G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
#inbox_የተላከልን

ኢንትራንስ ተፈታኞች ይቀጥላል👍

"ሰላም ጓደኞቼ የንባብ ስልታችሁን አካፍሉን ተብሎ ጥሪ በተደረገልን መሰረት የኔን ያጠናን መንገድ ላደርሳችሁ ወደድኩ አብራችሁን ቆዩ

entrance ቀላል የሆነ ነገር ግን ትኩረትና ጥበብ የሚፈልግ በመሆኑ ለጥሩ ውጤት የተጠበቁ ተማዎች ስለሚወድቁ በብዙወቻችን ዘንድ የሚፈራ አድርጎታል እነዚህ ተማሪዎች የወደቁት እውቀት ሳይሆን ብልሀት ስለጎደላቸው በመሆኑ ሞኝ በራሱ ብልጥ ደሞ በሰው ህይወት ይማራል እንዲሉ አበው entrance exam የ3 አመት ሽቶችን ብቻ ለማስተያየት ብትሞክሩ በጣም ቀላል ድግግሞሽ የበዛበት ከዛም በተጨማሪ ጥያቄዎችን ስታጤኗቸው በሁሉም ተማሪዎች ሊሰሩ የሚችሉ ፣ መካከለኛ እውቀት የሚፈልጉና በጣም ማሰብንና ማገናዘብን የሚጠይቁ ጥያቄዎች ናቸው ።
በተጨማሪ ደሞ ጥያቄዎች የሚወጡት ከየ ምዕራፉ በማመጣጠን ስለሆነ እኔ ሳነብ እራሴን የምጠይቀው ጥያቄ ከ ምዕራፍ አንድ የትኛውም አይነት ጥያቄዎች ቢወጡ መስራት እችላለሁ ወይስ አልችልም የሚል ነው እናንተም ስታነቡ እራሳችሁን እሄን ጥያቄ ጠይቁ ምክንያቱም ከላይ እንዳየነወ ጎበዝ ሆኖው የሚወድቁት ተማሪዎች ጉድለት ጥያቄዎች አለመስራታቸው ስለሆነ ጥያቄዎች በደንብ ለመስራት ሞክሩ በትግስት ስለተከታተላችሁኝ አመሰግናለሁ የ Concise English channel መስራቾችንም የነገ ህይወታችንን መንገድ ለማሳመር አብረውን ስለሚደክሙ ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ"

📌 Join and Share 👇👇👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
ለሴት ተማሪ ግቢ ይከብዳል እንዴ?

አንዲት ቤተሰባችን ይህን ጥያቄ አረቀበችልኝ ፤ እኔም ሴት ሆኜ ስሜቱን ስለማላውቀው ቀጥታ የሴት ጓደኞቼን ለጥያቄው ምላሽ እንዲሰጡኝ ጠየኳቸው።የመለሱልኝ መልስ ይህ ነበር

የግቢ ህይወት ለሴት በጣም ይከብዳል ልክ ለወንድ እንደሚከብደው ሁሉ! ልክ እናንተ ወንዶች የገንዘብ ችግር ፤ የእንቅልፍ እጦት...የውጤት መውረድ እንደሚያገጥማችሁ ሁሉ እኛም የጋጥመናል። ነገሩ ትንሽ ለየት የሚያረገው ሴቶች በሴትነታቸው አንዳንድ ከባባድ ፈተናዎች ግቢ ውስጥ ይጠብቃቸዋል። ለምሳሌ

ሀ) በGC ተማሪዎች መለከፍ

GCዎች ማለትም Graduation Class Students ከግቢ ተመርቀው የሚወጡበት ወራት ጥቂት ስለሆነ ህይወትን እስከ ጥግ ድረስ ሊቀጩ FRESH ሴቶችን እንደመዝናኛ አማራጭ ያረጋሉ 😊ግን ብዙም አታስቢ ፤ ልብሽን ካልሰጠሽ ሌላ ማንም ጫፍሽን አይነካሽም 😊😎

ለ) ያንቺ እኩያ - ልቀፍሽ በጉያ

እንዲህ አይነት ወንዶች ደግም ያንቺ እኮዮች ናቸው ፤ በአንድ ባች ማለትም እንዳንቺ ፍሬሽ ሆነው ካንቺ ጋር ማውደልደል ሚፈልጉ 😊 በቃ ሳቅ ስትይላቸው እና አንዳንድ የመቅበጥ እንቅስቃሴዎችን ስታሳያቸው የተፈቀሩ የሚመስላቸው ።ከዛን አንድ ቀን Lounge ቀጥሮ ሻይ ይጋብዝሽና እንደፈቀረ እና ያላንቺ መኖር እንደማይችል ይነግርሻል 😂😂 አይምሰልሽ በደምብ ነው ሚኖረው ፣ ምንም አያሳስብም

ሐ) ፕሮፌሰር ስጪኝ

እነኚ አይነት መምህራኖች ከ 1/100ኛ ናቸው ።በጣም ጥቂት ናቸው ።ሴትነትሽን ተጠቅመው ሊያተሊያታልሉሽ ሚሞክሩ ግን አያሳስብም

መ) ተከታይሽ ሲበዛ

በተለይ በጣም ቆንጆ ከሆንሽ በቃ ለሁሉም ቀበሮ ነኝ ብሎ ለሚያስብ ወንድ አንቺ ሚዳቋቸው ነሽ። ግን አያሳስብም ልብሽን ለትንሽ ለትልቁ እስካላሳየሽ ድረስ ማንም ምንም አያረግሽም 😊


በቃ ህይወትሽን ቀለል የሚያረጉ ምክሮች ደግሞ ከስር ተሰተዋል 😊 ሁሉንም አንብቢያቸው 😊



📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
ለ 2013 ዓ. ም ለ12ኛ ተፈታኝ በሙሉ ይህ መልክት ከትምርት ሚኒስተር አይደለም ወይም ከምታምኑት ቲክቫህ አይደለም ይህ መልክት ከዘንድሮ ተፈታኞች የተወጣጣ ሀሳብ ነው ውድ የ 2013 ኢንትራስ ተፈትነሽ ቤትሽ የተቀመጥሽው የተቀመጥከው ወንድምቼ እህቶቼ በትህትና አንብቡት አሁን ወደ ዋናው ዕርሳችን እንግባ ።

ሰኔ 1/10/2013 በኢትዮጲያ የሚገኙ የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተና እስከ ሰኔ 30 ድረስ የወሰዱበት ጊዜ ነበር እናም ዋናው ሀገር አቀፍ ፈተናው ሐምሌ መጨረሻ ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም ከትምርት ሚኒስተር ሐምሌ 12/2013 እንዲ እሚል ዜና ወጣ ውድ የ 2013 የሀገር ዓቀፍ ፈተና ተፈታኞች የሀገር ዓቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ በጥቅምት መጨረሻ የ 12ኛ ክፍል ወደ ዩኒቨርስቲ መጊቢያ ፈተና እንደሚፈትን ተናገረ ።

