G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
Forwarded from 💜
ክትባቱን በይፋ እቃወማለሁ!!! 💉

🦠እራሴን ለሰይጣንና ለሰራዊቱ አሳልፌ አልሰጥም ማንም በእኔ ህይወት ላይ መብት የለውም ከአምላኬ በቀር፤ዘመናዊ ባርነትን በፍፁም አልቀበልም❗️ እራሴን ና ሀገሬን ከሰይጣን ወጥመድ እጠብቃለሁ በክትባት ሰበብ የሰይጣን ባልደረባ መሆንን አልሻም ፤ሀይማኖቴን እጠብቃለሁ አምላኬ ደግሞ እኔን ይጠብቀኛል።

➡️እንደ አባቶቼ ያለክትባት መኖር እችላለው እንደ አባቶቼ ጠንካራ መሆን እሻለሁ አባቶቼ ያለክትባት ብዙ ዕድሜን ኖረዋል ግን እኔ ተከትቤ ግፋ ቢል እድሜዬ ከ50 አይበልጥም ስለዚህ ለሰውነቴ ክትባት ሳይሆን እምነት ነው የሚያስፈልጋት!!
📌📌📌📌📌📌📌
ኦርቶዶክስ፣ሙስሊም፣ካቶሊክ፣ፕሮቴስታንት ሳትል ክትባቱን ተቃወምና ሰብዓዊ መብትህን አስከብር ❗️ባንተ ህይወት ማንም እንዳይገባበት ራስህን አስከብር፤ካለበለዚያ የሰው ልጅ ጠላት ለሆነው ሰይጣን እራስህን አሳልፈህ በመስጠትህ ኋላ ላይ እንዳትቆጭ!!

አልሰማሁም አላወኩም ማለት አትችልም ምክንያቱም እኔ አሁን ነግሬሀለው የአንተ ስራ እራስህን ማዳን ነው!!! አስተውል መጥፊያህ ወደ በርህ እየቀረበ ነው!!!
ክትባቱን በይፋ እቃወማለሁ ‼️
🦠💉

እራስህን ብቻ ሳይሆን ወገኖችህንም ለማንቃት ይህን ፁሁፍ ለምታውቀው ሰው ሁሉ #ሼርርርርርርርርርር አድርግ
@Thehacher
Forwarded from Finance Today
ሰበር ዕለታዊ መረጃዎች‼️ግጭቱ ዛሬም ሙሉ ለሙሉ አለመቆሙ ተሰማ/አማራ ክልል መግለጫ አወጣ/አስፈሪው መከላከያ /የጆባይደን መልክተኛው ጉዳይ/ጠ/ር አብይ መልክት አስተላለፋ

linkun በመጫን ዝርዝር ዜናዎቹን ያድምጡ

https://youtu.be/cRu4k2xVPns
ችሎት!

ስብሃት ነጋ፣ ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ አምባሳደር አባይ ወልዱን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ!

ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ያቀረበው የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው የቀረቡት፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ችሎት የቀረቡት የዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክርን ለመስማት በተሰጠ ተለዋጭ ቀጠሮ ነው፡፡

ዐቃቤ ህግ ባሳለፍነው ሳምንት 50 ምስክሮች ማዘጋጀቱን መግለጹን ይታወሳል፡፡

Via:- FBC

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ሰዉ ከሆነ ፍጡር የማይጠበቅ በጣም አሰነዋሪ፣አሳዛኝ እና በጣም ዘግናኝ የሆነ ተግባር ነው" -ዋና እንሰፔክተር ዉባለም እርገጤ

በደብረ ማርቆስ ከተማ በካርቶን ተጠቅልላ የተገኘች ጨቅላ ህፃን አብማ ቤተክርሰቲያን ተቀረች።

ዛሬ ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ሲሆን በፎቶው በምታዪት ካርቶን ተጠቅልላ አብማ ቤተክርሰቲያን ልዩ ቦታዉ የነጋዴወች ሰንበቴ መብያ አዳርሸ ጎን በካርቶን ተጠቅልላ ህይወቷ አልፎ የተገኘች ጨቅላህፃን ህብረተሰቡ በሰጠዉ ጥቆማ ከተጣለበችበት ቦታ ተነሰታ በአካባቢዉ ነዋሪዎች ትብብር አብማ ቤተክርሰቲያን እንድትቀበር ተደርጓል።

የደ/ማርቆሰ ከተማ አሰተዳደር 1ኛ ፓሊሰ ጣቢያ የሴቶችና ህፃናት ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዋና እንሰፔክተር ዉባለም እርገጤ ፥ "የተከሰተዉ ጉዳይ በጣም እንዳሰዘናቸዉና ሠዉ ከሆነ ፍጡር የማይጠበቅ በጣም አሰነዋሪ፣አሳዛኝና በጣም ዘግናኝ የሆነ ተግባር ነው ብለዋል።

ኃላፊዋ አያይዘው አሁን አሁን እንዲህ ያለተግባር በከተማው እየተለመደ የመጣ ስለሆነ፦

- መጀመሪያ ላይ ሴቶች ላለማርገዝ ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረግ ቢችሉ

- ጥንቃቄ ማድረግ ሳይቻል ቀርቶ ችግሩ ከተከሰተ በአግባቡ በመዉለድ የሚያድግበትን ሁኔታ ማመቻቸት ቢቻል

- ለማሳደግ የአቅም ችግር ካለ ደግሞ ወልዶ ከመጣል ይልቅ ከመለሚከተዉ አካል ጋር በመነጋገር ድጋፍና እገዛ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ቢቻል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተጨማሪ ህብረተሰቡ ቤት አከራይቶ ሲያኖር ነፍሰ ጡር የሆኑና የመዉለጃ ጊዜያቸዉ የደረሱ ተከራዮችን ሲኖሩ መከታተል ቢችልና የተለየ ነገር ካጋጠመዉና መዉለዳቸዉን የሚያመላክት ነገር ሲኖርና ህፃን ከሌለ ለፓሊሰ ጥቆማ በመሰጠት እንዲተባባረ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃው ከደብረ ማርቆስ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ነው ያገኘነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጅማ፡ እሳት አደጋ ንብረት አወደመ!

በጅማ ከተማ ከረቢያን ሆቴል ውስጥ የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

በዛሬው እለት ቀኑ 6፡00 አከባቢ ከሆቴሉ ኩሽና የተነሳውን እሳት ለማጥፋት አንድ የእሳት አደጋ መኪና የተሰማራ ሲሆን፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ አደጋውን መቆጣጠር ተችሏል፡፡

የአዲስ ዘይቤ ሪፖርተር ከጅማ እንደዘገበው በእሳት አደጋው የደረሰው የንብረት ውድመት በመጣራት ላይ ይገኛል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Deleted Account
በዛሬው የከሚሴ ጦርነት

👉 በርካታ ልዩ ሃይሎች መንደር ውስጥ በሸመቁ ታጣቂ ኦነጎች ተገድለዋል።

👉 ሆስፒታል ምግብና ውሃ ሊያደርሱ የሄዱና በጥሩ ስነምግባራቸው የሚታወቁ 5 የከተማው ኦሮሞ ወጣቶች ሆስፒታሉን ከብበው በነበሩ የኦነግ ታጣቂዎች ለልዩ ሃይል ስንቅ ልታቀብሉ ነው በሚል ጥርጣሬ በጥይት የተመቱ ሲሆን ሁለቱ ወዲያው ሲሞቱ ሁለቱ ቆስለዋል፥ አንዱ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል።

👉 ኑሩ አሊ የተባለ የባህልና ቱሪዝም ኃላፊ ከከተማው ወጣ ባለ ቦታ ለልዩ ሃይሉ መረጃ ልትሰበስብ ነው በሚል በኦነግ ታጣቂዎች ተገድሏል።

👉 አንድ የፕሮቴስታንት ቸርች ተቃጥሏል።
አማራ ክልል: በሰሜን ሸዋ ዞን የተከሰተው የፀጥታ ችግር!

በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር መከሰቱ ይታወቃል። የተደራጁ ታጣቂዎች ከሸዋሮቢት ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ዙጢ ከተማ በቅርቡ በፈጸሙት ጥቃት ሀብትና ንብረት እንዳወደሙ ተነግሯል።

የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች የጸጥታ ስጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ነገር ግን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የኅብረተሰብ ክፍሎች ሸዋሮቢት ከተማ በመገኘት ነዋሪዎችን በማረጋጋት ላይ እንደሆኑ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ሰርጎ ገቦች እና ተመሳስለው የሚኖሩ አካላት አሁንም የኅብረተሰቡ ስጋት መሆናቸውን አንስተዋል።

በሸዋሮቢት ከተማ ዛሬ ሱቆች፣ ሆቴሎች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መዘጋታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል ሲል የዘገበው አብመድ የአማራ ክልል መንግሥትም አካባቢውን በደንብ ማደራጀትና ማኅበረሰቡ እራሱን እንዲከላከል ማድረግ እንዳለበት ጠቅሰዋል ብሏል።

ጥቃት በሚያደርሱ አካላት ላይ የማያዳግም ርምጃ በመውሰድም የሕዝቡን ሠላም እንዲጠብቅ ጠይቀዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እሸቱ ጌታቸው የጸጥታ ችግር ተከስቶባቸው የነበሩ አካባቢዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይል ቁጥጥር ሥር ናቸው ያሉ ሲሆን የመንግሥት የጸጥታ አካላትም ኅብረተሰቡን ለማረጋጋት ቅድሚያ ሰጥተው እየሠሩ መሆኑን አመላክተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መነጋገራቸው ተሰማ!

በአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የተላኩት ሴናተር ክሪስ ኩንስ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መነጋገራቸው ተሰምቷል።

አቶ ደመቀ መኮንን ለሴናተር ክሪስ ኩንስ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት እየተካሄደ የሚገኘው ድርድር ላይ ያላትን ቁርጠኝነት እንደነገሯቸው ተገልጿል።

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ 2023 ላይ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው የሕዳሴ ግድብ ከድህነት ለመውጣትና የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብላ ታምናለች። ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌትም በቅርቡ እንደሚከናወን አስታውቃለች።

ግብፅ እና ሱዳን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ምንም አይነት ስምምነት ላይ ሳይደረስ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት አከናውናለሁ ማለቷን ይቃወማሉ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (BÊŽÂ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ዘንድሮ ተላልፎ በቅርቡ በተሰጠው የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አፈጻጸም ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንዳስታወቁት የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አለም አቀፍ ወረርሽኝ በሆነው የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ወደ ዘንድሮ ተዘዋውሮ በቅርቡ መሰጠቱን አስታውሰው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነበረው የፈተና አሰጣጥ ሂደትም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣታቸው ፈተናው ያለምንም ችግር እንደተሰጠ በመግለጽ በዚህ ሂደት የተገኘው ተሞክሮም ግንቦት ወር ላይ እንደሚሰጥ በሚጠበቀው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ጥሩ ልምድ የተገኘበት እንደሆነም አስረድተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዲናኦል ጫላ የፈትና አሰጣጥ ሂደቱን አስመልክቶ ባቀረቡት ሪፖርት በአዲስ አበባ ፈተናው በ41 የፈተና ጣቢያዎች ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2/2013 ዓ.ም ያለምንም እንከን መሰጠቱን ገልጸው በዚህ ሂደትም የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ሁሉም በአፈጻጸሙ የተሳተፉ አካላት ላቅ ያለ ምስጋና እንደሚገባቸው አስታውቀዋል።

በመርሀ ግብሩ በተመሳሳይ ሁኔታ በኮቪድ 19 ምክንያት ወደ ዘንድሮ ተላልፎ የተሰጠው የ2012 ዓ.ም የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የውጤት ትንተና ቀርቦ ተሳታፊዎች ውይይት አካሂደውበታል።

@Free_Education_Ethiopia

Stay safe
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (BÊŽÂ)
“የአማራ ክልል ልዩ ኃይል የኢትዮጵያ ሠራዊት ሆኗል ማለት ይቻላል” - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

“የኤርትራ ሕዝብ እና መንግስት ከኢትዮጵያ ጥቃት ተፈፅሞባቸውን የሄዱ ወታደሮችን የተንከባከበበትን መንገድ ኢትዮጵያ መቼም አትረሳም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ “የኤርትራ ወታደር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ የገባበት ምክንያት የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ ስለሆነባቸው እንደሆነ ነግረውናል” ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ኤርትራን በሚያዋስነው ድንበር ላይ የኢትዮጵያ ሰራዊት ባለመኖሩ ምክንያት የኤርትራ ሰራዊት ድንበር አካባቢ ተሰማርቷል ሲሉ የሆነውን አስረድተዋል።

“ማንን የት ማስፈር እንዳለብን ለኛ መተው ያስፈልጋል” ሲሉ ከአሜሪካ በኩል የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ከትግራይ መውጣት አለበት በሚል ወጥቶ የነበረውን መግለጫ የተቃወሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የአሜሪካ ወታደር የት መስፈር እንዳለበት ኢትዮጵያ ሳትሆን ባለቤቷ አሜሪካ ነው የምትወስነው” ብለዋል።

“የአማራ ክልል ልዩ ኃይል የኢትዮጵያ ሠራዊት ሆኗል ማለት ይቻላል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ “ከፈለግን ሱማሌም ቢሆን ማሰማራት እንችላለን” ሲሉ ገልፀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
“ተላላኪ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ አይፈጠርም” - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ!

