G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
📌 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የታብሌት አጠቃቀም የትኩረት ነጥቦች፡-

✅1ኛ= ኦንላይን (Online) ፈተና ለመውሰድ በየክፍሉ ማገኘት የሚገቡ የፈተና መሳሪያዎች በክፍል ተማሪዎች ብዛት ልክ ታብሌት ኮምፒዮተር , በየክፍሉ አንድ ላብቶኘ , ሶኬት, ቻርጀር, ዲሽ, ጀኔሬተር(መብረት) ወዘተ ናቸው፡፡

✅2ኛ= ተፈታኝ ተማሪዎች ለ2 ሳምንት ከ2009 ዓ,ም እስከ 2011 ዓ,ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሀገር አቀፍ የተፈተኑትን ፈተና ጥያቄዎች በየት/ቤታቸው ተገኝተው ይለማመደሉ፡፡ ግን ታብሌት ከት/ቤት ውጭ መውሰድ አይቻልም፡፡

✅3ኛ= ታብሌቱ በተለያዩ አሻረዎች ማለትም በ5 ጣቶች, በፊት ገፅ በምራቅ
በጆሮና በአይን ከተማሪው ጋር ትውውቅ ያደረገ ስለሆነ ተማሪው ወደ ጎን ሲዞርና ሌላ ሠው ሲደረብ ታብሌቱ ይዘጋል፡፡ ስለዚህ ጥያቄ መስራት ስለማይቻል
በፍፁም ኩረጃን አያስተነግድም፡፡

✅4ኛ= ታብሌቱ የሚሠራው በዋይፋይ (Wi-Fi) በየክፍሉ በተዘረገው ሆኖ ቀጥታ አገር አቀፍ ማሰረጫ ጋር መረጃ ያስተላልፋል፡፡

✅5ኛ= ፈተናው አራትና በላይ ኮድ ምርጫውን ጭምር ማድረግ ይቻለል፡፡

✅6ኛ= ዲሽ ሲተከል በነፃ ቦታ ወይም ዛፍና ተራራ የማይገርድና ሲግናሎች በቀላሉ የሚገቡበት መሆን አለበት፡፡ በተተከለው ዲሽ ብቻ ታብሌቱ ስለሚሠራ ችግር እንዳይደርስ በአጥር አጥሮ በዘበኛ ማስጠበቅ አለበት፡፡ ዲሹ በቀጣይ ዲጂታል ቤተመፃህፍት አገልግሎት ስለሚሰጥና በቀጣይ ተማሪ ምዝገባ ከ9-12ኛ ክፍል ስለሚካሄድ የተሻሉ ተማሪዎችን ለመምረጥ ስለሚሰራ በጥንቃቄ መያዝ አለበት፡፡

✅7ኛ= ታብሌቱን ለተማሪዎች የሚያሰለጠኑ ባለሙያዎች በየት/ቤቱ ይመደባሉ፡፡

✅8ኛ= ፈተና ለሚያስፈፅሙ መ/ራንና ለሌሎች አካለት ስለቴክኖሎጂ አጠቃቀም አጫጭር ስልጠናዎች ይሠጣሉ፡፡

✅9ኛ= ፈተናው በኦን ላይን (online) መሰጠቱ ወጭ ከመቀነስ አኳያ በወረቀት
ግዥ, በቀለም ግዥ, ፈተና በማጓጓዝ, በእርማት ወዘተ ከሚያወጠው ወጪ በአምስት እጥፍ ያነሰ ነው፡፡

✅10ኛ= የፈተና ውጤቱን ለተማሪዎች ሞራል ካልሆነ ፈተና እንደጨረሱ ማለፊያውን ውጤት ማወቅ ይቻላል፡፡ ግን በቀናት ልዩነት ውጤቱን እንዲያውቁ
ይደረጋል፡፡