በዚን ሰዓት የሙሉ ተማሪው ስሜት ተረበሸ አስቡት እስቲ እሄን ምታነቡ ባለስልጣን አስተማሪ ተማሪዎች ሐምሌ ላይ ቁጭ ብለክ ጥቅምት ነው ምትፈተነው ስትባል በጣም ከባድ ነው ታጋሽ በመሆን ያቺም ቀን ደረሰች።

አሁን ትምርት ሚኒስተር ትኩስ ዜና አወጣ የ 2013 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሁለት ዙር እንደሚሰጥ እና የመጀመሪያው ዙር ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 /2014/ 3 ወር ድረስ እነደሚሰጥ በድረገፁ ለቀቀ ተማሪዎችም ደስ አላቸው ለፈተናው ቀን በመድረሳቸው ምንም ቢሆን የአማራ ክልል ተማሪዎች አብረውን ባይፈተኑም ልንገላገለው ስለሆነ ደስ አለን።

ጥቅምት 29 ደርሳ ድሮ ስሜን መፃፍ ስለምድ እንደተደሰትኩት ENGILSH ፈተና ላይ ስሜን ፅፌ ጀመርኩ ቀስ በቀስ የመጨረሻዋ ቀን ህዳር 2 ጨርሼ ወደ ቤቴ ገባው ከተፈተንኩኝ 3 ቀን ምላኝ ሳምንት አለፈኝ ወር አስቆጠርኩን ከተፈተንኩ ሁለት ወር ሊምላኝ አንድ ሳምንት ቀረኝ ሁለት ወር አስቆጠርኩ አማራ ክልል ያሉት የሀገሬ ልጆች ሳይፈተኑ ቆዩ ከትንሽ ጊዜ በዋላ ትምርት ሚኒስተር እንዲ አለ ትዝ ይለኛል ታህሳስ ውስጥ ነበር ይሄን ዜና የሰማውት

የ 2013 የ 12ኛ ክፍል አማራ ክልል አፋር ቤንሻንጉል ክልል በጦርነቱ ምክንያት ላልተፈተኑ ተማሪዎች ጥር 24 -27 / 2014 /5 ወር እንደሚፈትን ተናገረ እኛም ደስ አለን ቀኑም ደረሰ ፈተናቸውን ጀመሩ እነሱ ሲፈተኑ እኛ እነሱ እኪፈተኑ በኢትዮጲያ አቆጣጠር 3 ወር ማለት ነው 90 ቀን 90 ምሽትን ብዙ 24 ሰዓትን በትግስት አሳለፍን እነሱም ፈተናቸውን ጨርሰው ቁጭ አሉ ወሩ የካቲት ነው ከትምርት ሚኒስተር ለ ቴኪቫ አንድ ዜና መጣ ከ የካቲት 15 - 20/ 2014/ 6 ወር ድረስ የሀገር አቀፍ ፈተና ይፋ እንደሚሆን ተነገረ እኛም ያቺን ቀን በጉጉት ጠብቅናት አሁን የ አንደኛ ዙር እና ሁለተኛ ዙር ልዩነቱ ልንገራቹ አንደኛ ዙር የተፈተኑት ከሁሉም ቀድመው ነው ሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ልክ እንደ አንደኛ ዙር 90 ቀን 90 ምሽትን በ 3 ወር ም ሳይፈተኑ በትግስት ጠብቀዋል ግን ከተፈተኑ በ 19ኛ ቀናቸው ውጤታቸውን ሰሙ አሁን የካቲት 16 /2013 6 ወር ብዙ ተማሪዎችን ያጓጓው የሀገር አቀፍ ፈተና ተለቀቀ እኔንም ጨምሮ ሁሉም ተማሪ ተደሰቱ እስከ የካቲት 30 መቁረጫው እና ምደባ እንደሚደረግ ተነገረ እጥፍ ድርብ ደስታ ተሰማን

አሁን ውጤታችንን ከሰማን ሳምንት ሞላን እስካሁን ምንም የለም 15 ቀን አለፈን የ የካቲት ወር ተገባዶ መጋቢትን ተቀበልን መጋቢት 5 /2013/ 7 መቁረጫ ተነገረ በጣም ከባድ እና አሳዛኝ ስሜቶች ተደበላለቁ በጣም ብዙ ተማሪ ወደቀ አዘንን እየዋለ እያደረ ቅሬታዎች በዙ ከ ሰሜኑ በኩል ጉዳዩ እየከረረ መጣ።

ትምርት ሚኒስተር መጋቢት 9 - 13 / 2014 / 7 ወር ሀገር ምደባ አስተካክሉ አለ ቀኑም አለፈ የተስተካከለ ማስታወቂያ ወጣ እስከ መጋቢት 19 Placement ማለት ምደባ ተማሪዎች እስከዛ ጨረሱ ከምደባ በዋላ ምንም እምንቀበለው ነገር የለም አሉ የተማሪ ትግስት ከ 2013 ሐምሌ ጀምሮ እስከ መጋቢት 2014 ድረስ ደረሰ ለተማሪዎች 👏👏👏👏👏👏👏👏👏


ዛሬ ሚያዚያ 2 /2014 / 8 ወር ላይ እንገኛለን ይሄን ሁሉ ጊዜ ጠብቀን እስካሁን እንኳን ልንመደብ የት እደምንማር ሳናውቅ ቁጭ ብለናል ድሮ ግንቦት ተፈትነው ሰኔ አርፈው ሐምሌ መጨረሻ ውጤት መቶ ነሀሴ መቁረጫ እና ምደባ ተደርጎ መስከረም አዲስ ዓመት ዩኒቨርሲቲ ጊቢዎች ጥሪ ያረጉ ነበር ያሁኑ ስቃይ ነው አዲስ ስልጣን እንጂ ለውጥ መቼ መጣ ይሄ ለ 2013 ተፈታኞች በሙሉ መፅናናትን

👉 ውድ አንባቢያን ልብ እንድትሉ ምንፈልገው ይሄን ጽሁፍ ያዘጋጀነው ሚያዚያ 02 2014 ላይ ሆነን ነው ይህ ማለት የመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ፈተና ከጨረሱ አምስተኛ ወር ማለት ነው😢

