G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
357 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
እስኪ የተለያዩ ሰዎች ስለ Anthropology ያላቸውን የተሳሳተ መረዳት እንመልከት፣

📌Anthropology is limited to the study of "primitive"👴 societies.
ነገር ግን ይህ ትክክል አይደለም! Anthropology ስለ ጥንት/ስለ ቀደሙት ሰዎች/ነገሮች ብቻ ሳይሆን በአሁን ዘመን ስላሉትም👱‍♂ የሚያጠና ነው!

📌Anthropologists only study the rural people and rural areas.
ነገር ግን ስለ urban Peoples እና ስለ urban areasም ያጠናል [Urban Anthropology].

📌Anthropology is the study/analysis of fossil evidences of the proto-humans like that of Lucy/Dinkeneshe.
ስለ እነዚህም ያጠናል ነገር ግን anthropology ስለ human Evolution ብቻ ነው የሚያጠናው ካልን ስህተት ነው።

እነዚህና የመሳሰሉት ማብራርያቸው ስለ anthropology የተሳሳቱ ናቸው! ድንገት ፈተና ላይ ከመጡ miss ልታረጓቸው አይገባም!👌


UNIT TWO

Human Culture and Ties that Connect

በዚህ Chapter ስር በስፋት የምናየው "The anthropological concept of culture and helps students to increase their understanding the role and impact of culture in human life"


📝What Culture is and What Culture isn't

ምናልባት Culture ማለት ምን ማለት ነው ብትባሉ "ባህል" ልትሉኝ ትችላላችሁ። ባህል ማለትስ ምን ማለት ነው? ብንባል የማንነት መገለጫ😐። ነገር ግን ባህል እንዲህ በቀላሉ አይብራራም!

Alright, Now let's see some best definition about Culture.

📍Culture is a system of learned behavior shared by and transmitted among the members of the group.

በተወሰኑ ሰዎች መካከል የተለመደ፣ እነዚያ የአንድ ቡድን ሰዎች የሚጋሩት የተለመደ ባህሪ ነው ባህል የሚባለው።

📍Culture is a collective heritage learned by individuals and passed from one generation to another.
በሰዎች የተለመደ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ ቅርፅ ነው።


📝Characteristic Features
of Culture

1. Culture Is Learned: Culture is not transmitted genetically rather; it is acquired through the process of learning.

ባህል በዘር አይተላለፍም፣ ነገር ግን በመማር ልታገኙት የምትችሉት ነው።

This process of acquiring culture after we born is called enculturation.
🔖Enculturation is specifically defined as the process by which an individual learns the rules and values of one's Culture.
"ኢንከልቸሬሽን"👌 አንድን ባህል ለመልመድ የምታልፉበት Process ነው። ለምሳሌ፦ ቋንቋውን መልመድ፣ አለባበሱን ማድረግ..

2. Culture Is Shared

ሌላው የCulture Characteristics ይሄ ነው፣ ማለትም Culture Society ውስጥ ባሉት ቢያንስ ሁለት/ሶስት ሰዎች👨‍👩‍👧 የሚጋሩት መሆን አለበት። እንጂ አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ የራሴ የሆነ አለባበስ🥻ና ቋንቋ🗣 አለኝ ስለዚህ የራሴ #Culture አለኝ ማለት ትክክል አይደለም።🙅‍♂

3. Culture is Symbolic

📌ባህል በምልክት ሊገለፅ የሚችል መሆን አለበት፣ ለምሳሌ ሌላ ሀገር ሄዳችሁ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የለበሰ ሰው🇪🇹 ስታዩ በፍጥነት ኢትዮጵያዊ😍 እንደሆነ ትገምታላችሁ!

📌Symbol is something verbal or nonverbal, within a particular language or culture that comes to stand for something else.

4. Culture is All Encompassing

📌Culture is the sum total of human creation: intellectual, technical, artistic, physical, and moral!

ባህል እንደምናስበው ቀላል ነገር እንዳይመስላችሁ👀፣ ስለ አንድ ህዝብ ባህል እያጠናችሁ ነው ማለት፣ ስለዚያ ህዝብ አስተሳሰብ🧠፣ አነጋገር🗣፣ ድርጊት👩‍🚒 እና የመሳሰሉት ነገሮችንም ማጥናት ይኖርባችኋል።

5. Culture is Integrated

Cultures are not haphazard collections of customs and beliefs.
ባህል ቅርፅና መጣጣም ያጣ የትውፊትና የእሴት ውቅር አይደለም። [አማርኛዬ ከበዳቹ አ😁😁]

ለምሳሌ፦ የሰው ልጅ አካል ውስጥ ብዙ System አለአ (Respiratory system, Digestive System, Reproductive...Bio ረሳችሁ😊) እነዚህ አንድ ላይ መጥተው ነው አካላችን ጤነኛ ሚሆነው፣ Cultureም ልክ እንዲሁ ነው😃:- እሴቱ፣ ቋንቋው፣ አለባበሱ ምያምን አንድ ላይ Integrated ሆነው ነው ጤነኛ Culture ሚፈጠረው።

6. Culture Can Be Adaptive and Maladaptive

ይሄ ማለት ለምሳሌ፦ የሰው ልጅ ከTechnology💻 ጋር Adapt ማደረጉ (መልመዱ) በብዙ ጠቅሞታል፣ ነገር ግን ደግሞ በዚያው ልክ ብዙ Side effect አለው።[Maladpativeness]

Cultureም ልክ እንደዚሁ ነው Adapt ካደረጋችሁት ጥቅም ሲኖረው👌 ምናልባትም ደግሞ ችግርም ይኖረው ይሆናል[Maladpative].

7. Culture is Dynamic

📌Culture is changing constantly as new ideas and new techniques are added as time passes modifying or changing the old ways.

አየውላችሁ Culture አዳዲስ ሀሳብ እየተጨመረበት በመጣ ቁጥር በየጊዜው ሊቀያየር ይችላል። Static ነው ካለ እንዳትሰሙ🙅‍♂

📝𝔼𝕝𝕖𝕞𝕖𝕟𝕥𝕤/𝔸𝕤𝕡𝕖𝕔𝕥𝕤 𝕠𝕗 𝕔𝕦𝕝𝕥𝕦𝕣𝕖

Two of the most basic aspects of culture are material and nonmaterial culture.

1⃣Material Culture

🎈Material culture consist of man-made objects such as tools, implements, furniture, automobiles, buildings, dams, roads..
ከስሙ ራሱ እንደምትረዱት የቅርፃቅርፅ፣ የሚታዩት ነገሮች ባህል ነው። እኛ ባህል/Culture የሚመስለን አለባበስና ቋንቋ ምናምን ብቻ ነዋ😔

🎈The physical substance which has been changed and used by man.
የሰው ልጅ የፈጠራቸውና እራሱ የሰው ልጅ እየቀያየረ ሊጠቀምባቸው የሚችል ናቸው።

🎈It is referred to as Civilization.

