#ሻማው_ሲጠፋ
~~~~~~~~~~~~~~~~
~~~~~~~~~~
~~~~~
ሀዘን ካሰመጠው
ጨለማ ከዋጠው ፤
ከቀዝቃዛው ቤቴ አንድ ሻማ በርቷል ፤
የፍቅራችን እድሜ አንድ ዓመት ሆኖታል፡፡
አንቺ ግን የለሽም
ሁሉ ሞልቶ ሳለ አንቺ ግን የለሽም
፧
እንደ ባለቅኔው ቃላት እንዳጠረው፤
ትመጪ እንደው እያልኩ ልክ እንደ ዜመኛው ፤
ተስፋ ባጣ ሻማ እጠብቅሻለው፤
ቢሆንም አትመጪም
ግና ተስፋ አልቆርጥም ፡፡
እኚ ክፉ ሰዎች ክፉ ወዳጆቼ ፤
ስጋዬ ያልኳቸው ክፉ ዘመዶቼ ፤
አትመጣም ይሉኛል ፥ ሞታለች ይሉኛል ፤
"አብዷል" እያሉ አምተው ያሳሙኛል ፤
ሄዳለችም ብለው ልቤን ያቆስሉኛል፡፡
፧
እኔ ግን
ተስፋ ባጣ ሻማ እጠብቅሻለው ፤
ቢሆንም አትመጪም
ይህንን አውቃለው ፤
ግና ተስፋ አልቆርጥም
መቁረጥም አልችልም
፧
ግና ፍቅሬ የት ነሽ ፥ የት ይሆን ያለሽው ፤
ምን ባደርግሽ ይሆን እንዲ የጨከንሽው ፤
ላልተውሽ ላትረሽኝ በፍቅር የማልነው ፤
ምንስ ባስቀይምሽ ቃሉን የረሳሽው፡፡
፧
ጭር ካለው ቤቴ አንድ ሻማ በርቷል ፤
የፍቅራችን እድሜ አንድ ዓመት ሆኖታል፡፡
ከአንድ አንቺ በስተቀር እዚህ ሁሉ ሞልቷል ፤
ምንወደው ዘፈን ቤት ውስጥ ያስተጋባል ፤
ምትወጂው ምግብም ፥ ሽታው ልብ ያስርባል ፤
የምወደው ወይን ከፊቴ ተቀምጧል ፤
አልጋውም ተነጥፏል ፤
የፍቅራችን ምሽት በጨረቃ ደምቋል ፤
ግና ፍቅሬ
አንቺ ብቻ ቀርተሽ ሁሉም ባዶ ሆኗል፡፡
፧
ለፍቅራች ዕለት
ለዚህ ጣፋጭ ምሽት ያበራሁት ሻማ ፤
'ላዩ ሲበራ ፥ ከታቹ የደማ ፤
ሚስጥር ይነግረኛል
እውነት ያሳየኛል፡፡
በመስኮት የገባ ንፋስ ሲያረብበት፤
ብርሀኑን ሊያጠፋ ገፍቶ ሲመጣበት ፤
እርሱ አጎንብሶ ፥ ንፋስ ያሳልፋል፤
እድሜ ለመቀጠል እድሜውን ይቀጥፋል ፤
ጭር ካለው ቤቴ ያበራሁት ሻማ ፤
ሚስጥር ይነግረኛል ፤
እውነት ያሳየኛል ፤
"ፍቅርህስ ?" ይለኛል፡፡
፧
ፍቅሬ ምን ልበለው
ቀርታለችም አልል ፥ መጥታለች አልለው፤
አንድ ሻማ ይዤ እጠብቅሻለው ፤
ቢሆንም አትመጪም
ይህንን አውቃለው ፤
ባውቅም ተስፋ አልቆርጥም
መቁረጥም አልችልም፡፡
፧
ውዴ...
አንቺን ለመጠበቅ ያበራሁት ሻማ ፤
'ላዩ ሲበራ ፥ ከታች 'የደማ፡፡
፧
አሁን ሻማው ጠፍቷል ፥ እኔ ግን ቆያለው ፤
ለተስፋ ብርሃኔ ልቤን አነዳለው ፤
ቀልጦ ያለቀ ዕለት እኔው እመጣለው፡፡
........... ✏️ .........
.................... #ናሆም
👇👇👇
@getem0
@getem0
~~~~~~~~~~~~~~~~
~~~~~~~~~~
~~~~~
ሀዘን ካሰመጠው
ጨለማ ከዋጠው ፤
ከቀዝቃዛው ቤቴ አንድ ሻማ በርቷል ፤
የፍቅራችን እድሜ አንድ ዓመት ሆኖታል፡፡
አንቺ ግን የለሽም
ሁሉ ሞልቶ ሳለ አንቺ ግን የለሽም
፧
እንደ ባለቅኔው ቃላት እንዳጠረው፤
ትመጪ እንደው እያልኩ ልክ እንደ ዜመኛው ፤
ተስፋ ባጣ ሻማ እጠብቅሻለው፤
ቢሆንም አትመጪም
ግና ተስፋ አልቆርጥም ፡፡
እኚ ክፉ ሰዎች ክፉ ወዳጆቼ ፤
ስጋዬ ያልኳቸው ክፉ ዘመዶቼ ፤
አትመጣም ይሉኛል ፥ ሞታለች ይሉኛል ፤
"አብዷል" እያሉ አምተው ያሳሙኛል ፤
ሄዳለችም ብለው ልቤን ያቆስሉኛል፡፡
፧
እኔ ግን
ተስፋ ባጣ ሻማ እጠብቅሻለው ፤
ቢሆንም አትመጪም
ይህንን አውቃለው ፤
ግና ተስፋ አልቆርጥም
መቁረጥም አልችልም
፧
ግና ፍቅሬ የት ነሽ ፥ የት ይሆን ያለሽው ፤
ምን ባደርግሽ ይሆን እንዲ የጨከንሽው ፤
ላልተውሽ ላትረሽኝ በፍቅር የማልነው ፤
ምንስ ባስቀይምሽ ቃሉን የረሳሽው፡፡
፧
ጭር ካለው ቤቴ አንድ ሻማ በርቷል ፤
የፍቅራችን እድሜ አንድ ዓመት ሆኖታል፡፡
ከአንድ አንቺ በስተቀር እዚህ ሁሉ ሞልቷል ፤
ምንወደው ዘፈን ቤት ውስጥ ያስተጋባል ፤
ምትወጂው ምግብም ፥ ሽታው ልብ ያስርባል ፤
የምወደው ወይን ከፊቴ ተቀምጧል ፤
አልጋውም ተነጥፏል ፤
የፍቅራችን ምሽት በጨረቃ ደምቋል ፤
ግና ፍቅሬ
አንቺ ብቻ ቀርተሽ ሁሉም ባዶ ሆኗል፡፡
፧
ለፍቅራች ዕለት
ለዚህ ጣፋጭ ምሽት ያበራሁት ሻማ ፤
'ላዩ ሲበራ ፥ ከታቹ የደማ ፤
ሚስጥር ይነግረኛል
እውነት ያሳየኛል፡፡
በመስኮት የገባ ንፋስ ሲያረብበት፤
ብርሀኑን ሊያጠፋ ገፍቶ ሲመጣበት ፤
እርሱ አጎንብሶ ፥ ንፋስ ያሳልፋል፤
እድሜ ለመቀጠል እድሜውን ይቀጥፋል ፤
ጭር ካለው ቤቴ ያበራሁት ሻማ ፤
ሚስጥር ይነግረኛል ፤
እውነት ያሳየኛል ፤
"ፍቅርህስ ?" ይለኛል፡፡
፧
ፍቅሬ ምን ልበለው
ቀርታለችም አልል ፥ መጥታለች አልለው፤
አንድ ሻማ ይዤ እጠብቅሻለው ፤
ቢሆንም አትመጪም
ይህንን አውቃለው ፤
ባውቅም ተስፋ አልቆርጥም
መቁረጥም አልችልም፡፡
፧
ውዴ...