#SHARE
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
G-Tutorialclass pinned «📌 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የታብሌት አጠቃቀም የትኩረት ነጥቦች፡- ✅1ኛ= ኦንላይን (Online) ፈተና ለመውሰድ በየክፍሉ ማገኘት የሚገቡ የፈተና መሳሪያዎች በክፍል ተማሪዎች ብዛት ልክ ታብሌት ኮምፒዮተር , በየክፍሉ አንድ ላብቶኘ , ሶኬት, ቻርጀር, ዲሽ, ጀኔሬተር(መብረት) ወዘተ ናቸው፡፡ ✅2ኛ= ተፈታኝ ተማሪዎች ለ2 ሳምንት ከ2009 ዓ,ም እስከ 2011 ዓ,ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች…»
ከነገ ጥር 30 ቀን 2013 እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ድረስ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ ተደርጓል‼️

ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የዋጋ ክለሳው የተደረገው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ መሆኑን አሳውቋል።

በአዲሱ የዋጋ ክለሳ መሰረት

ቤንዚኒን በሊትር 25 ብር ከ82 ሳንቲም

ኢታኖል ድብልቁ ቤንዚን በሊትር 25 ብር ከ32 ሳንቲም

ነጭ ናፍጣ በሊትር 23 ብር ከ04 ሳንቲም

ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 20 ብር ከ27 ሳንቲም

ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 19 ብር ከ77 ሳንቲም

የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 35 ብር ከ12 ሳንቲም ሆናል።

ከነገ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ማደያዎች ሁሉ ይህ ክለሳ ተግባራዊ እንደሚደረግ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አሳውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ኢትዮጵያን ትንንሽ አገር እናደርጋታለን ቢሉም ትልልቅ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት እናሳያቸዋለን‼️
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ኢትዮጵያን ትንንሽ አገር እናደርጋታለን ቢሉም ትልልቅ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት እናሳያቸዋለን በማለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡ የቡሬ ከተማ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና የአቶ በላይነህ ክንዴ ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች በተገኙበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገኝተው ሲመርቁ ነው ይህን ያሉት፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ የተመረቁት ፋብሪካዎች ሰሊጥ ልኮ ዘይት ማስገባትን፣ ፍራፍሬ ልኮ ጭማቂ ማምጣትን የሚያስቀሩ የኢኮኖሚውን መዋቅራዊ ሽግግር የሚያሳልጡ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ ባለሀብቶችም የሥራ እድሎችን በመፍጠር እና ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ልብ እና ገንዘብን ያጣመሩ ባለጸጋዎች ሊሆኑ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

“በአሁኑ ሰዓት አገሪቱ እንድትከፋፈል እና ቀውስ ውስጥ እንድትገባ የሚፈልጉ ኃይሎች ቢኖሩም፣ እኛ ግን ትልልቅ ኢንዱስትሪዎችን እየገነባን እናሳያቸዋለን” ሲሉም ገልጸዋል፡፡ኢንዱስትሪዎችን ማምረቻ ብቻ ሳይሆን የመዝናኛ ማእከል እንዲሆኑ ማልማት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) ትግራይ ዉስጥ በተደረገዉ ጦርነት ለተጎዳዉ ሕዝብ ተጨማሪ ርዳታ ለመሰጠት ተስማሙ‼️

የዓለም ምግብ ድርጅት የበላይ ዴቪድ ቤስሌይ የትግራይ ርዕሠ-ከተማ መቀሌን ከጎበኙ በኋላ ትናንት እንዳሉት ድርጅታቸዉ ሠብአዊ ርዳታ ለማድረስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር «በተጨባጭ ርምጃዎች» ላይ ተስማምቷል።አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የቤስሌይን መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበዉ ዓለም አቀፉ ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት የሌለባቸዉ አካባቢዎችን ጨምሮ ለችግር ለተጋለጠዉ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ርዳታ እንዲያደርስ የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበዉን ጥያቄ ለማሟላት ተስማምቷል።ቤስሌይ ትናንት በቲዊተር ባሰራጩት መግለጫ ትግራይ ዉስጥ 3 ሚሊዮን ያሕል ሕዝብ «የኛን ርዳታ እየጠበቀ ነዉ» ብለዋል።«የምናጠፋዉ ጊዜ የለም።» አከሉ ኃላፊዉ።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
Adamtu share adrgu
የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀት ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር በኦንላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ዛሬ አስታውቋል።

በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮቪድ-19 ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ነው በወረቀት ለመስጠት የታሰበው ብሏል ሚኒስቴሩ።

ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ፈተናው እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል ተባለ።
የ12ኛ ክፍል ፈተና የካቲት 29 ይሰጣል።

የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2013 ዓ.ም የዲጂታል መታወቂያ ይሰራጫልም ብሏል።

የፈተናው ገለጻ የካቲት 26 ቀን ተካሂዶ ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በቀጥታ (ኦንላይን) ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
G-Tutorialclass pinned «የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀት ይሰጣል። ትምህርት ሚኒስቴር በኦንላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ዛሬ አስታውቋል። በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮቪድ-19 ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ነው በወረቀት ለመስጠት የታሰበው ብሏል ሚኒስቴሩ። ከየካቲት 21 እስከ…»
ባለቤቱንና ልጁን የገደለው ግለሰብ የሞት ውሳኔ ተላለፈበት።

በስልጤ ዞን በሳንኩራ ወረዳ "አለም ገበያ ከተማ" ልዩ ስሙ ጤና ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ/ም ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት የገዛ ባለቤቱንና የ4 ዓመት ልጁን በቤት ውስጥ እያሉ ቤት ላይ ቤንዝል አርከርክፎ ያቃጠለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ እንደተላለፈበት የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

በስልጤ ዞን በሳንኩራ ወረዳ አለም ገበያ ከተማ ልዩ ስሙ ጤና ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ/ም ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት የገዛ ባለቤቱንና የ4 ዓመት ልጁን በቤት ውስጥ እያሉ ቤት ላይ ቤንዝል አርከርክፎ ያቃጠለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ እንደተላለፈበት የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የስልጤ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋ/ኢ/ር ካሚል ሀምድ ስለወንጀል ድርጊቱ እንዳስታወቀው ተከሳሽ ይልማ ዱባለ የተባለው ግለሰብ ሟች ሀዲሪያ ሲራጅ የተባለችውን ባለቤቱን 12 ዓመት አረብ አገር ለፍታ ያመጣችውን ሀብት በስሜ አዙሪ በማለት የተጀመረው ጭቅጭቅ ውሎ እያደረ ሌላ አጀንዳ እያስከተለ በባልና ሚስት ያለውን ግንኙነት ይበልጥ እየከረረ ሲሄድ በስሜ ማዞር ያልፈለግሽው ንብረትሽን በጎን ሌላ ፍቅረኛ ስላለሽ ነው በማለት በመሀላቸው ያለውን ግንኙነት ወደ አደገኛ ደረጃ እንዲሸገር አድርገል፡፡ 
ተከሳሽ የገዛ ባለቤቱንና የልጁን የሚገልበትን ምቹ ሁኔታ አመቻችቶ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ/ም ቤንዝል ገዝቶ ወደ ቤት ሲመጣ ሟች ቤንዝሉን ለምን ገዛህው ብላ ስትጠይቀው ገዝቸው ሳይሆን ሞቴር ያለው ጓደኛ አስቀምጥልኝ ብሎኝ ነው ይላታል።
ቀኑ መሽቶ የ5 ወር ነፍሰ ጡር የሆነችው ባለቤቱ ሀገር አማን ነው ብላ የ4 ዓመት ህፃኑዋን በጉያዋ ታቅፋ በተናችበት በውድቅት ሌሊት ባሏ በቡና መውቀጫ ዘነዘና የተለያየ የሰውነት ክፍሏን ደጋግሞ በመምታት ህይወቷ እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ ቤቱን ዘግቶ በህይወት የነበረችው የ4 ዓመት ህፃን በቤቱ እያለች በቤንዝል አርከፍክፎ ቤቱን እንዲቃጠል አድርጎ የእናትና የልጅ ህይወት እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ ወደ ኦሮሚያ ክልል አጋሮ ከተማ ለጥቂት ወራት ተሰውሮ መኖር ይጀምራል፡፡  
የስልጤ ዞን ፖሊስ ተከሳሽ ይልማ ዱባለን ከተደበቀበት ኦሮሚያ ክልል አጋሮ áŠ¨á‰°áˆ› አድኖ በቁጥጥር ሾር አውሎ ምርመራውን ከዓቃቤ ህግ ጋር በመሆን ለስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀርባል የክስ መዘዝገቡ የቀረበለት የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን በጥንቃቄ መመልከት ይጀምራል፡፡ 
የቀረበለት የክስ መዝገብ የተመለከተው ፍ/ቤት ግራና ቀኙን ተመልክቶ ተከሳሽን እንዲከላከል ቢጠይቀውም ተከሳሽ መከላከል ባለመቻሉ ለተፈፀመው ወንጀል ተከሳሽን ይመጥናል ሌሎችንም ያስጠነቅቃል በማለት የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል መረጃውን ያገኘነው ከስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው፡፡
(ፌዴራል ፖሊስ)
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ‘የመደመር መንገድ’ መፅሃፍ ገበያ ላይ ዋለ‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ‘የመደመር መንገድ’ የተሰኘው መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ። መጽሐፉ፥ የለውጡን ፈለግ እና መደመር ያለፈበትን መንገድ እንደሚዳስስ ተነግሯል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
Forwarded from Deleted Account
ሰበር ዜና......እባክህ/ክሽ ካነበቡት በሁዋላ Shere አርጉት
😳😳😳😳😳😳😳😳😳😳
😯😯😯😯😯😯😯😯😯😯
😞😞😞😞😞😞😞😞😞😞
✅ ያልሰማ ካለ plz ለህይወትህ ስትል ስማ ✅
ትናንት በናሽናል ጂኦግራፊ ዋይልድ ቻናል ላይ
የተላለፈው ዜና አስደንጋጭ ነበር😟
, ማለትም ሳይንቲስቶች እንደገለፁት ከሆነ በጣም
አደገኛ እባብ 🐍ተገኝቷል ሳይንቲስቶቹ እንደተናገሩት
እባቡ ምግብ በበላ ቁጥር 0.5ሴ.ሜ ያድጋል
ምግቡን ደግሞ የሚበላው ቢበዛ በ 30 ሰከንድ
ውስጥ ነው ታዲያ ይህን እባብ በምንም አይነት
ሰው ሰራሽ መሳሪያ መግደል አለመቻሉ ነው ነገሩን
አስፈሪ ያደረገው ሊሞት የሚችለው እራሱን
በራሱ ከነከሰ ብቻ ነው ነገር ግን ሳይንቲስቶች
ሌላ የሚገድለውን ነገር እየፈለጉ ነው ይህ እባብ
በሰዉ ልጆች ታሪክ ከተመዘገቡ ገዳይ በጣም
አደገኛና መርዛማ ከሆኑ እባቦች ሁሉ ዋናው ነው😳
ታዲያ ይህ እባብ አንድ ቦታ ብቻ ነው የሚገኘው
እሱም
፨
፨
፨
፨
፨
፨
፨
፨
ኖኪያ 3310 የስልክ ቀፎ ላይ የጌም ምርጫ
ውስጥ snake xenzia. ላይ ነው ፡፡
በትእግስትና በጥሞና ስላነበባችሁት
አመሰግናለዉ 😂😂


እወዳቹሀለው መልካም አዳር 😍😍

ሼር አርጎ ማስደንገጥ እንዳረሱ 😂😂
@ethiofunnypp 🦋
ሁሌም ፈታ ለማለት join በሉ😍😍😘😘😘❤️❤️❤️
Forwarded from ĂĂ¸ĂąĂ¤
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (BÊŽÂ)
የ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ጉዳይ ፦

↘️የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በ2013 ዓ/ም መጨረሻ (ሰኔ አካባቢ) ፈተናቸውን እንዲወስዱ ለማድረግ ከወዲሁ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

↘️በ2012 ባች በታብሌቶች መዘግየት የቀረው የኦንላይ ፈተና የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ፈተናውን በኦንላይን እንዲወስዱ ለማድረግ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

↘️አጠቃላይ የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ወደ 800,000 ይሆናሉ።

↘️ትምህርት ሚኒስቴር ለ74 ዓመታት ሲሰጥ የነበረውን የፈተና አሰጣጥ ሂደት በመቀየር ከ2012 ባች ጀምሮ በኦንላይ ለማስፈተን ጥረት ቢያደርግም ግዢ የተፈፀመባቸው 500 ሺህ ታብሌቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ወደሀገር ባለመግባታቸው ሳይሳካ ቀርቷል፤ በ2013 ባች ግን ተግባራዊ ለማድረግ በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ አሳውቋል።

↘️የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ጫና የሚገኘውን የትምህርት ዘመን ከግምት ውስጥ አስገብቶ በ2013 ብሄራዊ ፈተና ላይ ችግር እንዳይገጥም ከወዲሁ እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

        @Free_Education_Ethiopia
Stay safe
የሰው ማገትና ግድያ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች እስከ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጡ!

