Forwarded from ETHIO-MEREJA®
በመቐለ ከተማ ጁንታው ቀብሮት የነበረ 13 የነዳጅ ታንከር ተገኘ!
በመቐለ ከተማ ልዩ ስሙ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጁንታው ለጦርነት ዓላማ ሊያውለው በድብቅ ቀብሮት የነበረ 13 የነዳጅ ታንከር ተገኘ። በታንከሩም ከ200 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ መገኘቱ ታውቋል።
በመከላከያ ሰራዊት የ25ኛ ፈንቅል ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ ምክትል ኦፕሬሽናል አዛዥ ሻምበል ዮሐንስ ማቲዎስ እንዳስታወቁት ጁንታው ለጦርነት ዓላማ አስቦ በድብቅ ቀብሮት የነበረው 13 የነዳጅ ታንከር በመከላከያ ሰራዊቱ አሰሳ በቁጥጥር ውሏል፡፡ በታንከሩም ከ200 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡ ጁንታው የትግራይ ህዝብ በነዳጅ እጥረት እንዲቸገር በማድረግ ዘርፎ ለራሱ እኩይ አላማ ቀብሮት ቆይቷል።
ሆኖም ጥቅመኛው ሃይል የደበቀው ታንከር እንዲገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ አስተዋኦ አድርጓል ብለዋል። በአካባቢው ተቀብሮ ለነዳጅ ማጠራቀሚያ ሊውል የነበረ ተጨማሪ ዘጠኝ ታንከር መገኘቱንም ሻምበል ዮሐንስ ገልጸዋል፡፡ የህወሓት ጁንታ ለራሱ ጥቅም ብቻ የቆመ የህዝብ ጠላት መሆኑን የሚያረጋግጡ የተለያዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች እየተገኙ ስለመሆኑም አብራርተዋል። በመቐለና በተደረገው አሰሳ ለህገ ወጥ ተግባር ሊውሉ የነበሩ ቁሳቁሶች መያዛቸውንም መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot

Forwarded from መርጌታ እፅዉብ
በዛሬው እለት የመግቢያ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች:-
1.አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ
መግቢያ ቀን:- ታህሳስ 15,16
2.ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ
መግቢያ ቀን:- ታህሳስ 15,16
3.ጂንካ ዩኒቨርስቲ
መግቢያ ቀን:- ታህሳስ 17,18 (እየተጣራ ነው)
4.ወለጋ ዩኒቨርስቲ
መግቢያ ቀን:- ለመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ታህሳስ 16,18 - ለሁለተኛ አመት እና ከዚያ በላይ ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 2
5.አስሳ ዩኒቨርስቲ
መግቢያ ቀን:- ለመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ጥር 15,16 - ለሁለተኛ አመት እና ከዚያ በላይ ከታህሳስ 19,20
6.ወልዲያ ዩኒቨርስቲ
መግቢያ ቀን:- ታህሳስ 19,20
@Timhrtministers

Forwarded from ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
በቡራዩ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ 10 ሚሊየን ብር የሆነ ንብረት ወደመ‼️
በቡራዩ ከተማ ትናንት ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ 10 ሚሊየን ብር የሆነ ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
አደጋው የደረሰው በቡራዩ ከተማ ገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ልዩ ስሙ ገብርኤል በሚባል አካባቢ ሲሆን በ16 ሱቆች፣ በ3 መኖሪያ ቤቶችና 3 ባርና ሬስቶራንቶች ላይ ቃጠሎ ደርሷል።
የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በአገዳው 10 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።
“እሳቱ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያስከተል በመቆጣጠር 25 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል” ብለዋል።
በአደጋው በሰው ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ ጠቁመው፤ እሳቱን ለመቆጣጠር ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ ጊዜ መውሰዱን ተናግረዋል።
እሳቱን በማጥፋት የኮሚሽኑ ሰራተኞች፣ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አካላትና የአካባቢው ነዋሪዎች መሳተፋቸውንም ገልጸዋል።
የአደጋው መንስዔ ገና እየተጣራ ሲሆን ህብረተሰቡ ለእሳት አደጋ መንስዔ ከሆኑ ተቀጣጣይ ነገሮች እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።
@Esat_tv1

Forwarded from Free Education Ethiopia ︎
📌ታዳጊው የቀዶ ህክምና በተደረገለት ማግስት በሆስፒታል ሆኖ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ወሰደ!
