✥ ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ።
ከላይ ለተጠቀሰውን ጥያቄ ይሔው መልሰናልን።
👉ውዶቸ በሕንጻው ቤተ እግዚአብሔር ተገኝተን እንሳለማለን እንሰግዳለን ይኸውም ለባለቤቱ ያለንን ፍቅርና አክብሮት ለመግልጽ ነው ።የመሳለማችን ወይም የመስገዳችን ምስጢር በቤተ እግዚአብሔር ፊት ሰለሆነ የምንስግደው ለእግዚአብሔር እንጂ ለሕንጻው አይደለም
✥✥ዘጸ 33÷10 ሙሴም ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ የደመና ዓምድ ይወርድ ነበር ፥በድንኳኑም ደጃፍ ይቆም ነበር እግዚአብሔርም ሙሴን ይናገረው ነበር ።ሕዝቡም ሁሉ የደመናው ዓምድ በድንኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር ህዝቡም ሁሉ ተንስቶ እያንዳንዱ በድንኳኑ ደጃፍ ይስግድ ነበር።
✥👉፪ኛ ዜና 7÷1-3 የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እዳቱ ሲወርድ የእግዚአብሔርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር በወለሉም ላይ በግንባራቸው ወደ ምድረ ተደፍተው ሰገዱ።እርሱም መልካም ነውና፥ምህርቱም ለዘለዓለም ነውና ብለውም እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
✥👉፪ኛ ሳሙ 12÷20 ዳዊትም ከምድር ተንስቶ ታጠበ፥ተቀባም፥ ልብሱንም ለወጠ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገብቶ ሰገደ።
✥👉መዝ 5÷7 እኔ ግን በምህረት ብዛት ወደ ቤትህ እግባለህ አንተንም በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እስግዳለሁ።
✥👉መዝ 29÷2 የስሙን ክብር ለእግዚአብሄር አምጡ፥በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ
✥👉መዝ 96 ፥9 በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ
✥👉መዝ 132÷7 ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንስግዳለን ።
✥👉መዝ 138 ÷2 ወደ ቅዱስ መቅደስህ እስግዳለሁ ስለ ምሕርት ና ስለ እውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ ፥በሁሉ ላይ ስምህን ከፍ ከፍ አደርጋለሁ ።
✥👉ሕዝ 46፥1-2 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦አለቃውም በስተ ወጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መንገደ ገበቶ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም ፥ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ና የድኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርቡ፥እርሱም በበሩ መድረክ ላይ ይስገድ ።
✥👉፩ኛ ነገ 9÷3 ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት…ሠርቶ በፍጸመ እግዚአብሔርም አለው፦በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ለመናህን ሰምቻለሁ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ ዓይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ።
✥👉ሐዋ.ሥራ 18÷22 ወደ ቂሣርያም በደረሰ ጊዜ ወጥቶ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ከሰጠ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወረደ።
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
✥ @GEB19bot ✥
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏

አላመሰግንም ከየት የመጣ ነው?
♥️♥️♥️"ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሞላባት አሰምታም እንዲህ አለች አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆናል? የሰላምታሽ ድምጽ ወደኔ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማህጸኔ ዘሏልና" ሉቃ ፩፥፳፰-፵፫
✔️✔️ልብ በሉ ሰላምታዋ መንፈስ ቅዱስን የሚሞላ ሴት እንዴት የተመረጠች ናት?
✔️✔️በመንፈስ ቅዱስ የተሞላች አረጋዊት ሴት አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የምትባል ሴት እንዴት አይነት መመረጥ ነው በኤልሳቤጥ ብቻ አይደለም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ይህንኑ ቃል አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ብሏታል ምን አይነት መመረጥ ነው?
✔️✔️ሰላምታዋን በሰማ ጊዜ በማሕጸን ያለ ጽንስ እንኳ በደስታ የዘለለ ምን አይነት ቅድስና ነው?
✔️✔️ታዲያ በመንፈስ ቅዱስ ተመልታ ኤልሳቤጥ ካመሰገነች ድንግል ማርያምን ፕሮቴስታንት አላመሰግንም የሚል ምን ተሞልቶ ነው?
♥️♥️♥️በመልአክ አንደበት ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንች ጋር ነውና፤ አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የተባለችን እናት እኛም እንደመልአኩ እናመሰግናታለን፡፡
♦️♦️♦️እኛስ መንፈስ ቅዱስን ተመልታ እመቤታችንን እንዳመሰገነቻት ኤልሳቤጥ እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እናመሰግናታለን መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን እንድትመሰ ን ሲያደርግ አይተናልና፡፡ የጌታዬ እናት እንላታለን በመንፈስ ቅዱስ ሆና የጌታዬ እናት አንች ወደኔ ትመጭ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል፤ አንች ከሰሰቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ፤ የማህጸንሽ ፍሬ የተባረከ ነው.... እያልን እናመሰግናታለን ይህን ያናገሰ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ በግልጽ አይተናልና፡፡
$$$ሰማያዊ መልአክና ምድራዊት ሴት ተባብረው በአንድ ቃል በአንድ መንፈስ ቅዱስ ያመሰገኗትን አላመሰግንም የሚሉ በምን መንፈስ ሆነው ነው? መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን አስመሰገነ እንጅ ሲከለክል አላየንም፡፡ አላመሰግንም የሚሉ ከምን እንዳገኙት እንኳ አይነግሩንም ሰይጣንና ክፉ የገንዘብ ፍቅር ክብሯን ሸፍኖባቸዋልና::
✍️✍️ እኛ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደተረዳነው እንደ መልአኩ ቅዱክ ገብርኤልና ቅድስት ኤልሳቤጥ እናመሰግናታለን፡፡ የአባቶቻችን አምላክ ፍቅሯን በልባችን ጣእመ ውዳሴዋል በከንደበታችን ያብዛልን፡፡አሜን!!!

✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ።አሜን🙏🙏🙏
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ክርስቲያናዊ ግዴታዎች
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
✅ #ጸሎት
✝ጸሎት ሁልጊዜም የህይወት ፍላጎቶችን ሁሉ ከሚገኙበት ከሰፊ ልቦና የሚመነጭ መሆን አለበት፤ በመጽሓፍ ቅዱሳዊ አገላለጽ ተክክለኛ የጸሎት ትርጉም ይህ ነው፡፡
✍"ስለዚህ እላቹሀለሁ የጸለያቹሁትን የለመናቹሁትን ሁሉ እንደገኛቹሁት እመኑ ይሆንላቹሀል"
📖ማር 11፥24
📖ዘዳ 4፥28
📖1ኛ ዜና 7፥14
📖2ኛ ዜና 15፥2
📖ምሳ 8፥17
📖ቆላ 3፥1
✝ሁሉንም የምፈጽመው በእምነት ነው፤ያለ ሃይማኖት እግዚአብሔርን ማገልገል ደሰ ማሰኘት አይቻልም፡፡
✝ጸሎታችንም አገልግሎታችንም በእምነት መቅረብ ካልቻለ ምላሹ ባዶ ነው፡፡
📖ዕብ 11፥6
❓ #ጸሎት_ምንድ_ነው
✝ #ጸሎት ‹‹ ጸለየ›› ከሚለው የግዕዝ ስረወ ቃል የተገኘ ነው፡፡
❓ጸለየ ማለት
✝አመሰገነ ለመነ ዘመረ ማለትን ሲገልጥ ጸሎት ማለት ልመና ምስጋና ዝማሬ ማለት ነው፡፡
✍"ጸሎት ይዕቲ ተናግሮተ ሰበእ ኃበ እግዚአብሔር ልዑል"
✍"ጸሎትስ ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገራት ናት"
📚ፍትሐ ነገስት 14
❓ #ጸሎት_ለማን_ወደ_ማን
✝ጸሎት የሚቀርበው ለእግዚአብሔር (ወደ እግዚአብሄር ነው)፡፡
📖መዝ 64፥2
📖ማቴ 7፥11
✍"የሚታየውን ተስፋ ማድረግ ተስፋ አይደልም"
📖ሮሜ 8፥24-26
✍"የዕለት ምግባችንን ስጠን" ብላቹሁ ለምኑ (ጸልዩ) ተብሎ ታዟል፡፡
📖ማቴ 6፥16
📖መዝ 80፥10
✝ፍጹም ዕርዳታን የምናገኘው ከእረሱ ነው።
"✍በመከራ ቀን ጥራኝ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ"
📖መዝ 49፡15
✝ነገር ግን ጸሎታችን ከፍላጋችን ከጥርጥር የጸዳ በእውነትና በእምነት የጸና መሆን ይገባዋል፡፡
📖ሉቃ 11፥1-13 ፤ 18፥1-18
✅ #እንዴት_መጸለይ_እንደሚገባ
✝ጌታችን ክርስቶስ እንዴት መጸለይ እንደሚገባ አስተምሩአል፡፡
📖ሉቃ 11፥11-4
📖ማቴ 3፥31-36
📖መዝ 104፥4
✅ #የጸሎት_ስርዓቶች
✝ጸሎት በማንኛውም ጊዜ በየትኛውም ቦታ ሊጸለይ ይችላል፡፡
1⃣ #ቀዊም
✝ለጸሎት በተነሳን ጊዜ ውስጣዊና አፋአዊ ሁለንተናን አዘጋጅቶ አለባበስን አስተካክሎ መቆም ነው፡፡
✍"ማዕለዳ በፊትህ እቆማለሁ ለአንተም ዕታያለሁ"
📖መዝ 5፥3
📖ዘፍ 24፥12-14
2⃣ #ቀኒተ_ኃቄ
✝ወገብን ታጥቆ ፊትን ወደ ምስራቅ መልሶ መቆም ነው።
✍"ጌታችን ወገባቹሁ የታጠቀ ይሁን"
📖ሉቃ 12፥35
📖ዩሐ 11፥41
📖መዝ 122፥1
📖ማቴ 14፥19
📖ማር 1፥41
📖ማር 7፥34
📖ሉቃ 9፥16
📖ዩሐ 11፥41
3⃣ #አትብ_(ማማተብ)
✝የቀኝ ጣቶችን በመስቀል ቅርጽ (አመሳል) አዘጋጅቶ ወይም በመስቀል ካላይ ወደ ታች ከግራ ወደ ቀኝ ማንቀሳቀስ (ማማተብ) ነው፡፡
✅ #የማማተብ_አስፈላጊነቱ
✝በጸሎት ጊዜ ህሊናን የሚዋጋ ክፉ መንፈስን፤ አጋንንትን ለማባረር የልዑል እግዚአብሄር የባህሪ ጌትነቱን ጥልቀት ምጥቀት ስፋት፤ ምልዓት ለማመልከት የአለም መድህን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ ለመግለጥ ነገረ መስቀሉን አምላክ በመስቀሉ የፈጸመውን የድህነት ስራ ለማሰብ በግራ ወድቀን የነበርነውን ወደ ቀኝ እንደመለሰን ከሞት ወደ ህይወት ከሲኦል ወደ ገነት እንዳሻገረን ለማረጋገጥ ነው፡፡
📖ዘጽ 8፥19፤ 17፥12 ፤31፥18
📖ሉቃ 11፥20
📖ሕዝ 9፥4
📖መዝ 8፥4
📖ምሳ 7፥3
📖ራዕ 7፥3
4⃣ #በመፍራት_በመንቀጠቀጥ_መቆም
✍"ሁልጊዜ እግዚአብሄርን በፊቴ አየዋለሁ በቀኜ ነውና አልታወክም"
📖መዝ 15፥8
✍"በወልደ እኃለ እምሕያው (ክርስቶስ) ፊት መቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁልጊዜ ትጉ"
📖ሉቃ 21፥36
5⃣ #ስግደትና_አስተብረኮት
✝ከጸሎት ስረዓቶች አንዱ ጸሎትን በስግደት መጀመር ነው፤ በጸሎቱ መካከል ስግደትን የሚነኩ ቃላት ሲነሱ መስገድ ነው፡፡
✍"እግዚአብሄርን ልታመልክ ለሱም ብቻ ልትሰግድ"
📖ማቴ 4፥10፤ 26፥36-39
✝ስግደታችን በአካል (በሰውነት) መውደቅ መነሳት ብቻ ሳይሆን በሰውነት በመንፈስ መሆን ይገባዋል፡፡
📖ዩሐ 4፥24 ፤
📖1ኛ ነገስ 18፥42፤ 8፥54
✝የሚጸልይ ሰው አንድ ወይም ሶስት ጊዜ ሰግዶ ጸሎት እንዲጀምር ታዟል፤ በእያንዳንዱ የጸሎት ወቅት 36 ጊዜ መስገድ ግዴታ መሆኑን አበው መንፈሳውያን ያስተምራሉ፡፡
🔹በዕለተ ሰንበትና በበዓለ ሀምሳ ወራት
🔸በጌታችንና በእመቤተችን በዓላት
🔹ስጋውን ደሙን በተቀበሉበት ዕለት ከአድኖና አስተብርኮ በቀር ስግደት አይከናወንም፡፡
📚ፍ ነገ 14፥135-37
📚ኒቅ 20፥32
6⃣ #ሰፊሐ_እድ_(እጅን_መዘርጋ)
✝ከጸለሎት ስርዓቶች አንዱ ጣቶቻችን አንደተዘረጉ ሆነው እጆቻችንን ወደ ላይ በመንሳት ነው፤ ይልቁንም በጥንቅ ጊዜ ልመናን በአጽንኦት በመሚለድ ጊዜ እጆቻችንን ዘርግተን ልንጸልይ ይገባል፡፡
📖መዝ 67፥31
✍"ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ተዘረጋለች"
📖1ኛ ጢሞ 2፡2፤
📖መዝ 87፥1-2፤ 142፥6
📖1ኛ ነገ 8፥23
✅ #እጆችን_የመዘርጋት_ትርጉም
✝የመለኮታዊ ኃይል ምልክት
📖ዘጽ 9፥29
✝በጸሎት የተለመደ ስርዓት
📖1ኛ ነገ 8፥22፤ 38፥54፤
📖መዝ 28፥2
✝የስልጣንና የፍትህ ምልክት
📖ኢሳ 25፥1-11
✝የመፍጠርና የመስራት መግለጫ
📖ኢሳ 45፥12
✝ከጥፋት መንገድ የመመለስና የመቅረብ ምልክት
📖ኢሳ 65፥2
✝ከቀቢጸ ተስፋ የመውጣት ድህነት የመፈለግ ነው
📖ኤር 4፥31
📖ሰቆ 1፥17
📖ዘፍ 48፥13-16
✅ #ለጸሎት_የሚያስፈልጉ_ግዴታዎች
✝ጸሎትን ስንተረጉም ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ነው ብለናል እግዚአብሔር ለባህሪው ንጹህ ቅዱስ ነው፤ ለሱ ወደ እርሱ የሚቀርብ ጸለሎት ከነዚህም መካከል ከጹህ ልብ ከፍጹም እምነትና ፍቅር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
❇️ #እውነተኛ_ፍቅር
✝ኦሪትንና ነብያትን አጠቃለው የሚተረጉሙ ሁለቱ ትዕዛዛት ፍቅረ እግዚአብሄርና ፍቅረ ቢጽ ናቸው፤ እነዚህ የትዕዛዛት አበጋዞች ብቻ ሳይሆኑ የመልካም ምግባራት ሁሉ መሰረቶች ናቸው፡፡ ቤት ያለ መሰረት አይጸናም፤ ፍቅር ወደ ትሩፋት ወደ ፍጹምነት የሚያደርስ የህሊና መታሰቢያ ነው።