#በጣም ያስጠላል😢

እባካችሁ ይሄን መልዕክት በትልልቅ ግሩፖች በትልልቅ ቻናል መልዕክት መቀበያ ቦቶች በመላክ ድምጻችንን እናሰማ🙏



ሚያዚያ 3 / 08/ 2014 ዓ. ም


📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
🎯 ግቢ ላይ ውጤት እንዴት መስራት እንችላለን።

@GTutorialclass ተፃፈ።

📌 Worksheet

Worsheet ማለት መምህሩ የሆነ chapter አስተምሮ እንደጨረሰ በተማራችሁት ትምህርት ዙሪያ ከበድ ከበድ ያሉ እና የ concept ጥያቄዎች ከተለያዩ መፅሀፍት አውጣጥቶ ፈተና ሊደርስ አካባቢ የሚሰጣችሁ ነው። በተለይ ፈለጣ የሚበዛበት ዲፓርትመንት የምትገቡ ልጆች worksheet የተለመደ ነው። መምህሩ worsheet ከሰጣችሁ ፡ ፈተናውን በዚህ መልክ ተዘጋጁ ማለቱ ነው። ከ worksheet ቱ ላይ ጥቂት የማይባሉ ጥያቄዎች ፈተና ላይ ይወጣሉ። መምህሩ ጥያቄዎቹን የሚያወጣው ከ መፅሀፍ ስለሆነ የጥያቄዎቹን መልስ ከዛው መፅሀፍ ታገኙታላችሁ ፡ ከሌለ ደግሞ Google ማድረግ ይጠበቅባችሗል። ስለዚህ የሚሰጣችሁን worksheet ጥሩ አድርጋችሁ ከሰራችሁ ፡ ፈተናውን ትሰሩታላችሁ።

📌 የአጠናን መንገድ(ስልት)

እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው🤔?

🎯 አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ።

🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ።

🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው።

ስለዚህ እንዴት እናብብ🤔

🔔 የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም🤷‍♀

ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ

🎯 የ ሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው።

🎯 መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ።

🎯 የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው።

🗣 ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን።

📌 የጊዜ አጠቃቀም

ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው።

📌 አለመሰልቸት

ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል።

📌 ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን።

ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ።

📌 Google

ለ ግቢ Google በጣም ወሳኝ ነገር ነው። Assignment መስራት ብትፈልጉ ፡ practical education በ video ማየት ብትፈልጉ ፡ የተለያዩ መፅሀፎችን እና የመፅሀፍ solution ማውረድ ብትፈልጉ ፡ ምናልባት መምህሩ የሰጣችሁ ኖት ካልገባችሁ እና ሳይንሱን መረዳት ብትፈልጉ ፡ Google ለነዚህ ሁሉ በቂ መፍትሔ አለው። ስለዚህ Google ን የቅርብ ወዳጅ አድርጋችሁ ወጤት መስራት ትችላላችሁ ፡ ሳይንሱን መረዳት ትችላላችሁ። በዚሁ አጋጣሚ ለ Google ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ😘

😊 The End

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
ENG entra ( 200-2011).docx
316.6 KB
📚 Grade 12 English.

📚 Entrance Questions.

📚 2000 - 2011 EC በየምዕራፉ የተከፋፈለ ነው።

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
BIOLOGY 2000 - 2009.docx
155.4 KB
📚 Grade 12 Biology.

📚 Entrance Questions.

📚 2000 - 2009 EC በየምዕራፉ የተከፋፈለ ነው።

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
GRADE 12 PHYSICS ENTERANCE EXAM (2000 – 2011 E.C).docx
499.1 KB
📚 Grade 12 Physics.

📚 Entrance Questions.

📚 2000 - 2011 EC በየምዕራፉ የተከፋፈለ ነው።

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
chemistry 2000-2011.docx
438.8 KB
📚 Grade 12 Chemistry.

📚 Entrance Questions.

📚 2000 - 2011 EC በየምዕራፉ የተከፋፈለ ነው።

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
Tutorial class for all student✍️✍️
𝐴𝑙𝑙 𝑡ℎ𝑖𝑛𝑔𝑠 𝑖𝑠 𝑝ossib𝑙e 𝑤𝑖𝑡ℎ 𝑟𝑒𝑎𝑑𝑖𝑛𝑔
https://t.me/GTutorialclass
Share this channel please 🙏🙏 share 👇👇👇 📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
በ video በ ቅርቡ

📚 Communicative English Skill I.

📚 Unit One - Study Skills.

📚 Grammar Focus - Present Perfect Tense.

📚 Targeted Group - First year University Students.

☑️Present Perfect Tense

🔰Affirmative form
I/we/they/you + have + V3.
He/She/It + has + V3

🎴Negative form
I/we/they/you+haven't+V3.
He/She/It + hasn't + V3.

🎁Question form
Have + I/we/they/you +V3?
Has + he/she/it + V3?

🍄Usage

🌹1⃣) to describe an event that happened in the past and are still true now because you can see the result.

📚 ከአሁን በፊት የተከናወነ አንድ ድርጊት ነበር፡ ታድያ ይኸ ከአሁን በፊት ተከናውኖ የነበረው ድርጊት ውጤቱ አሁን ላይ የሚይታይ ወይም ያለ ከሆነ ፡ ከአሁን በፊት ተከናውኖ የነበረው ድርጊት በ present perfect ይገለፃል።

📚 ማለትም ድርጊቱ ከአሁን በፊት(past) ነው ተከናውኖ ያለቀው ነገርግን የ ድርጊቱ ውጤት አሁን(present) ላይ የሚታይ ከሆነ ይኸን ድርጊት በ present perfect እንገልፀዋለን ማለት ነው።

🎯 Example 1

📚 ትናንት 11:00 አካባቢ ከዛፍ ላይ ወደክ በመውደቅህ ምክንያት ታመህ ወይም ተሰብረህ ዛሬ አልጋ ላይ ተኛህ። ስለዚህ ትናንት ከዛፍ ላይ መውደቅህ ከአሁን በፊት የተከናወነ ድርጊት ነው፡ በመውደቅህ ምክንያት ዛሬ ታመህ አልጋ ላይ መተኛትህ የትናንቱ ድርጊት ውጤት ነው። ዛሬ ታድያ ጓደኞችህ ምን ሁነህ ነው ብለው ቢጠይቁህ፡ ከዛፍ ላይ ወድቄ ነው ብለህ ነው ምትመልስላቸው። so,

🚼I have fallen from a tree.