“ኢትዮጵያ ማለት ታጥቆ ሲፎክር የነበረን ኃይልን በሶስት ሳምንት ውስጥ ብቻ መደምሰስ የቻለ መንግስት ያለባት አገር ናት” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ “ከየትኛውም መንግስት ጋር ጦርነትና አተካራ አልፈልግም፤ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከመጣ ግን አንገቴ ይቀላል እንጂ ለድርድር አልቀርብም” ሲሉ ለሕዝብ ተወካዮች ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ ተላላኪ መንግስት መፍጠር አይቻልም” ሲሉ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ይሀንን ለማድረግ የሚሯሯጡ አይሳካላቸውም” ሲሉ አስታውቀዋል።

“ኢትዮጵያ ትበተናለች የሚል ስጋት የለኝም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሽምቅ ውጊያ ግዜው አልፎበታል፤ አሁን ያለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ይህንን አይፈቅድም” ሲሉ ተናግረዋል።

“የሱዳን ሕዝብ ወንድም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሱዳንም ሆነች ኢትዮጵያ አሁን ላይ ባለባቸው ችግር ምክንያት ጦርነት ለማድረግ ዝግጁ ስላልሆኑ ውጊያ አያስፈልግም፤ በንግግር እንፍታው ሲሉ በድጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል።”

“ኢትዮጵያ ግብፅን የመጉዳት ፍፁም ዓላማ የላትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዳሴ ግድብ በተመለከተ ግን ቃል በተገባው መሰረት ይፈፀማል” ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
“የህወሓትን ምርጫ ሲያጅብ የነበረ ፖለቲከኛ ሁሉ…” - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ!

“ከምርጫ እንዳይወጡ የኦፌኮ አመራሮችን አነጋግሬ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን አሸናፊ የሚያደርግ ምርጫ እናደርጋለን” ሲሉ ተናግረዋል። “ብናሸንፍም በቅንነት እናገለግላለን፤ ከተሸነፍንም ያለማወላወል እናስረክባለን” ሲሉም ተደምጠዋል።

“አሁን ላይ ወደ ምርጫው ለመግባት ጥያቄ ያቀረቡትን አካላትን ጥያቄ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ይቀበለዋል ብዬ በፅኑ አምናለሁ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ “ዲሞክራሲን በሚፈለገው መጠን ለማስፋት ግን ግዜ ያስፈልጋል” ሲሉ ተናግረዋል።

“የህወሓትን ምርጫ ሲያጅብ የነበረ ፖለቲከኛ ሁሉ አሁን ላይ በምርጫው አንወዳደርም ማለታቸው የዘንድሮውን ምርጫ ትክክል አያደርገውም ማለት አይደለም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እፍርታም ፖለቲከኞች ቶሎ ብለው ወደ ምርጫው ቢገቡ መልካም ነው” በማለት ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Adam Getenet
ተወርዋሪው አማራ ልዩ ሀይል
ተሸንፈንም አናውቅምም ሚኒልክ ብርጌድ ዛሬ በፓርላማ መሸነፋቸው ያቃጠላቸው የኦነግ ደጋፊዎች በግልፅ ንዴታቸውን በስሜታዊነት ገልፀዋል የደረሳችውብን እናተ እንጂ እኛ አደለንም ወያኔ የሰጣቹ ወረዳ ነው በአማራ ክልል የኦሮሞ ዞን ሚባል መሬት የለም በገዛ መሬታችን ህዝባችን አይገደልም
ጀግናው አማራ ፋኖ ገበሬው ልዩ ሀይል የማያዳግም እርምጃውን አጠናክሮ እየቀጠለ ነው አጣዬ የተያዘው ቀበሌ ነፃ ወቷል
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ግንቦት 30 ይሰጣል‼️

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ በወረቀት ይሰጥ የነበረበትን ስርዐት በዚህ አመት ሙሉ በሙሉ አስወግዶ ፈተናውን ግንቦት ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ገልፀዋል ማምሻውን በነበራቸው መግለጫ አስታውቀዋል።

#በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮቪድ-19 ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው የአምናው ፈተና በወረቀት መሰጠቱንም አስታውሰው በዚህ አመት ለሚፈተኑት ወደ 700ሺ የሚጠጉ ተፈታኞች ታብሌቶች ገብተው ዝግጁ መሆናቸውንና የማጓጓዝ ስራ በመጀመር ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

ከሚያዚያ 3 እስከ 15 ቀን 2013 ዓ/ም ታብሌቶቹ እና የፈታኝ አስተማሪዎች ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱ ገልጸው ለተማሪዎች የ አንድ ወር የመለማመጃ ጊዜ እንደሚሰጣቸውም አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት የ2013 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ይሰጣል ተብሏል።


#share
@Timhrtministers
@Timhrtministers
#ሰበር_ዜና‼️

ኢትዮ-ኤርትራ፡

ኤርትራ ሠራዊቷን ከኢትዮጵያ ግዛት ለማስወጣት ተስማማች!

ኤርትራ በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ያስገባቻቸውን ወታደሮቿን ለማስወጣት ከስምምነት መደረሱን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ፣ አርብ ጠዋት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሐሙስ ዕለት አሥመራ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ባደረጉት ውይይት ኤርትራ ሠራዊቷን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማማታለች።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የድንበር አካባቢዎቹን ተረክቦ ጥበቃውን ወዲያውኑ እንደሚጀምር ሁለቱ መሪዎች ከስምምነት ደርሰዋል።

ዝርዝር መረጃውን እና የጠቅላይ ሚንስትሩ ጉብኝት በተመለከተ በዩትዩብ ገፃችን ይዘን እንመለሳለን

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
#ትኩረት!!

የጭላሎ ጋለማ ደን እሳት እየነደደ ነው።

በአርሲ ብሔራዊ ተራሮች ፓርክ በጭላሎ ጋለማ ደን ላይ የእሳት አደጋ በድጋሜ ተከስቷል።

በጭላሎ ተራራ ላይ የተከሰተዉን እሳት ለመቆጣጥር ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም እሳቱ ከአቅም በላይ መሆኑን የአረሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓረክ አስታውቋል፡፡

ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በአካባቢዉ የተገኙት የህብረተሰብ ክፍሎች የተከሰተዉን እሳት ለማጥፋት ያደረጉት ጥረት ከአቅማችዉ በላይ በመሆኑን ተናረዋል፡፡

ፓርኩ ከሚያካልላቸው ዘጠን ወረዳዎች ውስጥ በዘጠኙ (9) ወረዳዎች ዉስጥ የእሳት አደጋዉ የተከሰተ መሆኑን የአርሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አሳውቋል።

እሳቱ በፍጥነት እየተጓዘ እና አብዛኛዎቹን የተራራዉን ክፍል እያካለለ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ፓርኩ እሳቱ ከህብረተሰቡ አቅም በላይ በመሆኑ ለክልሉ አሳውቋል ፤ አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚፈልግ ጥሪ ማቅረቡን ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (π)
የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ በቀጣይ ሳምንት እንደሚጀመር የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የኦንላይ ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዝያ 15/2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

ምዝገባው የዞንና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች በሚያወጡት ፕሮግራም መሰረት እንደሚፈፀም ከቢሮው የፈተና ክፍል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአማራ ክልል በ2013 የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በግል ከ165 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አስፈታኝ ትምህርት ቤቶችም 370 ሲሆኑ የፈተና ጣቢያዎች ደግሞ 357 ናቸው፡፡

የ2013 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦንላይን እንደሚሰጥ ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የአክሱም ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ከጥቃት ተረፉ!

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አዲግራት አካባቢ የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ ድንገቴ ጥቃቱ በተደረገበት በቅርብ ርቀት ላይ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩት ወደ አክሱም ዩንቨርሲቲ የሚጓዙ ተማሪዎች ከጥቃቱ ተርፈዋል፡፡

የአዲስ ዘይቤ ሪፖርተር በአካባቢው ከነበሩ የዓይን እማኞች እንደተረዳው፡- ከአዲግራት አቅጣጫ በመምጣት ላይ በነበሩ የኤርትራ ወታደሮች ላይ የሕወሓት ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተዋል፡፡ በታጣቂዎቹ ጥቃት ወታደሮቹን ጨምሮ በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከል በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወደ ዓድዋ በማምራት ላይ የነበሩ ሲቪል ተጓዦችም ይገኙበታል፡፡ 8 የአካባቢው ገበሬዎችን ጨምሮ የ17 ሰዎች ህይወትም አልፏል፡፡ እንደ ዓይን እማኞች ምስክርነት በጥቃቱ 25 የሚጠጉ ወታደሮች፣ ገበሬዎችና ሲቪሎች ሞተዋል፡፡

ቤቶችም ተቃጥለዋል፡፡ በተሽከርካሪዎቹ ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ታፍነው ተወስደዋል፡፡ ወደ አክሱም ዩንቨርሲቲ በመጓዝ ላይ የነበሩት ተማሪዎችም ተኩስና ግርግሩን በመሸሽ ወደመጡበት መመለሳቸውን ሰምተናል፡፡

ምንጭ : አዲስዘይቤ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news