G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
ጅማ፡ እሳት አደጋ ንብረት አወደመ!

በጅማ ከተማ ከረቢያን ሆቴል ውስጥ የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

በዛሬው እለት ቀኑ 6፡00 አከባቢ ከሆቴሉ ኩሽና የተነሳውን እሳት ለማጥፋት አንድ የእሳት አደጋ መኪና የተሰማራ ሲሆን፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ አደጋውን መቆጣጠር ተችሏል፡፡

የአዲስ ዘይቤ ሪፖርተር ከጅማ እንደዘገበው በእሳት አደጋው የደረሰው የንብረት ውድመት በመጣራት ላይ ይገኛል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Deleted Account
በዛሬው የከሚሴ ጦርነት

👉 በርካታ ልዩ ሃይሎች መንደር ውስጥ በሸመቁ ታጣቂ ኦነጎች ተገድለዋል።

👉 ሆስፒታል ምግብና ውሃ ሊያደርሱ የሄዱና በጥሩ ስነምግባራቸው የሚታወቁ 5 የከተማው ኦሮሞ ወጣቶች ሆስፒታሉን ከብበው በነበሩ የኦነግ ታጣቂዎች ለልዩ ሃይል ስንቅ ልታቀብሉ ነው በሚል ጥርጣሬ በጥይት የተመቱ ሲሆን ሁለቱ ወዲያው ሲሞቱ ሁለቱ ቆስለዋል፥ አንዱ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል።

👉 ኑሩ አሊ የተባለ የባህልና ቱሪዝም ኃላፊ ከከተማው ወጣ ባለ ቦታ ለልዩ ሃይሉ መረጃ ልትሰበስብ ነው በሚል በኦነግ ታጣቂዎች ተገድሏል።

👉 አንድ የፕሮቴስታንት ቸርች ተቃጥሏል።
አማራ ክልል: በሰሜን ሸዋ ዞን የተከሰተው የፀጥታ ችግር!

በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር መከሰቱ ይታወቃል። የተደራጁ ታጣቂዎች ከሸዋሮቢት ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ዙጢ ከተማ በቅርቡ በፈጸሙት ጥቃት ሀብትና ንብረት እንዳወደሙ ተነግሯል።

የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች የጸጥታ ስጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ነገር ግን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የኅብረተሰብ ክፍሎች ሸዋሮቢት ከተማ በመገኘት ነዋሪዎችን በማረጋጋት ላይ እንደሆኑ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ሰርጎ ገቦች እና ተመሳስለው የሚኖሩ አካላት አሁንም የኅብረተሰቡ ስጋት መሆናቸውን አንስተዋል።

በሸዋሮቢት ከተማ ዛሬ ሱቆች፣ ሆቴሎች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መዘጋታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል ሲል የዘገበው አብመድ የአማራ ክልል መንግሥትም አካባቢውን በደንብ ማደራጀትና ማኅበረሰቡ እራሱን እንዲከላከል ማድረግ እንዳለበት ጠቅሰዋል ብሏል።

ጥቃት በሚያደርሱ አካላት ላይ የማያዳግም ርምጃ በመውሰድም የሕዝቡን ሠላም እንዲጠብቅ ጠይቀዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እሸቱ ጌታቸው የጸጥታ ችግር ተከስቶባቸው የነበሩ አካባቢዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይል ቁጥጥር ሥር ናቸው ያሉ ሲሆን የመንግሥት የጸጥታ አካላትም ኅብረተሰቡን ለማረጋጋት ቅድሚያ ሰጥተው እየሠሩ መሆኑን አመላክተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መነጋገራቸው ተሰማ!

በአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የተላኩት ሴናተር ክሪስ ኩንስ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መነጋገራቸው ተሰምቷል።

አቶ ደመቀ መኮንን ለሴናተር ክሪስ ኩንስ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት እየተካሄደ የሚገኘው ድርድር ላይ ያላትን ቁርጠኝነት እንደነገሯቸው ተገልጿል።

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ 2023 ላይ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው የሕዳሴ ግድብ ከድህነት ለመውጣትና የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብላ ታምናለች። ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌትም በቅርቡ እንደሚከናወን አስታውቃለች።

ግብፅ እና ሱዳን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ምንም አይነት ስምምነት ላይ ሳይደረስ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት አከናውናለሁ ማለቷን ይቃወማሉ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (BÊŽÂ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ዘንድሮ ተላልፎ በቅርቡ በተሰጠው የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አፈጻጸም ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንዳስታወቁት የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አለም አቀፍ ወረርሽኝ በሆነው የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ወደ ዘንድሮ ተዘዋውሮ በቅርቡ መሰጠቱን አስታውሰው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነበረው የፈተና አሰጣጥ ሂደትም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣታቸው ፈተናው ያለምንም ችግር እንደተሰጠ በመግለጽ በዚህ ሂደት የተገኘው ተሞክሮም ግንቦት ወር ላይ እንደሚሰጥ በሚጠበቀው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ጥሩ ልምድ የተገኘበት እንደሆነም አስረድተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዲናኦል ጫላ የፈትና አሰጣጥ ሂደቱን አስመልክቶ ባቀረቡት ሪፖርት በአዲስ አበባ ፈተናው በ41 የፈተና ጣቢያዎች ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2/2013 ዓ.ም ያለምንም እንከን መሰጠቱን ገልጸው በዚህ ሂደትም የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ሁሉም በአፈጻጸሙ የተሳተፉ አካላት ላቅ ያለ ምስጋና እንደሚገባቸው አስታውቀዋል።

በመርሀ ግብሩ በተመሳሳይ ሁኔታ በኮቪድ 19 ምክንያት ወደ ዘንድሮ ተላልፎ የተሰጠው የ2012 ዓ.ም የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የውጤት ትንተና ቀርቦ ተሳታፊዎች ውይይት አካሂደውበታል።

@Free_Education_Ethiopia

Stay safe
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (BÊŽÂ)
“የአማራ ክልል ልዩ ኃይል የኢትዮጵያ ሠራዊት ሆኗል ማለት ይቻላል” - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

“የኤርትራ ሕዝብ እና መንግስት ከኢትዮጵያ ጥቃት ተፈፅሞባቸውን የሄዱ ወታደሮችን የተንከባከበበትን መንገድ ኢትዮጵያ መቼም አትረሳም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ “የኤርትራ ወታደር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ የገባበት ምክንያት የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ ስለሆነባቸው እንደሆነ ነግረውናል” ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ኤርትራን በሚያዋስነው ድንበር ላይ የኢትዮጵያ ሰራዊት ባለመኖሩ ምክንያት የኤርትራ ሰራዊት ድንበር አካባቢ ተሰማርቷል ሲሉ የሆነውን አስረድተዋል።

“ማንን የት ማስፈር እንዳለብን ለኛ መተው ያስፈልጋል” ሲሉ ከአሜሪካ በኩል የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ከትግራይ መውጣት አለበት በሚል ወጥቶ የነበረውን መግለጫ የተቃወሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የአሜሪካ ወታደር የት መስፈር እንዳለበት ኢትዮጵያ ሳትሆን ባለቤቷ አሜሪካ ነው የምትወስነው” ብለዋል።

“የአማራ ክልል ልዩ ኃይል የኢትዮጵያ ሠራዊት ሆኗል ማለት ይቻላል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ “ከፈለግን ሱማሌም ቢሆን ማሰማራት እንችላለን” ሲሉ ገልፀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
“ተላላኪ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ አይፈጠርም” - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ!

“ኢትዮጵያ ማለት ታጥቆ ሲፎክር የነበረን ኃይልን በሶስት ሳምንት ውስጥ ብቻ መደምሰስ የቻለ መንግስት ያለባት አገር ናት” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ “ከየትኛውም መንግስት ጋር ጦርነትና አተካራ አልፈልግም፤ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከመጣ ግን አንገቴ ይቀላል እንጂ ለድርድር አልቀርብም” ሲሉ ለሕዝብ ተወካዮች ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ ተላላኪ መንግስት መፍጠር አይቻልም” ሲሉ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ይሀንን ለማድረግ የሚሯሯጡ አይሳካላቸውም” ሲሉ አስታውቀዋል።

“ኢትዮጵያ ትበተናለች የሚል ስጋት የለኝም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሽምቅ ውጊያ ግዜው አልፎበታል፤ አሁን ያለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ይህንን አይፈቅድም” ሲሉ ተናግረዋል።

“የሱዳን ሕዝብ ወንድም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሱዳንም ሆነች ኢትዮጵያ አሁን ላይ ባለባቸው ችግር ምክንያት ጦርነት ለማድረግ ዝግጁ ስላልሆኑ ውጊያ አያስፈልግም፤ በንግግር እንፍታው ሲሉ በድጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል።”

“ኢትዮጵያ ግብፅን የመጉዳት ፍፁም ዓላማ የላትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዳሴ ግድብ በተመለከተ ግን ቃል በተገባው መሰረት ይፈፀማል” ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
“የህወሓትን ምርጫ ሲያጅብ የነበረ ፖለቲከኛ ሁሉ…” - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ!

“ከምርጫ እንዳይወጡ የኦፌኮ አመራሮችን አነጋግሬ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን አሸናፊ የሚያደርግ ምርጫ እናደርጋለን” ሲሉ ተናግረዋል። “ብናሸንፍም በቅንነት እናገለግላለን፤ ከተሸነፍንም ያለማወላወል እናስረክባለን” ሲሉም ተደምጠዋል።

“አሁን ላይ ወደ ምርጫው ለመግባት ጥያቄ ያቀረቡትን አካላትን ጥያቄ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ይቀበለዋል ብዬ በፅኑ አምናለሁ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ “ዲሞክራሲን በሚፈለገው መጠን ለማስፋት ግን ግዜ ያስፈልጋል” ሲሉ ተናግረዋል።

“የህወሓትን ምርጫ ሲያጅብ የነበረ ፖለቲከኛ ሁሉ አሁን ላይ በምርጫው አንወዳደርም ማለታቸው የዘንድሮውን ምርጫ ትክክል አያደርገውም ማለት አይደለም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እፍርታም ፖለቲከኞች ቶሎ ብለው ወደ ምርጫው ቢገቡ መልካም ነው” በማለት ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Adam Getenet
ተወርዋሪው አማራ ልዩ ሀይል
ተሸንፈንም አናውቅምም ሚኒልክ ብርጌድ ዛሬ በፓርላማ መሸነፋቸው ያቃጠላቸው የኦነግ ደጋፊዎች በግልፅ ንዴታቸውን በስሜታዊነት ገልፀዋል የደረሳችውብን እናተ እንጂ እኛ አደለንም ወያኔ የሰጣቹ ወረዳ ነው በአማራ ክልል የኦሮሞ ዞን ሚባል መሬት የለም በገዛ መሬታችን ህዝባችን አይገደልም
ጀግናው አማራ ፋኖ ገበሬው ልዩ ሀይል የማያዳግም እርምጃውን አጠናክሮ እየቀጠለ ነው አጣዬ የተያዘው ቀበሌ ነፃ ወቷል
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ግንቦት 30 ይሰጣል‼️

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ በወረቀት ይሰጥ የነበረበትን ስርዐት በዚህ አመት ሙሉ በሙሉ አስወግዶ ፈተናውን ግንቦት ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ገልፀዋል ማምሻውን በነበራቸው መግለጫ አስታውቀዋል።

#በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮቪድ-19 ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው የአምናው ፈተና በወረቀት መሰጠቱንም አስታውሰው በዚህ አመት ለሚፈተኑት ወደ 700ሺ የሚጠጉ ተፈታኞች ታብሌቶች ገብተው ዝግጁ መሆናቸውንና የማጓጓዝ ስራ በመጀመር ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

ከሚያዚያ 3 እስከ 15 ቀን 2013 ዓ/ም ታብሌቶቹ እና የፈታኝ አስተማሪዎች ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱ ገልጸው ለተማሪዎች የ አንድ ወር የመለማመጃ ጊዜ እንደሚሰጣቸውም አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት የ2013 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ይሰጣል ተብሏል።


#share
@Timhrtministers
@Timhrtministers
#ሰበር_ዜና‼️

ኢትዮ-ኤርትራ፡

ኤርትራ ሠራዊቷን ከኢትዮጵያ ግዛት ለማስወጣት ተስማማች!

ኤርትራ በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ያስገባቻቸውን ወታደሮቿን ለማስወጣት ከስምምነት መደረሱን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ፣ አርብ ጠዋት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሐሙስ ዕለት አሥመራ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ባደረጉት ውይይት ኤርትራ ሠራዊቷን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማማታለች።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የድንበር አካባቢዎቹን ተረክቦ ጥበቃውን ወዲያውኑ እንደሚጀምር ሁለቱ መሪዎች ከስምምነት ደርሰዋል።

ዝርዝር መረጃውን እና የጠቅላይ ሚንስትሩ ጉብኝት በተመለከተ በዩትዩብ ገፃችን ይዘን እንመለሳለን

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
#ትኩረት!!

የጭላሎ ጋለማ ደን እሳት እየነደደ ነው።

በአርሲ ብሔራዊ ተራሮች ፓርክ በጭላሎ ጋለማ ደን ላይ የእሳት አደጋ በድጋሜ ተከስቷል።

በጭላሎ ተራራ ላይ የተከሰተዉን እሳት ለመቆጣጥር ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም እሳቱ ከአቅም በላይ መሆኑን የአረሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓረክ አስታውቋል፡፡

ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በአካባቢዉ የተገኙት የህብረተሰብ ክፍሎች የተከሰተዉን እሳት ለማጥፋት ያደረጉት ጥረት ከአቅማችዉ በላይ በመሆኑን ተናረዋል፡፡

ፓርኩ ከሚያካልላቸው ዘጠን ወረዳዎች ውስጥ በዘጠኙ (9) ወረዳዎች ዉስጥ የእሳት አደጋዉ የተከሰተ መሆኑን የአርሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አሳውቋል።

እሳቱ በፍጥነት እየተጓዘ እና አብዛኛዎቹን የተራራዉን ክፍል እያካለለ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ፓርኩ እሳቱ ከህብረተሰቡ አቅም በላይ በመሆኑ ለክልሉ አሳውቋል ፤ አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚፈልግ ጥሪ ማቅረቡን ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (π)
የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ በቀጣይ ሳምንት እንደሚጀመር የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የኦንላይ ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዝያ 15/2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

ምዝገባው የዞንና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች በሚያወጡት ፕሮግራም መሰረት እንደሚፈፀም ከቢሮው የፈተና ክፍል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአማራ ክልል በ2013 የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በግል ከ165 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አስፈታኝ ትምህርት ቤቶችም 370 ሲሆኑ የፈተና ጣቢያዎች ደግሞ 357 ናቸው፡፡

የ2013 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦንላይን እንደሚሰጥ ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የአክሱም ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ከጥቃት ተረፉ!

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አዲግራት አካባቢ የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ ድንገቴ ጥቃቱ በተደረገበት በቅርብ ርቀት ላይ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩት ወደ አክሱም ዩንቨርሲቲ የሚጓዙ ተማሪዎች ከጥቃቱ ተርፈዋል፡፡

