G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
የዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ:- (1)

-አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ/ም ተመራቂ፣ የሕክምና (Medicine) 4ኛ እና 5ኛ ዓመት እንዲሁም የሕግ 4ኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ ከኅዳር 24 - 27 እንደሆነ ገልጿል። መደበኛ ትምህርት ኅዳር 28 ይጀምራልም ብሏል።
የዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ:-

- የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች #ብቻ የመግቢያ ቀን ከታህሳስ 1 እና2 መሆኑን ገልጾልናል። ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማያስተናግድ መሆኑንም አስታውቋል።

- የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች #ብቻ ህዳር 29 እና 30 በሁሉም ግቢዎች በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ አስታውቋል።

- የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪ ተመራቂ መደበኛ ተማሪዎች #ብቻ ምዝገባ ህዳር 30 እና ታህሳስ 1 ብቻ መሆኑን ገልጿል። ታህሳስ 2 ትምህርት እንደሚጀምርም አስታውቋል።

- የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የዕጩ ተመራቂ የመደበኛ ተማሪዎች #ብቻ ታህሳስ 5 እና 6 በትምህርት ክፍላቸው ቀርበው ሪፓርት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
-የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመራቂ ተማሪዎቹን የመግቢያ ቀን ታህሳስ 01-02/2013 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል።

- የጋምቤላ ዩኒቨርስቲ በመደበኛው መርኃግብር እጩ ተመራቂ ተማሪዎቹን ከታህሳስ 5- 6 ድረስ በዩኒቨርስቲው በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አድርጓል።

- የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ የተመራቂ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 3 -4 መሆኑን አስታውቋል። ተማሪዎችም በአካል በመገኘት ሪፓርት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

- የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች፣ የሦስተኛ ዓመት የጤና ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች፣ ለክረምት የጤና ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ታህሳስ 3 እና 4 መሆኑን አስታውቋል።

- የሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ለተመራቂ ተማሪዎች መመዝገቢያ ቀን ህዳር 29 - ታህሳስ 1 ሆኗል። ታህሳስ 2 ለተማሪዎች ስለ ኮቪድ 19 ስልጠና ከተሰጠ በኋላ ታህሳስ 5 ትምህርት የሚጀመር ይሆናል።

- የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ምዝገባ ታህሳስ 3 እና 4 እንደሆነ አስታውቋል። ተማሪዎች ሲመጡም የሚታጠብ የፊት መሸፈኛ ማስክ እና ሌሎች ኮቪድ 19ን ለመከላከል የሚያግዙ ነገሮችን እንዲሁም ለዲጂታል መታወቂያ 3x4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ (በሶፍት ኮፒ) መያዝ ይጠበቅባቸዋል ብሏል።

- የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ህዳር 26 ና 27 ግቢ በመገኘት በአካል ሪፖርት እንዲያደርጉ አስታውቋል። ህዳር 28 ለተማሪዎች ስለ ኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ ማስጨበጫ(ኦረንቴሸን) ከተሰጠ በኋላ ህዳር 29 ትምህርት ይጀመራል ብሏል።

- የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ምዝገባ ከህዳር 28 -29 መሆኑን አስታውቋል። ታህሳስ 1 ትምህርት የሚጀመር መሆኑንም ገልጿል።

ETHIOMEREJA - MEDIA CHANNEL
⊰━━━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━━━⊰
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
የዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ:- (2)

-የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች (2 ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ) ዳግም ቅበላ ህዳር 25 እና 26 (አርብ እና ቅዳሜ) ቀን 2013 ዓ/ም እንዲሆን ተወስኗል። ስለዚህ ከላይ በተገለፁት ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲ እንድትገቡ ተብሏል። ትምህርት ህዳር 28/2013 ይጀምራል።

- የጅማ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ተመራቂ ተማሪዎች ምዝገችሁ ህዳር 28 ፣29 እና 30/2013 ዓ/ም ነው። በዚህ ምዝገባ ቀናት የሁሉም ዓመት የትያትር፣ መዚቃ እና ቪዡዋል አርት፣ ነባር PGDT እንዲሁም የ3ኛ ዓመት የባዮሜዲካል እና የ4ኛ ዓመት የማቴሪያል ሳይንስ እና የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባችሁብ እንድትፈፅሙ ተብሏል። የነባር እና አዲስ ድህረ ምርቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ምዝገባችሁን እንድትፈፅሙ ተብሏል።

- የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች ብቻ መግቢያ ቀን ህዳር 26 እስከ ህዳር 28 ነው።

- የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ሐሙስ እና አርብ ማለትም 24 እና 25/03/2013 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል።

- የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ከህዳር 28 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት እንደሚጀምሩ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

- የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎችን
ህዳር 28 -29 የጠራ ሲሆን ትምህርት የሚጀምርበት ቀንም ታህሳስ አንድ መሆኑን አስታውቋል።

- የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ህዳር 25 እና 26/03/2013 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል። ህዳር 28 ትምህርት እንደሚጀመርም ገልጿል።

-የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለተመራቂ ተማሪዎች እና ለጤና ሳይንስ ተማሪዎች (2 ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ የሆናችሁ) ምዝገባ ህዳር 25 እና 26 (አርብ እና ቅዳሜ) ቀን 2013 ዓ/ም መሆኑ ተገልጿል። ጥሪው የጤና ሳይንስ 1ኛ አመት ተማሪዎችን አይመለከትም ተብሏል።

[የሌሎች ዩኒቨርስቲዎች እንደወጡ እናሳውቃለን]

ETHIOMEREJA - MEDIA CHANNEL
⊰━━━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━━━⊰
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
"‹‹ሕወሓት የዘራውን እያጨደ ነው››
ከጊዜ ኋላ ሲራመድ የነበረውና ከስህተቱ ለመማር ያልቻለው ሕወሓት በመጨረሻም የዘራውን መረራ ፍሬ እየሰበሰበ ነው" የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በአልጀዚራ ላይ ባሰፈሩት ሀተታ እንደ ሕወሓት ያሉ ፓርቲዎች የመጨረሻ እጣ ፈንታም ከዚህ እንደማያልፍ ነው የጠቀሱት፡፡

-‹‹በኢትዮጵያ ያለው ግጭት እና የሕወሓት ከመጠን ያለፈ ብሔርተኝነት›› በሚል ርዕስ የወጣው የሙስጠፌ ጽሑፍ፤ ከሕወሓት አፈጣጠር ጀምሮ የነበሩ ብልሽቶችን ዳሷል፡፡
ሕወሓት የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ በጋብቻ፣ በንግድ፣ በሃይማኖትና በባሕል እጅግ የተሳሰረ የመሆኑን እውነታ በመካድ የማይታረቅ ልዩነት እንዳላቸው አድርጎ ሲሰብክ ኖሯል ሲሉ ነው የከሰሱት፡፡

-በዚህም አጥፊና ከፋፋይ የሆነውን ‹‹የእኛ እና እነሱ›› ትርክትን ፈጥሯል ይላሉ፡፡
ሀተታው ሲቀጥል የትግራይ ሕዝብ በጠላት እንደተከበበ አድርጎ በመስበክ በሚያስተዳድራቸው የመገናኛ ብዙኃን በኩልም ተከታታይ የጦርነት ዘጋቢ ፊልሞችን ሲያሳይ ስለመክረሙ አስታውሷል፡፡

-ሕወሓት ራሱን የብሔር፣ ብሔረሰቦች ሰላም ብቸኛ ጠባቂ አድርጎ ሲያስፈራራ መኖሩንም ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ሙስጠፌ ያነሱት፡፡ሕወሓት ለዓመታት በበላይነት ይዞት የነበረውን የማዕከላዊ መንግሥቱን ሥልጣን በ2010 ካጣ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተጀመሩ አገራዊ ማሻሻያዎችን ለመቀልበስ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል ሲልም ጽሑፉ ይነበባል፡፡

-በመላ አገሪቱ ግጭቶችን በተለያዩ መንግዶች ሲደግፍ እንደነበር በመክሰስ፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ኢትዮጵያ ሕግ ወደማስከበሩ ዘመቻ መግባቷንም ያስታውሳል፡፡(አሐዱ ቴሌቪዥን)
@ethio_mereja
🎲 እስካሁን ድረስ ለተመራቂ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች‼️

*ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 21-23
* ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 24 - 25
*አምቦ ዩኒቨርሲቲ ህደር 24 እና 25
*ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 23
*መቱ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 28 እና 29
*ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 25 እና 26
*ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ህዳር 25 እና 26
* ኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ ህዳር 25 ና 26
* ዲላ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 3 እና 4
* ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 3 እና 4
* ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 25 እና 26
* AASTU ህዳር 26 ና 27
* ጅማ የዩኒቨርስቲ ህዳር 28 -30
* ሐረማያ የዩኒቨርስቲ ህዳር 29-ታህሳስ 01
* አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 24-27
* Woldia University ህዳር 30 ና ታህሳስ 1
* ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 29 እና 30
* መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተህሳስ 5 ና 6
* ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ህዳር 26 እስከ 28
* አሶሳ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 03 ና 04
* Mettu University ህደር 28-30
* ሰላሌ ዩንቨርስቲ ህዳር 23


↘️ የሌሎችንም እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል::
@Timhrtministers
@Timhrtministers
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎቹን ታህሳስ 3 ያስመርቃል‼️

↘️ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጫላ ዋታ የተማሪዎች የገጽ ለገጽ የትምህርት ጊዜያቸውን አጠናቀው😂 ፈተና እየወሰዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

↘️ ዩኒቨርሲቲው በሁለተኛ ዙር የሚገቡ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
@Timhrtministers
@Timhrtministers
ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ‼️

🎲ተመራቂ ተማሪዎችና ከ#2ኛ ዓመት በላይ የሆናቹህ የህክምና ተማሪዎች ታህሳስ 1 እና 2 ግቢ ተገኝታቹህ ምዝገባ እንድታከናውኑ ተብላቹሃል።

📌ጥሪ ያልተደረገላችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ለወደፊት ጥሪ የምናደርግላችሁ መሆኑን በማወቅ ተዘጋጅታችሁ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን፡፡
@Timhrtministers
@Timhrtministers
Forwarded from Finance Today
የተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ !

ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ ፦

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በ2012 ዓ. ም ሁለተኛው መንፈቅ አመት የመማር ማስተማር ሂደት ተቋርጦ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ስለሆነም የተቋረጠዉን ትምህርት ለማስቀጠል ፦

1. በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበራችሁ ተማሪዎች ታህሳስ 1 እና 2/2013 ዓ.ም

2. ከተመራቂ ተማሪዎች ውጪ ያላችሁ ነባር ተማሪዎች

በሙሉ ታህሳስ 8 እና 9/2013 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመገኘት ትምህርታችሁን እንድትጀምሩ እየገለፅን በጉዞ ላይም ሆነ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት እና ጤና ሚኒሰቴር ያወጡትን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ መመሪያን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ስለሆነ አስፈላጊዉን የመከላከያ መንገዶች ዝግጅት አድርጋችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
የህወሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበረው ዜና ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት አስታውቋል!!!

የሰቆጣ ወረዳ ኮሙኒኬሽን በመጥቀስ ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ይህ መረጃ ከክልሉ እውቅና ውጪ እንደሆነ እና ያልተረጋገጠ መረጃ መሆኑን ክልሉ አስታውቋል።

በሌላ ዜና የሕወሓት ቡድን አስተባባሪዎችን ለህግ የማቅረብ ሂደቱ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ብልጽግና ፓርቲ በዛሬው እለት ወስኗል። የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሁለት ቀናት ስብሰባውን አጠናቋል፡፡ ምርጫ 2013 በስኬት እንዲጠናቀቅ ጠንካራ ዝግጅት እንዲደረግም ኮሚቴው ወስኗል፡፡
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
በህወሓት የጥፋት ቡድን የታጠቁ ወጣቶች መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ የመቀሌ አገር ሽማግሌዎች ጥሪ አቀረቡ‼️

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር ህዝብ በማወያየት ላይ ይገኛል።

በመቀሌ ከተማ ከጊዜያዊ አስተዳዳሩ ጋር ውይይት ያደረጉት የአገር ሽማግሌዎች ለአገር ህልውና፣ ሰላምና ልማት በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

ያለችን አንዲት አገር ነች፣ ሰላማችንን እውን ማድረግ የምንችለውም እኛው ነን፤ በአንድ አገር ላይ ሁለት የተለያየ የታጠቀ አካል ካለ ደግሞ ችግር ያስከትላል” ብለዋል።

በመሆኑም በህወሓት የጥፋት ቡድን በህገ ወጥ መንገድ የታጠቁ የመቀሌ ወጣቶች መሳሪያቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመከላከያ ሠራዊት እንዲያስረክቡ የአገር ሽመግሌዎች ጠይቀዋል።