2⃣Non-Material Culture

All Rights Reserved
🎈Non-material culture consists of the words the people use or the language they speak, the beliefs they hold, values and virtues they cherish, habits they follow.
ይሄ ደግሞ እኛ በተለምዶ የምናውቀው ነው፦ የዚያ ህዝብ አመለካከት፣ ትውፊት፣ ልማዳቸው፣ ቋንቋቸው ምናምን Non-material Culture ነው ሚባለው።

📝Some of the aspects of non-material culture:-

📍Values: are the standards by which member of a society define what is good or bad, beautiful or ugly.
Value (እሴት) ማለት ህብረተሰቡ ጥሩ ነው👌 ወይም መጥፎ ነው👎 ብሎ Judge ያደረገው ነገር ነው።

📍Beliefs: are basically Assumptions that refer to the acceptance that something exists or is True, especially without proof.
Beliefs (እምነት) ደግሞ አንድ ነገር ትክክል/እውነት ሊሆን እንደሚችል አምኖ መቀበል ማለት ነው።

እስኪ ሁለቱን በምሳሌ እንረዳ:- ሞጁሉ ላይ የሚገኘው ምሳሌ እንዲህ ይላል፦

"Education is Good" ይሄ የAmerica Society ውስጥ basic #Value ነው።

"Grading is the best way to evaluate Students" ይሄ ደግሞ እምነታቸው ነው። [ይሄ እምነት አይደል መከራ ሚያበላን😹]

🙌ከኔ ጋር ናችሁ! እንቀጥል

📍Norms: are ways of behaving that are considered normal in a particular society.
"Norm" ማለት ልማድ፣ ትውፊት የምንለው ነገር ነው። ለምሳሌ የበአል የበአል ሰሞን በሬ🐃 እያረዱ🔪፣ ቅርጫ እየተከፋፈሉ በአሉን ሚያከብሩት ነገር Social Norm ነው😎

📝Types of Norms (Informal)

1. Folkways፡ are informal rules and norms that, while not offensive to violate, are expected to be followed.
ይህ ማለት ለምሳሌ Taxi ውስጥ ለትልቅ ሰው መቀመጫ ካልለቀቃችሁ👎 ችግር የለውም፣ ማንምም አይፈርድባችሁም፣ ነገር ግን በSocietyው የተለመደው ከትልቅ ሰው ስር መነሳት ነው።

2. Mores [ሞሬስ]፡ are also informal rules that are not written, but, when violated, result in severe punishments and social sanction upon the individuals.
ይህ ደግሞ ለምሳሌ፡ የህብረተሰቡ አባል ሆናችሁ ብትሰርቁ ወይ ደግሞ ሰው ብትገድሉ ትቀጣላችሁ👊! ህግ ምናምን ስላለ ብቻ አይደለም ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ነገርም በSocietyው መካከል የተወገዘ ስለሆነ።

Mores distinguish the difference between right and wrong, while folkways draw a line between right and rude.

📖Cultural Unity and Variations

አንዳንድ Cultural Features በሁሉም Culture ውስጥ ይገኛሉ [Universal], አንድአንዱ ደግሞ በአብዛኛው ውስጥ ይገኛል ነገር ግን በሁሉም አይደለም [General], ሌሎች የባህል መገለጫዎች ደግሞ በተወሰኑ ባህላት ውስጥ ብቻ ነው ሚገኙት [Particular].

ለምሳሌ፣ Exogamy ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በሁሉም ማህበረሰብ ባህል የተከለከለ ነው"ሞጁሉ ነው ያለው😁 እንጂማ ስንት እናውቃለን.. ይሄ አሁን Universality ነው።

ሌላ ደግሞ የሴት ልጅ ግርዛት ለምሳሌ በአብዛኛው የአለማችን Culture ውስጥ የተከለከለ ነው..ይሄ Generality ነው

እና ደግሞ ሌላው የParticular ምሳሌ የሀገራችንን ደቡብ ህዝቦች አፋቸውን አይታችሁ ታውቃላችሁ የስረኛው ከንፈራቸው ላይ የሆነ ክብ ነገር አድርገውበት ምናምን🙈🙈😁😁

አልደከማችሁማ፣ እንቀጥል👍

📖Evaluating Cultural Differences

1. Ethnocentrism: refers to the tendency to see the behaviors, beliefs, values, and norms of one's own group as the only right way of living and to judge others by those standards.

Ethnocentrism ማለት የኔ ባህል፣ ሃይማኖት ፣ አመለካከት ...ይበልጣል ብሎ ማሰብና የሌላው ትክክለ እንዳልሆነ ጀጅ ማድረግ ነው።

📌Ethnocentrism is not characteristic only of complex modern societies.

By the way, Ethnocentrism ጥቅም አለው፦ in preserving traditions of one's own culture. [የራሳችሁን ባህል ለማስጠበቅ ይጠቅማል]

ግን ከጥቅሙ ይልቅ ጉደቱ የከፋ ስለሆነ እናንተ Ethnocentric አትሁኑ!😊

ይቀጥላል...Good Bye🤗

ጥያቄ እና አስተያይት👇


All Rights Reserved
General_Chemistry_Module.pdf
40 MB
📚 General Chemistry Module.

📚 Second Semester Freshman Course.
📚Freshman second semister course

📖Introduction to Emerging Technology

🔖Chapter 2 Data science

ሰላም ውዶች 🤗 በባለፈው ሳምንታት Introduction To Emerging Technology ምዕራፍ አንድን ተመልክተናል ዛሬ በአዲስ ምዕራፍ ስለ Data science ምንነት እንመለከታለን አብራቹን ቆዩ 🙌

📌 Data Science

Before we are going to Explain what Data science really is let Us look something about the meaning of the word Data First .

🎈 Data is is a collection of facts such as numbers , words, measurements, observations or just descriptions of things.

በአጭሩ Data ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት 🤔

Data ማለት ስብስብ ሲሆን ስብስቡም የቁጥር (2⃣ 5⃣0⃣ )የቃላት ( Cat , Man ) የ ስም (ABEL , DAGIM) የእድሜ የ ክብደት የተለያዩ ልኬቶች( 30 kg , 20℅ ) (Measurements) እና የመሳሰሉት ሊሆን ይችላል ።

The main examples of data are

📍weights 📍prices 📍costs 📍numbers of items sold
📍employee names
📍product names
📍addresses etc


ስለ Data ይህን ካየን Data ሂደቶችን (processes ) አልፎ ወደ ጠቃሚ ቅርጽ ሲቀየር Information እንለዋለን 👍

🎈Information is data that has been converted into a more useful or intelligible form.