📚 ታዲያ ብዙዎቻችን ድርጊቱ ማለትም ከዛፍ ላይ መውደቁ ትናንት ተከናውኖ ያለቀ ድርጊት ነው፡ ለምን በ simple past አይገለፅም የሚል ጥያቄ ልናነሳ እንችላለን። አሪፍ ጥያቄ ነው ነገርግን ማስተዋል ያለብን ነገር በትናንትናው ድርጊት ምክንያት ውጤቱ ማለትም ዛሬ ላይ ታሞ መተኛቱ ነው present perfect እንድንጠቀም ያደረገን። ነገር ግን ትናንት በመውደቁ ምክንያት ዛሬ ላይ ካልታመመ ጤነኛ ከሆነ፡ የትናንቱ ድርጊት አሁን ላይ የሚታይ ውጤት ስለለው በ simple past ይገለፃል። ልዩነቱ፡

🔘I have fallen from a tree.( አሁን ላይ ታምሜአለሁ ወይም ተሰብሬአለሁ ወይም የደረሰብኝ ጉዳት አለ ማለት ነው።)

🔘I fell from a tree.( አሁን ላይ የደረሰብኝ ጉዳት የለም እንደማለት ነው።)

🎯 Example 2

📚 ለምሳሌ ልጁ(the boy) መኪናውን አፅድቶ ጨርሷል። እና አሁን መኪናው ፅድት ብሎ አዲስ መስሏል። ተመልከቱ ልጁ መኪናውን አፅድቶ ጨርሷል ማለትም ከአሁን በፊት የተከናወነ ድርጊት ነው። ነገር ግን ውጤቱ ማለትም መኪናው ፅድት ብሎ አዲስ መምሰሉ አሁን ላይ የሚስተዋል የሚታይ ነው። ስለዚህ

🍄 The boy has cleaned the car. It looks new again.

🌹2⃣) to describe an event that happened a few minutes ago.

📚 ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት የተከናወነን ድርጊት ለመግለፅ። ማለትም ከ 10 ደቂቃ በፊት፡ ከ 15 ደቂቃ በፊት፡ ከ 20 ደቂቃ በፊት፡ ከ 5 ደቂቃ በፊት ወዘተ የተከናወኑ ድርጊቶችን ለመግለፅ present perfectን እንጠቀማለን ።

🎯 Example

📚 የ Arsenal ና chelsea ን ጨዋታ DSTV ቤት ሔደህ አየህ፡ ጨዋታው በ Arsenal አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ጨዋታው አልቆ ከ 20 ደቂቃ በሗላ ጓደኛህ ማን አሸነፈ ብሎ ቢጠይቅህ፡ ድርጊቱ ከትንሽ ደቂቃ(ከ 20 ደቂቃ) በፊት የተከናወነ ስለሆነ በ prsent perfect ትገልፀዋለህ።

🔘Arsenal has won the match.
ነገር ግን ጨዋታው ካለቀ ከ አንድ ቀን ምናምን በሗላ ማን አሸነፈ ብሎ ቢጠይቅህ በ present perfect ሳይሆን በ simple past ነው የምትገልፀው።so,

🔘Arsenal won the match.

🌹3⃣) to describe an event that started in the past and is still happening now.

📚 ካሁን በፊት ሲከናወን የነበረ አሁንም በመከናወን ላይ ያለ ድርጊትን ለመግለፅ present perfect ን እንጠቀማለን።

📚 እዚጋ ታድያ ድርጊቱ ከአሁን በፊት ለምን ያክል ጊዜ ተከናውኖ እንደነበር ለመግለፅ 'For' ን ስንጠቀም ፡ ከአሁን በፊት ሲከናወን የነበረው ድርጊት ከመቼ
ጊዜ ጀምሮ እንደተከናወነ ለመግለፅ ደግሞ 'Since' ን እጠቀማለን።

📚 እንዲሁም ካሁን በፊት(past) ሲከናወን የነበረ አሁንም በመከናወን ላይ ያለ ድርጊት መሆኑን ለማመልከት So far , till now , up to now የመሳሰሉትን መጠቀም እንችላለን። ትርጉማቸውም 'እስካሁን' ማለት ነው።

🎯 Example

📚 Million የ computer science መምህር ነው። computer science ን ከ 2006 ጀምሮ ለ 8 አመት አስተምሯል አሁንም በማስተማር ላይ ይገኛል። ስለዚህ😎

🔘Million has taught computer science for 6 years.(ለ 6 አመት አስተምሯል፡ አሁንም እያስተማረ ነው።)

🔘 Million has taught Computer Science since 2006.( ከ 2006 ዐ.ም ጀምሮ እስካሁን እያስተማረ መሆኑን።)

📚 እዚጋ ማስተዋል ያለብን ነገር million ከ 2006 ጀምሮ ለ 8 አመት አስተምሮ አሁን ላይ ግን ሌላ ስራ ይዞ ይኸን ትምህርት የማያስተምር ከሆነ በ present perfect ሳይሆን በ simple past ነው የምንገልፀው።

🔘Million taught Computer Science for 6 years.(ለ 6 አመት አስተምሮ ነበር አሁን ላይ ግን እያስተማረ አይደለም።)

🍄 Million ከ 2006 ጀምሮ እስካሁን computer science እያስተማረ መሆኑን ለመግለፅ ደግሞ👇

Million has taught computer science so far.(million እስካሁን CS እያስተማረ ነው) በ so far ቦታ till now ወይም up to now ን መጠቀም እንችላለን።

@Aconcise
📚 ግቢ ላይ ውጤት እንዴት መስራት እንችላላን ።

📚@GTutorialclass
@GTutorialclass ተፃፈ።


📚 ማንበብ + መረጃ 👀

ግቢ የቱንም ያህል ብታነብ ፡ ላይብረሪ ውስጥ ብትውል ብታድር ፡ ሺህ መፅሀፎችን ብታነቢ መረጃ ከሌለሽ ልፋትሽ ከንቱ ነው ፡ በለፋህበት ልክ አትሰራም መረጃ ከሌለህ😥። መረጃው ምን አይነት ይሆን🤔?

