G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ ታህሳስ 04 እና 05/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➢ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➢ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➢ ስድስት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ።

የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በቦቆጂ ካምፓስ ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በአሰላ ከተማ ዋናው ግቢ ሪፖርት እንድታደርጉ ተብላል፡፡

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🎯 ግቢ ላይ ውጤት እንዴት መስራት እንችላለን።

         ❇️Worksheet

🔰Worsheet ማለት መምህሩ የሆነ chapter አስተምሮ እንደጨረሰ በተማራችሁት ትምህርት ዙሪያ ከበድ ከበድ ያሉ እና የ concept ጥያቄዎች ከተለያዩ መፅሀፍት አውጣጥቶ ፈተና ሊደርስ አካባቢ የሚሰጣችሁ ነው። በተለይ ፈለጣ የሚበዛበት ዲፓርትመንት የምትገቡ ልጆች worksheet የተለመደ ነው። መምህሩ worsheet ከሰጣችሁ ፡  ፈተናውን በዚህ መልክ ተዘጋጁ ማለቱ ነው። ከ worksheet ቱ ላይ ጥቂት የማይባሉ ጥያቄዎች ፈተና ላይ ይወጣሉ። መምህሩ ጥያቄዎቹን የሚያወጣው ከ መፅሀፍ ስለሆነ የጥያቄዎቹን መልስ ከዛው መፅሀፍ ታገኙታላችሁ ፡ ከሌለ ደግሞ Google ማድረግ ይጠበቅባችሗል። ስለዚህ የሚሰጣችሁን worksheet ጥሩ አድርጋችሁ ከሰራችሁ ፡ ፈተናውን ትሰሩታላችሁ።

    ❇️የአጠናን መንገድ(ስልት)

🔰እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው🤔?

🎯 አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ።

🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ።

🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው።

ስለዚህ እንዴት እናብብ🤔

🔔 የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም🤷‍♀️

ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ

🎯 የ ሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው።

🎯  መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ።

🎯 የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው።

🗣 ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን።

     ❇️የጊዜ አጠቃቀም

🔰ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው።

      ❇️ አለመሰልቸት

🔰ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል።

   ❇️ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን።

🔰ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ።

    ❇️Google

🔰ለ ግቢ Google በጣም ወሳኝ ነገር ነው። Assignment መስራት ብትፈልጉ ፡ practical education በ video  ማየት ብትፈልጉ ፡ የተለያዩ መፅሀፎችን እና የመፅሀፍ solution ማውረድ ብትፈልጉ ፡ ምናልባት መምህሩ የሰጣችሁ ኖት ካልገባችሁ እና ሳይንሱን መረዳት ብትፈልጉ ፡ Google ለነዚህ ሁሉ በቂ መፍትሔ አለው። ስለዚህ Google ን የቅርብ ወዳጅ አድርጋችሁ ወጤት መስራት ትችላላችሁ ፡ ሳይንሱን መረዳት ትችላላችሁ። በዚሁ አጋጣሚ ለ Google ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ😘

          😊 The End

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👨‍🎓🧑‍🎓የተማሪዎች አይነት (types of learners)

📮ይህ ፅሁፍ ሁሉም የትምህርት ብቃት እንዳለው ነገር ግን የትምህርቱ ዘዴ እና አቀባበላችን እንደሚለያይ
ያሳያል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የተለያዩ አይነት ተማሪዎችን እና የሚቀላቸውን የመማር ዘዴ ማጣጣም ያስፈልጋል።
የራሳችሁ የመማር ምርጫ ከየት እንደሆነ መመርመርም አትርሱ።

🧑‍🎓1— የእይታ ተማሪዎች (Visual learners)

እነዚህ የተማሪ አይነቶች የሚገባቸው መማር በእይታ ሲሆን ነው። ያዩት ነገር እንዲሁ በቃል ከሚነገራቸው
ይልቅ አይረሳቸውም። እነዚህ ተማሪዎች በተግባር ማየት ካልቻሉ በሃሳባቸው እየሳሉ ቢያነቡ በቀላሉ ማስታወስ ይችላሉ።