በዲላ ከተማ የሚኖር ታዳጊ የቀዶ ህክምና በተደረገለት ማግስት በሆስፒታል አልጋው ላይ ሆኖ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ወስዷል።
ታዳጊው በዲላ ከተማ ታህሳስ 6 ቀን 2013ዓ.ም. ምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ አንድ ቦታ ደርሰን እንመጣለን ብሎ ከቤት ይዞት የወጣው የእንጀራ አባቱ በስለት ወግቶ ጉዳት ያደርስበታል።
በማግስቱ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመቀበል በዝግጅት ላይ የነበረው ታዳጊ አዲሱ ገብረሚካኤል በወቅቱ ባሰማው የይድረሱልኝ ጩኸት በአካባቢው የነበረ አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል ሆስፒታል ያደርሰዋል።
"ለፈተናው ስዓታት በቀሩበት ማግስት በተፈጸመብኝ ጥቃት ድንጋጤ ውስጥ ብገባም ቀደም ብዬ በቂ ዝግጅት በማድረጌ በሆስፒታል አልጋዬ ላይ ሆኜ ለመፈተን ባቀረብኩት ጥያቄ ተፈቅዶልኝ ተፈትኛለሁ በዚህም ጥሩ ውጤት እንደማመጣ እርግጠኛ ነኝ" ሲል ተማሪ አዲሱ ለኢዜአ ተናግሯል።
ታዳጊው ከታህሳስ 7/2013ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የተሰጠውን የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በብቃት ውስዶ ዛሬ ረፋዱ ላይ ማጠናቀቁን ፈታኝ መምህሩ ተናግረዋል።
ተማሪ አዲሱ በቀጣይ ቀናት ሶስተኛ የቀዶ ህክምና ተደርጎለት በጤናው ላይ መሻሻል ካሳየ ከሆስፒታል እንደሚወጣ ተገልጿል። ጥቃት ያደረሰበት ተጠርጣሪም በቁጥጥር ስር መዋሉን ፓሊስ ገልጿል።
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!

Forwarded from Abel Birhanu የወይኗ ልጅ
የ4 አመት ህፃን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱ ተገለፀ!
በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ዙሪያ ወረዳ የ4 አመት ህፃን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የወረዳው ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።
ተከሳሽ ''በስካር መንፈስ ተነሳስቼ ወንጀሉን ፈፅሚያለሁ ጥፋተኛ ነኝ'' ሲል ለፍርድ ቤት ቃሉን ሰጥቷል። ታህሳስ 8 የዋለው ችሎትም ተከሳሹን በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ዙሪያ ወረዳ የ4 አመት ህፃን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የወረዳው ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።
ተከሳሽ ''በስካር መንፈስ ተነሳስቼ ወንጀሉን ፈፅሚያለሁ ጥፋተኛ ነኝ'' ሲል ለፍርድ ቤት ቃሉን ሰጥቷል። ታህሳስ 8 የዋለው ችሎትም ተከሳሹን በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
Forwarded from ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አና አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በውጭ ቋንቋዎች ከሚጽፉ የ‘ሜይንስትሪም’ ሚዲያ ባለሙያዎችና የማህበረሰብ አንቂዎች ጋር ተወያዩ‼️
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታና የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ቃልአቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው ዕለት በእንግሊዝኛ፣ በአረብኛ፣ በፈረንሳይኛ እና በአገር ውስጥ ቋንቋዎች በ‘ሜይንስትሪም’ ሚዲያ እና በድረ ገጽ ከሚጽፉ ተንታኞች እና ከማህበረሰብ አንቂዎች ጋር በወቅታዊ እና ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደር ሬድዋን በውይይቱ ወቅት ካተኮሩባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል በአገሪቱ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ፣ ከታችኞቹ የአባይ ተፋሰስ አገራት ጋር በታላቁ የኢትዮጵያ ህሳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ለበርካታ ዓመታት ሲደረግ የቆየው የሶስትዮሽ ድርድር እና አገራቱ በድርድሩ ላይ የሚከተሉት አቋም ጂኦፖለቲካዊ አንደምታ፣ በአገሪቱ እየተተገበረ ያለው ሪፎርምና በሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም ከተግዳሮቶቹ ጀርባ ያለው ድብቅ ሚስጢር ይገኙባቸዋል።