📌 ለምሳሌ አንዳንድ ፈጣን ተማሪዎች በነሱ ዲፓርትመንት ውስጥ ያሉ ነባር ተማሪዎችን ( senior ) ይጠይቃሉ።

🤔 ለምሳሌ ነባር ተማሪዎች ያንን ኮርስ በሚወስዱበት ጊዜ ምን ምን መፅሀፍ ይጠቀሙ እንደነበር ፡ መምህራኖች ጥያቄ የሚያወጡበት መፅሀፍ ምን እንደነበር ይጠይቃሉ ፡ ከዛም መፅሀፋን ይቀበላሉ😉። ስለዚህ እናንተ ተፍ ተፍ ማለት ፡ የ ክላሳችሁን መጠየቅ ፡ ምን መፅሀፍ እንደተቀበሉ ምን መፅሀፍ እንዳላቸው ፡ መጠየቅ😁

📌 ሌላኛው ደግሞ መምህሩ ክላስ ውስጥ በሚያስተምርበት ሰአት ፡ ይኸን part በደምብ አንብቡ ፡ ይሄን ያዙ ምናምን እያለ ፈተና የሚወጣበትን part ሊጠቁም ይችላል። ክላስ ካልገባህ ወይ ደግሞ ክላስ ውስጥ የምንታቀላፊ ከሆነ ፡ ተበላሽ😂። ስለዚህ ክላስ የገቡ ተማሪዎችን መምህሩ ምን ምን እንዳለ መጠየቅ😉

📌 ሌላኛው ደግሞ Affirmative action 😳😂። ምን መሰላችሁ ፡ ለምሳሌ mid exam የሚወጣው chapter 1&2 ከሆነ ፡ መምህሩ 2 ቱን chapter አስተምሮ እንደጨረሰ ፡ ፈተናው 3 ወይም 4 ቀን ሲቀረው ለ ሴት ተማሪዎች ብቻ የሚሆን ለፈተናው የሚጠቅም መምህሩ tutorial ይሰጣቸዋል። ፈተና የሚወጣበትን part ያስተምራቸዋል ፡ ከ ፈተናው ጋ ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ይሰራላቸዋል። ኸረ እንደውም አንዳንድ ጊዜ ፈተና ላይ የሚወጣውንም ጥያቄ ይሰራላቸዋል🙈። ስለዚህ የ ክላሳችሁን ሴት ተማሪዎች እንዳትፋቷቸው😁። በ tutorial class መምህሩ ያፃፋቸውን ኖት ፡ ያሰራቸውን ጥያቄ በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ አንብቡ☺️
አሁን ደግሞ

😌 በ ግቢ ቆይታየ ከ መረጃ ጋ በተያያዘ ያጋጠመኝ አንድ ሁለት ገጠመኝ ላጫውታችሁ😅

🦸‍♂ " Mass and Heat transfer " የሚባል ኮርስ ወስደናል። እና እኔ አንዳንድ ጊዜ ከነሸጠኝ ክላስ አልገባም🤷‍♂። ከዛ ክላስ ባልገባሁበት ሰአት ፡ መምህሩ አስተምሮ ፡ በ Cartesian and cylindrical የሚሰራ proof ነበር። በ Cartesian የሚሰራውን መምህሩ proof አደረገላቸው። በ cylindrical የሚሰራውን ደግሞ እናንተ proof አድርጉ አላቸው ። " አደራ አደራ እንዳትረሱት " አላቸው😒። እኔ በወቅቱ ክላስ ስላልገባሁ መረጃው አልነበረኝም😢። ይኸን የሰሙ ተማሪዎች ላይብረሪ ገብተው proof ፋን ሽምድድ።

ከዛ mid exam ስንፈተን በ cylindrical proof አድርጉ ያላቸውን 8 mark ይዞ መጣ😞
እኔ መረጃው ስላልነበረኝ ከ 8ቱ 0 አመጣሁ🤨። ከዛ ይኸን ኮርስ 77.5 (B+) አመጣሁ ከ 100%። ግን መረጃው ቢኖረኝ ወይም ክላስ ባልቀጣ proof ፋን እሰራው ነበር ።

77.5 + 8 = 85.5( A )

🥺 አያችሁ አይደል በዚች የመረጃ ክፍተት A የማመጣውን ኮርስ B+ አመጣሁ😡


🗣 ከመረጃ ጋር በተያያዘ ሌላ ገጠመኝ

🦸‍♂ "Probability and Statistics" የሚባል ኮርስ ወስደናል። እና በወቅቱ መምህሩ ፈተና የሚያወጣበት ፡ አሳይመንት የሚያወጣበት መፅሀፍ ነበር። እና እኔ ደግሞ በወቅቱ መረጃው አልነበረኝም መምህሩ ያን መፅሀፍ እንደሚጠቀም። ከዛ መምህሩ የሰጠንን handout ለ ፈተና አንብቤ ገባሁ። ግን መምህሩ ጥያቄውን ከዛ መፅሀፍ ስለነበር ያወጣው 5/10 አገኘሁ😏። ያንን መፅሀፍ ያነበቡ ልጆች ግን ደፈኑት😁። ከዛ ከፈተና በሗላ ስጠይቃቸው "እንትን" የሚባል አሪፍ መፅሀፍ አለ ከዛ ነው ያወጣው አሉኝ ። ከዛ ተቀበልኳቸው🕺💃። ከዛ ለ mid exam ያንን መፅሀፍ ቅጥቅጥ አድርጌ አነበብኩ ፡ ሰራሁት☺️። ከዛ አሳይመንትም እንደዚሁ ከ መፅሀፉ ቁጥር እንኳን ሳይቀር አመጣው ፡ ከዛ እኛም ድፍን☺️። ምን ቀረ🤔? Final exam😴። ለ final exam አሁንም ያንን መፅሀፍ ቅጥቅጥ አድርጌ አነበብኩ ፡ ከዛ 'A' አመጣሁ🕺💃

🥺 አያችሁ አይደል ያንን መፅሀፍ ባልቀበል ወይም ደግሞ መረጃው ባይኖረኝ ፡ handout ቱን ብቻ ነበር የማነበው ፡ A አላመጣም ነበር።

‼️ በ ነገራችን ላይ Chemical Engineering, Electrical and Computer engineering, civil engineering ምናምን የምትገቡ ልጆች " probability and statistics" ኮርስ ትወስዳላችሁ ። የ ግቢ መምህሮች አሁን ያልኳችሁን መፅሀፍ ፈተና ለማውጣት ፡የ አሳይመንት ጥያቄ ለማውጣት ፡ handout ለማዘጋጀት ይጠቀሙበታል። ስለዚህ " probability and statistics" ኮርስ በምትወስዱበት ጊዜ ፡ በውስጥ መስመር አናግሩኝ እሰጣችሗለሁ።

🗣 የመጨረሻ ገጠመኝ ፡ አላብዛባችሁ😊

🦸‍♂ " Applied Electrochemistry" የሚባል ኮርስ ወስደናል። እና መምህሩ አሳይመንት አስቀድሞ ነበር የሰጠን። በቅፅል ስም " Smith " እያልን የምንጠራው ልጅ አለ ፡ መፅሀፍ በመጎርጎር 1ኛ ነው👌። አመናችሁም አላመናችሁም መምህሮች የሚጠቀሙበትን እያንዳንዱን መፅሀፍ ያገኘዋል ። እንደውም ከመምህሮች በላይ መፅሀፍ የሚያውቅ ይመስለኛል😁። በዚሁ አጋጣሚ ለ Smith ያለኝን አድናቆት እና ምስጋና መግለፅ እወዳለሁ🙏። ብቻ ምን አለፋችሁ መምህሩ አሳይመንቱን ያወጣበትን መፅሀፍ አገኘው🙈። ከዛ መፅሀፋን ስናየው መምህሩ note የሚያወጣውም ከዛው መፅሀፍ ነው ፡ መረጃ ይልሀል ይኸ ነው😜። እኛም አሳይመንቱን ድፍን😉። ከዛ ለ mid exam ፈተና ያንን መፅሀፍ አንብበን ገባን። ከክላሱ ዝቅተኛ ውጤት የመጣው 24 ከ 30። መረጃ ይሉሻል ይኸ ነው😉