በተከሰሱበት የሰው ማገትና ግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ሁለት ግለሰቦች እስከ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን አስተባባሪ አቶ አበበ ማስሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ግለሰቦቹ ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በፈጸሙት የሰው ማገት ወንጀል ተከሰዋል።

ተከሳሾች በተጠቀሰው እለት በመተማ ወረዳ ጉባይ ጀጀቢት ቀበሌ ልዩ ቦታው ኩሊት መገንጠያ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከሽንፋ ወደ ገንዳ ውሃ ሲጓዝ የነበረ ሲኖ ትራክ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ በማስቆም አሽከርካሪውንና ረዳቱን አግተው ወስደዋል።

እገታውን ከፈጸሙ በኋላ የታጋች ቤተሰቦችን በማስገደድ 150 ሺህ ብር ተቀብለው ታጋቾችን መልቀቃቸውን ተናግረዋል።

ግለሰቦቹ ታጋቾችን ወደ ጫካ በወሰዷቸው ወቅት ባደረሱባቸው ከባድ ድብደባና እንግልት አሽከርካሪው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።

ተጨማሪ የምስል መረጃዎችን ለማግኘት #የዩትዩብ ገፃችንን #subscribe ያርጉ👇
https://www.youtube.com/channel/UCHaghmzBorbg1g2Bb_cO5Vg

@ethio_mereja_news
@etho_mereja_news
ሳሚያ ሱሉሁ ሐሳን ቃለ መሃላ ፈጽመው የታንዛኒያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆኑ!

ታንዛኒያን ለቀጣዮቹ 5 ዓመታት ይመራሉ ተብሏል

ሳሚያ እስከ ጆን ማጉፉሊ ህልፈተ ህይወት ድረስ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ማገልገላቸው የሚታወስ ነው

ከደቂቃዎች በፊት ቃለ መሀላቸውን የፈጸሙት ፕሬዘዳንት ሳሚያ ታንዛኒያን ለቀጣዮቹ 5 ዓመታት ይመራሉ ተብሏል፡፡

ይህም ላለፉት 7 ዓመታት በምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩትን የ61 ዓመቷን አዛውንት ታንዛኒያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የቻሉ የመጀመሪያዋ ሴት ያደርጋቸዋል፡፡

እንደ ጎርጎሮሲያን ዘመን አቆጣጠር በ1960 በዛንዚባር ራስ ገዝ አስተዳደር የተወለዱት ሳሚያ ከ2015 ጀምሮ የማጉፉሊ ካቢኔ አባል ሆነው አገራቸውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በህዝብ አስተዳደር 2ኛ ዲግሪ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውም ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የታንዛኒያ ፓርላማ አባል እንደነበሩ የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ባለትዳር እና የ4 ልጆች እናትም ናቸው ሳሚያ፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከህዝብ እይታ የመሰወራቸው ጉዳይ ሲያነጋግር የነበሩት ፕሬዝዳንት ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ ትናንት የማረፋቸው ዜና ተሰምቷል።

በፕሬዝዳንቱ ሞት ምክንያትም ታንዛኒያ 14 ብሔራዊ የሀዘን ቀናትን አውጃለች።

ጎረቤቷ ኬንያም የስድስት ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን ማወጇን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል። የኬንያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ዛሬ ከታንዛኒያ አቻው ጋር ሊያደርግ የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ ለማጉፉሊ ክብር ሲባል መሰረዙንም የሃገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

እንደ ታንዛኒያ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 (2) ከሆነ የአገሪቱ ፕሬዘዳንት በሞት አልያም በሌላ በማንኛውም ምክንያት በስልጣን ላይ ሆኖ አገሪቱን መምራት ካልቻለ ምክትል ፕሬዘዳንቱ እንዲመሩ ይፈቅዳል።

@ethio_mereja_news