✍"ፍቀረ እግዚአብሄርና ፍቀረ ቢጽ እንደ ሞት እንደ መቃብር የጸናች ናት"
📖መኃ 8፡6
✍"እግዚአብሄርን ስንወድ ትዕዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሄርን ልጆች እንደንወድ በዚህ እናውቃለን"
📖1ኛ ዮሐ 5፥2
✝የሠመረ ጸሎት ለማቅረብ ህይወትን በፍቅር ማሰልጠን ያስፈልጋል፡፡
❇️ #የእምነት_ጽናት
✝ጸሎት የሚቀርበው #በሰማይ #የመትኖር #አባታችን ብላቹህ ለምኑ በተባለው መርህ መሰረት ለሰማያዊ አባታችን ነው፤ ስለሆነም እንደሚሰጠን አምነን ያለጥርጥር መጸለይ ይገባናል፤ መጠራጠር ትልቅ ኃጥያት ነው ጸሎትን ምላሽ ያሳጣዋል፡፡
✍"ጥበብ ያጣ ሰው ቢኖር ለሁሉ በልግስና ከሚሰጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይለምን ሣያጣጥል፤ ሣይሳደብ ይለምን ይሰጠዋል"
📖ያዕ 1፥5-8
📖ምሳ 2፥3
📖ማር 11፥24
📖ሲራ 1፥12-13
📖ሲራ 2፥10
✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን

Forwarded from የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️ (🙏✟ ኤፍሮን ✟🙏👈👉ያብዛን ያበርክተን ማለት ነው።👏)
✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን🙏🙏🙏
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና በአንተ እግዝእትነ ማርያም
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
⛪በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ አግዚአብሔር ከታሰራችሁበት የኃጢአት ማሰሪያ ይፍታችሁ ሲል 12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና 12 ጊዜ ደግሞ በእንተ እግዝእትነ ማርያመ መሐረነ ክርስቶስ ያስብላል፡፡ ካህናትና ምእምናን በሙሉ በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህንኑ 12 ጊዜ እንላለን፡፡
✔💠እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት አቤቱ ክርስቶስ ማረን ሲሆን
✔💠በእንተ እግክእትነ ማርያመ መሐረነ ክርስቶስ ደግመ ስለ እመቤታችን ማረያም ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን ማለት ነው ፡፡
✔💠እስራ ሁለት ጊዜ እግዚኦ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት ፣ በእንተ እግዝእትነ ማርያመ ደግሞ ለሌሉቱ 12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሰራነው ኃጢአት በሃያአራቱ 24ቱ ሰዓት ምሕረትን እናገኝ ዘንድ ነው፡፡
✔💠ሌላው አሥራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት
1. በስመ ሥላሴ ነው ፡፡ በእያንዳንዱ ፊደል
አ ብ ወ ል ድ መ ን ፈ ስ ቅ ዱ ስ
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪
2. የድህነታችን ምክንያት በሆነችው በእመቤታችን ስም ፈደል
ቅ ድ ስ ት ድ ን ግ ል ማ ር ያ ም
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪
✔💠አቆጣጠሩም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደታች ፣ ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት / በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ነው ፡፡
✔💠ከጠቋሚ ጣት ወደታች ፡- አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለቡን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን ፡፡
✔💠መሐል ጣት ወደላይ ፡- ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን በቀለበት ጣት ✔💠ወደታች ስንቆጥር ፡- ለፍርድ መምጣቱን፣
✔💠በትንሿ ጣት ወደላይ ስንወጣ ፡- ደግሞ ሁላችንን በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው ፡፡
✔💠በእንተ እግዝእትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ፡- ከትንሽ ጣት ወደታች ይጀመርና በጠቋሚ ጣት ወደ ላይ ይፈጸማል ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን የሚያሳይ ምሥጢር ነው፡፡
Share
💠💠💠💠💠💠💠💠 💠💠
💠 @Geb19 💠 💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

Forwarded from Yóha baba
የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።
የማቴዎስ ወንጌል 1 : 25
የማቴዎስ ወንጌል 1 : 25
Forwarded from Yóha baba
ግራ ገብቶኛል ለምን እንደተባለ
✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን🙏🙏🙏
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
የበኩር ልጇን
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
👉ውዶቸ በዚህ ክፍል የምናየው መናፍቃን 🙋የሚያነሡት “የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም/ማቴ1:25/” የሚለውን ነው። ስለዚህም የበኩር ልጇን ከወለደች በኋላ ዮሴፍ “በግብር አውቋታል” የሚል አስተሳሰብ በአነርሱ ዘንድ ስላለ እንደሚከተለው አናብራራለን ፡፡
👉“እስክትወልድ አላወቃትም ” ማለት ከወለደች በኋላም አላወቃትም ማለት ነው፡፡
💠“እስከ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁለት አገባብ አለው፡፡
✔- ፍጻሜ ያለው እስከ እና
✔- ፍጻሜ የሌለው እስከ ማለት ነው፡፡
➕⛪“እስከምትወልድ ድረስ” የሚለው ላይ የምናገኘው እስከ ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው፡፡ ትርጉሙም ከወለደች በኋላም በግብር አላወቃትም የሚል ነው፡፡
