G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
351 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
አሳሳቢ ነው‼️
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ቁጥር በየዓመቱ እየቀነሰ ነው ተባለ‼️
ምንም እንኳ የብሔራዊ ፈተና ማለፊያ ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎች ቁጥር መሻሻል ቢያሳይም፣ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ብዛት በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ይገኛል።

በ2017 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ብዛት 581,905 ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 48,929 (8.4 በመቶ) የሚሆኑት ብቻ የማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል። ይህ አሃዝ ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ ዝቅተኛ ነው። ለምሳሌ በ2014 ዓ.ም. 896,520 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል። የተፈታኞች ቁጥር ማሽቆልቆል በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ብቻ የተገደበ አይደለም።

በተባበሩት መንግስታት የህጻናት ተራዳኦ ድርጅት (UNICEF) ሪፖርት መሰረት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ህጻናት በግጭት፣ መፈናቀል እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል። ሪፖርቱ፤ ከ6,000 በላይ ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን ከ10,000 በላይ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ወይም ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ብሏል።

በተጨማሪም፤ በርካታ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑበት ክልል፤ #አማራ ክልል ሲሆን ብዛታቸውም 4.4 ሚሊዮን መሆኑን ገልጿል። በ #ኦሮሚያ ክልል 3.2 ሚሊዮን እና በ #ትግራይ ክልል1.2 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውንም ሪፖርቱ ማስታወቁ ይታወቃል።
#አዲስ ስታንዳርድ
==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋት ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ መቀመጧን ጥናት አመለከተ‼️
ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋትና የኢንተርኔትን ነጸነት በመገደብ ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን በብሉምስበሪ አሳታሚ ላይ የታተመ የጥናት መጽሐፍ አመላከተ።


“የኢንተርኔት መዘጋት በአፍሪካ” በሚል ርእስ በፊሊሽያ አንቶኒዮ እና ቶኒ ሮበርትስ የተጠናውና መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ባደረገው ብሉምስበሪ አሳታሚ ድርጅት ላይ በመጸሐፍ መልክ ታትሞ የወጣው ጥናት በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2024 በአህጉረ አፍሪካ በሀገራት የተፈጸመውን የኢንተርኔት መዘጋት ገምግሟል።


በዚህም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2024 ባሉት በለፉት ዘጠኝ ዓመታት 193 የኢንተርኔት መዘጋት በአፍሪካ አህጉር መመዝገቡን ገልጿል።
በተጠቀሱት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ በተፈጸሙ የኢንተርኔት መዘጋት ድግግሞሽ መጠኖች ሀገራትን በደረጃ ያስቀመጠው ጥናቱ ኢትዮጵያን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ሰላሳ ጊዜ ኢንትርኔት የዘጋች በሚል ከ55ቱ የአፍሪካ ሀገራት በአንደኛ ደረጃ አስቀምጧታል።
==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2
ፆታ ሊያስፈትሹ‼️
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የባለቤታቸውን ጾታ ሴትነት ለማረጋገጥ ሊያስፈትሹ ወስነዋል ተባለ!!

የትዳር አጋራቸው ቀዳማዊት እመቤት ብሪጂት በተደጋጋሚ ጾታቸውን የቀየሩ ወንድ እንጂ ሲወለዱ ሴት አልነበሩም የሚለውን ወቀሳ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኝ ሊያስፈትሿቸው ነው።