አንቺን ለመጠበቅ ያበራሁት ሻማ ፤
'ላዩ ሲበራ ፥ ከታች 'የደማ፡፡
፧
አሁን ሻማው ጠፍቷል ፥ እኔ ግን ቆያለው ፤
ለተስፋ ብርሃኔ ልቤን አነዳለው ፤
ቀልጦ ያለቀ ዕለት እኔው እመጣለው፡፡
........... ✏️ .........
.................... #ናሆም
👇👇👇
@getem0
@getem0
//ሰለሞን ሳህለ //
እዚያ ቦታ ቀኑ መሽቶ
እዚህ ቦታ ቀኑ ሳይመሽ
የልብሽን እያወራሽኝ
የነፍሴን ደግሞ እያሳየሁሽ
"እስካሁን ድረስ እስካሁን
የት ነበርክ?" ብለሽ እየጠየቅሽ
እስካሁን ድረስ እስካሁን
"አንቺስ የት ነበርሽ?" እያልኩሽ
በእጆችሽ ልታቅፊኝ ስትይ
ከእነ እጆችሽ እያቀፍኩሽ
"ፍቅር እንዲህ ነዉ?" እያልሽኝ
"ፍቅር አንች ነሽ" እያልኩሽ
"ተበድያለሁ" ስትይኝ
በበደሉሽ እየተቆጣሁ
ከቀረበዉ መጠጥ በላይ
ዉብ ሳቅሽን እየጠጣሁ
የነበርኩበትን ትቼ
ወዳለሽበት እየመጣሁ
ከተደበቅሽበት ሳገኝሽ
አንችም ወጣሽ እኔም ወጣሁ
የበረደዉ ልብሽን
ለፍቅር ፀሃይ አሰጣሁ
ዘለላ የእድሜየን ክር
ስሩን ፈልጌ በጣሁ
እኔንም አንቺንም ሆኜ
ብቸኝነትን ቀጣሁ
ፍቅር በላሽ ፍቅር ጠጣሁ
@getem0
@getem0
እዚያ ቦታ ቀኑ መሽቶ
እዚህ ቦታ ቀኑ ሳይመሽ
የልብሽን እያወራሽኝ
የነፍሴን ደግሞ እያሳየሁሽ
"እስካሁን ድረስ እስካሁን
የት ነበርክ?" ብለሽ እየጠየቅሽ
እስካሁን ድረስ እስካሁን
"አንቺስ የት ነበርሽ?" እያልኩሽ
በእጆችሽ ልታቅፊኝ ስትይ
ከእነ እጆችሽ እያቀፍኩሽ
"ፍቅር እንዲህ ነዉ?" እያልሽኝ
"ፍቅር አንች ነሽ" እያልኩሽ
"ተበድያለሁ" ስትይኝ
በበደሉሽ እየተቆጣሁ
ከቀረበዉ መጠጥ በላይ
ዉብ ሳቅሽን እየጠጣሁ
የነበርኩበትን ትቼ
ወዳለሽበት እየመጣሁ
ከተደበቅሽበት ሳገኝሽ
አንችም ወጣሽ እኔም ወጣሁ
የበረደዉ ልብሽን
ለፍቅር ፀሃይ አሰጣሁ
ዘለላ የእድሜየን ክር
ስሩን ፈልጌ በጣሁ
እኔንም አንቺንም ሆኜ
ብቸኝነትን ቀጣሁ
ፍቅር በላሽ ፍቅር ጠጣሁ
@getem0
@getem0
💔 ትዝታ እና ሻማ🔥
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ከሰሙ ክምር ላይ አንድ ክር ይታያል
እሱን ባየው ቁጥር...
የክሩ አቀማመጥ ያንቺን ይመስለኛል
:
:
ብርሐንና ጥላ እሳትና ቅኔ
በጨለማ መሀል የምራመድ እኔ
ልፈታ እጥራለው
ላስር እጓጓለው
በትንሿ ቤቴ..
ከሻማችን በላይ መብራቱ ምንድነው?
:
:
በቤቴ ታሪክ ውስጥ በቤቴ ብራና በጉልህ የሰፈረ
``ሻማ ሂወቴ ነው`` የሚል ቃል ነበረ
ሻማ ሂወቴ ነው ክሩ ደግሞ አንቺ
በርግጥ ቅኔ አደለም ቢሆንም ግን በርቺ
ባንቺው ስለሚያምር አንቺው ቃሌን ፍቺ
ይላል ብራናዬ!
የቤቴ አንድ ገፅ አንዱ ምዕራፌ
ያኖርኩትኝ ለሷ በሻማዬ ፅፌ
(እንዴት ነው የፃፍኩት...)
:
ያው እንደምታውቂው
የዚ መብራት ነገር አይታመንም ብዬ ሻማ ገዝቻለው
ግን ከገዛው ወድያ ሻማ ነው ወዳጄ መብራቱን ትቻለው
ሁሌ ማታ ማታ እሱን እያበራው
ሳበራ ሳጠፋ ብዙ ሳምንት ቆየው
ከላታት ባንቺ ቀን ባንቺ ተከፍቼ
ቤቴ ተቀምጬ ሻማዬን አብርቼ
አንቺን እያሰብኩኝ ሻማውን እያየው
ቁጥሩን ባላውቀውም ብዙ ሰዐት ቆየው
ሻማዬ ሲበራ ሻማዬ ሲያልቅብኝ
ካይምሮዬ ሰፈር አንቺን ለኮሰብኝ
ፍቅርሽ ፍቅር ነበር ያውም ሰማያዊ
መዳፍሽ የመለአክ ሁሉን ቻይ ቤዛዊ
ትዝታሽ ግን ውዴ
ትዝታሽ ግን ውዴ እንደ ሻማዬ ክር
እያቀለጠኝ ነው ሰም አድርጎኝ ፍቅር
ሰም መሆን ክፋቱ
ወይ ሰው መሆን ከንቱ
ሲያቀልጠው ይኖራል የትዝታ እሳቱ
:
:
ካይምሮዬ ሰፈር የነደደው እሳት
ሰም ነበረች እና ልቤን አቀለጣት
ለነገሩ ትቅለጥ ድሮም የኔ አይደለች
ነዳ የምታነደኝ ክሬ ግን እሷ ነች
እኔ ምስኪን ሻማ ባልሞላ ኑሮዬ
እሳት ፍም ትዝታን ተሸክሜ ችዬ
አለው እኖራለው እድሜ ለሷ ብዬ
ትዝታና ሻማን በሳት አቃጥዬ!