👉መናፍቃን እዚህ ላይ ያለውን እስከ ፍጻሜ ያለው አድርገው የሚወስዱት ከሆነ የሚከተሉትን ማስረጃዎችን እንዴት ሊተረጉሟቸው እንደሚችሉ እንመልከት፡፡
✔“… ቁራውም የጥፋት ውኃ እስኪጎድል ድረስ አልተመለሰም” ዘፍ8፡7 ይላል፡፡ ይህ ማለት ከጎደለ በኋላም አልተመለሰም ማለት እንጅ ከጎደለ በኋላ ተመለሰ ማለት አይደለም፡፡
✔ “… ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ የነገርኩህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና፣ ዘፍ 28፡15 ይላል፡፡ ይህ ማለት የነገርኩህን ሁሉ ካደረግሁልህ በኋላ ሁሉ አልለይህም ማለት እንጅ የነገርኩህን ሁሉ ካደረግሁልህ በኋላ እተውሃለሁ ማለት አይደለም፡፡
✔“ ሳሙኤልም እስከሞተበት ቀን ድረስ ሳዖልን ለማየት ዳግመኛ አልሄደም” 1ኛ ሳሙ 15፡35 ይላል፡፡ ይህ ማለት ሳሙኤል ከሞተ በኋላ ሳዖልን ሊያይ አልሄደም ማለት እንጅ ከሞተበት ቀን በኋላ ሳዖልን ሊያይ ሄዷል ማለት አይደለም፡፡
✔✔ “…ሜልኮል እስከሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም” 2ኛ ሳሙ6፡23 ይላል፡፡ ይህ ማለት ከሞተች በኋላም ልጅ አልወለደችም ማለት እንጅ ከሞተች በኋላ ልጅ ወልዳለች ማለት አይደለም፡፡ ሰው ከሞተ በኋላ ይወልዳል የሚል እምነት ካላቸው ምናልባት አናውቅም፡፡
✔✔ “… በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰማ፡፡ እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሠረይላችሁም” ኢሳ 22፡14 ይላል፡፡ ይህ ማለት ከሞታችሁ በኋላም በደላችሁ ፈጽሞ አይሰረይላችሁም ማለት እንጅ ከሞታችሁ በኋላ በደላችሁ ይሰረይላችኋል ማለት አይደለም፡፡
✔✔“…የባሪያዪቱም ዓይን ወደ እመቤቷ እንደሆነ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ነው” መዝ 122፡2 ይላል፡፡ ይህ ማለት ከማረን በኋላም ዓይናችን ወደ እግዚአብሔር ነው ማለት እንጅ ከማረን በኋላ ዓይናችንን ወደ እግዚአብሔር አናደርግም ማለት አይደለም፡፡
💠👉“የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም/ማቴ1:25/ ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስን ከወለደች በኋላም ዮሴፍ በግብር አላወቃትም ማለት እንጅ ከወለደች በኋላ ዮሴፍ በግብር አውቋታል ማለት አይደለም።

🌷ከብጹዕ አቡነ ሺኖዳ አንደበት🌷
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
👉"አስታውስ"👈
💠 ደካማነትህን አስታውስ ፣ ያን ጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ
በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም፡፡💠
.............................
💠 የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ ፣ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል፡፡ በእግዚአብሔር
ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል፡፡
ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል።💠
.......................
💠 የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ ፡፡
የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ
ይገባሃልን?
የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል፡፡
ሞት እንዳለ አስታውስ ፣ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ፡፡
̋̋̋ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው፡፡˝ መክብብ 1፡14 ማለትን ትረዳለህ።💠
..........................
💠በእግዚአብሔርፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ ፣ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና።💠
...........................
💠ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ። በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ
ይሆናል፣ ስለዚህም
በከንቱ በመኖር አታጠፋውም፣ "በዋጋ ተገዝታችኋልና" 1ኛ ቆሮ.6:20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ።💠
.........................
💠በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፤ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ።💠
..........................
💠በዚህ ዓለም እንግዳመሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ
ዘወትር አስታውስ። ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ።💠
..........................
💠በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ። ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ
የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና።💠
........................
💠ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ፣ ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ።💠
.........................
💠 የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ።
እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል።💠
...........................
