G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
MORAL UNIT 5 PP.pptx
344.3 KB
@GTutorialclass
ቆንጅዬ short note ነው
እቤት ለመሸምደድማ ልዩ ነው
📃📃📃📃📃📃
ግቢ ውስጥ Grade እንዴት ነው ሚሰራው 🤔

❇️ GPA or CGPA ምን ማለት ነው ላላችሁኝ 😍

ጉድ የማያልቅበት ትምህርት ሚንስተር የሚያወጣው አዲስ ህግ እስካልኖረ ድረስ የሁሉም ግቢዎች grading system ተመሳሳይ ነበር

በእያንዳንዱ ሴሚስተር

Out of 20 or 30% Test, Quizzes , group work or Assignment

Out of 20 or 30 % MID EXAM

Out of 50% Final Exam

ለእያንዳንዱ ኮርስ የሶስቱ ድምር ውጤት ሴሚስተር መጨረሻ ላይ ይደመርና ለጠቅላላ ኮርሶቹ ተካፍሎ ግሬድ ይሰራላቹሃል ።

የስድስቱም ኮርሶች ድምር Garde ከተሰራ በኋላ የምታስመዘግቡት ውጤት የትምህርት መስክ ለመምረጥ ትምህርት ሚኒስተር ባወጣው range ልክ value ይኖረዋል ።

GPA ማለት በሁሉም ሴሚስተር የምታስመዘግቡት ግሬድ ማለት ነው

CGPA ማለት Average Grade ማለት ነው።

🔔 በመጀመሪያው ሴሚስተር የተጠቀሱትን አምስት የትምህርት መስኮች join ለማድረግ የምትፈልጉ ተማሪዎች ለውድድር የሚታየው first semister GPA ብቻ ይሆናል ፤ የተቀሩትን የትምህርት መስኮች join ማድረግ የምትፈልጉ ተማሪዎች ግን የሚያዝላቹህ የሁለቱም ሴሚስተር Average or CGPA ይሆናል ማለት ነው።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር አለ የተባለው ወይም ትላንት Post ያደረኩላቹህ 20% entrance , 30% PRE-FEILD ምናምን የተባለውን ነገር በሁሉም ዩንቨርሲቲዎች ላይ በዚህ ዓመት ተግባራዊ ሆነም አልሆነ የመጀመሪያ ሴሚስተር ግሬድ ግን ማንኛውንም የትምህርት መስክ ለመምረጥ ትልቁን ድርሻ ይይዝላቹሃል ፡ ስለሆነም 20%ቷ እውን ከሆነች entrance exam ስለተበላሸብኝ ብላቹህ ተስፋ አትቁረጡ ፤ ሲጀመር 20% ምናምን የተባለው ጉዳይ የሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ማህተምና የክብርት ሚኒስተሯ ፊርማ ስላረፈበት አስደንግጦኝ Post አደረኩላቹህ እንጂ እስካሁን 100% እርግጠኛ ሆኖ ለማውራት የሚያስደፍር ማረጋገጫ ከበላይ አካላት አልደረሰንም ፤ ትምህርት ሚኒስተርም ተማሪው ሁለት ልብ ሆኖ እየጨለለ ባለበት ባሁኑ ወቅት ምንም አይነት ማስተባበያ አልያም ማረጋገጫ አለመስጠቱ አስከፍቶኛል ።

ለማንኛውም ግን በውስጥ መስመር ብዙ ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ ግሬድ calculation አልገባንም ባላችሁኝ መሰረት ከአራት ወራት በፊት post ያደረኩላችሁን በድጋሚ ለማስታወስ እገደዳለሁ

For instance AAU first semister coursoch እነዚህ ናቸው ብንልና የኮርሶቹም ECTS እንደሚከተለው ቢሆን

♨️Critical thinking...... #5Ects
Psychology........... #5Ects
♨️ General Physics. #5Ects
English .............. #5Ects
♨️Geography ..........#5Ects
♨️Mathematics......# 6Ects
♨️Physical fitness (pass or fail)
Total credit hours #31Ects

ተማሪ አለባቸው ደብድባቸው እርገጣቸው😂 የተባለ ተማሪ በመጀመሪያው ሴሚስተር ያስመዘገበው ውጤት

1) Critical thinking-------> 77 🔫B+
2) Psychology ---------->82 🔫A-
3) Gen' Physics --------->59.9🔫C
4) Mathematics---------->42 🔫D
5) English ------------>68 🔫B-
6) Geography ------------->64 🔫C+

ነው ብንል የተማሪ ሙጃን ግሬድ እንደሚከተለው ማወቅ ይቻላል

በቅደም ተከተል calculate ማድረግ
🔍 Credit hour × grade

5×3.5 =17.5
5×3.75 =18.75
5×2 =8
6×1 =6
5×2.75 =13.75
5×2.5 = 12.5

Total sum=76.5
Semister grade = Total sum÷Total credit hour
76.5÷31=2.467GPA
ስለዚህ ተማሪ ሙጃ በመጀመሪያው ሴሚስተር የሰራው ግሬድ 2.46 ነው ማለት ነው ።


Status of first year students in the first semister ፤ የአንደኛ አመት ተማሪዎች በመጀመሪያው ሴሚስተር የሚያስመዘግቡት ግሬድ እንደሚከተለው ወደ ቀጣዩ ሴሚስተር Pass or Fail ያስብላቸዋል


GPA Status
1.75-4.00 Promoted
1.50-1.75 Warning
1.00-1.50 🔫Academic dismissal( ለአንድ ዓመት ላግ )

0.00-1.00 Complete dismissal ከትምህርት ዓለም ሙሉ በሙሉ ላግ 😤)

ከዚህ ውጭ ደግሞ በአንድ ሴሚስተር ሶስት ኮርሶች የፈሉበት ተማሪ ሴሚስተር ላግ ይኖርበታል ምናምን የሚባልም ነገር አለ ቢሆንም ግን የኛ ቤተሰቦች ሁሉም ለሜዲስን ስለሚቸክሉ F ምናምን እንደማያሳስባቸው ይሰማኛል 😀

ከላይ የጠቀስኩላቹህ የግሬድ አሰራር ካልገባቹህ ደግማቹህ አንብቡትና በድጋሚ ካልገባቹህ ባቅራቢያቹህ የሚገኙ ነባር ተማሪዎችን refer አድርጉ ።


━━━━━━━━━━━━
🎯 Join & Share
@GTutorialclass
🎯 Contact & Ads
@GTutorialclass 👇👇👇
━━━━━━━━━━━━
1