የህወሃት ቡድን በጫና በርካታ ወጣቶችን በማስታጠቅ በተለይ በክልሉ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር መስራቱ ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም ገልጸዋል።

የአገር ሽማግሌዎቹ የትግራይ ህዝብ የሚፈልገው ሰላም፣ ልማትና አብሮነትን እንደሆነ ገልጸው፤ የህወሃት ቡድን ወጣቶችን በማስታጠቅ ወደ ግጭትና አለመረጋጋት ማምራቱን አውግዘዋል።

በህገ ወጥ አካል መሳሪያ የታጠቁ ወጣቶች መሳሪያውን በአፋጣኝ ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

መቀሌ ከተማ አሁን ላይ በአንፃራዊነት ሰላምና መረጋጋት እየተስተዋለባት ይገኛል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተቀናጅተው የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ በመቆጣጠር ላይ መሆናቸውም ይታወቃል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
Forwarded from Finance Today
#UPDATE!!

ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የህወሃት ቡድን መሪዎች በእግራቸው መሸሽ ከመጀመራቸው በፊት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ከ40 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪዎች በመከላከያ ሰራዊቱ እጅ ገብተዋል

ቡድኑ ሰራዊቱን መቋቋም ተስኖት ወደ ገጠራማ ስፍራ በእግር መጓዝ ሲጀምር በታጣቂዎቹ በኩል ለማጥቃት ቢሞክርም እንዳልተሳካለት የ32ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ ተናግረዋል።

ፅንፈኛው ቡድን የመንገድ መሰረተ ልማት በሌለበት ከማይጨው 60 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ዴላ ወረዳ ከ40 በላይ የመንግስት እና በርካታ የግል
ተሽከርካሪዎችን ይዞ ለመደበቅ ያደረገው ሙከራም መክሸፉን ነው ኮሎኔል ደጀኔ የተናገሩት።

ተሽከርካሪዎቹን ከፅንፈኛው ቡድን ሀይሎች አስጥሎ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰራዊቱ ባደረገው ፍተሻ በተሽከርካሪዎቹ ውስጥ መታወቂያ እና ፓስፖርቶች ተገኝተዋል።

የተለያዩ ሰነዶቻቸውን ጥለው ከሸሹት መካከል የቀድሞው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ
ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ህይወት ፣ የማይጨው አስተዳዳሪ የነበረው ሀፍቱ ኪሮስ እና ሌሎች የወረዳ አመራር የነበሩ ሰዎች ሰነድ ይገኝበታል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ መሰረት ጌታቸው ረዳ በዴላ በኩል ከሸሸው ቡድን ውስጥ እንደሚገኝበትም ነው ኮሎኔል ፀጋዬ የገለጹት፡፡

በመከላከያ ሰራዊቱ ከተያዙት ተሽከርካሪዎች መካከል ስድስቱ በአሻራ
የሚከፈቱ እጅግ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ አራቱ ለኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ስራ ከፌደራል መንግስቱ ለትግራይ ክልል የተበረከቱ አምቡላንሶች ይገኙበታል።

ፅንፈኛው ቡድን ሲጠቀምባቸው የነበሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች እና ቦቴዎችንም ሰራዊቱ ወደ ማይጨው ከተማ እንዲገቡ አድርጓል ብለዋል።
(ዘገባው የfana ነው)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
#BREAKING_NEWS

በአገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነበሩ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ

በሃገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነበሩ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ መንግስት እና ህዝብ የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ወደ ጐን በመተው መቀመጫቸውን ትግራይ ክልል በማድረግ የህዋሃት ፀረ-ሠላም እና ፀረ-ህዝብ ከሆኑ ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል በጽንፈኝነት አስተሳሰብ በመነሣት በሀይል ወደ ስልጣን የመምጣት ፍላጎትን ካነገቡ ፀረ-ሠላም ሀይሎች ተልዕኮ በመቀበል በሀገር ውስጥ ሌሎችን በማደራጀት ሀገር የመበተን፣ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር እና ህገ-መንግስታዊ ሥርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ መንገድ በመሳተፍ ህዝብ በመንግስት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው በማድረግ በአገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ በተለያዩ የአመራር ደረጃ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል፡-

