G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
351 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
በአፍሪካ ከፍተኛ የግብረ ሰዶማውያን ቁጥር የሚገኙባቸው 10 ሀገራት‼️
1.ደቡብ አፍሪካ/especially in cape town/
2.ኬንያ
3.ሲሸልስ
4.አንጎላ
5.ሞዛምቢክ
6. ናሚቢያ
7.ቦትስዋና
8.ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ
9.ኬፕ ቨርዴ
10.ሌሴቶ ናቸው።

====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👏2👍1
ከ1884-1885 ሰባት ዋና ዋና የአውሮፓ ሀገራት በንግድ ሰበብ አፍሪካን ለመቀራመት በጀርመን በርሊን/Berlin conference/ ድብቅ ውሳኔ አሳለፉ፣ማን ማንን መውረር እንዳለበት ተስማሙ።
ብዙ የአፍሪካ ሀገራት የአውሮፓውያንን ቅኝ ግዛት ተጎነጩ። የብዙ የአፍሪካ ሀገራት ባህላቸው፣ ወጋቸው፣ሀይማኖታቸው፣ ነፃነታቸው፣ታሪካቸው ጠፋ፣ተበረዘ። ቋንቋቸው ተቀየረ፣በቅኝ ግዛት ማቀቁ፣የባሪያ ንግድ ሰለባ ሆኑ፣ብዙዎች የውቅያኖስ ሲሳይ ሆኑ፣በሀገራቸው ባይተዋር ሆኑ፣እንደሰው ሳይሆን እንደ እንስሳት ተቆጠሩ፣ንብረታቸውንና ማዕዳናቸውን እራሳቸው ጭነው እራሳቸው ውቅያኖስ አቋርጠው ለአውሮፓውያን አስረከቡ።
በወቅቱ ኢትዮጵያን ለመውረር እና ቅኝ ግዛት ለመግዛት የተመደበችው ጣሊያን ግን ድል አልቀናትም፣በኢትዮጵያ ጀግኖችና ብልሃተኛ መሪዎች እና አባቶች አድዋ ላይ ተደባይቶ ተመለሰ።
የአድዋ ድል በወቅቱ በጨለማ ውስጥ ለሚገኙት የአፍሪካ ሀገራት የጨለማ ውስጥ ችቦ ለኮሰ፣የነፃነት ተምሳሌት ሆነ፣የጥቁር ህዝቦች ኩራት ሆነ፣ኢትዮጵያም በቅኝ ግዛት ሳትገዛ፣ቋንቋዋ፣ባህሏ፣የአመጋገብ ስርዓቷ፣ሀይማኖቷ...ሳይበረዝና ሳይጠፋ በኩራት የአፍሪካ ተምሳሌት ሆነች።
አድዋ ፍቀህ የማጥለው፣ልትበርዘው የማትችለው የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ነፃነትን ለሚሹ ፍጡራን ሁሉ ተምሳሌት ነው።
"ከላይ ያስቀመጥኩት ምስል አፄ ምኒልክ መጋቢት 23 ቀን 1888 ለፈረንሳዩ ጓዳቸው የፃፉት የድል ደብዳቤ ነው።
ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን❗️
እንኳን አደረሳችሁ

====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🔥2👍1
እንኳን ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!

#Ethiopia   #ኢትዮጵያ   #Adwa  #share #GTutorialclass
🙏2
ናይጀሪያ በጾም ሰዓት ምግብ ተመግበዋል በሚል 25 ሰዎችን አሰረች‼️
የናይጀሪያዋ ኮኖ ግዛት በረመዳን የጾር ላይ ምግብ ሲመገቡ አግኝቻቸዋለሁ ያለቻቸውን 20 ሰዎች ስራለች፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አምስት ሰዎች ደግሞ ምግብ ሲሸጡ ነበር በሚል የጣሰሩ ሲሆን ሁሉም ታሳሪዎች በሸሪዓ ህግ እንደሚዳኙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በዚች ግዛት በእስልምና የጾም ወር ወቅት በአደባባይ ምግብ መመገብ ክልክል ነው፡፡