ⓜⓡ◦ ⓣⓡⓤⓜⓟ
2011 O.12
@getem0
@getem0
ለአስተያየት/ግጥም ለመላክ
@dada_habtish
@dada_habtish
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ከሰሙ ክምር ላይ አንድ ክር ይታያል
እሱን ባየው ቁጥር...
የክሩ አቀማመጥ ያንቺን ይመስለኛል
:
:
ብርሐንና ጥላ እሳትና ቅኔ
በጨለማ መሀል የምራመድ እኔ
ልፈታ እጥራለው
ላስር እጓጓለው
በትንሿ ቤቴ..
ከሻማችን በላይ መብራቱ ምንድነው?
:
:
በቤቴ ታሪክ ውስጥ በቤቴ ብራና በጉልህ የሰፈረ
``ሻማ ሂወቴ ነው`` የሚል ቃል ነበረ
ሻማ ሂወቴ ነው ክሩ ደግሞ አንቺ
በርግጥ ቅኔ አደለም ቢሆንም ግን በርቺ
ባንቺው ስለሚያምር አንቺው ቃሌን ፍቺ
ይላል ብራናዬ!
የቤቴ አንድ ገፅ አንዱ ምዕራፌ
ያኖርኩትኝ ለሷ በሻማዬ ፅፌ
(እንዴት ነው የፃፍኩት...)
:
ያው እንደምታውቂው
የዚ መብራት ነገር አይታመንም ብዬ ሻማ ገዝቻለው
ግን ከገዛው ወድያ ሻማ ነው ወዳጄ መብራቱን ትቻለው
ሁሌ ማታ ማታ እሱን እያበራው
ሳበራ ሳጠፋ ብዙ ሳምንት ቆየው
ከላታት ባንቺ ቀን ባንቺ ተከፍቼ
ቤቴ ተቀምጬ ሻማዬን አብርቼ
አንቺን እያሰብኩኝ ሻማውን እያየው
ቁጥሩን ባላውቀውም ብዙ ሰዐት ቆየው
ሻማዬ ሲበራ ሻማዬ ሲያልቅብኝ
ካይምሮዬ ሰፈር አንቺን ለኮሰብኝ
ፍቅርሽ ፍቅር ነበር ያውም ሰማያዊ
መዳፍሽ የመለአክ ሁሉን ቻይ ቤዛዊ
ትዝታሽ ግን ውዴ
ትዝታሽ ግን ውዴ እንደ ሻማዬ ክር
እያቀለጠኝ ነው ሰም አድርጎኝ ፍቅር
ሰም መሆን ክፋቱ
ወይ ሰው መሆን ከንቱ
ሲያቀልጠው ይኖራል የትዝታ እሳቱ
:
:
ካይምሮዬ ሰፈር የነደደው እሳት
ሰም ነበረች እና ልቤን አቀለጣት
ለነገሩ ትቅለጥ ድሮም የኔ አይደለች
ነዳ የምታነደኝ ክሬ ግን እሷ ነች
እኔ ምስኪን ሻማ ባልሞላ ኑሮዬ
እሳት ፍም ትዝታን ተሸክሜ ችዬ
አለው እኖራለው እድሜ ለሷ ብዬ
ትዝታና ሻማን በሳት አቃጥዬ!
ⓜⓡ◦ ⓣⓡⓤⓜⓟ
2011 O.12
@getem0
@getem0
ለአስተያየት/ግጥም ለመላክ
@dada_habtish
@dada_habtish
እህት መድሀኒቴ
–ሌቱ ጨለም ብሏል ጨረቃ ሙታለች
ጎሁ ሊገሰግስ ሲሶኛ ቀርታለች
ፀጥታው ደስ ይላል ተኝተዋል ሰዎች
የቀኑ አድክሟቸው
ጨለማ ውጧቸው
ባይኖሩም እርግቦች ማየት ተስኗቸው
—ለኔ ግን ገና ነው እሩቅ ነው ምሽቱ
ቲኒሿ ጎጆ ላይ ጠፍቶብኝ መብራቱ
በፀና ታምሜ በሽታየ ብርቱ
ብርድ ልብሴ ሞቆ
ላበቴ እጅግ ልቆ
አለሁኝ ብቻየን አካሌ ሰው ናፍቆ
–ድንገት ተመኘሁኝ አሰኝቶኝ
የራስ ህመሜ ቢጠናብኝ
እንደ ጎመራ ተንተክትኮ አልቆም ቢለኝ
የዛኔ ነው የከጀልኩኝ
–ተነስቸ ፋኑስ ለኩሸ
ውሀ አፍልቸ ስኳር ለግሸ
እንዲጣፍጥልኝ ቅመም አፍሸ
ብጎነጭ ተመኘሁ ፍራሼ ላይ ሁኜ አንሶላ ለብሸ
ብጣራ ታግየ ሀሞቴን አፍስሸ
ለካስ ብቻየን ነኝ ዝም ነው ምላሸ
–ድንገት ብልጭ አለ ህመሜ ላይበቃኝ
ጭንቅ የለኝ ይመስን ሀሳብ አከለብኝ
ደህና የተውኩትን ቁስሌን በንጨት ነካኝ
አሁን ብትኖርልህ
የናት ልጅ እህትህ
ላብህን ሳትፀየፍ እቅፍ ምታረግህ
–ሙቀትህን አብርዳ ህልምህን ልትሞላ
ፋኑሱን ምትለኩስ ሻዩን ልታፈላ
ደግፋ አጠጥታ ይችን ብላ አታላ
ቤቱ ሲዘጋብህ
ከፋች ምትሆንህ
ምነኛ ደግ ይሆን አንድ እህት ቢኖርህ
–ዳሩ ምን ዋጋ አለው ድሮም ብቸኛ ነኝ
ሰው ወልዶ ሲጥለኝ ጉዳት ቢያሳድገኝ
የ እህቱ ላይበቃ ጎደኛም ባይኖረኝ
ከፊሎች ሲያለቅሱት
ያልቻሉ ሲያወሩት
ከሁሎችም ሳልሆን አለሁ እንደያዝኩት
ብትኖር ጥሩ ነበር አንድ እህት ከቤቴ
ባትኖርም አልኩኝ እህት መድሀኒቴ💔😞
@getem0
@getem0
–ሌቱ ጨለም ብሏል ጨረቃ ሙታለች
ጎሁ ሊገሰግስ ሲሶኛ ቀርታለች
ፀጥታው ደስ ይላል ተኝተዋል ሰዎች
የቀኑ አድክሟቸው
ጨለማ ውጧቸው
ባይኖሩም እርግቦች ማየት ተስኗቸው
—ለኔ ግን ገና ነው እሩቅ ነው ምሽቱ
ቲኒሿ ጎጆ ላይ ጠፍቶብኝ መብራቱ
በፀና ታምሜ በሽታየ ብርቱ
ብርድ ልብሴ ሞቆ
ላበቴ እጅግ ልቆ
አለሁኝ ብቻየን አካሌ ሰው ናፍቆ
–ድንገት ተመኘሁኝ አሰኝቶኝ
የራስ ህመሜ ቢጠናብኝ
እንደ ጎመራ ተንተክትኮ አልቆም ቢለኝ
የዛኔ ነው የከጀልኩኝ
–ተነስቸ ፋኑስ ለኩሸ
ውሀ አፍልቸ ስኳር ለግሸ
እንዲጣፍጥልኝ ቅመም አፍሸ
ብጎነጭ ተመኘሁ ፍራሼ ላይ ሁኜ አንሶላ ለብሸ
ብጣራ ታግየ ሀሞቴን አፍስሸ
ለካስ ብቻየን ነኝ ዝም ነው ምላሸ
–ድንገት ብልጭ አለ ህመሜ ላይበቃኝ
ጭንቅ የለኝ ይመስን ሀሳብ አከለብኝ
ደህና የተውኩትን ቁስሌን በንጨት ነካኝ
አሁን ብትኖርልህ
የናት ልጅ እህትህ
ላብህን ሳትፀየፍ እቅፍ ምታረግህ
–ሙቀትህን አብርዳ ህልምህን ልትሞላ
ፋኑሱን ምትለኩስ ሻዩን ልታፈላ
ደግፋ አጠጥታ ይችን ብላ አታላ
ቤቱ ሲዘጋብህ
ከፋች ምትሆንህ
ምነኛ ደግ ይሆን አንድ እህት ቢኖርህ
–ዳሩ ምን ዋጋ አለው ድሮም ብቸኛ ነኝ
ሰው ወልዶ ሲጥለኝ ጉዳት ቢያሳድገኝ
የ እህቱ ላይበቃ ጎደኛም ባይኖረኝ
ከፊሎች ሲያለቅሱት
ያልቻሉ ሲያወሩት
ከሁሎችም ሳልሆን አለሁ እንደያዝኩት
ብትኖር ጥሩ ነበር አንድ እህት ከቤቴ
ባትኖርም አልኩኝ እህት መድሀኒቴ💔😞
@getem0
@getem0
........መፅናኛ ለሰካራምች.......
✍ጌትነት እንየው
በቀን እንግድነት - ከአለም እልፍኝ ገብቶ
ባይተዋር ሲሆኑ የሚመስል ጠፍቶ
ህሊናን ሲሸብብ ፣ የሰው ተንኮል ደርቶ
መንፈስን ሲደፍቅ ፣ የሰው ግፉ ምልቶ
ንፁህ ልብ ሲያፍን ፣ ክፋቱ ከርፍቶ
ሚዛንን ሲስቱ ፣ በቀን ሰው ተገፍቶ
ይሄን ጊዜ ሰውን፦
ባይጠሉትም ፈርቶ
ባይፈሩትም ሰግቶ
ከምላሱ ሸሽቶ
ይህንን የቀን ሰው ፣ ከቀን ጋራ ትቶ
ምሽት ተከናንቦ ፣ መሸታ ቤት ገብቶ
ብርሌ አንደቅድቆ ፣ መለኪያ ለግቶ
ለግቶ ለግቶ
ጨልጦ ጠጥቶ
ቢሰደቡም ሰምቶ
ቢመቱም ተመቶ
ቢገደሉም ሞቶ
ብቻ እርሱ ፈጣሪ፦
"ይቅር" እንዲላቸው ፣ ለማርያም ልጅ ሰቶ
ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ ፣ ጨርቅ ሆኖ ቡትቶ
እንደ ህፃን ድሆ ፣ ተማደሪያ ገብቶ
ቢቻል በር ዘግቶ
ካልተቻለም ትቶ
ቀበቶ ሳይፈቱ፦
ጫማ ሳያወልቁ ፣ ታልጋ ተዘርግቶ
ከሞት ከፍ የሚል ፣ እንቅልፍ አንቀላፍቶ
ተ...ኝ...ቶ ተ....ኝ....ቶ
አሁንም ተኝቶ
ሌቱ አልቆ ቀን ሲሆን ፣ ማለዳ ነቅቶ
ማታ በጠጅ ጠርቶ
ማታ በጠጅ ነፅቶ
እራስን ካገኙት
ጠዋት እንደ ክፃን ሁሉንም እረስቶ
ንጡህ ወደኔ ይቅረቡ
ብሎ እንዳላላቸው ጌታ በመዝገቡ
የየዋህነት ገፅ የፍቅር ድርሳኑ
አርጎ እንደፃፋቸው ህፃናት ከሆኑ
ምናለ ቢጠጡ
ምናለ ቢሰክሩ
በቀን ያደፈትን በምሽት ካጠሩ
@getem0
@getem0
✍ጌትነት እንየው
በቀን እንግድነት - ከአለም እልፍኝ ገብቶ
ባይተዋር ሲሆኑ የሚመስል ጠፍቶ
ህሊናን ሲሸብብ ፣ የሰው ተንኮል ደርቶ
መንፈስን ሲደፍቅ ፣ የሰው ግፉ ምልቶ
ንፁህ ልብ ሲያፍን ፣ ክፋቱ ከርፍቶ
ሚዛንን ሲስቱ ፣ በቀን ሰው ተገፍቶ
ይሄን ጊዜ ሰውን፦
ባይጠሉትም ፈርቶ
ባይፈሩትም ሰግቶ
ከምላሱ ሸሽቶ
ይህንን የቀን ሰው ፣ ከቀን ጋራ ትቶ
ምሽት ተከናንቦ ፣ መሸታ ቤት ገብቶ
ብርሌ አንደቅድቆ ፣ መለኪያ ለግቶ
ለግቶ ለግቶ
ጨልጦ ጠጥቶ
ቢሰደቡም ሰምቶ
ቢመቱም ተመቶ
ቢገደሉም ሞቶ
ብቻ እርሱ ፈጣሪ፦
"ይቅር" እንዲላቸው ፣ ለማርያም ልጅ ሰቶ
ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ ፣ ጨርቅ ሆኖ ቡትቶ
እንደ ህፃን ድሆ ፣ ተማደሪያ ገብቶ
ቢቻል በር ዘግቶ
ካልተቻለም ትቶ
ቀበቶ ሳይፈቱ፦
ጫማ ሳያወልቁ ፣ ታልጋ ተዘርግቶ
ከሞት ከፍ የሚል ፣ እንቅልፍ አንቀላፍቶ
ተ...ኝ...ቶ ተ....ኝ....ቶ
አሁንም ተኝቶ
ሌቱ አልቆ ቀን ሲሆን ፣ ማለዳ ነቅቶ
ማታ በጠጅ ጠርቶ
ማታ በጠጅ ነፅቶ
እራስን ካገኙት
ጠዋት እንደ ክፃን ሁሉንም እረስቶ
ንጡህ ወደኔ ይቅረቡ
ብሎ እንዳላላቸው ጌታ በመዝገቡ
የየዋህነት ገፅ የፍቅር ድርሳኑ
አርጎ እንደፃፋቸው ህፃናት ከሆኑ
ምናለ ቢጠጡ
ምናለ ቢሰክሩ
በቀን ያደፈትን በምሽት ካጠሩ
@getem0
@getem0
#ልብ_የሚነካ
መጋቢት 1993 ዓም ኬቨን ካርተር የተባለ ደቡብ አፍሪቃዊ የፎቶግራፍ ባለሙያ ሱዳን ውስጥ ተከስቶ በነበረው ርሀብ ከተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ልኡክ ጋር ለበጎ አድራጎት ስራ ወደ ደቡብ ሱዳን ያመራል ፡፡ በአንዷ መከረኛ እለትም ይህቺን ከታች የምትመለከቷትን ምስል በካሜራው አስቀረ፡፡
‹‹ርሀብ አድቅቆት የገዛ ራሱን መሸከም ያቃተው ህፃን ልጅ እና ይህን ህጻን ለመብላት የቋመጠ ጥንብ አንሳ›› የረሀብን ክፉ ገፅታ ፣የድርቅን አሰቃቂ ሁነት፣የምስኪኖችን እልቂት ፣ቃላት ሊገልፁ ከሚችሉበት አቅም በላይ በሆነ መንገድ በድንቅ ካሜራው ለአለም አስቃኘ፡፡ ‹‹ቀጫጫ እጆች እንኳን ለመሮጥ፣ለመቦረቅ ይቅርና የገዛ አካሉን ለመሸከም ያዳገተው እግር፣ መቆም የከበደው ገላ እና በርሀብ በሞቱ ሰዎች የደለበ ፈርጣማ አሞራ!!››
ይህን ፎቶ ከወራት በኃላ በ 1993 ዓም ለኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ተሸጦ ታተመ፡፡ ምስሉ በመላው አለም ታየ፡፡ፎቶግራፈሩ፣ክብር እና ዝናን አተረፈ፡፡ ተሸለመ፣ተሞገሰ፡፡ዓለም ስለፎቶግራፈሩ አወራ፡፡
ከዚህ ሽልማት በኃላ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በአንድ አስተዋይ ጋዜጠኛ የተወረወረች ያልተጠበቀች ጥያቄ ግን የህይወቱን አቅጣጫ እስከወዲያኛው ቀየረችው፤ አመሳቀለችው፡፡
‹‹ህፃኗ ልጅ እንዴት ሆነች….ታደግካት?!!>> አይኖቹ ፈጠጡ….ላብ አጠመቀው………ቃላት ከአንደበቱ ጠፋ!! በምናብ ወደ ደቡብ ሱዳንዋ የርሃብ መንደር ተሰደደ፡፡ ጠያቂው ግን ድጋሚ በጩኸት ጠየቀ ‹‹ህፃንዋን ልጅ ታደግካት ?? ነው ፎቶዋን ብቻ ነው ይዘኸው የመጣህ????›› ካርተር ጋዜጣዊ መግለጫውን አቋርጦ ወጣ፡፡ ከወዳጅ ከዘመድ ሁሉ ተሰወረ፡፡ ከራሱ ጋር ተጣልቶ ለብቻው ውሳኔ አልባ ዶሴ ከፈተ፡፡ በገዳይዋ ፊት ጥሏት የሄደው የጎስቋላ ህፃን ነፍስ ለወራት እንቅልፍ ነሳው፡፡ ካርተር ራሱን ወነጀለ፡፡የፎቶግራፍ ሽልማቱን ባሸነፈ በሦስት ወሩ በልጅነቱ ሲቦርቅ ባደገባት ‹‹ፓርክሞር›› በተባለች ለምለም ቀዬ በ33 አመቱ እራሱን ገድሎ ተገኘ፡፡ራሱን የሞት ፍርድ ፈረደበት ፡
መጋቢት 1993 ዓም ኬቨን ካርተር የተባለ ደቡብ አፍሪቃዊ የፎቶግራፍ ባለሙያ ሱዳን ውስጥ ተከስቶ በነበረው ርሀብ ከተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ልኡክ ጋር ለበጎ አድራጎት ስራ ወደ ደቡብ ሱዳን ያመራል ፡፡ በአንዷ መከረኛ እለትም ይህቺን ከታች የምትመለከቷትን ምስል በካሜራው አስቀረ፡፡
‹‹ርሀብ አድቅቆት የገዛ ራሱን መሸከም ያቃተው ህፃን ልጅ እና ይህን ህጻን ለመብላት የቋመጠ ጥንብ አንሳ›› የረሀብን ክፉ ገፅታ ፣የድርቅን አሰቃቂ ሁነት፣የምስኪኖችን እልቂት ፣ቃላት ሊገልፁ ከሚችሉበት አቅም በላይ በሆነ መንገድ በድንቅ ካሜራው ለአለም አስቃኘ፡፡ ‹‹ቀጫጫ እጆች እንኳን ለመሮጥ፣ለመቦረቅ ይቅርና የገዛ አካሉን ለመሸከም ያዳገተው እግር፣ መቆም የከበደው ገላ እና በርሀብ በሞቱ ሰዎች የደለበ ፈርጣማ አሞራ!!››
ይህን ፎቶ ከወራት በኃላ በ 1993 ዓም ለኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ተሸጦ ታተመ፡፡ ምስሉ በመላው አለም ታየ፡፡ፎቶግራፈሩ፣ክብር እና ዝናን አተረፈ፡፡ ተሸለመ፣ተሞገሰ፡፡ዓለም ስለፎቶግራፈሩ አወራ፡፡
ከዚህ ሽልማት በኃላ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በአንድ አስተዋይ ጋዜጠኛ የተወረወረች ያልተጠበቀች ጥያቄ ግን የህይወቱን አቅጣጫ እስከወዲያኛው ቀየረችው፤ አመሳቀለችው፡፡
‹‹ህፃኗ ልጅ እንዴት ሆነች….ታደግካት?!!>> አይኖቹ ፈጠጡ….ላብ አጠመቀው………ቃላት ከአንደበቱ ጠፋ!! በምናብ ወደ ደቡብ ሱዳንዋ የርሃብ መንደር ተሰደደ፡፡ ጠያቂው ግን ድጋሚ በጩኸት ጠየቀ ‹‹ህፃንዋን ልጅ ታደግካት ?? ነው ፎቶዋን ብቻ ነው ይዘኸው የመጣህ????›› ካርተር ጋዜጣዊ መግለጫውን አቋርጦ ወጣ፡፡ ከወዳጅ ከዘመድ ሁሉ ተሰወረ፡፡ ከራሱ ጋር ተጣልቶ ለብቻው ውሳኔ አልባ ዶሴ ከፈተ፡፡ በገዳይዋ ፊት ጥሏት የሄደው የጎስቋላ ህፃን ነፍስ ለወራት እንቅልፍ ነሳው፡፡ ካርተር ራሱን ወነጀለ፡፡የፎቶግራፍ ሽልማቱን ባሸነፈ በሦስት ወሩ በልጅነቱ ሲቦርቅ ባደገባት ‹‹ፓርክሞር›› በተባለች ለምለም ቀዬ በ33 አመቱ እራሱን ገድሎ ተገኘ፡፡ራሱን የሞት ፍርድ ፈረደበት ፡
☁አንድ አርገን ደመና☁
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በሰማይ ተሰባሰብ አንዴ ጩህ ደመና፤
ጩኸትህን ሰምተን፣
ዝናብ ልንጠለል፣
እኔና ልጅቷ እንመጣለንና።
በዛ በምትወደው በዝናቡ ልጅህ አንዴ ደምንልኝ፤
ለሰው የማልነግረው በልቤ ላይ ያለ እኔ ጉዳይ አለኝ።
አንተ እኮ ስትጮህ!