💠 የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ። በውስጥህ
ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን። ዘወትርም ቅዱስ
የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን፡፡💠

✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨✝️
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን🙏🙏🙏
✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨✝️
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
🌷ልጆቼ ሆይ🌷
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
👉ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው፡፡ ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ የሚመጣውን ደስታና ሰላም አትሻ፤ ለዚህኛው ኑሮ ሙትና ለእግዚአብሔር ሕያው ሁን፤ ለእግዚአብሔር ቃል የገባኸውን አትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል፡፡ ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፤ ተጠማ፥ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔር የምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታድናት ዘንድ፡፡”
👉🏽(አባ እንጦንስ)👈🏾

👉ሰበር ዜና
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአሥሩ ማኅበራት ኅ ብረት በየሁለት ሳምንቱ የደረሰበትን ለምዕመናን ለማሳወቅ በገባው ቃል መሠረት ባለፉት አስር ቀናት ከመንግሥት ጋር የተወያየባቸውን ጉዳዮች በመግለጫ አሣውቋል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወም የሚንቀሳቀሰው የአዲስ አበባ አስተባባሪ ኮሚቴ ሒደታዊ መግለጫ፤
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ላይ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም የሚንቀሳቀሰው የአዲስ አበባ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ፣ መስከረም 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ለመስከረም 4 ቀን 2012 ዓ.ም. የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ከመንግሥት በቀረበለት የእንነጋገር ጥያቄ መሠረት ከሚመለከታቸው የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ውይይት በመጀመሩ ኮሚቴው ሰልፉ እንዲዘገይ በመወሠን በችግሮች ላይ ተወያይቶ መፍትሔ ለማሰጠት እንደወሰነ መግለጹ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም፣ በየጊዜው የሚኖረውን የውይይት ሒደት እና ውጤት፣ ቢያንስ በየኹለት ሳምንቱ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ለማሳወቅ ቃል መግባቱም ይታወሳል፡፡
አስተባባሪ ኮሚቴው በገባው ቃል መሠረት፥ ባለፉት ዐሥር ዕለታት፣ በተመረጡ ስድስት ክልሎች እና ኹለት የከተማ አስተዳደሮች፣ ማስረጃዎችን አጠናቅሮና የውይይት አርእስተ ጉዳዮችን ለይቶ ልኡካንን በማሰማራት፣ ከርእሳነ መስተዳድሮች ጀምሮ ከሚመለከታቸው ከፍተኛ መንግሥታዊ ሓላፊዎች ጋራ ሲወያይ ሰንብቷል፡፡ በውይይቱም፣ በዋናነት ከአነሣቸው አንኳር ነጥቦች መካከል፡-
1. በጥቃት ሕይወታቸውን ላጡ ካህናት እና ምእመናን እንዲሁም ለተቃጠሉ እና ለተዘረፉ አብያተ ክርስቲያን ካሳ እንዲከፈል፤
2. ርእዮተ ዓለም መር ከኾኑ ስሑት ትርክቶች የተነሣ በሃይማኖታዊ ማንነታቸው ምክንያት ብቻ ለልዩ ልዩ አካላዊ እና ሥነ ልቡናዊ ጥቃቶች ተዳርገው፥ ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ፣ ከማኅበራዊ ኑሮ የተገለሉ፣ ከሓላፊነት ቦታቸው እና ከሥራ መደባቸው የተባረሩ፣ ዛሬም በዚሁ ጫና ውስጥ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ተገቢውን ፍትሕ እንዲያገኙ፤
3. የቤተ ክርስቲያንን ትክክለኛ ማንነት እና አገራዊ ውለታ በአገባቡ የማይገልጹ፣ ሕጋዊ እና መዋቅራዊ ድጋፍ ያላቸው የሚመስሉ፣ ሌሎች እምነቶችን ለበቀል የሚያነሣሱ በአጠቃላይ ኦርቶዶክሳውያንን ለጥቃት ያመቻቹ እና ያጋለጡ ስሑት ትርክቶች እንዲታረሙ፤
4. ለሕዝብ አገልግሎት የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ሓላፊነት አላግባብ በመጠቀም፣ በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን ላይ ልዩ ልዩ ስልታዊ ጫናዎችን ያደረሱ፣ ቀን ቀጥረው የተከሠቱና ለመከላከል የሚቻሉ ጥቃቶችን ያላስቆሙ፣ ይብሱኑ ጥቃቶቹን ያቀዱና ያቀነባበሩ ባለሥልጣናት፣ በገቢርም የፈጸሙ ቡድኖች እና ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ፤
5. ጥቃቶቹ እና ጫናዎቹ እንዲገቱ ለመንግሥት ጥያቄ ያቀረቡ ኦርቶዶክሳውያን፣ አቤቱታቸው ፖሊቲካዊ መልክ እና ይዘት እየተሰጠው ለእስር እና እንግልት መዳረጋቸው እንዲቆም እና የታሰሩትም እንዲፈቱ፤
6. በልዩ ልዩ ሰበቦች ሽፋን በመንግሥት ሓላፊዎች ፖለቲካዊ ድጋፍ ጭምር በሙሉ እና በከፊል የተነጠቁ የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች እንዲመለሱ፣ ለመመለስ የማያስችል ኹኔታ ካለ ደግሞ ትክ ቦታዎች እንዲሰጡ፤
7. ለዐዲስ አብያተ ክርስቲያን መትከያ፣ ለመካነ መቃብር፣ ለባሕረ ጥምቀት እና ለመስቀል ደመራ በዓል አከባበር እንዲሁም ለራስ አገዝ ልማት የሚውሉ ቦታዎች በሕግ አገባብ እንዲሰጡ፤
8. በተለያዩ አህጉረ ስብከት የሚገኙና የተወረሱ የቤተ ክርስቲያን ቤቶች እና ሕንፃዎች እንዲመለሱ፤