😊 በዚሁ አጋጣሚ Chemistry ነክ የምትማሩ ልጆች ለምሳሌ Medicine, pharmacy, biomedical engineering, medical laboratory, Chemical engineering, biology, Chemistry.... የምትገቡ ልጆች Applied organic Chemistry, Analytical chemistry, inorganic chemistry, Applied Electrochemistry....ስለምትማሩ እንዲሁም የ natural science ተማሪዎች freshman course ላይ General Chemistry ስለምትማሩ አሁን የነገርኳችሁን መፅሀፍ ተጠቀሙ ። አሪፍ የሆኑ የ concept ኖቶችን ታገኛላችሁ ፡ አሪፍ አሪፍ ጥያቄዎችን ታገኛላችሁ። በቃ Chemistry እንዲገባችሁ ከፈለጋችሁ መፅሀፋን ተጠቀሙበት።

የመፅሀፉ ስም 👇
" University of Meinosota"

የመፅሀፋ መገኛ 👇
Library ( natural library)

🙋‍♂ ሀሳቤን ስጠቀልለው ፡ ግቢ ላይ ማንበብ ብቻውን አይጠቅምም። መረጃ አነፍናፊ መሆን አለባችሁ። ስለ ፈተናው አወጣጥ ፡ ፈተናው ምን part ላይ አንደሚያተኩር ፡ ፈተናው ምን መፅሀፍ ላይ ሊወጣ እንደሚችል ምናምን መረጃዎች ሾልከው ይወጣሉ ። ስለዚህ ከንባብ በተጨማሪ መረጃ ላይም አደራ ትኩረት አድርጉ ።

📌 Join and share 👇👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
📖 How to become A straight A student

📝 The unconventional strategies Real college students use to score high while studying less

Author : Carl New port

በ Concise English Channel
(@Aconcise) ብቻ የሚቀርብ ።

ክፍል አንድ

" Go big or Go home , seriously Work Hard when You work and You will have plenty of time to play Hard "

📚 ወደ ተመደብኩበት ግቢ በገባሁበት የመጀመርያ አመት እንዴት ለፈተና ማንበብ ፣ አሳይመንቶችን መስራትና ግዜን በአግባቡ መጠቀም እንዳለብኝ ምንም ፍንጩ አልነበረኝም ። ልክ እንደ አብዛኛው ተማሪ ማጥናት ማለት የመምህራንን Note እስከቻልነው ድረስ ደግሞ ደጋግሞ ማንበብ ብቻ የሚል እምነት ነበረኝ ነገር ግን College እንደ High school አልነበረም ።

📚 ግዜ በገፋ ቁጥር የተሻለ መንገድ እንዳለና እሱን ለመፈለግ ውሳኔ ላይ መድረስ እንዳለብኝ ተሰማኝ ። በዙርያዬ ያሉት ሌሎች ተማሪዎች በተመሳሳይ ሁኔታው ውስጥ ቢሆኑም አንዳቸውም ለምን ብለው ጠይቀው እንደማያቁ እና ሁኔታውን ለመለወጥ ፍላጎት እንደሌላቸው ተረዳው ።

📚 ለረጅም ሰአታት አድካሚና አታካች የአጠናን መንገድን ተከትሎ በማንበብ መካከለኛ ውጤትን ማምጣት ልፋቴን እንደማይመጥን ስረዳ እንቅልፌንና በግቢ ውስጥ ያለኝን ማህበራዊ ህይወቴን በማይጎዳ መልኩ በውጤት ልዩ ሆኜ መውጣት እንዳለብኝ ከውሳኔ ላይ ደረስከኝ ። ለአብዛኞቻችን ረጅም ሰዓታትን እንቅልፋችንን እያጣን ካላጠናን ውጤታማ መሆን አንችልም የሚለውን የተሳሳተ እምነት በመስበር ኮከብ ሆኜ ለመውጣት ወሰንኩኝ።

📚 ለአብዛኛው ተማሪ የማይሆን መስሎ አይቻልም ብሎ የሚያስበውን በተፈጥሮዬ ቀና ነበርኩኝና በቀን ለአጭር ሰዓታት በማንበብ እንቅልፌንና ማህበራዊ ህይወቴን ሳልጎዳ ውጤታማ የምሆንበትን መንገድ ለመከተል በመወሰን የነበረኝን የአጠናን መንገድ እና የተሳሳተ እምነት በመጣል ውጤታማውን መንገድ ፍለጋ ሙከራ ጀመርኩኝ ።

📝 ይቀጥላል

🎯 Join And Share .

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
@Aconcise Logic short note 1.pdf
632.5 KB
📚 Logic and Critical thinking.

📚 Chapter one short note.

📚 እጥር ምጥን ያሉ በብስለት የተዘጋጀ ነው። ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት አመቺ ነው። ንባብ ለጀመራችሁ ፍሬሽማኖች።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
@Aconcise Logic short note 2.pdf
999.2 KB
📚 Logic and Critical thinking.

📚 Chapter two short note

📚 እጥር ምጥን ያሉ በብስለት የተዘጋጀ ነው። ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት አመቺ ነው። ንባብ ለጀመራችሁ ፍሬሽማኖች።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
@Aconcise Logic short note 3.pdf
1.8 MB
📚 Logic and Critical thinking.

📚 Chapter three short note.

📚 እጥር ምጥን ያሉ በብስለት የተዘጋጀ ነው። ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት አመቺ ነው። ንባብ ለጀመራችሁ ፍሬሽማኖች።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
👍1
@Aconcise Logic short note 4.pdf
1 MB
📚 Logic and Critical thinking.

📚 Chapter four short note.

📚 እጥር ምጥን ያሉ በብስለት የተዘጋጀ ነው። ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት አመቺ ነው። ንባብ ለጀመራችሁ ፍሬሽማኖች።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
@Aconcise Logic short note 5.pdf
1.3 MB
📚 Logic and Critical thinking.

📚 Chapter five short note.