1) ኮማንደር ሰለሞን አብርሃ ብስራት
2) ኮማንደር ሀይለማርያም ብርሃኔ ገ/ማርያም
3) ም/ኢ/ር ክብሮም ገብሩ ገ/እግዚአብሄር
4) ም/ኢ/ር አረጋዊ ገ/ሂወት አስፋዉ
5) ረ/ኢንስፔክተር ገዛኢ ገ/ሂወት ገ/ስላሴ
6) ረ/ኢንስፔክተር ተስፋ ኪሮስ ግደይ
7) ረ/ኢንስፔክተር አርአያ ገ/አናንያ ኪዳኑ
8)ረ/ኢንስፔክተር ሰለሞን ወላይ ወ/አብዝጊ
9) ዋ/ሳጅን ሀይላይ ወልዱ ገ/ማርያም
10) ዋ/ሳጅን ሀፍቱ ካህሳይ አብርሃ ናቸው።
በመሆኑም መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለይም ደግሞ ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፤ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ የአገራችን የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታው የህዋሃት የጥፋት ቡድን ተፈላጊዎች አባላት አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ተግባር በያላችሁበት የድርሻችሁን እንድትወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ እያቀረበ፤ በቀጣይም የጁንታው ርዝራዥ ቡድን ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራው አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እየገለፀ በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
Forwarded from Finance Today
Forwarded from Finance Today
በደብረፂዮን ቢሮ መውጫ ፊት ለፊት 300 ሜትር እርቀት ያለው በኮንክሪት የተሰራ ማምለጫ ተገኘ::

ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚገኝበት ቢሮ ውስጥ ለውስጥ ከ300 ሜትር በላይ የኮንክሪት ዋሻ ተገኘ!

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቢሮ ውስጥ ለውስጥ ከ300 ሜትር በላይ የኮንክሪት ዋሻ ይህን ይመስላል!

🎬 የምስል ዘገባ 🎬

💰 ፓኬጅ ከገዙ 3.20 ብር 💰

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
ወታደሮችን በሲኖትራክ እስከመጨፍለቅ የዘለቀው የጁንታው የክፋት ጥግ!

ሃምሳ አለቃ ደረጀ አንበሳ በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ የጥገና ባለሙያ ናቸው። በእናት ጡት ነካሾች ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ከምሽቱ አራት ሰዓት ያልታሰበ ጥቃት ተፈጸመባቸውና ያለምንም ጥፋታቸው ተይዘው ለእስር መዳረጋቸውንና ቀላሚኖ እሰርቤት መታሰራቸውን ይገልጻሉ። "ከቀላሚኖ እስር ቤት ወደ አግቤ በመቀጠልም ከትንሽ ቀን በኋላ ወደ ተንቤን መምህራን ኮሌጅ ወሰዱን። የመከላከያ ሠራዊትን የከባድ መሳሪያ ድምፅ ሲሰሙ የ90 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ አስጀመሩን። ልክ 40 ኪሎ ሜትር እንደተጓዝን ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ሲኖ ትራክ መኪና ከኋላችን መጣ። ተጓዡ ወደ 1,200 ሰው ነበር። ከአስፋልት እንድንወጣ ካለመፈቀዱም በላይ ከአስፋልቱ መሀል ከወጣን ልዩ ሀይል ተኩሶ ይመታን ነበር።

ከግራና ከቀኝ ገደላማ የሆነ ጠባብ ቦታ ላይ ስንደርስ ሲኖ ትራክ መኪና ልከው ከኋላችን ነዱብንና የሚገድለውን እየገደለ፣ ያቆሰለውን እያቆሰለ ሄደብን። እኔንም አንድ እግሬን አገኘኝና እግሬ ከተሰበረ በኋላ ተንከባልዬ ጉድጒድ ውስጥ ገባሁ። እዚያው ጉድጓዱ ውስጥ ከተጎዱ ጓደኞቼ ጋር ተኝቼ አደርኩ። ሲኖ ትራኩ ቢያንስ እስከ 50 ሜትር የተጓዘው በሰዎች ላይ ነበር። በዚህም ግማሹ ሞተ፣ ግማሹ ቆሰለ የቀረውም ወደገደል ገባ። እንግዲህ የራሳችን ወገን ነው እንዲህ አይነት በደል የፈፀመብን። ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ድርጊት ነው። ስንት ዓመት ሙሉ አብረናቸው ኖረን በመኪና ሲጨፈልቁን በጣም ነው የተሰማኝ፤ በጥይት ቢገድሉኝ ይሻል ነበር" ይላል::

በወቅቱ ሴቶችም ህፃናትም አብረውን ነበሩ ማን እንደሞተ ማን እንደተረፈ አንኳን አላውቅም ያለው ወታደሩ "በወቅቱ በሕይወት የተረፋትም ተበታተኑ፤ አንዳንዶቹም ቆስለው ወደጫካው ገቡ፤ የሞቱትም እዛው ቀሩ አምስት የምንሆን ሰዎች እዛው አድረን ከሞቱት ሰዎች መሀል በሕይወት ወጣን። የሞቱ ልጆችን እንኳን ለመለየት አልቻልኩም፤ አጠገቤ ነው እየጮሁ የሞቱት፤ ምንም ልረዳቸው አልቻልኩም። በወቅቱ እኔም በሁለት እግሬ መቆም አልችልም ነበርና በጉልበቴ ዳዴ እያልኩ ነው የወጣሁት" ሲል የውቅቱን አሳዛኝ ሁኔታ ይገልፃል:: (ኢፕድ)
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
በማይጨው ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍተሻ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳሪያዎች መገኘታቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ‼️

በማይጨው ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍትሻ ከ426 ሺህ በላይ የክላሽ ጥይት፣ ከ3500 በላይ የብሬን ጥይት፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ክላሽንኮቭና ሽጉጦች፣ ከ1100 በላይ ልዩ ልዩ የእጅ ቦንቦች መያዙን የመከላከያ ሚኒስቴር ለዋልታ በላከው መግለጫ አስታውቀል፡፡በዕዙ የ32ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ብርጌድ ዋና አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል መላኩ ገላነህ እንዳሉት ከሃዲውን ሃይል ለማጥፋት ከተደረገው የህግ ማስከበት ዘመቻ መጠናቀቅ በኋላ በማይጨው ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍተሻ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳሪያዎች መገኘታቸውን አረጋግጠዋል።ከተማዎችን የጦርነት አውድማ ለማድርግና ዜጎችን ለከፋ ችግር ለመዳረግ በማለም ሰራዊት በህግ የሚከለከልባቸው ቦታዎች ተለይተው በእምነት ተቋማት፣ በመማሪያ ክፍሎች፣ በአገልግሎት መስጫ ተቋማትና በመንግስት መስሪያ ቤቶች በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ ተከማችቶ መገኘቱንም ዋና አዛዡ አረጋግጠዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የክለሳ ትምህርት በቴሌቪዥን ይሰጣል - ት/ሚ
*******
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለመከለስ የሚያስችል የቴሌቪዥን ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሚሰራጭ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ፕሮግራሙ ሰባት የትምህርት ዓይነቶችን ማለትም እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስን እንደሚያካትት ተገልጿል፡፡
ፕሮግራሙ ከሰኞ እስከ እሁድ በድግግሞሽ እንደሚተላለፍ የገለፀው ሚኒስቴሩ ወላጆች ለልጆቻቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
የስርጭት የጊዜ ሰሌዳውን ጨምሮ የተዘጋጀውን ፕሮግራም በአማራጭነት በሚከተሉት ማህበራዊ ሚዲያ ማግኘት እንደሚቻልም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
Portal - www.eict.edu.et
YouTube -Educational Plasma Programs Grade 11-12
Telegram - የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን (MOE-TV)
---------------------------------------------------
በዚህ አዲሱ የፌስቡክ ገፅ የተለያዩ አነቃቂ እና ከጉዞ ጋር የተገናኙ ቪዲዮዎችን አጋራቹሀለው በዚህ ሊንክ አዲሱን የፌስቡክ ገፄን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ሁኑ። አመሰግናለሁ
Abel Birhanu የወይኗ ልጅ ❗️
https://www.facebook.com/abelvideo24/
---------------------------------------------------
ክቡራን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየታችሁን የዜና የመረጃ ጥቆማችሁን ከሰር ባለው ሊንክ አድርሱኝ:: አመሰግናለሁ
አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)
👉@abel21bot
Forwarded from Rose
WORK BOOK-ECONOMICS-GRADE-11&12.pdf
738.3 KB
Economics Work Book for Grade 12

ከ2004-2011 ድረስ ያሉትን የማትሪክ ጥያቄዎች በክፍል እና በምእራፍ ከፋፍሎ የተቀመጠ

👌🏾ለማጥናት ይመቻል

Brought to you by
@Free_Education_Ethiopia
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
📷የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚ ሌተናል ኮሎኔል ዶክተር ሎሬት አብይ አህመድ
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