🧑‍🎓2— የተግባር ተማሪዎች (Kineshetic learners)

እነዚህ በበኩላቸው ራሳቸው በተግባር የሞከሩት ነገር ቶሎ ይገባቸዋል፣ አይረሱትም። ሰው ሲያደርግ ከማየት
በላይ ራሳቸው በማድረግ ይማራሉ። ለነዚህ ወደ ተግባር እየቀየሩ መሞከር ይመከራል።

🧑‍🎓3– የመስማት ተማሪዎች (auditory learners)

እነዚህ አንድን ነገር ከሰሙት በቂያቸው ነው። ብዙ ከማጥናት በላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲያዳምጡ ይመከራሉ። የሰሙትን ነገር ይረዳሉ።

🧑‍🎓4– የጭንቀት ተማሪዎች (Stress learners)

ያስጨነቃቸው ነገር አይረሳቸውም። ተጨናንቀው ግዴታ አውቄ መግባት አለብኝ ካሉ ማን እንደነሱ። ትኩረት
መስጠት እና መጣር ይመከራሉ።

🧑‍🎓5— የመዝናናት ተማሪዎች (Ease learners)

ዘና ፈታ ብለው ያነበቡት እና የተማሩት አይረሳቸውም። እነዚህ ሳይጨናነቁ፣ አእምሯቸውን ዘና አድርገው እና ጥሩ ስሜት ውስጥ ሆነው ቢያነቡ በጣም ውጤታማ ይሆናሉ።

🧑‍🎓6– የፅሁፍ ተማሪዎች (Scrubble learners)

ለየት ባለ መልኩ ትምህርት ወደ አእምሯቸው የሚገባው ሲፅፉት ነው። እንዳልረሳው ብለው ቢፅፋም
ስለማይረሱት ደግመው ላያዩት ይችላሉ። እነዚህ ሲያጠኑ ደጋግመው እንዲፅፉ እና ከጥናት በሗላም ራሳቸውን የሚፈትኑት ያጠኑትን በወረቀት ላይ ደግመው
ለመፃፍ በመሞከር እንዲሆን ይመከራል።

🧑‍🎓7— የእምነት ተማሪዎች (trust learners)

አነዚህ ከሚያምኑት ወይም ከሚያከብሩት አለያም ከባለስልጣን የተሰጠን ትምህርት በጭራሽ አይረሱም። ትምህርቱ ሳይሆን መምህሩ ነው ለነሱ ወሳኙ። ይሄን
ከሆን የተማርነውን ከምናምነው ሰው እንደተነገረ አድርገን እያሰብን ድጋግሞ ከማጥናት የተሻለ ምክር አይኖርም።

🧑‍🎓8— በማስተማር የሚማሩ (teach learners)

እነዚህ አንድን ነገር ካስተማሩት አለቀ—ተመጠጠ ማለት ይቀላል። እና ሁሌም ተማሪ ስለማይገኝ የተወሰነ አንብበው ቀሪውን– ቆም ብሎ፣ ተማሪዎች
እንዳሉ ራስን አሳምኖ፣ ጮክ ብሎ በማስተማር ማጥናት ይመከራል።

🧑‍🎓9— ተመሳሳዩን በመስራት የሚማሩ (copy learners)

ለየት ባለ ሁኔታ ያዩትን ወይንም የተማሩትን ነገር አስመስለው ሲሰሩት አይረሱትም። ያየነውን ነገር ደግመን ሁሉንም ቅደም ተከተል ሳንረሳ አስመስሎ
ለመስራት በመሞከር እንዲያጠኑ ይመከራል።

⭐️#ማጠቃለያ፦ አንድ አይነት ዘዴ በመጠቀም የሁሉንም ተማሪዎች የመማር ምርጫ እና ብቃት ማሟላት አይቻልም።
ከኢትዮጵያ መምህራን መድረክ - partially edited

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
Logic chapter 1.pdf
249.3 KB
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
💊 Pharmacy | ፋርማሲ

