G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
357 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
Channel name was changed to «G Tutorial ይመቻል 👌👌»
Channel name was changed to «Tutorial class with 𝐆𝐞𝐛𝐫𝐞 ይመቻል 👌👌»
📚 Communicative English Skill II.

📚 Unit 2 - Speculation about the Future of Science.

📚 Grammar - Future Tenses.

🙌 እሺ ተወዳጆች ሆይ እንዴት ናችሁ😊unit 2 ላይ እንግዲህ እስካሁን ስለ Present Continuous(Present Progressive) Tense እና ስለ Simple Future Tense ተምረናል። ዛሬ ደግሞ ስለ Going to እንማራለን። በሌላ አባባል የ will እና የ going to ልዩነትን እንመለከታለን ማለት ነው። ፈተና ስለሚወጣበት በደንብ ተረዱት🙏። ዳይ ወደ ክላስ attendance ይያዛል መቅረት አይቻልም😁

📚 Will Vs Going to

🔷 1) Going to is used to express planned future action.(intentions).

🎯 ወደፊት ወይም future ላይ ለሚከናወነው ድርጊት ፡ ዛሬ ላይ ዕቅድ ከወጣለት ወይም program ከተያዘለት፡ ያ ወደ ፊት ለመከናወን ዛሬ ወይም አሁን ላይ ዕቅድ የወጣለትን ድርጊት በ Going to ይገለፃል ማለት ነው። ስለዚህ ሁለት ሀሳቦችን ልንረዳ ይገባል።

🔰 ሀሳብ 1 - ወደፊት ወይም future ላይ የሚከናወነው ድርጊት።

🔰 ሀሳብ 2 - ወደፊት ወይም future ላይ ለሚከናወነው ድርጊት ዕቅድ መውጣቱ ወይም program መያዙ።

🎯 ስለዚህ ወደፊት ለሚከናወነው ድርጊት አሁን ዕቅድ መውጣቱ ወይም program መያዙ ፡ Going to እንድንጠቀም ያስገድደናል። ስለዚህ Going to እና Present Progressive የሚያመሳስላቸው ወይም አንድ የሚያደርጋቸው አገልግሎት አለ። ሁለቱም planned future action ንን ነው የሚገልፁልን።

🌹 Examples 1

📚 ምሳሌ፡ ኮሮና ከጠፉ በሗላ ላሊበላን ለመጎብኘት ዕቅድ ካወጣህ ወይም program ከያዝክ፡

🔰 ሀሳብ 1 - ወደፊት የሚከናወነው ድርጊት ማለትም ኮሮና ከጠፉ በሗላ ላሊበላን መጎብኘት።

🔰 ሀሳብ 2 - ወደፊት ለሚከናወነው ድርጊት ማለትም ላሊበላን ለመጎብኘት አሁን ላይ ዕቅድ ወይም program መያዝህ። ስለዚህ፡

✈️ I am going to visit
Lalibela after corona Virus.

✈️ I am visiting Lalibela after Corona Virus.

📚 ሁለቱም ምሳሌዎች possible ናቸው። ትርጎማቸውም፡ ከኮረና በሗላ ላሊበላን እጎበኛለሁ ማለት ነው።

🌹 Example 2

ለምሳሌ - ክላስ ውላችሁ ወደ ዶርም ስትመለሱ ዶርሙ ቆሽሿል😢🙆‍♀🙆‍♂ኸረ ዶርሙ ቆሽሿል። ነገ ማፅዳት አለብን ብላችሁ ወሰናችሁ ወይም ዕቅድ ያዛችሁ። ስለዚህ ነገ ለማፅዳት ዕቅድ ስለያዛችሁ በ Going to ትገልፁታላችሁ ማለት ነው። ስለዚህ🙇‍♂

🚰🛁 The Dorm is Very dirty. We are going to clean it tommorow.

🔶 2) Going to is used to predict the future on the basis of the present evidence.( predictions based on current circumstance).

