ አገኘሁ ብሎ
መጤ ሳያርፍበት፣
ንግስናሽን ይዘሽ
ነይና ተኝበት።
እንደዛ ከሆነ፡፤
ፍቅራችን አይሎ
እውነት እንሆናለን፣
እኔ ባሪያ ሆኘ አንች ደግሞ ንግስት
valantines day ሁሌ እናከብራለን።
@getem0
ተማጥኖ ለገመድ
(ልዑል ሀይሌ)

እንፈራገጣለሁ
ያሰረኝን ገመድ ታግዬ ለመፍታት፤
የማሠሪያ ዕጣ ነው
በነፃነቱ ልክ
እስረኛዋን ነፍሴን ነፃ የሚያወጣት፤
.
ነፃ ውጣ ገመዱ!
አትገደብ በኔ በገላዬ ልኬት፤
የኔ ስቃይ አይሁን
ያንተ ጥጋት ስኬት፤.
.
የውልህ ገመዴ!...
ኑሮን እወቅበት ክንድህን አበርታ፤
ስንት ልብስ መሰለህ
ታጥቦ ሚጠብቀው ከላይህ ሊሰጣ፤
ስንት ስጋ አለልህ
ቋንጣነትን ብሎ አንተን የሚማጠን፤
ሂድ መከታ ሁነው
እስራቴን ለቅቀህ
ጀግን በፍጥረትህ በመክሊትህ መጠን፤
.
የውልህ ገመዴ!...
አትያዘኝ ጨምድደህ አትፍቀድ እስራት፤
አሳሪውን ትተህ
ውስጥህን አድምጠው ፍርቱናህን ኑራት፤
.
ገመድ ሆይ ልቀቀኝ!!
አታብዛው ጭንቀቴን ነፃ ሁን ተፈታ፤
አንተም እስረኛ ነህ
ዕድሜህን ከፈጀህ
ለአሳሪው ትዕዛዝ ገላህ ከተረታ፤
ነፃ ሁን ገመዴ!!..

፯-፮-፳፻፲፩ ዓ.ም.

@getem0
@getem0
የመስኩ ላይ ቁርሾ! !!!


ሲጀምሩ ፤
ሁለቱም ቆርኬዎች ፤
አብረው ከኖሩበት ፤
ከሚያምረው መስክ ዳር ፤
እየጋጡ ነበር ፤
ከጨፌው ማሳ ላይ ፤ እየፈነደቁ ፤
ድንገት ሳይታሰብ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ወዳጅ ዘመድ መስለው ፤ ወደዚያ ዘለቁ ።
ቆርኬዎቹ ዘንተው ፤
ሳር ከሚግጡበት ፤
ደረሱ ተኩላዎች ፤ እየተፋነኑ ፤
ውሃ በሞላው አፍ ፤
የጨፌውን ማማር ፤
የጋጮቹን ገላ ፤ እያስተነተኑ ፤
የተኩላ መንጎች ፤
እንኳን በስጋቸው ፤
በተቆላለፈው ፣ በቀንዳቸው ቀኑ ።
ቆርኬዎቹ ጠግበው ፤ እስኪፈነጥዙ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ሳሩ ላይ ዋሉበት እየተሟዘዙ ።
ጀመሩ ቆርኬዎች ፤
በጥጋብ ጀመሩ ቀጠሉ ማስካካት ፤
ተኩላ ተናቃ ፤
በጨዋታ መሃል ሸር ለማስገባት ።
እንደዚህ አላቸው ተኩላ አባ ሴራ ፤
ከአያት ቅም አያቶች ታሪክ ስናጣራ ፤
አለቃ ሚሆነው የቆርኬዎች አውራ ፤
ታግሎ የጣለ ነው ፤
ተፋልሞ ሚገዛ ከገጠሙት ጋራ ።
ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ጠቅልሎ ፤
በቀንዱ ጀመረው ፤
ካንደኛው ትከሻ አንዱ ቆርኬ ዘሎ ።
ተኩላ ዳር ቆማ ፤
በጭብጨባ በአጀብ ፤
በል በለው ትላለች ፤ በክፋት አንደበት ፤
ጀግና ማለት በኛ ፤
የጫካው አርበኛ ፤ የሚዘመርለት ፋኖ እየተባለ ፤
ቀንድን በቀንድ ይዞ ፤
አንገቱን ጠምዝዞ መሬት ላይ የጣለ።
በግብግብ መሃል ፤
ገራገር ቆርኬዎች ፤
የተኩላን ፊሽካ ፤ ሰምተው ተናነቁ ፤
ቀንዳቸው ተጣልፎ ፤
ሁለቱም ሜዳው ላይ ዘፍ ብለው ወደቁ ።
በተጠለፈ ቀንድ ፤ በተገመደ አንገት ፤ ወድቀው ተጋጠሙ ፤
ራስ በራሳቸው በጀመሩት ትግል ማንም ሳያሸንፍ ሁለቱም ደከሙ ፤
በተኩላ ተንኮል አብሮ አደግ ቆርኬዎች ሞትን ተሸለሙ ።
ይህን ያየ ቆርኬ ፤
የወንድሞቹ ሞት ፤ በተኩላዎች ሴራ መሆኑን ተረድቶ ፤
ከሞቱበት ሳር ላይ ፤
ካለው ትልቅ ዛፍ ላይ ፤
እንዲህ ብሎ ጻፈ ብእሩን አውጥቶ ።