ከፍተሻው በኋላም ፕሬዝዳንት ማክሮን ሚስታቸውን በፎቶ እና በሳይንሳዊ ማስረጃ ሴት መሆኗን ለአለም ያሳያሉ ተብሏል።

ቀዳማዊት እመቤት ብሪጂት በወርሃ ግንቦት በቬትናም ጉብኝታቸው ወቅት የባለቤታቸውን ፊት ጥፊ በሚመስል መልኩ ሲገፈትሩ መታየታቸውን ተክትሎ በጾታቸው ጉዳይ እውነቱ እንዲታወቅ ግፊት እየተደረገባቸው ይገኛል።
#ቢቢሲ
==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🤣2
የመመዝገቢያ መስፈርቶች‼️
በቅድመ-ምረቃ እና በድኅረ-ምረቃ መርሐ-ግብር ተመዝጋቢዎች የሚከተሉትን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-
👉የትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያሳውቀውን የከፍተኛ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ መግቢያ መስፈርት የመቁረጫ ነጥብ አሟልተው መገኘት አለባቸው፤
👉ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች በከፍተኛ ትምህርት በቅድመ-ምረቃ ደረጃ ለመመዝገብ በሠለጠኑበት የሙያ መስክ በደረጃ 4 ወይንም በቀድሞ 10+3 ወይንም 12+2 ዲፕሎማ ያጠናቀቁ ሆነው በሙያው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC level 4) ተፈትነው ያለፉበትን፤ እንዲሁም በሙያው ቢያንስ የሁለት ዓመት ሥራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ እኚህ መረጃዎች በምዝገባው ዕለት ተሟልተው ሳይቀርቡ መስፈርቱን ያላሟላ ተመዝጋቢ መቀበል የተከለከለ ነው፡፡

👉ለ2ኛ ዲግሪ ተመዝጋቢዎች በባለሥልጣኑ ህጋዊነቱ የተረጋገጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤ እንዲሁም National Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት ያላቸው መሆን አለባቸው ፡፡

👉ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለመግቢያ መስፈርት የሚያገለግለው በባለስልጣኑ የአቻ ግምት ሲሰራለት ብቻ ይሆናል፡፡
👉ከተጠቀሱ መመሪያዎች ውጪ ገብተው ለሚማሩ ኃላፊነቱ የተመዝጋቢዎቹ እና የተቋማቱ ብቻ ይሆናል።
==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍1
72ቢሊዮን ዶላር ለወደብ‼️
ኢትዮጵያ ላለፉት 36 አመታት ለጅቡቲ የወደብ ኪራይ 72 ቢሊዮን ዶላር ከፍላለች። ይህ በአሁኑ የዶላር ምንዛሪ ተመን ወደ ብር ሲቀየር 10 ትሪሊዮን ብር ነው።
የጅቡቲ ህዝብ ብዛት 1.1 ሚሊዮን አካባቢ ሲሆን 10 ትሪሊዮን ብር ለጅቡቲ የህዝብ ብዛት ሲካፈል ኢትዮጵያ ለእያንዳንዱ የጅቡቲ ዜጋ 9.5 ሚሊዮን ብር ገደማ ከፍላለች ማለት ነው። እስካሁን ለጅቡቲ ወደብ ኪራይ የተከፈለው ብር 12 የህዳሴ ግድቦችን ይገነባ ነበር።

==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
2
ጴጥሮስ ማስረሻ የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ጴጥሮስ ማስረሻ አሸንፏል።

የውድድሩ አሸናፊ ጴጥሮስ ማስረሻ የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆኗል።
2
የደመወዝ ጉዳይ‼️
መንግስት ከመስከረም 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ የደመወዝ ጭማሪ ተደርጓል ቢልም እስካሁን ድረስ ወደየትኛውም መስሪያ ቤት የተላለፈ የደመወዝ ጭማሪ ሰርኩላር እንደሌላ አረጋግጠናል።
የደመወዝ ጭማሪ ተደርጓል መባሉን ተከትሎ ያለ ምንም ምክንያት በሸቀጦች እና በፍጆታ እቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል። የደመወዝ ጭማሪው ከመስከረም ወር ጀምሮ ቢሆንም የመስከረም ወር ደመወዝ ክፍያው የሚፈፀመው ግን በጥቅምት ወር መሆኑን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አሳውቆ ነበር። ሆኖም እስካሁን ድረስ የደመወዝ ጭማሪውን አስመልክቶ ዝርዝር የደመወዝ ጭማሪ እና አፈፃፀም መመሪያ አልወጣም፣በርካታ ሰዎችም መረጃ እየጠየቁ ይገኛሉ።
የሚመለከተው አካል በዚህ ዙሪያ መረጃ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአማካይ አንድ ሰው 80 አመት ቢኖር...