🎯 አሁን ላይ(present) ያለውን ተጨባጭ ማስረጃ መሰረት በማድረግ ስለ ወደፊቱ ለመተንበይ Going to ን እንጠቀማለን። ስለዚህ ሁለት ሀሳቦችን እንረዳ😎

🔰 ሀሳብ 1 - ወደፊት(future) ላይ ይከናወናል ወይም አይከናወንም ተብሎ የተተነበየው ድርጊት።

🔰 ሀሳብ 2 - ድርጊቱ ወደፊት(future) ይከናወናል ወይም አይከናወንም ተብሎ ለተተነበየው ድርጊት አሁን(present) ላይ ያለው ተጨባጭ ወይም በቂ ማስረጃ። ስለዚህ😊

🎯 ወደፊት ይከናወናል ወይም አይከናወንም ተብሎ ለተተነበየው ድርጊት አሁን ላይ ያለን ማስረጃን መሰረት አድርጎ ከተነነበዬ፡ ያ ወደፊት(future) ላይ ይከናወናል ወይም አይከናወንም ተብሎ የተነነበዬው ድርጊት በ Going to ይገለፃል ማለት ነው።

🌹 Example 1

አንተና ጓደኛህ walk እያረጋችሁ፡ ከዛ አንተ ወደ ሰማይ ቀና ስትል፡ ዳመናው በጣም ዳምኗል ወይም ጠቁሯል። ከዛ ጓደኛህን ተመልከት፡ የጠቆረውን ደመና፡ ዝናብ ሊዘንብ ነው አልከው። ስለዚህ

🔰 ሀሳብ 1 - ወደፊት ይከናወናል ብለህ የተነበይከው ድርጊት ማለትም ዝናብ ሊዘንብ ነው ብለህ መተንበይህ ወይም predict ማድረግህ።

🔰 ሀሳብ 2 - ዝናብ ሊዘንብ ነው ብለህ ለመተንበይህ አሁን ላይ ያለው ማስረጃ ማለትም ደመናው መጥቆሩ። ስለዚህ😎

🙌ዝናብ ሊዘንብ ነው ብለህ ለመተንበይህ ደመናው መጥቆሩ ማስረጃ ስለሆነ፡ ትንቢትህን በ Going to ትገልፀዋለህ ማለት ነው።

🌧🌨 Look at the dark clouds. It is going to rain.

🌹 Example 2

አንተ ጥሩ ስሜት እየተሰማህ አይደለም። ጥሩ ስሜት ስላልተሰማህ ለጓደኛህ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም ሊያመኝ ነው መሰል አልከው። ስለዚህ፡

🔰 ሀሳብ 1 - ወደፊት ይከናወናል ብለህ የተነበይከው ማለትም መታመምህ።

🔰 ሀሳብ 2 - ልታመም ነው ብለህ ለመተንበይ አሁን ላይ ያለህ ማስረጃ ማለትም ጥሩ ስሜት አለመሰማትህ። ስለዚህ ፡

😣😫 I feel bad. I am going to sick.

🙌 የዛሬውን ክላስ ከመጨረሳችን በፊት የትናንትናው ትምህርት ላይ አንድ የረሳሁት ነገር አለ። ትናንት ስለ Simple future tense ተምረናል አይደል። አንዲት የተረሳች ነገር አለች ሞጁላችሁ ላይ ያለች። እርሷም👇

📚 Simple Future Tense is used to express Future Facts.

🎯 ወደፊት(future) የሚከናወኑ ነባራዊ ዕውነታዎችን በ simple future እንገልፃቸዋለን።

ለምሳሌ አሁን ህዳር ወር ላይ ነን። የሚቀጥለው ወር ደግሞ ታህሳስ ነው። so,

The Next Month will be December.

🙌 የዛሬውን ክላስ በዚህ ጨረስን። ነገ ስለ simple present ተምረን chapter 2 ን እንጨርሳለን። ከዛ ቀጣይ ሳምንት Mid Exam ፈተና ትፈተናላችሁ። ከፍተኛ ውጤት ላመጡ 3 ተማሪዎች ሽልማት ይኖረናል።

📌 መልካም ቀን❗️

©A+ Tutorial Class.
© Your Success is guaranted with A+ Tutorial Class.
Channel name was changed to «Tutorial classu ይመቻል 👌👌»
📚 Addis Ababa University Emerging Technology.

📚 Last year Mid Exam.

📚 Source - ATC

📌 Join and Share 👇👇👇

@kegebregar
Global trends ቀለሜ.pdf
1.1 MB
🌀Global trends የትም ማይገኙ Mid እና final exams ስብስብ።

♻️Share and Support Us.
═══════════════════
Join us 👇👇
🎖📖🎖
━━━━━━
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
▬▬▬▬▬▬▬▬
𝐘𝐞𝐝𝐢𝐫𝐞 𝐦𝐢𝐝 𝐞𝐱𝐚𝐦 𝐛𝐥𝐚𝐜𝐡𝐢𝐡𝐮 𝐥𝐞𝐭𝐞𝐲𝐞𝐤𝐚𝐜𝐡𝐢𝐡𝐮𝐠𝐧 𝐭𝐞𝐦𝐚𝐫𝐢𝐰𝐞𝐜𝐡 𝐥𝐞𝐠𝐳𝐞𝐰 𝐲𝐜𝐡 𝐞𝐲𝐮𝐚𝐭🤔🤔🤔🤔🤔🤔🕶️👓📖📖
📚 Organic Chemistry.

📚 Chapter Three.

📚 Stereochemistry.

🙌 ሰላም የተከበራችሁ የ A+ Tutorial Class ቤተሰቦች😊❗️የ ዛሬው ትምህርታችን Organic Chemistry ነው። ፈተና ላይ ብዙ ጥያቄ ስለሚወጣበት ከ Chaptter 3 እንጀምራለን። መልካም ቆይታ ተወዳጆች ሆይ🙌::

📚 Stereochemistry, a subdiscipline of chemistry, involves the study of the relative spatial arrangement of atoms that form the structure of molecules and their manipulation. 

🎯 Stereochemistry ማለት የ Chemistry ክፍል ሲሆን በዋናነት የሚያጠናው የ molecule ሎችን three dimensional አቀማመጥ ነው። ማለትም molecule ሎች በ x , በ y እና በ z አቅጣጫ የሚኖራቸውን አቀማመጥ ወይም መዋቅር የሚያጠና የ Chemistry ክፍል ነው።

🌹 Stereoisomerism

📚 ታዲያ Stereochemistry ስለ ሞሎኪዩሎች 3D አቀማመጥ በሚያጠናበት ጊዜ በዋናነት የሚያጠናው ስለ stereoisomerism ነው። ታዲያ ለመሆኑ stereoisomerism ምንድን ነው🤔

📚 Stereoisomers are isomers which have the same molecular formula and sequence of bonded atoms (constitution), but differ in the three-dimensional orientations of their atoms in space.

🎯 Stereoisomers ማለት ሁለት molecule ሎች ተመሳሳይ የሆነ molecular formula ኑሯቸው ነገር ግን በእነዚህ ሁለት molecule ሎች ውስጥ የሚገኙት atom ሞች በ x በ y እና በ z አቅጣጫ የተለያየ አቀማመጥ ሲኖራቸው stereoisomers ይባላሉ። ስለዚህ ሶስት ሀሳቦችን እንረዳ😎

🔰 ሀሳብ 1 - ሁለት molecule ሎች አሉን።

🔰 ሀሳብ 2 - ታዲያ ሁለቱም molecule ሎች ተመሳሳይ Molecular Formula አላቸው። ሁለቱም molecule ሎች ተመሳሳይ molecular formula አላቸው ማለት ደግሞ በ ሁሉቱም molecule ሎች ውስጥ የሚገኙት atom ሞች ተመሳሳይ ናቸው እንዲሁም እኩል የ atom መጠንም(ብዛት) አላቸው። ለምሳሌ

🔷 Molecule 1 - CHBrCl
🔷 Molecule 2 - CHBrCl

👆 ሁለቱም molecule ሎች ተመሳሳይ የሆነ molecular formula ነው ያላቸው። ተመሳሳይ Atom እንዲሁም እኩል የ Atom ብዛት ነው ያላቸው።

🔰 ሀሳብ 3 - ታዲያ እነዚህ ተመሳሳይ molecular formula ያላቸው ሁለቱ molecules የተለያየ 3D አቀማመጥ ነው ያላቸው። ማለትም በ ሁለቱ molecule ሎቹ ውስጥ የሚገኙት atom ሞች በ x በ y እና በ z direction የተለያየ አቀማመጥ ነው ያላቸው።