📚 እጥር ምጥን ያሉ በብስለት የተዘጋጀ ነው። ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት አመቺ ነው። ንባብ ለጀመራችሁ ፍሬሽማኖች።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
#Advert

ስለ 📚 @GTutorialclass ሰምታችሁ ይሆን🤔</span>

🥇ዛሬ ላይ በጣም ብዙ የTelegram ቻናሎች ማስታወቂያቸው ስለሚዘዋወር ፣ አይታችሁት ከሆነ ዝም ያላችሁት እንዳትሸወዱ።

🏆እኛ የመጣነው በምክኒያት ነው።🏆

🗂በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ብትሆኑ ፡ ምንም ሊያስጨንቃችሁ አይገባም
🤌ምክንያቱም፡
እኛ
@GTutorialclass አለንላችሁ።

🪴ከ9ኛ ክፍል እስከ University ድረስ በሁሉም የትምህርት አይነቶች Handout በጠየቃችሁን የትምህርት ደረጃዎች ግልጽ እና ውብ አድርገን እናዘጋጃለን።

📚ምናልባት ሰፋ ያለ ይዘት ያለው መጽሃፍ አንብባችሁ ይሆናል። ታዲያ በዚህ ጊዜ ሃሳባችሁን ጠቅለል አድርጎ የሚይዝ MindMap ያስፈልጋችሃል።
ለእሱ ደግሞ እኛ አለን፡
🔖MindMap እጥር ምጥን አድርገን በአንድ Page ላይ ብቻ ሙሉ ሃሳቡን ቁጭ አድርገን እፎይ እናስብላለን።

📖ቀን በቀን ደግሞ Tutorials ይኖረናል። አጭር ግልጽ እና ውብ በሆነ አቀራረብ ውድ ውዱን ሁሌም ለእናንተ አለን እያልን አንድ እርምጃ ከፍ ከፍ እያልን ስኬት ላይ እናደርሳለን

📒ምናልባት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ከብዷችሁ ከሆነ መብትሄው እኛ ጋር አለ።
📁የAdvanced Worldwide English በአማርኛ እያዋዛን ስለምናቀርብ ምንም ሊያሳስባችሁ አይገባም።
📒English Entrance examination ከመነሻው እስከ መድረሻው በአማርኛ ግልጽ እና ልዩ በሆነ መንገድ በማቅረብ ላይ ነን።

📘Cambridge university World book በየቀኑ የሚያወጣቸውን የEnglish Vocabulary ከማርኛ ትርጉም ጋር ቀን በቀን....

🔐በሌላ በኩል ደግሞ🔐
📌 ከተለመደው የመጽሃፍ ይዘቶች ለየት ባለ መልኩ ምርጥ Advanced የተባሉትን መጽሃፎች እኛ ጋር ታገኛላችሁ።

❤️ይቀላቀሉን......
💕ትርፋችሁ እልፍ ነው፡ ምክንያቱም የሚሰራው ሁሉም ነገር ስለ ፍቅር ስለሆነ....
❤️ለሚወዱት የሚሰጥ ልዩ፡ ስጦታ፡ የደከሙለትን ፡ መስዋዕት ከፍሎ ያገኙትን ያለገደብ ማካፈል ነው።

💡💡💡💡💡💡💡💡
💡📚@GTutorialclass
:
@GTutorialclass💡
💡💡💡💡💡💡💡💡
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💕ለእናንተ እኛ አለን 💕
🎈ትርፋችን የእናንተ ደስታ ነው🎈
🤌🤌🤌🤌🤌🤌🤌🤌🤌
💡📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :
@GTutorialclass💡
👍1
BDU Statistics and probability Mid Exam.pdf
6.3 MB
📚 Bahirdar University.

📚 2014 Statstics and Probability Mid Exam.

📚 Targeted group - 2nd year Engineering students.

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
💭 የካንፓስ የመጀመርያ አመት ቆይታ ......በትንሹ

📚 ፍሬሽማን መሆን እንደእናንተ ስብዕና ይወሰናል ። የተለያየ ሰው የተለያየ experience ነው ያለው ። ግን ብዙዎች ጋር የሚኖረውን የፍሬሾች የጋራ ኑሮ ቆንፅለን ለማየት እንጥራለን ...!


💡 ናፍቆት .....!

📚 አንዳንድ ከቤታቸው ሱቅ ለመላክ ካልሆነ ወጥተው የማያቁ ልጆች ድንገት ከቤተሰብ ሲርቁ ምናምን አይችሉም ይነፋረቃሉ ...ከሰው ጋር የማይግባቡ ዝጋታም ልጆች ስላሉ እነሱም ... ለብቸኝነት ሲጋለጡ ሊከብዳቸው ይችላል ። አንድ ነገር እወቁ ከምትወዷቸው ሰዎች መለየት ይሄ የመጀመርያቹ ሊሆን ይችላል ግን ብርቅ አይደለም ...አቅፎ የሚያስተዛዝን ፤ ህመምን የሚጋራ ደስታን የሚካፈል ጓደኛ ቤተሰብ ወዳጅ መለየት በጣም ከባድ ነገር ነው ። ግን ቻሉት በህይወታችሁ ነፍ ግዜ ከምትወዷቸው የህይወት አጋጣሚ ይለያቹሃል ። ካንፓስም የምታገኟቸው ልጆች ከአመታት ውብ የጓደኝነት ቆይታ በኃላ ትለያያላችሁ ። ናፍቆት ያለ ነው ግን መቻል ነው ። በካንፓስ ጥሩ ጓደኛ ያዙ ...እስክትለምዱት ነው ። ከዛ ይለቃቹሃል ።


💡 ምግብ ....!

📚 እንደ እናትህ ውይ ልጄ ተነስ ቁርስ ብላ ና ትተኛለህ አቡኪያዬ ...ምናምን የለም በጠዋት ተነስተህ ሰልፍ ካልወጣህ ሲሞረሙር ይውላል ካፌ ሊያልቅም ይችላል ....ሻይ በዳቦ ለመብላት ይሄ ያክል ሰልፍ ልትልም ትችላለህ ግን በመክሰስ ሰዓት 12 ስለሆነ ራት የሚገረሰው ችከላ ካደርክ ይሞረሙራል...ዳቦ ራሱ ስንት ጣዕሙ ..ከረሃብ ይሻላል ። ሩዝ ፤ ፍርፍር ...ስላለ አትቸጋገር ....ግን ጥሩ ነገር መብላት የለመደ ሰው....ወይኔ ግቢው ጥሩ ባልቴት የሌለው ይመስል ..ጥቅል ጎመን ብለው ቀጭን ሾርባ ጎመን ጣል ጣል ያለበት ሊያቀርቡ ይችላሉ ...ታዲያ አሪፍ ነገር የለመደ አይችልም 500 ብር አከባቢ ይገጨውና ውጪ ይበላል .... ምግቡ እንደ ካንፓሱ ነው በተለይ በቅርቡ የተከፈቱ አርሲ ፤ ቦንጋ ምናምን ምንም አይልም ባህርዳርም አሪፍ ነው ። ሃሮማያማ በሳምንት አራቴ ነው ስጋ የምትግጡት ...ብቻ ብዙ ልጆች የጣፈጠ ነገር ለምደው እነደ ነገሩ የሚሰራው ምግብ አይጥማቸውም ።



💡 ጓደኛ መረጣ ...!