ይህ ማለት 960 ወራት ብቻ ነው ያለን።
 ወይም 4,160 ሳምንታት ብቻ።

እስኪ ቆም ብለህ አስብ..

የህይወትህ "ባትሪ" ያለው 4,160 ሳምንታት ብቻ ነው።

አሁን እድሜህ 30 ከሆነ፣ 1,560 ሳምንታትህ አልቋል! ቀሪው 2,600 ብቻ ነው።

እድሜህ 25 ከሆነ፣ 1,300 ሳምንታትህ ተቃጥሏል! ቀሪው 2,860 ነው።

ጨዋታው ይሄ ነው፡ እያንዳንዱ ሳምንት አንድ 'Block' ነው

አስበው፣ የህይወትህን ሳምንታት በሙሉ በወረቀት ላይ እንደ ትናንሽ ሳጥኖች ብትስላቸው።ከዛ እያንዳንዱ ያለፉት ሳምንታቶችህ በጥቁር ቀለም ቢቀቡና ያንን ምስል ብትመለከተው፣ ምን ይሰማሃል?

ምን ያህል ብዙ ሳጥኖች በጥቁር እንደተቀቡ ስታይ ትደነግጣለህ።

ምን ያህል ትንሽ ነጭ ሳጥኖች እንደቀሩህ ስታይ ትፈራለህ።

ይህ ፍርሃት ግን ጥሩ ነው!

ምክንያቱም እያንዳንዱ የቀረህ ነጭ ሳጥን ምን ያህል ውድ እንደሆነ እንድትረዳ ያደርግሃል!

ለቀጣዩ አንድ ሳምንት፣ ይህንን አንድ ጥያቄ እራስህን ጠይቅ፦

"ይህ ሳምንት በህይወቴ ታሪክ ውስጥ ቢፃፍ፣ ርዕሱ ምን ይሆን ነበር?"

ስለ ቢዝነሴ ያቀድኩበት ሳምንት?

በከንቱ ጭንቀት ያሳለፍኩት ሳምንት?

"ከምወዳቸው ሰዎች ጋር ጊዜ ያሳለፍኩበት ሳምንት"

"ቲክቶክ ላይ Scroll እያረኩ ያባከንኩት ሳምንት"?


ይህንን  ጥያቄ ስትጠይቅ፣ ጊዜን እንደ ገንዘብ ማየት ትጀምራለህ።

እያንዳንዱን ቀን በዕቅድ ትኖራለህ።

ለማይጠቅሙ ነገሮች ጊዜህን መግደል ታቆማለህ

የቀሩህን ነጭ ሳጥኖች፣ በህይወትህ ውስጥ ምርጥ በሆኑት ታሪኮች ትሞላቸዋለህ።

ጊዜህን እየገደልክ ነው ወይስ ኢንቨስት እያደረክበት ነው?


📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass


From That library.
🥰21👍1
ጭማሪው አልተራዘመም‼️
ከያዝነው መስከረም ወር ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች ይፋ የተደረገው የደሞዝ ማሻሻያ አልተራዘመም፣ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ የተደረገ ጭማሪ የተደረገው የደመወዝ ክፍያ ይፈፀማል።
"ተራዝሟል የሚለው መረጃ ከየት እንደመጣ አላውቅም። መረጃው ለህዝብ ይፋ ከተደረገ ጀምሮ ከመስከረም የሚጀምር የደሞዝ ጭማሪ ለማስፈፀም ስራ ስንሰራ ቆይተናል"- ሲሉ አንድ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባልደረባ ለመሰረት ሚዲያ ተናግረዋል።
በዚህም አዲስ የደሞዝ ማሻሻያ መሰረት ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደሞዝ ከብር 4,760 ወደ ብር 6,ዐዐዐ እንዲያድግ መደረጉ ይታወሳል። በተጨሜሪም ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደሞዝ ከብር 21,492 ወደ ብር 39,000 እንዲሁም የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6,940 ወደ ብር 11,500 መደረጉ በወቅቱ ይፋ ተደርጎ ነበር። ይህም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል ተብሏል።
==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
መብራት ተቋርጧል‼️
መብራት በደብረብርሃን፣በወልዲያ፣ በቆቦ፣በሸዋሮቢት፣በሰቆጣ፣በአዳማ፣በሁመራ፣በወላይታ፣ በቢሾፍቱ፣በአላማጣ፣በጅጅጋ፣ በቀብሪ ደሃር፣በባሌሮቤ በአፋር፣በአዲስ አበባ የተወሰኑ ቦታዎች እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍል ከ ምሽቱ 1:20 ሰዓት ጀምሮ መብራት መቋረጡን ቤተሰቦች ያደረሱን ጥቆማ ያመላክታል።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2
መብራት ለምን ተቋረጠ👇
በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች በከፊል የኃይል መቋረጥ ተከስቷል‼️
ከሰበታ ቁጥር 1 የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ወደ ጥቁር አንበሳ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ፤ ከጥቁር አንበሳ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ወደ አዲስ ዌስት ወይም ኮልፌ ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋዉ 132 ኪ.ቮ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ መደበኛ የጥገና ሥራ ሲከናወን ውሏል፡፡

ይሁንና ጥገናው ተጠናቆ መስመር በሚሞከርበት ጊዜ በተፈጠረ የመስመሮች መነካካት በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች የኃይል አቅርቦት መቋረጡን እና መስመሩን መልሶ ለማገናኘት እርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጿል።፡
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
ማሳሰቢያ‼️
በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤

በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 14/2018 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡-

1. የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ስሚቀበል ምርጫችሁ ውስጥ ማካተት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

2.አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምርጫ ውስጥ የማይካተቱ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🙏2
ወጥ የሆነ ታሪፍ‼️
በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ የትራንስፖርት ታሪፍ ተግባራዊ ሊደረግ ነው‼️
ክልሎችንና የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ለአሐዱ አስታውቋል።

ተሽከርካሪዎች ከአንዱ ክልል ወደሌላኛው ክልል ሲንቀሳቀሱ የተለያየ ታሪፍ እንደሚጠቀሙ በሚኒሰቴሩ የትራንስፖርት አገልግሎትና ቁጥጥር ዘርፍ አማካሪ አቶ አሰፋ ሀዲስ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ እንኳን የነበረው ታሪፍ ተመሳሳይ እንዳልነበረ የገለጹም ሲሆን፤ ለአብነትም ከመገናኛ ወደ ጣፎ ሲሄድና ከጣፎ ወደ መገናኛ ሲመጣ ይለያይ እንደነበር አንስተዋል።

የታሪፍ ወጥነት አለመኖር የአስተዳደር ጉዳዮችን ጨምሮ በርካታ ችግሮችን ያስከትል እንደነበር የተናገሩት አማካሪው፤ በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ ታሪፍ እንዲኖር ለማድረግ ሲሰራበት መቆየቱን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት ከክልሎች ጋር ውይይት በማድረግ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጀመራቸውን አስረድተዋል።