Keep in mind 🤗

Data is unorganized, while information is structured or organized.

በደምብ ግልጽ ለማረግ ያህል እቺን አጭር ምሳሌ እንመልከትና በቀጥታ ወደ Data science እንግባ 🏃‍♂ 🏃‍♀

Assume that ተማሪ ብሩክ 👨‍💼 የ ፍሬሽ ማን ተማሪ ነው በመጀመርያው ሴሚስተር ብሩክ በ LOGIC COURSE ያስመዘገበውን ውጤት እንመልከት 👀 :

Test 1 10/10 😀
Test 2 30/30 😲
Assignment 20/20 🧐
Final Exam 49/50 😳

According to our definition Data ስብስብ ነው በዚ ምሳሌ መሰረት የ ብሩክ ውጤት የቁጥር ስብስብ ስለሆነ Data እንለዋለን እንበልና የብሩክ መምህር ይህን የቁጥር ስብስብ ደምሮ አባዝቶ አካፍሎ ሂደቶችን አልፎ ብቻውን ትርጉም የማይሰጠውን የቁጥር ስብስብ ወይንም Data የ ብሩክን Grade A + ወይንም 4.00 ብሎ ለማስቀመጥ ተጠቀመበት እንበል ይህን ሲያረግ Data ው ትርጉም ሊሰጠን ወደሚችል ቅርጽ ተለወጠ እንላለን ያ ደግሞ Information ይባላል ተረዳችሁኝ Ok እንቀጥል 🤝

📌 What is Data science ?

The term Data Science was coined at the beginning of the 21st Century. It is attributed to William S.

Data science የምንለው ከ Raw Data የሂሳብ የ Programming እና Scientfic methods ተጠቅመን ጥቃሚ እውቀትን ወይም ፍሬ ነገር ማውጣት ስንችል ነው ።

Data science is a multi-disciplinary field that uses scientific methods, processes, algorithms, and
systems to extract knowledge and insights from structured, semi-structured and unstructured data.

A person who study data science is Called Data scientist


📌 Data processing Cycle

🎈Data processing cycle as the term suggests a sequence of steps or operations for processing Data .

Data processing Cycle የምንለው አንድን Raw Data ጥቅም ሊሰጥ ወደሚችልበት ቅርጽ (Usable form ) ለመቀየር የሚያስፈልግ ሂደት ማለት ነው ።

🎈Data processing Has three basic steps :

INPUT

PROCESSING

OUTPUT

Keep in mind 🤗

Data processing is the re-structuring or re-ordering of data by people or machines to increase their usefulness and add values for a particular purpose .

በአጭሩ Input Processing እና Output ምን ማለት እንደሆኑ እንመልከት :

🌱 Input : the task where verified data is coded or converted into machine readable form.


🌱Processing : Processing is the transformation of the input data to a more meaningful form (information) in the CPU

🌱Output : is the production of the required information

ለዛሬ በምዕራፍ ሁለት የነበረን ቆይታ ይህን ይመስላል 🙌 Module አንብቡ ያልገባቹ ካለ በ ላይ ፃፉልን በቀጣይ በምዕራፍ 2 የቀሩትን ለማጠቃለልና የተወሰነ ምሳሌ ለማየት እስክንገናኝ 🙌



All rights reserved
📝Data Types with their Description

📖Emerging Technology
📝 Common Data Types with their Example

📖Emerging Technology
ሰላም ውድ የ A + Tutorial class ተከታታዮች 🙌

A + Tutorial class በ 1 ኛው ሴሚስተር ከ 1500 በላይ ተማሪዎችን ይዞ በነበረው Private ቻናል የነበረን ቆይታ አይረሳም አሁንም በ 2 ኛ ሴሚስተር ከ concise English Telegram channel ጋር በመተባበር ለሚሰጠው ትምህርት ምዝገባውን ለማገባደድ ጥቂት ቀናት ብቻ ይቀሩታል ።

ከዚ በፊት ከተስተዋሉ ችግሮች መካከል ምዝገባ ስትፈጽሙ ከ Admin የተላከላቹን Link ለሌላሰው share ማድረግ Screen shoot እያነሱ ማጋራት ህጋችን አይፈቅድም 🙅‍♂

ስለዚህም ውድ ተማሪዎቻችን 🥰 ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከንደዚ አይነት ድርጊት እንድትቆጠቡ ነገር ግን የምንለቀውን ማስታወቂያ ለ ጓደኛ ለክፍል ተማሪዎች በግቢና በ ክፍል Telegram Group ላይ Share በማድረግ እናንተም እነሱም ተጠቃሚ በመሆን ድጋፋችሁን እንድትገልጹን መልዕክታችን ነው ።

ጥያቄና አስተያይት👇


All rights reserved !
📚 Communicative English Skill II

📙 Chapter One

📕 Life Skill

📚 Active and Passive Voice

🙌 ተወዳጆች ሆይ ሰላም ለእናንተ የ Communicative English Skill II ኮርስን ዛሬ መማር እንጀምራለን። እስከ ሴሚስተሩ መገባደጃ ድረስ አሪፍ እና ደስ የሚል ቆይታ እንደሚኖረን ተስፋ አደርጋለሁ። የ A+ tutorial class ቤተሰቦች የሆናችሁ ሁላችሁም ይህን ኮርስ አሪፍ ውጤት እንደምታመጡም እርግጠኛ ሁኜ መናገር እፈልጋለሁ።

📌 Communicative English Skill II ኮርስ ላይ በዋናነት የ ሰዋ ሰው ህጉን ወይም Grammar ክፍሉን ነው የማስተምራችሁ ምክንያቱም ፈተና በብዛት የሚወጣው Grammar ክፍሉ ላይ ስለሆነ። ለፈተና ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ህይወታችሁ ጥሩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት እንዲኖራችሁ ሊያደርጉ የሚችሉት ኖቶችን አዘጋጅቴ አቀርብላችሗለሁ።

📌 የዛሬው ትምህርታችን የሚሆነው Active and Passive Voice ነው። ይህ ትምህርት ለእናንተ አዲስ አይደለም። ምናልባት ከ ስምንተኛ ክፍል ጀምሮ እየተማራችሁ የመጣችሁት ነው። ነገር ግን በርካታ ተማሪዎች Active and Passive Voice በቅጡ ጠንቅቀው አያቁትም :- ለመረዳትም ይቸገራሉ።