በእነዚህ ዋና ዋና ጉዳዮች ምክንያት በአገሪቱ ላይ የሚደርሰውን አሉታዊ ተጽኖ ለመመከት ከዜጎች የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፣ በተለይ የማህበረሰብ አንቂዎች አገራዊ ፈተናዎችን ለመሻገርና አና መግባባትን ለመፍጠር ያላቸውን ከፍተኛ ሚና ተገንዝበው ከትናንሽ አጃንዳዎች እየወጡ በዋና ዋና አገራዊ አጃንዳዎች ላይ በማተኮር የማህበረሰቦችን አብሮነት ማጠናከር እና የባዕዳንን እኩይ አጃንዳዎች ማክሸፍ እንዳለባቸው በአጽንኖት ተናግረዋል።
አቶ ሬድዋን አክለውም የማህበረሰብ አንቂዎች መንግሥት ነቅቶ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማገዝ፣ የአገር ብሄራዊ ጥቅሞች እንዲከበሩ ማድረግ እንዲሁም በህዝቦች መካከል የአብሮነትና የወንድማማችነት መንፈስ እንዲጎለብት ማስቻል አለባቸው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የትግራይ ህዝብ የጁንታውን ርዝራዦች አሳልፎ ሊሰጥ ይገባል- ዶ/ር አረጋዊ በርሄ
መንግስት የጁንታውን ርዝራዦች የትግራይ ህዝብ አሳልፎ እንዲሰጥ ያቀረበውን ጥሪ በደስታ በመቀበል ለራሱ ሰላም እና ደህንነት ሲል አሳልፎ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ገለጹ፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ከዋልታ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ በሀገር ላይ ክህደት የፈጸመው ጁንታ ከምንም እና ከማንም በላይ ሲጨቁነው እና ሲዘርፈው የኖረው የትግራይን ህዝብ ነው፡፡
በትግራይ ክልል የነበሩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህገ መንግስቱ በሚፈቅድላቸው መንገድ በክልሉ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ ጽንፈኛው የትህነግ ቡድን አፈና ሲያደርግባቸው መቆየቱን የገለጹት ዶ/ር አረጋዊ፣ አሁን ላይ ግን ምቹ መደላድል ይፈጠራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
የትግራይ ተወላጅ የሆኑት አቶ ዮሃንስ ሃይሉ በበኩላቸው፣ አስፈላጊ በሆነው መንገድ ሁሉ በክልሉ ከተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸው፣ የህወሓት ጁንታው ቡድን ላለፉት ረጂም አመታት ሲጨቁነው ከቆየው ህዝብ ውስጥ ተሸሽጎ እንዳለና ይህን ጁንታ በማጋለጥ የትግራይ ህዝብ አኩሪ ታሪክ ሊሰራ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደሩ እያከናወነ ያለው ስራ የሚደነቅ እንደሆነና በቀጣይም ጠንከር ያሉ የቤት ስራዎች የሚጠብቅ በመሆኑ እያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጎን ሊቆም እንደሚገባም ጠይቀዋል፡፡መንግስት በክልሉ ያቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደርም ህበረተሰቡን በማወያየት ስራውን የጀመረ ሲሆን፣ በራስ ወዳዱ ጁንታው ቡድን የተበላሸውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለማስተካከል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

በልደታ ክ/ከተማ ስልጤ መስኪድ ጀርባ በፈነዳ ቦንብ የሰው ህይወት አለፈ ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ በፈነዳ ቦንብ የሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ዛሬ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ተኩል በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦንብ ጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአምስት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ ገልጿል።
በኮሚሽኑ የልዩ ልዩና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ያለው የምርመራ ሂደት እየተጣራ መሆኑን ገልፀው፤ የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህብረተሰቡ ግልጽ ይደረጋል ነው ያሉት።
በተለያዩ ቦታዎች እንደ አልባሌ በሚጣሉ ቦንቦችና ፈንጂዎች ንፁሀን ሰለባ መሆናቸውን አስታውሰው ያሰታወሱት ዳይሬክተሩ፤ ህብረተሰቡ ምንነታቸው ያልታወቁ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ከመነካካት በመቆጠብ ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጥቆማ ማድረግ እንደሚገባ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ኢትዮጵያ ለወሰደችው ሕግ የማስከበር ተግባር ሕጋዊነት እውቅና በመስጠታቸው አመሰገኑ!
የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ኢትዮጵያ ለወሰደችው ሕግ የማስከበር ተግባር ሕጋዊነት በመረዳታቸው እና እውቅና በመስጠታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመሰገኑ።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ 38ኛ አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በጅቡቲ ተካሂዷል። በዚህ ጉባኤም የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለፃቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገፃቸው አስታውቀዋል።
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ኢትዮጵያ ለወሰደችው ሕግ የማስከበር ተግባር ሕጋዊነት በመረዳታቸው እና እውቅና በመስጠታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመሰገኑ።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ 38ኛ አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በጅቡቲ ተካሂዷል። በዚህ ጉባኤም የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለፃቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገፃቸው አስታውቀዋል።
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
Forwarded from ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
በውጭ ሀገራት እየኖሩ የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ተጠርጣሪዎች ከኢንተር ፖል ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ለማዋል ይሰራል-የፌደራል ፖሊስ‼️
በውጭ ሀገራት እየኖሩ ከጁንታው ጋር ተባባሪ በመሆናቸው የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ተጠርጣሪዎች ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚሰራ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። በፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል መላኩ ፋንታ ዛሬ በመቐለ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። ምክትል…
@Esat_tv1
@Esat_tv1
በውጭ ሀገራት እየኖሩ ከጁንታው ጋር ተባባሪ በመሆናቸው የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ተጠርጣሪዎች ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚሰራ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። በፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል መላኩ ፋንታ ዛሬ በመቐለ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። ምክትል…
@Esat_tv1
@Esat_tv1
Forwarded from ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
በአማራ ክልል የ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው‼️
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡
ክልል አቀፍ ፈተናው በ5 ሽህ 162 የፈተና ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ከትምህርት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
የፈተና ቁሳቁሶች ተሟልተው ክልል አቀፍ ፈተናው እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ገልፀዋል፡፡
ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው የፀጥታ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል፡፡
በመደበኛ፣ የማታ እና የግል ተፈታኞችን ጨምሮ ከ415 ሽህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ መገለጹን አብመድ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Forwarded from ቅናሽ ገበያ /DISCOUNT MARKET
#Ethiopia : የመተከል ጉዳይ የውጪ ሀይለኝኛ እጅ ሳይኖርበት አይቀርም:: ትናት በዶሊ ቀበሌ ቁጥራቸው 300 የሚሆኑ የተደራጁ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎች ላይ በወሰዱት ጥቃት የመከላክያ ሰራዊት አባልን ጨምሮ ስድስት ሰው መሞቱ ታውቋል:: የቲክቫህ አባላት መረጃን ከስፍርው እንዳደረሱት መከላክያ ገብቶ እርምጃ ባይወስድ የተደራጁት ታጣቂዎች ብዙ ሰው ይገሉ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል::
Forwarded from ቅናሽ ገበያ /DISCOUNT MARKET
በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ 100 ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ!
#Ethiopia : በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት ከንጋቱ 11:00 ሰዓት አካባቢ ለውጥን በማይፈልጉ አማጺያን የበርካታ ሰዎች ሞት እና ንብረት መውደሙን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አዛዥ ኮሎኔል አያሌው በየነ ተናግረዋል።
ቀጠናውን በበላይነት የሚመራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአጥፊዎች ላይ በወሰደው እርምጃም 42 ጸረ ሰላም ሃይሎች መደምሰሳቸውን ኮሎኔል አያሌው ገልጸዋል። 7 የሚደርሱ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል።
ምንጭ:- የዞኑ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ
#Ethiopia : በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት ከንጋቱ 11:00 ሰዓት አካባቢ ለውጥን በማይፈልጉ አማጺያን የበርካታ ሰዎች ሞት እና ንብረት መውደሙን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አዛዥ ኮሎኔል አያሌው በየነ ተናግረዋል።
ቀጠናውን በበላይነት የሚመራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአጥፊዎች ላይ በወሰደው እርምጃም 42 ጸረ ሰላም ሃይሎች መደምሰሳቸውን ኮሎኔል አያሌው ገልጸዋል። 7 የሚደርሱ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል።
ምንጭ:- የዞኑ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ
Forwarded from ቅናሽ ገበያ /DISCOUNT MARKET
የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በመተከል ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱን እንዳረጋገጠ ገለጸ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱን የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ባካሄደው የጥናትና ቁጥጥር ስራ እንዳረጋገጠ ገለጸ።
በመተከል ዞን እየደረሰ ባለው የዜጎች ጭፍጨፋ፣ የንብረት ውድመትና ከቤት መፈናቀል የክልሉ መንግስትና የጸጥታ መዋቅር ድርጊቱን መከላከልና ማስቆም ለምን እንዳልቻሉ ለመመርመርና ለማጥናት ተሞክሯል ብሏል ተቋሙ።
ጉዳዩን የሚመረምር የጥናትና ቁጥጥር ቡድን ወደ አካባቢው በመላክ ባደረገው ጥናትም በዞኑ ማንዱራ፣ ዳንጉር፣ ጉባ፣ ደባጤ፣ ቡለንና ወንበራ ወረዳዎች ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ የተካሄደ መሆኑን እንዳረጋገጠ አመልክቷል።
“እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ163 በላይ ዜጎች ህይወት ያለፈ መሆኑን እንዲሁም ከ31 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን ለመረዳት ተችሏል” ብሏል በመግለጫው።
በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት የክልሉ መንግስት አስተዳደር አካላት፣ የፓርቲ አመራሮችና የጸጥታ መዋቅር አካላት እንደተሳተፉም ጠቁሟል።
ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት የነበራቸው ድጋፍና ክትትል ዝቅተኛ እንደነበር ገልጾ፤ “”ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተል የነበረው የኮማንድ ፖስት ከችግሩ ክብደትና ስፋት አንጻር የሰራው የጸጥታ ማስከበር ስራና በአጥፊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ደካማ እንደነበር የተቋሙ የጥናትና የቁጥጥር ቡድኑ ለይቷል” ብሏል።
በመሆኑም በየትኛውም ደረጃ ላይ ያለ የመንግስት መዋቅር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ቀዳሚ ተግባርና ሃላፊነቱን ተገንዝቦ የዜጎችን ንብረትና ደህንነት በአግባቡ እንዲጠብቅና ዳግም ተመሳሳይ ጉዳት እንዳይደርስ አሳስቧል።
ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመተከል ዞን ከህብረተሰቡ ተወካዮችና ከአመራሮች ጋር ተወያይተው ያስቀመጧቸው አቅጣጫዎች በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆኑ ምክረ ሃሳብ ሰጥቷል።
በተጨማሪም በወንጀል ድርጊቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የነበሩ አካላት በህግ እንዲጠየቁ፣ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድና ለህዝቡም ይፋ እንዲሆን መጠየቁን ተቋሙ ለብስራት በላከው መግላጫ አስታውቋል።
የፌዴራል የጸጥታ መዋቅር አካላት ህጉ በሚፈቅደው መንገድ ከሁሉም ክልሎች የተቀናጀ የጸጥታ ሃይል በማዋቀር በክልሉ ተሰማርቶ የዜጎችን ህይወትና ንብረት ሊታደግ በሚችልበት ቁመና ላይ እንዲገኝ መንግስት ከውሳኔ ላይ እንዲደርስ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።