አጠቃላይ ታሪፉ ከነዳጅ በተጨማሪ የተሽከርካሪው ደህንነት፣ የሹፌርና የረዳት ደመወዝ እንዲሁም፤ የገበያ ሁኔታውን በተመለከተ ጥናት እንደተካሄደበት የገለጹም ሲሆን፤ ታሪፍ የሚወጣው ይህ ሁሉ ግምት ውስጥ ገብቶ ነው ብለዋል።
በዚህም መሠረት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
የት/ት ሚኒስቴር መልዕክት‼️
በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ለመማር ያለፋችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል እስከ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ድረስ እንድታመለክቱ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማይቀበል መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ዘንድሮ በሪሚዲያል ፕሮግራም ለሚገቡ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ውጤት ከ40% በላይ ያመጡ ሊሆን እንደሚችል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተናገሩ ሲሆን የሪሚዲያል ፕሮግራም ቀስ በቀስ እየቀረ ይሄዳል ብለዋል።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
1👍1
ከምፅዋ ታሪክ‼️
የብርጋዴር ጀኔራል ተሾመ ተሰማ የመጨረሻዋ መልዕክት-ከምፅዋ‼️
ከጥዋቱ 1:30 ሲሆን ጀነራል ተሾመ ተሰማ ምጽዋ ከተማ ላይ የተወሰኑ የጦር መኮንኖችንና ማዕረግተኞችን ሰብስበው ንግግር አደረጉ።

"ሻዕብያ ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ ምጽዋን ለመያዝ ቆርጦ መነሳቱ ጥርጥር የለውም። እኔ የሚጠበቅብኝን አደራ ተወጥቻለሁ። ከጥር 30 ጀምሮ እስከ የካቲት 9/1982 የሞት ሽረት ትግል አድርጌያለሁ። ከዚህ በኋላ የራሴን ህይወት በክብር ማጥፋትና ለኢትዮጵያ ጀግኖች ታላቅ ተምሳሌት ከመሆን ሌላ አማራጭ የለኝም።

ጀግንነት ማለት በሁሉም መልክ ለጠላት ምቹ ሁኖ አለመገኘት ነው። እኔ ዛሬ ብሞት ብሸነፍም በታሪክና በመጭው የኢትዮጵያ ትውልድ ፊት አልሸነፍም። የአጼ ቴወድሮስን እድል በማግኘቴ በጣም እኮራለሁ።

ጎበዝ ስሙኝ! ይህ የአደራ መልክቴ ነው። ነገ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይደርስ ይሆናል። ምን አልባት አምላክ ካለ ከእናንተ አንዱ መልዕክቴን ያደርስልኛል።

ዛሬ ሻብያ ምጽዋን ይቆጣጠራል ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ሀገሬ እና ህዝቧ ትልቅ አደጋ ነው ምናልባትም የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ደንበር የሆነውንና ለዘመናት በአባቶቻችን የደም ዋጋ ጸንቶ የቆየውን የባህር በራችንን በመዝጋት በምድር ተወስነን እንድንቆይ ይደረግ ይሆናል። ይህ ደግሞ የሞት ሞት ነው።

የፈለገ ጊዜ ይጠይቅ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ የባህር በር አልባ ሁኖ በኢምፔሪያሊስቶችና ጋሻ ጃግሬወቻቸው ተሸንፎና እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም። ይህ ከሆነ የአጼ ዮሐንስ፣ የራስ አሉላ አባነጋና የእኔን ጨምሮ የአብዮታዊ ሰራዊት አባላት አጥንትና ደም በኢትዮጵያውያን ትውልድ ሁሉ እስከ ዘላለሙ ይፈርዳል።

ጊዜውን ጠብቆ የኢትዮጵያ ጀግና ምጽዋን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚያስረክብ እምነቴ የጸና ነው።

አንድ ሰው ቤት ሲሰራ የሚሰራው ቤት በርና መስኮት አሉት። አንድ ሰው ደግሞ ሞተ እንበል መቃብሩ በርና መስኮት የለውም። ይህ ምሳሌ ከገባችሁ ባህር በር የሌላት ሀገር ሞቶ ከተቀበረ ሰው የምትለየው በትንሹ ነው።

ቀይ ባህር ለእኔ ዘላለማዊ ቤቴ እንዲሆን ወስኛለሁ። ደስተኛ እና እድለኛ ጀነራል ነኝ።

(ታደሰ ቴሌ ሳልባኖ-አየ ምፅዋ )
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
3