የአዲስ ዘይቤ ሪፖርተር በአካባቢው ከነበሩ የዓይን እማኞች እንደተረዳው፡- ከአዲግራት አቅጣጫ በመምጣት ላይ በነበሩ የኤርትራ ወታደሮች ላይ የሕወሓት ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተዋል፡፡ በታጣቂዎቹ ጥቃት ወታደሮቹን ጨምሮ በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከል በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወደ ዓድዋ በማምራት ላይ የነበሩ ሲቪል ተጓዦችም ይገኙበታል፡፡ 8 የአካባቢው ገበሬዎችን ጨምሮ የ17 ሰዎች ህይወትም አልፏል፡፡ እንደ ዓይን እማኞች ምስክርነት በጥቃቱ 25 የሚጠጉ ወታደሮች፣ ገበሬዎችና ሲቪሎች ሞተዋል፡፡

ቤቶችም ተቃጥለዋል፡፡ በተሽከርካሪዎቹ ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ታፍነው ተወስደዋል፡፡ ወደ አክሱም ዩንቨርሲቲ በመጓዝ ላይ የነበሩት ተማሪዎችም ተኩስና ግርግሩን በመሸሽ ወደመጡበት መመለሳቸውን ሰምተናል፡፡

ምንጭ : አዲስዘይቤ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#FAKE NEWS
ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ትምህርት ይቋረጣል‼️

ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ትምህርት ይቋረጣል ፤ ዩንቨርሲቲዎች ይዘጋሉ በሚል የሚናፈሰው መረጃ ትክክለኛ አለመሆኑንና ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚባክን የትምህርት ጊዜ እንደማይኖር ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ስለሆነም ተማሪዎች ባልተረጋገጠ መረጃ ግራ አትጋቡ ፤ አዲስ ነገር ሲደርሰን የምናሳውቃቹህ ይሆናል!

#SHARE
ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን👇👇
@Timhrtministers
@Timhrtministers
የጉራፈርዳ ጥቃት ...

በማነታቸው ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈፀመባቸው መሆኑን በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ተናግሩ።

ጥቃት የተፈፀመው አብዛኛው በሚባል ደረጃ በአማራ ተወላጆች ላይ ሲሆን በተፈፀመው ጥቃት የሰው ህይወት መጥፋቱን፣ ሃብት እና ንብረት መውደሙን ተጠቂዎች አሳውቀዋል።

ችግሩ በመንግስት ይፈታል/የንፁሃን ጥቃት ያስቀማል እየተባለ ቢጠበቅም ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ እና እየከፋ መምጣቱን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የጥቃቱ ሰለባዎች ጥቃት እየተፈፀመብን ያለው "ውጡ" በሚል ነው ብለዋል።

ከተፈፀመው ጥቃት የተረፉ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው እና ከቄያቸው ተፈናቅለው ይገኛሉ።

የተፈናቀሉት ወገኖች በብርድ እና በፀሃይ እየተሰቃዩ ነው።

ህፃናት ፣ እናቶች ፣ ነፍሰ ጡሮች ተፈናቅለው ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የጥቃቱ ሰለባዎች በቀጣይ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፀመ መንግስት ጥበቃ እንዲያደርግላቸው የጠየቁ ሲሆን እራሳቸውን ተደራጅተው ከጥቃት እንዲጠብቁም አስተዳደራዊ መዋቅር ይፈጠረልን ሲሉ መጠየቃቸውን የአ/ብ/ኮ ዘግቧል።

ከጉራፈርዳው ጥቃት ጋር በተያያዘ መልዕክት ያስቀመጡ የጉራፈርዳ ቢፍቱ ቲክቫህ አባላት ከሰሞኑ በገለቲ ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን ፣ በርካቶችም መፈናቀላቸውን ገልፀዋል።

ወረዳው አሁንም መረጋጋት አይታይበትም ያሉ ሲሆን ነዋሪው በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ መሆኑና መንግስት ታጥቀው ንፁሃንን በሚገድሉት ላይ እርምጃ እንዲወስድ ሲሉ ጠይቀዋል።

የጉራፈርዳ ወረዳ አስተዳዳሪ በእጅግ ስልካቸው ለማግኘት የነዋሪዎችን ደህንነት ፣ ስለደረሰውን ጉዳት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ስልክ ብንመታላቸውም ስልካቸውን አልተነሳም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከጉራፈርዳ ወረዳ ጋር በተያያዘ ...

ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ የተገኘው ከደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ወሰኑ ወዳጆ ይፋዊ የማህበራዊ ገፅ ሲሆን የጉራፈርዳ ወረዳ አስተዳደር በወረዳው ያለው ችግር ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት ይገልፃል።

ወረዳው ከጥቅምት ወር ከአንድ ቀበሌ የጀመረው የፀጥታ ችግር ከቀን ወደ ቀን ወደሌላ ቀበሌ እያካለለ የ "ሽፍታ" ቁጥርም እየጨመረ በመምጣቱ ወረዳው ከአቅም በላይ መሆኑን ከዚህ በፊት 24/6/2013 ዓ/ም በደብዳቤ የፀጥታ ኃይል እንዲመደብለት ፣ በቂ ትጥቅ እንዲላክለት ይህም በወቅቱ ካልቀረበ ያለው ችግር ከወረዳው ከአቅም በላይ መሆኑን አሳውቆ እንደነበር አስታውሷል።

ከዞኑ የተጠየቀበት ቀን ጀምሮም ከክልል ጋር በመነጋገር የተጠየቀው ጥያቄ ባለመሟላቱ አሁንም ከ3 ቀበሌ ወደ 6 ቀበሌ የፀጥታ ችግሩ መስፋፋቱን አመልክቷል።

በአጭር ጊዜ ወረዳው ፦
- መከላከያ ሰራዊት እንዲመደብለት
- ለሚሊሻ ወባላት ትጥቅ እንዲመቻችለት
- ከፖሊስ አባላት ጀምሮ የጥይት ፍሬ የሌላቸው መሆኑና
- በወረዳው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማውጣቱ ምንም የጥሬ ገንዘብ ስለሌለው ምላሽ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተጠየቁት ጥያቄዎች ምላሽ ካላገኙ / ካልተመቻቸ በአሁን ሰዓት የፀጥታው ሁኔታ ወረዳው መቆጣጠር የማይችልበት እና ከአቅም በላይ መሆኑን እንዲታወቅ ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ ግብር በደብረ ማርቆስ እና ጎንደር መካሄድ ጀምሯል!

የአማራ ብልጽግና ፖርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ እና ጎንደር ዞኖች መካሄድ ጀምሯል።

በደብረ ማርቆስ በተጀመረው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ ሀላፊ አቶ አብርሃም አልኸኝና ሌሎችም የክልሉና የዞኑ የስራ ሀላፊወች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር በድጋፍ ሰልፉ ላይ እንደገለፁት ብልፅግና የኢትዮጽያን እንድነት የሚፈታተኑ ሀይሎች በፅናት በመታገል ያሸንፋቸዋል ብለዋል።

ፅንፈኛ ብሄርተኝነት የወለዳቸው ችግሮችን ለመቅረፍም ብልፅግና ፓርቲ የአማራ ህዝብ እሴቶች የሆኑትን ወንድማማችነትንና አብሮነትን በማቀንቀን የተደገሱልንን ፈተናዎች ለመሻገር በትጋት እንደሚሰራም ገልፀዋል።

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ በተፈተኑ አመራሮች የተደራጀ በስሜት ሳይሆን በስሌት የሚራመድ ፓርቲ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ህዝቡ በምርጫው ድምፁን ለብልፅግና እንዲሰጥም ጠይቀዋል።

ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅም ሁሉም አካል ለሰላም ዘብ እንዲቆምም ጥሪ አቅርበዋል።

በተያያዘ ዜና የአማራ ብልጽግና ፓርቲ በጎንደር የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሀግብር እያካሄደ ነው።

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ በአራቱ የጎንደር ዞኖች ማለትም በማእከላዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ጎንደር ዞኖችን ጨምሮ የጎንደር ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉበት የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃግብር በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመርኃግብሩ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የምርጫ ቅስቀሳ መርኃግብሩ አካል የሆነው የፓርቲው የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት "አምፖል" የያዘ ቢልቦርድ በይፋ ተመርቋል።

#via Ebc

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news