📌 የ እንግሊዝኛ Grammar ክፍል በተለይም ደግሞ Tense ያለ Active and passive voice ከ ባህር ላይ የወጣ አሳ ማለት ነው። ምክንያቱም በ ዕለት ተ ዕለት ኑሯችን የምንናገራቸው ቃላቶች እና ዐ.ነገሮች ከ 90% በላይ የሚሆኑት Active and passive voice ናቸው። ስለዚህ በደምብ ልናውቀው የሚገባ የ Concept ትምህርት ነው።

📌 እንግዲህ ለእናንተ ለመረዳት ምቹ እና ግልፅ ይሆናል ብዬ ያሰብኩትን ኖት አዘጋጅቼላችሗለሁ😎። መረዳት የሚጠይቅ ነው በጥንቃቄ ተመስጣችሁ አንብቡት። እንዲሁም ልምምድ ማድረግ የሚጠይቅ ነው:- ለዚህም የሚሆን Excerises ኦችን እለቅላችሗለሁ።

📌 የ Active and passive voice ትምህርት ፅንሰ ሀሳቡን መጀመሪያ ተረዱት። ከዛ ፎርሞቹን(forms) በቃላችሁ ያዙ:- ግዴታ ነው ፎርሞቹን መያዝ😡። ከዛ practise አድርጉ። ምክንያቱም ፈተና ላይ በብዛት የምትጠየቁት Active voice ወደ Passive voice ቀይሩ ነው :- እንዲሁም Paragraph(passage) ይሰጣችሁ እና የቀረቡትን verbs በ Active and passive voice ሙሉ ተብላችሁ ትጠየቃላችሁ:- እንዲሁም ደግሞ passage ይሰጣችሁ እና የትኞቹ ዐ.ነገሮች Active ናቸው የትኞቹ ደግሞ passive ናቸው በአጭሩ passive እና active የሆኑትን ለዩ ተብላችሁ ትጠየቃላችሁ። ስለዚህ ፅንሰ ሀሳቡንም ማወቅ አለብን እንዲሁም ደግሞ ፎርሞቹን የግዴታ በአግባቡ መያዝ አለብን።

👇አሁን ወደ ትምህርቱ እንሒድ። አብራችሁን ቆዩ❗️


All Rights Reserved.
🌹 Active & Passive Voice


📚 ሁላችንም ቀን በ ቀን ከምንናገራቸው ንግግሮች ወይም ዐረፍተ ነገሮች መካከል አብዛኛዎቹ Active & passive ዐ.ነገሮች ናቸው። ታድያ Active and passive voice ምንድን ናቸው? ፎርማቸውስ(forms) ምን ይመስላል? የሚለውን እንመልከት።

🎯 ምሳሌ 1:-

🐒 ጦጣዎች ሙዝ ይወዳሉ።

በዚህ ዐ.ነገር ላይ ፡ የ ዐረፍተ ነገሩ ባለቤት ወይም subject ቱ 👉 ጦጣዎች ናቸው። ጦጣዎች ምን አደረጉ? ብለን ብንጠይቅ፡ ሙዝ ይወዳሉ፡ ነው የሚሆነው መልሱ። ማለትም ጦጣዎች ሙዝ የመውደድ ድርጊትን ስለፈፀሙ። ስለዚህ ከዚህ ምሳሌ የምንረዳው ነገር ፡

😎 የ ዐረፍተ ነገሩ ባለቤት(Subject) ድርጊቱን የሚያደርግ ወይም የሚፈፅም ከሆነ ፡ ዐረፍተ ነገሩ Active Voice ይባላል።

🍌 ሙዝ ምን ሆነ ወይም ምን ተደረገ? ተብሎ ቢጠየቅ፡ መልሱ የሚሆነው👇

🔹 ሙዝ በ ጦጣዎች ይወደዳል።

የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት ወይም subject ደግሞ ሙዝ ነው። ሙዝ ምን ተደረገ ተወደደ። ስለዚህ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት ማለትም ሙዝ ድርጊት ተቀባይ ነው ማለት ነው። ምክንያቱም የጦጣዎች የመውደድ ድርጊት በእርሱ ላይ ስለተፈፀመ። ስለዚህ፡

የ ዐረፍተ ነገሩ ባለቤት(subject) ድርጊቱን ተቀባይ ከሆነ ፡ ዐረፍተ ነገሩ Passive Voive ይባላል። ስለዚህ😊

🔹ጦጣዎች ሙዝ ይወዳሉ።
(Active Voive)

🔸ሙዝ በጦጣዎች ይወደዳል።
(Passive Voive)

🙌 ግን እዚጋ ማስተዋል ያለብን ነገር፡
ሙዝ በጦጣዎች ይወደዳል ወይም ሙዝ ይወደዳል። ማለት እንችላለን። በጦጣዎች የሚለውን መተው ይቻላል።

🎯 ምሳሌ 2:-

🔎 ልዑል አይጧን ገደላት።

በዚህ ዐ.ነገር ላይ ፡ የ ዐረፍተ ነገሩ ባለቤት ወይም subject ቱ 👉 ልዑል ነው። ልዑል ምን አደረገ? ብለን ብንጠይቅ፡ አይጧን ገደላት፡ ነው የሚሆነው መልሱ። ማለትም ልዑል አይጥ የመግደል ድርጊትን ስለፈፀመ። ስለዚህ ከዚህ ምሳሌ የምንረዳው ነገር ፡

😎 የ ዐረፍተ ነገሩ ባለቤት(Subject) ድርጊቱን የሚያደርግ ወይም የሚፈፅም ከሆነ ፡ ዐረፍተ ነገሩ Active Voice ይባላል።

🐰 አይጧ ምን ሆነች ወይም ምን ተደረገች? ተብሎ ቢጠየቅ፡ መልሱ የሚሆነው👇

🔹 አይጧ በልዑል ተገደለች።

የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት ወይም subject ደግሞ አይጧ ናት። አይጧ ምን ተደረገች ተገደለች። ስለዚህ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት ማለትም አይጧ ድርጊት ተቀባይ ነች። ምክንያቱም የልዑል የመግደል ድርጊት በእርሷ ላይ ስለተፈፀመ። ስለዚህ፡

የ ዐረፍተ ነገሩ ባለቤት(subject) ድርጊቱን ተቀባይ ከሆነ ፡ ዐረፍተ ነገሩ Passive Voive ይባላል። ስለዚህ😊

🔹ልዑል አይጧን ገደላት።
(Active Voive)

🔸አይጧ በልዑል ተገደለች።
(Passive Voive)

🙌 ግን እዚጋ ማስተዋል ያለብን ነገር፡
አይጧ በልዑል ተገደለች ወይም
አይጧ ተገደለች። ማለት እንችላለን። በልዑል የሚለውን መተው ይቻላል።

🎯 ምሳሌ 3:-

📩 ሲሳይ ደብዳቤ እየፃፈ ነው።

የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት ወይም subject ሲሳይ ነው። ሲሳይ ምን አደረገ? ተብሎ ቢጠይቅ ፡ ደብዳቤ እየፃፈ ነው፡ ነው መልሱ የሚሆነው። ስለዚህ የዐ.ነገሩ ባለቤት ማለትም ሲሳይ ድርጊት አድራጊ ነው ማለት ነው። ምክንያቱም ደብዳቤ የመፃፍን ድርጊት እያደረገ ስለሆነ። ስለዚህ፡

😎 የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት ማለትም ሲሳይ ድርጊት አድራጊ ወይም ፈፃሚ ስለሆነ ፡ ዓረፍተ ነገሩ Active Voice ነው ማለት ነው።

💌 ደብዳቤ ምን ተደረገ ወይም ደብዳቤ ምን እየተደረገ ነው? ተብሎ ቢጠየቅ፡ መልሱ የሚሆነው👇

🔻ደብዳቤ እየተፃፈ ነው።
ወይም
ደብዳቤ በሲሳይ እየተፃፈ ነው።

የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት ወይም subject ደግሞ ደብዳቤ ነው። ደብዳቤ ምን እየተደረገ ነው? እየተፃፈ ነው። ስለዚህ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት ማለትም ደብዳቤ ድርጊት ተቀባይ ነው ማለት ነው። ምክንያቱም ተፃፊ ስለሆነ። ስለዚህ😊

የ ዐ.ነገሩ ባለቤት ማለትም ደብዳቤ ፡ ድርጊት ተቀባይ ስለሆነ ዐ.ነገሩ Passive Voice ነው ማለት ነው። ስለዚህ😎

🔶ሲሳይ ደብዳቤ እየፃፈ ነው።
(Active Voice).

🔷ደብዳቤ እየተፃፈ ነው።
(Passive Voice). ወይም

🔴ደብዳቤ በሲሳይ እየተፃፈ ነው።
(Passive Voice).
ስለዚህ ከምሳሌ 1÷ምሳሌ 2 እና 3 የምንረዳው ነገር፡

📘 Active Voice - The Subject is the doer of the action.

📕Passive Voice - The Subject is the receiver of the action.

📚 ስለዚህ አንድ ዐ.ነገር Active voice ነው የምንለው የ ዐ.ነገሩ ባለቤት(subject) ድርጊት አድራጊ ከሆነ ወይም በሌላ አባባል ድርጊቱን የሚያደርግ ወይም የሚፈፅም ከሆነ ነው። እንዲሁም

📚 አንድ ዐ.ነገር Passive voice ነው የምንለው የ ዐ.ነገሩ ባለቤት(subject) ድርጊት ተቀባይ ከሆነ ወይም በሌላ አባባል ድርጊቱ እሱ ላይ የሚከናወን የሚፈፀም የሚደረግ ከሆነ ነው።

😎 በ እርግጠኝነት አሁን ጠለቅ ያለ መረዳት ይኖራችሗል ብዬ አስባለሁ🙌

📚 አሁን ደግሞ ምሳሌ 2 እና 3 ን መሰረት በማድረግ እንዴት Active Voice ወደ passive voice እንደሚቀየር የሚያሳይ አንድ formula እንመልከት።

🌹 ምሳሌ 1

🍄 ጦጣዎች ሙዝ ይወዳሉ።
(Active voice)

🔰የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት(subject) - ጦጣዎች

🔰 የዚህ ዐ.ነገር ግስ(verb) - ይወዳሉ

🔰 የዚህ ዐ.ነገር ተሳቢ(object) - ሙዝ

🍄 ሙዝ በጦጣዎች ይወደዳል።
(Passive Voice)

የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት(subject) - ሙዝ

የዚህ ዐ.ነገር ግስ(verb) - ይወደዳል

የዚህ ዐ.ነገር ተሳቢ(object) - ጦጣዎች

🌹 ምሳሌ 2

🍄 ልዑል አይጧን ገደላት።
(Active Voice)

🔰የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት(Subjcet) - ልዑል

🔰 የዚህ ዐ.ነገር ግስ(verb) - ገደላት

🐰የዚህ ዐ.ነገር ተሳቢ(object) - አይጧ


🍄 አይጧ በልዑል ተገደለች።
( Passive Voice)

የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት(subject) - አይጧ

💪 የዚህ ዐ.ነገር ግስ(verb) - ተገደለች

🏃‍♂የዚህ ዐ.ነገር ተሳቢ(object) - ልዑል


🤷‍♂ ስለዚህ ከዚህ የምንረዳው ነገር፡

💁‍♂ Active voivce ወደ passive voice ሲቀየር 👇

1ኛ) Active voice ላይ object የነበረው አካል passive voice ላይ subject ይሆናል ማለት ነው።

2ኛ) Active voice ላይ subject የነበረው አካል ፡ passive voice ላይ object ይሆናል ማለት ነው።

3ኛ) Active voice ወደ passive voive ሲቀየር የ ዐ.ነገሩ ግስ(verb) ምን ይሁን?

😊 ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆነው፡

📚 ግሶች(verbs) ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ከ Tense ጋር ነው። ታድያ Active Voice ወደ passive voice ሲቀየሩ ፡ Active voice ላይ የነበሩ ቴንሶች(tenses) ወደ passive voice ሲቀየሩ እንዴት እንደሚቀየሩ እንመልከት።
👍1
🔰Tenses in the Passive Voice.
_______

🌹 Past Tenses in the Passive Voice.

A) Simple Past Passive.
Sub + was/were + V3.

e.g1)🔻 Leul killed the rat.(Active)

🔺The rat was killed.(passive)

e.g2) He invited us.(active).

We were invited.(passive)

B)past continuous passive.
Sub +was/were+being +V3.

e.g1) Sisay was writing a letter.(Active).

A letter was being written by Sisay.(passive).

e.g2) He was inviting us.(Active).

We were being invited.(passive)

C)Past perfect passive.
Sub + had + been + V3.

e.g1) Leul had killed the rat.( active).

The rat had been killed by Leul.( passive).

🌹 Present Tense in the Passive Voice.

A) Simple present passive.
Sub + is/am/are + V3.

e.g1) Leul kills the rat.(Active).
The rat is killed.(passive).

e.g2) He invites me.(Active
I am invited.(passive)

e.g3) He invites us.(active)
We are invited.(passive)

e.g4) Apes adore banana.(active)
Banana is adored by Apes.(passive)


B)present continuous passive.