9. በቤተ ክርስቲያን ይዞታ ሥር ለሚገኙ፣ በቀጣይ በሚደረስባቸው ስምምነቶች ለሚመለሱ እና ዐዲስ ለሚሰጡ ቦታዎች፣ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እና/ወይም ደብተር እንዲሰጥ፤
10. በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ኦርቶዶክሳውያን፣ በሕግ አገባብ የተፈቀደላቸውን የሥርዐተ እምነት ነፃነት በመጋፋት እየደረሱባቸው የሚገኙ ጫናዎች እንዲቆሙ፤ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በእነኚህ ነጥቦች መነሻነት፥ የየክልሉ ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የሚመለከታቸው የቢሮ ሓላፊዎች፣ የዞኖች እና የልዩ ወረዳዎች አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በተካሔዱ ውይይቶች፡-
•በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ በስፋት በመወያየት ከሞላ ጎደል መግባባት ላይ ተደርሷል፤
•የጋራ መግባባት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች ለመፍታት የጊዜ ገደብ ተቀምጧል፤
•አፈጻጸማቸውን በቅርበት ለመከታተልና ቀጣይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ በቅንጅት ለመሥራት ከመንግሥት እና ከየአህጉረ ስብከቱ የተውጣጡ አካላት ያሉበት የጋራ ኮሚቴ ተቋቁሟል፤
•በክልሎቹ በተቋቋሙት የጋራ ኮሚቴዎች አስተባባሪነት፣ በየዞኖቹ በመንግሥት እና በቤተ ክርስቲያን ተወካዮች መካከል ጉዳይ ተኮር ጥልቅ ውይይቶች እንዲደረጉ ከስምምነት ተደርሷል፤
•ይህ እንዳለ ኾኖ፣ መግባባት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል በመንግሥት በኩል፥ በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያንንና የምእመናን ቤቶችን መልሶ ግንባታዎች በመጀመር፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተነጠቁ ይዞታዎችን በመመለስ እና የይዞታ ማረጋገጫ ለሌላቸው የአብያተ ክርስቲያን ቦታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ በመስጠት ተግባራዊ ምላሾች ተጀምረዋል፡፡
በአስተባባሪ ኮሚቴው የቀረቡ ጥያቄዎች የተሟላ እና ተገቢ ምላሽ እስከሚያገኙ ድረስ፣ ጥረቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ኮሚቴው ከተደረጉት ውይይቶች በፌዴራል መንግሥትም ደረጃ መታየት የሚገባቸውን ችግሮች በመለየት ከሚመለከታቸው አካላት ጋራ የሚነጋገር ሲኾን፣ ቀደም ሲል ቃል በገባው መሠረት፣ ለየጉዳዮቹ የተቀመጠውን ቀነ ገደብ ተከትሎ ዝርዝር ዘገባ የሚያቀርብ ይኾናል፡፡
በዚህ አጋጣሚ፣
• በተንቀሳቀስንባቸው ቦታዎች ኹሉ፣ ተገቢ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን በማቅረብ፣ ተወካዮችን በመመደብ፣ በውይይቶችም በንቃት እና በመሪነት በመሳተፍ አስተዋፅኦ ለአደረጉ የአህጉረ ስብከት ጽ/ቤቶች፣ በተዋረድ ለሚገኙ የማህበራትና የአገልጋዮች ኅብረት፤ የውይይት መድረኮችን ከማመቻቸት ባሻገር ለልኡካኑ መልካም አቀባበል ለአደረጉ የመንግሥት አካላት ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
• ከሁሉም በላይ መላው ሕዝበ ክርስቲያን የኮሚቴውን ጥሪ በመቀበል ከኮሚቴው ጎን በመሆን ለሰላማዊ ሰልፍ ራሱን በማዘጋጀቱና፤ ሰልፉም እንዲዘገይ ኮሚቴው ያስተላለፈውን መልዕክት በመቀበል ምላሹን በትዕግስት በመጠበቁ ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በቀጣይም መላው ሕዝበ ክርስቲያን የኮሚቴውን ሪፖርትና መልዕክት በትዕግስት እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መስከረም 13 ቀን 2012 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
ምንጭ:-ማህበረ ቅዱሳን

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••
🌷 ኦርቶዶክሳዊ መዝሙርና ምሥጢራዊ ሥርዓቱ🌷
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
👉መዝሙር የባሕርይ አምላክ ልዑል እግዚአበሔር በሰማይና በምድር የሚመሰገንበትና ዐቢይ የጸሎት ክፍል የሆነ ጣዕመ ዜማ ነው፡፡ እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ መዝሙር መልካም ነውና ለአምላካችን መዝሙር ያማረ ነውና እነዚህን ቃላት (መዝ.146፥1፣ዘጸ.15፥1-22፣ ኢሳ.61፥5፣ራእ.15፥1፣ራእ 5፥6-14፣መዝ.65፥1-5 መመልከት ስለ መዝሙር ያስረዳል፡፡
👉✥ከዚህም ጋር መዝሙር ማለትምን ማለት ነው፦ያልን እንደሆነ መዝሙር ፣ዘመረ፣አመሰገነ ካለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙም ምስጋና፣ልመና ወይም መማጸን፣ ማራራት፣ ማስደሰት፣ መደሰት፣ ማዜም ማለት ነው፡፡ ከዚሁም ሌላ እግዚአብሔርን በእጽፍ ድርብ ማመስገን ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የእግዚአብሔር ቃል ፅኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን፡፡ ለአምላክ ለመድኃኒታችን እልል እንበል፡፡ በምሥጋና ወደፊቱ እንድረስ፡፡ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል፡፡ እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና ይለናል፡፡ (መዝ.32፥1-5፣መዝ 149፥1፣ መዝ.150፥1-6 ፣መዝ 80፣1-3፣ማቴ 26፣30፣ማር 14፥26፣የሐዋ 16፥25፣ቆሳ 3፥16-25፣ራእ 14፥1-3፣ማቴ 21፥9፣ማር 11፥9፣ሉቃ 19፥36።
👉መዝሙር ማዜም ማለት ነው ስንልም ዜማ ማለት ራሱ በቀጥታ ሲፈታ ስልት ያለው ጩኸት (ድምፅ ማሰማት) ማለት ነው፡፡
👉ይሁን እንጂ ዜማ የምስጋና ብቻ ሳይሆን የሐዘን፣የልቅሶ፣የቀረርቶ፣የሽለላ፣የፉከራና የደስታ ሁሉ ስሜት መግለጫ ድምፅ ነው (ኢሳ.6$1-5፡፡ ማቴ.26$30) ፡፡
👉ከዚህ ላይ ግን ዜማ ባልን ጊዜ የቤተ ክርስቲያናችንን የምስጋና መዝሙር ድምፅ ማለታችን ነው፡፡ ለምን ቢሉ ዜማ ራሱን የቻለ ጥሬ ቃል (ነባር) ቢሆንም ዘመረ፣አመሰገነ፣አዜመ ካለው ቃል ጋር በጠባይና በግብር ይመሣሠላልና ነው፡፡
የዜማ ምልክቶች
👉የያሬድ ዜማ በቂና ጥሩ ጥሩ ምሳሌ ያላቸው ብዙ ምልክቶች ያሉት ቢሆንም ለአብነት ያህል ግን ስምንቱን ዐበይት ምልክቶች እናያለን፡፡ እነዚህም ዜማውን ለሚማር ደቀ መዝሙርና ለሚዘምረው ሁሉ በምልክትነት ሲያገለግሉ ምሳሌያቸውንና ምሥጢራቸው ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ስለኛ የተቀበለውን መከራ የሚያስታውሱ ናቸው፡፡ እነዚህም የኋላ ሊቃውንት ከጨመ…ቸው ከድርስና ከአንብር በስተቀር ዋና ዋናዎቹ የቅ/ያሬድ ምልክቶች ብቻ ሲዘረዘሩ ይህንን ይመስላሉ፡፡
1. ይዘት - በአይሁድ ጭፍሮች ለመያዙ (ማቴ.26፥50)፣
2. ሂደት - ታሥሮ ለመጐተቱ፣
3. ጭረት - ለግርፋቱ ሰንበር፣
4. ድፋት - አክሊለ ሶክ (የእሾክ አክሊል) ለመድፋቱ፣
5. ደረት - ሲሰቅሉት በመስቀሉ ላይ አንጋለው ከደረቱ ላይ ቆመው እየረገጡት ለመቸንከሩ፣
6. ርክርክ - ለደሙ ነጠብጣብና አወራረድ፣ ለችንካሩ ምልክት፣
7. ቁጥር - በጦር ተወግቶ ፈጽሞ መሞቱ ለመታወቁ፣ እንዲሁም
8. ቅንዓት ደግሞ በቅንዓተ አይሁድ ለመገደሉ፣
👉ምልክትና ማስታወሻዎች ሲሆኑ ስምንት መሆናቸውም ስምንቱም ማኀበረ አይሁድ ተባብረውና መክረው በብዙ ስቃይ ጌታን ለመገደላቸው ምሣሌ ነው፡፡ እነዚህ ስምንቱ ማኀበረ አይሁድ ማን ማናቸው ቢሉ፡-
💠ጸሐፍት ፈሪሣውያን፣
💠ሰዱቃውያን፣
💠ረበናት (መምህራነ አይሁድ)፣
💠መገብተ ምኩራብ (የምኩራብ ሹማምንት)፣
💠መላሕቅተ ሕዝብ (የሕዝብ ሽማግሌዎች
💠ሊቃነ ካሕናት፣
💠ኃጥአንና
💠መጸብሓን (ቀራጮች)ናቸው፡፡
👉በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን የማኀበር ጸሎት ሲደርስ በጣዕመ ዜማ ወይም በመዝሙር ማመስገንና መጸለይ የተለመደና የተወደደ ሥርዓት ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሲከናወን ለምሥጋናውና ለጸሎቱ ማጐልመሻ ሆነው የሚቀርቡትን ንዋየ ቅድሳትና የጸሎቱ ቅደም ተከተል ሁሉ በቂ ምክንያትና ምሳሌ ያለው ሆኖ መገኘቱ እኛን የኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች በጣም ያኮራናል፡፡ ይህንንም ለመረዳት በጸሎተ ማኀሌት ማለት የምስጋና መዝሙር በሚቆምበት ጊዜ የሚፈጸመውን ከልብ መመልከትና ማገናዘብ ይገባናል፡፡
👉✥💠ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር የቱ ነው?
👉ጥንታውያን ኦሪየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በመባል የሚጠሩት ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ሶርያ፣ አርመንና ሕንድ በእምነታቸው (የተዋሕዶን ትምህርተ ሃይማኖት በመጠበቃቸው) አንድ ቢሆኑም በሥርዓተ መዝሙር (ማለትም በመዝሙር ዜማና አቀራረብ) ግን በመጠኑ ይለያያሉ፡፡ለምሳሴ ግብፃውያን የዜማ መሣሪያዎቻቸው ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከቅዳሴ በፊትና በኋላ በመዘመራችን፣ ሌሊት ማኀሌት በመቆማችን፤ ሥርዓታችን ተመሳሳይ ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መዝሙራትን ኦርቶዶክሳዊ ነው የምትለው ትምህርተ ሃይማኖትዋን፣ ሥርዓትዋን፣ ታሪኳንና ትውፊትዋን ሲጠብቅ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ በግብፃውያን ሥርዓት ከዜማቸውና ከመዝሙር መሣሪያዎቻቸው ውጭ መዘመር አይፈቀድም፡፡
👉በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም አንድ መዝሙር #ኦርቶዶክሳዊ ነው፣ የቤተ ክርስቲያን ነው ሊባል የሚችለው በትምህርተ ሃይማኖትዋ፣ በሥርዓትዋ፣ በትውፊትዋ መሠረት፣
የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓት እና ትውፊት የጠበቀ ሲሆን
👉በጉባዔው ሆነ በግል የምንዘምረው፣ አልያም ደግሞ በካሴት አስቀርፀን የምናሳትመው መዝሙር አዕማደ ምሥጢራትን፣ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ታሪከ ቤተ ክርስቲያንንና ሥርዓትዋን መጠበቅ አለበት፡፡
👉ለምሳሌ መዝሙሩ ድንጋዩን ፈንቅሎ ክርስቶስ ተነሥቷል የሚል ስንኝ ቢኖረው ከቤተ ክርስቲያን ትምህርት የወጣ ይሆናል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ የተነሣው መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል እንጂ መቃብሩን ፈንቅሎ መግነዙን ፈትቶ አልነበረምና፡፡ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28 በማለዳ የወጣው የእግዚአብሔር መልአክ በመቃብሩ ደጃፍ ላይ የነበረውን ድንጋይ አንከባልሎ እንደተቀመጠበት ይነግረናል፡፡ በእኩለ ሌሊት ድንጋዩን ያንከባለለው መልአኩ እንጂ ጌታችን የተነሣው በታተመው መቃብር ነወ፡፡
ወይም ደግሞ፡-
👉‹‹በሥላሴ አርአያ የተፈጠረ ሰው
እንደ ዱር አበባ ረግፎ ቀሪ ነው›› የሚል ግጥም ቢኖር የዚህ ግጥም መልእከት ከምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ጋር የሚቃረን ይሆናል፡፡ የሰው ልጅ ፈርሶ በስብሶ፣ እንደ ዱር አበባ ወድቆ የሚቀር ሳይሆን በዳግም ምጽዓት እንደገና ታድሶ የሚነሣ ነው፡፡ ይህ ለእንስሳት ሊቀጸል እንጂ ለሰው ልጁ ሊነገር አይገባውም፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ልዑል እግዚአብሔርን፣ ቅዱሳንን፣ ንዋያተ ቅድሳትን፣ ወዘተ የምትጠራበት፤ እምነቷንና ፍቅርዋን የሚገልጹ ቃላት አሏት፡፡ እነዚህ ቃላት ዘመን ወለዶች ሳይሆኑ ከጥንት ጀምሮ ቅዱሳን አበው ልመናቸውን፣ ምልጃቸውን፣ ምሥጋናቸውን ያቀረቡባቸው፣ ልጆቻቸውን ያስተማሩባቸው፣ አንድ ገጽ ጽሑፍ ሊገልጣቸው የማይችላቸውን ምሥጢራት በአንድ ቃል የገለጡባቸው ናቸው፡፡ የምንዘምራቸው መዝሙሮች እነዚህን

