G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
#ጠምባሮ

" መምህራን ኑሮ አቅቷቸው አብዛኞቹ ንብረታቸውን፣ ሞባይላቸውን እየሸጡ ነው " - የ3 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህር

መምህራን ደመወዝ ስላልተከፈላቸው ሥራ በማቆማቸው ምክንያት እስከዛሬ በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ትምህርት አልተጀመረም።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኘው ጠምባሮ ልዩ ወረዳ፣ ለተከታታይ 3 ወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን ሥራ እንዳቆሙና የዘመኑ የመማር ማስተማር ሒደትም እስከ አሁን እንዳልተጀመረ ገልጸዋል።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ መምህር ፤ የ3 ወር ደመወዝ አላገኘንም መምህራን ኑሮ አቅቷቸው አብዛኞቹ ንብረታቸውን፣ ሞባይላቸውን እየሸጡ ነው፤ ትምህርት እስካሁን ያልጀመረበት ዋናው ምክንያት ደመወዝ አለመከፈሉ ነው ብለዋል።

እኚሁ መምር ደመወዝ ሊከፈል ያልቻለው ወረዳው ውስጥ ያሉ አስተባባሪዎች መምራት ስላልቻሉ ነው ብለዋል።

" ከክልል ደመወዝ ይላካል ከክልል የሚላከውን ገንዘብ በአንድ ቀን በውሎ አበል ያወጡታል በዚህም እኛን ችግር ውስጥ ጥለውናል ተማሪ ፣ ወላጆች ፣ ህፃናትም እንዲቸገሩ ሆኗል ፤ ተማሪዎች ትምህርት ባለመማራቸው አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንስከመውደቅ እና ስደትን እንስከመምረጥ ድርሰዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

" እኔም ከመምህርነት ውጭ ሌላ ስራ የለኝም ደመወዝ ስላልተከፈለኝ የምበላውን እየምጠጣውን አጥቻለሁ " ብለዋል።

ሌላው ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ መምህር መሰረታዊው የትምህርት ስራ እንዳይጀመር ያደረገው የደመወዝ ችግር ነው ብለዋል። ተጓዳኝ የልማት ችግሮች ፣ የፖለቲካ ምላሽ ከሚፈልጉ ጉዳዮችም መኖራቸውን አንስተዋል።

ተማሪዎች በበኩላቸው ፤ ወደ ትምህርት ሳይመለሱ ከ2 ወር በላይ እንደባከነ ገልጸዋል። ይህም ከፍተኛ የመደበል ስሜት እንዳሳደረ ጠቁመዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ተማሪ ሌሎች በባከነው ጊዜ ምክንያት ሌሎች የሀገሪቱ ተማሪዎች ላይ መድረስ እንደሚያስቸግር ተናግሯል። ዕጣ ፋንታችንም አናውቅም ብሏል።

አንድ ወላጅ በበኩላቸው ለችግሩ መፍትሄ የሚሰጥ ጠፍቷል ሲሉ ተናግረዋል። ትውልዱ ወደ ጭለማ እየሄደነው ሲሉ አክለዋል።

የማዕከላዊ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ በፈቃዱ፣ በደመወዝ አለመከፈል የተነሳ የጠንባሮ ልዩ ወረዳን ጨምሮ እንደ ሀዲያ ዞን ባሉ አካባቢዎች የዘመኑ የመማር ማስተማር ስራ እንደተቋረጠ አምነዋል።

የችግሩ መንስኤ በበጀት እጥረት እና በተያያዥ ምክንያቶች ናቸው ብለዋል። ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረግን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በአዲስ አመት እንዴት የበጀት እጥረት ይከሰታል ተብለው ሲጠየቁ ፤ በዋናነት ከማዳበሪያ እዳ ጋር በተያያዘ እንደሆነ አመልክተዋል።

እዳው 5 ፣6 ፣ 7 ፣ 8 ዓመት የነበረ እንደሆነ ጠቁመው ያ እዳ መቆረጥና በየጊዜው በሚከሰተው የበጀት እጥረት ወረዳዎች ስለሚበደሩ ብድሩ ተከማችቶ ዛሬ ላይ መድረሱን ገልጸዋል።

ኃላፊው ለመፍትሔው፣ ከዞኖቹ የሥራ ኃላፊዎች ጋራ እየመከሩ እንደሆነ አስታውቀዋል።


ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
2
#WolkiteUniversity

በ2015
ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ #የተመደባችሁ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት #ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2014 ዓ.ም የመጀመርያ ሴሚስተር በውጤት እና በተለያዩ ምክንያቶች ዊዝድሮዋል (Withdrawal) በመሙላት #ላቋረጣችሁ የዳግም ቅበላ (Readmission) ተማሪዎች በሙሉ፡-

👉 የምዝገባ ጊዜ ህዳር 20-21/2016 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ህዳር 24/2016 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

💥ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የሚከተሉትን ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡

1ኛ. መሰናዶ ያጠናቀቃችሁበትን ሰርተፍኬት፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውን ከማይመለስ አንድ ኮፒ ጋር እና አራት 3x4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ

2ኛ. አንሶላ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡
ይህንን የመግቢያ ጊዜ አሳልፎም ሆነ ቀድሞ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

━━━━━━━━━━━━━━━━━
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች

በ2015 ዓ.ም  የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት ወደ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ #የተመደባችሁ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት #ያመጣችሁ  ተማሪዎች በሙሉ፡-
የምዝገባ ጊዜ  ታህሳስ 05-07/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል ሙሉውን ከላይ ይመልከቱ

━━━━━━━━━━━━━━━━━
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2
📢ስንቶቻችሁ ዝግጁ ናችሁ

📚 ስለምትይዙት ሻንጣ ሳይሆን ጫናዎችን ለመጋፈጥ በ ስነ ልቦና ምን ያክል ዝግጁ ናችሁ

🙄 ለ አንድ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ ከ አሁን በፊት ከሚሰጠው መደበኛ ጊዜ ማነሱ የማይቀር ነው። በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 2 unit ልትጨርስ ትችላላችሁ። ፍሬሽ ናችሁ ብለው አስተያየት ካላደረጉላችሁ☹️::

አሳይመንት እና ፈተና ሊደራረብባችሁ ይችላል። ይህ ነገር የሚሆነው ለትንሽ ጊዜ ስለሆነ ወደ ፊት ሊመጣ ያለውን ተስፋ እያደረጋችሁ ፡ ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴዎችሁ ዕቅድ እና ፕሮግራም አውጥታችሁ በፅናት እና በብቃት እንደምታልፋት እርግጠኛ ነኝ። ደግሞ ለአንድ ሴሚስተር በግ ተራ እና over መውጣት ይለፋችሁ🤨

😂 ሀይስኩል እና መሰናዶ ላይ ፍትፍት አድርገው ፡ ብትንትን አድርገው ሲያስተምሯችሁ የነበሩ ወርቅዬ መምህራኖቻችሁን ግቢ ስትገቡ አታገኛቸውም። በቃ በአጭሩ የግቢ መምህራኖች እንደምትፈልጉት አድርገው ላያስተምሯችሁ ይችላሉ። ስለዚህ ጎበዝ senior ተማሪዎችን እና Google ን እንዳትፋቷቸው።

🙏 አደራ አደራ አደራ የምላችሁ ነገር ቢኖር ፡ ብዙ ኪሎሜትሮችን አቋርጣችሁ የምትሔዱት ለመማር ፡ የሆነ ነገር ለማግኘት ነው። ስለዚህ፡

የመጀመሪያ አመት ላይ ውጤት ስሩ። አሁንም አደራ የምላችሁ ነገር የመጀመሪያ አመት ላይ ትኩረታችሁን ወደ ትምህርት አድርጉ እና ውጤት ስሩ።

📍 ውጤታችሁ በየ ሴሚስተሩ በምትወስዱት credit hours መሰረት እየተደመረ ነው cumulative የሚሰራው። ስለዚህ፡

🎈የመጀመሪያ አመት ላይ ውጤት ከሰራችሁ ፡ በሚቀጥሉት አመታት ውጤታችሁ ዝቅ ቢል እንኳን ያን ህክል በጣም አይወርድም።

🎈የመጀመሪያ አመት ውጤት ካልሰራችሁ ግን ፡ በቀጣዮቹ አመታት አሪፍ ውጤት ብትሰሩ ራሱ በለፋችሁበት እና በሰራችሁ ልክ አይሆንም ውጤቱ።

📚 የመጀመሪያ አመት ውጤት ብዙ ገፀ በረከት አለው።

👉 ወደምትፈልጉት ዲፓርትመንት ትገባላችሁ።
👉 የሚቀጥሉትን አመታት በአንፃራዊነት ፈታ ብላችሁ ትማራላችሁ።
👉አትጫሩም😜። ሲጀመር ግቢ ላይ ትንሽዬ ካነበባችሁ መጫር አይታሰብም።
👉 ደግሞ ውጤት ሰራን ብላችሁ፡ እንዳትደነፋ እሺ። Be calm!
👉 የሀገሪቱ የትምህርት ስርአት ነው ውጤት ስሩ ብዬ እንዲጨቀጭቃችሁ ያደረገኝ። በምትገቡበት ዲፓርትመንት ዘላቂ የሆነ ዕውቀት እንዲኖራችሁ አድርጋችሁ አንብቡ። ለ interview ይጠቅማችሗል። አትሸምድዱ Google ን ተጠቀሙ።

ስለ ግቢ ብዙ ነገር ማለት ይቻላል እሱንም live ገብታችሁ ልትኮመኩሙት ነው😎......

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2
#MekelleUniversity

በ2016 ዓ.ም በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ለተመደባቹህ አዲስ ተማሪዎች ከህዳር 28-30/2016ዓ.ም ባለው ጊዜ ሪፖርት እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።


💥የምዝገባ ቦታ
፨ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዓዲ ሐቂ ግቢ
፨ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ

👉ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ መያዝ የሚጠበቅባችሁን ነገራት ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ‼️


━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
📚 ብዙዎች ግቢ ላይ መንግስት የመደባቸውን ፊልድ ብቻ ገግመው ይቸክላሉ ነገር ግን በዚ የውድድር አለም አንድ ሳብጀክት ማስተር ከማረግ የተለያዮ ሳብጀክቶች ይዞ መሯሯጥ አይከፋም ። እናም ቢያንስ ሁለት ከበዛ 3 ዲግሪ ይዛችሁ መውጣት ይኖርባቸቹሃል..!

📚 ለምሳሌ ፦ ሶፍትዌር ኢንጅነሪግ ተመድባቹሁ  በሳምንት 4 ቀን ከሆነ የምትማሩት ቅዳሜ እና እሁድ አልያም የማታ በዲስታንስ በመማር አንድ ዲግሪ   በኖርማል ከምትማሩት  ወጣ ያለ ፤  ለምሳሌ ማኔጅመነት አልያም ኢኮኖሚክስ ብትማሩ አሪፍ ነው ። በዲስታንስ መማር አልያም ቅዳሜ እና እሁድ መርጣቹሁ ዮኒቨርስቲው በሚያመቻቸው ዕድል መማር ትችላላቹህ ። በርቀት ስለሆነ  ለፈተና ግዜ እያነበቡ ፈተናውን በመውሰድ መመረቅ ይቻላል የኖርማል ሳብጀክቱን ሳይጋፋባችሁ የሶሻል ትምህርቶች በ3 አመት ስለሚያልቁ በሁለተኛው አመት ጀምራቹሁ በአራተኛው መጨረስ ትችላላቹሁ በመጨረሻው አመት ሙዱም ስለማይኖራቹሁ GC ስትሆኑ ሌላ ዲግሪ በማኔጅመንት ወይም በመረጣችሁት ይኖራቹሃል ።

💬  በመጀመርያው አመትም መጀመር ትችላላቹሁ ግቢውን እስክትላመዱ ሊያስቸግራቹሁ ስለሚችል አንድ አመት ታግሳችሁ ቢሆን ግን ይመረጣል ።

   የክፍያው ነገር 

📚 ክፍያው የተጋነነ አይደለም በወር 300- 400 ብር ነው ፤ በ10 ሺ ብር ከጎበዛቹሁ አንድ ዲግሪ ማለት ነው ። ያውም ከኖርማሉ ቀድማቹሁ ። ሲኒየሮችን ብታናግሩዋቸው ታዲያ ያግዛቹሃል ።

   ነጥብ

📚 የርቀት ወይ በማታ ስለሆነ ብዙ የሚከብድ ፈተና የለም ። ትንሽ ካነበባችሁ ከ 2.8 በላይ ማምጣት ቀልድ ነው ። ኖርማሉን ኮ ስንቶች በ2 ነው ሚመረቁት ታዲያ ትዕግስት ይጠይቃል ። አንዳንዴ ኖርማል ክላስ ጋር ክላሽ ሊያረግ ይችላል ።  ምንግዜም ለኖርማሉ ነው ቅድሚያ መስጠት ያለብን ።

ሶስተኛዋ  ዲግሪስ

📚 በካንፓስ ቆይታቹሁ በጣም የምታቃጥሉዋት ግዜ ክረምት ነች ። ብዙዎች ዕረፍት በሚል ይቀመጣሉ ። እናት እና አባትህ አንተ ተስፈ አርገው ፤ በየአመቱ 100 ሺ ህዝብ እየተመረቀ ስራ በሚያጣበት ሀገር ማረፍ ዘበት ነው ።  ደሞስ ቁጭ ብሎ ድንጋይ ከመሞቅ ፥ ፊልም ከማየት 24 ሰዓት  ከመጋደም አንድ ዲግሪ ብትጨምር አይሻልም ። አብዛኞቹ ካንፓሶች (summer course) ሰመር ኮርስ ይሰጣሉ  ። በክረምት ለ3 አመት በመማር አንድ ዲግሪ መጨመር ትችላላቹሁ ። 3ተኛ ዲግሪ ማለት ነው ።ከትምህርተ ወደ ትምህርት  ከደበራችሁ  ደሞ ሌላ ከህይወታቹ ጋር የሚገናኝ ነገር ። ፊልም መማር ፤ ሙዚቃ መማር ፤ መንጃ ፍቃድ ፤ ቋንቋ መማር ፤ ብቻ አለመተኛት ።ግዜን አለማቃጠል ነው ። ዕረፍት የለሽ በመሆን መማር ነው ።

💬 አንዳንድ ልጆች ክረምቱን ገንዘብ ለመሸቀል በት በት ይላሉ ይሄም በጣም አሪፍ ነገር ነው ። ቤተሰብ ማስቸገር በጣም አስጠሊ ነገር ነው ። ብቻ ክረምታችሁን በአልባሌ ጉዳይ ማሳለፍ የለባችሁም አንደኛችሁን ታርፋላችሁ ። በርትቶ ሰግጦ መማር ነው ።

   ኧረ ልፋቱስ

📚 አዎ አድክም ነገር ነው ። ነገር ግን ቀልድ አይደለም በሶስት ዲግሪ መመረቅ ቀልድ አይደለም ። ስራ በአንዱ ብታጡ እንኳ በአንዱ አታጡም ደሞ አንዱን ማስተር ማረግ ከቻላችሁ ያበደ CV ያዛቹሁ ማለት ነው ። የትኛውመ ድርጅት ቢሆን ሊቀጥራቹሁ ይንገበገባል ። ወይስ በአንድ ተመርቆ ድንጋይ ማስጣት ይሻላላል ። የእናንተ ምርጫ ነው ።

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2👏1
⚙️ ልብህን የሚሰብረው ከሰዎች ብዙ መጠበቅ ነው፤ ስለዚህ ከሰዎች ብዙ አጠብቅ። እህቴ የሚከፋሽ ሌሎች የሚያደርጉልሽን ጠብቀሽ ስላላገኘሽ ነው።

🤔 ከሰው መጠበቁን አቁመን ደስታችንን ከፈጣሪና ከራሳችን ልብ ውስጥ ማግኘት ነው ያለብን፤ ያኔ አንዱን ቀን ደስ ብሎን ሌላኛውን ቀን አይከፋንም ምክንያቱም ደስታችን ሌሎች ላይ ጥገኛ አይደለም።

@🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
2
🔥Addictive students

የግቢ ተማሪዎችና የሱሳምነት ፈተና

ማንኛውም ተማሪ ቢሆን ግቢ ወይም ዩንቨርሲቲ ሲገባ የመጀመሪያ   ትኩረቱ ትምህርትና ትምህርት ብቻ በመሆኑ ምንም አይነት እንቅፋት ቢያጋጥመው ከአላማው እንደማያሰናክለው እርግጠኛ በመሆን ወደ ዩንቨርሲቲ ይቀላቀላል ።  ይህን እንጂ ብዙውን ተጨባጭ በምናይበት ጊዜ ነገሩ እንዲህ ቀለል የሚል አይመስልም ፥ ምክንያቱ ደግሞ ባላሰብነው መንገድ እንቅፋቶች ስለሚያሰናክሉን ነው።
ከትምህርት ገበታችን የሚያሰናክሉን ብዙ ነገሮች ቢኖሩም እኔ ግን ለዛሬ ስለ ሱስ ለመፃፍ ከጀልኩ ።
ካልተሳሳትኩ 99%u ተማሪ ወንድም ይሁን ሴት ከቤተሰቡ አደራ ተቀብሎ ብሎም ተመርቆ ወደ ዩንቨርሲቲ ሲላክ ከማንኛውም ዓይነት ሱስ ነፃ እንደሆነ አስባለሁ፤ ስለ ቀሪዋ1%ት  ምንም ማለት አልፈልግም ምክንያቴ ደግሞ ከቤተሰባቸው በላይ ልመክራቸው ስለማልችል ነው


እናም እነዚህ ብዙሃኑ ተማሪዎች ግቢ ሲገቡ ከሚሸነፉባቸው ነገሮች ውስጥ በሱስ መጠመድ ግንባር ቀደሙ ነው ማለት እችላለሁ።
ስለ ሱሱ ሳይሆን ማውራት የምፈልገው ስለ መንስኤው ነው
ለሱሳምነት አሳልፈው ከሚሰጡን ምክንያቶች መካከል ትልቁና ዋናው እኔም ሁሌ የምላቹህ አስተሳሰባችን ነው ፤ የእውነት ዩንቨርሲቲ  መግባት ማንነታችንን ሊገዛን አይገባም
የብዙ ፍሬሾች ችግር ግቢ ሲገቡ የዘመኑን እርድና መምረጣቸው ነው ፤ ስለ ዘመኑ አራዳነት ባለፈው ጽሁፌ ነግሬያቹህ ነበር ካልረሳችሁት
አራዳ ነኝ ብለህ ወይም ብለሽ ባላሰብከው መንገድ እንዳትሰናከል ፡ እንዳትሰናከዪ..

እናም እስከቻላችሁት ድረስ የዘንድሮ አዲስ ገቢ ተማሪዎች (ፍሬሾች) ክፉ ደጉን እስከምትለዩ ድረስ ብትረጋጉና ሙሉ ለሙሉ ትምህርታቹህ ላይ ብቻ ብታተኩሩ ከሱስ አደጋ ለመዳን ሰበብ ሊሆናቹህ ይችላል ባይ ነኝ።

ሌላው መንስኤ ደግሞ 👇👇
ጓደኛ ነው
ለግቢ ቆይታችን እጅግ በጣም ወሳኙ ነገር ጓደኛ ነው
የሀገሬ ሰው እንዲህ ይላል " ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለሁ " (አቦ ምን አይነት ድንቅ ንግግር ነው )

ማንኛውም ሰው ወደደም ጠላ በጓደኛው ተፅእኖ ስር ይወድቃል እናም ግቢ ስትገቡ አደራችሁን ከኢቦላ በላይ የምትቀርቡት ጓደኛ ያስፈራቹህ
ሰዎች ስንባል social animaሎች በመሆናችን በየትኛውም የህይወታችን ክፍል ውስጥ ተገንጥለን መኖር አንችልም ፤  ግቢ ደግሞ ካለ ጓደኛ በጣም ከባድ ነው ፡ ለምን መሰላቹልህ ከቤተሰብ በመራቃቹህ ብዙ ክፍተት ሊፈጠርባቹህ ይችላል በተለይ ሴቶች  ስለዚህ ስለ ምትጎዳኙት ተማሪ ጠንቅቃቹህ ማወቅ አለባቹህ ።

ሌላው ደግሞ ከግቢ ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን  ከመጎብኘት መጠንቀቅ ያስፈልጋል

በተለይ አንዳንድ ግቢዎች አከባቢ ያሉ መጠጥ ቤቶችና ጫት ማላመጫዎች ብሎም ምናምን ማጨሻ ቤቶች ሆን ተብለው ተማሪውን ከትምህርት ገበታው ለማሰናከል የተዘጋጁ ይመስላሉ ።

እንደው አደራ ብዬ የምላቹህ እንደዚህ አይነት ቦታዎች ላይ ድርሽ እንዳትል ፥ ብዙ ወንድም እህቶች የሚሸወዱት እንደቀልድ በመልከስከስ ነው።
በቃ የጓደኛዬን ሙድ አላበላሽም ምናምን ብለው በርጫ ቤት ይከሰታሉ ፡ ለተወሰኑ ቀናት አይቅሙም ፣ አያጨሱም ምናምን ፤ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ግን ከነባሮቹ በርጮሎጂስቶች ብሰው ቁጭ ይላሉ። ( በማይቀለድ ነገር አትቀልዱ)

ሌላ ሳልነግራቹህ የማላልፈው ኦቨር የሚሏትን ጨብሲ ነው

ብዙ ሳላወራ በጥቂቱ ኦቨር ማለት ወደ ከተማ ወጣ ብሎ መጠጥ ቤት ሂዶ  መስከር ማለት ፤ ጣጣው በስካር ብቻ ቢያቆም ትንሽ ይሻል ነበር ችግሩ ግን ብዙ ነው
በትንሹ እንኳ የlocal( የከተማው ጎረምሶች) ጡንቻ መመዘኛ ይሆናሉ፣ ስልክ ይነጠቃሉ ፣ ግቢ ይበጠብጣሉ ፣ ዶርም ይበጠብጣሉ ( ሻታ ይበረግዳሉ)...... አያልቅም

እባካቹህ የቤተሰቦቻችሁን አደራ አትብሉ ፥ እድሜያችሁንም በከንቱ ሱስ አትግደሉ

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🔥2
#WerabeUniversity

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ትምህርት ዘመን አዲስ የተመደባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 24 እና 25/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በ2015 ዓ.ም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ በተመሳሳይ ህዳር 24 እና 25/ 2016 ዓ.ም መሆኑም ተገልጿል።

የአንደኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር መማር ማስተማር ሒደት ህዳር 26/2016 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል፡፡

በተለየያ ምክንያት የአንደኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ሳትጨርሱ ዊዝድሮ ያደረጋችሁ እንዲሁም በውጤት ምክንያት የመልሶ ቅበላ ሞልታቹ ትምህርት ያቋረጣቹ ተማሪዎች ህዳር 27/2016 ዓ.ም ሪፖርት ማድረግ ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እንዲሁም የለሊት አልባሳት (አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ) እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ ታህሳስ 04 እና 05/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➢ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➢ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➢ ስድስት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ።

የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በቦቆጂ ካምፓስ ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በአሰላ ከተማ ዋናው ግቢ ሪፖርት እንድታደርጉ ተብላል፡፡

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🎯 ግቢ ላይ ውጤት እንዴት መስራት እንችላለን።

         ❇️Worksheet

🔰Worsheet ማለት መምህሩ የሆነ chapter አስተምሮ እንደጨረሰ በተማራችሁት ትምህርት ዙሪያ ከበድ ከበድ ያሉ እና የ concept ጥያቄዎች ከተለያዩ መፅሀፍት አውጣጥቶ ፈተና ሊደርስ አካባቢ የሚሰጣችሁ ነው። በተለይ ፈለጣ የሚበዛበት ዲፓርትመንት የምትገቡ ልጆች worksheet የተለመደ ነው። መምህሩ worsheet ከሰጣችሁ ፡  ፈተናውን በዚህ መልክ ተዘጋጁ ማለቱ ነው። ከ worksheet ቱ ላይ ጥቂት የማይባሉ ጥያቄዎች ፈተና ላይ ይወጣሉ። መምህሩ ጥያቄዎቹን የሚያወጣው ከ መፅሀፍ ስለሆነ የጥያቄዎቹን መልስ ከዛው መፅሀፍ ታገኙታላችሁ ፡ ከሌለ ደግሞ Google ማድረግ ይጠበቅባችሗል። ስለዚህ የሚሰጣችሁን worksheet ጥሩ አድርጋችሁ ከሰራችሁ ፡ ፈተናውን ትሰሩታላችሁ።

    ❇️የአጠናን መንገድ(ስልት)

🔰እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው🤔?

🎯 አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ።

🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ።

🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው።

ስለዚህ እንዴት እናብብ🤔

🔔 የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም🤷‍♀️

ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ

🎯 የ ሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው።

🎯  መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ።

🎯 የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው።

🗣 ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን።

     ❇️የጊዜ አጠቃቀም

🔰ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው።

      ❇️ አለመሰልቸት

🔰ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል።

   ❇️ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን።

🔰ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ።

    ❇️Google

🔰ለ ግቢ Google በጣም ወሳኝ ነገር ነው። Assignment መስራት ብትፈልጉ ፡ practical education በ video  ማየት ብትፈልጉ ፡ የተለያዩ መፅሀፎችን እና የመፅሀፍ solution ማውረድ ብትፈልጉ ፡ ምናልባት መምህሩ የሰጣችሁ ኖት ካልገባችሁ እና ሳይንሱን መረዳት ብትፈልጉ ፡ Google ለነዚህ ሁሉ በቂ መፍትሔ አለው። ስለዚህ Google ን የቅርብ ወዳጅ አድርጋችሁ ወጤት መስራት ትችላላችሁ ፡ ሳይንሱን መረዳት ትችላላችሁ። በዚሁ አጋጣሚ ለ Google ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ😘

          😊 The End

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👨‍🎓🧑‍🎓የተማሪዎች አይነት (types of learners)

📮ይህ ፅሁፍ ሁሉም የትምህርት ብቃት እንዳለው ነገር ግን የትምህርቱ ዘዴ እና አቀባበላችን እንደሚለያይ
ያሳያል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የተለያዩ አይነት ተማሪዎችን እና የሚቀላቸውን የመማር ዘዴ ማጣጣም ያስፈልጋል።
የራሳችሁ የመማር ምርጫ ከየት እንደሆነ መመርመርም አትርሱ።

🧑‍🎓1— የእይታ ተማሪዎች (Visual learners)

እነዚህ የተማሪ አይነቶች የሚገባቸው መማር በእይታ ሲሆን ነው። ያዩት ነገር እንዲሁ በቃል ከሚነገራቸው
ይልቅ አይረሳቸውም። እነዚህ ተማሪዎች በተግባር ማየት ካልቻሉ በሃሳባቸው እየሳሉ ቢያነቡ በቀላሉ ማስታወስ ይችላሉ።

🧑‍🎓2— የተግባር ተማሪዎች (Kineshetic learners)

እነዚህ በበኩላቸው ራሳቸው በተግባር የሞከሩት ነገር ቶሎ ይገባቸዋል፣ አይረሱትም። ሰው ሲያደርግ ከማየት
በላይ ራሳቸው በማድረግ ይማራሉ። ለነዚህ ወደ ተግባር እየቀየሩ መሞከር ይመከራል።

🧑‍🎓3– የመስማት ተማሪዎች (auditory learners)

እነዚህ አንድን ነገር ከሰሙት በቂያቸው ነው። ብዙ ከማጥናት በላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲያዳምጡ ይመከራሉ። የሰሙትን ነገር ይረዳሉ።

🧑‍🎓4– የጭንቀት ተማሪዎች (Stress learners)

ያስጨነቃቸው ነገር አይረሳቸውም። ተጨናንቀው ግዴታ አውቄ መግባት አለብኝ ካሉ ማን እንደነሱ። ትኩረት
መስጠት እና መጣር ይመከራሉ።

🧑‍🎓5— የመዝናናት ተማሪዎች (Ease learners)

ዘና ፈታ ብለው ያነበቡት እና የተማሩት አይረሳቸውም። እነዚህ ሳይጨናነቁ፣ አእምሯቸውን ዘና አድርገው እና ጥሩ ስሜት ውስጥ ሆነው ቢያነቡ በጣም ውጤታማ ይሆናሉ።

🧑‍🎓6– የፅሁፍ ተማሪዎች (Scrubble learners)

ለየት ባለ መልኩ ትምህርት ወደ አእምሯቸው የሚገባው ሲፅፉት ነው። እንዳልረሳው ብለው ቢፅፋም
ስለማይረሱት ደግመው ላያዩት ይችላሉ። እነዚህ ሲያጠኑ ደጋግመው እንዲፅፉ እና ከጥናት በሗላም ራሳቸውን የሚፈትኑት ያጠኑትን በወረቀት ላይ ደግመው
ለመፃፍ በመሞከር እንዲሆን ይመከራል።

🧑‍🎓7— የእምነት ተማሪዎች (trust learners)

አነዚህ ከሚያምኑት ወይም ከሚያከብሩት አለያም ከባለስልጣን የተሰጠን ትምህርት በጭራሽ አይረሱም። ትምህርቱ ሳይሆን መምህሩ ነው ለነሱ ወሳኙ። ይሄን
ከሆን የተማርነውን ከምናምነው ሰው እንደተነገረ አድርገን እያሰብን ድጋግሞ ከማጥናት የተሻለ ምክር አይኖርም።

🧑‍🎓8— በማስተማር የሚማሩ (teach learners)

እነዚህ አንድን ነገር ካስተማሩት አለቀ—ተመጠጠ ማለት ይቀላል። እና ሁሌም ተማሪ ስለማይገኝ የተወሰነ አንብበው ቀሪውን– ቆም ብሎ፣ ተማሪዎች
እንዳሉ ራስን አሳምኖ፣ ጮክ ብሎ በማስተማር ማጥናት ይመከራል።

🧑‍🎓9— ተመሳሳዩን በመስራት የሚማሩ (copy learners)

ለየት ባለ ሁኔታ ያዩትን ወይንም የተማሩትን ነገር አስመስለው ሲሰሩት አይረሱትም። ያየነውን ነገር ደግመን ሁሉንም ቅደም ተከተል ሳንረሳ አስመስሎ
ለመስራት በመሞከር እንዲያጠኑ ይመከራል።

⭐️#ማጠቃለያ፦ አንድ አይነት ዘዴ በመጠቀም የሁሉንም ተማሪዎች የመማር ምርጫ እና ብቃት ማሟላት አይቻልም።
ከኢትዮጵያ መምህራን መድረክ - partially edited

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
Logic chapter 1.pdf
249.3 KB
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
💊 Pharmacy | ፋርማሲ

🦠ፋርማሲ ከ other health ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአድሱ የትምህርት ስርአት freshman course ጨምሮ የ5 አመት ትምህርት ነው ።
ፋርማሲ ስትገቡ የምትማሯቸው ኮርሶች mostly chemistry ነክ around [ 60%] ,biological around [25%] እና ሌሎችም አሉ ።ስለዚህ chemistry የሚወድና አንባቢ ተማሪ በብቃት ይወጣዋል።

🔬ፋርማሲ ስትማሩ የሚያስደስቱ ነገሮች ፦

🔺የመድሃኒት ቅመማ በላብላቶሪ ትሰራላችሁ ፤ ከባህላዊ ህክምናና ከእፅዋት እንዴት መድሃኒት ማግኘት እንደምትችሉ  ታውቃላችሁ  ፤ በላብላቶሪ ውስጥ lotion, cream, gel, shampoo, sanitaizer....የመሳሰሉትን ኮስሞቲክስ ታመርታላችሁ ፤መድሃኒትን አይጥ ላይ በመውጋት ትመራመራላችሁ ወዘተ....

💊በፋርማሲ ስትመረቁ ምን ትሰራላችሁ? ገቢውስ እንዴት ነው ? 🤔

1️⃣, clinical pharmacy የሚባለው hospital ውስጥ ተቀጥራችሁ

2️⃣, 🧪pharmaceutical company የመድሃኒት ፋብሪካና በተወሰነ መልኩ የኮስሞቲክስ ፋብሪካ ጋር

3️⃣, የመድሃኒትና የምግብ ቁጥጥር ማለትም ወደ ሀገር የሚገቡና የሚወጡትን መፈተሽ

4️⃣, በግላችሁ community pharmacy በመክፈት በተለይ ቤተሰቦቻችሁ በገንዘብ የሚያግዟችሁ ከሆነ በጣም አዋጭ ነው።

5️⃣, 💉የማንኛውንም የህክምና መድሃኒትና ቁሳቁስ በ pharmacist ቁጥጥር ስር ነው የሚገዛው (የሚቀርበው) ስለዚህ እዛ ላይም የናንተ ሙያ አለ።

6️⃣, የ fingerprint,forensics, food toxicity,drug toxicity,.....የመሳሰሉትን የወንጀል ምርመራ ላይ መስራት ይቻላል ።

7️⃣, እኛ ሀገር ብዙም ባይኖር የመድሃኒት ጥናትና ምርምር ላይም ትሰራላች

⭕️ስለ ገቢው፦ እውነቱን ለመናገር በፋርማሲ ትምህርት  ከተመረቃችሁ በኋላ ስለ ገንዘብ አያሳስባችሁም ። እያጋነንኩ አይደለም ከቻላችሁበት በጣም ባለሀብ ትሆናላችሁ ። ስለ ፋርማሲ ብትጠይቁ ቀድመው የሚነግሯችሁ businesses ነውና እሱ አያሳስባችሁ ።

📌ስራ ላላገኝ እችላለሁ? እንደማንኛውም የጤና ተማሪ ከhospital,ጤና ጣቢያ ትሰራላችሁ plus ሌላ አማራጭ በግል ትሰራላችሁ ወይም ከላይ ከ ተራ  ቁጥር 2-7 ያሉት አማራጮች አሉላችሁ ።

📺ትምህርቱ ከባድ ወይስ ቀላል? pharmacy ከ medicine በመቀጠል የሚመደብ ስለሆነ ከበድ ይላል ነገር ግን chemistry,biology and labolatory ነክ ትምህርቶ ለሚሰራና ለሚያነብ ተማሪ በቀላሉ ማለፍ ይችላል ። እንደዬ ዩንቨርስቲው ቀለል ባለ መልኩ የሚያስተምሩም አሉ ። ስለዚህ ጠንከር ያለ ተማሪ ቢሆን የተሻለ ውጤት ያመጣል።

🔘በአጠቃላይ ፋርማሲ ከሌሎች የጤና ዘርፎች ለየት የሚያደርገው ብዙ የስራ መስኮች ያሉትና ጥሩ የሚባል ክፍያ የሚገኝበት መሆኑ ነው።

🚖ስለ ፊልድ መረጣ በተመለከተ እንደ medicine ገና የመጀመሪያ ሴሜስተር ኮርስ እንደጨረሳችሁ ነው ። ሌሎች other health ግን 1ኛ አመት ከጨረሳችሁ በኋላ ነው።

⭐️ለRemedial እና ለ12 ተማሪዎች   ቻናል👇
@GTUTORIALCLASS
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
1