Sub + is/am/are + being + V3.

e.g1) He is inviting me.(active).
I am being invited.(passive).

e.g2) He is inviting us.(active).
We are being invited.(passive).

e.g3) Sisay is writing a letter.(active).
A letter is being written.( passive).

C)present perfect passive.
Sub + has/have + been + V3.

e.g1) Kids has played football.( active)
Football has been played.(passive).

e.g2) He has invited them.( active).
They have been invited by him.( passive).

🌹Future Tense in the passive voice.

A) simple future passive.
Sub + will + be + V3.

e.g1)He will invite us.(active)
We will be invited.(passive)

B)Future perfect passive.
Sub + will + have + been + V3.

e.g1) He will have invited us.( active).

We will have been invited by him.( passive).

🌹 Modal auxiliary verb in the passive voice.

Modal auxiliary verbs የሚባሉት May, Must, Ought to, Can, Could, Might...etc ናቸው።

Sub + modal auxiliary verb + be + V3.

e.g1) She must buy some cookies.(active).
Some cookies must be bought by her.(passive).

e.g2) Corona Virus can kill humans.(active).
Humans can be killed by corona virus.(passive).

ስለዚህ active voice ወደ passive voice ለመቀየር የ ቴንስ ፎርሞቹን( tense forms) በጥንቃቄ መያዝ አለብን።

አሁን ደግሞ rules አሉ ፡ እነሱን እንመልከት።

Rule 1
The passive voice can be used with all tenses.However, past perfect continuous, present perfect continuous, future continuous and future perfect continuous are not frequently used in the passive voice.

Rule 2
Intransitive verbs are not used in passive voice. Verbs like die, sneeze, disappear, vanish, go, sleep, sit etc are intransitive verbs.

🔷 Examples

The old woman was died last week.(wrong).
✔️ The old woman died last week.(correct).

He has been disappeared. (wrong).
✔️ He has disappeared.( correct).

Rule 3
When the subject of the active sentence is negative word like nobody, nothing and no one, the passive form will be negative.
🔴Examples

Nobody knows the book.(active).
The book is not known.(passive).

No one has reached the secrets.(active).
The secrets have not been reached.

📌 ማስታወሻ:-

የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከምትወስዱት Communicative English ኮርስ ላይ active ወደ passive ወይም passive ወደ active ቀይሩ ተብሎ ብዙ ጥያቄ ስለሚወጣበት ፎርሞቹን(forms) በደንብ ልትይዙ ይገባል።

👨‍🏫👩‍🏫 በቀጣይ ደግሞ Active voice እንዴት ወደ passive voice እንደሚቀየር የሚያሳዩ ህጎችን እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ህጎችን እናያለን።
👍1
Calculus - J. Stewart.pdf
23.4 MB
📚 James stewart Calculus

📚 Applied math 1 reference Second Semester Freshman Course
👍1
Thomas_Calculus.pdf
22.1 MB
📚 Thomas calculus

📚 Applied Math 1 Reference Second Semester Freshman Course.

© A+ Tutorial Class
📕 Emerging Technology

በቀጣይ የምናነሳው ርዕስ ላይ ስለምናየው ይህን ምስል👆 በደምብ ተመልከቱት
How to Study 7th Edition.pdf
877.9 KB
📓How to Study

📓ከዚህ በፊትም ተማሪዎች በትምህርታቸው እንዴት ጎበዝ ሊሆኑ እንደሚችሉ በ1st Semister Channel ላይ በፁፍ ለቀናል።
📚Freshman 2nd Semister Course

📖Anthropology

📔 Chapter 2 [Continued]


2. Cultural Relativism

📌States that cultures differ, so that a cultural trait, act, or idea has no meaning but its meaning only within its cultural setting.

ይህ ማለት ምን መሰላችሁ የአንድን ሰው ባህል፣ አመለካከት፣ ድርጊት ከእነርሱ እነርሱ ካሉበት Context ተነስተን ሳይሆን ከራሳችን ተነስተን የእነርሱን ነገር ስንገመግመው ማለት ነው።

📌"Cultural relativism suspends judgment and views about the behavior of people from the perspective of their own culture."

የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም እንደሚባለው😎 የሌላውን ሰው ባህል የእነርሱ ጫማ ውስጥ ገብተን ስናየው ነው እንጂ በሩቁ መፈረጅ ትክክል አይደለም።🙅‍♂ የእነርሱ ባህል እነሱን ደስ ሊያሰኝ ይችላል ነገር ግን እኛ የእነርሱን ባህል መናቅ የለብንም። Respect For cultural differences😊

ነገር ግን እዚህ ላይ ሰዎች የተለያየ ሀሳብ አላቸው። Cultural Relativism ጥሩ ነው ብለው የሚያምኑም አሉ።
📙"Mirror for Humanity" ሚለው መፅሐፍ ላይ በስፋት አለ፣ ካገኘው ለቅላችኋለው።

3. Human Rights

መቼስ ይህን እንደገና ባብራራላችሁ ለቀባሪ ማርዳት ይሆንብኛል😊

"The idea of human rights challenges cultural relativism by invoking a realm of justice and morality beyond and superior to the laws and customs of particular countries, cultures, and religions."

እንዴት መሰላችሁ "የሰው መብት ከባህል፣ ከትውፊት ምናምን በላይ ነው።" ለምሳሌ ሰዎችን መግደል፣ ባሪያ ማድረግ፣ ሴቶችን መጨቆን 😓ባህላቸው የሆነ ማህበረሰብ ልክ ቅድም Cultural difference ስለሆነ Respect ማድረግ አለብን እንላለን?? አይሆንም! Humans have the right to not be murdered, injured, or enslaved or imprisoned without charge!

ስለዚህ እንዲህ አይነቱን የሰውን መብት የሚጋፋውን Culture, Condemn እናረጋለን እንጂ መቻቻል ነው ምናምን ብለን ዝም አንልም።


📖Culture Change

📌Why and how do cultures change?

ከዚህ በፊት እንዳየነው Culture በየጊዜው እየታደሰ Modify እየሆነ ይመጣል፣ መለስ ብላችሁም ያለፉትን Society Culture ብታዩ ተመሳሳይ ሆኖ አታገኙትም፣ በቃ በየጊዜው አዲስ ሀሳብ/አመለካከት ሲመጣ ይቀየራል።

Culture change can occur as a result of the following Mechanisms:

📍Diffusion: The process by which cultural elements are borrowed from another society and incorporated into the culture of the recipient group is called diffusion.

'Cultural elements' ሚባሉት ቋንቋ፣ ልማድ (Value ብለን የተማርነው)፣ እሴት (Norms)...እነዚህ ነገሮች ከአንዱ Society ወደ ሌላው ሲሸጋገሩ ነው #Diffusion ሚባለው። እንደውም Biology ላይ አታስታውሱም😀

📌Diffusion is direct when two cultures trade with, intermarry among, or wage war on one another.
አንዱ ባህል ከሌላው በቀጥታ ሲኮርጅ😁 ማለት ነው።

📌 Diffusion is forced when one culture subjugates another and imposes its customs on the dominated group.
ይህ ደግሞ ለምሳሌ በCivilization ስር የነበረው Society የእነዚያን Colonize ያደረጉትን ሰዎች ባህል በግዴታ ሊቀበል ይችላል።

📌Diffusion is indirect when items or traits move from group A to group C via group B without any firsthand contact between A and C.
ይህን Physics ላይ ጎበዝ የሆኑ ይረዱታል "zeroth law of thermodynamics"😃😃 ከስሙ እንደምትረዱት indirectly በአማላጅ በኩል😇 ባህሉን መቀበል ነው።

2. Acculturation

🏮Is the exchange of cultural features that results when groups have continuous firsthand contact.
ይህ ደግሞ ሁለቱ የSociety አካላት #ቀጣይነት ያለው ግንኙት/firsthand contact ሲኖራቸው ነው።

👉"This usually happens in situations of trade or colonialism."
ይህን ከForced diffusion የሚለየው Continuous መሆኑ ነው።

3. Invention

🏮The process by which humans innovate, creatively finding solutions to problems is a third mechanism of cultural change.

የተለያዩ ነገሮች invent ሲደረጉ ባህል መቀያየሩ ሚታወቅ ነገር ነው። ለምሳሌ በጥንት ዘመን እናንተ ሳትወለዱ እኛ በድንጋይ ነበር እሳት የምናቀጣጥለው😁 ይኀው በእናንተ ዘመን ክብሪት፣ ከዚያ electric ምናምን መጣ።

4. Globalization


🏮"Encompasses a series of processes, including diffusion and acculturation, working to promote change in a world in which nations and people are increasingly interlinked and mutually dependent."
እንግዲህ ዘመኑ እንደምታውቁት እየዘመነ ነው፣ ሀገራትም ከሀገራት ጋር የራሳቸው የሚያስተዋዉቁትና የሚለዋወጡት ነገሮች ስላሉ ከዚህ የተነሳ ባህላቸው ሊቀየር ይችላል። ይኀው ይሄ የምዕራባውያኑ Modernism ሀገራችንን ተጠናውቶት...😢

📙Marriage, Family and Kinship

1⃣Marriage👰🤵

The term marriage is not an easy terms to define.
እኛ እንደምናስበው ቀላል አንምሰላችሁ😊 by the way ጋብቻ በሁሉም Society ውስጥ አይደለም ያለው። ለምሳሌ [ከሞጁሉ] አንድ Nayar, Southern India ማህበረሰብ አለ፣ እና እዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ተጋብቶ፣ ልጅ ወልዶ፣ ቤተሰብ መስርቶ መኖር ሚባል ነገር የለም🙅‍♂። በአንድ Ceremony ላይ ሴቷ👩‍🦳 አንዱን ሸበላ👱‍♂ ትይዝና ስነ ስርዓቱን ተካፍለው ሚፈልጉትን አድርገው ከጨረሱ በኃላ ይለያያሉ፣ በቃ ከዚያ በኃላ እሱም አያውቃትም እሷም አታውቀውም። እንዲህ አያስጠላም??😐 እና ሚገርማችሁ እንዲህ አይነትም Society አለ ለማለት ነው።


📓Rules of Marriage

🏮Societies also have rules that state whom one can and cannot marry.
👍1
🏮The most common form of prohibition is mating with certain type of kin that are defined by the society as being inappropriate sexual partners. These prohibitions on mating with certain categories of relatives known as incest taboos.

🔖"Incest taboos" ማለት በጣም የሚቀራረቡ የስጋ ዝምድና ያላቸው ሰዎች [Nuclear Family] ሲጋቡ ማለት ነው። ለምሳሌ mother-sons, father-daughters, and brother-sisters. እንዲህ አይነት ደግሞ የተከለከለ ነው። በፈጣሪም በህብረተሰቡም ዘንድ።😊

📌Marriage is, therefore, a permanent legal union between a man and a woman. It is an important institution without which the society could never be sustained.
ስለዚህ ጋብቻ የSocietyው ህልውና እንዲቀጥል በማድረግ ውስጥ ትልቅ ሚና አለው። ደግሞም አምላክ የፈጠረው ስርዓት ስለሆነ ቅዱስ ነው።😊

📓Mate Selection: Whom Should You Marry?🤔
በእርግጥ ይህን በዚህ እድሜ መማራችን ይጠቅማናል። ስለዚህ ማንን እናግባ?😊 ከመሬት ተነስተህ ያማረችህን ሁሉ አገባለው ብትል አይሆንም፣ አንቺም እንደዛው።

1. Exogamy: is the rule by which a man👱‍♂ is not allowed to marry someone👱‍♂ from his own social group.
ይህኛው በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የምትኖሩ ከሆነ መጋባትን የሚከለክል ህግ ነው። አስባችሁታል ሰፈር ውስጥ አብራችሁ ያደጋችሁትን፣ የምታፈቅራትን ልጅ አታገባም ሲባል🙈😁

In fact, there are some definite reasons for which practice of exogamy got approval.
📌የመጀመሪያ በተለይ በድሮ ዘመን (አሁንም በገጠራማ አከባቢ) በአንድ ማህበረሰብ የሚኖሩ ሰዎች Probably የስጋ ዝምድና ስለ ሚንራቸው፣ የአንትን Society ሴት ማግባት፣ እህትን እንደማግባት ነው ሚቆጠረው።

📌Attraction between a male and female gets lost due to close relationship in a small group.
አንድን ነገር Adapt ካደረጋችሁት፥ ከጊዜ ቆይታ በኃላ እርካታ ላታገኙበት ትችላላችሁ፤ ልክ እንደዚያው በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ካደጋችሁት ሰው ጋር ተጋብቶ ለመኖር እርካታ ላይሰጣችሁ ይችላል።

2. Endogamy: A rule of endogamy requires individuals to marry within their own group and forbids them to marry outside it.
ይህ ደግሞ የExogamy ተቃራኒ ነው። እዚህ ላይ ከSocietyአችሁ ውጪ ማግባት አይፈቀድም።

📌Religious groups such as the Amish, Mormons, Catholics, and Jews have rules of endogamy.
📌Castes in India and Nepal are also endogamous.

I think ይሄኛው በብዙ ሃይማኖትና ባህላት ዘንድ ታዋቂ ነው። ከእነሱ ሀይማኖት እና ባህል ውጪ ጋብቻን አይፈቅዱም።

3. Preferential Cousin Marriage: This type of marriage is practiced in one form or another in most of the major regions of the world. There are two types:

📍Cross Cousin: are children of siblings of the opposite sex.
ይህ ማለት "የእናቴ ወንድም ልጆች እና የአባቴ እህት ልጆች" ሲጋቡ ማለት ነው። ልብ በሉ👀 ደግማችሁ አንብቡት!

📍Parallel Cousins: is when marriage takes place between the children of the siblings of the same sex.
ይሄ ማለት ደግሞ "የእናቴ እህት ልጆች እና የአባቴ ወንድም ልጆች" ሲጋቡ ማለት ነው።
ገብቶአቹዋላ Paralle ሲል ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ናቸው ሚጋቡት ማለቱ አይደለም፥ ነገር parallel የተባለው በእናት👱 እህት👱‍♀ እና በአባት🧔 ወንድም🧔 ልጆች መካከል መሆኑ ነው።

🎈The most common form of preferential cousin marriage is between cross cousins.
ከዚያኛው ይልቅ Cross Cousin ነው አብዛኛው ሰው የሚጠቀመው።

4. The Levirate and Sororate

📍The Liverate: is the custom where by a widow is expected to marry the brother (or some close male relative) of her dead husband.
ይሄኛው "ባሏ የሞተባት ሴት👩‍🦱 የባሏን ወንድም ወይም የቅርብ ዘመድ👱‍♂ ስታገባ ማለት ነው።"

📍 The Sororate: is the custom where by a died women's husband is expected to marry a Sister (or some close female relative) of his died wife.
ይሄ ደግሞ "ሚስቱ የሞተችበት ባል🧔 በሞተችው ሚስቱ ፋንታ የሚስቱን እህት ወይም የቅርብ ዘመድ👱‍♀" ሲያገባ ነው።

📓Number of Spouses

ስንት እጮና ይኑረን? ሚለውን እዚህ ስር እናያለን፥ አሁን ነገሩ ወደ እኛ እየመጣ ያለ ይመስላል😁

🔖Monogamy: the marriage of one man to one woman at a time.
Maths ላይ One to One ብላችሁ እንደተማራቹት አይነት ነው😁

🔖Polygamy: marriage of a man or woman with two or more mates. Polygamy can be of two types.

📌Polygyny: [ፖሊጂኒ] the marriage of a man to two or more women at a time.
📌Polyandy: [ፖሊያንዲ] the marraige of a woman to two or more men at a time.

ለምሳሌ ቅድም ያየነው "The Sororate" ላይ አንዱ ሚስቱ የሞተችበት ባል እህቷን ካገባት፣ ሁለት ሴቶች👱‍♀👱 ስላገባ Sororal Polygny ይባላል።

የሚገርማችሁ Polygamy Advantageም አለው ይባላል🙈

📌It produces more children, who are considered valuable for future economic and poltical assets.
ልጆች ሲበዙ ከእነዚያ መሃል አንዱ አድጎ ሃብታም ከሆነ ለቤተሰቡ ኢኮኖሚ ጥሩ ነው። ይህ ግን አጥጋቢ አይደለም😊

📌DisAdvantageኡን ካየን ደግሞ በሚስቶች መካከል መቀናናት (አንዷ በሌላው ስትቀና) ሊፈጠር ይችላል😁

📓Economic Consideration of Marriage

እስኪ አሁን ደግሞ በጋብቻ ጊዜ ሊኖሩ ሚችሉ ወጪዎችን እንይ🙈

🏮These may take place either before or after the marriage can be divided into three categories:
1. Bride Price
2. Bride Service
3. Dowry

1. Bride Price: ሌላ ስሙ "Bride Wealth" ነው፥ is the compensation given upon marriage by the family of the groom🤵 to the family of the bride👰.
የሙሽራው ቤተሰብ ለሙሽራይቱ ቤተሰብ ካሳ [Compensation] ሲሰጥ ነው። ይህ እንደምታውቅት በብዙሃኑ አፍሪካውያን ዘንድ የተለመደ ነው።😊

2. Bride Service: is when the groom works for his wife's family.
ይህ ደግሞ በመፅሐፍ ቅዱስ📖 ዘፍጥረት ላይ አንብባችሁ ከሆነ ያዕቆብ👱‍♂ የላባን ልጅ ራሄልን👱‍♀ ለማግባት ሲል የላባ🧔 ቤት ውስጥ ለ14 አመት ላባን አገልግሎት ነበር። ስለዚህ Bride Service ማለት ሙሽራው ሙሽራይቱን ለማግባት ቤተሰቧን ሲያግዝ ማለት ነው።

3. Dowry: involves a transfer of goods or money in the opposite direction, from the bride's family to the groom's family.
ይሄኛው ወንዶች ሙሽሮችን ይመቻቿል😂 ምክንያቱም በተቃራኒ ስለሆነ፣ ለነገሩ ለሙሽሮቹኮ ምንም ጥቅም አይኖረውም ምክንያቱም በቤተሰቦቻቸው መካካል የሚደረግ ስለሆነ🤷‍♂

📓Post-Marital Residence

🔖Is where the newly married couple lives after the marriage ritual is governed by cultural rules, which are referred to as post-marital residence rule.
እኔና ሚስቴ ከተጋባን በኃላ የት እንኑር የእነሷ ቤተሰቦች ጋር ወይስ የኔ ቤተሰብ ጋር ወይስ ሌላ ቦታ🤔
እነዚህን ያዟቸው👇👇 ፈተና ላይ አይቀሩም!!

📌Patrilocal Residence: the married couple lives with or near the relatives of the husband's father.

📌Matrilocal Residence: the married couple lives with or near the relatives of the wife.

📌Avunculocal Residence: The married couple lives with or near the husband's mother's brother.

📌Ambilocal/Bilocal Residence: The married couple has a choice of living with relatives of the wife or relatives of the husband.

📌Neolocal Residence: The Married couple forms an independent place of residence away from the relatives of either spouse.

Alright በጣም አበዛው መሰለኝ ለዛሬው ይህ በቂ ነው😊 Athropology ማንበብን ይፈልጋል፣ በደንብ በርትታችሁ አንብቡ ከዚያ በኃላ A/A+ አመጣ ይሁን የሚል ስጋት አይገባቹም🤗

ጥያቄ ምናምን ካላችሁ👇


©All Rights Reserved!