የግዛቲቱ ፖሊስ ያልተገባ የጸጉር አቆራረጥ፣ የተገላለጠ እና ሰውነትን የሚያሳይ አለባበስ የሚከተሉ ሰዎችን እንደሚያስር አስጠንቅቋል፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት በነበረው ተመሳሳይ የጾም ወቅት ፖሊስ የማይጾሙ ሰዎችን አስሮ የነበረ ሲሆን ታሳሪዎቹ እንደሚጾሙ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ከእስር ተለቀው ነበርም ተብሏል፡፡

====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2
ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ‼️
ደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ በተለያዩ መርሃግብሮች ያሰለጠናቸውን 1811 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት ለ17ኛ ጊዜ እያሥመረቀ ይገኛል።
ለተመራቂ ተማሪዎች፣ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ልጆቻችሁን ለምታስመርቁ ወላጆች እንኳን ደስ አላችሁ።
Congratulations
አዩዘሀበሻ
===================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2
መውጫ ፈተና ወስደው ለወደቁ ተማሪዎች Special Diploma ሊሰጥ ነው።
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተከታታይ ውይይት ሲያደርግ መቆየቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ይህን ተከታታይ ውይይት ተከትሎ የመውጫ ፈተና መሰጠት ከተጀመረበት ሐምሌ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናውን ወስደው ለወደቁ ዕጩ ተመራቂዎች ልዩ ዲፕሎማ ሰርተፊኬት በቅርቡ መሠጠት እንዲጀመር ውሳኔ ላይ መድረሱን አሳውቋል።

ተማሪዎቹ ሥራ እየሠሩ በማንኛውም ጊዜ የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ መውሰድ የሚችሉበት ዕድል ክፍት እንዲሆን መደረጉንም ገልጿል።

ፈተናውን ወስደው የሚያልፉ ተፈታኞች በስፔሻል ዲፕሎማው ምትክ ዲግሪ ይሰጣቸዋል ተብሏል።

የስፔሻል ዲፕሎማ የደመወዝ ስኬል እንዲወጣለት ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከስቪል ሰርቪስ ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን ህብረቱ አሳውቋል።

===================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2
Attention‼️
ደህንነታቸውና ጥራታቸው ያልተረጋገጠ የምግብ ዘይት ፣ የለውዝ ቅቤ እና የከረሜላ ምርቶች ይፍ ሆኑ‼️
የሀገሪቱን አስገዳጅ ብሔራዊ እና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃ ሳያሟሉ በተጨማሪም ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ የዋሉ የለውዝ ቅቤ ፣የምግብ ዘይትና የከረሜላ ምርቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የህዝብ እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አበራ ደመቀ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በተሰራው የገበያ ቅኝት የተለያዩ የለውዝ ቅቤ ፣የምግብ ዘይትና ከረሜላ ምርቶች ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጡና የሀገሪቱን አስገዳጅ ብሔራዊ እና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃ ሳያሟሉና ሳይለጥፉ ሲቀርቡ የነበሩ ምርቶች ተገኝተዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ ምግቦች እንደ ለውዝ ቅቤ ፣የምግብ ዘይትና ከረሜላ ምርቶች ላይ ባደረገው የገበያ ቅኝት ቁጥጥር ምርቶቹ የአምራች ድርጅት ስም ያልተጠቀሰባቸው፣ የአምራች አድራሻ ያልተገለፀ፣ አስገዳጅ የደረጃ ምልክት ፣የምርቱ መለያ ቁጥር የሌላቸው ፣የምርቱ ጥሬ ግብዓት ዝርዝር ያልተገለፀና የመጠቀሚያ እና የማብቂያ ጊዜ የሌላቸው ምርቶች መሆናቸው ተለይተዋል።

በገበያ ቅኝት ወቅት የተገኙት ምርቶች  የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ያላሟሉ እና የደረጃ ምልክት ያለጠፉ ፣ ስለምርቱ የተለጠፉ ወይም የተፃፉ የምርት ገላጭ ፅሁፍ አስገዳጅ ደረጃ ያላሟሉ መሆናቸው መለየት የተቻለ በመሆኑ የምርቶቹን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አቶ አበራ አሳስበዋል፡፡

በገበያ ቅኝት ወቅት የተገኙ ምርቶች ዝርዝር መካከል የተለያዩ ለውዝ ቅቤ ምርቶች ይገኛሉ። እነዚህም

1. ማዕዛ የለውዝ ቅቤ
2. አያልነህ የለውዝ ቅቤ
3. አደይ የለውዝ ቅቤ
4. አፊያ የለውዝ ቅቤ
5. ስካይ የለውዝ ቅቤ
6. ያሚ የለውዝ ቅቤ

በተጨማሪም የተለያዩ የምግብ ዘይት ምርቶች

1. ሙሃ የተጣራ የምግብ ዘይት
2. ኤርሚያስ የምግብ ዘይት
3. እፎይ የምግብ ዘይት
4. እናት የምግብ ዘይት
5. ፍትህ የተጣራ የምግብ ዘይት
6. ጣራ የተጣራ የምግብ ዘይት 
7. ዝናሽ ንጹህ የምግብ ዘይት
8. አስሊ ንጹህ የምግብ ዘይት
9. ንጹህ የምግብ ዘይት
10. ዛራ የምግብ ዘይት
11. ሞያ የምግብ ዘይት
12. እፎይታ ንፁህ የምግብ ዘይት

አስር (10)የተለያዩ ምንም አይነት ገላጭ ጹሁፍ የሌላቸው የከረሜላ ምርቶች መሆናቸውንም ህብረተሰቡ እንዲያቃቸው ባለስልጣኑ አስታውቋል።
====================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ 📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዘጠኝ ሰከንድ ቪዲዮ ህይወት ቀየረች‼️
ከ50  ሚሊዮን ናይራ በላይ ተሰበሰበለት‼️
በርግጠኝነት የዚህን ልጅ ፎቶ ከዚህ በፊት አይታችሁታል ።
አልበርት ይባላል ። እና በዚህ የሰከንዶች ቪዲዮ ላይ ፡ እናቱ ፕላፕምሌት ስትሰጠው ላለመብላት ብሎ ሲያለቅስ ፡ በዛው ቅፅበት ደግሞ ምግቡን እንዲበላ አያቱ በዜማ ስታባብለው ማልቀሱን አቁሞ ሲስቅ ይታያል ።
.......
የዚህ ጋናዊ  ታዳጊ የአልበርት ቪዲዮና ፎቶ ፡ በፌስቡክ ቲክቶክና ኢንስታግራም ላይ ፡  የተለያየ ሚም እየተሰራበት ታዋቂ ከመሆኑም በተጨማሪ ለብዙ ሰወች የገቢ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል ። በተለይ ቪዲዮው ለመጀመሪያ በተለቀቀበት የቲክቶክ አካውንት ከ370 ሚሊዮን በላይ ሰወች የተመለከቱት ሲሆን ከዛም በኋላ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰወች ሚም ሰርተውበት ፡ በአለም ዙሪያ ያሉ በመቶ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሰወች አይተውታል ።
...
አስገራሚው ነገር ይህ የዚህ ልጅ ቪዲዮ በቲክቶክ የተለቀቀበት መንገድ ራሱ አስገራሚ ነበር ። ይህን ቪዲዮ ለመጀመሪያ ጊዜ ፖስት ያደረገው ሰው ፡ ቪዲዮውን ያገኘው ከሰው ላይ በገዛው ስልክ ውስጥ ነበር ። በኋላ እንደታወቀው ይህን ቪዲዮ የቀረፀው የታዳጊው ልጅ አጎት ሲሆን ፡ ስልኩን በሸጠበት ወቅት ቪዲዮው ባለመደለቱ ፡ ይህን ያገኘው ሰው ይህን ያህል ቫይራል ይሆናል ብሎ ሳያስብ እንደቀልድ ፖስት አደረገው ።
....
በዚህ መልክ ፡ በአጋጣሚ ቫይራል የሆነው ይህ ቪዲዮ ታዋቂ ከሆነ  በኋላም የተለያዩ ኮንተንት ክሪኤተርስ ወደቤቱ እየሄዱ ለቪው ማሳደጊያ ቪዲዮ እየቀረፁ ሲለቁ ነበር ።
በቅርቡ ግን አንድ ታዋቂ የጋና ቲክቶከር ፡ ይህን ልጅ በተመለከተ በሰራው ቪዲዮ የጤና ችግር እንዳጋጠመው እና በድህነት ውስጥ እንደሚኖር ገልፆ ፡  እንዲታገዝ ጥሪ አቀረበ ።
...
ይህን ጥሪም ተከትሎ በሳምንት ጊዜ ውስጥ በጋና እና ናይጄሪያ እንዲሁም በሌሎች ሀገራት ከሚኖሩ ቲክቶከሮች ሀምሳ  ሚሊዮን ናይራ  የተሰበሰበለት ሲሆን እስካሁን በቀጠለው የገቢ ማሰባሰቢያ  ይህን ታዋቂ ልጅ ለመደገፍ ብዙዎች ቃል ገብተዋል ።
....
እና ይህንን መረጃ  ያጋራው ዌብ ሳይት ፅሁፉን ሲዘጋ እንዲህ ብሏል ።
When it’s your time, even people who never knew you will come to bless you
Via Wasihun tesfaye
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
👍61🥰1
ፎርብስ የ2025 የቢሊየነሮች ዝርዝር ይፋ አደረገ‼️

ፎርብስ መጽሔት 39ኛውን አመታዊ የቢሊየነሮች ዝርዝር ያወጣ ሲሆን ዘንድሮ የቢሊየነሮች ብዛት ከመቼውም ጊዜ የበለጠ መሆኑን ዘግቧል።

በዝርዝሩ ውስጥ 3,028 ቢሊየነሮች የተካተቱ ሲሆን ይህ ቁጥር ከአምናው በ247 ከፍ በማለት ሪከርድ ሰብሯል።

የነዚህ ቢሊየነሮች ሀብት ድምር 16.1 ትሪሊየን ዶላር የተገመተ ሲሆን ይህም ከአለማችን አጠቃላይ ሀብት ውስጥ 15% ነው።

ዝርዝሩን የሚመሩት የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ባለቤቶችና አለቆች ሲሆኑ ከአንደኛ እስከ አስረኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ወንዶች ናቸው። በተጨማሪም ከምርጥ አስሩ ውስጥ ስምንቱ አሜሪካውያን ናቸው።

የቴስላ፣ ስፔስ ኤክስ፣ ኤክስ እና ኤክስ ኤ.አይ ባለቤትና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አማካሪ የሆነው ኢላን መስክ የ342 ቢሊየን ዶላር ባለሀብት በመሆን አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ከመስክ ቀጥሎ የሜታ መስራች ማርክ ዙከርበርግ በ216 ቢሊዮን ዶላር፣ የአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስ በ215 ቢሊየን ዶላር፣ የኦራክል ኮምፒውተር ድርጆት መስራች ላሪ ኤሊሰን በ192 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም የሉዊ ሺቶን እና ሌሎች የቅንጦት ምርቶች ቢዝነስ ባለቤት በርናርድ አርኖልት እና ቤተሰቡ በ178 ቢሊየን ዶላር ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ5.1 ቢሊየን ዶላር ባለሀብት በመሆን 700ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ከ3,028ቱ ቢሊየነሮች ውስጥ 406ቱ ሴቶች ሲሆኑ የዋልማርት ወራሽ የሆነችው አሊስ ዋልተን በ101 ቢሊየን ዶላር ትመራለች።

የዘንድሮው ዝርዝር ውስጥ 22 አፍሪካውያን ቢሊየነሮች የሚገኙ ሲሆን ናይጄሪያዊው የ23.9 ቢሊየን ዶላር ባለቤት አኪኮ ዳንጎቴ ከአለም 83ኛ ከአፍሪካና ከጥቁሮች ደግሞ አንደኛ ሆኗል።
ጅቡቲም ውጡልኝ አለች‼️
በትናንትናው ዕለት የጂቡቲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጽያዊያን ሀገሪቱን በ30ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፉን በጅቡቲ ታጁራ ከተማ የሚኖሩ የአዩዘሀበሻ ቤተሰቦች ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት ፑንትላንድ እንዲሁም ሶማሊላንድ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን በርካታ ኢትዮጵያውያንን ማስወጣታቸው ይታወሳል።
አዩዘሀበሻ
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass