G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
በኦሮሚያ ክልል በኦነግ ሸኔ ላይ በተወሰደ እርምጃ 160 የሚሆኑት ሲደመሰሱ፣ 68 በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ አስታውቀዋል፡፡‼️

በተጨማሪም 1 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ለቡድኑ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ እና 104 የሚሆኑት ከህወሓት ቡድን ጋር በቀጥታ ግንኙነት የነበራቸው መሆኑ ተረጋግጦ በቁጥጥር ስር ውለዋል እንዳሉ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

'ሽፍታው' በሚንቀሳቀስባቸውን ዞኖች የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ጠንካራ ስራ እየተሰራ እንዳለም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡በቦረናና ጉጂ ዞን ቡድኑን ለመያዝ ከአባ ገዳዎችና ነዋሪዎች ጋር እየተሰራ እንዳለም ገልፀዋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
Forwarded from Finance Today
የሕወሓት ጁንታን ተልእኮ ተቀብለው በአዲስ አበባ ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 800 የሚጠጉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!!

ከሃዲውን የሕወሓት ጁንታ ተልእኮ ተቀብለው በአዲስ አበባ የተለያዩ ጥቃቶችን ለመፈፀም እና የፀጥታ መደፍረስ እንዲከሰት አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 800 የሚጠጉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገ ጠንካራ ክትትል ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥራ ማዋሉን ነው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩ ህገ- ወጥ ዝውውር ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክተር ኮማንደር ግርማ ተሰማ ያስታወቁት።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሩሲያ በማንኛውም ሁኔታ ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም አስታወቀች‼️

ሩሲያ በማንኛውም ሁኔታ ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም በልኡካን ቡድኗ አማካይነት ዛሬ አስታውቃለች። ሩሲያ ይህንን የገለጸችው አራት አባላትን የያዘውን የልዑካን ቡድን መርተው ከህዝብ ተወካዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በተወያዩት አምባሳደር ኤቭጊኒ ቴሬክሂን አማካኝነት ነው።

አምባሳደሩ፣ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሀገራዊ ሁኔታ ሩሲያ እንደምትገነዘብ አስታውሰው፤ በየትኛውም ሁኔታ ከጎንዋ በመሆን ከ120 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እንፈልጋለን ብለዋል። አምባሳደር ቴሬክሂን አክለውም፣ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በመረዳዳት እና በመተማመን የተመሠረተ የረጅም ጊዜ ወዳጅነት መሆኑን አስታውሰዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላት ግንኙነት የቆየ መሆኑን ገልጸው፣ ይኸው የቆየው ወዳጅነት እንዲጠናከር በጋራ ልንሠራ ይገባልም ብለዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ጦርነት እያካሄደች ሳይሆን የሕግ የበላይነትን የማስከበር እና ሰላምን የማረጋገጥ ዘመቻ ላይ መሆኗን ገልጸው፤ የሰላም ማስከበር ሥራው በአፋጣኝ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ሀገሪትዋ ወደነበረችበት ሰላም እንደምትመለስ መናገራቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
መቀለ ከ50-60 ኪ.ሜ ርቀት ተከባለች።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ትናንት በሰጡት መግለጫ ትላልቅ ከተሞችን ጨምሮ አብዛኛው የትግራይ ክልል መሬት በአገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አክሱም፣ አደዋ እና አዲግራት ከተሞች ደግሞ በቅርቡ ከህወሓት ነጻ የወጡ ከተሞች ናቸው ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፤ የክልሉ መዲና የሆነችውን መቀለን ለመቆጣጠር መከላከያ ሠራዊት ከ50 እስከ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ተከባ እንደምትገኝ ተናግረዋል።

አምባሳደሩ ጨምረው እንደተናገሩት፤ የህወሓት ኃይሎች ለቀው ለመውጣት ሲገደዱ በመሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እያደረሱ እየሸሹ ነው ብለዋል። እንደምሳሌም የአክሱም አየር ማረፊያ ላይ ጉዳት እንዲደርስ መደረጉን እንዲሁም ከስድስት ያላነሱ ድልድዮች እንዲፈርሱ መደረጋቸውን እና መንገዶች መቆፈራቸውን ተናግረዋል።

አምባሳደር ሬድዋን "የመቀለ ከተማ ነዋሪ እውነታውን ተረድተው፤ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የህወሓት መሪዎችን አሳልፎ መስጠት ይኖርበታል" ብለዋል።
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያስተሳስረው የዲማ - ራድ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ።‼️

60 ነጥብ 2 ኪሜ እርዝመት ያለው ይህው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፍጻሜውን ማግኘቱ አማራጭ የገቢ ወጪ ንግድን ለማሳለጥ ከፍተኛ ተቀሜታን ያበረክታል።የዲማ - ራድ ድልድይ የመንገድ ግንበታ ፕሮጀክት ለሀገራችን ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝላትን ቡናን ጨምሮ የፍራፍሬ ፣ማር እና ቅመማ ቅመም ምርት ውጤቶችን ከምዕራቡ የአገሪቷ ክፍል ወደ ውጪ በመላክ ሀገራዊ ሚናው የጎላ ሲሆን በአካባቢው ያሉትን አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

መንገዱ ከዚህ ቀደም ለትራንስፖርት አመቺ ያልሆነ የተጎዳ ጠጠር መንገድ የነበረ ሲሆን መስመሩ ሊያበረክተው ከሚችለው ፋይዳ አኳያ ወደ አስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እንዲያድግ ተደርጓል፡፡
ፕሮጀክቱን በኢትዮጵያ መንግስት በተመደበ 856 ሚሊዮን ብር ገንብቶ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ኮንስተራክሽን ስራዎች ኮርፖራሽን ነው።

የማማከር እና የቁጥጥር ስራውን ያከናወነው ደግሞ የኢትዮጵያ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ኮርፖራሽን ነው፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘም የደቡብና ጋምቤላ ክልልን የሚያገናኘው የዚሁ የመንገድ ትስስር አካል የሆነው የሚዛን ዲማ የመንገድ ፕሮጀክትም በመጠናቀቅ ላይ ነው።ይህው ፕሮጀክት 91 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመትን ይሸፍናል።ለፕሮጀክቱ የሚውለውን 1.2 ቢሊየን ብር የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው።የመንገድ ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው MCC17 የተባለ የቻይና አለማቀፍ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ነው።የማማከሩን ተግባር ደግሞ የህንዱ አርቪ አሶሲዬት ኮንሰልታንሲ ከኢትዮጽያው አማካሪ ድርጅት ኔት ጋር በጋራ እየሰሩ ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ይሄን አሪፍ የሆነ ቻናል በመቀላቀል እና ጓደኛዎንም እንዲቀላቀሉ በማድረግ ይጥቀሟቸው እረሶም ይጠቀሙ ሁሌም አሪፍ አሪፍ መረጃዎችን እናደረሶተለነ።
የ8ተኛ እና የ12ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ ሊራዘም እንደሚችል ፊደል ፖስት አስታወቀ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የክፍል ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ሐሙስ ዕለት ከሰዓት በኃላ በነበረው የውይይት ጊዜ ትምህርት ሰኞ ማለትም በ21/03/2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የተነጋገሩ መሆኑን ሆኖም ይህም አሁንም ጊዜያዊ ፕሮግራም መሆኑን አሳውቀዋል።
ተማሪ እና ወታደር ሁሌም ለፈተና ዝግጅ ነውና ቢራዘምም እንኳ ተስፍ ባለመቁረጥ ተማሪዎቹ ማንበባቸውን እንዲከጥሉም አሳስበዋል።
ገና ጥርጣሬ ስለሆነ የመጨረሻ ውሳኔ ሲወሰን የምናደርስዎ ይሆናል
Channel name was changed to «ወቅታዊ ሹክታዎች»
መቀሌን ለመጠበቅ ሁሉም ዜጋ መሳሪያ እንዲታጠቅ መልክት ተላልፎል ሲል አልጀዚራ ዘገበ‼️

Getachew Reda promised to “arm each and every civilian to defend the city of Mekelle”, the capital city of Tigray with a population of about 500,000 people.

'Fight to the death’

Since the conflict erupted on November 4, hundreds of people have been killed and about 40,000 have fled into neighbouring Sudan.

The leader of Ethiopia’s dissident Tigray region has said his people are “ready to die” defending their homeland, rejecting Prime Minister Abiy Ahmed’s ultimatum that they surrender within 72 hours.
©አልጀዚራ

@Esat_tv1
@Esat_tv1
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
የ12ኛ ክፍል አገር ዐቀፍ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ፈተናው መንግሥት በትግራይ እና ሌሎችም የአገሪቱ አካባቢዎች የጀመረውን ሕግን የማስከበርና ፀጥታን የማረጋገጥ ሥራ ካጠናቀቀ በኋላ በሚቆረጥ ጊዜ ገደብ ይሰጣል ነው የተባለው።

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቋል። መግለጫ የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታው ሚሊዮን ማቲዎስ የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግን እንደየክልሎች ዝግጁነት ከታኅሣሥ 1 እስከ 30/2013 ይሰጣል ብለዋል። (ት/ት ሚኒስተር)

SHARE | ሼር
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ሀገራት ጣልቃ እንዳይገቡ አሳሰቡ❗️

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ማለዳ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ገፆቻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ሀገራት በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት መርህ መገዛት አለባቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና እንዲሁም የአፍሪቃ ኅብረት መስራችና አባል ሀገር በመሆን ረጅም ታሪክ ያላት ሀገር መሆኗን በማስታወስ፤ ለሁለንተናዊ ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲሁም ለፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ህግጋትና መርሆዎች ጠንካራ አቋም እንዳላት ገልፀዋል ።

ሀገሪቱ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በተመድ እና በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ተእልኮዎች ውስጥ የምታደርጋቸው ተሳትፎዎች ህግ አክባሪ መሆኗንም ማሳያዎች ናቸው ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ አያይዘውም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ «ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ» ለማገዝ ያለውን ፍላጎት በበጎ እንደሚያመለከቱትና ፤ነገር ግን ዓለም አቀፍ ሕግን መሠረት ባደረገ መልኩ ሊተገበር ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያ መንግሥት የድጋፍ ጥሪ እስኪያቀርብ ድረስ ሊጠብቅ እንደሚገባ አሳስበዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወዳጆቻችን ሰጡን ላሉት ምክርና ትኩረት አመስግነው፤ ነገር ግን በውስጥ ጉዳይ ምንም አይነት ጣልቃገብነትን እንደማይቀበሉ ገልፀዋል።በመሆኑም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህንን ተገንዝቦ በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠብ ጠይቀዋል።
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
በትግራይ "የጦር ወንጀል" እንዳይፈጸም ስጋት ገብቶኛል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለፀ።

የተባበሩት መንግሥትታ ድርጅት የ72 ሰዓታት ቀነ ገደቡ ሲጠናቀቅ በመቀለ ሊከሰት የሚችለው ሁኔታ ከወዲሁ አሳስቦኛል አለ። የጦር ወንጀል ሊፈጸም ይችላል የሚል ስጋት እንዳለውም ደርጅቱ ከወዲሁ አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ መቀለ ከተማ መቃረቡን ተከትሎ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለማስቀረት የህወሓት አመራሮች እና የትግራይ ክልል ኃይሎች እጃቸውን እንዲሰጡ ባለፈው እሁድ ምሽት የ72 ሰዓታት የጊዜ ገደብ መስጠታቸው ይታወሳል።

ይሁን እንጂ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የጠቅላይ ሚንስትሩን ጥሪ እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል። የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤል (ደ/ር) የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ እንደማይቀበሉትና ክልላቸውን የማስተዳደር መብታቸውን ለማስጠበቅ እስከመጨረሻው ለመታገል ብሎም ለመሞት ዝግጁ እንደሆኑ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚንስትሩን ጥሪ ተከትሎ በርካታ የትግራይ ኃይሎች እጅ መስጠታቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ትናንት አስታውቋል። ሦስተኛ ሳምንቱን በደፈነው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ግጭት በርካቶች ተገድለዋል፣ ከ40ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ ቀያቸውን ጥለው ወደ ጎረቤት አገር ሸሽተዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ ጦርነቱ ቶሎ ካላበቃ በሚቀጥሉት 6 ወራት ብቻ 200ሺ ዜጎች ሊፈናቀሉ ይችላሉ ብሎ ይሰጋል። የተራድኦ ድርጅቶች የሰብአዊ ቀውሱ ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ ምሥራቅ አፍሪካን ሊያተረማምስ የሚችል ችግር ሊፈጥር ይችላል እያሉ ነው። (ቢቢሲ)
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
ውቅሮ ከተማ‼️

ትናንት ምሽት ሰራዊቱ የውቅሮ ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል::

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትናንትናው እለት የውቅሮ ከተማን ሙሉ ለሙሉ እንደተቆጣጠረ የመረጃ ምንጫችን የገለፁልን ሲሆን ሰራዊቱ መቀሌ ከተማን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ መሆኑን ገልፀውልናል።

በትናንትናው እለት በሜካናይዝድ የታገዙ የፌዴራል መንግስት ኃይሎች ከሰላሳ እስከ አርባ ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኙ አካባቢዎች መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘራቸውን መገለፁ ይታወሳል።

ከመንግስት አካል በጉዳዩ የሚደርሰን መረጃ ካለ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

@Esat_tv1
@Esat_tvtv1
Forwarded from Finance Today
በመተከል ዞን 23 የጸረ-ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጁንታውን የሕወሓት የጥፋት ተልዕኮ ይዘው በንጹኃን ዜጎች ለይ ጥቃት ሲያደርሱ በነበሩ 23 የጸረ-ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ የጸጥታ አካላት ትናንት በወሰዱት የተቀናጀ እርምጃ በዞኑ ማንዱራ ወረዳ 17፣ በዳንጉር ወረዳ 2፣ በጉባ ወረዳ ደግሞ 4 በድምሩ 23 ጸረ-ሠላም ያላቸውን ኃይሎች መደምሰሱን ነው የገለጸው።

ኮማንድ ፖስቱ፣ በመተከል ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት እያደረሠ ባለው ኃይል ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ከወትሮው በተለዬ መልኩ አጠናክሮ መቀጠሉን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ ታሪክ በተለይ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ከፍተኛ ስምና ጀግንነትን የተጎናፀፈውን 21ኛ ክፍለ ጦርን ትህነግ/ህወሃት ደምስሼዋለሁ ብለው ነበር የክፍለጦሩ አዛዦችና ወታደሮች ስለ ክፍለ ጦራቸው ከአንደበታቸውና ከስፍራው የሚሉትን ስሙ::

🎬የምስል ዘገባ🎬

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
* ማስታወሻ

አሮጌውን የብር ኖት በአዲስ የመቀየሪያ የሶስት ወር ጊዜ ሊጠናቀቀ 17 ቀናት ቀርተውታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
ፅንፈኛው ቡድን ደምስሼዋለሁ ብሎ የሀሰት ዜና ያሰራጨበት 21ኛ ክፍለጦር አሁንም በጀግንነት እና በከፍተኛ ድል  እንደቀጠለ ነው!

ፅንፈኛው ቡድን ደምስሼዋለሁ ብሎ የሀሰት ዜና ያሰራጨበት 21ኛ ክፍለጦር አሁንም በጀግንነት በከፍተኛ ድል እየገሰገሰ መሆኑን የክፍል ጦሩየኦፕሬሽን ምክትል አዛዥ ኮሎኔል መንግስቱ ደሴ ተናግረዋል። በራያ ግምባር ህግን የማስከበር ተልዕኮ የተሰጠው ክፍለጦሩ ከዚህ ቀደም ጁንታው ተዘጋጅቶ ምሽግ ገንብቶ የነበረበትን ወሳኝ ቦታዎች እያስለቀቀ የገጠመውን ሰራዊትም እየደመሰሰ እየተጓዘ መሆኑን አሳውቀዋል።

⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
በቅርብ ቀን መቀሌ ላይ እንገናኛለን!

የ21ኛ ክ/ጦር 3ኛብርጌድ አዛዥ ኮ/ል ተክሉ ውሪሳ ° ክፍለ ጦራችንን ደመሰስናቸው ካሉን ሃይሎች ጋር በቅርብ ቀን መቀሌ ላይ እንገናኛለን። የጀግኖችን የሃይል ምት መቋቋም ያቃተው የከሃዲው ቡድን ሃይል በዛሬው እለት ብቻ ከ300 በላይ ላውንቸርና ብዛት ያላቸው ድሽቃዎችን ጥሎ ነው የፈረጠጠው" ብለዋል።

የ21ኛ ክ/ጦር 3ኛብርጌድ 3ኛ ሻለቃ አዛዥ ሻምበል ሲሳይ ተሾመ " ለትህነግ ውሸት አዲስ ነገር አይደለም ። ኢትዮጵያውያንን ለበርካታ አመታት ሲዋሽና ሲዘርፍ የነበረ ቡድን ነው። ይህ ደግሞ ለእርሱ የሞቱን መፍጠን ፣ ለእኛ ደግሞ የድላችን መድመቅ ማሳያ መስታወታችን ነው" ብለዋል ።

ም/አስር አለቃ ዋሲሁን አበበ " መሬት ላይ ያለው እውነት በጣም የተለየ ነው። ይሰበራሉ ተብለው የማይታሰቡ ኮንክሪት ምሽጎች በማይታመን ጀግንነት ተሰብረዋል። ይሄን መቋቋም ያቃተው ከሃዲው ቡድን ከመዋሸት ውጪ አማራጭ እንዳይኖረው አድርገን ቀብረንዋል"ብሏል።

ም/አስር አለቃ ሃዊ ረጋሳ" የተሸነፈ ብዙ ያወራል። እኔ የ21ኛ ክ/ጦር ሃኪም ነኝ። ከቀላል ቁስለኛ ውጪ ይህ ነው የሚባል ከባድ ጉዳት አላየሁም።ሰራዊቱ በከፍተኛ ጀግንነት ከጠላት አፍንጫ ስር ነው ያለው ። ጠላትን በቁጥጥር ስር አውለን ለህዝባችን እስከምናስረክብ ድረስ ፈጣን ጉዟችን አይገታም " ብሏል።

Via : FDRE Defense force
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