ሰፊ መስክ ሳለ ፤
ሰፊ ጨፌ ሳለ ፤ በዚህ በመንደሩ ፤
ያንዲት እናት ልጆች ፤
አንተ ወግድልኝ
እኔ ነኝ አለቃ ፤
እኔ ነኝ ባለ ሹም በሚሉት አምቡላ ስለተሳከሩ ፤
ሞሰቡ ሳይቸግር ፤
እኔ በሚል እሳት ፤ ተበላልተው ቀሩ ።

((( ጃ ኖ )))💚💛

ሸጋ ጁምኣ!!💚💛


@getem0
@getem0
አታፍቅር አይባል ሆኖብን ተፈጥሮ
አይገኝም እና መውደድ በቀጠሮ
አንድ ቀን ሰይሞ የፍቅርን ውሎ
ቀኑን ቢሰይመው ቫላንታይን ብሎ
ፍቅር የለም እያለ
የሚያስበው ጭራሽ
አንዷን ሲላት
ሰማሁ እንኳን አደረሰሽ
ቅድሚያ ልክ ነበር
ደግሞ አፈረሰው
ቫላንታይን ሞልቷል
ፍቅር ነው የጠፋው


በቀን ሶስት ጊዜ
ሲጣሉ የኖሩ ሁለት ጥንዶች ስታይ
ዛሬ ላይ ተቃቅፈው
ፍቅርን ቢሰሩ አላፊ አግዳሚው ላይ

ዛሬን ላይ ባየኸው ፈፅሞ አትደመም
ነገ ስታያቸው
እሱ በግራ ነው እሷ በቀኝ አለም

ስለዚህም ቀኑን በኔ እይታ ወሰንኩ
ስሙንም ቀይሬ
ማላታይኑ ደይ እንዲሆን አፀደቅኩ

ፅሁፉ እኔን አይወክልም‼️

@getem0
*ፍቅር ነው የራበኝ*(ሳሙኤል አዳነ)
*
ደህና ነኝ እንዳልል
ደህንነቴ ጠፍቷል ፣
እሞኛል እንዳልል
ይሄው ፊቴ ፈክቷል ።
ሰው ሲያየኝ ጤነኛ ፣
ውስጤ በሽተኛ ፣
ቆይ ምን ብየ ላውራ
ሰሚ ሰው አግኝቼ ፣
በልቤ ጠራ ውስጥ
የትኛውን ትቼ ፣
*
አይቶ በሚፈርድ
ጆሮ ጠቢ ምላስ በሞላበት ሀገር ፣
ለየትኛው ሰሚ
ለየትኛው ሀኪም ህመሜን ልናገር ።
ከማንነት በላይ ፣
ከምንነት በላይ ፣
ምን ቃል ሊተነፈስ ?
በሽፋን መለኪያ
ምን እውነት ሊታፈስ ?
*
ፍቅር ነው የራበኝ..
እሱ ነው ያመመኝ ..
የሀገሬ መሬት ሰው እያካሰሰ ፣
ሰው እያናከሰ፣
የሀገሬ ቋንቋ
ዘር እያስቆጠረ ፣
ክልል እያጠረ ፣

ያዳም የ አብራክ ክፋይ
ሰውነት ቀረና ፣
በጎሳ በብሄር
ታጥሮ ህልውና ፣

በሽብር አይምሮ
ሀገር ይታመሳል ።
ለማይጠቅም አለም
ንጹህ ደም ይፈሳል ።
ክብር የ ሰው ስጋ
በግፍ ይቆረሳል ።
አፍ አየቀደመ
የህሊና ደወል
መሰማት ተስኖት ፣
የአምላክ ቃል ይፈርሳል ።
*

ይሔው ነው ህመሜ

የእድሜያችን ጣሪያ
ሰማኒያ ላይሞላ ፣
በሳር በቅጠሉ
ባፈር ስንባላ ፣
እኔ ነኝ የኔ ነው ፣
ማንነቴ እንትን ነው ፣
የሚል እድር ፈላ ።
በሉ እስኪ ንገሩኝ
ማንነት ምንድን ነው?
ምንነት የቱ ነው ?
*
ሰው ከመባል ወዲያ
ምን ትርጉም ተገኝቶ ?
ከአምላክ ፍጡር ውጭ
ምን ጠላት መጥቶ ?
*
ምንድን ነው ነገሩ ፣
ዝንትአለም መናከስ
ደምበር እያጠሩ ፣
በመግባቢያ ቋንቋ
በትውልድ ቀየ ዘር እየቆጠሩ ፣
ምንድን ነው ?ዘር መቁጠር
ዘር ማሳለይ እንጅ
ሰው ላይ ምን ያደርጋል ፣
ማን በሀሩር ደርቆ
ማን በዝናብ ያድጋል?
*

አመሉ ነው እንጅ ፣
ሞኝነት ነው እንጅ፣
ጥንትም ተፈጥሮውን
ሰው በአምላክ ካመነ፣
ማን ሀባሻን መርጦ
ማን ፈረንጅ ሆነ ?
ከግዜሩ ሆኖ አንጅ
ፍጥረት የተሰጠ ፣
ይሁንልኝ ብሎ
ማን ፆታ መረጠ ።
*
ከአፈር ተፈጥሮ
አፈር የሚሆን ሰው ፣
ከአፈር ጋር ታግሎ
አፈር የሚቆርሰው ፣
ምነው? ይሄ ትውልድ
ከራስ የዘለለ ማስተዋል አነሰው ።
*
ይገርማል ...
በማለዳ ፀሀይ
በምሽት ከዋክብት ቀን እየተዋጀ፣
ህዝቤ አንደጎበጠ
ቅን ሆኖ ቀን ሳያይ ሰማኒያውን ፈጀ ።
ፍቅር ነው የራበኝ ...........
*

03/02/2011
2:00pm
አ.አ

@getem0
@getem0
** ሰውና ምላሱ *******
አምሮብኝ አጊጬ፥
ቢያዩኝ ተለውጬ፥
ሀብት ንብረት ኖሮኝ ከማጣት አምልጬ፥
..........ቀን ከሌት ብለፋ፥
..........ኑሮዬን ላፋፋ፥
ጥርሴ ሲስቅ ሲያዩኝ ጭንቀቴ ሲጠፋ፥
ሰርቼ በበላሁ ፀዳል ፊቴ ፈክቶ፥
ለፍቼ ባገኘሁ ቤት ማጀቴ ሞልቶ፥
ብኖር ሁለን ችዬ ከሰው ተስማምቼ፥
የግር እሳት ሆነ ይህ ለጠላቶቼ።
"እሷማ ሰላቢ ሌባ ናት ሟርተኛ፥
ሳትሰራ የምታገኝ ጠንቋይ መተተኛ፥
ገንዘብና ንብረት፥
ሰው አቀራት ውበት ፥
ሁሉን ከኛ ሰልባ ክብሯን ሾመችበት።"
.........ስትሉኝ ሰምቼ
..........በጣም ተከፍቼ
ሀብትና ውበቴን ሁሉን ነገር ትቼ፥
ለናንተው አድልቼ ከሰዎች ሸሽቼ፥
ብኖር ሁሉን ጥዬ በሬን ዘጋግቼ፥
በዚህስ መች ተዉኝ
"ጭራሽ ይባስ ብላ ንብረቷን አምክና፥
ገንዘቧን ለሰዎች ለወንዶች በትና፥
ይኸው ባዶ እጆቿን ቀረች በጎዳና፥"
ስትሉኝ ስማሁኝ ወይ የኔ ፈተና።
ቦርጭ አውጥቶ ሆዴ ቢወፍር አካሌ፥
አረገዘች አሉኝ አወየው እድሌ።
እሱንም ሰምቼ
በጣም ተከፍቼ
አካሌን ባከሳ ፍዳዬን በልቼ፥
አስወረደች ሲሉኝ ሰማሁ በጆሮቼ።
አረዲያ እስከመቼ.....
ኤጭ አሁንስ በቃኝ አስጠላኝ መኖሩ፥
ሰለቸኝ እናንተን ማለት እሹሩሩ።
የምላሳችሁ መርዝ ወደማይደርስበት፥
ከሀሜት አምልጬ እፎይይይ የምልበት፥
እናንተም አርፋችሁ እኔም ልረፍበት፥
..........አሁን እኳን ተዉኝ..........
ሞታቹን አልነካሁ ሞቴን ልሙትበት።
@getem0
፨ አትመለስ ፨፨፨፨፨፨፨
ይኸውልህ ውዴ............
የስከዛሬው ፍቅር የስካሁን መውደዴ፥
እንደሻማ ቢቀልጥ ውሀ ቢሆን ባንዴ፥
ምን ሊበጀኝ እንባ ለምንስ መንደዴ?
ካልተመቸህ ልቤ ከጎረበጠብህ፥
ፍቅሬ ካልጣፈጠህ ሀሞት ከሆነብህ፥
መለየትን ወዶ ከሸፈተ ልብህ፥
አልከለክልህም ግዴታም የለብህ።
እግርህን አስሬ አቲድ አልልክም፥
መልሱልኝ ብዬም አማላጅ አልክም።
እውነቴን ነው ውዴ ሁን እንደ ፈቃድህ፥
ከሰለቸህ ፍቅሬ ተሟጦ መውደድህ፥
ሂድ እሸኝሀለሁ ጨርቅ ይሁን መንገድህ።
ግና
እንዳለፈው ጊዜ ልክ እንደትላንቱ፥
አስሰህ ስትመጣ ሲበቃህ ዙረቱ፥
ያው እንደለመድኩት እጆቼን ዘርግቼ፥
ምቀበልህ መስሎህ ከ'ቅፌ አስገብቼ፥
አትመለስ ከቶ ዳግም ላታገኘኝ፥
በመሀላ ብዛት በቃል ልትደልለኝ።
ባክህ ተለመነኝ
አትድከም አትምጣ በማምዬ ሞቷ፥
ስለማይመለስ አንዴ ከቆረጠ የሴት ልጅ አንጀቷ።
@getem0
የፍቅር መግለጫ
ከእወድሀለሁ ሌላ፣
ከአፈቅርሀለሁ ሌላ፣
ምን አለ ቢመጣ ምን አለ ቢፈጠር፣
ለፍቅሬ ማሳያ እገልፅበት ነበር።

እውነት ነው የምልህ ፣
እወድሀለሁ ስልህ፣
ፍቅርህን ሚተካ አምሳያ ሚሆነው፣
ፈልጌ አስፈልጌ........
ቃላት ስላጣሁ ነው።

ኪያ ብዬህ ነበር የኔ በመሆንህ፣
ስሞች መርጫለሁ ፍቅሬ እንዲገባህ፣
ግን... ግን.. .....
ለመጠሪያ እንጂ ከቶ አልቻሉም ፍቅሬን ሊገልፁልህ።
ለሰርክ አዲስ ፍቅርህ
ሁሌም ለሚዋበው፣
ቃል እስኪገኝ ድረስ
እንዲሁ ልበልህ በቃ እወድሀለው
በቃ አፈቅርሀለው።

@getem0