🦠ፋርማሲ ከ other health ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአድሱ የትምህርት ስርአት freshman course ጨምሮ የ5 አመት ትምህርት ነው ።
ፋርማሲ ስትገቡ የምትማሯቸው ኮርሶች mostly chemistry ነክ around [ 60%] ,biological around [25%] እና ሌሎችም አሉ ።ስለዚህ chemistry የሚወድና አንባቢ ተማሪ በብቃት ይወጣዋል።

🔬ፋርማሲ ስትማሩ የሚያስደስቱ ነገሮች ፦

🔺የመድሃኒት ቅመማ በላብላቶሪ ትሰራላችሁ ፤ ከባህላዊ ህክምናና ከእፅዋት እንዴት መድሃኒት ማግኘት እንደምትችሉ  ታውቃላችሁ  ፤ በላብላቶሪ ውስጥ lotion, cream, gel, shampoo, sanitaizer....የመሳሰሉትን ኮስሞቲክስ ታመርታላችሁ ፤መድሃኒትን አይጥ ላይ በመውጋት ትመራመራላችሁ ወዘተ....

💊በፋርማሲ ስትመረቁ ምን ትሰራላችሁ? ገቢውስ እንዴት ነው ? 🤔

1️⃣, clinical pharmacy የሚባለው hospital ውስጥ ተቀጥራችሁ

2️⃣, 🧪pharmaceutical company የመድሃኒት ፋብሪካና በተወሰነ መልኩ የኮስሞቲክስ ፋብሪካ ጋር

3️⃣, የመድሃኒትና የምግብ ቁጥጥር ማለትም ወደ ሀገር የሚገቡና የሚወጡትን መፈተሽ

4️⃣, በግላችሁ community pharmacy በመክፈት በተለይ ቤተሰቦቻችሁ በገንዘብ የሚያግዟችሁ ከሆነ በጣም አዋጭ ነው።

5️⃣, 💉የማንኛውንም የህክምና መድሃኒትና ቁሳቁስ በ pharmacist ቁጥጥር ስር ነው የሚገዛው (የሚቀርበው) ስለዚህ እዛ ላይም የናንተ ሙያ አለ።

6️⃣, የ fingerprint,forensics, food toxicity,drug toxicity,.....የመሳሰሉትን የወንጀል ምርመራ ላይ መስራት ይቻላል ።

7️⃣, እኛ ሀገር ብዙም ባይኖር የመድሃኒት ጥናትና ምርምር ላይም ትሰራላች

⭕️ስለ ገቢው፦ እውነቱን ለመናገር በፋርማሲ ትምህርት  ከተመረቃችሁ በኋላ ስለ ገንዘብ አያሳስባችሁም ። እያጋነንኩ አይደለም ከቻላችሁበት በጣም ባለሀብ ትሆናላችሁ ። ስለ ፋርማሲ ብትጠይቁ ቀድመው የሚነግሯችሁ businesses ነውና እሱ አያሳስባችሁ ።

📌ስራ ላላገኝ እችላለሁ? እንደማንኛውም የጤና ተማሪ ከhospital,ጤና ጣቢያ ትሰራላችሁ plus ሌላ አማራጭ በግል ትሰራላችሁ ወይም ከላይ ከ ተራ  ቁጥር 2-7 ያሉት አማራጮች አሉላችሁ ።

📺ትምህርቱ ከባድ ወይስ ቀላል? pharmacy ከ medicine በመቀጠል የሚመደብ ስለሆነ ከበድ ይላል ነገር ግን chemistry,biology and labolatory ነክ ትምህርቶ ለሚሰራና ለሚያነብ ተማሪ በቀላሉ ማለፍ ይችላል ። እንደዬ ዩንቨርስቲው ቀለል ባለ መልኩ የሚያስተምሩም አሉ ። ስለዚህ ጠንከር ያለ ተማሪ ቢሆን የተሻለ ውጤት ያመጣል።

🔘በአጠቃላይ ፋርማሲ ከሌሎች የጤና ዘርፎች ለየት የሚያደርገው ብዙ የስራ መስኮች ያሉትና ጥሩ የሚባል ክፍያ የሚገኝበት መሆኑ ነው።

🚖ስለ ፊልድ መረጣ በተመለከተ እንደ medicine ገና የመጀመሪያ ሴሜስተር ኮርስ እንደጨረሳችሁ ነው ። ሌሎች other health ግን 1ኛ አመት ከጨረሳችሁ በኋላ ነው።

⭐️ለRemedial እና ለ12 ተማሪዎች   ቻናል👇
@GTUTORIALCLASS
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
1
📢👨‍💻General Introduction to Computing and Informatics school.