ዕንቁ የሆኑ ቃላት ማፋለስ የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም መልእክቱን ያዛባዋልና፡፡
👉ለምሳሌ አንድ መዝሙር #ኢየሱስ ጓዴ ነው የሚል ቃል ሊጠቀም አይችልም፡፡ ይህንን ቃል የተጠቀመ አባት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የለም፡፡ ቃሉ የጌታችንን ክብር የሚያሳንስ ነውና፡፡ ቤተ ክርስቲያን ጌታችንን አምላክ፣ አምላከ አማልክት፣ የጌቶች ጌታ፣ የንጉሦች ንጉሥ፣ መድኃኒተ ዓለም፣ ወዘተ. እያለች ትጠራዋለች እንጂ እንደ ሥራ ባልደረባ #ጓዴ ብላ አትጠራውም፡፡
👉በአንዳንድ መዝሙራት ላይ ደግሞ ሕዝቡን የበለጠ ለመሳብ ወይንም አንድን ነገር የበለጠ ለመግለጥ እየተባለ ያልተደረገ እንደተደረገ ሆኖ የሚቀርብበት አጋጣሚም አለ፡፡
👉ለምሳሌ ጌታችን #ከአጥንቱ አንድም አይሠበርም (ዘጸ.12÷46) የሚለው ቃል ይፈፀም ዘንድ አጥንቱ አልተሠበረም፡፡ ነገር ግን በአንዳንድ የስቅለት መዝሙራት ላይ #አጥንቱ እስኪሠበር ተገረፈ የሚል ሐረግ ይገኛል፡፡ ይህ ግን ከቅዱሳት መጽሐፍት ትምህርት የወጣ ነው፡፡ ስለ እመቤታችን ሐዘን በሚዘመሩ መዝሙራትም ላይ #በመስቀሉ ሥር ስትወድቅ ስትነሣ እያለቀሰች ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች በሚል አኳኋን ይቀርባል፡፡ ነገር ግን እመቤታችን አስቀድሞ ስምዖን፡፡ ‹‹በነፍስሺ ሰይፍ ያልፋል›› (ሉቃ.2÷35) በማለት ነግሮአት ስለነበር መከራውን ታውቃለች፡፡ ሐዘንዋ ተስፋ የመቁረጥ ሳይሆን የእናትነት ፍቅርዋን የሚገልጥ ነው፡፡
👉ስለዚህ የምንዘምረው መዝሙር የቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓትና ትውፊት የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ይህንንም ለማወቅ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በእምነታቸው በተመሠከረላቸው አባቶችና መምህራን ማሳረም፣ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ጠንቅቶ መማር፣ መጻሕፍት ቅዱሳትን ማንበብና በእግዚአብሔር ቤት ዘወትር መኖር ዋና መፍትሔዎቹ ናቸው፡፡
✥💠ዜማው ያሬዳዊ ሲሆን💠✥
👉ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 13ዐዐ ዓመታት ያህል ለልዑል እግዚአብሔር ምሥጋናዋን ታቀርብ የነበረበት ዜማ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ነው፡፡ በዚህ ዜማ ተጠቅመው አያሌ ቅዱሳን ምሥጋናቸው በልዑል እግዚአብሔር ፊት ቀርቦላቸዋል፡፡ ክብረ ቅዱሳንንና፣ ርስት መንግስተ ሰማያትን ወርሰዋል፡፡ በየጊዜው የተነሡ የቤተ ክርስቲያናችን አበው (እነ አባ ጊዮርጊስ፣ እነ አባ ዘድንግል) ሰዓታትን፣ ማኀሌተ ጽጌን፣ ሰቆቃወ ድንግልን በዚሁ በያሬድ ዜማ ዘመሩት እንጂ ሌላ ዜማ ለመፍጠር አልፈለጉም፡፡ እግዚአብሔር የዘረጋው መንገድ እያለ ለምን ሌላ መንገድ ይፍጠሩ!
👉አሁንም ሆነ ለወደፊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እግዚአብሔር በቅዱስ ያሬድ አማካኝነት የሰጣትን ይህንን ዜማ እንደምትጠቀምበት ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ባወጣው ደንብ ምዕ.5/26/1/ሀ ላይ ደንግጓል፡፡ አጽንቷል፡፡ በመሆኑም ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ የምንዘምረው መዝሙር ይህን ዜማ የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
ምክንያቱም፣
👉ዜማው እግዚአብሔር ወዶ ፈቅዶ የሰጠን እንጂ ቅዱስ ያሬድ በጥበቡ የተፈላስፎ፣ ተራቅቆ፣ ያመጣው አይደለም፡፡
👉ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንድንጠቀምበት፤አባታችን እግዚአብሔርንም እድናመሰግንበት ጠብቃ ያቆየችን ወስናም የሰጠችን ነውና፡፡
👉የዜማው ሥርዓት፣ ባሕልና የመሣሪያዎቹ ትርጉም ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ መልእክት ያለው ነውና፡፡
👉አንዳንድ ዘማሪያን የመናፍቃኑን ዜማ ስለሚወዱት በግድ ዜማውን እየጐተቱ በከበሮ በማጀብ ያሬዳዊ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ ነገር ግን ያሬዳዊ ዜማ ማለት #የተጐተተ ዜማ ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሁሉንም ላለመልቀቅ የሚደረግ ጥረት ካልሆነ በቀር የራሳችን አለን፡፡ የራሳችን እያለንም ወደ ጐረቤት መጓዝ አያስፈልግም፡፡
👉ክርስቲያን የሆንነው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት ተጠምቀን ነው፡፡ ክርስቲያን ለመሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን የመጣነው ሕግዋን ሥርዓትዋን አክብረን እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሰጠውን ጸጋና በረከት ለማግኘት እንጂ እምነት፣ ሥርዓትና ሕግ ለዋጮች ለመሆን አይደለም፡፡ ስለዚህም ቀድመን የመጣንበትን ምክንያት አንርሳ፡፡ እኛ የምኖረው እግዚአብሔርን በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት መሠረት እያገለገልን እንጂ በቤተ ክርስቲያንና በክርስትና ሽፋን የገዛ ፍላጐታችን እያሟላን መሆን የለበትም፡፡
👉የራሳችን ዜማ ፈጥረን ከካሴቱ ሽፋን ላይ #የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ዜማና ሥርዓት የጠበቀ ስላልነው ብቻ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር መሆን አይችልም፡፡