አንተ እኮ ስትደምን!
አንድ ታደርጋለህ እንኳን እኔና እሷን ርግብና እባብን።
እሺ በፈጣሪ እሺ ባለም ጌታ፤
ክፉውን በሚያስር ደግን በሚፈታ።
እረ በኤልሻዳይ አንተን ባበጃጀው፤
አንዴ በሰማዩ ብትደምን ምነው።
ዛሬ ብትሄድም ትታኝ በጎዳና፤
አንተ ስትደምን ዝናብህን ፈርታ ትመጣለችና።
ለመጀመርያ ቀን እጄን የነካች፤
ለመጀመርያ ቀን ክንዴ እሷን ያቀፈው፤
አንተ በሰማይ ላይ ስለደመንክ ነው፣
ስለዘነብክ ነው።
ስለዚ ደመና!
እኔን ተወኝና እሺ በዛ ፍቅር፤
እሺ ደምንልኝ እሺ ካፍያክ ይቅር።
ዛሬ እኔን አልፋ ውዴ ሄዳለችና፤
ልክ እንደ ድሮአችን አንድ አርገን ደመና።
ⓜⓡ◦ ⓣⓡⓤⓜⓟ
2011 O.15
@getem0
@getem0
ለአስተያየት/ግጥም ለመላክ
@dada_habtish
@dada_habtish
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በሰማይ ተሰባሰብ አንዴ ጩህ ደመና፤
ጩኸትህን ሰምተን፣
ዝናብ ልንጠለል፣
እኔና ልጅቷ እንመጣለንና።
በዛ በምትወደው በዝናቡ ልጅህ አንዴ ደምንልኝ፤
ለሰው የማልነግረው በልቤ ላይ ያለ እኔ ጉዳይ አለኝ።
አንተ እኮ ስትጮህ!
አንተ እኮ ስትደምን!
አንድ ታደርጋለህ እንኳን እኔና እሷን ርግብና እባብን።
እሺ በፈጣሪ እሺ ባለም ጌታ፤
ክፉውን በሚያስር ደግን በሚፈታ።
እረ በኤልሻዳይ አንተን ባበጃጀው፤
አንዴ በሰማዩ ብትደምን ምነው።
ዛሬ ብትሄድም ትታኝ በጎዳና፤
አንተ ስትደምን ዝናብህን ፈርታ ትመጣለችና።
ለመጀመርያ ቀን እጄን የነካች፤
ለመጀመርያ ቀን ክንዴ እሷን ያቀፈው፤
አንተ በሰማይ ላይ ስለደመንክ ነው፣
ስለዘነብክ ነው።
ስለዚ ደመና!
እኔን ተወኝና እሺ በዛ ፍቅር፤
እሺ ደምንልኝ እሺ ካፍያክ ይቅር።
ዛሬ እኔን አልፋ ውዴ ሄዳለችና፤
ልክ እንደ ድሮአችን አንድ አርገን ደመና።
ⓜⓡ◦ ⓣⓡⓤⓜⓟ
2011 O.15
@getem0
@getem0
ለአስተያየት/ግጥም ለመላክ
@dada_habtish
@dada_habtish
ቀጥረሽኝ....
ፈላስፋ አደረግሽኝ(ርእሱ ነው)
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
።።።።
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
"የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።፣።።፣።፣
እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
።።።።
ወደ ጫማዬ ሳይ !
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!
@getem0
@getem0
ፈላስፋ አደረግሽኝ(ርእሱ ነው)
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
።።።።
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
"የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።፣።።፣።፣
እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
።።።።
ወደ ጫማዬ ሳይ !
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!
@getem0
@getem0
#ይሄን_ታውቂው_ይሆን
.
ኤፊ ማክ
.
የቤቴን መግቢያ በር ፣
አሽሙረኛ አናፂ ፣ ወዳንቺ አቁሞት
ስትወጪ እንደ ፀሀይ ፣
ስትገቢ እንደጀምበር ፣ አያለሁ ባግራሞት
ታውቂው ግን እኔንጃ ፣
ተፈጥሮሽ ካይን ጋር ፣ እንዳለው ቃለ ውል
በሄድሽበት መንገድ ፣
ላፍታ ያየሽ ሁሉ ፣ አብሮሽ እንደሚውል
እንኳን የዘየርሽው ፣
ያኮረፍሺው ቢኖር ፣ እንዴት ሆኖ ሊሆን
የረገጥሽው አፈር ፣
ፍቅርሽ ለደቆሰው ፣ መዳኒት እንደሆን
ይሄን ታውቂው ይሆን?
ከሳቅሽ ሚቀዳው ፣
ካዘንሽ ሚሸመን ፣ የከተማው አየር
እንኳን የቤታችን ፣
የሰፈሩ ጠረን ፣ ባንቺ እንደሚቀየር
ሰንበት አስቀድሰሽ ፣
የቅድስናሽ ልክ ፣ በሰው አፍ ሲተረክ
እንኳን ጎረቤትሽ ፣
ሀገሬው በሙላ ፣ ባንቺ እንደሚባረክ
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አድባር እንደሚሉሽ ፣
ጥለት ሲዘቀዘቅ ፣ ሀዘን ቤት ሲጠና
አልቃሽ እና አስለቃሽ ፣
ሀዘንተኛ ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚፅናና
ፍቅር እና ክብር ፣
ሰዋዊ ግብረገብ ፣ በጎደላት አለም
ቅንዝረኛ ወጣት ፣
አየኋትኝ ብሎ ፣ እንደ ሚስለመለም
ኑሮሽ ሲስተካከል ፣
የቀበሌው ኗሪ ፣ ባንቺ እንደሚሸለም
ካንድ እራስሽ አልፈሽ ፣
ከስጡኝ ተላልፈሽ ፣ ስተርፊ ለብድር
አንዴ የማይበላ ፣
የድሃው ሰፈር ሰው ፣ ጠግቦ እንደሚያድር።
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አያድርገውና...
ድንገት ወንድ ካየን ፣ እቤትሽ ከትሞ
እኔና መሰሌ ፣
ወር እንደምንተኛ ፣ ጨጓራችን ታሞ
ይሄን ታውቂው ሆን?
አታውቂው ይሆናል ፣ እኔ ግን አውቃለሁ
በጉርብትናዬ...
ወድጄሽ ወድጄሽ ፣ ወድጄሽ አልቃለሁ።
።።።።።
@getem0
@getem0
.
ኤፊ ማክ
.
የቤቴን መግቢያ በር ፣
አሽሙረኛ አናፂ ፣ ወዳንቺ አቁሞት
ስትወጪ እንደ ፀሀይ ፣
ስትገቢ እንደጀምበር ፣ አያለሁ ባግራሞት
ታውቂው ግን እኔንጃ ፣
ተፈጥሮሽ ካይን ጋር ፣ እንዳለው ቃለ ውል
በሄድሽበት መንገድ ፣
ላፍታ ያየሽ ሁሉ ፣ አብሮሽ እንደሚውል
እንኳን የዘየርሽው ፣
ያኮረፍሺው ቢኖር ፣ እንዴት ሆኖ ሊሆን
የረገጥሽው አፈር ፣
ፍቅርሽ ለደቆሰው ፣ መዳኒት እንደሆን
ይሄን ታውቂው ይሆን?
ከሳቅሽ ሚቀዳው ፣
ካዘንሽ ሚሸመን ፣ የከተማው አየር
እንኳን የቤታችን ፣
የሰፈሩ ጠረን ፣ ባንቺ እንደሚቀየር
ሰንበት አስቀድሰሽ ፣
የቅድስናሽ ልክ ፣ በሰው አፍ ሲተረክ
እንኳን ጎረቤትሽ ፣
ሀገሬው በሙላ ፣ ባንቺ እንደሚባረክ
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አድባር እንደሚሉሽ ፣
ጥለት ሲዘቀዘቅ ፣ ሀዘን ቤት ሲጠና
አልቃሽ እና አስለቃሽ ፣
ሀዘንተኛ ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚፅናና
ፍቅር እና ክብር ፣
ሰዋዊ ግብረገብ ፣ በጎደላት አለም
ቅንዝረኛ ወጣት ፣
አየኋትኝ ብሎ ፣ እንደ ሚስለመለም
ኑሮሽ ሲስተካከል ፣
የቀበሌው ኗሪ ፣ ባንቺ እንደሚሸለም
ካንድ እራስሽ አልፈሽ ፣
ከስጡኝ ተላልፈሽ ፣ ስተርፊ ለብድር
አንዴ የማይበላ ፣
የድሃው ሰፈር ሰው ፣ ጠግቦ እንደሚያድር።
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አያድርገውና...
ድንገት ወንድ ካየን ፣ እቤትሽ ከትሞ
እኔና መሰሌ ፣
ወር እንደምንተኛ ፣ ጨጓራችን ታሞ
ይሄን ታውቂው ሆን?
አታውቂው ይሆናል ፣ እኔ ግን አውቃለሁ
በጉርብትናዬ...
ወድጄሽ ወድጄሽ ፣ ወድጄሽ አልቃለሁ።
።።።።።
@getem0
@getem0
።።።በላይ በቀለ ወያ።።።
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ረስታ ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ ፣ የሁሉም የሆነው!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ....
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅን ዐይን..
ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ...
ትንሽ ስትዘነጊኝ ፣ ብዙ እንደማስብ!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!
።።፣፣፣፣፣፣።።።።፣፣፣፣፣፣።።።።።።።
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡
ነግሬሽ ነበረ
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ስትጥል ፣ እድሜዋ ይሔዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ጭንቅላቴን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው!
።።።።
ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ።
ግን እነግርሻለሁ ፣ ዛሬም ሳልታበይ
ነግሪያት ነበር ስል ፣ አንቺ ሰደበኝ በይ።
።።።
ግን እነግርሻለሁ
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ያፈቅራታል ፣ አንዱም ጋር የለችም!!!
@getem0
@getem0
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ረስታ ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ ፣ የሁሉም የሆነው!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ....
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅን ዐይን..
ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ...
ትንሽ ስትዘነጊኝ ፣ ብዙ እንደማስብ!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!
።።፣፣፣፣፣፣።።።።፣፣፣፣፣፣።።።።።።።
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡
ነግሬሽ ነበረ
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ስትጥል ፣ እድሜዋ ይሔዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ጭንቅላቴን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው!
።።።።
ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ።
ግን እነግርሻለሁ ፣ ዛሬም ሳልታበይ
ነግሪያት ነበር ስል ፣ አንቺ ሰደበኝ በይ።
።።።
ግን እነግርሻለሁ
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ያፈቅራታል ፣ አንዱም ጋር የለችም!!!
@getem0
@getem0
ቃላቶች አጠሩኝ
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ድንገት ሳስታውስሽ ውል ስትይብኝ፣
እንቅልፌ አባሮ ትዝታሽ ሲጠራኝ፣
ታድያ በዚህ ጊዜ ደብተሬን አንስቸ እሞነጭራለሁ፣
ያውብ ስብዕናሽን እከትብላሻለሁ፣
ያውብ አካልሽን በብዕሬ ልከትብ ጉዞ እጀመራለሁ፣
ጉዞየን ጀምሬ ገና ሳልጨርሰው መሀል እቀራለሁ፣
ቆንጆ በሀሪሽን መግለጫ ቃላቶች ፈልጌ ፈልጌ ፈልጌም አጣለሁ፣
ግን ተስፍም አልቆርጥም አፍጨረጨራለሁ፣
የቻልኩትን ያክል እሞነጭራለሁ።
ግና ብናባቴ ቃላቶች አጣሁኝ፣
የማደረገው ባጣ ቃላቶች ሲያጥሩብኝ፣
ዝም ብየ አሳንሽ እንከን የለሽ አልኩኝ፣
ግን ፍቅሬ ይቅርታ አሳነስኩሽና እንዳትቀየሚኝ፣
ዝም ብለሽ ተረጅ ቃላቶች አነሱኝ፣
እራሳቸው አንስው እኔንም ጉድ ሰሩኝ፣
ያውብ አንቺነትሽን ለመግለፅ ስሞክር መንገድ ላይ አስቆሞኝ፣
ውዴ አንችን ለመግለፅ ቃላቶች አጠሩኝ።
✍ Seye ibnu nur
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ድንገት ሳስታውስሽ ውል ስትይብኝ፣
እንቅልፌ አባሮ ትዝታሽ ሲጠራኝ፣
ታድያ በዚህ ጊዜ ደብተሬን አንስቸ እሞነጭራለሁ፣
ያውብ ስብዕናሽን እከትብላሻለሁ፣
ያውብ አካልሽን በብዕሬ ልከትብ ጉዞ እጀመራለሁ፣
ጉዞየን ጀምሬ ገና ሳልጨርሰው መሀል እቀራለሁ፣
ቆንጆ በሀሪሽን መግለጫ ቃላቶች ፈልጌ ፈልጌ ፈልጌም አጣለሁ፣
ግን ተስፍም አልቆርጥም አፍጨረጨራለሁ፣
የቻልኩትን ያክል እሞነጭራለሁ።
ግና ብናባቴ ቃላቶች አጣሁኝ፣
የማደረገው ባጣ ቃላቶች ሲያጥሩብኝ፣
ዝም ብየ አሳንሽ እንከን የለሽ አልኩኝ፣
ግን ፍቅሬ ይቅርታ አሳነስኩሽና እንዳትቀየሚኝ፣
ዝም ብለሽ ተረጅ ቃላቶች አነሱኝ፣
እራሳቸው አንስው እኔንም ጉድ ሰሩኝ፣
ያውብ አንቺነትሽን ለመግለፅ ስሞክር መንገድ ላይ አስቆሞኝ፣
ውዴ አንችን ለመግለፅ ቃላቶች አጠሩኝ።
✍ Seye ibnu nur
የወፍ መንገድ
(መዘክር ግርማ)
"እንሂድ" አለችኝ፣ ተነሥታ እንደዘበት
"እንሂድ" አለችኝ ፣ወፍ ወደ ጮኸበት
"እውነት?!
እንሂድ ምናሻኝ ፣ አሁኑ እንነሳ
ግን የምንደርበው ፣ ልብስ ብንይዝሳ?"
ይችን ቃል ባወጣ
በቁጣ
"ከመቼ ወዲህ ነው ፣ ወፍ ልብስ የምታውቀው? ይልቅ እሷን ምሰል ፣ ልብስህን አውልቀው!"
ብላኝ ልብሷን ጥላ
ትታኝ ገሰገሰች ፣ ወፏን ተከትላ፡፡
"እሺ ስንቅ እንያዝ?" ልላት አሰብኩና
ተውኩት ሳልጀምረው
የትኛዋ ወፍ ነች፣ስንቅ ይዛ የምትዞረው?!
በቃ ተከተልኳት፣
ጥብቅ አ'ረገችኝ ፣ጥብቅ አደረኳት፡፡
አንደበቴ ሰላ ፣ ዝማሬ ጀመረው
ልቤ ክንፍ አወጣ፣ መንሳፈፍ አማረው
ከመቼ ወዲህ ነው፣ ወፍ የማትበረው?!
በ መዘክር ግርማ (ወደ መንገድ ሰዎች)
2010
@getem0
@getem0
(መዘክር ግርማ)
"እንሂድ" አለችኝ፣ ተነሥታ እንደዘበት
"እንሂድ" አለችኝ ፣ወፍ ወደ ጮኸበት
"እውነት?!
እንሂድ ምናሻኝ ፣ አሁኑ እንነሳ
ግን የምንደርበው ፣ ልብስ ብንይዝሳ?"
ይችን ቃል ባወጣ
በቁጣ
"ከመቼ ወዲህ ነው ፣ ወፍ ልብስ የምታውቀው? ይልቅ እሷን ምሰል ፣ ልብስህን አውልቀው!"
ብላኝ ልብሷን ጥላ
ትታኝ ገሰገሰች ፣ ወፏን ተከትላ፡፡
"እሺ ስንቅ እንያዝ?" ልላት አሰብኩና
ተውኩት ሳልጀምረው
የትኛዋ ወፍ ነች፣ስንቅ ይዛ የምትዞረው?!
በቃ ተከተልኳት፣
ጥብቅ አ'ረገችኝ ፣ጥብቅ አደረኳት፡፡
አንደበቴ ሰላ ፣ ዝማሬ ጀመረው
ልቤ ክንፍ አወጣ፣ መንሳፈፍ አማረው
ከመቼ ወዲህ ነው፣ ወፍ የማትበረው?!
በ መዘክር ግርማ (ወደ መንገድ ሰዎች)
2010
@getem0
@getem0
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የሶስት ቀናት የአውሮፓ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ከማድረግ በተጨማሪ በትናንትናው ዕለት ከተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ለመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በፍራንክፈርት ስታዲየም ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸውም “አንድ ሆነን ለለውጥ እንነሣ፤ ዘመኑ የሚያስተኛ አይደለም፤ ተለያይተንም አንችለውም፡፡ ዛሬ ላይ ተባብረን በርትተን በሠለጠነ መንገድ በመሥራት ነገን አብረን እንገንባ፤ ይሄ ሁሉ ውጣ ውረድ አልፎ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በእግራችን እየተራመድን የዛሬዋን ቀን በደስታ አስታውሰን እንኳንም ለዚህች ታላቅ ሀገር ደከምን ብለን በደስታ እንደምንሞላ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።
(አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገጻችው)
@getem0
@getem0
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ከማድረግ በተጨማሪ በትናንትናው ዕለት ከተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ለመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በፍራንክፈርት ስታዲየም ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸውም “አንድ ሆነን ለለውጥ እንነሣ፤ ዘመኑ የሚያስተኛ አይደለም፤ ተለያይተንም አንችለውም፡፡ ዛሬ ላይ ተባብረን በርትተን በሠለጠነ መንገድ በመሥራት ነገን አብረን እንገንባ፤ ይሄ ሁሉ ውጣ ውረድ አልፎ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በእግራችን እየተራመድን የዛሬዋን ቀን በደስታ አስታውሰን እንኳንም ለዚህች ታላቅ ሀገር ደከምን ብለን በደስታ እንደምንሞላ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።
(አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገጻችው)
@getem0
@getem0