🫡 እሺ በቅድሚያ እንኳን ወደ Computing & informatics በደህና መጡ😀

በጠቅላላ ለማየት ያክል በዚህ ዘርፍ ውስጥ 4 ታዋቂ ዘርፎች አሉ

✔️*1 software engineering
✔️ 2 computer science 
✔️ 3 information technology
✔️ 3 information science(not in all universities )

ሁሉንም በዝርዝር እና ከ Applicationናቸው ጋር እንይ፡፡

📚1 Software engineering - ይህ feild በይበልጥ የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ እና logic የሚጠይቅ ነው፡፡ ዋና አላማውም ሶፍትዌር ማቀልጸግ እንዲሁም deployment ላይ ያተኩራል፡፡ በዚህ ፊልድ ውስጥ ስለ app development, web development, software development እና system maintaining ላይ በትኩረት ይሰራል፡፡ ብትገቡበት መልካም ፊልድ ነው፡፡
• ዲግሪ በ SE ካላችሁ ማስተርሳችሁን በሚከተሉት department መስራት ትችላላችሁ፡፡
- MSC software engineering

📚. 2 computer science - ይህ ቲዮሪ የሞላው department ነው። ተግባር ተኮር ላይ ብዙም አያተኩርም፡፡ ይህ ፊልድ ኮምፒውተር ኮምፒውተር እንዲሆን የሚያስችሉትን ነገሮች ላይ ያተኩራሉ ለምሳሌ ስለ operating systems በጥልቀት ይማራሉ programming course ይወስዳሉ ግን ዋና ትኩረቱ ስለ science of computers ነው ትንሽ theory አለው፡፡
• ዲግሪ በ CS ካላችሁ ማስተርሳችሁን በሚከተሉት department መስራት ትችላላችሁ፡፡
- MSC software engineering

TIP 1 : ለምሳሌ ኮምፒውተር ላይ ሁለት software layers አሉ system software እና application software ስለዚህ ስለ system software በጥልቀት የሚያጠናው እና apply የሚያደርገው computer science ሲሆን application software የሚሰራው ደግሞ software engineering ነው፡፡


📚3. information technology : ይህ department ተግባር ተኮር ከሚባሉት አንዱ ነው፡፡ ዋና አላማው information እና technology አጣምሮ መስራት ነው ከሌሎቹ ትንሽ ለየት የሚያደርገው physics ትንሽ አለው😫 ምክንያቱም computer maintainance ስለምትማሩ electronics part ላይ physics አለው በተጨማሪም ስለ logic get ምናምን ትማራላችሁ፡፡ networking በደንብ የምትማሩ ሲሆን it specialist ስትሆኑ የኔትዎርክ ጓደኛ መሆናችሁ አይቀርም በተጨማሪም database በደንብ ትማራላችሁ ልክ እንደ is፡፡
• ዲግሪ በ IT ካላችሁ ማስተርሳችሁን በሚከተሉት department መስራት ትችላላችሁ፡፡
- MSC software engineering

📚4 information science - ይህ department የሚያተኩረው ስለ መረጃ ነው፡፡ በተለይም ስለ degital መረጃዎች፡፡ ይህ ፊልድ አብዛኛው ሰው ያልተረዳው ቢሆንም በውስጡ ስለ cyber security እና deta science በተጨማሪም artificial intelligence እና data analysis በተጨማሪም Networking እና database አለው፡፡
• ዲግሪ በ IS ካላችሁ ማስተርሳችሁን በሚከተሉት department መስራት ትችላላችሁ፡፡
- MSC artificial intelligence
- MSC information science
- MSC software engineering
...

TIP 2 : የ computing ዘርፍ መግባት ከፈለጋችሁ ፍቅር እና መሰጠት ይፈልጋል፡፡ አራቱም almost 75% ተመሳሳይ ናቸው፡፡ የትኛውም ብትማሩ አዲስ ነገር መፍጠር ካልቻላችሁ እና አቅማችሁ ካላሳያችሁ ብዙም ውጤታማ አትሆኑም

Thanks to Sami from School of Computing and Informatics, Jimma university.
━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
📢 Department tip

🩻 RADIOLOGY

ራዲዮሎጂስት በሕክምና  ምስል ላይ የተካነ የዶክተር ዓይነት ነው ፡፡ የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች የተለያዩ ሁኔታዎችን ወይም ጉዳቶችን ለመመርመር ፣ ለመቆጣጠር እና ለማከም የሚረዱ እንደ ኤክስ-ሬይ ያሉ ምስሎችን ይተነትናሉ ፡፡

የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች ከሬዲዮግራፍ አንሺዎች የተለዩ ናቸው ፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ሁለቱም ባለሙያዎች ከህክምና ምስል ጋር የሚሰሩ ቢሆኑም የራዲዮግራፍ አንሺዎች ማሽነሪውን የሚሰሩ ሰዎች ናቸው

➻ለሬዲዮሎጂ ባለሙያ የሆነ ዶክተር ራዲዮሎጂስት ይባላል ፡፡

🔬 የምርመራ ራዲዮሎጂ ባለሙያዎችን እና የሕክምና የፊዚክስ ባለሙያዎችን ጨምሮ የተለያዩ የራዲዮሎጂ ዓይነቶች አሉ ፡፡

የሚከተሉትን ጨምሮ በርካታ የተለያዩ የራዲዮሎጂ ልዩ ዓይነቶች አሉ ፡፡
➾ዲያግኖስቲክ ራዲዮሎጂ

ዲያግኖስቲክ ራዲዮሎጂስቶች በሽታዎችን ለመመርመር እና ለማከም የሕክምና ምስሎችን ይጠቀማሉ ፡፡ የተለያዩ: -
ኤክስሬይ radionuclides አልትራሳውንድ የኤሌክትሮ ማግኔቲክ ጨረር

➾ጣልቃ ገብነት ራዲዮሎጂ

ጣልቃ-ገብነት የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች ህክምና የሌላቸውን ችግሮች ላለባቸው ሰዎች ህክምና ለመስጠት የህክምና ምስሎችን ይጠቀማሉ ፡፡
ለምሳሌ ፣ ጣልቃ ገብነት የራዲዮሎጂ ባለሙያ የቀዶ ጥገና አሰራርን ለመደገፍ የሕክምና ምስሎችን ሊጠቀም ይችላል ፡፡
ይህ ምስል የቀዶ ጥገና አሰራሮችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ወደ ፈጣን የማገገሚያ ጊዜያት ሊያመራ ይችላል ፡፡ ጣልቃ ገብነት ራዲዮሎጂስቶች በተለምዶ በቁልፍ ቀዳዳ ቀዶ ጥገና ላይ ይሰራሉ ​​፡፡
የቁልፍ ጉድጓድ ቀዶ ጥገና በትላልቅ ሰዎች ምትክ ትናንሽ ቁርጥራጮችን መሥራት እና ጥቃቅን ካሜራዎችን በመጠቀም በሰውነት ውስጥ ማየትን ያካትታል ፡፡
➾የጨረር ኦንኮሎጂ

አንድ የጨረር ኦንኮሎጂስት ካንሰርን ለማከም በጨረር ላይ የተመሠረተ ሕክምናን ይጠቀማል ፡፡ ይህ ቴራፒ የካንሰር ሴሎችን ለመጉዳት ከፍተኛ የኃይል ጨረር መጠቀምን ያጠቃልላል ፣ ይህም ተጨማሪ እንዳይሰራጭ ያደርጋቸዋል ፡፡

ምልክቶችን ለመቀነስ ወይም በአንዳንድ ሁኔታዎች ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ ለመፈወስ ይረዳል ፡፡

➾የሕክምና ፊዚክስ

የሕክምና የፊዚክስ ሊቃውንት የፊዚክስን ግንዛቤ በመጠቀም የህክምና ልምድን በተለያዩ መንገዶች ይደግፋሉ ፡፡

ለምሳሌ የታካሚዎችን ደህንነት እና የውጤቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በሕክምና ምስል ቴክኒካዊ ገጽታዎች ላይ ምክር መስጠት እና ማድረስ ይችላሉ ፡፡

አንዳንድ የህክምና የፊዚክስ ሊቃውንት እንዲሁ ተመራማሪዎች በመሆናቸው አዲስ የህክምና ቴክኖሎጂን በማዳበር ሚና ይጫወታሉ ፡፡ የሕክምና የፊዚክስ ሊቃውንት በዛሬው ጊዜ ሐኪሞች በተለምዶ የሚጠቀሙባቸውን እንደ ማግኔቲክ ድምፅ ማጉላት ምስል (ኤምአርአይ) ያሉ ብዙ መሣሪያዎችን አፍርተዋል ፡፡

👩‍🏫RADIOLOGIST ኦች የት መስራት ይችላሉ

🔬 የራዲዮሎጂስቶች በክሊኒካዊ ጽ / ቤቶች ፣ በሆስፒታሎች ወይም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መሥራት ይችላሉ ፡፡ የራዲዮሎጂስቶች ሥራ እንደየራሳቸው ሥራ ይለያያል ፡፡

🔬 ሁሉም የራዲዮሎጂስቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላል በሕክምና ምስል አያያዝ ዘዴዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላል

▸የተሰላ ቶሞግራፊ (ሲቲ)
▸መግነጢሳዊ ድምጽን መለዋወጥ
▸ፖታሮን ኢነርጂ ቶሞግራፊ
(ፒኤስኤ)
▸X-rays
▸አልትራሳውንድ
▸የኑክሌር ሕክምና
▸የተመጣጠነ ምስሎች...

    👩‍🏫 በ ቅድመ ምረቃ ዲግሪ መርሐ ግብር የስንት አመት ትምህርት ነው

☘️ሙሉ የሬዲዮሎጂ ባለሙያ ለመሆን 13 ዓመታት ያህል ይወስዳል ነገር ግን እንደ ነዋሪነት ትክክለኛ የሬዲዮሎጂ ልምምድ 8 ብቻ ነው ፡፡

☘️የራዲዮሎጂ ባለሙያ ለመሆን የሚወስደው መንገድ ረጅም እና ከባድ ነው ፡፡☺️
የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች በመጀመሪያ ከአራት ዓመት ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ማግኘት አለባቸው ፡፡ ከዚያ በኋላ የ 4 ዓመት የህክምና መርሃግብር መከተል እና የ 2 ዓመት የመማሪያ ክፍል ትምህርትን ፣ ከዚያም የ 2 ዓመት ክሊኒካል ልምዶችን እንደ የህፃናት ህክምና ፣ የአእምሮ ህክምና ፣ የቀዶ ጥገና እና የውስጥ ህክምና የመሳሰሉትን የሚያካትት የህክምና ማስተር ዲግሪያቸውን ማግኘት አለባቸው ፡፡

☘️የሕክምና ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ በሬዲዮሎጂ መስክ ስፔሻሊስት ሆነው የሬዲዮሎጂ ነዋሪዎችን ማጠናቀቅ አለባቸው ፡፡

☘️ነዋሪዎቹ ወደ ተለየ የራዲዮሎጂ subareas መዞር እና የራሳቸውን ምርምር ማካሄድ አለባቸው።

☘️የራዲዮሎጂ ነዋሪነት ከ 4 እስከ 5 ዓመት ሊወስድ ይችላል ፡፡ በመቀጠል ፣ ብዙ የራዲዮሎጂስቶች ስፔሻሊስት ለመሆን የጓደኝነት ጓደኞችን ያጠናቅቃሉ ፡፡

☘️በተጨማሪም ፣ አዳዲስ የሕክምና ቴክኖሎጂዎች ብቅ ማለት ራዲዮሎጂስቶች ቀጣይ የትምህርት ትምህርቶችን እንዲወስዱ እና እውቀታቸውን በየጊዜው ለማቆየት ተጨማሪ ስልጠና እንዲያገኙ ይጠይቃል ፡፡

☘️ስለዚህ ፣ የሬዲዮሎጂ ባለሙያ ለመሆን በአጠቃላይ እስከ 13 ዓመት ሊወስድ ይችላል ፡፡ ረዘም ያለ ብቃቶች ቢኖሩም የሬዲዮሎጂ ባለሙያ ለመሆን ቢያስፈልግዎትም ሥራው ራሱ ብዙ የገንዘብና የግል ጥቅሞችን ያስገኛል ፡፡

👩‍🏫RADIOLOGY የሙያ ዘርፍ ላይ ብቁ እና ስኬታማ የሆነ ባለሙያ ምን ምን ሙያዊ ተግባራትን ያከናውናል

☘️ የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች የሕክምና ምስል (ራዲዮሎጂ) አካሄዶችን ( ምርመራዎችን) በመጠቀም ጉዳቶችን እና በሽታዎችን ለመመርመር እና ማከም፡፡ እንደ ኤክስ-ሬይ ፣ የታመቀ ቶሞግራፊ (ሲቲ)ማግኔቲቭ ሬንጅ ምስል (ኤምአርአይ) ፣ የኑክሌር መድኃኒት ፣ ሲቲ ፒትትሮን ኢነርጂ (ፒኤስኤ) እና አልትራ።

👩‍🏫  RADIOLOG ከባድ ነው ወይስ ቀላል🤔

☘️የራዲዮሎጂ ባለሙያ መሆን ምን ያህል ከባድ ነው?

የራዲዮሎጂ ባለሙያ መሆን አንድ ሰው የባዮሎጂ ፣ የፊዚክስ ፣ የኬሚስትሪ እና የመድኃኒትን ውስብስብነት በጥልቀት እንዲረዳ የሚጠይቅ ከባድ ሥነ-ስርዓት ነው። የእነሱ ምስል ቴክኒኮችን እንዴት እንደሚሠራ እና ፊዚክስ እና ባዮሎጂ እንዴት እንደሚገናኙ ለማወቅ የራዲዮሎጂስቶች ስለ ፊዚክስ ብዙ ማወቅ አለባቸው።

👩‍🏫 ገቢውስ ምን ያክል ነው😋

☘️አጭጮርዲንግ ቶ Salary.com፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሬዲዮሎጂ ባለሙያው አማካይ ደመወዝ እስከ ግንቦት 414,890 ፣ ​​28 እ.ኤ.አ. ከ $ 2020 ዶላር ነው ፣ ግን አጠቃላይው መጠን ከ 360,690 እስከ 479,890 ዶላር ነው ፡፡

የደመወዝ ብዛት በትምህርት ፣ በብቃት ፣ ተጨማሪ ሙያዎች ፣ በሙያዎ ውስጥ ያሳለ numberቸውን ብዛት ጨምሮ በብዙ አስፈላጊ ነገሮች ላይ በመመስረት በስፋት ሊለያይ ይችላል ፡፡😚

ከማንኛውም ሌላ ድር ጣቢያ በበለጠ በእውነተኛ-ጊዜ እና በመስመር ላይ ካሳ ውሂብ አማካኝነት Salary.com ትክክለኛውን የካሳ ግብዎን እንዲወስኑ ያግዝዎታል።
በሜድስፔክ ዓመታዊ የሕክምና ማካካሻ ሪፖርት መሠረት ራዲዮሎጂ በሦስቱ ከፍተኛ ደመወዝ ከሚከፈላቸው የሕክምና ባለሙያዎች መካከል ቦታውን እንደያዘ ይቆያል ፡፡

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
📢 የታላቅ መልዕክት ለፍሬዎች....!

✔️ግቢ በየትኛውም ሰዓት ብትደርሱ ስለሚያስተናግዷቹህ በጭራሽ ቤርጎ እንዳትከራዩ ፤ በተለይ ከሩቅ ቦታ የምትመጡ ተማሪዎች ግቢው ስለሚረ'ዳቹህ ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳትዳረጉ ፤ ስርቆትም ሊኖር ስለሚችል ለብቻቹህ ከሆናቹህ ቤርጎ ባትከራዩ ፒስ ነው(በተለይ ሴቶች)

✔️ከብዙ ወከባዎች ለመትረፍ ከፈለጋቹህ አንድ ቀን ቀደም ብላቹህ ግቢ ግቡ ማለት ግቢው በ29 ከጠራ እናንተ በ28 ግቡ ያስገቧቹሃል ፤ ቀደም ብሎ የሚመጣን ተማሪ አናስተናግድም የሚሉት ሳክስ ነው ፤ቀደም ብላቹህ ከመሄዳቹህ በፊት ግን ነባር ተማሪዎችን ለማንኛውም አናግሩ ።

✔️ሻንጣ እንዳይቀያየርባቹህ የናንተን ሻንጣ የምትለዩበት መለያ ምልክት ይኑራቹህ ፤ ብዙ ሻንጣ ሊኖር ስለሚችል በስህተት እንዳይቀያየር (ለክፉም ለደጉ ግን ስልክ ቁጥር የሆነ ቦታ ላይ አስፍሩበት በወረቀትም ቢሆን....!)

✔️ግቢ በር ላይ ጥብቅ ፍተሻ ስለሚኖር ባለፈው የጠቀስኩላችሁን ነገሮች ይዛቹህ እንዳትመጡ ፤በስህተት ካመጣቹህ በር ላይ ይቀሟቹሃል ።
የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ቅርብ ቦታ አስቀምጡ ማለት ሻንጣ ውስጥ አታርጉት ፤ በር ላይ ቅድሚያ ስለምትጠየቁ ሁሉንም ዶክመንቶች በእጃቹህ ለመያዝ ሞክሩ ።

✔️ወንዶች ፀጉራችሁን ከልክ በላይ አታሳድጉ ቀለምም አትቀቡ ፤ የመጀመሪያ ቀናቶች ላይ ፀጉር ምናምን ሊባል ስለሚችል በተቻላቹህ ያህል እይታ ውስጥ የሚያስገባ የፀጉር style አይኑራቹህ(ምቺ ያስመታቹሃል....!)

✔️ሴቶች አለባበስ ላይ ወጥ አትርገጡ ፤
አንዳንዶቻቹህ ለትምሮ የምትሄዱ እስከማትመስሉ ድረስ ትራቆታላቹህ ፥ የምር አይነፋም ይብራብሽ እርድናም አይደለም ( ለነገሩ ግቢ በር ላይም አይፈቱሽም ጥበቃዎች...!)

✔️ግቢ ስትገቡ ፀባያቹህ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን ትዕግስተኛ መሆን አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ከማንም ጋር ብትጣሉ ካለምንም ማስተዛዘኛ የመባረር እድላቹህ ይሰፋል ።

✔️የጥላቻና የዘረኝነት ንግግሮችንም ይሁን አመለካከቶችን በፈጠራቹህ ጌታ ይሁንባቹህ እንዳትጠቀሙ ፤ የማንንም ስብዕና የሚነካ ንግግር በስህተት እንኳ እንዳትናገሩ ።

✔️ ግቢ ውስጥ ማንንም እንዳትንቁ ፤ እኔንም ጨምሮ ፤ ከየትኛውም ከተማ ልትመጡ ትችላላቹህ ግቢ ውስጥ እስካላቹህ ድረስ ግን እኩል ናቹህ ማለትም አትበላለጡም።

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
1👍1