📚 ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ሶስቱን ሀሳቦች መሟላት የሚችሉ ሁለት molecule ሎች Stereoisomers ይባላሉ። ስለ እነሱ የሚያጠናው ሳይንስ ደግሞ Stereoisomerism ይባላል😊

🙌 ምሳሌዎችን ብንመለከት አሪፍ ነበር። ግን በዚህ መፃፍ አስቸጋሪ ነው። ግን እስኪ በቃል ልንገራችሁ። ከላይ ያሉትን molecues(CHBrCl) እንመልከት። ምሳሌ ነው የምናየው stereoisomers ምን እንደሆኑ

🔷 Molecule 1

👉 Carbon ከመሀል ይቀመጣል።
👉 Hydrogen በ x direction ይቀመጣል።
👉 Bromine በ y direction ይቀመጣል።
👉 Chrlorine በ z direction ይቀመጣል።

🔷 Molecule 2

ሁለቱ molecule ሞች stereoisomers ለመባል በ Molecule 2 ውስጥ ያሉት atom የ 3D አቀመማጠቸው ከ molecule 1 ጋ መለያየት አለበት። ምሳሌ

👉Carbon ከመሀል ይቀመጣል።
👉 Hydrogen በ y direction ይቀመጣል።
👉 Bromine በ x direction ይቀመጣል።
👉 Chrlorine በ z direction ይቀመጣል።

አያችሁት አይደል የ Molecule 1 እና Molecule 2 ልዩነት🙌። ምን ይባላሉ stereoisomers ይባላሉ።

📚 ታዲያ የ atom ሞቹን 3D አቀማመጥ መሰረት በማድረግ stereoisomers በሁለት ይከፈላሉ። እነርሱም👇

🎯 Enantiomers(Optical isomers).
🎯 Diastereomers.

🙌 ለዛሬ በዚህ ይብቃን። ግን ለመፃፍ ያስቸግራል😞። Chapter 3 ን ጠቅለል አድርጎ የሚያሳይ Diagram ከታች ለቅቄላችሗለሁ።
📚 CommuniCative English Skill II

📚 Chapter Two.

📚 Speculation the Future of Science.

🙌 በባለፈው ትምህርታችን ስለ Future tense ተምረናል። በተለይም ደግሞ ስለ

👉Present Continuous Tense
👉 Simple Future Tense
👉 Going to Vs Will

ተምረናል። ዛሬ ደግሞ ስለ Simple Present Tense እንማራለን። ብዙዎቻችን የ simple present tense ን ጥቅም እናቀዋለን። በመደበኛነት እኛ ከምናውቀው ባሻገር ሌላ የተለየ ጥቅም አለው። እሱን ነው ዛሬ የምናየው።

📚 Simple Prezent Tense is Used to express time tables and schedules.

📚 Time table and schedule ማለት ከላይ በፎቶ የምታዩት ማለት ነው። አንድን ነገር ወደፊት ለማከናወን ጊዜ ሰሌዳ ካወጣን ያነን ወደፊት የሚከናወነውን ድርጊት በ simple present tense እንገልፀዋለን ማለትነው።

📚 ለምሳሌ Mid Exam ሰኞ ከሆነ የምትጀምሩት። ማለትም ሐሙስ ይጀመራል የሚል የጊዜ ሰሌዳ ስለወጣለት በ simple present tense ይገለፃል ማለት ነው። so

📌 Mid Exam starts on Monday.

📚 ሌላ ምሳሌ ቅዳሜ አያቶቼን እያለሁ ብለህ/ብለሽ እቅድ ካወጣችሁ በ simple present ትገልፁታላችሁ ማለት ነው። ስለዚህ

📌 I visit my grandparents on Saturday.

ስለዚህ ስለ Future Tense ይህን ካየን በቂ ነው። Teacher guide ዱ ስላላችሁ Activity 2.11 ንን check እያደረጋችሁ ስሩት።

📚 ነገር ግን ስለ Future tense ጥያቄ አዘጋጅቼ እለቃለሁ።