"ጓደኛ መረጣ ላይ መጠንቀቅ አለባችሁ ። በጣም መጥፎ ሰዎችም ጥሩ ልጆችም ይኖራሉ ። ከሱሰኛ ፤ ጨባሽ ፤ ዘረኛ ..ራቁ..በቢሊዮን ማይል ራቁ ...ከእናንተ ጋር የሚሄድ ሰው ፈልጋችሁ ከዶርም ውስጥ አንድ የልብ ጓደኛ በቂ ነው ። ታዲያ ምንም መጥፍ ባህሪይ ቢኖርባቸው ከዶርም ልጅ አትጣሉ ...ትቸገራላችሁ ተንከባክባችሁ ....ተከባብራችሁ በፍቅር አርጉት ...ጓደኛ ምርጫችሁን ተጠንቀቁ ዝም ብሎ ሲያነብ የሚውል የሚተሽንም ሰው አትጠጉ በቃ አራዳ ሆናችሁ ማንበብ ሲኖርበት የሚያነብ ፈታ ግድ ሲል የሚፍታታ ነገሮች የሚገቡ ምርጥዬ ሰው ፈልጉ ።


💡 ሱስ....

📚 በዙ ሰዎች ካንፓስ በጓደኛ ምክንያት ያልሆነ ነገር ውስጥ ይገባሉ ይሄ መሆን የለበትም ...ምንም ቢሆን ሱስ አለም እንዳትገቡ ...ያለባችሁ ችግር ይበቃል ... አንዳንዴ ግዜ ሊተርፋችሁ የምትሰሩት ታጡም ይሆናል ...ሱስ ከምትገቡ አንዷን/ዱን ጠብሳቹሁ ተጃጃሉ እሱ ይሻላል ... ጭራሽ ሱሰ ውስጥ ራሳችሁን እንዳታገኙ በርቱ ....!




💡 መወዛገብ ......!

📚 ከጠበቃችሁ በጣም የተለየ ነገር ሊገጥማችሁ ይችላል ....ያኔ ውዝግብግብ የተለመደ ነው ።ተሳስታችሁ የሰው ዶርም ከች ትሉም ይሆናል ።ብዙ ግዜ ልጆች እስኪለምዱ ድረስ እንዳይጠፋባቸው አንዴ ባዮት መንገድ ብቻ ነው የሚጓዙት ....ሌላ አጭር መንገድ ቢኖርም አይሄዱም በረጅመ ይሄዳሉ የፍሬሽ ነገር የተለመደ ነው ። በቃ በየስርቻው ሲዋሰቡ ፤ ትምህርት ብሎ መጥቶ አባቱን በሬ አሽጦ ፤ እናቱን ፆም አሳድሮ እሱ ጫት ቤት ፤ ቅምቀማ ስታዮት (2 or 3 ተማሪ እንዳይመስሏቹሁ ወደ ግማሽ የሚጠጋው ተማሪ .)...በቃ ላይብረሪው ውስጥ 3 ሰው ብቻ ስታዮ ....ትደነግጣላችሁ ወይኔ ካንፓስ ልትሉም ትችላላችሁ ...!ለምግብ ሰልፍ ስታዮ ..ዋይፋይ ሰዎች ለሊት ሙሉ ሲጠቀሙ ስታዮ....በቃ ትወዛገባላችሁ ...ትምህርት ቤት ያላችሁ መሆኑ ትዝ የሚላችሁ ...የፈተና ሰሞን ነው ላይብረሪ 3 የነበረው ሰው መቀመጫ አጥቶ አንድ ወንበር ለሁለት ተቀምጦ ስታዮ ...ዶርም አዳር ሲቸከል ስታዮ ይገባቹሃል ።



💡 የአስተማመር አይነት ....!.

📚 እንደ Highschol 40 ደቂቃ ሳይሆን 3 ሰዓት ሙሉ አንድ ሳብጀክት ትዳረቃላችሁ .....እሱም ደህና መመህር ካጋጠማችሁ ነው የሚገባችሁ ። በቃሉ እየተጀነነ ሲያወራ የሚውል.... ኖት የሚቸከችክ ...ደብተር ሁላ የሚያርም አለ ። የለመዳችሁት አይነት ...የመማር ማስተማር ሂደት ሲቀየር አትደናገጡ እንደ አየሩ መሆን ነው ። እስከትለምዱት ነው ።



💡 ወሲብ.......!


📚 ወሲብ ከባድ ነገር ነው ። እንኳን እንዲሁ ተለቃችሁ ወትሮም ....የporno ቪዲዮ ይታየዋል ለጉድ በቃ ። ሱሰኞች ካጋጠማችሁማ ዶርም ላይ ...በቃ ላይብረሪ ሁላ ወሲብ ይፈፀማል ......በጣም አስጠሊ ነገር ነው ። ይሄ አይወራ እዛው እዮት .....


💡 ሙድ መያዝ .....❗️

📚 ፍሬሾች ገና ከመግባታችሁ ...የሲኒየሪዎች ነቆራ አይጣል በቃ ምንም ስለማታውቁ ...የማይሆ ነገር ሊነግራቹሁ ይችላል የመመዝገቢ ቦታ ጠይቃችሁ ሽንት ቤት ሊሊሉካችሁ ይችላሉ ። ግን አይደብራችሁ እናንተም በተራቹሁ አየር ስለምትይዙ ....ፈታ በሉበት እስክትለምዱ አየር አታብዙ አትኳትኑ ልጎብኝ እያላችሁ አታካሉ ወሬ ሰብስቡ መጀመርያ ። የመጀመርያ ምግብ ካፌ ማሰታወሻ ፎቶ አንሱት ።

📚 ሁሉንም አውርተን አንጨርሰውም ....በቃ የቀረ ካለ ግቢ ታዮታላችሁ ፥ ብዙ አትጨናነቁ እኛም አለን አዳዲስ ነገር እንነግራቹሃለን ። አይዞን ..! ከዘካንፓስ ጋር ትወጡታላችሁ ...!

© Source - 📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass.

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass