G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።

በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።

ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@GTutorialclass 
Let’s be the positive influence in our world!
Stay Safe
Channel name was changed to «Tutorial class for all student✍️✍️»
የት/ት ሚኒስቴር ቅሌት‼️‼️
ከ140 ወደ 601።።
ለትውልድ የምትቆረቆሩ ሼር አድርጉት‼️
~~~~
ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ቲሊሊ የአንድ ተማሪ ውጤት 140 ሆኖ ይመጣል፡፡ተማሪው በጣም ጎበዝ ስለነበረ ከተማሪው በላይ መምህሮቹ በተማሪው ውጤት ይበሳጫሉ፡፡ምክንያቱ ልጁን ጠቅቀው ያውቁታልና፡፡እናም መምህሮቹ ተቆጪተው ብቻ አልቀሩም፣ወደ ትምህርት ሚኒስቴር አቤት አሉ፡፡ት/ት ሚኒስቴርም ጫናውና ግፊቱ ሲበረታበት የተማሪውን ውጤት እንደገና ለማየት ተገደደ፡፡ፈተናው ድጋሜ ሲታረም የተማሪው ውጤት ከ140 ወደ 601 ተተኮሰ፡፡አስቡት በዚህ አይነት መንገድ ስንቱን ባለራዕይ ወጣት አምክነውት እንደሚቀሩ፡፡መምህሮቹ ግፊት ባያደርጉ ኑሮ የዚህ ልጅ እጣፋንታ ምን ይሆን ነበር? ሲያጠቁር ተሳስቶ ነው ተብሎ አልባሌ ቦታ ወድቆ ይቀር ነበር፡፡
እነዚህ ጉደኞች የስንቱን ህልም አቀጪጨው እንዳስቀሩት ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡እንገዲህ እነዚህ ናቸው ለትምህርት ጥራት በሚል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህራን የብቃት ፈተና እንፈትናለን የሚሉት?

@GTutorialclass. 🤳

መጋቢት 5/2014 ዓ.ም
========================
ትምህርት ሚኒስቴር ላይ የተማረ የሰው ሀይል አለመኖር ስራዎችን በዕቅድ ና በስሌት ከማከናወን ይልቅ በግዴለሽለት ማከናወን ና መርህ አልባነት መሆን መዘዙ👇

"‼️ ትውልድ ‼️
-----------------------
ትምህርት ሚንስቴር የ 2013/14 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ላይ #በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግፍ ነው የሰራው።

1- ገና ሲጀመር የ10ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና ያለ ምንም #ስርቆት ከተጠናቀቀ በሗላ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ማለፊያውን በጣም ዝቅ በማድረግ ወዳቂውን ተማሪ እንደገፍ ማሳለፍ።

2- በ11ኛ ክፍል የት/ት ዘመን 2012 በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ 2ኛው ሴሚስተር #ሳይማሩ ቀርቷል፣ እንዲሁ ተማሪዋቹ ከ8 ወር በላይ ያለ ት/ት ቤታቸው እንዲቀመጡ ተደርጓል። እናም ተማሪዎች በ2013 አ/ም የ11ኛ ክፍልን #ሳይጨርሱ 12ኛ ክፍል እንዲገቡ ተደረገ።

4- ከዛም የመንግስት ት/ት ቤት ተማሪዎች 12ኛ ክፍልን ሲማሩ ግን እንደድሮው በተከታታይ ቀናት አልነበረም፤ በሳምንት #ሶስት ቀናት ነበር የተማሩት፣ በተመሳሳይ የግል ት/ት ቤቶች ግን #ሙሉ ሳምንቱን አንድም ቀን ሳይዘሉ ነበር ሲያስተምሩ የከረሙት።

5- ይህ ታድያ ለአብዛኞቹ የመንግስት ት/ት ቤቶች መፅሀፍትን ለመጨረስ #በቂ ጊዜ አልነበረም። በግል ት/ት ቤቶች ግን መፅሀፍትን በተያዘላችው ጊዜ መጨረስ ችለዋል።

6- በተለይ ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የ #Economics ት/ት ብዙ ወራትን በምንበብ ቢያሳልፉም በመጨረሻ ልፋታቸው #ከንቱ ሆኗል።

6- እንዲሁም በ2013 በተቀሰቀሰው ጦርነት፥ በጦርነት አካባቢዎች የነበሩ #ተማሪዎች ለጥናት እና ለመማር ማስተማር አስችጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነበር ያሳለፉት።

እንደ ከዚ በፊቱ መንግስት የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት #የኢንትርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ይዘጋል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ነገር ግን አገልግሎቱ በ #VPN እንዲሰራ ተደርጎ ነበር።

ፈተናዎቹ ሲሰጡ በነበረው መጭበርበር ሙሉ በሚባል ደረጃ ፈተናዎቹ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረገፃች #ተለቀቁ
ላንብብ ብሎ ደብተሩን የያዘው ተማሪ እንደ ጅል ጥናቱን ትቶ ስልኩን ይዞ የነበረው እንደ ብልህ ነው የታየው። ፈተናዎች በ #Telegram #tiktok... በስርአት በቀይ እስብርቶ መልሳቸው ተከቦበት ነበር የወጡት። ከዚህም ባለፈ ፈተናዎቹ ከባድ ነበሩ የመንግስት ተማሪዎች በፍፁም #ያልተማሯቸው የ 11ኛ ክፍል 2ኛ ሴሚስተር እና እና የ12ኛ ክፍል ጥያቄዎች ተካተውበት ነበር።

ታድያ ይህን ሁሉ በመረዳት መንግስት ተማሪዎችን መርዳትና መደገፍ ሲገባው ጭራሽ ማለፊያው ታይቶ #በታሪክ የማይታዋቅ ሆኗል።
ከዚህም ይባስ ተብሎ በመጨረሻ ቀን የተሰጠው #የCIVIC ፈተና በቀን ብዛት ወሬው ደርሶት ከተለቀቀው የሰራው ምስኪኑ ተማሪ ስለበዛ #የCIVIC ፈተና እንዳይያዝ ተደረገ።
ማለትም ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ #600 እንዲያዝ ፤ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ #500 እንዲያዝ ሆነ።

አስተውሉ👇
ማለፊያ ለወንድ በ ተፈጥሮ ሳይንስ #363

ይህ ማለት ፈተናው ከ 700 የሚያዝ ቢሆን ማለፊያ #423 ሊሆን ነው ማለት ነው።

ከዚ በፊት የሚታወቀው የግል ሴክተሩ በደንብ እንዲሰራበት ማለፊያ ዝቅ ሲደረግ ነበር ባሁኑ ግን እንዲያውም #300 ሆኗል።
#የደሀ ልጅ ጎዳና ላይ ይውደቅ የሚል ውሳኔ ተላልፏል። ከአንድ ት/ት ቤት እንዴት ሁሉም ተማሪ ይወድቃል? በአሁኑ የታየው እንግዲ ይሄው ነው ከአንድ ት/ት ቤት አንድም ሰው ማለፍ ያልቻሉባቸው ብዙ የ መንግስት ት/ት ቤቶች ናቸው።

ተማሪ እንዳይማር የሚደረግበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

@GTUTORIALCLASS